Telegram Web Link
📕ኢየሩሳሌም ዳግም በሙስሊሞች እጅ መልሳ የማትገባ ይመስላችሗል አል አቅሷ መልሶ ነፃ የማይወጣ ይመስላችሗል⁉️ አትጠራጠሩ


የቅርቡን የዚህችን እጅግ ጥንታዊት ከተማ ታሪክ እናንሳ እንኳ ቢባል
፨ ለ በርካታ መቶ አመታት በባይዛንታይን ሮሞች አረመኔያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የቆየችው ቁድስ በነ ኻሊድ ኢብን ወሊድ እና አቡኡበይዳ ኢብን አልጀራህ የሚመራው ጦር ባይዛንታይኖችን አንበርክኮ ቁድስ ዳግም በሙስሊሞች እጅ ለመግባት ችላ ነበር ። የቁድስን ቁልፍ ቦታው ድረስ ሂደው የተቀበሉት ኡመር ኢብኑል ኸጧብ የቁድስን ነዋሪዎች ነፃነት አውጀው ነበር የተመለሱት ። ቁድስ ከዚያ በሗላ አበበች አሸበረቀች በፍትህና በኢስላማዊው ስልጣን ተንቆጠቆጠች ።

፨ በኡመር ጊዜ ሙስሊሞች ከተቆጣጠሯት በሗላ ቁድስ እስከ መጨረሻው በሙስሊሞች እጅ አልቆየችም ። የሙስሊሞችን መከፋፈልና እርስበርስ መባላት ተጠቅመው ባይዛንታይኖች ዳግም ቁድስን ተቆጣጠሩ ። ቁድስ ( ኢየሩሳሌም ) ዳግም የጨለማ ዘመን ውስጥ ገባች ። ከተማዋን በደል ግፍና ጭካኔ ሞላት !! በከተማዋ የሚስኪኖች ዋይታና የገዥዎች ከልክ ያለፈ አረመኔነት እንጅ አይሰማም አይታይም ነበር ! ቁድስ በባይዛንታይኖች እንደዚህ በበደል ተውጣ ቆዝማ አዝና ብዙ አመታትን አሳለፈች !!

፨ አሏህ #ሰልጁቅ የተሰኙ ቱርኮችን ከወደ ምስራቅ ኤዥያ አስነሳ ። የሰልጁቅ የልጅ ልጅ የሆኑት እነ ቱግሪል ፣ ቻግሪ ፣ አልፕ አርስላን ፣ መሊክ ሻህ የመሳሰሉ ተወዳዳሪ አልባ ጀግና የጦር መሪዎች የአለም ልእለሀያል የነበረውን የባይዛንታይን ሮም ስርወመንግስት ስብርብር አድርገው የቱርኮች የኢስላም ገባሪ አደረጉት ። ከሰልጁቆች ጎሳ #ከኪኒክ የሚመዘዘው የሰልጁቆቹ ጦር መሪ #አቲሲዝ_ቤይ ባይዛንታይኖችን አንኮታኩቶ ዳግም ቁድስ ነፃ አወጣት ። አላህ ዲኑን በማን እንደሚረዳው ይአጅባል ። ገና ከሰለሙ ጥቂት አመታትን ያስቆጠሩት ሰልጁቅ ቱርኮች የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን በሙሉ አስመልሰው ከቻይና እስከ ሮም ያሉ የኢስላም ጠላቶችን በጉልበቶቻቸው አንበረከኳቸው ።

፨ በሀያሎቹ ወራሪዎች የሰልጁቆች የአባሲድና የኸዋርዚም ሙስሊም መንግስታቶች ሲደመሰሱ አሁንም ዳግም አውሮፓዊያን ተባብረው " የመስቀል ጦርነት " በሙስሊሞች ላይ አወጁ ። ሁሉንም የአውሮፓ መንግስታት ባካተተውና በጳጳስ ክሊመንት በተባረከው በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች እንደ ቅጠል ረገፉ !! ኢየሩሳሌምን ( ቁድስ ) የሰው ደም ሀይቅ ሆኖ ተንጣለለባት ። ህፃናት አዛውንት ሳይሉ ፣ ሴት ደካማ ሳይሉ መስቀላዊያኑ ሁሉንም በሰይፋቸው አረዷቸው ። ቁድስም ዳግም በጭራቆች እጅ ገባች ።
፨ አሁን ደግሞ ቁድስን ዳግም ማስመለስ የአንድ በአሁኗ የኢራቋ ቲክሪት ከተማ የተወለደ ኩርዳዊ ሙጃሂድ ተራ ሆነ ። ያ ሙጃሂድ የሙጃሂድ ልጅ ሰላሁዲን አልአዩቢ ይባላል ።
ሰላሁዲን በሰልጁቅ የጦር መሪ በነበረው በኢማዱዲን ዘንኪ ልጅ በኑረዲን ዘንኪ አመራር ስር ሆኖ በወታደራዊ ክህሎት ተኮትኩቶ በኡለሞች ተርቢ ታንፆ አደገ ። አባቱ ሰላሁዲንን ከልጆች ጋር ሲጫወት ባገኘው ጊዜ ብድግ አደረገና ፍርጥ አደረገው ። እና ተቆጣው ሰደበው ። " እኔ አድገህ ቁድስን ታስመልሳለህ እያልኩ አንተ እዚህ አቧራ ታቦላለህ ?" አለው ። ሰላሁዲን አላለቀሰም ። ለምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና ።
ሰላሁዲን ቁድስን ነፃ ሳያወጣ በፊት ስቆ አያውቅም ተደስቶ አያውቅም ። ያ የአሏህ ወልይ በቱርኮች ጥምረት መላው የአውሮፓ መስቀላዊ ጦርን ደምስሶ ኢየሩሳሌም ( ቁድስን ) ዳግም ነፃ አወጣ ።

፨ ከዚያ በሗላ በግብፅ የነገሱት ቱርኮቹ ማምሉኮች ተረክበው ኢየሩሳሌምን ጠብቀው አቆዩ ።
፨ ከነርሱ በሗላ የአለማችን የምንጊዜውም ሀያሉ ኢምፓየር የሚሰኘው የኦቶማን ኺላፋ ( ደውለቱል ኡስማኒያ ) ቦታውን ተክቶ በየትኛውም የአለም ጫፍ ያለን የኢስላም ሉአላዊነት ሳያስደፍር ለ 500 አመታት ቀጥ አድርጎ ገዛ ። ያኔ እንኳንስ ቁድስንና ትሪፖሊን እንኳ ማጥቃት የኦቶማኖችን ጀሃነም ያስከትላል ። አውሮፓን በእንብርክኳ ያስኬዳት ፣ ሩሲያን ወገቧን የሰበራት ያ የኦቶማን ኺላፋ እሶከ ውድቀቱ መጨረሻ ድረስ ቁድስን መካንና መድናን ለጠላት አሳልፎ አልሰጠም ነበር !

፨ አሁን ቁድስ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላ በክርስቲያን_አይሁዳዊያን ጥምረት ስር ነች ። እነሆ ቁድስ ማንባት ከጀመረች ድፍን አንድ ክፍለዘመን ሊሞላት ነው ።

እና ከዚያ ሁሉ ጨለማ የወጣች ቁድስ አላህ አሁን ሌላ ሰላሁዲን ፣ ሌላ አቲሲዝ ቤይ ፣ ሌላ አልፕ አርስላንን አይልክላትም ብላችሁ ታስባላችሁ ??? በፍፁም አታስቡ !
ወድቆ መነሳት ፤ ጨለሞ መብራት የቁድስ ተፈጥሮዎች ናቸው !
ቁድስን አንድ ጊዜ አረቦች ፣ 3 ጊዜ ቱርኮች አንድ ጊዜ ኩርዶች ነፃ አውጥተዋታል ! አሁንስ እነማን የነፃነት ሰንደቁን ይዘው ቁድስን ነፃ ያወጡ ይሆን ??? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል !
ግና አትጠራጠሩ ቁድስ ነፃ ትወጣለች

--------------------------------------
https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
-------------------------------------https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
--------------------------------------
ይህ የኛ ግሩፕ ነው ስለአቂዳችን ስለማህብሰቡ ልዩነት ማወቅ ፈለገ ይቀላቀል መወያያ መድረክ ነው ለሁሉም

https://www.tg-me.com/muwehidoch
💍💍💍💍ትዳር💍💍💍💍

ትዳር ሰላም ነው ኢማንን ይሞላል፣
ከሀራም አርቆ በሀላል ያብቃቃል፣
ከወዳጅ ዘንዳም ውዴታን ያሰፍናል፣
ጀነትን ለመግባት ሰበብም ይሆናል፣

እናማ እህቴ ስሚኝ ልምከርሽ፣
ትዳር በልጅነት ነው ብለው ሲሉሽ፣

ስሚያቸው እውነት ነው ትዳር በልጅነት፣
ልጅም በልጅነት አላህ ከፈቀደም፣
መግቢያም ወደ ጀነት፣
እናማ ዉዷ እህቴ ነቃ በይ፣
በዲኑ ጠንካራ ከመጣልሽ መርሃባ በይዉ፣

አላህ ፈርቶ በተሎ ወደ ሀላል ሚቻኮለውን እውነተኛውን ጀነት ናፋቂው መልካሙን የትዳር አጋር ይወፍቃቹ

آمين يارب العالمين 🤲
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️አጭር ታሪክ❤️

በአንድ መንደር ውስጥ ስዕል እየሳለ በውድ ዋጋ በመሸጥ የሚተዳደር ሽማግሌ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን አንድ የመንደሩ ነዋሪ የሆነ የኔ ቢጤ መጣና
"አንተ ሰዓሊ ነህ። ስዕል እየሳልክ ብዙ ስለምታገኝ ሀብተም ሆነሀል፤
ግን ለድሆች አትሰጥም፤ ባለ ልኳንዳ ቤቱ እንኳ ሁሌ ስጋ
ለድሀች በነጻ ያድላል።" አለው……
ሽማግሌው ሰዓሊም ☺️ፈገግ
ከማለት ውጪ ምንም መልስ አልሰጠውም ……ድሀው ሰውዬም
በመንደሩ እየዞረ ሽማግሌው ሀብታም እንደሆነና ግን ስስታም
እንደሆነ አናፈሰ። የመንደሩ ሰዎች አዛውንቱን ጠሉት……
ከጊዚያት በኃላ አዛውንቱ ታመመ። አንድ እንኳ የሚያስታምመው
ሰው አጥቶ ሞተ 😭😭😭😭……ከዚያን ቀን በኃላ ባለ ልኳንዳው ስጋ ማደሉን አቆመ።
ለምን እንዳቆመ የመንደሩ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት……
"እስከ ዛሬ የማድላችሁ እኮ ሰዓሊው ስለሚከፍለኝ ነው" ብሎ መለሰላቸው።😭😭😭😭😭

@OnlyFortruthersJ
☞ዝሙት☜
በኢስላም የሌለ ፍቅረኛ የሚባል የካፊር ሱና ነው በሀራም
የተጣመረ ነው፡፡
የዝሙት አደጋው!
©አለኝ የምንላትን ኢማን ያጠፋብናል፥
©ሀራም ነውና የመንፈስ ሰላም አይገኝበትም፥
©ለጭንቅት ይዳርገናል፥
©ከአላህ ራህመት ያስወጣናል፥
©ከሁሉም ነገር ላይ በረካን ያነሳብናል፥
©የነብዩን(صلى الله عليه وسلم ) ሱናም ይፃረራል፥
©ሰላማችንን ይነሳናል፥
©በራስ መተማመናችን ይቀንሳል፥
©አሏህ ዘንድ ያስቀጣል፥
©በሰው ዘንድም ያስጠላል፥
©የሪዝቅን በር ይዘጋል፥
@ጤናን ያውካል፥
ስለዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ ከዚና ራሳችንን እንጠብቅ ከቻልን
ማግባት ካልሆነ ግን አሏህ እስኪዘውጅን ድረስ መሶበር ነው፡፡
ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ማስተዳደር
የቻለ ያግባ ጋብቻ ለአይን ገደብ ነው ብልትንም ይበልጥ ጠባቂ
ነው፡፡ ይህን ያልቻለ ይጹም፡፡
አሏህ ሱ.ወ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል!
ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻘْﺮَﺑُﻮﺍ۟ ﭐﻟﺰِّﻧَﻰٰٓ ۖ ﺇِﻧَّﻪُۥ ﻛَﺎﻥَ ﻓَٰﺤِﺸَﺔًۭ ﻭَﺳَﺂﺀَ ﺳَﺒِﻴﻠًۭﺎ
ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡
መንገድነቱም ከፋ{አል-ኢስራእ፡ 32}
ስለዚህ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ሁሉም ነገር
ሀላል ሲሆን ነው ደስ እሚለው ለአንድ ቀን ደስታ ብለን የዘላለም
ጸጸት አናትርፍ አሏህ እኮ ለኛ ብዙ ውለታዎችን ነው የዋለልን
ዚናን ሀራም ሲያደርግብን ኒከህን ሀላል አደረገልን ኸምርን
(መጠጥን) ሀራም ሲያደርግብን ወተት የተፈጥሮ ምንጭ የሆነውን
ውሃ ለስላሳ የመሳሰሉትን ሀላል አድረገልን ታዲያ እሱ ሀላል
ያደረገልንን ትተን ለምን ሀራሙ እንመርጣለን? ያ የከለከለን ነገር
እኛን ስለሚጎዳ እንጂ ቢጠቅመን ኖሮ ይፈቅድልን ነበር፡፡
አብዛሀኛውን ግዜ ለዝሙት ምንጋለጠብት መንገድ ከተቃራኒ ጾታ
ጋር ለብቻ አብሮ መቀመጥ ነው፡፡
እህቴ እሱ እንደ ወንድሜ ነው ብለሽ ከሰው ርቀሽ ከተቃራኒ ጾታ
ጋር አብረሽ አትቀመጪ ወንድሜ አንተም ብትሆን እንደ እህቴ ናት
ብለህ ለብቻ ከሷ ጋር አትቀመጥ ምክንያቱም በመካከላችሁ
ሼይጧን ይገባልና፡፡
ሀቢቡና ሙሀመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል!
ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ለብቻቸው ከተቀመጡ ሶስተኛቸው
ሸይጧን ነው፡፡
አሏህ ከሸይጧንና ከነፍሲያ ተንኮል እንዲሁም ከመጥፎ ጓደኛ
ይጠብቀን አሚን አሏሁመ አሚን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

#የኢብሊስ_አሟሟት

ዱንያ ልትጠናቀቅ ጥቂት ሲቀራት እና ጡሩንባው
ከመነፋቱ በፊት የሰው ልጆች በየመገበያያዎቻቸው ላይ
በመገበያየት ላይ ሳሉ ድንገት ከፍተኛ ድምፅ ይፈጠርና
ከምድር ሰዎች ግማሹ በድንህጋጤ ሲሞት የተቀሩት
ደግሞ ልክ አውሬ እንዳየ እንስሳት ይደናበራሉ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉም ብዙ ሳይቆዩ ከወደ ሰማይ በኩል
ከፍተኛ የሆነ እና የመብረቅ ነጎድጓድ መሳይ ድምፅ
መጥቶ የተቀረውን ፍጥረት ከሙታን ተርታ ያሰልፋል።
ያን ግዜ ምድር ከህያዋን ፍጥረታት ባዶ ትሆናለች።
ጂኖች፣ ሰዎች እና ሰይጣናት በሙሉ ሙተው ምድር ላይ
ኢብሊስ ብቻውን ይቀራል።ይህች ቅፅበት በአላህ እና
ለኢብሊስ መካከል የነበረችዋ ቃል ኪዳን ምትፈፀምባት
ናት።
አላህም ለመለከል መውት እንዲህ ይለዋል፦"እኔ
በመጀመሪያዎቹም በመጨረሻዎቹም ፍጥረታቴ ቁጥር
ያህል ረዳቶችን መድቤልሃለሁ። የሰማይን እና የምድር
ነዋሪያንን ጉልበት ሁሉ ሚያክል ላንተ ሰጥቼሀለሁ።
ዛሬ የቁጣን እና የበቀልን ልብስ አልብሼሀለሁ። በበቀል
እና በቁጣ ተሞልተህ ወደ ረገምኩት ኢብሊስ ውረድ።
ሞትንም አቅምሰው። ከሞት ምሬትም ፍጥረታት፣ ጂኖች
እና ሰዎች ሁሉ የቀመሱትን እጥፍ ድርብ አድርገህ
አቅምሰው።
ዘባኒያዎችም የጀሀነምን ሰንሰለት ይዘው ይጠብቁሀል።
ከጀሀነም በሆኑ 70,000 አውሬዎችም ተጠቅመህ ግም
የሆነች ነፍሱን ገሽልጣት።ከዝያም ማሊክ/የጅሀነም
ጠባቂን በሯን እንዲከፍት ጥራው" ይላል።
ከዝያም መለከል መውት ለአላህ ትዕዛዝ በመተናነስ ወደ
ምድር ፍፁም አስፈሪ በሆነ ገፅታው ይወርዳል። በዚያ
ገፅታው ሰው፣ጂን እና መላዕክት ቢመለከቱት ትዕይንቱን
መቋቋም አቅቷቸው ይቀልጡ ነበር።
መለከል መውት ምድር ወርዶ ልክ ኢብሊስን
እንደተመለከተው በከፍተኛ ድምፅ ይጮህበት'ና ኢብሊስ
ራሱን ሲስት አንድ ግዜ ይጠልዘዋል።
ይህን ግዜ መለከል መውትም እየተከተለው፦"ቁም አንተ
እርጉም ዛሬ ባጠፋኸው ነፍስ ቁጥር ሁሉ አንተንም ሞትን
አቀምስሃለሁ። ስንት እድሜ ጨርሰሃል!!! ምን ያህል ክፍለ
ዘመናትንስ ነው ፍጥረትን በማጥመም የከረምከው!!!!?
በጀሀነም ሚቆራኙህ ስንት ቁራኛዎች እንዳሉህ ብታይ!
ዛሬማ ባንተ እና በአላህ መካከል የነበረችው ቃል ኪዳን
ምትፈፀምበት ቀን ናት። ዛሬ ወዴት ትሸሻለህ!!!?"
ይለዋል።
ከዝያም ኢብሊስ ወደ ምስራቅ ጫፍ ይሸሻል። ይሁን
እንጂ ፊቱ ላይ መለከል መውትን ያገኘዋል። ባህር ውስጥ
ይሰምጣል። አሁንም ከፊቱ መለከል መውትን ያገኛል፤
ባህርም ይተፋዋል።
ምንም ሳይታክት በተቻለው መጠን ለመሸሽ ምድርን
ይዞራል። ይሁን እንጂ ምንም ማምለጫም ሆነ መሸሸግያ
አይኖርም።ከዝያም ምድር ወገብ ላይ የአደም ቀብር
በሚገኝበት ስፍራ ይቆም'ና፦"አንተ አደም!!! ባንተ ሰበብ
ነው እርጉም ሆኜ የቀራሁት። ምን ነበር ባልተፈጠርክ!'
ይላል።
ከዝያም ኢብሊስ ለመለከል መውት፦"በምን አይነት ፅዋ
ነው ሞትን ምታቀምሰኝ?! ይለዋል።
መለከል መውትም፦"በ ለዟ፣ በሰቀር እና በእሳት ሰዎች
ፅዋ ነው አባዝቼ እማቀምስህ" ይለዋል።
ይህን የተመለከተው ኢብሊስም ጥቂት መሬት ላይ በፀፀት
ይንከባለልና ወደ ምስራቅ እና ወደ ምዕራብ ሲመላለስ
ዘባኒያ የተባሉት የጀሀነም ወታደሮች ድሮ ኢብሊ ከሰማይ
የወረደባት ቦታ ላይ ከጀሀነም አውሬዎች ጋር ሁነው
ይይዙታል።
በአውሬዎቹ እየተዘረገፈ እና እየተሰቃየ ላልተወሰነ ግዜ
በጣዕረ ሞት ላይ ይቆያል። ከዝያም ሀዋ እና አደም
ትዕይንቱን እንዲያዩ ይደረጉ'ና፦"ጠላታችሁን ተመልከቱ።
የሞትን ፅዋም እንዴት እንደሚቀምስ እዩ" ይባላሉ።
ሀዋ እና አደምም፦"ጌታችን ሆይ!!! ፀጋህን እኛ ላይ
ሞልተህልናል" ይላሉ።
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭@OnlyForTruthersj
#በቅዱስ_ቁርዓን_ከተጠቀሱት_የ25ቱ_ነቢያት_ስም_ከነአመጣጡ_እና_ሐገራቸውን !!!

👉ካነበባችሁ በኋላ ለሌሎች ማስተላለፍ አትርሱ👈

بسم الله الرحمن الرحيم الحمدلله رب العالمين
والصلاة والسلام على رسول الله صلى الله عليه وسلم


1⃣ #አደም عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ9 ሱራዎች እና #በ25 አንቀጾች ውስጥ #25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣ #ኢድሪስ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ2 ሱራዎች እና #በ2 አንቀጾች ውስጥ #2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

3⃣ #ኑሕ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ30 ሱራዎች እና #በ50 አንቀጾች ውስጥ #50 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

4⃣ #ኢብራሒም عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ25 ሱራዎች እና #በ63 አንቀጾች ውስጥ #69 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

5⃣ #ሉጥ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ14 ሱራዎች እና #በ27 አንቀጾች ውስጥ #27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

6⃣ #ኢስማዒል عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ8 ሱራዎች እና #በ12 አንቀጾች ውስጥ #12 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

7⃣ #ኢስሐቅ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ12 ሱራዎች እና #በ16 አንቀጾች ውስጥ #17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

8⃣ #ያዕቁብ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ10 ሱራዎች እና #በ10 አንቀጾች ውስጥ #16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

9⃣ #ሁድ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #3 ሱራዎች እና #በ7 አንቀጾች ውስጥ #7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣0⃣ #ሷሊሕ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ9 ሱራዎች እና #በ25 አንቀጾች ውስጥ #25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣1⃣ #ሹዐይብ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ10 አንቀጾች ውስጥ #11 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣2⃣ #ሙሳ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ34 ሱራዎች እና #በ131 አንቀጾች ውስጥ #136 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣3⃣ #ሐሩን عليه سلام ፡- ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ13 ሱራዎች እና #በ20 አንቀጾች ውስጥ #20 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣4⃣ #ዳዉድ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ #በ9 ሱራዎች እና #በ16 አንቀጾች ውስጥ #16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣5⃣ #ሱለይማን عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ7 ሱራዎች #በ16 አንቀጾች ውስጥ #17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣6⃣ #ኢልያስ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ1 ሱራ እና #በ2 አንቀጾች ውስጥ #2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣7⃣ #አዩብ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ4 አንቀጾች ውስጥ #4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣8⃣ #ዩኑስ عليه سلام ፡- ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ4 አንቀጾች ውስጥ #4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

1⃣9⃣ #ዩሱፍ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ3 ሱራዎች እና #በ26 አንቀጾች ውስጥ #27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣0⃣ #በአል_የሰዕ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ2 ሱራዎች እና #በ2 አንቀጾች ውስጥ #2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣1⃣ #ዙል_ኪፍል عليه سلام ፡- ይህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ2 ሱራዎች እና #በ2 አንቀጾች ውስጥ #2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣2⃣ #ዘከሪያ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ6 አንቀጾች ውስጥ #7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣3⃣ #የሕያ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ5 አንቀጾች ውስጥ #5 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣4⃣ #ዒሳ عليه سلام ፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ11 ሱራዎች እና #በ25 አንቀጾች ውስጥ #25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

2⃣5⃣ #ሙሐመድ عليه سلاة وسلام፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ #በ4 ሱራዎች እና #በ4 አንቀጾች ውስጥ #4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#የነቢያቶች ሐገር 👇👇

1⃣ #አደም عليه سلام = ስሪላንካ سيرلانكا (Sirilanka)
2⃣ #ኑህ عليه سلام = ጆርዳን جردان (Jordan)
3⃣ #ሹዓይብ عليه سلام = ሶሪያ صريا (Soria)
4⃣ #ኢብራሒም عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
5⃣ #ኢስማኤል عليه سلام = ሳኡዲ አረቢያ صود أعربيا (Saudi arebia)
6⃣ #ያእቆብ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
7⃣ #ያህያ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
8⃣ #ዘከሪያ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
9⃣ #ኢስሃቅ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
1⃣0⃣ #ዩሱፍ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (Palistain)
1⃣1⃣ #ሉጥ عليه سلام = ኢራቅ إراق (Iraq)
1⃣2⃣ #አዩብ عليه سلام = ጆርዳን جردان (Jordan)
1⃣3⃣ #ሁድ عليه سلام = የመን يمن (Yemen)
1⃣4⃣ #ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم = ሳኡዲ አረቢያ صعد أعربيا (Saudi arebia) ( ከሁሉም በተለየ መልኩ የተላኩት ለአለም ህዝቦች ነው። )
1⃣5⃣ #ሙሳ عليه سلام = ግብፅ إجبت (Egypt)
1⃣6⃣ #ሐሩን عليه سلام = ግብፅ إجبت (Egypt)
1⃣7⃣ #ሷሊህ عليه سلام = የመን يمن (Yemen)
1⃣8⃣ #ሱለይማን عليه سلام = ግብፅ إجبت (Egypt)
1⃣9⃣ #ኢሊያስ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (palastin)
2⃣0⃣ #ዳውድ عليه سلام = ኢራን إران (Iran)
2⃣1⃣ #ኢሳ عليه سلام = ፍልስጤም فلسطم (palastin)
2⃣2⃣ #ኢድሪስ عليه سلام = ኦማን عمان (Oman)
2⃣3⃣ #ዩኑስ عليه سلام = ኢራን إران (Iran)
2⃣4⃣ #ዙልኪፍል عليه سلام = ጆርዳን جردان ( Jordan )
2⃣5⃣ #አልየስእ عليه سلام = ሶሪያ صريا ( Soria)
#የአሏህ سبحانه وتعالى እዝነት እና ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን‼️
أمين اللهم أمين يارب العالمين

#ሳታነቡት_እንዳታልፉት بارك الله فكم
#ለወዳጅዎ_በሙሉ_ሼር አድርጉላቸዉ🙏🙏🙏

@ONLYFORTRUTHERSJ
ኦሮሞ ነኝ፣ ያውም አማራ
በትግረኛ የምናገር፣ ጉራግኛ የማወራ
እንደውም ሁሉን ብሔር ነኝ፣ "ሰው" ተብዬ የምጠራ
ዘር እንዳልቆጥር ዘሬ ሰው ነው፣ በሰውነት የምኮራ
አመጣጤን ምገነዘብ ፣ አካሔዴ የማይጠፋኝ
"ሰው ሁን" ብሎ የፈጠረኝ ፣ "ሰው ነኝ" ሲሉ የማይከፋኝ
እንደነቢይ አስተምሮት ፣ ዘረኝነት ሚከረፋኝ
በሰው ደስታ የምደሰት ፣ የሚያስከፋኝ የሰው ሲቃ
ጥንቅቅ ያልኩኝ ሰው ነኝ በቃ!!!!
jabir al habeshiy
ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ኩፍር ነው በዚህ ምርጫ ላይ የሚሳተፉም ሙርተድ ካፊሮች ናቸው።

ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል፡፡ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 60 ]

በዚህች አያ ላይ አሏህ ሱወ በጣጉት መፋረድን ይፈልጋሉ የምትለዋ ንግግር ጣጉት ማለት
ﻭﺍﻟﻄﺎﻏﻮﺕ؛ ﻋﺎﻡ ﻓﻲ ﻛﻞ ﻣﺎ ﻋﺒﺪ ﻣﻦ ﺩﻭﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺭﺿﻲ ﺑﺎﻟﻌﺒﺎﺩﺓ ﻣﻦ
ﻣﻌﺒﻮﺩ ﺃﻭ ﻣﺘﺒﻮﻉ ﺃﻭ ﻣﻄﺎﻉ
"ጣጉት በጥቅሉ ማንኛውም ከአላህ ውጪ የሚመለክ፣የሚገዙት፣የሚከተሉት ወይም የሚታዘዙት አካልማለት ነው" ሼኹል ኢስላም ሙሃመድ አብድል ወሃብ(ረዐ)ሪሳላቱን ፊማዕና አት ጣጉት

ማንኛውም አካል ወይም ሰው ከአላህ ውጪ የሚመለክ፣የሚታዘዙት እና የሚከተሉት በሙሉ ጣጉት ይባላል አንድ ሰው ሂወቱን በሙሉ በመስገድ ፣ ስለ ኢስላም በማስተማር ፣ ጀሃድ በማድረግ፣ሰላት በመስገድ፣ዳዕዋ በማድረግ፣ቁርአን በመቅራት፣ፆም በመፆም ቢያሳልፍም
ጣጉትን ካላስተባበለ እና ካልካደ የሰራቸው መልካም ስራዎች አንዳቸውም ተቀባይነት አያገኙም ምክንያቱም አንድ ሰው ሙስሊም ለመሆኑ የመጀመሪያ ማረጋገጫው ከአላህ ውጪ ያሉ አካላትን በሙሉ አምልኮ አንደማይገባቸው ማስተባበል እና በመካድ በመሆኑ ነው፡፡

የአላህ ህግ ሸሪዐ ምርጫ ሊደረግበት የተገባ ነገር አይደለም ሸሪዓን ለምርጫ (ለህዝብ)
ማቅረብ በተውሂድ ላይ መሠረታዊ ችግር የመኖሩ ምልክት ነው

“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ፡፡(16:36)

ከጣጉት መራቅ የሚለው ከንግግርም ባለፈ ጠለቅ ያለ ምልከታ አለው አታምልክ ሳይሆን
አትቅረብ የሚለው ትዕዛዝ ጠንከር ያለ ነው ምሳሌ ከአላህ ውጪ ያሉ አካላቶችን ትዕዛዝ ከአላህ ህግ ትዕዛዝ በላይ በማድረግ መቀበል ግልፅ ክህደት ነው ይህንንም እንዲደረግ ካዘዙ መሪዎች ሆኑ የሃይማኖት አባቶች መራቅ ግዴታ ይሆንብናል

ጣጉቶችን ማምለክ(መታዘዝ እና ማገልገል) የአይሁዳያን እና የነሷራወች ካፊሮች ባህሪ ነው ቀሳውስቶቻቸውን እና የሃይማኖት አባቶቻቸውን ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎቻቸውን በሚፃረር መልኩ ህጉን ሲቀይሩባቸው አሜን ብለው በመቀበል ከአላህ ሌላ ያመልኳቸዋል ሙስሊምም ቢሆን
ማንኛውም ከአላህ ውጪ ያለ አካል አላህ ያዘዘውን ቀጥተኛ ድንጋጌ ተግባራዊ እንዳይሆን ሲከለክል፣ክልክል ያደረገውን ሲፈቅድ አሜን ብሎ በዝምታ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረጉ ከአላህ ውጪ ያለ ጣጉቶችን እንደማምለክ ነውና በዚህ ዲሞቅራጢያዊ ምርጫ የሚሳተፉም ወደዛች የሚጠሩም ሙርተድ ኩፋሮች ናቸው የአላህ ህግ ሲቀየር አብረው ተሳታፊ ናቸው

ሸይጧን ሰዎች በአላህ ላይ እንዲያጋሩ የሚፈልገው ልክ እንደርሱ ከሃዲ እንዲሆኑ እና ከአላህ ርቀው ጣጉት እንዲገዙ ስለሚፈልግ ነው የአላህን ህግ እንድንጥስ ከሚያዙን አካላቶች ፖርላማ ውስጥ መግባት ሆነ ጣጉት ህጎችን መርዳት ማስፈፀም ሆነ ማንኛውም የጣጉት ህግ እንድንታዘዛቸው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ የምናደርግ ሰዎች ተውሂዳችን ላይ ትልቅ ድክመት ነው ጣጉትን ሊረዱት አይገባም በጣጉት መካድ እንጅ ጠዋጊታውያኖችም ሙሽሪክ ሙርተድ ኩፋሮች ናቸው በጣጉት ያልካደ ና ጠዋጊታውያኖችንም ያላከፈረ ያልተዋጋ ተውሂዱ ላይ ክፍተት አለ በአህ አምኖ በጣጉት ያልካደን ሙስሊም ነኝ ባይ የእስልምናን ባህሪ ቢያንፀባርቅም ካፊር ነው ወሏሁ አዕለም
የእርዳታ ጥሪ
በአላህ ሼር አድርጉት ‼️😭

• እናቷ እያለቀሰችየነገረችን 😭

• በጎላ ሠፈር ዮሴፍ ሞተር ቤት ፊትለፊት መንደር የምትኖር እፁብ አየለ ትባላለች የ15 ዓመት ወጣት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነች በጭንቅላት ቲቢ እና በጭንቅላት እጢ መሠቃየት ከጀመረች 6 ወሯ ነው ቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል ከተኛች 3 ወሯ አትሰማም አትናገርም ! የእናትን ነገር ታቁታላቹ ቀን ሌሊት እያለቀሰች ነው !

ወላጅ እናቷ እዛው እየዋለች እያደረች የምታስታምም ስትሆን አሁን ግን መድሀኒት መግዣ መንቀሳቀሻ ቀለብ ቀሪ ቤተሠብ ማስተዳደር አልቻልኩም ልጄን የተሻለ ሕክምና የተሻለ መድሀኒት እንድታገኝ በሀሳብም በገንዘብም እርዳታችሁ በፈጣሪ ስም አይለየኝ ትላለች ወላጅ እናቷ እያለቀሠች

094 021 5213 ንብረት በሬቻ / እናቷ
1000030804398 ንብረት በሬቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
2024/09/28 04:22:17
Back to Top
HTML Embed Code: