Telegram Web Link
ከሻዕባን ወር 15'ኛው ሌሊት
(ليلة النصف من شعبان)
===================

የሚያዝን፣ የሚራራ፣ የሚምር ...." ጌታ " ባርያ መሆን ምነኛ መታደል ነው::የበዛ ዕድል፤ የማያልቅ ገፀ- በረከት ፤ሁሌ አዲስ ፤አንዱ ሲያልቅ ሌላ ኽይር ስራ.... ...!እነሆ የዛሬዋ ፀሀይ ስትጠልቅ የተከበረችው 15ኛዋ የሸዕባን ሌሊት ትጀምራለች፤ይህች ሌሊት ልዩና የተከበረች ናት::
ይህች ሌሊት ብዙ በረከትንና መልካም ስጦታን የያዘች ሌሊት ነች፣ከታቢዒዮች መሀከል ሌሊቷን በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው አድርገው የሚያሳልፏት ነበሩ፣በዚህች ሌሊት ልዩ ደረጃ ዙሪያ የተለያዩ ነቢያዊ ሀዲሶች ተዘግበዋል፣ከነዛም መሀከል:–
①አቡ ሙሳ አል አሽዐሪይ(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት፤
የአላህ መልእክተኛﷺእንዲህ ብለዋል
*«إِنَّ اللَّهَ لَيَطَّلِعُ فِي لَيْلَةِ النِّصْفِ مِنْ شَعْبَانَ،*فَيَغْفِرُ لِجَمِيعِ خَلْقِهِ،*إِلَّا لِمُشْرِكٍ أَوْ مُشَاحِنٍ» *.

*رواه ابن ماجه وابن حبان وغيرهما.
قال الإمام الهيثمي في مجمع الزوائد:
"رَوَاهُ الطَّبَرَانِيُّ فِي الْكَبِيرِ وَالْأَوْسَطِ،
"በሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ላይ በእርግጥም አሏህ በእዝነቱ (ብቅ ይልና) በሱ ላጋራና ለተጣሉ ሰዎች ሲቀር ለሁሉም ፍጡራኖቹ ማሀርታውን ይለግሳል"
ኢብኑ ማጀህ ኢብኑ ሂባንና ሌሎችም ዘግበውታል።

ኢማም ሀይሰሚይ መጅመዑ ዘዋኢድ በሚለው መፅሀፋቸው ላይ"ይህን ሀዲስ ጦበራኒይ በ"ከቢር"እን በ"አውሰጥ"የሀዲስ ጥራዛቸው ላይ ዘግበውታል፣እናም ሁሉም የሀዲሱ አቀባዮች ታማኝ ናቸውም"ብለዋል

②ሰዪደህ ዓኢሸህ(ረ.ዐ)እንዲህ ትላለች
: فقدت النبي صلى الله عليه وسلم ذات ليلة، فخرجت أطلبه، فإذا هو بالبقيع، رافعاً رأسه إلى السماء. فقال : (أكنت تخافين أن يحيف الله عليك ورسوله؟) فقلت : يا رسول الله ظننت أنك أتيت بعض نسائك.
فقال : (إن الله تبارك وتعالى ينزل ليلة النصف من شعبان إلى السماء الدنيا، فيغفر لأكثر من عدد شعر غنم بني كلب)
خرّجه الإمام أحمد والترمذي وابن ماجه .
የዛች ሌሊት የአላህ መልእክተኛንﷺ አጣዃቸውና፥ ለመፈለግ ወጣሁ፤እሳቸውም "በቂዕ" ውስጥ ራሳቸውን ወደ ሰማይ ቀና አርገው ነበር፤እንዲህም አሉኝ "አላህና መልእክተኛው ባንቺ ላይ በዳይ እንዳይሆኑ ትፈሪያለሽን?አሉኝ::እኔም" አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዷ ባልተቤቶ ዘንድ ሄደው ይሆናል ብዬ ጠርጥሬ
ነበር"አልኳቸው::ከዛ እሳቸው እንዲህ አሉኝ "በእርግጥም በረከቱ የበዛና የላቀው አላህ በሸዕባን አጋማሽ
ሌሊት ወደ ቅርቢቷ ሰማይ–እዝነቱ–ይወርድና፣ከ"በኒ ከልብ"ጎሳ በግና ፍየሎች ቁጥር በላይ ለሆኑ ባሮቹ ይምራል)

ኢማም አህመድ፣ቱርሙዚይ፣ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
ዐብደሏህ ቢን

③ዐምር(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት፣የአላህ መልእክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፣
(إن الله ليطلع إلى خلقه ليلة النصف من شعبان، فيغفر لعباده، إلا اثنين : مشاحن، أو قاتل نفس).
وخرّجه إمام أحمد
وابن حبان في "صحيحه" من حديث معاذ، مرفوعاً.
"በሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ላይ በእርግጥም አሏህ በእዝነቱ (ብቅ ይልና) ከተጣላና ነፍስን ከገደለ ሰው ውጪ፥ ለሁሉም ባሮቹ ማሀርታውን ይለግሳል"
ኢማም አህመድ እንዲሁም ኢብኑ ሂባን በ"ሶሂሃቸው"ከሙዐዝ ሀዲስ ወደ ሰዪዳችን ከፍ አድርገው ዘግበውታል

ስለ ሌሊቷ - ከዑለማኦች አንደበት
=======================
①ኢማሙ ሻፊዒይ(ረህመቱሏሂ ዐለይህ)
وَبَلَغَنَا أَنَّهُ كَانَ يُقَالُ : إنَّ الدُّعَاءَ يُسْتَجَابُ فِي خَمْسِ لَيَالٍ فِي لَيْلَةِ الْجُمُعَةِ, وَلَيْلَةِ الْأَضْحَى, وَلَيْلَةِ الْفِطْرِ, وَأَوَّلِ لَيْلَةٍ مِنْ رَجَبٍ, وَلَيْلَةِ النِّصْفِ مِنْ شَعْبَانَ.
በአምስት ሌሊቶች ዱዐእ ተቀባይነቱ የጎላ ነው ይባል እንደነበረ ደርሶናል::እነርሱም:–
1:የጁሙዐ ሌሊት
2:የዒደል አድሀ ሌሊት
3:የዒደል ፊጥር ሌሊት
4:የረጀብ ወር የመጀመሪያው ሌሊት
5:የሸዕባን 15 ሌሊት ናቸው
አል ኡም 1/265
🔹🔹🔹
②ኢብኑ ረጀብ አል ሀንበሊይ(ረህመቱሏሂ ዐለይህ)"ለጧኢፉል መዓሪፍ"በተባለው መፅሀፋቸው ውስጥ

(አንድ ሙዕሚን በዚህች ሌሊት ዒባዳዎች ላይ ሊጠነክር፣እንዲሁም ወንጀሉ እንዲማርና እንዲሸፈን፣ችግሮችም እንዲወገዱ ዱዐ በማድረግ ሊያሳልፈው ይገባል::ከዛ በፊት ግን በዛች ሌሊት አሏህ ወደሱ ለተመለሰ ይመለሳልና ተውበት(ወደ አሏህ መመለስን)ያስቀድም!ብለዋል::
🔹🔹🔹
③ዐጧእ ቢን የሳር(ረህመቱሏሂ ዐለይህ) በ"ለጧኢፉል መዓሪፍ" ኪታብ ላይ እንደተጠቀሰው"ከለይለተል ቀድር ቀጥሎ ከሸዕባን 15ኛው ሌሊት የምትበልጥ አንድም ሌሊት የለችም!

በዚህች ሌሊህ አሏህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ "እዝነቱን" ያወርድና በሱ ካጋራ፣ከተጣሉና፣ዝምድና ቆራጭ ከሆኑ ሰዎች ውጪ ለሁሉም ባሮቹ ይምራል)ብለዋል።
🔹🔹🔹
④ኢማም አል ከርማኒ(ረ.ዐ)
"ኻሊድ ቢን መዕዳን፣ሉቅማን ቢን ዓሚር፣እና ሌሎችም በዚህች ሌሊት ከልብሶቻቸው ውስጥ ምርጡን ይለብሳሉ፣ሽቶን ይቀባሉ፣ኩል ይኳላሉ፣በዛች ሌሊት በመስጂድ ውስጥ እየሰገዱ ያሳልፋሉ,ኢስሃቅ ቢን ራሀወይሂም በዚህ ተግባር ላይ ገጥመዋቸዋል" መሳኢል 🔹🔹🔹
⑤ኢማም አል ቁስጠላኒ(ረ.ዐ)እንዲህ ብለዋል
"ኻሊድ ቢን መዕዳንን እና መክሁልን የመሳሰሉ፣ከሻም ሀገር የሆኑ ታቢዒዮች በሻዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት ላይ በአምልኮ ላይ ይለፉ ነበር፣ሰዎችም ሌሊቷን ማላቅ ከነሱ ነው የያዙት"
አል መዋሂብ 2/259
🔹🔹🔹
⑥ኢብኑ ሀጀር አል ሀይሠሚይ(ረ.ዐ)እንዲህ ብለዋል:-
"ጭማቂው ይህች ሌሊት ደረጃ ያላት፣ልዩ የሆነ መሀርታና፣የዱዓእ ተቀባይነት የሚከሰትባት ሌሊት ነች"
አል ፈታወል ፊቅሂየቱል ኩብራ 3/377
🔹🔹🔹
⑦ከሀንበሊይ መዝሀብ ሊቃውንቶች ውስጥ አንዱ የሆኑት ኢማም አል በሀውቲይ(ረ.ዐ)እንዲህ ይላሉ:-
"የሸዕባን ወር አጋማሿ ሌሊትማ በውስጧ ትሩፋት አለ፣ከሰለፎች መሀከል በሌሊቷ ውስጥ የሚሰግዱ ነበሩ"
ሸርሁ ሙንተሀል ኢራዳት 2/80
🔹🔹🔹
⑧ኢብኑ ኑጀይም(ረ.ዐ)እንዲህ ይላሉ,
"ከሚወደዱ ተግባራት መሀከል የረመዷንን አስርት ሌሊቶች፤የሁለቱን ዒድ ሌሊቶች፤የዙል ሂጃ አስሩን ሌሊቶች፤የሸዕባን አጋማሽ ሌሊትን ሀዲሶች ላይ እንደተገኘው ህያው ማድረግ ነው
አል በህሩ ራኢቅ 2/56
____\\\______
እናም ይህ የተከበረ ለይል እንዳያመልጠን በዱዓ በዚክር በሶላት በቁርኣንና በተለያዩ በጎ ተግባራት እናሳልፈው::
___
በአኢማ ሚድያ እና ኮምኒኬሽን ዲፓርትመንት የተሰናዳ
የዛሬዋ ሌሊት ብዙ ኸይራትንና በረከቶችን የያዘች ሌሊት ነች፣በተለያዩ የዒባዳ አይነቶች ሌሊቱን ህያው ማድረግ እንደሚወደድ ዑለማኦቻችን ይገልፃሉ .....
___
በዚህ ሌሊት ብዙሃን መሻይኾቻችን ከሚሰሯቸው በጎ ተግባራት መሀከል
☞ከመግሪብ ሶላት በዃላ 3 ጊዜ ሱረቱ ያሲንን መቅራት
–የመጀመሪያውን ያሲን እድሜያችን አላህን ከመታዘዝ ጋር እንዲያረዝምልን
–ሁለተኛውን ያሲን ከመቅሰፍቶችና ከፈተናዎች አላህ እንዲጠብቀንና ሲሳያችንን እንዲያነሳልን
–ሶስተኛውን ለልብ መብቃቃትና ለመጨረሻ ማማር(ሁስነል ኻቲመህ)
☞ከእያንዳንዱ ያሲን በዃላ በምስሉ ላይ የተቀመጠውን ዱዓእ መቅራት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ሼር ሼር ሼር
በሐዲስ የመጣልን ጨረቃን አይተን ጾም እንድይዝ ጨረቃን በማየት እንድናፈጥር ነው፡፡በዚህም መሰረት በየሚዲያው እንዲህ የሚል"ረመዷን የሚጀምረው ሚያዝያ 5 ነዉ:: ነብያችን(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ; አንድ ሰው ለሌላ ሰው ረመዷንን ለመጀመሪያ ጊዜ ካሳወቀ እሳት በሱላይ ሀራም ትሆንበታለች " ውሸት ቅጥፈት ነው፡፡
አንደኛ ረመዷን ሚያዚያ 5 እንደሚጀምር ከየት ታወቀ?በሐዲስ የመጣው ሽዕባን 29 ላይ ጸሀይ ከገባች በኋላ ጨረቃን በመከታተል ከታየች ቀጣዩ ቀን ረመዷን 1 እንደሚል ነው... ጨረቀ ከተጋረደችና ካልታየችን ደግሞ ሸዕባንን 30 ቀን ሞልተን ከዛ ረመዷንን 1ንድ ብለን እንጀምራለን!
ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ብለዋል የሚሉት በየትኛው ሐዲስ ነው?እያወቁ በነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ መዋሸት ከባድ ወንጀል መሆኑን አያቁም?፡፡እና የሚያስተላልፉት ነገር ስህተት ነው በጭራሽ እንደዚህ የሚል ሐዲስ አልመጣም!ውሸት ነው ስለዚህ ያገኘነውን ሼር አናድርግ!


Share/ሼር ለሁሉም
Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv
በናይጀሪያ “ከ1,800 በላይ የሚሆኑት ታራሚዎች ከወህኒ
ቤት”አመለጡ ተባለ
ፖሊስ ለጥቃቱ ተገንጣይ ቡዱን የሚላቸውን “የቤያፍራ
ተወላጆች” ተጠያቂ አድረግዋል
ከጥር ወር ወዲህ በርካታ የናይጄሪያ ፖሊስ ጣቢያዎች ጥቃት
እየደረሰባቸው ይገኛል
እስረኞቹ ከወህኒ ቤት ያመለጡት ሮኬት፣ በራሪ ቦምብ ፣ መትረየስ ፣
ፈንጂ እና ጠመንጃ የያዙ ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ
ነው፡፡
ታጣቂዎቹ ከናይጄሪያ ትልቁ ከተማ ሌጎስ በስተደቡብ ምስራቅ 400
ኪ.ሜ (260 ማይል) ርቀት በምትገኘው ኦወሪ ከተማ ፤በሚገኘው
የማረሚያ ቤቱ አስተዳደራዊ ስፍራ ላይ ፍንዳታ በማካሄድ ወደ
ወህኒ ቤቱ ቅጥር ግቢ ለመግባት ፈንጂዎችን መጠቀማቸውንም
ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
የናይጄሪያ ማረሚያ አገልግሎት ሰኞ ማለዳ ከጥቃቱ በኋላ 1 ሺህ
844 እስረኞች ማምለጣቸውን አረጋግጧል፡፡
የናይጄሪያ ፖሊስ ጥቃቱን “የቤያፍራ ተወላጆች” ስበስብ እንደሆነ
በሚነገርለትና በታገደው ተገንጣይ ቡድን ተፈፅመዋል ሲል ቡዱኑን
ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ፖሊስ ተገንጣይ ያለው ቡዱን ተጠያቂ ቢያደርግም፤ ቡዱኑ ግን
ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ኃላፊነት እንደማይወስድ መግለፁን
የፈረንሳዩ የዜና ወኪል/ኤ.ኤፍ.ፒ) ዘግበዋል፡፡
ምንም እንኳን አስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም፤ ከጥር
ወር ወዲህ በርካታ የደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ ፖሊስ ጣቢያዎች
ጥቃት ማስተናገዳቸውና በዚህም ከፍተኛ መጠን ያላቸው
ጥይቶችም መዘረፋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
"ሌባው" የመስጅድ ኢማም
=================

ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኝ መስጂድ ኢማም የሆኑትን ሸይኽ ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች።

«ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት። ያም ቢሆን ባለቤቷ ኢማሙን ተከትሎ ሶላት ላለመስገድ ወሰነ።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። ስለዚህ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን ሹክ አላት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው ገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። እርሱም ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።

የመስጅዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ « ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ አለመቅራታችሁ ገርሞኝ ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።

እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን ቃል ከፍተን ያነበብነው? 😢 ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው ወገኖቼ የአላህ ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።

#ውዶቼ ካነበብኩት ላካፍላቹ ብዬ ነው! እንደምትማሩበት ተስፋ አረጋለው! ቢያንስ ለ10 ሰው share... እናርግ
ብስራት 👨ብስራት 🧔ብስራት
💚💚💚💵💵💵💵💵💵
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ነገን በተስፋ ጉዳይ የማስፈፀም ስራ ለ1000 ሰብስክራይብ መደዋወል መለመን ሰብ 4 ሰብ በቃ ይለናል በርካሽ ዋጋ ቻናላችሁን ሰብ ማስጨመር ጀምረናል 💚💚💚😉
በአጭር ግዜ ውስጥ ማለትም
በ20 ቀን ቻናላችሁን እናሳድገዋለን
ሞኒታይዝ እናስገባለን ክፍያው
እርካሽ መሆኑ ለየት ያደርገናል
ከእዚሁ ጋር ተያይዞ
ቪድዮቻችሁ ብዙ ቪዩ ያገኛል
ክፍያ ከስራ በፊት መሆኑ ለየት ያደርገናል ቶሎ በሉ ፍጠኑ ወረፋ ያዙ ስለስራችን ከዚ ቀደም የሰራንላቸው ሠወች ይመሰክራሉ
ይህ ድርጅር በቀላሉ ምንም ማይነቃነቁ ቤተሰቦችን ከብዙ ቪው ጋር ያገናኛል 🙈🙈💵💵 በዚ መመዝገብ ትችላላችሁ
👇👇👇👇
@jabirtube
Watch "
👇👇👇👇👇👇👇

ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ሙስሊሙን ኡማ አይወክልም የሀጂ ተቃራኒ ቡድኖች መታየት ያለበት ቪድዮ" on YouTube
https://youtu.be/ksWNpFvsivQ
قال الله تعالى:
(( إِنَّ اللَّهَ لا يَغْفِرُ أَنْ يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَنْ يَشَاءُ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا))[النساء:48]
---------------------------------------አላህ በእርሱ ማጋራትን በፈፁም አይምርም ።ከዚህ ሌላ ያለውንም ሓጢያት ላሻውም ሰው ይምራል በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ሃጢያት በእርግጥ ቀጠፈ ። ሱራ ኒሳእ 48
قال الله تعالى:
(( إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللّهُ عَلَيهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ ))[المائدة:72]
---------------------------------------እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ ። መኖሪያውም እሳት ናት ። ለበዳዮችም ምንመ ረዳቶች የላቸውም ። ሱራ ማኢዳ :72
قال الله تعالى:
(( وَلَوْ أَشْرَكُواْ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُواْ يَعْمَلُونَ ))[الأنعام:88]
ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበረው ከነሱ ላይ ይታበሳል (መና ይሆናል) ሱራ አንኣም :88
قال الله تعالى:
(( وَمَن يُشْرِكْ بِاللّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلاَلاً بَعِيدًا ))[النساء:116]
በአላህም የሚያጋራ ሰው ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርገጥ ተሳሳተ። ሱራ ኒሳእ :116
قال الشيخ سليمان بن عبدالله رحمه الله:
قال ابن كثير: أخبر تعالى أنه {لا يغفر أن يشرك به} ، أي: {لا يغفر} لعبد لقيه وهو مشرك به، {ويغفر ما دون ذلك} ، أي: من الذنوب {ويغفر ما دون ذلك} من عباده.
ሼክ ሱለይማን ኢብን አብዱርህማን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ :- ኢብን ከሲር እንዲህ አሉ አላህ አወሳ እሱ
{لا يغفر أن يشرك به} ،
በሱ ያጋሩበትን ሰው አይምርም ። ማለትም ምህርት አያድርግለትም በሱ አሻረኮ አላህን ለተገናኘ ሰው
{ويغفر ما دون ذلك}
ከዛ ውጭ ላለው ነገር ግን ይምራል ። ማለትም ከወንጀል ከባሮቹ ላይ (ይምራል) ።
قلت: فتبين بهذا أن الشرك أعظم الذنوب، لأن الله تعالى أخبر أنه لا يغفره، أي: إلا بالتوبة منه، وما عداه، فهو داخل تحت مشيئة الله إن شاء غفره بلا توبة وإن شاء عذب به.
وهذا يوجب للعبد شدة الخوف من هذا الذنب الذي هذا شأنه عند الله،
እንዲህ አልኩ:- ልብ በል በዚህ ሽርክ ትልቅ ወንጀል ነው ፣ምክኒያቱም አላህ እንደማይምር አውስቷልና በተውባ ብቻ ቢሆን እንጅ ። ከዛ ያለፈ(ከሽርክ ውጭ ያለው ጉዳይ) ከአላህ ፈቃድ በታች ነው ከፈለገ ይምረዋል ያለ ተውባ ወይም ይቀጣዋል ስለዚህም አንድ በሪያ ከዚህ ወንጅል አጥብቆ መሽሽ አለበት ይህ አላህ ዘንድ እንዲህ የተባለውን።
وإنما كان كذلك؟ لأنه أقبح القبح وأظلم الظلم إذ مضمونه تنقيص رب العالمين، وصرف خالص حقه لغيره، وعدل غيره به كما قال تعالى: {ثم الذين كفروا بربهم يعدلون} ولأنه مناقض للمقصود بالخلق والأمر مناف له من كل وجه، وذلك غاية المعاندة لرب العالمين، والاستكبار عن طاعته والذل له، والانقياد لأوامره الذي لا صلاح للعالم إلا بذلك. فمتى خلا منه خرب وقامت القيامة.

(تيسير العزيز الحميد ٨٨
ለምን እንደዛ ሆነ? ያ መጥፎ አስከፊ እና ከዙልም ትልቁ ዙልም ስለሆነ ነው ። የሰማየት እና እምድር ፈጣሪን አላህን ማሳነስ ያሰይዛል ከሱም ወደሌላ ማዘንበልን የስከትላል አላህ እንዳለው {ثم الذين كفروا بربهم يعدلون}
ከዛም እነዛ የካዱት ከጌታቸው ጋር ጣኦታትን ያስተካክላሉ ። ሱራ አንኣም: 1 ። ይህ መጣረስ ለአላህ የተገባውን ነገር ለፉጡር ማድርግን ያሳያል ለአላህ ብቻ የተደረጉትን ነገር ለዛም መዳረሻው አላህን እንቢ ማለት ነው ከ ትዕዛዙ መኩራራት ነው እናም የግድ ለአላህ ሁሉን ነገር ትእዛዙን መፈፀም ግዴታ ወደሱም እራስን መስጠት ነው ይህን የተወ ያኔ ቂያም ቆመች ።

#ተይሲር_አዚዝ_ሃሚድ_:88
‏قال ابن عبد البر - رحمه اللّٰه - :

« الحق ثقيل ، وطلابه قليل ».

بهجة المجالس 1/128
ኢብን አብዱል በር ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ :-
ሃቅ ትልቅ(ከባድ)ነው እሱን የሚማሩት ግን ጥቂቶች ናቸው ።
ቢሁጀቲ አልመጃሊስ (1/128)
Forwarded from ቢላሉል ሀበሽይ ጀመአ (ABDUREZAK 😋😍😉)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Y erdata teri ymetmelektut wenidmachni be tena tamobenale le wegni derash weg nw le allah belachu enirdawe wenidmachnin
le allah belachu erduleni k allhegar aberni enadenw yerdata teri
@Wesmani777
Watch "ማልቀስ ማይፈልግ አይክፈተው ልብ ይነካል እኮ "ምን ተሻለ "" on YouTube
https://youtu.be/0K2xFQPS3E0
Forwarded from Elham Murad
Forwarded from Elham Murad
VID-20210502-WA0006.mp4
10.7 MB
Video from Elham Murad
Watch "محمد العريفي" on YouTube
https://youtube.com/shorts/JotP52faXhs?feature=share
VERY IMPORTANT!!!

This msg is for everyone . If u find any child crying on the road showing his/her address on a piece of paper and asking u 2 take him/her to that address, please if u're so sympathetic, take that child 2 d Police Station and don't take him/her to that address. It is a new way of gang Stealing, Raping & Kidnapping. Pls, forward 2 all Ur loved ones. One msg from u may save a life or property. Plz circulate. Let us b security conscious.

4wrded as received
ውድ የተሌግራም ቻናል ቤተሰቦቼ
እንኳን ለ 1442ኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ወንድማቹህ jabir
2024/09/28 06:17:37
Back to Top
HTML Embed Code: