Telegram Web Link
ምርጥ ግጥም

ከአርጦግሮል ወዳጆች በኢትዮጵያ ግሩፕ





ጀግና አምጦ የወለደኝ
ከብሮ መኖር ያስተማረኝ
ግዙፍ ጠላት ማይበግረኝ
እኔ ማለት ኦርቶግሮል ነኝ
ኦርቶግሮል ነኝ የሱለይማን
የሚፈራኝ ኢንሱም ሸይጣን
ከሳዕደዲን እስከ ኖያን
ተንኮል ዘርቶ የሚያጭድን
ሞት ዘርቼ ደም የማጥን
የኦርቶግሮል ነኝ የኢስላም ልጅ
ለዲን ኖሬ ለዲን ማረጅ
ከአርሰላን ከአያቴ
የኦጎዝ ዘር ማንነቴ
ያስቋጠረኝ ከልቤ ላይ
ኢስላም ነግሶ ድል እስከማይ
ዱሩ ቤቴ ልብሴም ሰማይ
ካላህ በቀር ሌላ እንዳላይ
የታተመ ከልቤ ላይ
ሀሰኑል በስሪ እንዲህ አሉ

ላንተ ነገር ያመጣልህ ሰው መልሶ
ካንተም ለዛኛው እንደሚወስድለት
እርግጠኛ ሁን ።

ተንቢሁል ጋፊሊን (173)

JOIN US
👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERS
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ፡- ‹‹አንዳችሁ እምነት ሊኖረው አይችልም - ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ፡፡››
عن أنس، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
(لا يؤمن أحدكم حتى يحب لأخيه ما يحب لنفسه).

.https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFhaDhllwlCadjFDlw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምርጥ ግጥም

ከአርጦግሮል ወዳጆች በኢትዮጵያ ግሩፕ





ጀግና አምጦ የወለደኝ
ከብሮ መኖር ያስተማረኝ
ግዙፍ ጠላት ማይበግረኝ
እኔ ማለት ኦርቶግሮል ነኝ
ኦርቶግሮል ነኝ የሱለይማን
የሚፈራኝ ኢንሱም ሸይጣን
ከሳዕደዲን እስከ ኖያን
ተንኮል ዘርቶ የሚያጭድን
ሞት ዘርቼ ደም የማጥን
የኦርቶግሮል ነኝ የኢስላም ልጅ
ለዲን ኖሬ ለዲን ማረጅ
ከአርሰላን ከአያቴ
የኦጎዝ ዘር ማንነቴ
ያስቋጠረኝ ከልቤ ላይ
ኢስላም ነግሶ ድል እስከማይ
ዱሩ ቤቴ ልብሴም ሰማይ
ካላህ በቀር ሌላ እንዳላይ
የታተመ ከልቤ ላይ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Nejwi online shopping (feyruz 💎 dimond•) via @like
ባረከላሁ ለኩማ😍
ወ ባረክ አለይኩማ😍😍
ወጀመአ በይነኩማ😍😍😍
ፊል ከይር👏👏👏👏


መብሩክ መብሩክ
ሙብሩክ መብሩክ
መብሩክ መብሩክ👍👍
ሙአዙ😍😍😍😍

ረጅም
እድሜ እና
ጤና ከ ሙሉ
አፊያ ጋር

ተመኘው❤️❤️❤️❤️❤️

መልካም ጋብቻ
ለ ሙአዝ ሀቢብ እና
ለ ለይላ ይማም
💍💍💍
Forwarded from Al_Faaruuq_bot
ይህን ምርጥ ቻናል እንደምትወዱት እርግጠኛ ነኝ በቅርቡ ተከፍቶ ተወዳጅነት ያተረፈው ቻናል ነው እናንተም ተጠቀሙበት
♻️በዚህ ቻናል የሚተላለፉ የፅሁፍ አይነቶች;— ♻️
① ወደ አማረኛ የተተረጎሙ አጫጭር ፈትዋዎች፣
② በውስጥ መስመር ለሚላኩ ዲናዊ ጥያቄዎች የተሰጡ የኡለሞች ምላሾች፣
③ እጥር ምጥን ያሉ የቀደምት ኡለሞች ድንቃድንቃ ንግግሮቻቸው፣
④ አዝናኝና ፈገግ የሚያደርጉ ግን ቁም ነገር አዘል አጫጭር የዑለሞች ፈትዋ
⑤ አጫጭርና ቀላል ተከታታይ የዓቂዳና የፊቅህ ፅሁፎች
➅ ከጀናዛው ማጠቢያ ክፍል ተከታታይ ደእዋ
➆ የረሱል ﷺ ጣፋጭ ሀዲሶች

እና ሌሎችም ይቀርባሉ። ይከታተሉ፣ ለወንድምና እህትዎ ያስተላልፉ፣
ሰዎችን ወደ ጥሩ ነገር ያመላከተ ልክ እርሱ እንደሰራው ነው የሚቆጠርለት።"
ሀሳብና አስተያየት ካላቹህ
@Faaruuq1 አድርሱን ቻናሉን ለመቀላቀል ከታች አስገባኝ ሚለውን ጠቅ አርጉት


አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ
አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ኡድህያ መታወቅ ያለባቸው 30 ነጥቦች

በዒድ ቀን ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ ደግሞ ኡድሒያን ማረድ ነው፡፡ ስለሆነም ስለ ኡድሒያ ጥቂት እንተዋወስ፡-

1. ‹ኡድሒያ› ማለት በዒድ አል-አድሓ ቀንወደ አላህ (ሱ.ወ.) ለመቃረብና ትዕዛዙን ለመፈጸም ተብሎ የሚታረድ እንሰሳ ነው፡፡ በዱሓ ወቅት ማለትም ረፋድ ላይ ስለሚታረድ ስያሜውን ‹ዱሓ› ከሚለው አገኘ ያሉም አሉ፡፡

2. ኡድሒያ ሸሪዓዊ ድንጋጌ ያለው ጉዳይ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ‹ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም፡፡› (አልከውሠር፡2) ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) እንዳሉት መስዋእት የተባለው ‹በዒድ አልአድሓ ቀን የሚፈጸም እርድ ነው፡፡›

3. በአነስ (ረ.ዐ.) ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሁለት ቀንዳም የሆኑ በጎችን በማረድ አንዱ ለርሳቸውና ለቤተሰባቸው ሌላኛው ለተከታዮቻቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

4. ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ.) እንዳሉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በመዲና ሳሉ አሥር አመት ሙሉ ኡድሒያ አርደዋል፡፡

5. ብያኔው ላይ የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን አብዛኞቹ ዑለሞች ‹ሱና ሙአከዳ/ አጽንኦትና ክብደት የተሰጠው ሱና› ያሉ ሲሆን እነ ኢማም አቡ ሐኒፋና ኢብኑ ተይሚያ ደግሞ ‹ግዴታ ነው› ብለዋል፡፡

6. ኡድሒያ ለማረድ ኒያ ያለው ሰው አሥሩ የዚልሒጃ ቀናት ከገቡ በኋላ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን መቆረጥ የለበትም፡፡

7. ኡድሒያ ለማረድ ያሰበ ሰው እንሰሳውን ሲገዛም ሆነ ሲያርድ ኒያውን ማስገኘት ይኖርበታል፡፡

8. ኡድሒያ የሚታረደው ከዒድ ከሶላት በኋላ ነው፡፡ ከዒድ በኋላ ባሉት ሶስቱ ቀናት ውስጥም ማረድ ይቻላል፡፡ በላጩ ግን መልካምን ነገር ቶሎ ለመፈፀም መሽቀዳደም ነው፡፡

9. የዒድ አልድሓ ቀን ሳይበሉ መውጣት እንዲሁም ከሶላት ከተመለሱ በኋላ ካረዱት እንሰሳ መመገብ ሱና ነው፡፡

10. ለኡድሒያ የሚታረደው እንሰሳ ምርጥና ውድ፣ ሲያዩት የሚያምርና የሰባ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሶሓቦች ለኡድሒያ የሚያርዱትን እንሰሳት በመቀለብ እስከ መታረጃው ቀን ድረስ ያሰቡ ነበር፡፡

11. ኡድሒያ ከእስልምና ምልክቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የእስልምናን ምልክቶችን መገለጫዎች ማክበር አላህን የመፍራት ምልክት ነው፡፡

12. ለኡድሒያ የታረደውን እንሰሳ ሶስት ቦታ በመክፈል አንድ ሶስተኛውን መብላት፣ አንደ ሶስተኛውን ሀዲያ/ስጦታ መላክ እንዲሁም አንድ ሶስተኛውን ለድሆች መመጽወት ያስፈልጋል፡፡

13. ለኡድሒያ የሚታረዱ እንሰሳት በዋናነት በግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ናቸው፡፡ ዶሮ ሆነ ሌሎች የሚበሊ እንሰሶች ለኡድሒያ አይበቁም፡፡

14. ለኡድሒያ የሚታረደው እንሰሳ በግ ከሆነ ስድስት ወር፣ ፍየል አንድ አመት፣ ከብት ሁለት አመት፣ ግመል አምስት አመት የሞላው መሆን ይኖርበታል፡፡

15. ግመልና ከብትን ለሰባት ሆኖ ማረድ ይቻላል፡፡

16. ለኡድሒያ የሚታረድ እንሰሳ ምንም ዓይነት እንከንን ነውር የሌለበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ነውርና እንከን ሲባል ዐይኑ የጠፋ፣ የታመመ፣ የሚያነክስ፣ የከሳ፣ ያረጀ፣ ላቱ፣ ጆሮው ወይም ከአካል ከፍሉ አንዳች ነገር የተቆረጠና የመሳሰለውን ነው፡፡

17. ለኡድሒያ የሚታረድ እንሰሳ ቆዳው መሸጥ የለበትም፡፡ በአግልግሎት ክፍያ መልክም ለአራጅ መስጠት አይቻልም፡፡

18. የኡድሒያ ባለቤት ኡድሒያውን በራሱ እጅ ቢያርድ፣ በራሱ እጅም ቢያከፋፍል መልካም ነው፡፡ የአምልኮ ተግባር ነውና፡፡

19. በሚያርድበት ጊዜም ‹ቢስሚላህ አላሁ አክበር› በማለት ቀጥሎም ‹አልላሁም ሃዛ ዐንኒ ወዐን አህሊ በይቲ፡፡ አልላሁምመ ተቀብበል ሚንኒ/አላህ ሆይ! ይህ ከኔ እና ከቤተሰቤ ነው፡፡ አላህ ሆይ ተቀበለኝ› ማለት ይኖርበታል፡፡

20. ቤተሰቡ የበዛ ቢሆንም እንኳን ለሙሉ ቤተሰብ አንድ ኡድሒያ በቂ ነው፡፡

21. የሚታረደው እንሰሳ የራስ ንብረት መሆን አለበት፡፡ ያለባለቤቱ ፈቃድ፣ ሰርቆም ሆነ ነጥቆ ማረድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በንጹህ እንጂ በውሸት ገንዘብ ወደ አላህ (ሱ.ወ.) አይቀረብምና፡፡

22. ለኡድሒያ ታስቦ አንድ ሰው አንድን በግ ወይም ፍየል መጋራት አይችልም፡፡ ከሰባት በላይ በሆነ ሰውም አንድን ከብት ማረድ አይበቃም፡፡

23. ኡድሒያን ከሰላት በፊት ማረድ አይቻልም፡፡ ከጊዜው በፊትም ሆነ ከጊዜው በኋላ ማረድ እንደማንኛውም ሥጋ እንጂ ኡድሒያ አትሆንም፡፡

24. አራጅ የእርድ ሥነሥርኣትን መጠበቅ አለበት፡፡ የሚታረደውን እንሰሳ ወደ ቂብላ ማዞር፣ የአላህን ሥም ማውሳት፣ አንደኛውን እንሰሳ ሌላኛው ፊት አለማረድ፣ የሚያርዱበትን ቢላዋ በሚገባ መሳልና ቶሎ ማሰረፍ ጥቂቶች ናቸው፡፡

25. ኡድሒያ ማረድ ለማይችል ሰው እሱን ነግሮና አስፈቅዶ ለሱ አስቦ ማረድ ይቻላል፡፡

26. ድሃ ሰው የተላከለትን የኡድሒያ ሥጋ መሸጥም ሆነ ሌላ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል፡፡

27. ኡድሒያን ሰው ወክሎ ማሳረድ ይቻላል፡፡ የሚታረደለት ሰውም ጸጉሩን ጥፍሩን ከመንካት መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

28. ዑለማኦች ኡድሒያን ማረድ ያልቻሉ ሰዎች ሀሳብ ሊገባቸው እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ሁለት በጎችን በሚያርዱበት ወቅት አንዱን አቅም ለሌላቸው ህዝቦቻቸው አርደዋልና፡፡

29. ኡድሒያ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም ወደሱ መቃረቢያ ተግባር ከመሆኑም በላይ የመተዛዘንና የመተሳሰብ ተምሳሌት ነው፡፡ በዕለቱ ድሆች ጠግበው ይውላሉ፡፡ ሥጋ አያምራቸውም፡፡

30. የኡድሒያ ቀን አላህን ማውሳት የሚጎላበት ነው፡፡ ፀጋውንም ደጋግመን እናመሰግንበታለን፡፡ ቅኑንና ተወዳጁን ነቢይ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ.) እና ልጃቸውን ኢስማዒልን እናስታውስበታለን፡፡

ወላሁ አዕለም፡፡

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!

ኢዱን አላህን በማመስገን እና በማላቅ ትዕዛዛቱን በመፈፀም ታላቅ አጅር የምናገኝበት አላህ ያድረግልን!!

አሚን!!
አሚን!!

ይህን መልዕክት ሼር በማድረግም ላልደረሳቸው እናዳርስ
ቻናላችን ላይ ከተመረጡ ግጥሞች በድምፅ
<unknown>
ከቻናላችን ከ 30 በላይ ተወዳዳሪወች
የተመረጡ ለ 100 ብር ካርድ የታጩ 8 ግጥሞችን በድምፅ ስሙት 👏👏
ሌሎች ሚመጡ ግጥሞች ሊታጩ ይችላሉ
ሳሊም ከከሚሴ
ሀኒ ነኝ
የመሳሰሉት

@ONLYFORTRUTHERSJ
የአፍሪካ አካዳሚ ስልጠና ሁለት መመዝገቢያ ፎርም እንዴት እንደሚሞላ በሚከተለው ሊንክ ገብተው በፌስቡክ ገጻችን ላይ መመልከት ይችላሉ።

https://www.facebook.com/191430540870370/posts/3839388269407894/
Don't miss out on fasting tomorrow (Arafah day):

Abu Qatadah (May Allah be pleased with him) reported:

The Messenger of Allah (ﷺ) was asked about the observance of Saum (fasting) on the day of 'Arafah. He said, "It is an expiation for the sins of the preceding year and the current year."

[Muslim]

@ONLYFORTRUTHERSJ (telegram)
2024/09/28 20:16:39
Back to Top
HTML Embed Code: