Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
..የሟችን ጀናዛ የሚያጥብ የሚሸኝና የሚቀብር ቤተሰብ..ዘመድ..ጎደኛ ..ወዳጅ ማንም የለም ...የመንግስት አካላት ጀናዛውን በእሳት አቃጥለው በጉድጓድ ውስጥ ይበትኑታል......በፓኪስታን በኮሮና ቫይረስ ለሚሞቱ ዜጎች እየተደረገ ያለው ግበዓተ መሬት ይኸው ነው......
.....ወላጅ ልጁን.. ልጅ ወላጁን መቅበር ካልቻለ....ባል ሚስቱን...ወዳጅ ወዳጁን...ጎደኛ ጎደኛውን ጀናዛውን በትከሻው ተሸክሞ ካልሸኘ ቀብሩን መፈፀምና እርሙን ማውጣት ካልቻለ.......ከዚህ በላይ ስቃይና ቅጣት ምን ሊኖር ???
አለም በዚህ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት አድሮባታል........እኛ ያለነው የት ነው????
"ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ....ሞኝ ከሆንክ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ"
"ልብ የምንልበት ትምህርት አትንፈገን...እኛን ለሌሎች መማሪያ አታድርገን"
@ONLYFORTRUTHERSJ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አማርኛ ወይም እንግለዘኛ ለምትሉ እጅግ ልብ ሚነካ ቪድዮ 😭
@ONLYFORTRUTHERSJ
♡ስለ ረመዳን የመጨረሻ 10 ቀናቶች
የሚተገበር ምክር:-
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
①☞ በያንዳንዱ የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ውስጥ
አንድ ብር ሰደቃ ስጥ......

-- ስለዚህ ለይለተል ቀድር ላይ ከደረሠች ለ 84
አመታት ያክል ሠደቃ እንደሠጠህ ይቆጠርልሀል።

②☞ በያንድአንዱ ለሊት ሁለት ረክዓ ሰላት ስገድ...

--ለዚህ ለይለተል ቀድር ላይ ከደረሠች እያንድአንዱ ቀን
ለ 84 አመታት ያክል እንደሰገድክ ይቆጠርልሀል።

③☞ በያንዳንዱ ለሊት ሱረቱል ኢኽላስ (ቁል ሁወሏሁ ኣሐድ)
ሶስት ሶስት ጊዜ እንቅራ....

--ሰለዚህ ለይለተል ቀድር ላይ ከደረሰች ለ 84 አመታት
ያክል ሙሉውን ቁራን እንደቀራህ ይቆጠርልሀል።

@ONLYFORTRUTHERSJ
🔖ዱዓችን መቅቡል እንዲሆን (ተቀባይነት) እንዲኖረው ...

▪️ዱዓእ የተከሱት ችግሮችን ያስወግዳል ያልተከሰቱትን ይከላከላል።
ከቀደር ጋር ሰማይ ላይ ትግል ገጥሞ መጥፎ ቀደርን ይመልሳል!

▫️አላህ በአግባቡ ዱዓእ የሚያደርጉ ሰዎችን በሙሉ ዱዓእ ይሰማል።
ስለሆነም ሳንሰላች ለዲን ለዱኒያ የሚበጁ ዱዓዎች አዘውተረን እናድርግ

▪️አሁን ላይ ደግሞ ብዙ ችግሮችን እያስከተለና ሀገራችን ላይም እየተባባሰ ያለውን የኮሮና በሽታ አላህ እንዲያነሳልንም ሁላችንም ትክክለኛ ዱዓእ እናብዛ!
▫️ዱዓእ ተቀባይነት እንዲኖረው መሟላትና መጠበቅ ያለባቸው ዋና ዋና አደብና መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው

1/ ዱዓውን ሲያደርጉ አላህ እንደሚሰማ እርግጠኛ ሆኖና ተማምኖ በኢኽላስና በየቂን ዱዓእ ማድረግ፣
2/ ለአላህ መተናነስና ራስን ዝቅ ማድረግ፣
3/ ልብን መሰብሰና እጅን ወደ ላይ አንስቶ የአይንን እይታም ገታ በማደረግ መማጸን፣
4/ ዘውትር መልካም ስራ መስራትና ወንጀልን መተው፣
5/ ተውበትና ኢስቲግፋር ማድረግ፣
6/ አላህን በመልካም ስምና ባህሪያቱ መማጸን፣
7/ ምግብ፣ መጠጥና ልብስ ባጠቃላይ መገልገያና መተዳደሪያን ሐላል ማድረግ፣
8/ ዱዓእ/ልመናችን ውስጥ ወንጀል/ አላህ የሚጠላውን ነገር መጠየቅና ዝምድና መቁረጥን አለማካተት፣
9/ የዱዓችን ጅምርና መዝጊያ ላይ አላህን ማወደስና ነቢዩﷺላይ ሰለዋት ማውረድ፣
10/ ተስፋ ሳይቆርጡና ሳይቸኩሉ በትእግስት ደጋግሞ ዱዓእ ማድረግ ናቸው።

▪️የሚጠቅም እውቀት፣ የሚጠግብ አንጀት፣ የስራ ተቀባይነት፣ የዱዓእ ሙስተጃብነት፣ ሙሉ ጤንነት አላህ ይስጠን "ኣሚን"

✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ
ረመዷን 18/1441
@ONLYFORTRUTHERSJ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሶሀቦች እና የሰለፎች ምንገድ
@ONLYFORTRUTHERSJ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/29 20:32:14
Back to Top
HTML Embed Code: