Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ሞልቶ የገነፈለው “የሞጣውን ጥቃት አስመልክቶ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ይመልከቱ። ለሌሎችም
ሼር በማድረግ ያስተላልፉ።

https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
………………………………………
ህመም ቢሰማሽ ብታጪ አፊያ
ያረቢ በያ
ዘመድ ወዳጅ ፊት ቢነሳሽ
እሱ አይረሳሽ
ጭንቀት ከቶ ቢበዛብሽ
ወደሱ አልቅሺ
ቢቸግርሽ ምንም ባትደምቂ
ጀሊሉን ጠይቂ
የሚያስጠጋሽ ብታጪ ጉያ
ያአላህ በያ
ባይልልሽ ዘርም ባተኪ
በርሱ ተመኪ

ጌታዬ ሰሚ ነው አላህ ነውና ባለብዙ መላ*2
ጀሊሊ ሁሉን ያይላ አላህ አትከጅይ ከሱማ ሌላ*2

ሙነሺድ ኢድሪስ ሸርሞሎ(ያረቢ አማን)

JOIN
@MuneshidEdris
Forwarded from Yasmina
Aselamuwaleykim 🙏
Bismillah ....Hello friends 🙌 secret of success😳
It's not something difficult to be successful in life . If a person do have dream in life even if it's something simple 🤦‍♀ to accomplish it and then if that person have done well he is said to be "successful" 👍 because he has done the thing that he dreamed for in life . And a person who is successful do have a goal ,mission and tools to fight to reach his or her aim these people's doesn't have nothing uniqe they have 24 hours as the rest of the peoples it's because they struggle a lot to make their dream true nothing more . Before centuries companions of prophet Mohammed (s.a.w) were successful of guiding us from the life of darkness to life of light because of this things 1. they get rida (permission) of Allah for their works .
2. they struggle a lot
But now a days we are not having both so , we are getting back to the life of jahiliya ( darkness )😔 we all have to wake up and work hard to be successful Muslim and Muslimah and spread "Tewhid " all over the world and as such we could easily get rida Allah for our "good "works ...Yasmina 🤗
Join 👇👇👇👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERSJ
👆👆👆👆👆👆👆👆
እሰልምልሻለሁ
(ክፍል አንድ)
፨፨፨
በወላጅ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ አደገች፡፡ ያዉም በምቾትና በድሎት፡፡ የምትፈልገው ሁሉ እየተሟላላት፡፡ ቅርበቷ ይበልጥ ለአባቷ ነው፡፡ ሲበዛ ትወደዋለች፡፡ አምርሮ ይወዳታልም፡፡ ይሳሳላታል፡፡ ዘወትርም ይመክራታል፡ ትምህርቷ ላይ እንድታተኩር፣ ከዓላማዋ እንዳትዘናጋ፣ ጥሩ ጓደኞች እንዲኖራት፣ በኢማኗ እንድትጠነክር፣ በሶላቷ እንድትበረታ … የሁልጊዜ ምክሩ ነው፡፡

፨፨፨
አደገች፣ በአካልም በዕድሜም ጠነከረች፡፡ 18ኛ ዓመቷን ያዘች፡፡ 11ኛ ክፍል ደረሠች፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን “ይህቺን ልጅ አንድ በላት ስለሷ እየሰማሁት ያለው ነገር ጥሩ አይደለም፡፡” ትላለች እናት፡፡
“ምንድነው እሱ? ምንድነው የምታወሪው?” ይላታል አባት፡፡ አያምናትም፣ ያጣጥልባታል፡፡ ይጨቃጨቃሉ፡፡
አባት ልጁን በእጅጉ ያምናታል፡፡ ትልቅ ደረጃ እንደምትደርስም ያስባል፡፡ “በልጄ እተማመናለሁ፣ መቼም አታሳፍረኝም” ይላል፡፡ አቅርቦም ያወራታል፡፡
፨፨፨
እናት ወሬው ሲበዛባት ልጇን አስቀምጣ ጠየቀቻት፡፡ “የሆነ ነገርማ ጀምረሻል” አለቻት፡፡ ልጅት ዐይኗን በጨው አጠበች፡፡ ሽምጥጥ አድርጋ ካደች፡፡
ወሬው አልተቋረጠም፡፡ እናትም እረፍት አጣች፡፡ ለባለቤቷ በተደጋጋሚ አሳሰበች፡፡
እሱም ልጁን ጠራት፡፡ ስለሚወራው ነገር እውነት ዉሸትነት እንድትነግረው ብሎ በፍቅር ጠየቃት፡፡ በማባበልም ለመናት፡፡ ፈጽሞ አላደርገዉም፤ የኔ ሥራ አይደለም አለች፡፡ እሱም የበለጠ ተማመነባት፡፡ ከበፊቱ ይበልጥ አመናት፡፡ ደስም አለው፡፡ ልጄማ እንደዚህ አታደርግም አለ፡፡ ተባብረው እናትን አሳጧት፡፡ ኩም አደረጓት፡፡ የመንደር ወሬ ይዘሽ እየሮጥሽ የልጄን ሥም አታጥፊ አላት -ለሚስቱ፡፡ መደባደብ ነበር የቀራቸው፡፡
፨፨
ቀን አልፎ ቀን ተተካ፡፡ እውነት ተደብቃ አልቀረችም፡፡ እንደ እርግዝና ሁሉ በጊዜ ሂደት እየወጣችና እያፈጠጠች መጣች፡፡ ከሆነ ልጅ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ታወቀ፡፡ ጉዳዩ ሲታወቅ አመነች፡፡ አባት አፈረ፡፡ እናት ድሮም ብዬ ነበር አንተ አትሰማኝም፣ ትንቀኛለህ … ብላ ተቆጣች፣ ባሏ ላይ ጮኸች፡፡ በአጭሩ ማስቆም ሲቻል ያንተ ቸልተኝነት ነው ለዚህ ሁሉ የዳረገን አለች፡፡
ልጅቷን መከሯት፡፡ ግንኙነቱን እንድታቆምም ጠየቋት፡፡ እንደማትችል መለሰች፡፡ ጭራሽ እንዲድሯት አፍ አውጥታ ጠየቀች፡፡ “ወደጄዋለሁ፤ በቃ አልችልም፤ አሁኑኑ ኒካሕ ካላሠራችሁልኝ!” አለች፡፡

ቢቆጧት፣ ቢመክሯት አልሰማ አለች፡፡ ልጅነት፣ ወጣትነት፣ ፍቅር፣ ስሜት …. ተደማምረው ጋረዷት፡፡
የልጁ ማንነት ተጠና፡፡ ሙስሊም አይደለም፡፡ ቤተሰቦቹም አይደሉም፡፡ ሙስሊም ዘመዶችም የለዉም፡፡ ግና “እሰልምልሻለሁ” ብሏታል፡፡ ላይለያዩ፣ ላይከዳዱ ቃልኪዳን ተገባብተዋል፡፡
፨፨
ወላጆች በመጨረሻም ተሸነፉ፡፡ የልጃቸዉን ሀሳብ ተቀበሉ፡፡ ልጁ የወላጆቹን ሰፈር ቀይሮ ሌላ አካባቢ ተከራየ፡፡ የመስጊድ ሰዎች ዘንድ ቀርቦም በይፋ ሰለመ፡፡ እዚያው መስጊድ አካባቢው ኑሮዉን አደረገ፡፡ በሶላቱ በረታ፡፡ በመስጊድ ሰዎችም ታወቀ፡፡ ከጀማዓው ወጣቶች ጋር ተቀራረበ፡፡
፨፨
ከወራት በኋላ ሽማግሌ ላከ፡፡ ኒካሕ እሠሩልኝ አለ፡፡ ልጅትም ሀሳቡን ደገፈች፡፡ ወላጅ ግን ቀስ በይ አላት፡፡ ቢያንስ ዓመት ሁለት ዓመት እናጥናው፤ እስቲ በእስልምናውም ላይ በደንብ ይርጋ ያጣጥም አሏት፡፡
፨፨፨
ተጨማሪ ጥቂት ወራት አለፉ፡፡ ልጅት አሁንም ኒካሕ ካልታሠረልኝ ብላ አመፀች፡፡ ሐራም ላይ ብወድቅ ኃላፊነቱ የናንተ ነው ብላ አሳሰበች፡፡ አልተቀበሏትም፡፡ ችላ አሏት፡፡ የልጅ ነገር ይኸው ነው ብለው ናቋት፣ ተቆጧት፡፡ እሷ ግን ልቧ ሸፈተ፡፡
፨፨፨

ግና አንድ ቀን ያልታሰበውና ያልተጠበቀው ሆነ፡፡ ከቤት ወጥታ ኮበለለች፡፡ ልጁን ብላ እነርሱን ትታ ጠፋች፡፡ ፍቅር ብላ ወደ አፍቃሪዋ ተጠጋች፡፡ እናት አለቀሠች፡፡ አባት የሆነዉን ማመን አቃተው፡፡ እነርሱን ፈርታ ከዐይናቸው ራቀች፡፡ ከአንድ ሁለት ወር በኋላ ፈልገው አገኟት፡፡ ልጃቸው መጎዳቷን አዩ፡፡ መጨከን አቃታቸው፡፡ አሳዘነቻቸው፡፡ የወላድ አንጀት ሆነባቸው፡፡ እርቅ እና ሽምግልናውን ተቀበሉ፡፡
፨፨
ልጁ ወሊይ እና ዋስ አምጣ ተባለ፡፡ ሴት ልጅ ተራ ዕቃ አይደለችም፤ ዝምብለው አንስተው ወላጅ ዘመዱ ለማይታወቅ ሰው የሚያስረክቧት ርካሽ ነገርም አይደለችም፡፡ ሴት ልጅ ዉድ ናት፡፡
ልጁ መለሰ - አባቴ በሕይወት የለም አለ፡፡ እናቱም አክራሪ አማኝ እንደሆነችና መስለሙን ከሰማች ራሷን ሁሉ ልታጠፋ እንደምትችል፣ አሊያም ለዘላለሙ ቆርጣ እንደምትጥለው ተናገረ፡፡ ሰፈር መኖሪያቸዉን ጠቆመ፡፡ ግና የትኛውም ዘመዱ መስለሙን እንዲያውቁበት እንደማይፈልግ አስረዳ፡፡ በሂደት እና ቀስ በቀስ እኔ ራሴ እነግራቸዋለሁ አለ፡፡
፨፨፨
ወላጆች ግራ ተጋቡ፡፡ መወሰንም አቃታቸው፡፡ የልጃቸው ነገርም አሳሰባቸው፡፡ እሷ ጫናዋን ጨመረች፡፡ ልጁ ኒካሕ እንዲያስሩለት ብሎ የመስጊድ ሰዎችን ይዞ መጣ፡፡ ከነርሱ መካከል አንዱ ዋስ ሆነ፡፡ ከቤተሰብም ሆነ ዘመድ አንድም አልነበረም፡፡ ኒካሑ ታሰረ፡፡ እሺታም ተበላ፡፡ መጠነኛ ፕሮግራም ተዘጋጀ፡፡

(ይቀጥላል )
እሰልምልሻለሁ
(ክፍል ሁለት )

ምንጭ ፦ የፍቅር በረከት መጽሐፍ
በሙሐመድ ሰዒድ (ABX)

ልጅት ደስ አላት፡፡ ያፈቀረችዉንና አብራው መኖር ያሰበችዉን አገኘች፡፡ ከወላጆቿም ታረቀች፡፡ ምክርና ምርቃት ተቀብላ በክብር ወጣች፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የወላጅ ደስታ ግማሽ ነበር፡፡ የልጃቸው ዕጣፈንታ አሳስቧቸዋል፡፡ ጎናቸው በሀሳብ አላርፍ ብሏል፡፡ ወዲህም ቢሆን ክብራቸው የተሟላ አልነበረም፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ ለልጃቸው ሲያስቡላት የኖሩትና አሁን የሆነው ነገር አልገጠመላቸዉም፡፡ ቁጭት ቢኖርም የአላህን መሻት ወደው ተቀበሉ።
፨፨፨


ሙሽሪት ጠቅላ ከባሏ ጋር ሄደች፡፡ ወደተከራዩት ቤት ገባች፡፡ እገዛም ተደረገላቸው፡፡ አንድ ላይ መኖር ጀመሩ፡፡ ወራት አለፉ፡፡ እሷም አረገዘች፡፡ ግና ድንገት የሆነ ቀን ግን ያልታሰበው ሆነ፡፡ ባል ከቤት እንደወጣ ቀረ፡፡ አልተመለሰም፡፡ የት እንደገባም አልታወቀም፡፡

፨፨፨
ልጅት በሆነው ነገር ደነገጠች፡፡ የተፈጠረዉን ማመን አቃታት፡፡ ወላጆቿን ስንቴ እንደበደለች አሰበች፡፡ ግራ ገባት፡፡ መሄጃ ጠፋት፡፡ ብቻዋን ብትሆን ብን ብንን ብላ በጠፋች ነበር፡፡ ሁለት ራስ ሆና ግን እንዴት ትሁን!፡፡

አሁንም ወላጅ ጥሎ አልጣላትም። ከነችግሯ ደረሰላት፡፡ እኛው አለንልሽ አሏት፡፡ ወደቤታቸው መለሷት፡፡ ልጅት በሆዷ የተሸከመችዉን ይዛ ተመልሳ ወደልጅነት ቤቷ ገባች፡፡
፨፨፨

በአካባቢው ትልቅ ክብር በሚሠጠው ወላጇ ቤት ሌላ እፍረት መጣ፡፡ ጎረቤት ጉድ ጉድ! አለ፡፡ ባዳ አንሾካሾከ፡፡ ሀሜተኞች ጮማ ወሬ አግኝተው ፈነጠዙ፡፡ ሓሲዶች በወላጆቿ ክብር ሳቁ፣ ተሳለቁ፡፡ በርግጥም ጉዳዩ ለሌሎች ለመንገርም ለማስረዳትም ከባድ ነበር፡፡

እና

ወዳጆቼ! እስልምና ጋብቻ ይፋ እንዲሆን ያዛል፡፡ የቤተሰብ ትዉዉቅንም ያበረታታል፡፡ ከሁለቱም ወገን በኩል ወኪል ይኖር ዘንድ መስፈርት ያደርጋል፡፡ የባል ወኪል/ዋስ የሆነ ሰው ባል ድንገት ቢጠፋ ፈልጎ ያቀርባል፡፡ የሚታወቅ የባል ቤተሰብ፤ ባል በሌለበት ሁኔታ ሚስት ብትቸገር ሚስትን ያረጋጋል፣ ያግዛል፣ ልጆችን ይንከባከባል፡፡
የሚስት ወኪል ደግሞ ለምትዳረው ልጅ ጠበቃ ነው፡፡ እንዳትስት፣ እንዳትሳሳት፣ እንዳትታለል፣ የተሻለዉን ነገር እንድትመርጥ ያግዛታል፡፡ የሚጠቅም የሚጎዳትን ይጠቁማታል፡፡ ልጅን ያማክራታል፡፡

እና

ሴት ልጅን ለማይታወቅ ሰው መዳር ጣጣው ብዙ ነው፡፡ በተለይ ትዳር ዉስጥ ስምምነት ከጠፋ ዕዳው መዓት ነው፡፡
**

ወጣት ሴቶች በትዳር ጉዳይ ቤተሰብ የሚላችሁን ሥሙ፡፡ እነርሱ ትልቅ የሕይወት ልምድ ዉስጥ ያለፉ በመሆናቸው ነገሮችን በትክክል ይረዳሉ፡፡ ሁኔታዎች በሚገባ ያስተዉላሉ፣ ጉዳዮችን በጥልቀት አርቀው ያያሉ፤ በትክክል ይገነዘባሉ፡፡ ሲበዛ ያስተውላሉ፡፡ የሚጠቅማችሁን እንጂ የሚጎዳችሁን አያደርጉም፡፡ ወላጆች መስፈርት የሚያበዙት፣ የባልን ወገን ምንነት አጥብቀው የሚያጠያይቁት፣ ለማጨናነቅና ለማካበድ አይደለም፡፡ ለልጃቸው ዋስትና ያለው ዘላቂ ትዳር አስበው ነው፡፡
እነርሱ ለኛ የማይታየን ብዙ ነገሮችን ያያሉ፤ ከብዙ አቅጣጫም ይመለከታሉ፡፡

በብዙ ጉዳዮች ላይ ወላጆቻችን በርግጥም በኛ ጉዳይ ትክክል መሆናቸዉን የምናውቀው እኛም ወላጅ የሆንን ጊዜ ነው፡፡ እስከዚያው ግን አይመስለንም አይዋጥልንም፡፡ የፍቅር መቀስ የሆኑም ይመስለናል።
ወላጆቻችንን የምንወድ፣ ክብራቸው የሚያስጨንቀን ከሆነ ትዕዛዛቸዉን እናክብር፤ አስተያየታቸዉን እንቀበል፣ ሀሳባቸዉን እናዳምጥ፡፡

፨፨፨፨ ሌላው ...
አንድ ሰው ቢሰልም ለራሱ ጉዳይ ነው፡፡ ለራሱ ጥቅም እንጂ ለማንም አይደለም፡፡ መስለም የሚፈልግ ሰው ለሰው ሳይሆን ዲኑን መርምሮ፣ እውነቱን ተረድቶ ሐቁን ተቀብሎ መሆን አለበት፡፡ አላህን አምኖ፣ እስልምናን ወዶ ወደ እምነቱ የገባ ሰው መቼም ቢሆን እስልምናን አይለቅም፡፡ ሰዉን ብሎ፣ ዉበትን ፈልጎ፣ ገንዘብ ተመኝቶ፣ በቁንጅና ተስቦ እስልምናን የተቀበለ ግን ያሰቤነገር የተቀየረ ቀን ይቀየራል፣ ዉበት የረገፈ ቀን ይመለሳል፣ ቁንጅና የጠፋ ቀን ሀሳቡን ያነሳል፡፡

፨፨፨
“እሰልምልሻለሁ" አለኝ” ብሎ መጃጃል ተገቢ አይደለም፡፡ የሚሰልም ወንድ ላንች ሳይሆን ለራሱ ለዱንያ አኺራው ጥቅም ሲል ነው መስለም ያለበት፡፡ የምትሰልም ሴትም እንዲሁ። ካልሆነ ካንች ካንተ የተጣላ ቀን ወደ ኩፍሩ ይመለሳል፡፡ ከዓለማዊ ጥቅም ጋር የተያያዘ ነገር እንዲሁ ነው፡፡ ለፍቅር የሰለመ፣ ለቁንጅና የሰለመ፣ ለገንዘብ የሰለመ፣ ፍቅር ሲያልቅ አብሮት ያልቃል፡፡ ገንዘብ ሲጠፋ አብሮት ይጠፋል።
ዘመኑ የጥቅም ዘመን እንደሆነ ብዙዎቻችን አስተዉለን ይሆን?!
💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜
፨፨፨፨፨፨፨፨
ምንጭ - የፍቅር በረከት መጽሐፍ
በሙሐመድ ሰዒድ
ያልሰማ ካለ plz ለህይወትህ ስትል ስማ
ትናንት በናሽናል ጂኦግራፊ ዋይልድ ቻናል ላይ
የተላለፈው ዜና አስደንጋጭ ነበር😟
, ማለትም ሳይንቲስቶች እንደገለፁት ከሆነ በጣም
አደገኛ እባብ 🐍ተገኝቷል ሳይንቲስቶቹ እንደተናገሩት
እባቡ ምግብ በበላ ቁጥር 0.5ሴ.ሜ ያድጋል
ምግቡን ደግሞ የሚበላው ቢበዛ በ 30 ሰከንድ
ውስጥ ነው ታዲያ ይህን እባብ በምንም አይነት
ሰው ሰራሽ መሳሪያ መግደል አለመቻሉ ነው ነገሩን
አስፈሪ ያደረገው ሊሞት የሚችለው እራሱን
በራሱ ከነከሰ ብቻ ነው ነገር ግን ሳይንቲስቶች
ሌላ የሚገድለውን ነገር እየፈለጉ ነው ይህ እባብ
በሰዉ ልጆች ታሪክ ከተመዘገቡ ገዳይ በጣም
አደገኛና መርዛማ ከሆኑ እባቦች ሁሉ ዋናው ነው😳
ታዲያ ይህ እባብ አንድ ቦታ ብቻ ነው የሚገኘው
እሱም








ኖኪያ 3310 የስልክ ቀፎ ላይ የጌም ምርጫ
ውስጥ snake xenzia. ላይ ነው ፡፡
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
በትእግስትና በጥሞና ስላነበባችሁት
አመሰግናለዉ እወዳቹሀለው😍😍😘
ፈገግታ ሱና ነል😘
✳️ሼር መደረግ እንዳይረሳ❇️
👍👍👍👍👍👍😂😂

@ONLYFORTRUTHERSJ
👆👆👆👆
❤️ አፈቅርሃለሁ!! ❤️

ይህን ስትሰማ እንደምትደነግጥ አውቃለሁ፤ ግን አንተ ለኔ ብዙ ትርጉም አለህ፡፡ ሁሌም ወደ አንተ ልቀርብ እጥራለሁ ነገር ግን ያንተ ልብ ወደ ሌላ የሸፈተ ይመስለኛል፡፡

🔰ሀሳቤን ላንተ በሰጠሁ ቁጥር ወዳንተ በተጠጋሁ ቁጥር አንተ ግን ስለሌላ ታስባለህ፡፡ ጠርቼህ ምላሽ ሳላገኝ ስቀር ልቤ ይታመማል፡፡ ሁሉ ነገሬን ላንተ ልሰጥ እሞክራለሁ አንተ ግን ዝግጁ የሆንክ አይመስለኝም፡፡

🔰እባክህን እንዳፈቅርህ ፍቀድልኝ እኔኮ #ቁርዐን ነኝ፡፡ ለሌሎችም Share
በማድረግ ንገራቸው ሁሌም እንደምወዳቸውና እንደማፈቅራቸው ለምታወጣው ጊዜና ገንዘብ እኔ ተጠያቂ እሆናለሁ፡፡”
በየቀኑ ከጓደኛችን የተላከልንን የፅሁፍ መልዕክት በጉጉት እናነባለን፤ ግን እልቅናው ከፍ ያለው ጌታችን አላህ የላከውን ደብዳቤምን ያህል ከፍተን እያነበብን ነው??

👹የሸይጣን ወዳጅ ይህንን መልዕክት Share ሊያደርገው ይቅርና ማንበብ
እንኳ አይፈልግም፡፡ የአላህ ወዳጆች ግን ለሌሎች share ያደርጉታል፡፡

share 👆👆👆👆👆

@Anu_official
ሰሞኑን #ኮሮና_ቫይረስ በመባል የሚታወቅ በዓለማችን እየተሰራጨ በዋናነት ደሞ በቻይና ሐገር የወጣውን በሽታ ምክንያት በአላህ እገዛ እንድንጠበቅ ዘንድ ይህንን ዱዓእ እንድናዘወትር ዶ/ር ሼይኽ #ከማል_አል_ሁት ነግረውናል ዱዓኡም ይኼ ነው።
عن د. كمال الحوت
مع انتشار ما بسمى بالفيروسات والانفلونزا ردد بكل ثقة وتوكل على الله هذا الدعاﺀ:
..((تحصنت بذي العزة والجبروت واعتصمت برب الملكوت وتوكلت على الحي الذي لايموت
اللهم اصرف عنا الوباء
وقنا شر الداء بلطفك
ورحمتك إنك على كل شئ قدير)) ..
علمه لغيرك
አላህ ይጠብቀን ሐገራችን ሐበሻንም አላህ ይጠብቃት አሚን

#ሼር #ሼር ይደረግ
@Taha_islamic_Channal
.......#10ቱምርጥ__አባባሎች.......

ፈጣሪ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን አይፈታውም ፈጣሪ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም ፈጣሪ ካልገለጸ እውቀት ጥበብ አይሆንም

ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡፡ ዛሬ ብታገኝ ነገ ታጣለህ ዛሬ ብታሸንፍ ነገ ትሸነፋለህ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባል መዶሻ አለ፡፡ መልካምነት ዋጋ ያስከፍልሃልና ሁሌም ፍጹም መልካም ሰው ሁን

ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡

የአንተነትህ ትልቁ ምዕራፍ ከእውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡

ንጹህ ልብ ልክ እንደ አበባ ናት! ፍሬ ባናገኝባትም ውበቷ ግን እጅግ ማራኪ ነው፡፡

የውድቀት መጀመሪያ ራስህን አዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው
ፍጻሜህ እንዲያምር ራስህን አታመጻድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን ጥፈፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ፡፡

ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል ይመለሳልና፡፡

በህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት

እውነትነ የሚናገር ሰው አፉ ክፉ ይመስላል ልቡ ግን ንጹህ ነው

ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ለመርዳት ወደሗላ አትበል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰው ሆይ👌👌

👉ዛሬ ላይ ምንም ቆንጆ ብትሆን ነገ ልክ ቀብር ስገባ አስቀያሚ ነህ፤
👉ዛሬ ላይ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ ትባላለህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም ሃብታም ብትሆን ነገ ግን 1ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም እንኩዋን በቤተሰብ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን ትቀራለክ፤
👉ዛሬ ላይ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፤
👉ዛሬ ምንም በዘርና በጎሳ ብትመካ ነገ አንተ ብቸኛ ነህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም ሁን ምን ነገ አንተ ሬሳ ነህ ሬሳ።
👉ዛሬ ብትናፈቅ ነገ እንዳትሸታቸው ሰዋች ቶሎ ይጥሉካል ፤
ስለዚህ ዛሬ ላይ ለዘለአለም ህይወት የሚጠቅመንን ስራ ብንሰራ መልካም ነው።
ወደ አሏህ እንመለስ መንገዱንም እሱ ያቅናል
🌺🌺🌺🌺
አሜን።
@ONLYFORTRUTHERSJ
👇👇👇👇👇👇👇👇

ሰኞ ጥያቄ እና መልስ አለ

ቢስሚላህ ሰኞ ማታ 2 30 ሁለት ተኩል እስከ 4 ሰአት ጥያቄወች ይለቀቃሉ አሸናፉው 1 GB 🙈 ይሸለማል አስሩንም ጥያቄ የመለሰ አሸናፊ ሲሆን ሙሉውን የመለሱ ከ 1 በላይ ካሉ ቀድሞ የመለሰውን እንሸልማለን


የጥያቄ እና የመልሱ ህጎች 💥

1—አንዴ ከላኩ ማስተካከል ጭራሽ አይቻልም ካስተካለ / ካስተካከለች ሙሉው መልሱ ተቀባይነት አይኖረውም በርጋታ መልሱ


2—መልሶቹ ሚመለሱት በአማርኛ በአረበኛ ወይም አማረኛውን በእንግልዝኛ ነው !!

3 — ከመልሳችሁ ጋር አብራችሁ ስማችሁን የ ቴሌግራም ሳይሆን የትክክለኛ ስማችሁን እና አድራሻችሁን ከየት እንደሆናችሁ ትልካላችሁ
መልሶቹ ሚመለሱት በዚ አካውን ነው👇
@Bchegha


5—ቢስሚላህ እንዳትረሱ መልካም እድል 1 ወር ሚቆይ 1 GB እንዳያመልጣችሁ

እስከ ውድድሩ 3’000 ቤተሰብ መግባት አለብን please share share share & share 👍

@ONLYFORTRUTHERSJ
#ልቤን_የነካ_ደብዳቤ!! ልብ ያለው ልብ ይበል።

#አፈቅርሃለሁ!!
.
ያበጠው ይፈንዳ በውስጤ አምቄ የያዝኩትን ልንግርህ ስለሆነ
አንድ ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት እስከ መጨረሻው አንብበው አፈቅርሃለሁ!! በጣም በጣም በጣም አፈቅርሃለሁ። አሁንም ደግሜ ደጋግሜ እነግርሃለሁ ፊት ጀምሬ ነው የማፈቅርህ አሁንም አፈቅርሃለሁ፡፡ ይህን ስትሰማ እንደምትደነግጥ አውቃለሁ፤ ግን
አንተ ለኔ ብዙ ትርጉም አለህ፡፡ ሁሌም ወደ አንተ ልቀርብ እጥራለሁ ነገር ግን ያንተ ልብ
ወደ ሌላ የሸፈተ ይመስለኛል፡፡ሀሳቤን ላንተ በሰጠሁ ቁጥር ወዳንተ በተጠጋሁ ቁጥር አንተ
ግን ስለሌላ ታስባለህ፡፡ ጠርቼህ ምላሽ ሳላገኝ ስቀር ልቤ ይታመማል፡፡ ሁሉ ነገሬን
ላንተ ልሰጥ እሞክራለሁ። አንተ ግን ዝግጁ የሆንክ አይመስለኝም፡፡ እባክህን እንዳፈቅርህ ፍቀድልኝ፤ ፍቅሬን ተቀበለኝ።
እኔኮ ቁርዓን ነኝ! እኔኮ ቁርዐን ነኝ!!እስኪ ዛሬ ስንቴ ገልጠህ አንብበህኛል? ሞባይልህን
ስንቴ አውጥተህ ተጠቅመህበታል? ተው ከሞባይል አታስበልጠኝ እኔ እኮ ነኝ ቀብር
ስትገባ ከነኪርና ከሙንከር ጥያቄዎች የማላቅቅህ በል አሁኑኑ ግለጥና ባማረ ድምፅህ ቅሪኝ… ሁሌም እንደምወዳቸውና እንደማፈቅራቸው
ለምታወጣው ጊዜና ገንዘብ እኔ ተጠያቂ እሆናለሁ፡፡ በየቀኑ ከጓደኛችን የተላከልንን የፅሁፍ መልዕክት በጉጉት እናነባለን ግን
ልእልናው ከፍ ያለው ጌታችን አላህ የላከውን ደብዳቤ ምን ያህል ከፍተን እያነበብን ነው??
የሸይጣን ወዳጅ ይህንን መልዕክት share
ሊያደርገው ይቅርና ማንበብ እንኳ
አይፈልግም፡፡ የአላህ ወዳጆች ግን ለሌሎች share ያደርጉታል፡፡አሁንም እያደረጉት ነው
አይደል? የቁርዓንን ፍቅር አላህ
ይስጠን!! አሚን አሚን

@ONLYFORTRUTHERSJ
Forwarded from አህለ ሱና ወል ጀማዐህ
بسم الله الرحمن الرحيم
አንድ ቀን አንድ ተማሪ ኡስታዙን እንዲህ ብሎ ጠየቀ ተስፋ መቁረጥ ከምንድን ሚመጣው ኡስታዙ እንዲህ አለው ተስፋ መቁረጥ ሚመጣው
ከኢማን ድክመት ነው የኢማን ድክመት ሚመጣው ወንጀልን ከመስራት ነው ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል እምነት አላህን በመታዘዝ ይጨምራል አላህን በማመፅ ደግሞ ይቀንሳል) ሰዎች አላህን ከማስታወስ ሲርቁ ልባቸው ደርቃ ጥሩን ነገር መስራት አይችሉም እንግዲህ የሁሉም ምክንያቱ አላህን ከአለማስታወስ ነው አንተም ከእነዚህ ሰዎች ላለመሆን አላህ በቀንም በሌሊት አውሳ ረሱል ሰ.ዐ.ወ በሁሉም ሰአት አላህን ያወሱ ነበር ብሎ መለሰት
Alhamdulilah#Semu



🌿❤️ እዉነተኛ ጓደኛ ማለት🌿🌿

እሱ ጋር መሆን ስታበዛ የሚትሰችዉ፣

🌿❤️❤️ ስትለየዉ የማይረሳህ፣

🌿❤️ ስትቀርበዉ የሚቀርብህ፣

🌿❤️ስትርቀዉ ከአንተ ላለመለየት
የሚጥር፣

🌿❤️❤️ላንተ ያለዉ ዉዴታ ከቃላት ይልቅ በተግባር የሚገልፅልህ ነው።
ሚስጥርህን ሚስጥሩ አድርጎ የመጠብቅ

🌿❤️ጓደኛ ማለት ሁሌም በልብ ዉስጥ የሚኖር እንጂ
አዲስ ሰዉ ባገኘህ ቁጥር የምትለዉጠዉ አይደለም

🌿❤️ ሁሌ በደስታህ ሰአት አብሮህ የሚሆን ሳይሆን
በችግርህ ሰአት ከጎንህ የሚቆም ነዉ።

🌿❤️በደስታህ ጊዜ አብሮህ የሚዘል ሳይሆን በችግርህ ደራሽ ነዉ ጓደኛ።

🌿❤️እዉነተኛ ጓደኛ ማለት፡-ሁል ጊዜ በምላሱ አንተን የሚሸነግል ሳይሆን ሁል ጊዜ መልካምነቱን፣ደግነቱ፣ታማኝነቱን ና እነዲሁም ፍቅሩን በተግባር የሚያሳይ ነዉ...!!!

🌿❤️ እዉነተኛ ጓደኛ የበረሃ ጥላ ነዉ።

@ONLYFORTRUTHERSJ
2024/10/01 13:37:10
Back to Top
HTML Embed Code: