Telegram Web Link
👇👇👇👇👇👇👇👇
📝 "ሀዋን ማን ገደላት"

( አብዲ ኢክላስ)

ክፍል አንድ (1)

ለወትሮ ሳቅ እና ጨዋታ የማይለያት ፍንድቅድቋና ውድ እናት የነበረችው ሀዋ ዛሬ ባልተለመደ መልኩ ፊቷ ጭልም ስሜቷም ራድ ሰውነቷም ቅዝቅዝ ብሏል። ይህ ሁኔታ በጣም ያስፈራቸው እጅግ የሚወዷትና የሚሳሱላት ሁለት ትናንሽ ልጆቿ ኻሊድ እና ሱመያ ስልምልም ባለ ምልከታ በፍርሀት እና ግራ በመጋባት ስሜት ደጋግመው ይመለከቷታል። ነገር ግን ሀዋ የነሱ ሁኔታ ግርም ያላት አትመስልም ብቻ የራሷ ስሜት ውስጥ ሆና ግራ በገባው መንፈስ አንዴ እላይ አንዴ እታች ትማትራለች።

ልቧ በሀይል እየመታ እንደሆነ የገባት ሀዋ ዛሬ ከሌላው ቀን ምን የተለየ ነገር እንደተፈጠረ ምንም ሊገባት አልቻለም። ብቻ ልጆቿም እሷን አየተመለከቱ እንደሆነ ስለገባት አንዴ ወደነሱ ዞር ብላ <<አዳበ ነውም ሰርታችኋል>> ወደመኝታ ሲገባ የሚደረገውን ዱዐ ማለቷ ነው። ልጆቹም አዳበ ነውም መስራታቸውን በአዎንታ ግንባራቸውን ነቅንቀው አሳዩዋት። በርግጥ ኻሊድ እና ሱመያ አዳበ ነውም ሳይሰሩ እንደማይተኙ ታውቃለች ግን ምትናገረው ስለጠፋት ይህቺን ተነፈሰች።

ሀዋ ሁኔታዋ በጣም ግራ ስለገባት ለራሷ እንኳን እንቆቅልሽ ስለሆነባት ልጆቿ ፊት እንዲ መሆን እንደሌለባት ስትረዳ ገብተው እንዲተኙ አዘዘቻቸው። ነገር ግን ኻሊድም ሆነ ሱመያ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው እሷም እነሱም በደንብ አሳምረው አውቀዋል። ከዛም አልፎ ውስጣቸው የተፈጠረውን ጥያቄ ቢጠይታቋት ባለችበት ስሜት በመጥፎ ሁኔታ እንደምታመናጭቃቸው አልያም እነሱ ስሜቷን እንደተረዱ በማወቋ ይበልጥ እንደምትፈራ ስለተረዱ ይመስል ብቻ ዝም ብለዋት ተያይዘው ወደየ ክፍላቸው ገቡ። ነገር ግን ሱመያ ምንአልባት ልጅነት ስላለባት ቶሎ እንቅልፍ ወሰዳት። ኻሊድ ግን አይኑ እንደፈጠጠ ግራ እንደገባው ጆሮውን ወደ በር ለጥፎ የናቱን እንቅስቃሴ አንድ በአንድ መከታተሉን ያዘ።

ሀዋ በጣም ግራ ተጋብታለች ውስጧ በጣም ፈርቷል ምን እንደተፈጠረ ዛሬ ምን እንደነካት በቅጡ አልገባትም። ብቻ ልቧ በፍርሀት ርዶባታል ነገር ግን ዛሬ እንቅልፍ ካልወሰዳትና ካልተኛች ከዚህ ስሜት እንደማትወጣ ስለገባት ወደ እንቅልፏ ስታመራ ሁል ግዜ ለስለስ ባሉ አማርኛዎች እጅግ ውብ በሆኑ ቃላት እያፅናና እያለሰለሰ የሚያስተኛትን የልጆቿ አባት ክፍለ ሀገር ለፊልድ ስራ እላይ እታች የሚማትረውን የምንግዜም ጀግናዋን የቁርጥ ቀን ወንድ ብቸኛ የሷ ልዩ ሰው ሰሚር ዛሬ በስልክ ደወላ እሱን ማውራት እንዳለባት አመነች። እሱን ማናገር እንደምትችል ትዝ ሲላት በደስታ እየተፍለቀለቀች ስልኳን አውጥታ ቁጥር መታች ነገር ግን ህይወት እኛ እንደ ምንፈልገው ቢሆን ኖሮ ምንኛ ባማረ ምንኛ ጣፋጭ በሆነ ነበር የሰሚር ስልክ ጥሪ አይቀበልም። ይበልጥ ግራ ገባት ውስጧ ፈራ በአንድ በኩል በሷ መጨነቅ አብሯት በሰቀቀን ውስጥ ያለው ኻሊድ ድምፁን ጮክ አድርጎ ቁርዐን ቢቀራ እንደ ሌላ ግዜ ደስ እንደሚላት ዛሬ ግን እንደማይሆን አምኗል ምክንያቱም ኻሊድ ለሷ ቁርዐን የሚቀራላት ሰኞ እና ሀሙስ ድምፁን ከፍ አርጎ ነውና ዛሬ ቀኑ ረቡዕ ነው። በዛሬ ቀን ይሄን ቢያረግ ይበልጥ እንደ ሚያስጨንቃት ስለ ገባው ድምፁን ቀንሶ የሚወደውን የቁርዐን ሱራ ለመቅራት ወሰነ። ያሲን...

ሀዋ በሌላ በኩል ጥቅልል ብላ ብትተኛ እንቅልፍ ለመውሰድ ብትሞክር ነገሩን እንደምትረሳው ስለገባት ይሄን ለማድራግ የመጨረሻ ስራዋ የግቢውን በር ለመቆለፍ ድንገት ብድግ አለች። የግቢውን በር ቆልፋ መተኛት እንደምትችል ውስጧ ስላመነ ገና ከመነሳቷ አስፈሪው ነገር ጀመረ። ድንገት መብራት ሄደ በዚህ ግዜ ሳታስበው ጮህች ከዚያም ደንግጣ አፏን ያዘች። ዋይይ.... ብላ መጮኋ ሲገባት ወደ ልጆቿ መኝታ ቤት ተመልክታ አለመስማታቸውን አረጋገጠች። ከዚያም የስልኳን መብራት አብርታ ወደውጪ ለመውጣት ስትሞክር ከፍተኛ ዶፍ ዝናብ መብረቅ ቀላቅሎ በአንዴ ዧ..ማለት ጀመረ። ይሄን ስትመለከት ነገሮች እየፈተኗት እንደሆነ ስለገባት የግቢውን በር ዛሬ ሳትቆልፍ ማደር እንደሌለባት አምናለችና ድንገት የመኖሪያ ቤቱን በር ስትከፍተው ከፊት ለፊቷ አንድ ነገር ድቅን አለ ሀዋ ሳታስበው ራሷን ስታ ወደቀች።

ከፊት ለፊቷ ምን ተደቅኖ ይሁን?.... ዛሬ ሀዋ ምን ነክቷት ይሁን?....

ይቀጥላል.......
@ONLYFORTRUTHERSJ
Audio
ሀዋን ማን ገደላት ክፍል 1 👆👆
´ 🌟❤️🌟
” የሚያካፍሉት ትንሽ እውቀት ከማያካፍሉት ብዙ እውቀት በእጅጉ ይበልጣል።” ዶ/ር ሙስጦፋ ሰባዒ

❤️🌟❤️
” ከእሳት መራቅና እና ጀነት መግባት የፈለግ፤ በአላህና በመጭው ዓለም ያመነና ሰዎች እንዲያደርጉለት የሚሻውን ነገር እርሱም ለእነርሱ የሚያደርግ ሆኖ ሞት ታግኘው።” ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)


@islamik_channal🌟
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Subhanellah 😭😭😭
The Dua of the oppressed slaves 😳are acceptable even if they are disbelievers🙊.
@ONLYFORTRUTHERSJ
Forwarded from R𝖊𝖆𝖑 :)
ማስጠንቀቂያ

#የአይን_ብሌናችንን_እንዳናጣ_ጥንቃቄ

የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽን በተመለከተ የቀረበ መረጃ፡፡

🌑የ2012 ዓ.ም ግርዶሽ የሚታየው፡-

- ሰኔ እሁድ 14/2012 ዓ.ም ነው፣
- በግርዶሹ 6፡00 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል፡፡
- በመላ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡
- በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
- የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

- ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል፡፡
- ፀሐይ 98% ትሸፈናለች፡፡

🌑የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡-

- ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡


🌑ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት

- ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012 ዓ.መ
- 11፡00 ሰዓት ይጀምራል፣
- ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33


‼️ማስጠንቀቂያ፡-

- በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣
- በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡
- ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡
- መነጽሩ አገር ውሰጥ አይገኝም፡፡
-ለፀሀይ ግርዶሽ የሚሆን መነፀር አለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ
- ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣በጣም ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል
- ዐይናችን ሊፈስ ይችላል፣


አብዛኛው ኢትዮጽያዊ መረጃው ስሌለው እና የፀሀይ ግርዶሽ የሚታይበት ቀን ስለደረሰ ቢያንስ ለ ሚወዷቸው 10ሰወች ሼር በማድረግ መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ የበኩልውን ይወጡ

🎖ዶ/ር ሊያ ታደሰ

@Dr_Lia_Taddese
@Dr_Lia_Taddese
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቁ ይሆን ?
#ረዥሙ የካዕባ መክፈቻ ሲሆን
#የመሃሉ የመቃም ኢብራሂም መክፈቻ ናቸው።

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈

ቻናሉን ሼር በማድረግ #ከበጎ ስራው ተቋዳሽ ይሁኑ።
( مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ ) صحيح مسلم برقم/ 5007

•┈┈•◈◉#ቻናላችን 👇👍 ◉◈•┈┈•

https://www.tg-me.com/islamik_channal🌿
"ሀዋን ማን ገደላት"
( አብዲ ኢክላስ)

ክፍል ሁለት (2)

ሀዋ ከፍተኛ የይድረሱልኝ ሲቃ እና ጥሪ ብታሰማም ሀሊድ እና ሱመያ ድንገት ሳያስቡት እንቅልፍ ወስዷቸዋልና የሚደርስላት ሳታገኝ በሲቃ ታፍና ረጅም ሰአታትን ቆየች። ነገር ግን ምን እንደተፈጠረ ሳይታወቅ ምሽቱ ነግቶ ጨለማው ለፀሀይ ቦታ ለቀቀ። ጠዋት ሀሊድ ከተኛበት ቦታ ሲነሳ ቁርዐኑን እየቀራ ባለበት አንገቱን ወደ ቀኝ ሰብሮ ሳያስበው እንቅልፍ ሸለብ አርጎት በዛው ነውና የተኛው አንገቱን በጣም አሞት ነቃ። ልክ እንደነቃ የተኛበትን ሁኔታ ሲመለከት ማታ የነበረውን ሁሉ አስታወሰ ወድያው እናቱን ለመፈለግ ወደሳሎን እሮጠ።

ወደሳሎን እሮጦ ሀዋ...ሀዋ....እያለ እየጮህ በየእቤቱ በየኩሽናው ቢፈልጋት ሀዋን የበላት ጅብ አልጮህ አለ። ነገር ግን ሱመያ ከተኛችበት መኝታ ቀስቅሶ መረበሽ ስላልፈለገ በእርጋታ ነገሮችን ማሰብ ጀመረ። የመጀመሪያ ስራው ሊሆን የሚችለው ሀዋ ጋ ስልክ መደወል ነበርና የሞባይል ስልኩን አውጥቶ የሀዋን ቁጥር መታ። ስልኩን ደውሎ ገና ወደ ጆሮው እንዳስጠጋ ግቢ ውስጥ አንድ ስልክ በጣም ሲጮህ ሰማው ይህ ስልክ የሀዋ መሆኑን በጥሪው ያውቀዋል። ሀሊድ እየተንደረደረ ወጥቶ ከግቢ ውስጥ የ ሀዋ ስልክ ወደ ሚጮህበት አቅጣጫ ሲሄድ የሀዋ ስልክ መሬት ወድቆ በደም ተለውሶ ተስብሮ አገኘው። ይሄን ግዜ ሀሊድ የሚሆነውን አጣ የያዘውን ስልክ ድንገት ሳያስበው ለቀቀው ብርክ ብርክ አለው እጁ መንታቀጥቀጥ ጀመረ የሚናገረውን አጥቶ ከመሬት ቁጭ አለ።

ይሄን ግዜ የሳሎኑ በር ተከፍቶ ሱመያ ከ እንቅልፏ ገና እንደነቃች አይኗን እያሻሸች ወደ ሀሊድ መጥታ የሆነውን ሁሉ ተመለከተች። ይህን ግዜም ጠየቀችው <<እናቴ የታለች? ሀዋ የት ነች?>> ብላ ሀሊድን ጠየቀችው። ሀሊድ የሚመልስላት መልስ ቢያጣ ከአይኖቹ እንባ እየፈሰሰ ሱመያን እቅፍ አርጎ ወደ ደረቱ አስጠጋት ለማባበል ቢሞክርም እየሸወዳት እንደሆነ ስለተረዳች ሱመያ ሀሊድን አጥብቃ ጠየቀችው። ይሄን ግዜ እናታቸው የሄደችበትን እሱም እንደማያውቅ እሱም ግራ እንደገባውና ቤተሰቦቻቸው ጋ መደውል እንዳለባቸው ተስማምተው ቤተሰቦቻቸው ጋ ደወሉ። ወድያው የሀዋ እንጀራ እናት ጋ ስልክ ጠራ። ሀሊድ ለሀዋ እንጀራ እናት በጣም ለምትወዳቸው ውዷ እናትየው ስልክ እንደደወለ እናትየው እትዬ መርየም በጣም ተደናግጠው ከ አንዲት ልጃቸው ከሙና ጋ እየተሯሯጡ መጡ።

ሙና የሀዋ እኩያ ስትሆን በአባት ብቻ የምትገጥማት እህቷ ነች። እንጀራ እናትየውም ለሙና ወላጅ እናት ናቸው። ይሄን ግዜ ሙና እና እናትየው ተሯሩጠው ወደ እቤት ገቡ እንደገቡ ያለውን ሁኔታ ሲያዩ በጣም ደነገጡ። ሙና ለውትሮ ከሀዋ ጋ ምትስማማ ትምሰል እንጂ በጣም እልህ ያለባት በሀዋ የምትቀና በሀዋ ቁንጅና ሰዎች ለሀዋ በሚስጧት መውደድና እያንዳንዱ ነገሮቿ የሚያስቀናት እኩያማች እህቷ ነች። ሀዋ እና ሙና መንትያ የሚመሳሰሉ ሁለቱም የሚያምሩ ናቸው ።

እትዬ መርየም ወደ እቤት እንደገቡ ሀሊድን እቅፍ አድርገው የተፈጠረውን ሁሉ ጠየቁት። እሱም አንድ በአንድ ከምሽት ጀምሮ ሀዋ ከነበረችብት ስሜት አንድ ሳያስቀር እያንዳንዱን በዝርዝር አስረዳቸው። ይሄን ግዜ እትዬ መርየም እጅግ ግራ ተጋቡ <<ልጄን ምን ነክቷት ይሁን?..ምን አገኘብኝ?..እሷ የሙት ልጅ ነች..እሷ ተውዳጅ ነች ...ሰው ላይ የመትደርስ ...ሰው የማትነካ.....ውድ እና ምስኪን ልጅ ነች....ዛሬ ምን አይነት ሰይጣን አገኛት ይሁን??..>> ብለው እንባቸውን ለቀቁት። ይሄን ግዜ ሙና በእናትየው ለቅሶ ተናዳ <<ምን ያስልቅስሻል?..ምንድነው የሚያስለቅስሽ? ምን ሆነች ገና መች አወቅና ቁርጡን!!!....>> ብላ በንዴት እናትየው ላይ ጮህች ነገር ግን እትዬ መርየም የሙናን ነገር ያውቁታልና ምንም ሳይመልሱላት ስልካቸውን አውጥተው ወደ ፖሊስ ጋ ደወሉ።

......ከሰአታት በኋላ ግቢውን ፖሊስ ወረረው እያንዳንዱን ቦታ ፎቶ ቢያነሳ መረጃ ቢያፋልግም እንኳን ሀዋ የገባችበትን ያገኘ ያያት እንኳን እኔ አለሁ የሚል አንድም ሰው አልተገኘ አንድም ጅብ አልጮህም። በዚ ሁኔታ ቀኑ ወደ መምሽቱ ተቃርቧል በዚህ ወቅት ድንገት የ ሀዋ ስልክ ጠራ ሁሉም ወደ ሀዋ ስልክ አይናቸውን ሲያደርጉ ስልኩ ላይ #የኔ_ውድ_ባል_ሰሚር ይላል ይሄን ግዜ ሁሉም በጣም ፈሩ እጃቸው ተብረከረከ ከመሀከላቸው ደፍሮ ስልኩን የሚያነሳ አንድ ሰው ጠፋ።

ሰሚር እጅግ መልከ መልካም የዋህ በጣም ተውዳጅ የቀይ ዳማ ፊት ያለው እና ባለሉጫ ፀጉር ረዘም ያለ ወጣት በጣም ሲበዛ ሀዋን የሚውድ በፍቅራቸው የሚቀናባቸው ለባለቤቱ ትገቢውን ግዜ መስጠት የሚችል ልጆቹን እና ቤተሰቡን የሚወድ እጅግ በጣም ተወዳጅ ወንድ ነው። ሰሚር ስልኩን ሲደውል ሙና ድንገት ተቅለብልባ ስልኩን አነሳችው ወድያውኑ <<ሄሎ ሰሚርዬ....>> አለች በዚህ ሁኔታዋ ሁሉም ግራ ተጋቡ። እትዬ መርየም በቆሪጥ ወደ ጎን ትመልክተዋት አፋቸውን እንደማሽሟጠጥ አሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ሙና ለሰሚር ያላት ስሜት እጅግ ግራ ስለሚያጋባና በጣም በሀዋ ስለምትቀናባት ከእህቷ ቀምታ የምትወስድ ስለምትመስል እጅግ ስለምትወደው ነው።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰሚር አንድ ጥያቄ ጠየቀ <<የምወዳት ሚስቴ የልጆቼ እናት ሀዋ የት ሂዳ ነው?>> ሲል ሙና ተቅለብልባ ቀለል ባለ ስሜት <<አይ እእ...ሻ..ሻወር ልትታጠብ ገብታ ነው >> ብላ ቀለል ባለ ስሜት መለሰችለት። ነገር ግን የሰሚር ምላሽ እንደ ሙና ቀላል አልነበረም <<..እ በይ እንግዲ አሁን እየመጣሁ ነው በቃ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ስለምደርስ ሀዋን ተዘጋጅታ እንድትጠብቀኝ ንገሪያት >> ብሎ ቆሌዋን ገፈፈው ይህን ግዜ ሙና ደንግጣ ስልኩን ከ እጇ ላይ ለቀቀችው።

ይቀጥላል.......
Forwarded from Ayat Real Estate S.C
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@Ethiopian_News_zena
@Ethiopian_News_Zenabot
የሀሙስ ማታ ቡና
Sadat
የሀሙስ ማታ ቡና
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

﴿ إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَنْ تَبُورَ ﴾.

@ONLYFORTRUTHERSJ
"ሀዋን ማን ገደላት"
( አብዲ ኢክላስ)

ክፍል ሦስት (3)

....አሁን ከምሽቱ 12 ሰዐት ሆኗል። ሁሉም እጅግ ግራ በተጋባ ስሜት በፍርሀት እና በጭንቀት ተውጠው እርስ በእርስ እየተያዩ ተቀምጠዋል። በአንድ በኩል ሀዋ ሞታለች ብልው እርማቸውን እንዳያወጡ አልያም አልቅሰው ለቀስተኛ እንዳይጠሩ የሀዋ ሬሳ አልተገኘም። አለች ብለውም እንዳያስቡ ሀዋ የት እንዳለች ማወቅ አልቻሉም። ግራ ተጋብተዋል... በሌላ በኩል ሰሚር እየመጣሁ ነው በማለቱ ለሀዋ ያለውን ፍቅር እና አክብሮት ስለሚያውቁ እጅግ በጣም እንደሚጎዳ እንደ ሚደነግጥ እና ህይወቱ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስላሰቡ በጣም ስግተዋል።

ከሁሉም በላይ ሰሚር ያለበት የልብ ድካም በጣም አስጨንቋቸዋል። ምክንያቱም ከዶክተር የታዘዘለትን መድሀኒት በመውሰድ ላይ የሚገኘው ሰሚር ከፍተኛ የሆነ ደስታም ከፍተኛ የሆነ ሀዘንም ህይወቱን ሊቀማው እንደሚችል ዶክተሩ ነግሮታል። ይህንን መላ ቤተሰቡ በማወቁ ዛሬ ጭንቀታቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል። ሰሚር ከጥቂት ደቂቃዎች ለኋላ እመጣለሁ ካለ አንድ ሰዐት ቢቆጠርም እሱ እንደማይዋሽ እመጣለው ካለ እንደሚመጣ ስላወቁ እያንዳንዳቸው ሲመጣ የሚዋሹበትን መንገድ የሚሸውዱበትን አልያም እሱን የሚያፅናኑበትን መንገድ በማሰብ ተጠምደው በራሳቸው ሀሳብ ውስጥ እላይ እታች ይባዝናሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የሙና ስሜት ግን ከሌሎቹ በጣም የተለየ ነው። ከእትዬ መርየም፣ከሱመያ እና ከኻሊድ የሙና ስሜት ቀዝቀዝ ብሏል። ውስጧ ላይ ምን እያሰበች እንዳለ እጅግ ግራ ምታጋባዋ ሙና እንደነሱ ብዙም የፈራች የጨነቃት አትመስልም። እንደውም የምትወደው ባሏ እንደሚመጣ ተነግሯት በጉጉት የምትጠብቅ ሙሽራ መስላ እራሷን እያሰማመረች ትገኛለች። ፈገግታ ከፊቷ ያልተለያት ሙና በጣሙን እሱን የናፈቀች በጣም የምትወ ደው የልጆቿ አባት እየመጣ ያለ እንጂ ሞት የምታረዳው አልያም መጥፎ ዜና የምትነግረው አንድ የእህቷ ባል እየመጣ በጭራሽ አይመስልም። ይህ ሁኔታ ግራ ቢያጋባቸውም እንኳን እሷን ትተው በራሳቸው ሀሳብ ተውጠዋል።

እትዬ መርየም ዛሬ በሙና ስሜት ላለመገረም ሁለት ምክንያት አላቸው። አንደኛው፦ሀዋ እጅግ በጣም ተወዳጅ ስለሆነችና አባታቸውም ከሁለቱ አስበልጦ የሚወደው ሀዋን ስለነበር ሙና በጣም ትቀናለች። ሁለተኛው ደሞ፦ያኔ አቶ ዩሱፍ የሀዋ የሙና አባት ከመሞታቸው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ <<እኔ ከመሞቴ በፊት ወግ ማረጌን ለሚያሳየኝ ባል ይዞ የመጣ ሰው ንብረቴን ይወርሳል ከግማሽ የበለጠውን ንብረት ለሱ አወርሳለሁ።>> ብለው ለሁለት ሴት ልጆቻቸው ተናዘዙ። ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ባል ለመፈለግ ቢሞክሩም..... ለሙና ሳይሳካላት ሀዋ ቀደመች። ሰሚርን አግብታ ያለውን ንብረት ሰማንያ አምስት በመቶ የወረሰችው ሀዋ የተንደላቀቀ ህይወት እየኖረች እንደሆነ የተረዳችው ሙና እያንዳንዱን ቀን በእህቷ መበለጧ እያብነከነካት ውስጧን እየበላው አመታት ተቆጥረዋል። ዛሬ ግን ቀን ለሙና የወጣላት በሀዋ ላይ የደረሰው ችግር ለሙና ፀሀይ የሆነላት ይመስላል። ምክንያቱም ሀዋ ባለችበት በዚህ ችግር ውስጥ ሙና ለሰሚር የተሻለ ሰው ሆና ለመታየት የምትፈልገውን ከማግኘት ወደኋላ አትልም።ምክንያቱም ሙና ሞገደኛ ስሜት ያላትና ለቤተሰቧ ብዙም ፍቅር የሌላት በራሷ ስሜት ውስጥ የምትኖር ወደክፉ የምታደላ እንስት በመሆኗ ነው።

በአንድ በኩል ኻሊድ እና ሱመያ ሀለቱም በዛ ትንንሽ እጆቻቸው ትቅፍቅፍ ተደታራርገው ፊታቸው ጭር ብሎ በጣም ከፍቷቸው ምንም ሳይተነፍሱ ከ አይናቸው እንባ ይዥጎደጎዳል። ይህን ግዜ እትዬ መርየም ወደ ኻሊድ ጠጋ አሉና አንድ ጥያቄ ጠየቁት <<ልጄ እንደው ሀዋ ላይ ጉዳት ያደርስባታል ብለህ ምታስበው ወይም የሚያስፈራራት ወይም ችግር የሚፈጥርባት እኛ በሌለንበት ሰሚር በሌለበት የሚመጣ ሰው አለ እንዴ እዚ ቤት? >> በማለት ጥያቄ አቀረቡለት። ይህን ጊዜ ኻሊድ በእንባ በተሞላ ንግግር እንዲህ ሲል መለሰላቸው...<<አ..አ..አይ ግን ሀዋ ሁል ግዜ ማታ ማታ የዋህ ሰው ጠላት አይጠፋውም እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳ ጠንካራ ሁኑ ትለን ነበር ለምን እንደሆነ ግን አይገባኝም ነበር እኔ ይሄ ቀን ይፈጠራል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር.... በዛ ላይ የድሮ እጮኛዋ ማታ ማታ እየደወለ ያስፈራራታል።..የኔ እንጂ የማንም አትሆኝም እያለ የልጆች እናት እንደሆነች እንኳን ስትነግረው እሰማለሁ።...እሱ ግን የሚሰማት አልመሰለኝም..እእ በሌላ በኩል ደሞ..>>ብሎ ንግግሩን ገታ አደረገ። ይህን ግዜ እትዬ መርየም በጣም ለመስማት ቀረብ ብለው..እ..በሌላ በኩል ምን ልጄ?...በማለት ጠየቁት። ኻሊድ ማውራት የፈለገ አይመስልም በአንድ አይኑ ሙናን ተመለከታት። ይሄን ግዜ እትዬ መርየም ነገር የገባቸው ይመስል <<እእ በቃ ተወው እንግዲ አውቄዋለሁ አትጨነቅ አንተ>> በማለት መለሱለት። ይሄኔ የትዬ ሀሊድ ጥርጣሬ ልክ ይሁን አይሁን ሳይገባው ግራ በተጋባ ስሜት ልንገራቸው አልንገራቸው ማለት ያዘ። ከዚያም<<እ..እ ገብቶታል ማለት የፈለኩት ግን የዋህ ስለሆነች የዋህ ሰው ጠላት አያጣም ብዬ ነው።>>በማለት ቃል ተነፈሰ። ይህን ብሎ እንደጨረሰ ድንገት የጊቢው በር ተንኳኳ ይሄኔ ሁሉም በፍርሀት ከመቀመጫቸው ተነስተው ድንገት ቆም አሉ።

ይቀጥላል.......
የዛሬው የኮቪድ-19 መረጃ ለማግኘት ቻናላችን የቀላቀሉ
@Ethiopian_News_zena
Aselamuwaleykim😊
Hello guys 🤗 ... It's Yasmina✌️
Past as a lesson 🤠
Mind Storming 😕
- how to deal with the past ?🧐
- how to use the past as a weapon for the future ? 😳
- lesson to take away from past ? ☹️
- codes to not stuck on past ? 😎
Universal Truth🤨
" There is nothing that's eternal in this world😭."
Past is one of the stages in life 🙊that everyone of us will surely face.
In any spots of the universe we are living, there are pasts that are preserved😮 to take lessons from them.
There are two types of pasts based on feeling 😕
- fabulous past
Is a past in which people wish to not miss any moment of it😏, and while this past is taking place they feel like the time is hastening so much to taste it😋.
Cruel Past
It's a past in which people feel so aggressive🤯.
and think that the time is not totally going becouse of their curiousness to pass it.
It's a state in which people get in hard mental illness😩. Coz , they try to blame the nature of their bad past. as a result, it's somehow difficult to heal from the wound that their past left for them.
The main reason of a suicide 😳across the world is because of the unjust past they have.🥺
Becouse they think the way to forget the past is to kill them selves🥶.
But, it's a wrong sight 😭☹️you can fix your past. by, your strong effort😃 and then time it self will help you recover from cruel Past you are😱.
there are three ways that people's used to act when there past is cruel.
- pretend like they are okay by, putting fake smiles on their face though, they don't heal their wound of their past😔.
- neither pretend they are okay 🙊nor heal their wound of their past😔.
- heal their wound first and show pure smile😊.
People's have to learn to deal with their pasts in a right way. by, giving the suitable medication that it need☝️.
The first medication is to remove the bad side 🧐of the past and to take a lesson from it😕.
But, if not you aren't only gonna hurt yourself, but also you will hurt people's that surround you. Even, you will give a chance for people's that make your past awful win😏 .
So, it's better to forget the bad, and forgive the oppressers😯.
There are certain codes that let you not stuck in your past 🤫
- don't isolate your self from other people's.
- don't be stubborn on your bad ideology of your past.
- Swallow all the bad images of your past.😜
- think life like a game😂, if you don't score good today then tomorrow will be your day😊.
- give the exact medication for your past wound, if not with a very short time the wound will revive again in harder way🙊.
- try not to have anything bad inside you towards the people that were the cause for your bad past 🤨, so as to have life filled with joy.
- learn to forget and move forward as much as you can😜.
To Sum up, Past is not a spot of life, that's designed to let you feel bad😒, but it's a chance for you to use the lesson of your past as a weapon to fight life matters🙂.
Your life will get over when you stuck on your past 😞. recognize when the sun rises it's new beginning and new chance for you to live your life😅.
May Allah (s.w.t) help us recover so quickly from our cruel past ..... Aminn🙏🙏
👇👇👇👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERSJ
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ይወዳደሩ 🏆🏆🏆ይሸለሙ
የመጀመሪያው ዙር ኢስላሚክ ፎቶ
ውድድር ከሰኔ 10 እስከ ሰኔ 15 ይካሄዳል ይወዳደሩ ይሸለሙ
🥇ኛ– ለወጣ የ500mb እና የሁለት ሳምንት admin ይሆናሉ ።
🥈ኛ – ለወጣ የ250 mb ሽልማት እና የአንድ ሳምንት አድሜን ይሆናሉ።
🥉ኛ – ለወጣ የ45 mb ሽልማት እና የሶስት ቀን admin ይሆናሉ።
ኢስላማዊ ፎቶዎች
→ የመስጂድ ፎቶዎች ታሪካዊ ፎቶ እና ዘመናዊ ማራኪ መስጂዶች
→ የመድረሳ ፎቶዎች የራስዎ የትዝታ ፎቶዎች ሊሆኑ ይችላሉ
→ ኢስላማዊ አልባሳት ፎቶዎች የራስዎን ወይም የሌላ
→ኢስላማዊ ቦታዎች ፎቶ
→ ሙስሊም አዛዉንት አባቶች ወይም እናቶች ፎቶ
.........
ሌሎችም ኢስላማዊ መልዕክት ያላችው የጀመአ የተለያዩ ኢስላሚክ ፎቶ

ይላኩ ይሸለሙ 🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
🏆🏆🏆🏆🏆🏆


ለመመዝገብ በውስጥ መስመር ይመዝገቡ
@shems

@kitshaa
@nadia11111111
ይመዝገቡ ይወዳደሩ 🏆🏆 ይሸለሙ

ሌሎች ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሳተፉ ቻናላችንን ይጋብዙ
T.me/sinatube
2024/09/29 08:27:56
Back to Top
HTML Embed Code: