Telegram Web Link
Dr Edosa ...Students service Director at Ministry of Science and Higher Educations ,speaking at 39th General Unions assembly. #Arbaminch Uni
Join @MUSUofficalchannell
🎉 Congratulations
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE (Bereket Gudisa)
ሀገር አቀፉ የተማሪዎች ህብረት ጉባኤ!

39ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት  ጉባኤ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረ እንደነበር በጉባኤው የተሳተፉ አባላት አስረድተዋል፡፡

በተለይም የ COVID-19 በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያሳደረው ጫናና የዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ጉዳይ ዋነኛ የውይይቱ ነጥቦች መሆናቸውን የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንትና የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ አባል ተማሪ እያቸው ተሻለ ገልጾልናል፡፡

እንደ ተማሪ እያቸው ገለጻ በቅርቡ አጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደረሰው ጉዳት የስነልቦና ጫና እና መፍትሄዎቻቸው በተጠና መልኩ እንደ ሃገር  በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካኝነት መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል ብሏል፡፡

በዝግጅቱ ጋሞ አባቶች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ እንዲሁም ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተውበታል፡፡

PHOTO: Duresa

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE (Bereket Gudisa)
ሀገር አቀፉ የተማሪዎች ህብረት ጉባኤ!

39ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት  ጉባኤ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረ እንደነበር በጉባኤው የተሳተፉ አባላት አስረድተዋል፡፡

በተለይም የ COVID-19 በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያሳደረው ጫናና የዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ጉዳይ ዋነኛ የውይይቱ ነጥቦች መሆናቸውን የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንትና የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ አባል ተማሪ እያቸው ተሻለ ገልጾልናል፡፡

እንደ ተማሪ እያቸው ገለጻ በቅርቡ አጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደረሰው ጉዳት የስነልቦና ጫና እና መፍትሄዎቻቸው በተጠና መልኩ እንደ ሃገር  በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካኝነት መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል ብሏል፡፡

በዝግጅቱ ጋሞ አባቶች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ እንዲሁም ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተውበታል፡፡

PHOTO: Duresa

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
The 39th Ethiopian Higher Education Institutions Students Union general Assembly announcement that was hosted by Arbaminch Uni will be posted after an hours ,all our students are supposed to read it.
Thank you.
Join @MUSUofficalchannell
On behalf of the Dereja Family, We Thank you for your participation and support of the Nation's first Virtual Career Expo's resounding success . Moreover, We are happy to announce that we will be having second round Virtual Career Expo in November.

#Dereja
#Virtualcareerexpo
#Findyournextstep
39ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት  ጉባኤ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከነሃሴ 21-23/2012 ዓ.ም በሰላም አጠናቀናል ፡፡

በስብባችን ያነሳናቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፦
1. በCovid-19 ምክንያት አጠቃላይ የተማሪዎች  ሂወት በእቅድ ለመምራት የደረሰውን ማህበራዊ ምስቅልቅል በስፋት ተነስቷል ፡፡ ተማሪዎች የግል ስራ እንኳ ለመስራት ቁርጥ ያለ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን አለመታወቁ በእቅድ ለመመራት እንደተቸገርንና አሁንም የበሽታው ተሎ መጥፋት አሳሳቢ ስለሆነ በጥንቃቄ ጎን ለጎን ት/ት ይጀመርልን የሚለው በስፋት ተንፀባርቋል ፡፡
2. ኮሮና እንደ አለም የመጣ ችግር  ስለሆነ ትግሉ እንደ ዓለም ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሃገራችን ደግሞ ከግዜ ወደ ጊዜ እያሳሰበን የመጣው የፖለቲካው ብልሽትና የዘረኝነት ጉዳይ በእጅጉ እንዳሳሰበንና የተማሪዎች መገደል ፡አፈና መፈፀም በትኩረት ቁጭት በተሞላበት መንገድ ተነስቷል ፡፡
3.ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ አስተሳሰብ የሚንፀባረቅባቸው የፌዴራል ተቋም መሆናቸውን ቀርቶ የክክል ወይም የፅንፈኛ ፖለቲከኛ መፈንጫ መሆናቸው ተማሪዎቻችን እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪነታቸው ለመምራት የተማሪዎች ህብረት ፈተና ውስጥ እንደገባን ተነስቷል ፡፡
4.የፌዴራል መንግሥት ሃገር ለሚያፈርሱ ፖለቲከኞች ለማወያየት  ትኩረት የሰጠው ጊዜ  ያክል  በግማሽ እንኳ ትኩረት ሰጥቶ አወያይቶን ና በሃገር ጉዳይ የተማሪዎች ስሜት አንጸባርቀን የምናውቅበት የፌዴራል መንግሰት መድረኮች በአግባቡ እያገኘን እንዳልሆ ተነስቷል ፡፡
5. የእኛው ዘመን መወሰን ያለብን እኛ እንጂ እድሚያቸው በመገጋደልና በመናቆር ጨረሰው የእኛ ዘመን በመገዳደል  እንዲያልቅ ከሚሰሩ ፖለቲከኞች እራሳችን ቆጥበን ከምንመራቸው ተማሪዎች ጋር ሃይማኖትና ብሄር ሳይለየን በዩኒቨርሲቲ ተማሪነታችን ልንታገላቸው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
6. መንግሥት ጠንከር ያለ ህግ የማስከበር ስራ መስራት አለበት እንጂ ተማሪ እየተገደለ፡ ተማሪ እየታፈነ መቀጠሉ የህሊና ጠባሳ እንደሆነብን ተንፀባርቋል ፡፡
7.በcovid-19 የተቋረጠው ት/ት ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ይደረግ ቢባልም አንደኛው ወሰነ ት/ት ፋይናል ፈተና ሳይጨርሱ የቀሩ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉና እንዲታሰብበት የሚለውም ተነስቷል ፡፡
በጥቅሉ በሶስት ቀን ቆይታችን ያልተነሱ የተማሪዎች ጉዳይ አለ ማለት አይቻልም ፡፡
-
ከሳይንስና እና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር የመጡ ባለ ድርሻ አካላት በመድረኩ ያንፀባረቁት ነገር በCovid-19 ምክንያት ባለው አለም አቀፍ ሁኔታና የበሽታው ባህሪ  በግልፅ አለመታወቁ ዝግጀት እንዲደረግ አቅጣጫ ከመስጠት ባሻገር ቁርጥ ያለው ቀን ለመወሰን እንደተቸገሩ ገልፀዋል ፡፡ በተለይ ት/ት ከፍተው እንደገና የዘጉ ሃገራት ስላሉ እንዲህ አይነት ጉዳይ ቢያጋጥመን ተማሪዎቻችን የበለጠ ሞራላቸው ሊጎዳ ስለሚችል የሚለው ውዝግብ እንደከተታቸው ገልፀዋል ፡፡
ያም ሁኖ ትምህርት ይከፈት የሚለው የመንግሥትም አቋም እንደሆነ እና ለዛም ሲባል የምርመራ ዘመቻ በስፋት ተካሂዶ ብዙ ቁጥር ያለው ሰው እየተያዘ እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡
በተለይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎች ኳራታይ መሆናቸው ተጨማሪ ፈተና እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡ ከዝግጅቱ በተጨማሪ ጎን ለጎን ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር ት/ት ሲጀመር እንዴት መቋቋም አለብን በሚለው ውይይት እንደሚካሄድ አመላክተዋል ፡፡
እስከዛው ግን የሚጠሩበት ጊዜ ቅርብ ሊሆን ስለሚችልና የሚጠናቀቅበትን ጊዜ አጭር ስለሚሆን ተማሪዎች እያነበቡ በመንፈስም ተረጋግተው እንዲጠብቁ የሚል ምክራቸው ለግሰዋል ፡፡
****-***
ሌላው እኛም እንደተማሪ ህብረት የመፍትሔ አቅጣጫ የምንለውን ነገር ከተማሪዎች አስተያየት በመሰብሰብ ጭምር ተጨማሪ ውይይት በቅርብ ቀን የሚኖረን ይሆናል፡፡
ከዛ ባሻገር Covid-19 ዓለም አቀፍ ስለሆነ ያደረሰብን ጫናም እንደ አለም ነው፡፡
አሁንም እያሳሰብን ያለው ነገር ተማሪዎች በነፃነት እየተማሩ እንዳልነበርና በተለይ ከሚኖሩበት ክልል ውጭ የሚሄዱ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሳይሆን በቅኝ ግዛት ተማርከው የሄዱ ያክል ተሳቀው፡ አለፍ ሲልም ግድያና አፈና እደረሰባቸው እየተማሩ መሆናቸው አሳስቦናል፡፡
*-*
ሚዲያዎችና መንግሥት ፈቃደኛ ከሆኑም በቅርብ ጊዜያት አጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደረሰው ጉዳት፡የስነልቦና ጫና እና መፍትሄዎቻቸው በተጠና መልኩ እንደ ሃገር  በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካኝነት መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል፡፡
   
"🇪🇹እናት ሃገራችን ለዘላለም ትኑር🇪🇹 "
    
 የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተማሪዎች ህብረት

Addis Abeba, Ethiopia
          
     join  @MUSUofficalchannell
Breaking news!
Mekelle University is preparing to start Community centered TV channel. Community radio is already giving service. #We_really_care MU
Join @MUSUofficalchannell
የሞሞና ቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን እንገኛለን። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኮሚኒቲ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ አካል የሆነው የሞሞና ቴሌቪዥንን በሳተላይት ለማሰጀመር የማሳራጭያ እቃዎች ዝርዝር ጥናት እና የስቱዲዮ ግንባታ ቅደመ ዝግጅት ዛሬ በ26/12/2012 ዓ/ም በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች ቀርቦ አሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ የኮሚኒኬሽን ምህንድስና ኢንጂነሮች፣ የእንፃ ግንባታ እና ዲዛይን ባለሞያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሮች፣ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒሽን መምህራን፣ የትያትር እና ጥበባት መምህራን እና ባለድርሻ አካልት የተሳተፉ ሲሆን ገንቢ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም በቅደመ ዝግጅት ስራዎቻችን ላይ የታዩ ጉደለቶች ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተዋል።

የዩኒቨርስቲያችን የማሕበረሰብ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች፣ ተማሪዎች እና መምህራን የተግባር ትምህርት ማሰልጠኛ እንዲሁም ለማሕበረሰባችን አማረጭ የመረጃ ምንጭ በመሆን የማሕበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥበት ይሆናል።

https://www.facebook.com/110168646998819/posts/325094585506223/

"We really care"

(VIA Mr Bereket Hasen).
Join @MUSUofficalchannell
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉባዔ ተካሄደ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
39ኛው የህብረቱ ጉባኤ የተካሄደው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት አጀማመርና የኮቪድ -19 ተፅዕኖ እንዲሁም ሰላማዊ መማር ማስተማርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል፡፡
ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደው ምክክር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስን ከመግዛትና የባህል ብዝሃነትን ከማስተናገድ አንፃር የተማሪዎች ህብረት ሚና በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በማጠቃለያው የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በመማር ማስተማር ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደርጉት ሂደት ተገቢውንና ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዘው በሰላማዊ መንገድ በማስተባበር ሊሆን ይገባል ተብሏል፡፡
በጉባዔዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መምህራንና ተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ፣ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንትና አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጋበዙ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች እና አሰልጣኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት በማድረግ ተሳትፈዋል፡፡
2024/09/25 07:23:59
Back to Top
HTML Embed Code: