Telegram Web Link
We thank you EASYO , EHIESU and other team members , it had been great Discussion. Gratitude to the Distinguish guests too.🙏🙏🙏
Join👉 @MUSUofficalchannell
Dereja.com is Giving virtual training for our Mekelle University Graduating Students for 3 and more consecutive days. We thank you @Derejaofficial for you commitment.we encourage our graduating students to take the training . For more Join
👇👇👇👇
@MUSUofficalchannell
👆👆👆👆
Good morning from #Ashegoda Wana gibi. Thanks @mahle07 for sharing us.
Greetings from @mahle07. share us campus life to @Abrhaley_Arefaine and say hi to your friends . For more join us 👇👇👇👇
👉👉 @MUSUofficalchannell
Welcome back Dear Connection! Nice to meet you again Dears!
የትምህርትና ስልጠና መስኩን ከኮቪድ 19 በኃላ ለማስጀመር በሚከናወኑ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምክክር መድረኩ ዛሬ በአዲስ አበባ ሲጀመር እንደአገር የወረርሽኙ ስርጭትንና የሴክተሩ ትምህርት የማስጀመር ዝግጅት እንደሚዳሰስበት ጠቁመው "ከመንግስት አቅጣጫ አግኝተን የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ስንከፍት ተማሪዎችን በምን ሁኔታ መቀበል እንዳለብን እንመክራለን" ብለዋል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መልሰው ሲከፈቱ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ፣ የአስተዳደርና አካዳሚክ ጉዳዮች ላይም ምክክር ይደረጋል ተብሏል፡፡

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሳይጠናቀቅ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደአገራችን በመግባቱ የ2012 ዓ.ም ትምህርት እንዴት ይጠናቀቅ በሚለው እና የ2013 ዓ.ም እንዴት ተጀምሮ ይቀጥል የሚለው ላይ ትኩረት አድርጎ እቅድና መመሪያዎችን አዘጋጅቶ መስራት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል በወረርሽኙ ምክንያት የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢቋረጥም ትምህርትን በኦንላይን ከማስቀጠል ጎን ለጎን ዩኒቨርስቲዎች የለይቶ ማቆያ እና ማገገሚያ ማዕከላት በመሆን፣ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን በማምረት፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችና በምርምር በመሳተፍ እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌቱ በትናትናው ዕለት ለተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ ያበረከተውን ድጋፍ አውስተው "እንኳን ደስ አለን" ብለዋል፡፡ በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናቸውንም አቅርበው ድጋፉ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል፡፡

ወ/ሪት ራሔል ለማ ከጤና ሚኒስቴር "የኮቪድ 19 ስርጭት በአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ያለው እንድምታና ዓለምአቀፍ ተሞክሮ" በሚል ርዕስ የዓለምአቀፉን ተሞክሮና በአገራችን የኮቪድ 19 ወቅታዊ የስርጭት ሁኔታን የዳሰሰ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ያለእድሜ ጋብቻና የምገባ ፕሮግራም መቋረጥ ማስከተሉንና እንዲሁም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው በመቆየታቸው የትምህርት ብቃትና ችሎታ ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ እየጨመረ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ ደረጃ (ፒክ) ላይ አለመድረሱን ገልፀው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ መውረድ ያሳየባቸው አንዳንድ አገራት የተለያዩ ጥንቃቄዎችን አድርገውና የንፅህና መጠበቂያዎችን በማሟላት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከከፈቱ በኃላ መልሰው የዘጉ አገራት መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ግን በኦንላይን እያስቀጠሉ እንደሆነ ገልፀው የገፅ ለገፅ ትምህርት መክፈት የሚያስቡ አገራት ራሳቸውን ገምግመው የሚያስጀምሩበት የተዘጋጀ ዓለምአቀፍ መመሪያ መኖሩንም ገልፀዋል፡፡

ወ/ሪት ራሔል የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ ለመክፈት እንዲቻል ለማድረግ መሰራት አለባቸው ያሏቸውን የተለያዩ ምክረኃሳቦችን አቅርበዋል፡፡ ከምክረኃሳቦቹ መካከል ከእቅድ ፖሊሲና ማስተባበር አንፃር፡ ከጤና ተቋማት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንዳለበት፣ ፖሊሲ እቅዶችና መመሪያዎች ሲዘጋጁ ሰራተኞቻቸውን ያገናዘቡ ሊሆኑ እንደሚገባ፣ የታቀዱት ስራዎች በመመሪያው መሰረት መሟላታቸውንና እየተሰሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሁለት ሜትር ርቀት ለማስጠበቅ የማይቻል ከሆነ ሰፋፊ አዳራሾችን መጠቀም፡ አንዴ ብቻ የሚያገለግሉ የምግብ ማቅረቢያዎችን መጠቀም፤ ምዝገባ ኦንላይን እንዲሆን ማድረግ፣ አንዳንድ ኮርሶችን በከፊልም ይሁን ከተቻለ በሙሉ ኦንላይን ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በመኝታ ክፍሎች የሚኖርን የተማሪዎች ብዛት መቀነስ፣ ከተቋማት ውጪ ከማህበረሰቡ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት መቀነስ፣ ታጥበው ተመልሰው አገልግሎት ላይ የሚውሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ የእጅ ንፅህና መጠበቂያዎችን ማሟላት እና የሚከፈቱ መስኮቶችና በሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ ከቀረቡት ምክረኃሳቦች መካከል ይገኙበታል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ሊታዩ የሚገባቸው ብለው ባቀረቧቸው ምክረ ኃሳቦች መሰረትም የወረርሽኙ የመጨመር ፍጥነት፣ የለይቶ ማቆያ የሆኑ ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለማዘጋጀት የሚፈጅው ጊዜ እና የአከፋፈት ሂደቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም አንዴ ከተከፈተ በኃላ ተጠርጣሪ ቢገኝ ምን ማድረግ እንችላለን የሚለው ሊታሰብበት እንደሚገባና ለዚህም ከአሁኑ ዝግጅት መጀመርና ከፌደራል ጀምሮ የተዋቀረ እና የራሱ መመሪያ የተዘጋጀለት የዝግጅትና ትግበራ ሂደት ተዘጋጅቶ ሊሰራበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን እየተከላከሉ ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት መከናወን ያለባቸው የአካዳሚክና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ያሉበት ዝግጅት የቀረበ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ትምህርት ማስጀመር ይቻላል ተብሎ ሲፈቀድ ለማስጀመር እንዲችሉ መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርቦበታል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዩኒቨርስቲዎች የኮቪድ 19 ምልክት የሚታይባቸው ተማሪዎች ቢገኙ የለይቶ ማቆያ የሚሆኑ ቦታዎችን ከአከባቢያቸው ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር በግቢያቸው እንዲያዘጋጁ የሚል ይገኝበታል፡፡

በመድረኩ 5 ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡

በ2 ቀን የምክክር ቆይታቸው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 2 ግምገማ፣ የ10 ዓመት የልማት እቅድ ፣ የ2013 እቅድና ዝግጅት ምዕራፍ፣ የትምህርትና ስልጠና መረጃ ስርዓት፣ የትምህርት፣ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር ፖሊሲ፣ የትምህርት፣ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ ደንብ፣ ተቋማትን በትኩረትና በተልዕኮ ማደራጀት ቀጣይ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠናቅቀው ወደስራ ሊገቡ ዝግጁ የሆኑ ፖሊሲዎች ደንቦችና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች ቀርበው ውይይት የሚካሄድባቸው ይሆናል፡፡
#MoSHE
2024/09/25 19:29:09
Back to Top
HTML Embed Code: