Telegram Web Link
Mekelle University Student Union
Photo
From #File, 2012/2013EC Graduation Class cerebration memory. Just #Historic Graduation. #Congratualation.
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ተማሪዎቹን በራሱ ዩኒቨርሲቲ ሊጠራ መሆኑን አሳወቀ !

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ዝርፊያና ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ዛሬ በነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ስነስርዓት ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዩኒቨርሲቲውን ወደነበረበት የቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ያሳወቁት ፕሮፌሰሩ የሁሉም አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን አጠናቆ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ እንደሚጠራቸው ፕ/ር ገብረእየሱስ አሳውቀዋል።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ላይ በደረሰው ውድመት እና ዝርፊያ ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ለ12ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ያላጠናቀቁትን ትምህርት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በመማር ነው አጠናቀው የተመረቁት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Congratulations! Dear all Axum University GC Students,on the behalf of Mekelle University Students Union Office.
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ህብረት ለማጠናከር እየተሰራ ነዉ፡፡
====================================
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና በጎንደር ዩኒቨርስቲ አስተባባሪነት መጋቢት 10 /2013 የተጀመረዉ የ2 ቀናት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት አመራሮች የዉይይት መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር ጋሻው አንዳርጌ ዉይይቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህብረቱ አመራሮች የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙና ሰላማዊ መማር ማስተማር እንድሰፍን የበኩላቸዉን እንዲወጡ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ በበኩላቸዉ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ላይ በማተኮርና የብሩህ እሳቤ እና መልካም እሴቶች ባለቤት በመሆን በመማር ማስተማርና አገር ግንባታ የድርሻቸዉን እንዲወጡ ህብረቱ ምሳሌ መሆን እንደሚገባዉ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአደንዛዥ እጾችና መድሀኒቶች መከላከል ረቂቅ መመሪያ ቀርቦም ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በትምህርት ጥራት፤ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎች የተሰጠ ትኩረት፤ የተማሪዎች ህብረትና የዩኒቨርስቲዎች ቅንጅትን እንደዚሁም ሊደረግላቸዉ ስለሚገባ ድጋፍ በሚመለከትና ሌሎች ከመማር ማስተማር ጋር በተያያዙ ርዕሰጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎችን አንስተዉ ዉይይት ከተካሄደባቸዉ በኋላ በቀጣይ ስራዎች ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በፕሮግራሙ የሀገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ ኦሊ በዳኔን ጨምሮ የ45ቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንቶችና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ጎንደር ዩኒቨርስቲ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የቱሪስት መስህብ የሆኑትን የፋሲል ግንብና ቤተ-መንግስቶች በመጎብኘትና ልምድ በመለዋወጥ ተጠናቋል፡፡

Join @EHEISUOfficialChannell
ጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ፦

የብቃት ምዘና ፈተናው ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙ ፦

• ነርሲንግ - 20/07/2013 ዓ.ም

• ጤና መኮንን - 21/07/2013 ዓ.ም

• ህክምና እና ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ - 22/07/2013 ዓ.ም

• ፋርማሲ እና አንስቴዥያ - 23/07/2013 ዓ.ም

• ሚድዋይፈሪ - 24/07/2013 ዓ.ም

* የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች በቀጥታ በተማሩበት ተቋም ወይም የተማሩበት ተቋም በሚገኝበት ከተማ በሚገኝ የመፈተኛ ጣቢያ የሚመደቡ ይሆናል፡፡

* ለዳግም ምዘና /Re-Exam/ በOnline Registration የተመዘገቡ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የመፈተኛ ከተሞችን የመረጡ ተመዛኞች በቀጥታ በመረጡት ከተማ በሚገኝ የምዘና ጣቢያ የሚመደቡ ይሆናል (የመፈተኛ ከተሞችንና ጣቢያዎችን ይህን ተጭነው ይመልከቱ telegra.ph/MoHEthiopia-03-21)

@WCUSU
2024/09/23 05:20:28
Back to Top
HTML Embed Code: