Telegram Web Link
Forwarded from Ab®ish Ⓐ🔐
at Jimma Uni Syposem , our MU managements with National Students Union.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
የጤና ሚኒስትር የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረኃሳብ ማቅረቡን ተከትሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በጅማ ዩኒቨርስቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡
በውይይታቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች እንደሚመክሩና የዩኒቨርስቲዎች ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር የተደረገ የዝግጅት ምዕራፍ ስራ ያለበት ደረጃ ገምግመው በአፋጣኝ መሰራት ያለባቸው ሁኔታዎች ላይ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
በቆይታቸው ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በጋራና በጥልቀት በመወያየት ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ መክፈት ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡
2024/09/24 21:33:16
Back to Top
HTML Embed Code: