Telegram Web Link
"የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋግጥልን ትምህርት እንጀምራለን" - ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት አመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ ተይዟል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ የቀነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል፡፡

በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታበተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡

ከትላልቅ ከተሞች እርቀው የሚገኙና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
_

1. የብቃት ምዘና ፈተናው ከጥቅምት 09 እስከ 13/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2. ከዚህ በፊት የተሰጡትን የብቃት ምዘና ፈተናዎች ወስደው ፈተናውን ያላለፉ ተመዛኞች
ከመስከረም 13 እስከ 27/2013 ዓ.ም በኦንላይን hple.moh.gov.et ላይ
በመግባት ለዳግም ምዘና (Re-Exam) መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. በ online registration system ለመመዝገብ ተመዛኞች የኢሜይል(email)
አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
4. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች አስፈላጊ መረጃዎችን በትክክል
መሙላት እና የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉበትን ከተማ ከተዘረዘሩት
አማራጮች ውስጥ መምረጥ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
5. በ online registration የተመዘገቡ ተመዛኞች ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የመለያ
ቁጥር (Registration No) መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸው ከተማሩበት ተቋም
በቀጥታ ስለሚላክልን በኦንላይን ሲስተም (online registration) መመዝገብ
የለባቸውም፡፡
7. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች ለፈተናው የተመደቡበትን የፈተና
ጣቢያ (Exam Center) ከጥቅምት 02/2013 ዓ.ም ጀምሮ በድረ-ገጽ
www.moh.gov.et ወይም በfacebook: Ministry of health, Ethiopia
በመግባት መመልከት ይችላሉ፡፡
8. ተመዛኞች በምዘና ወቅት እርሳስ፣ መቅረጫ፣ ላጲስ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ
መታወቂያ ይዘው መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ከዚህ ውጪ ሞባይል ስልክን ጨምሮ
ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ፈተና ክፍል ይዘው መግባት
አይችሉም፡፡
9. የCOVID-19 ወረርሽኝን ከመከላለል አንፃር ሁሉም ተመዛኞች በፈተና ወቅት የአፍና
አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (Face-mask) ማድረግ እና ሌሎች አስፈላጊ መከላከያ
መንገዶችን መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተመዛኞች የፈተና ፕሮግራሙን ከተማሩበት የትምህርት ተቋም እና ከላይ ከተጠቀሱት
የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከጥቅምት 02/2013 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. በፈተና ወቅት መኮረጅ ወይም ማስኮረጅ እና ማንኛውም ዓይነት የፈተና ማጭበርበር
ድርጊት መፈጸም የፈተና ውጤት ያሰርዛል፡፡
12. ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5-324185 በመደወል ወይም ወደ
[email protected] መልዕክት በመላክ ማግኘት ይቻላል፡፡

@MOH
Good News!!
ጤና ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ!

የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር እንደየአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምክረ ሀሳብ ማቅረቡን ኢቲቪ ዘግቧል።
#EBC
#TikhvaEthiopia

Join @MUSUofficalchannell
ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይን ይተዋወቋቸው

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 (07/01/2012 ዓ/ም)

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በሰሯቸው የምርምር ስራዎች በስፋት ይታወቃሉ። በሀገራችን ከሚገኙ ጥቂት የፕሮፌሰርነት ማእረግ ካላቸው ሴት እንስቶች መካከልም አንዷ ናቸው። የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን አባይ ተወልደው ያደጉት በትግራይ ክልል በውቕሮ ከተማ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመቐለ እና አዲግራት ተከታትለዋል። ከዛም በመቀጠል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በማቅናት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ በPlant science በዲፕሎማ በ1976 ዓ/ም ተመርቀዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በእርሻ ወኪልነት ካገለገሉ ሲሆን በቀድሞ የአለማያ ግብርና ዩኒቨርስቲ በPlant science የዲግሪ ትምህርታቸውን በ1984 ዓ/ም አጠናቀዋል።

በመቀጠልም ለሁለት አመታት በመቐለና ደብረብርሃን የእርሻ ምርምር ተቋም ካገለገሉ በኃላ መቐለ ዩኒቨርስቲ ሲመሰረት በ1986 ዓ/ም መቀላቀል ችለዋል። ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ ከጀማሪ መምህርነት በመነሳት የዩኒቨርስቲውን እርሻ በማስጀመር፣ በምርምር ፣ገበሬዎችን የሚያሳትፉ ፕሮጀክቶች በማካሄድ፣ በግብርናው ዘርፍ ስድስት የሚደርሱ አዳዲስ ዝርያዎችን ከተለያዩ ተመራማሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ለአርሶ አደሮች አድርሰዋል።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጥናቶችን በማድረግ አዳዲስ የትምህርት ስርአቶችን በመቅረፅ የምግብ ሳይንስ እና የድህረ ምርት ብክነት ትምህርት ክፍልን በማቋቋም
የአካባቢ፣ የሥርዓተ-ፆታ እና የልማት ጥናት ተቋም በምስረታ ሂደትና በዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። እንዲሁም የተለያዩ የቤተ ሙከራዎችንም በመክፈት ዩኒቨርስቲው አሁን ለደረሰበት ደረጃ
የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ ችለዋል ።

ፕ/ር ፈቴን ኣባይ በ1986 ዓ/ም ወደ አንግሊዝ በማቅናት ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ በገጠር ሀብት አስተዳደር (Rural Resource Management) በ1988 ዓ/ም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል። በማስከትልም በ ኖርዊዬ Plant Breeding and Seed Science የሶስተኛ ዲግሪያቸውን (PHD) በ1999 ዓ/ም አጠናቀዋል ።

በአጠቃላይ ፕሮፌሰር ፈቴን አባይ 87 ሳይንሳዊ ፅሑፎችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ማሳተም ችለዋል። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሴኔት ባፀደቀው መሰረት ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል። በዚህም በሀገራችን ከሚገኙ ጥቂት የፕሮፌሰርነት ማእረግ ካላቸው ሴት እንስቶች መካከልም አንዱ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ ባከናወኗቸው ጠንካራ ስራዎቻቸው በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሽልማቶችን እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ባሳዩት የላቀ ውጤት እና የስራ አመራር ብቃት ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች ምክትል ፕረዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አሁን ላይ በመቐል ዩኒቨርስቲ የሰኬት ጉዞ ላይ የማይነጥፍ አሻረቸውን ካተሙት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወትን በመተካት ተጠባባቂ የመቐለ የኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ተሹመዋል።
From Mekelle University Ayder Comprehensive Hospital College .
The Ethiopian Higher Education Institutions Students Union will participate at the Forum in Jimma,Ethiopia. Representing our Higher Institutions Students.

from 21-22/09/2020

"Hope you return soon! "
Forwarded from Mekelle University Student Union (Ab®ish Ⓐ 🔐)
The Ethiopian Higher Education Institutions Students Union will participate at the Forum in Jimma,Ethiopia. Representing our Higher Institutions Students.

from 21-22/09/2020

"Hope you return soon! "
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠያ ቅድመ ዝግጅትና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት የግምገማ መድረክና አውደ ርዕይ ከነገ ጀምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ይካሄዳል።

የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችም ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው ይጠበቃል። በምክክር መድረኩ ሁሉም የከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሳተፉ ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
2024/09/25 01:37:57
Back to Top
HTML Embed Code: