Telegram Web Link
ኣዮኹም ናይና ግጥሚ ቁ-293
===================
ናይ ሰላም ኣምባሳዳር ኮይና እያ ብኣኻ
-----------------------መቐለ ዩኒቨርሲትና
ናብ ታሕቲ ወሪድካ ጠቢቕካ ብምስራሕ
---------------------ምስቲ ለባም ህዝብና
ሕልፊ እያ ካብ ኩለን ካብ ላዕለዎት ትካላት
----------------------ዘለዋ ኣብ ሃገርና።

እንት ሐዚ ግና

ብሽጣራ ኣቢቹ እንከይሓሰብናዮ
---------------------ዋላ እንተተልዓልካ
ዝግበኣካ ሰሪሒኻ ኢኻ እትሓስቦ ኩሉ
-------------------------ሓንቲ ከይገደፍካ
ንቲ ፅቡቕ ስራሕኻ ጎሊሁ ዝርአ
---------------------------ክብሪ ይግበኣካ
ዝተረፈ እዋን ግዜኻ ይባረኽ
---------------------------ሰላም ይኹነልካ።
GG ፀረ-ባንዳ(04/01/2012 ዓ.ም)

Join @MUSUofficalchannell
Congratulations Prof Fetin Abay - Acting President of Mekelle University and thank you Prof Kindeya G.hiwot.

Join @MUSUofficalchannell
በመቐለ ዩኒቨርስቲ የማይረሳ አሻራን ያተሙት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት

--------

በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 የተዘጋጀ

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ከመጀመሪያ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ እና ከጀርመናዊው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጆአኪን ከርዚግ በመቀጠል ሶስተኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ናቸው።

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (ከቀድሞዉ አለማያ) በስነ-እፅዋት (Forestry) በጥቅምት 1985 ዓ/ም የወርቅ ሜዳሊያ በመውሰድ የተመርቁ ሲሆን የማስተረስ ዲግሪያቸውን ደግሞ እንግሊዝ ሀገር ተምረዋል፡፡ መቐለ ዩኒቨርሲቲን በአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደ ጀርመን ሀገር በመሄድ የፒ ኤች ዲ ትምርህታቸውን ተከታትለዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ዩኒቨርስቲውን ከጥቅምት 1986 ዓ/ም ጀምሮ በመምህርነት፣ በትምህርት ክፍል ሃላፊነት፣ በምርምርና ስርፀት ሃላፊነት፣ በምርምህርና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተባባሪ ምክትል ፕሬዚዳንትነት፣ በጥናትና ማሕበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትን፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትን እንዲሁም ከግንቦት 28/2005 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በመሆን በታታሪነት እና በቁርጥኝነት አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት በዓለም አቀፍ መፅሔቶች የታተሙ በርካታ ሳይንሳዊ ፅሑፎችን በመገምገም፣ የማስተርስ እና የፕ ኤች ዲ ተማሪዎችን በማማከር በአካዳሚክ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ ሲሆን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ከ64 በላይ ሳይንሳዊ ፅሑፎችን አሳትመዋል። በሃምሌ 26/2009 ዓ/ም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሴኔት ባፀደቀው መሰረት የሙሉ ፕሮፌስርሺፕ ማዕረግ አግኝተዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት በምርምህር እና በትምህርት ዘርፍ እንዲሁም በአመራር ክህሎታቸ
ክህሎታቸው ባደረጉት አስተዋፅዖ በብዙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቿል፡፡ በምርምር development Cooperation prize እ.ኤ.አ. በ2004፣ በአመራር ክህሎት የAfrica leadership Award for Education leaders እ.ኤ.አ. በ2015 እና የዓመቱ ምርጥ ሽልማት ከHargeisa University እ.ኤ.አ. በ2019 ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ከተሰጧቸው ዓለም አቀፍ እውቅናዎች እና ሽልማቶች ተጠቃሽ ናቸው።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት እንደ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በሁሉም ዘርፎች እና ፕሮጅክቶች አዘወትረው ጠንካራ ድጋፍና ተሳትፎዎችን ያደረጉ ሲሆን መቐለ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተ ጀምሮ ከሁለት ካምፓሶች ወደ ስምንት ካምፓሶች ሲያድግ በነበረው ጉዞ ግንባር ቀደም በመሆን፣ የዩኒቭርስቲው የምርምር ዘርፍ እንዲያድግ፣ የማሕበረሰብ አገልግሎት እንዲጠናከርና ተጨባጭ ማሕበራዊ ለውጥ እንዲመጣ፣ የአካዳሚክ ዘርፉ እንዲዘምን በማድረግ፣ የዩኒቨርስቲውን ዓለም አቀፋዊነት ከፍ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅዖ በማድረግ እንዲሁም በሀገረችን እና በክልላችን ጉዳዮች ላይ የድርሻቸውን በማበረከት በመቐል ዩኒቨርስቲ የማይረሳ አሻራቸውን አትመዋል።

የዩኒቨርስቲያችን ማሕበረሰብ ሬዲዮ ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ለመቐለ ዩኒቨርስቲ እና ለማሕበረሰባችን ላባረከቱት ታላቅ ስራ ክብርና ምስጋና እያቀረበ ለውድ አድማጮቻችን የፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወትና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ጉዞን ሚዳስስ ልዩ ፕሮግራም ወደፊት ውደ እናንተ የሚየደርስ ይሆናል።
If you want to learn more about our startup please check out www.lesan.ai
Forwarded from Deleted Account
😈የተለያዩ የ hacking ወሬዎች

📱💻ስለ ቴክኖሎጂ ትምህርት አዘል መረጃዎችን

▶️የተለያየ የvideo tutorial

📱የተመረጡ የተለያዩ አዳዲስ የ 📲android phone አፓችና ጌሞችን በነፃ

🗳package hack ማረጊያ app አሰራር

🔐telegram hack ለማረግ

🔓Facebook hack ለማረግ

🖤telegram member ለማብዛት

የሚያገኙበት ምርጡ ሀገራዊ ገፅ🇪🇹
Join ያድርጉን
👽👽👽👽💻💻💻💻
Mekelle University Student Union pinned «Congratulations Prof Fetin Abay - Acting President of Mekelle University and thank you Prof Kindeya G.hiwot. Join @MUSUofficalchannell»
the above is vacancy announcement from Gambella University
2024/09/25 03:19:57
Back to Top
HTML Embed Code: