Telegram Web Link
Dereja.com is Giving virtual training for our Mekelle University Graduating Students for 3 and more consecutive days. We thank you @Derejaofficial for you commitment.we encourage our graduating students to take the training . For more Join
👇👇👇👇
@MUSUofficalchannell
👆👆👆👆
Good morning from #Ashegoda Wana gibi. Thanks @mahle07 for sharing us.
Greetings from @mahle07. share us campus life to @Abrhaley_Arefaine and say hi to your friends . For more join us 👇👇👇👇
👉👉 @MUSUofficalchannell
Welcome back Dear Connection! Nice to meet you again Dears!
የትምህርትና ስልጠና መስኩን ከኮቪድ 19 በኃላ ለማስጀመር በሚከናወኑ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምክክር መድረኩ ዛሬ በአዲስ አበባ ሲጀመር እንደአገር የወረርሽኙ ስርጭትንና የሴክተሩ ትምህርት የማስጀመር ዝግጅት እንደሚዳሰስበት ጠቁመው "ከመንግስት አቅጣጫ አግኝተን የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ስንከፍት ተማሪዎችን በምን ሁኔታ መቀበል እንዳለብን እንመክራለን" ብለዋል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መልሰው ሲከፈቱ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ፣ የአስተዳደርና አካዳሚክ ጉዳዮች ላይም ምክክር ይደረጋል ተብሏል፡፡

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሳይጠናቀቅ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደአገራችን በመግባቱ የ2012 ዓ.ም ትምህርት እንዴት ይጠናቀቅ በሚለው እና የ2013 ዓ.ም እንዴት ተጀምሮ ይቀጥል የሚለው ላይ ትኩረት አድርጎ እቅድና መመሪያዎችን አዘጋጅቶ መስራት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል በወረርሽኙ ምክንያት የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢቋረጥም ትምህርትን በኦንላይን ከማስቀጠል ጎን ለጎን ዩኒቨርስቲዎች የለይቶ ማቆያ እና ማገገሚያ ማዕከላት በመሆን፣ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን በማምረት፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችና በምርምር በመሳተፍ እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌቱ በትናትናው ዕለት ለተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ ያበረከተውን ድጋፍ አውስተው "እንኳን ደስ አለን" ብለዋል፡፡ በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናቸውንም አቅርበው ድጋፉ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል፡፡

ወ/ሪት ራሔል ለማ ከጤና ሚኒስቴር "የኮቪድ 19 ስርጭት በአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ያለው እንድምታና ዓለምአቀፍ ተሞክሮ" በሚል ርዕስ የዓለምአቀፉን ተሞክሮና በአገራችን የኮቪድ 19 ወቅታዊ የስርጭት ሁኔታን የዳሰሰ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ያለእድሜ ጋብቻና የምገባ ፕሮግራም መቋረጥ ማስከተሉንና እንዲሁም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው በመቆየታቸው የትምህርት ብቃትና ችሎታ ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ እየጨመረ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ ደረጃ (ፒክ) ላይ አለመድረሱን ገልፀው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ መውረድ ያሳየባቸው አንዳንድ አገራት የተለያዩ ጥንቃቄዎችን አድርገውና የንፅህና መጠበቂያዎችን በማሟላት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከከፈቱ በኃላ መልሰው የዘጉ አገራት መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ግን በኦንላይን እያስቀጠሉ እንደሆነ ገልፀው የገፅ ለገፅ ትምህርት መክፈት የሚያስቡ አገራት ራሳቸውን ገምግመው የሚያስጀምሩበት የተዘጋጀ ዓለምአቀፍ መመሪያ መኖሩንም ገልፀዋል፡፡

ወ/ሪት ራሔል የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ ለመክፈት እንዲቻል ለማድረግ መሰራት አለባቸው ያሏቸውን የተለያዩ ምክረኃሳቦችን አቅርበዋል፡፡ ከምክረኃሳቦቹ መካከል ከእቅድ ፖሊሲና ማስተባበር አንፃር፡ ከጤና ተቋማት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንዳለበት፣ ፖሊሲ እቅዶችና መመሪያዎች ሲዘጋጁ ሰራተኞቻቸውን ያገናዘቡ ሊሆኑ እንደሚገባ፣ የታቀዱት ስራዎች በመመሪያው መሰረት መሟላታቸውንና እየተሰሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሁለት ሜትር ርቀት ለማስጠበቅ የማይቻል ከሆነ ሰፋፊ አዳራሾችን መጠቀም፡ አንዴ ብቻ የሚያገለግሉ የምግብ ማቅረቢያዎችን መጠቀም፤ ምዝገባ ኦንላይን እንዲሆን ማድረግ፣ አንዳንድ ኮርሶችን በከፊልም ይሁን ከተቻለ በሙሉ ኦንላይን ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በመኝታ ክፍሎች የሚኖርን የተማሪዎች ብዛት መቀነስ፣ ከተቋማት ውጪ ከማህበረሰቡ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት መቀነስ፣ ታጥበው ተመልሰው አገልግሎት ላይ የሚውሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ የእጅ ንፅህና መጠበቂያዎችን ማሟላት እና የሚከፈቱ መስኮቶችና በሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ ከቀረቡት ምክረኃሳቦች መካከል ይገኙበታል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ሊታዩ የሚገባቸው ብለው ባቀረቧቸው ምክረ ኃሳቦች መሰረትም የወረርሽኙ የመጨመር ፍጥነት፣ የለይቶ ማቆያ የሆኑ ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለማዘጋጀት የሚፈጅው ጊዜ እና የአከፋፈት ሂደቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም አንዴ ከተከፈተ በኃላ ተጠርጣሪ ቢገኝ ምን ማድረግ እንችላለን የሚለው ሊታሰብበት እንደሚገባና ለዚህም ከአሁኑ ዝግጅት መጀመርና ከፌደራል ጀምሮ የተዋቀረ እና የራሱ መመሪያ የተዘጋጀለት የዝግጅትና ትግበራ ሂደት ተዘጋጅቶ ሊሰራበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን እየተከላከሉ ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት መከናወን ያለባቸው የአካዳሚክና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ያሉበት ዝግጅት የቀረበ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ትምህርት ማስጀመር ይቻላል ተብሎ ሲፈቀድ ለማስጀመር እንዲችሉ መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርቦበታል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዩኒቨርስቲዎች የኮቪድ 19 ምልክት የሚታይባቸው ተማሪዎች ቢገኙ የለይቶ ማቆያ የሚሆኑ ቦታዎችን ከአከባቢያቸው ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር በግቢያቸው እንዲያዘጋጁ የሚል ይገኝበታል፡፡

በመድረኩ 5 ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡

በ2 ቀን የምክክር ቆይታቸው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 2 ግምገማ፣ የ10 ዓመት የልማት እቅድ ፣ የ2013 እቅድና ዝግጅት ምዕራፍ፣ የትምህርትና ስልጠና መረጃ ስርዓት፣ የትምህርት፣ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር ፖሊሲ፣ የትምህርት፣ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ ደንብ፣ ተቋማትን በትኩረትና በተልዕኮ ማደራጀት ቀጣይ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠናቅቀው ወደስራ ሊገቡ ዝግጁ የሆኑ ፖሊሲዎች ደንቦችና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች ቀርበው ውይይት የሚካሄድባቸው ይሆናል፡፡
#MoSHE
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት እንደገና ለማስጀመር ከጤና ተቋማትና አጋር አካላት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጎልበት እንዳለባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ተቋማቱ ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል የተደረገው ዝግጅት ለመንግሥት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው ይላል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተቋርጦ የነበረውን የተቋማቱ ትምህርት ዳግም ለማስጀመር የሚደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ግብረ ኃይል ባለብዙ ዘርፍ ተሳትፎ ቡድን አባል ወይዘሪት ራሄል ለማ እንዳሉት አገሮች ትምህርት ቤቶችን የሚከፍቱት የበሽታው ስርጭት መቀነስ ሲጀምር ነው።

በኢትዮጵያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ወረርሽኙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመሆኑ መቼ የመጨረሻው ስርጭት ላይ እንደሚደርስ በትክክል አይታወቅም ብለዋል።

ወረርሽኙ ከተከሰተበት መጋቢት 4 ቀን 2012 ጀምሮ እስካሁን ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥርም

ከ 0 ነጥብ 3 በመቶ እንደማይበልጥም ገልጸዋል።

በመሆኑም የተቋረጠውን ትምህርት በተቋማቱ እንደገና ለመጀመር ከጤና ተቋማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት መፈተሽ አለባቸው ብለዋል።

ከፖሊሲና እንዲሁም የዕድሜና ተጓዳኝ የጤና እክል ያለባቸውን የተቋማቱን ማኅበረሰብ አባላት ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተቋማት የራሳቸውን ዝርዝር እቅድ እንደሚያዘጋጁ ገልጸዋል።

ዕቅዱ በሽታውን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ መዘጋጀቱንና የተጋላጭነት ሁኔታው ለመንግሥት ቀርቦ ፈቃድ ሲያገኝ ተማሪዎችን ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች በበኩላቸው ተቋማቱ የኮቪድ-19 ሕክም ማዕከላት ሆነው እያገለገሉ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋማቱ ማገገሚያ፤ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ሆነው ስለሚያገለግሉ በቀላሉ ለትምህርት ዝግጁ ማድረግ ከባድ እንደሆነ አመልክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ተማሪዎች የሚገባቸውን እውቀት ገብይተው ወደ ቀጣዩ ደረጃ መሸጋገር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ለዚህም “በተለየ ሁኔታ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ትምህርቱንም በተለየ ሁኔታ መስጠት ይጠይቃል” በማለት አሳስበዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርቱን የጨረሱ ተማሪዎች በሰባት ቀናት፤ ከ51 እስከ 75 በመቶ የተማሩ በ20 ቀናት፤ 20 በመቶ የቀራቸው በ45 ቀናት፤ እንዲሁም የመጀመሪያውን ወሰነ ትምህርት ያልጨረሱና ሁለተኛውን ያልጀመሩ በሁለት ወራት ማጠናቀቅ እንዲችሉ ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
Join us @MUSUofficalchannell
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️

MOSHE በሰጠው መግለጫ የኮሮና ሁኔታ ታይቶ ተማሪዎች በ 2013 ወደ ግቢ እንደሚመለሱ ይጠበቃል

🎲ተማሪዎች በሁለት ምድብ ወደ ግቢ ይገባሉ

🔗ምድብ 1:- የ 4ኛ ፣ 5ኛ አመትና ከዛ በላይ ያሉ ተማሪዎች( ይህ ምድብ ማንኛውንም ተመራቂ ተማሪዎች ያጠቃልላል)።

🔗 ምድብ 2:- ከ 1ኛ --3ኛ አመት ተመራቂ #ያልሆኑ ተማሪዎች

በዚህም መሰረት ምድብ 1 ወደ ግቢ ገብተው ሁለት ወር ተምረው ሲመለሱ ምድብ 2ቶች ይቀጥላሉ

📍የትምህርት ሁኔታው ከ ሰኞ--እሁድ የሚሰጥ ሲሆን በ 2013 የ 2012'ን ና የ 2013'ን ኮርስ እንጨርሳለን ተብሏል።

🖊በአጭሩ መስከረም ላይ የኮሮናን ስርጭት በማየትና የመንግስት ይሁንታ ታክሎ ተማሪዎች ወደ ግቢ ሊመለሱ ይችላሉ

ዩኒቨርስቲዎች ማቆያ ሆነው ሳለ ተማሪዎች ወደ ግቢ ስገቡ እነዚህ ታማሚዎች የት ይሆናሉ የሚልም ጥያቄ ነው?

ሌላ መረጃዎችን እየጣረን ስለሆነ በቅርቡ እናደርሳቹሀለን

###
ግቢ ገብታቹህ ለሚጠብቃቹህ ጫና ካሁኑ በራሳቹህ እንድትዘጋጁ አደራ ተብላቹሃል

Via ©ATC
EID Mubarak
🕋🕋• EID AL ADHA •🕋🕋

🕌 ኢድ ሙባረክ🕌

• ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሕብረት ስም እንኳን ለ 1441 የ ኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ‼️

• በዓሉን የሰላም የጤና እና የፍቅር እንዲሆን ከልባችን እንመኛለን ‼️

መልካም በዓል
የ2012 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለ2 ወራት ተምረው እንዲመረቁ አቅጣጫ ተቀመጠ!

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው በቤታቸው የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎችን ያቋረጡትን ትምህርት ከ45 ቀን እስከ 2 ወር በሆነ ጊዜ ውስጥ ተምረው በማጠናቀቅ እንዲመረቁ አቅጣጫ መቀመጡን 'አዲስ ማለዳ ጋዜጣ' በዛሬው ዕትሙ መረጃውን ይዞ ወጥቷል።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለፀው ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች በተቀመጠው ጊዜ ያለፋቸውን ትምህርት አጠናቀው ወደ 2013 የትምህርት ዘመን እንዲሸጋገሩ ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው አቅጣጫ ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመለሱ ቀን እንዳልተቆረጠለት ተመላክቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለስ እንዳለባቸው ኮቪድ-19 ያለበትን ደረጃ ያገናዘበ የመንግስትን ውሳኔ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ ነው ተብሏል #AddisMaleda
Forwarded from MIT Information Posting board
@hidaseismydam join this amazing national group for our voice abt the #GERD. thanks Evander @vovoye for creating this group. we are one!
Join us @MUSUofficalchannell
Forwarded from CHANNEL 29
ትግራይ ሚዲያ ሃውስ (TMH) መደበኛ የሳተላይት ስርጭት ጀምሯል፤

Eutelsat 8W
Frequency : 11595
Polarization : Vertical
Sybol Rate : 27500
FEC : Auto

TMHን
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE (Bereket Gudisa)
በኦንላይን የሚሰጥ ትምህርትን የሚደግፍ መመሪያ ተግባራዊ ተደረገ!

የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ያስችላል የተባለለትና ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ በኦንላይን ትምህርት እንዲሰጥ የሚያስችል መመሪያ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ ትምህርትን የሚደግፍ መመሪያ ያልነበረ ሲሆን፣ ከዚህ በኃላ ግን መመሪያው የሚጠይቀውን ሁሉ አሟልቶ ፍቃድ ያገኘ ተቋም የከፍተኛ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማካሄድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኦንላይን የእውቅና ፍቃዳቸውን የሚያድሱበትና የሚያወጡበት ምቹ ሁኔታም እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአገር ውስጥ የሚኖሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎችን መረጃ በሙሉ በማዕከል ለመያዝ የሚያስችል እና በየወቅቱ ትምህርት ላይ ያሉትን ለመቆጣጠር የሚያግዝ ዌብ ቤዝድ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡ - #MOSHE

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Forwarded from Dereja
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Few weeks left for Dereja's National Virtual Career Expo 2020, In partnership with Jobs Creation Commission - Ethiopia supported by Mastercard Foundation. Stay Tuned.

#Dereja
#DerejaAcademy
#virtualcareerexpo
#youthdevelopment
Forwarded from DW Info®
2024/09/26 23:18:57
Back to Top
HTML Embed Code: