Telegram Web Link
#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

ይኸው ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን በትግራይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ዛሬ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ፋና ብሮድካስቲንግ የዘገበው።

በትምህርት ሚኒስቴር  የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ " ቡድኑ ወደ መቐለ የሚያቀናው በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለመምከር ነው " ብለዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ቡድን በመቐለ ቆይታው ከመቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ትምህርት ዳግም መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ገልፀዋል።

በተጨማሪ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ትምህርትን ዳግም ለማስጀመር በሚቻልበባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቅንቶ በዩኒቨርሲቲው ዳግም የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጉ መጠቆሙን ፋና ብሮክዳስቲንግ ዘግቧል።

Via -@tikvahethiopia
- @tikvahuniversity
Mekelle University Student Union
Dear students Our e-student web is working so if their is any thing you want you can acess it. Website address : mymu.edu.et/auth/login Join @MUSUofficalchannell
alot of questions comes basically
I. Some of you forget your password
II.some of you can't access from remote area
Answer
I. U can get the new password only from the registrar office and this is done physically.if there is any option you can have the new password we are trying our best. so please wait untill there is any solution we can give you.
2. I think its been long time the system isnt functioning and the system is now to busy so please try it when the traffics is free.

Thank you!!
Join @MUSUofficalchannell
አምስት አባላትን የያዘው የትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በመቐለ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው።

በሚኒስቴሩ የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የተመራው ቡድን በመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ዳግም ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው፡፡

ወደ መቐለ ያቀናው ቡድን በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋና ሀጎስ (ዶ/ር)፣ ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛይድ ነጋሽ (ዶ/ር) እና ከሌሎች የክልሉ የትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

የትምህርት ዘርፍ ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ሰምተናል።

Source -@tikvahuniversity
Join @MUSUofficalchannell
በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ) ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
Greeting message from Mekelle University.
መቐለ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ልኽቀቱ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከወራት በኋላ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባወጣው መልዕክት፤ የተቋሙን ልኽቀት ለመመለስ የሁሉንም የትብብር ድጋፍ ጠይቋል፡፡

ባለፉት ሁለት አስቸጋሪ ዓመታት በሀሳብ እና ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብረው ለነበሩ ዓለም አቀፍ አጋሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡
በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ስራ ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ስራ ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል እንደገለጹት፥ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ስራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

 በዚህም መሰረት መጀመሪያ የባለሙያዎችና ቀጥሎም አምስት አባላት ያሉት የአመራር ቡድን በክልሉ በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በቦታው በመሄድ የጉዳት ዳሰሳ ጥናት ማድረጉን አንስተዋል፡፡

ልዑካኑ ከመቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራትና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር በፍጥነት ስራ ማስጀመር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከሩን ጠቁመዋል፡፡

 የመቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራትና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ የዳሰሳ ጥናት በዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች እና አባላት ቀርቦ ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

 በተቋሙ የተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ ዩኒቨርሲቲዎቹ ወደነበሩበት እስከሚመለሱ የማያቋርጥ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግ አቅጣጫ መቀመጡንም ስራ አስፈጻሚዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

 ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በማቀድ በቀጣይ ወደ ስራ በሚገቡበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

Source-FBC
#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

ስለሆነም ተማሪዎች ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደባችሁበትን ተቋም ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website: https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ

result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint

የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Cut Point for Remedial Program
#Grade-12
(Remedial )ፕሮግራም ና ዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
Prof. Domenico pioneered a visit to Mekelle University after an over two years communication blackout in Tigrai.
Prof. Domenico Patassini from lUAV University of Venice,Italy has visited Mekelle University to reinitiate the
partnership between the two universities. In his staying from Jan 23rd to Feb1st 2023, he held a series of discussions with the president of our university Dr. Fana Hagos, the Scientific Director of ElIT-M
Dr. Haddush Goitom and dean of the School of Architecture and Urban Planning Mr. Tuumay Allene. He also undertook a collective and individual consultive meeting with his PhD students from the school. In her discussion with Prof. Domenic, Dr. Fana Hagos extended her appriciation to him and the university of IUAV for their pioneer initiation to reinistate the partnership.
The president moreover underscored that Mekelle University is also undertaking necessary preparations to resume networking with all our partners.

Source- Mekelle University official
FB page
#AKSUM UNIVERSITY

Aksum University is loading for resumption!

In fact, it was hard to stay being disconnected from the
connected world for a couple of years. But now, we are on board in the digital world, and we will continue to be dedicated to find new ways to enact its mission of teaching, research and community service engagements.

Join @MUSUofficalchannell
✍️To hear News about
Tigrai Universities
#Axum University
Vacancy
Join @MUSUofficalchannell
#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444

ትምህርት ሚኒስቴር
Hello every body how is every thing on going
#AKSUM UNIVERSITY
call for Financial and Material Support
2024/09/23 01:28:33
Back to Top
HTML Embed Code: