Telegram Web Link
Forwarded from Deleted Account
ጥብቅ ማሳሰብያ!ውድ ግቢ የገባችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች!!
#ኣሁን በዩኒቨርሲቲያችን የምስተዋሉ ያሉት የኮቪድ-19 ቸለልትነት በሃላ ዋጋ እንደሚያስከፍል ኣምናችሁ ለሚከተሉትን መመሪያዎች እንዲትተገብሩ የዩኒቨርሲቲው መመሪያ ያስገድዳል::
1,ማንም ተማሪ ከግቢ መውጣትና መግባት ከቀን 25/02/2013ዓ/ም ለ7ቀናት የተከለከለ ነው::ከ7ቀናት በሃላ ግን ሁኔታውን ታይቶ ልሻሻል ይችላል::
2,ማንኛውም ተማሪ ማስክ የማድረግ÷ኣለመጨባበጥ÷ኣለመተቃቀፍ÷ኣለማሳሳም ግደታ ኣለበት::
3,ማንኛውም ተማሪ በካፌ÷በWifi እና ሌሎች ተራርቆ መቀመጥና መሰለፍ ግደታ ኣለበት::
4,ማንኛውም ተማሪ ከተመደበበት ዶርም መቀየርና ማደር የተከለከለ ነው::
5,በሁሉም ዘርፎች የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል የወጡ ደንቦች ካላከበረ በዩኒቨርሲቲው መምሪያ እና በሳይንስና ከፍተኛ ት/ት ሚ/ር የወጣ ደንብ በቀጥታ ከዩኒቨርሲቲው ይባረራል::ስለዚህ ውድ ተማሪዎቻችን "ታሞ ከማማቀቅ ኣስቀድሞ መጠንቀቅ"ነውና ኣስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን::

Join @MUSUofficalchannell
#LawExitExam 

የህግ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam ) ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይጀምራሉ። በኮቪድ ምክንያት የትምህርት ተቋማት ከተዘጉ በኋላ ወደ 2013 የተዛወረው ፈተና ቀጥሎም በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ዳግም ሊራዘም ችሏል።

በዚህ ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም። እስካሁንም ፈተናውን ላመለጣቸው ተማሪዎች ያሉ አማራጮች እንዲህ ተብለው አልተጠቀሱም።

የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ፈተናው ከታህሳስ 13-16 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወሳል።

ለተፈታኞች መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ምኞታችን ነው!
ለሁሉም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች

በሐገራችን በኮሮና ስጋት ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲዘጉ በመወሰኑ ምክንያት ወደየ አካባቢያችን መመለሳችን ይታወቃል።

ከኮሮና መልስ ጥቅምት 23-24 ተመራቂ ተማሪዎች ቅድሚያ ገብተው እንዲመረቁ #ትምህርት_ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎች ወደ መማር ማስተማር ሂደቱ ኣንዲመለሱ ውስኖ እንደነበር እሚታወቅ ነዉ ሁኖም#ጥቅምት 24 በተፈጠረው ግጭት ትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ያልደረሱ ተማሪዎች በቤታቸው እንዲቆዩ መወሰኑን እንዲሁም።

ከዛም ኋላም ተቀቡላቹ የነበሩት ተማሪዎች በተፈጠረው ሁኔታ ሳይረብሹ የመማር ማስተማር ሂደቱ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጓዝ ዩኒቨርስቲያችን አስተዳደር እና ማሕበረሰብ የበኩሉን አስተዋኦ ማረግ ይታወቃል።
#ነገሮች ሲረጋጉ እና ወደ ነበሩበት ሲመለሱ በጊቢው ውስጥ የነበሩትን ተማሪዎች ሊያስመርቅ ችሏል ::

#ሆኖም ኣንዳንድ ተማሪዎቻችን በነበሩ ሁናቴዎች በመስጋት ተምርታቸውን ትተው ወደየ ትውልድ ቀያችው መመላሳቸው የሚዘነጋ ኣይደለም። በዚህም ምክንያት ሊመርቁ አልቻሉም ዩኒቨርስቲያችንም ይህን በመገንዘብ ተማሪዎች ተመልሰው ገብተው ያቋረጡትን ትምህርት ጨርሰው እንዲመርቁ ወስኗል ::
# ይህንም ተገንዝባችሁ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው እራሱ ማስታወቅያ አውጥቶ እስኪጠራችሁ በያላችሁበት በትእግስት ኣንድትጠበቅ እናሳስባለን ::

አመሰግናለሁ
Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
# የተመራቂ ተማሪዎችን ሽኝትን (farewell) በተመለከተ

ዩኒቨርስቲያችን ለ 28 ተኛ ግዜ ያስመረቃቸውን ተማሪዎቹን ዛሬ 14/04/13 ዓ.ም ወደየ ኣካባቢያቸው እንዲመለሱ ማረግ ችሏል :: ዩኒቨርስቲያችን የተማሪዎቹን እንግልት ለመቐነስ መዳረሻቸውን በተወሰነ ቦታዎች በማረግ የባስ Service አገልግሎት እንዲያገኙም አድርጓል:: በፀጥታው ረገድ ያለውን ሁናቴ ምቹ እንዲሆን እና ተማሪዎች ከስጋት ነፃ ሆነዉ እንዲጓዙ ከፀጥታ ኣካላት ጋ በመሆን እንዲሸኙ ተደርጓል::
# ለምሳሌ መደረሻቸውን ኣዲስ አበባ የሆኑትን ተማሪዎያች እስከ #ኣላማጣ


Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
#መቐለ #አዲግራት #አክሱም

ዛሬ ከ MoSHE እና ከ መቐለ , ኣዲግራት, ኣክሱም ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እየተካሄደ በለው ውይይት ብዙ ከተነሱ ሓሳባች መካከል ስለ አዲግራት እና ኣክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ኣንዱ ነበር።

ለዚህም ጉዳይ እንደ መፍትሄ ተደርጎ የተወሰነው የአክሱም እና የአዲግራት ተመራቂ ተማሪዎች ወደ መቀሌ ዩንቨርሲቲ በመሄድ ተቋርጦ የነበረውን ትምርታቸው ኣጠናቃው እንዲመረቁ ነዉ ::
በቀጣይም ስለ ፦
📌የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች፤
እና
📌 የአክሱም እና ኣዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ፤
# ውሳኔዎች እንደሚኖሩ ተስፋ እንናደርጋለን ውሳኔዎች እንደተወሰኑ ለተማሪዎቻችን በፍጥነት እንደምንገልፅ ማሳወቅ እንወዳለን ::

Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
ለሁላችሁም የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበራችሁ በአለመረጋጋቱ ሳቢያ ቤታችሁ ለምትገኙ

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለ28ተኛ ግዜ 3291 ተማሪዎችን ማስመረቑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በነበረዉ አለመረጋጋት ሳቢያ የተወሰናችሁ ተመራቂ ተማሪዎች ወደየ ቤታቸው መሄዳችሁ የማይዘነጋ ነዉ ።
*በተጨማሪ ብዙዎቻችሁ እንዴት እና በምን መልኩ እንደምትረቁ እና መቼ ልትጠሩ እንደምትችሉ እየጠየቃችሁ ትገኛላችሁ ::
*ዩኒቨርስቲያችን ከዚ ቀደም እንደገለፀው ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ መግለፁ ይታወሳል።

📌 ስለዚ ውድ ተማሪዎቻችን ዩኒቨርስቲያችን ተመራቂ ተማሪዎቹን በተቻለ መጠን ቀድሞ ለመቀበል እና #ልዩ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ እየሰራ መሆኑን በመገንዘብ ተማሪዎች ከሚናፈሰዉ ወሬ እና ከኣንዳንድ ነገሮች እራሳችሁን ነጻ በማድረግ ዩኒቨርስቲው ህጋዊ በሆነ ማስታወቅያ ወይም በዩኒቨርስቲው ማህበራዊ ሚዲያ የመግቢያ ቀን እስኪገለፅ ትንሽ እንድትታገሱ በትህትና እንጠይቃለን ::

Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
ለ አዲግራት ተመራቂ ተማሪዎች ሁሉ

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፏል።

በ2012 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጥገና ላይ ስለሆነ ትምህርታቸውን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተምረው እንደሚመረቁ MoSHE አሳውቋል።

ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 1 የምዝገባ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ኩሃ ግቢ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ጥር 2 ትምህርት ይጀምራል።
ማስታወቅያ

ዩኒቨርስቲያችን በጠየቀው መሰረት MoSHE ከ ትራንስፖርት ሚንስተር ጋር በመተባበር ኣስር (10) ባሶችን እንደሚያገኝ ታውቋል::
እነዚህ ባሶች በአሁኑ ሰዓት መንገድ ላይ እንደሆኑ እና እሁድ ገብተው እንደሚያድሩ ማወቅ ችለናል።እኝህም ባሶች በተለያየ ምክንያት ወደየ ቀያቸው መሄድ ላልቻሉ ተማሪዎች የሽኝት ኣገልግሎት ለመስጠት ነው ።

አገልግሎቱን የሚሰጣቸው ተማሪዎች :-
1. መደረሻቸውን ደቡባዊ ትግራይ የሆኑ ፤
2. ከክልል ውጪ ላሉት ተማሪዎችን ደግሞ እስከ አዲስ አበባ ለሆኑ፤
3. የትግራይ ተማሪዎች ሆነው ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የሚሄዱ ካሉ፤

ይህን በመገንዘብ ያልተመዛገባችሁ ተማሪዎች በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የተማሪ ህብረት ቢሮዎች እንድትመዘገብ እናሳስባለን ::
N.B፦
📌ባሶቹ ልክ #ሰኞ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ከየ #ጊቢው እንደሚነሱ አውቃችሁ ተማሪዎች አስፈላጊዉን የሆነውን ዝግጅት ሁሉ እንድታደረጉ እንጠይቃለን።
📌 እንዲሁም ጊቢው ውስጥ ላሉት ተመራቂ ተማሪዎች ጓደኞች እና ወላጆችን የሆናችሁ ይህን ተገንዝባችው ተማሪዎችን እንድታሳውቁልን በትህትና እንጠይቃለን ።

Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
ማስታወቂያ

የመቐለ ዩኒቨርስቲ የ 2012 ዓ.ም ተመራቂሁናችሁ በወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተመረቃችሁ ተማሪዎች፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ካቋረጣችሁበት በመቀጠል ጨርሳችሁ እንድትመረቑ የአጭር ግዜ ልዩ ፕሮግራም ስለተዘጋጅ ጥር 5/2013 ዓ.ም በኣካል ተገኝታችሁ እንድትመዝገቡ ጥሪ እናቀርባለን።

Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
Announcement

Mekelle University has arranged a Short Special Study Completion Program for Class of 2020 students who missed their graduation due to the recent unrest. We call upon those who missed the graduation to avail in campus and register.

#Registration date: Jan. 13, 2021

Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.
ለራያ ዩኒቨርስቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ተደረገ።

የራያ ዩኒቨርስቲ ጥር 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚያካሂድ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ተገኝተው ምዝገባ እንዲያካሂዱ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን መደበኛ ትምህርት ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ከአቻ ባቾቻቸው ጋር ጥሪ ይደረግላቸው ዘንድ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አሳስቧል።
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
ፅ/ቤት
።።።።

ለመቐለ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞችና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላም አደረሳችሁ!

ባለፈው አመት ሊመረቁ የነበሩ ነገር ግን በ Covid - 19 ወረርሽኝና በጸጥታ ችግር ምክንያት ማጠናቀቅ ያልቻሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አገባድደው ሊመረቁ እንደቻሉ ይታወቃል።
# እንኳን ደስ አላችሁ ለማለትም እንፈልጋለን #

ዩኒቨርስቲያችን ባደረገው ከፍተኛ ዝግጅት ተመራቂ ተማሪዎቹን ቀደም ብሎ መቀበል ችሎ ኣንደነበር ማስታወስ ይቻላል። እንዲሁም በተቻለ መጠን ከነበረው ኣለመረጋጋት ቶሎ በመውጣት በሙሉ ኃይሉ በመስራት ሊያስመረቅ ይችላል። በተጨማሪም ቀሪ ተማሪዎቹን ለመቀበል ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።

ዩኒቨርስቲያችን ያለፈውን ዓመት ትምህርት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በሚደርገው ጥረት ውስጥ ተማሪዎች የሚኖራችሁ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያምናል። ስለሆነም ይሄንን በመገንዘብ ተማሪዎቻችን ሙሉ ጊዚያችሁን በሚባል ደረጃ ለትምህርት እንድትጠቀሙበት እናሳስባለን።

በዓሉ ሲከበር በመተሳሰቡ፣ በመተጋገዝ፤
ርቀታችን በመጠበቅ፤ ሊሆን ይገባል ::


መልካም በዓል
ለሁላችንም !!!

አብርሃለይ አረፋይኔ
የኢት/ከፍ/ትም/ተቋ/ተማ/ህብረት ም/ፕሬዝዳንት እና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳንት
ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም
#adigrat university
የዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ መቐለ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ አሪድ እየገብ ይገኛሉ።

አብርሃለይ አረፋይኔ
የኢት/ከፍ/ትም/ተቋ/ተማ/ህብረት ም/ፕሬዝዳንት እና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳንት
#adigrat university #mekelle university

We are welcoming our Adi-grat University Students by mobilizing our Volunteer Mekelle University Students Union at main Campus.

Office of Mekelle University Student's Union.
2024/09/23 19:20:56
Back to Top
HTML Embed Code: