Telegram Web Link
#ምን_የቀረ_ምክር_አለ⁉️
     አሚር ሰይድ

ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ የገጠር ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ ﷺ መጣና “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በምድርም ሆነ በዘልአለማዊው ዓለም (አኺራህ) የሚጠቅመኝ ነገር ልጠይቅህ መጣሁ” አላቸው፡፡ እሳቸውም “ያሻህን ጠይቅ" አሉት፡፡

እሱም
ከሰዎች በላይ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡ እሳቸውም
>>“አላህን ፍራ ከሰዎች በላይ አዋቂ ትሆናለህ' አሉት፡፡

ከሰዎች የበለጥክ ሀብታም ለመሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“አላህ የሰጠህን ነገር በፀጋ የምትቀበል ሁን፤ ከሰዎች የበለጥክ ሁብታም ትሆናለህ" አሉት፡፡

“ከሰዎች የበለጠ ፍትሀዊ  ሰው መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ለራስህ የምትወደውን ለሌሎች ሰዎች ውደድ! ከሰዎች የበለጠ ፍትሀዊ ሰው ትሆናለህ' አሉት፡፡

ከሰዎች የበለጥኩ መልካም መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"ለሰዎች ጠቃሚ ሁን፤ ከሰዎች በበለጠና መልካም ትሆናለህ" አሉት፡፡

ከሰዎች በበለጠ ወደ አላህ የቀረብኩ መሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“አላህን ማስታወስን አብዛ፣ ከሰዎች በበለጠ ለአላህ የቀረብክ ትሆናለህ" አሉት፡፡

እምነቴ ምሉእ እንዲሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“ሥነ-ምግባርህን መልካም አድርግ ! እምነትህ ምሉእ ይሆናል" አሉት፡፡

መልካም ከሚፈፅሙት መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"አላህ የማታየው ብትሆንም እንኳ እሱ ያይሃልና እንደምትመለከተው አድርገህ ተገዛው፧ መልካም ከሚፈጽሙት ሰዎች መሆን ትችላለህ" አሉት፡፡

“አላህን በቅን ከሚታዘዙት መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው::
>>“አላህ ግዴታ ያደረገብህን ተግባራት ፈፅም፣ አላህን በቅን ከሚታዘዙት ትሆናለህ" አለት፡፡

“አላህን ከኃጢአት የጠራሁ ሆኜ ለመገናኘት እፈልጋለሁ አላቸው፡፡
>>“ሚስትህ ጋር ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከፈፀምክ በኋላ ለመንፃት ብለህ ታጠብ፤ ከኃጢአት የፀዳህ ሆነህ አላህን ትገናኘዋለህ" አሉት፡፡

“በትንሳኤ ቀን (የውመል ቂያማህ) ብርሃን ውስጥ ሆኜ ከሞት መቀስቀስ እፈልጋለሁ'' አላቸው፡፡
>>“ራስህን አትበድል፤ ማንንም ሰው አትበድል፡ በትንሳኤ ቀን በብርሃን ውስጥ ሆነህ ትቀሰቀሳለህ" አሉት፡፡

ጌታዬ በትንሳኤ ቀን እንዲያዝንልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “ለራስህ እዘን፤ ለባሪያዎቹም እዘን፤ በትንሳኤ ቀን ጌታህ ያዝንልሃል" አሉት፡፡

ኃጢአቶቼ እንዲያንስልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “ምሕረት መጠየቅን አብዛ፤ ኃጢአቶችህ ያንሱልሃል" አሉት፡፡

"ከሰዎች በበለጠ ቸር ለመሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ችግሮችህን ለፍጡራን አቤት አትበል፤ ከሰዎች በበለጠ ቸር ትሆናለህ" አሉት፡፡

"ከሰዎች በበለጠ ብርቱ መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"በአላህ ላይ ተመካ፤ ከሰዎች በበለጠ ብርቱ ትሆናለህ" አሉት፡፡

“አላህ ሲሳዬን እንዲያሰፋልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ንፅሕናን አብዛ፤ አላህ ባንተ ላይ ሲሳይህን ያሰፋልሃል'' አሉት፡፡

“አላህንና መልዕክተኛውን ከሚወዱ ሰዎች መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“አላህና መልዕክተኛ የሚወዱትን ውደድ፤ አላህንና መልዕክተኛውን ከሚወዱ ሰዎች ትሆናለህ" አሉት፡፡

“በትንሳኤ ቀን ከአላህ ቅጣት የተጠበቅኩ መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “አላህ ከፈጠራቸው ፍጡራኖች በአንዱም ላይ አትበሳጭ" አሉት፡፡

“ዱዓዬ ተቀባይነት እንዲያገኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ሁሉንም ክልክል የሆኑ ነገሮች ከመመገብ ራቅ፧ ዱዓህ ተቀባይነትን ያገኛል" አሉት፡፡

“ጌታዬ በትንሳኤ ቀን እንዳያጋልጠኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “በትንሳኤ ቀን ጌታህ እንዳያጋልጥህ ከፈለግክ ብልትህን ከዝሙት ጠብቅ” አሉት፡፡

“ጌታዬ በትንሳኤ ቀን ገመናዬን እንዲደብቅልኝ እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>የወንድሞችህን ገመና ደብቅ፡ አላህ ያንተን ገመና በትንሳኤ ቀን ይደብቅልሃል" አሉት፡፡

ከኃጢአቶችና ከስህተት ነፃ የሚያደርግ ነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡
>>"እንባ፣ ቅን ታዛዥነትና በሽታዎች ናቸው" አሉት፡፡

በአላህ ዘንድ በላጩ ምንዳ የትኛው ነው? አላቸው፡፡
>>“መልካም ሥነ-ምግባር፣ መተናነስና በመከራ ጊዜ ትዕግስት ማድረግ ናቸው˚ አሉት፡፡

በአላህ ዘንድ በጣም ትልቁ ኃጢአት የትኛው ነው?" አላቸው፡፡
>>መጥፎ ሥነ-ምግባርና ስግብግብነት ናቸው አሉት፡፡

በምድራዊውና በዘልዓለማዊጡ ዓለማት የአላህን ቁጣ የሚያበርዱ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?" አላቸው::
>> "በድብቅ የምትሰጥ ሰደቃህ (ምፅዋት) እና ዝምድናን መቀጠል ናቸው" አሉት፡፡

በትንሳኤ ቀን የጅሀነምን እሳት የሚያጠፋ ነገር ምንድን ነው?" አላቸው፡፡
>>“በምድራዊው ዓለም ችግርና መከራ ሲያጋጥም ትዕግስት ማድረግ ነው” አሉት፡፡"

ሀምሌ17/11/2016
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ትልቅ_አስተምህሮ
  አሚር ሰይድ

ዐብዱረሕማን ኢብኑ ሰሙራህ (ራዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺአንድ ቀን ወደኛ መጥተው የሚከተለውን ነብያዊ ንግግር አደረጉልን። እንዲህም አሉን-

“ዛሬ ቀን አንዳች የሚገርም ሕልም አይቻለሁ እርሱም

➊. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የሞት መልአክ ሕይውቱን ሊነጥቀው ወደርሱ _ መጣ _ ለወላጆቹ የነበረው ቅን ታዛዥነት ወደርሱ በመምጣት የሞት መልአክ የሰውየውን ሕይወት እንዳይወስድ ሲከለክልለት ተመልክቻለሁ !

➋. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ሰይጣኖች ከበውት ሳለ የአላህ ማስታወስ ወደርሱ በመምጣት ሰይጣኖችን ከርሱ አባረረለት፤

➌. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የጀሀነም መላእክት ከበውት ሳለ የሚሰግዳት ሰላት ወደርሱ በመምጣት ከእጃቸው ስትነጥቀው ተመልክቻለሁ

➍. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በጥም ሳቢያ ከአንድ ኩራ አጠገብ ሊጠጣ ሲል ተባረረ፡፡ ጾም ወደርሱ በመምጣት ሲያጠጣው ጥሙንም ሲያረካለት ተመልክቻለሁ

➎. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ነብዮች በቡድን በቡድን ተቀምጠው ሳለ ወደ አንድ ቡድን በሄደ ቁጥር እንዳይቀመጥ ይከለከልና ይበረር ነበር፡፡ ለጀናባ ያደረገው ትጥበት ወደርሱ በመምጣት ከኔ ጐን ሲያስቀምጠው ተመልክቻለሁ !

➏. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊቱም፣ ከጀርባውም፤ ክቀኙም ከግራውም _ ከሁሉም : አቅጣጫው : ጨለማ አካብቦት ነበር፡፡ ያደረጋቸው ሐጅና ዑምራ መጥተው ከጨለማ አውጥተው ወደ ብርሃን ሲያስገቡት ተመልክቻለሁ

➐. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በእጆቹ የእሳት ነበልባልን ሲከላከል የሰጣት ምጽዋት ወደርሱ መጥታ በእሱ ላይ ጥላ ስትሆን ተመልክቻለሁ

➑. ከሕዝቦቼ መካከል አንድ ሙእሚኖችን ሲያናግር እነሱ ግን አያናግሩትም ነበር። ሲቀጥለው የነበረው ዝምድናን የመቀጠል ተግባር ወደርሱ በመምጣት ሙእሚኖች ሆይ! እሱ ዝምድናውን ሲቀጥል የነበረ ሰው ነውና እናግሩት ጨብጡትም ሲላቸው ተመልክቻለሁ

➒. ክሕዝቦቼ መካከል አንዱ የጀሀነም ዘበኞች አዋክበውት ላለ ሲፈፅመው የነበረው በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ተግባር ወደርሱ በመምጣት አከዘበኞቹ እጅ ነፃ ሲያደርገውና ወደ እዝነት መላእክት ሲያስረክበው ተመልክቻለሁ!

➓.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊቱ አንዳች ግርዶሽ ኖሮ ሳለ መልካም ሥነ-ምግባሩ ወደርሱ በመምጣት እጁን ይዞ ወደ ጌታው ሲያስገባው ተመልክቻለሁ

➊➊.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የሠራው ሥራ መዝገብ በግራ እጁ መጣለት፡፡ ለአላህ ያለው ፍራቻ ወደርሱ በመምጣት መዝገቡን በቀኝ እጁ ሲያደርግለት ተመልክቻለሁ፤

➊➋.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የመልካም ሥራዎቹ ሚዛን ክብደት ሲያንስ ከአብራኩ የተገኙት ልጆቹ ሲሞቱ ያደረጋቸው ትዕግስቶች ወደርሱ በመምጣት ክብደቱ ከፍ እንዲል አደረጉ፡፡ በዚህም ከቅጣት ሲድን ተመልክቻለሁ፤

➊➌.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በእሳት ላይ ሲንሳፈፍ አላህን ፈርቶ ያፈሰሳት እንባው ወደርሱ መጥታ ያለበትን እሳት በማጥፋት ከእሳት ነፃ ስታወጣው ተመልክቻለሁ፣

➊➍.ከሕዝቦቼ መካከል እንዱ በጀሀነም አፋፍ ላይ ሳለ አላህን በፅኑ የመፈለጉ ባሕሪው ወደርሱ  በመምጣት ከጀሀነም እንዲርቅ ሲያደርገው ተመልክቻለሁ፤

➊➎.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በሲራጥ ላይ ልክ ኃይለኛ ነፋስ ሲመጣ ከወዲያ ወዲህ እንደምትወዛወዝ የቴምር ዛፍ እሱም ሲንቀጠቀጥ በአላህ ላይ ያለው መልካም ጥርጣሬ ወደርሱ በመምጣት እንዲረጋጋና ባለበት እንዲረጋ ሲያደርገው ተመልክቻለሁ፤

➊➏.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ሲራጥ ላይ በደረቱ ሲሳብና ሲድህ በኔ ላይ ያደረገው ሶላት (አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ) ወደርሱ በመምጣት በትክክል በሲራጥ ላይ እንዲሄድ ስታደርገው ተመልክቻለሁ፤

➊➐.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊት የጀነት በሮች ሲዘጉ በእርግጥ ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም እኔም የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን አረጋግጦ የሰጠው ምስክርነት ወደርሱ በመምጣት የጀነት በሮችን ከፍታ ጀነት እንዲገባ ስታደርገዉ ተመልክቻለሁ ብለዉ ተናግረዋል፡፡


ይህ ነብያዊ ሐዲስን አቡ ሙሳ አል-መድየኒይ (ረ.ዐ) “አት-ተር ጊቡ ፈር-ል- ኺሷል አል-መንጂይያህ" በተሰኘው መፅሀፋቸው የዘገቡት ሲሆን ኢብኑ ተይሚይያህ (ረ.ዐ) ይህን ነብያዊ ሐዲስ ትልቅ ቦታ ከመስጠታቸው ባሻገር "ለትክክለኛነቱ በርካታ ማስረጃዎች አሉ'' በማለት ተናግረዋል፡፡

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
💚 #ሀቢቡና_ሙሀመድ

    አሚር ሰይድ

ኢብኑ ኢስሀቅ እንደዘገቡት ሐሊመንት ቢንት አል ሀሪስ ስለ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ አስተዳደግ እንዲህ ሰትል አስተላለፈች


    «ድርቅ በሆነበት ዓመት ከሌሎች የበኒ ሰዕድ እንስቶች ጋር ሆኜ የማደጎ ልጅ ፍለጋ ወደ መካ መጣን፡፡ ከደከመች ነጭ አሀያ ላይ ሁኜ ነበር የመጣሁት። ልጄ እና አንዲት ያረጆች ግመል አብራን ነበረች። ምንም ወተት አትታለብም ነበር። ልጃችን ሲርበው ስለሚያለቅስ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ የለንም። ጡቴ ምንም ነገር የለውም፡፡ ግመሌም ጋቷ ደርቋል" አላህ ከዚህ ጭንቅ እንደሚገላግለን ተስፋ እናደርግ ነበር።

መካ ደረስን። የአላህ መልዕክተኛ ﷺበማደጎ ልጅነት ቀርበውላት አልወስደውም ያላለች ሴት አላውቅም። የቲም ነው ሲባሉ ሴቶች ሁሉ ይተዉታል። «እናቱ ምን ታደርግልኛለች?» በማለት። ምክንያቱም የማደጎ ልጅ የምንወስደውም ከአባቱ አንዳች በጎ ነገር ፍለጋ ነው፡፡

ሁሉም ባልንጀሮቼ የማደጎ ልጅ አገኙ። እኔ ብቻ ቀረሁ። ከነቢዩ ውጭ ሌላ አጣን። ባዶ እጃችንን ልንመለስ ስንል ባሌን ሁሉም ባልንጀሮቼ የማደጎ ልጅ አግኝተው እኔ ባዶ እጄን አልመለስም» አልኩት፡፡ እናም ይህን የቲም ልጅ ለመውሰድ መወሰኔን ነገርኩት።

«ጥሩ አስበሻል። ምናልባትም አላህ በርሱ ስበብ በረከትን ይስጠን ይሆናል» አለ። ሄድኩና ያዝኩት። ሌላ ልጅ ስላጣሁ ብቻ ነው ይህን የቲም ለመውሰድ የተገደድኩት። ይዤው ወደ መኖሪያዬ ስሄድ ጡቴ ወተት ቋጠረ። ይህ ልጅ እስኪጠግብ ጠጣ። ወንድሙም እንዲሁ ጠጣ። ባለቤቴ ወደ ግመሏ ሄደ። ጋቷ ሞልቶ አገኘው፡፡ አለባትና ለኔም ለርሱም ጠጣን።

ጥሩ ሌሊት አሳለፍን። ሲነጋ “ሐሊማ ሆይ! የተባረከ ልጅ ያገኘሽ ይመስለኛል። እርሱን ካገኘን በኋላ እንዴት ዓይነት ደግና በረከታማ ሌሊት እንዳሳለፍን አላየሽምን?» አለኝ።

አላህ በረከቱን ያክልልን ጀመር። ወደ አገራችን ስንመለስ አህያዬ ጉልበት ጨመረች። ፈጥና ትገሰግስም ገባች። ባልንጀሮቼL «ይቺ የመጣሽባት አህያ አይደለችምን?» ይሉኝ ነበር። እርሷው መሆኗን ስነግራቸው አንዳች ነገር እንዳገኛት ይነግሩኛል። በዚህ ሁኔታ ከበኒ ሰዕድ ምድር ደረስን አገራችንን ገባን"

በአላህ እምላለሁ በዚሀች ምድር ላይ እንደቀያችን ደረቅ ወይም ምድራ በዳ የሆነ ምድር ያለ አይመስለኝም። ይህም ሆኖ ግን ፍየሎቼ ውለው ሲገቡ ጠግበውና ወተታቸው ሞልቶ ነው፡፡ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የፍየሎቻቸው ጋቶች ደርቀው ጠብታ ወተት እንኳ በማይሰጡበትና በሚራቡት ሁኔታ የኔ ፍየሎች ይጠግባሉ፡ ይታለባሉ፡፡ ከኔ ፍየሎች ጋር እንዲያሰማሩ ይመክሯቸው ነበር"

እረኞችም ፍየሎቻቸውን ከኔ ፍየሎች አጠገብ ያሰማራሉ። ግን የነርሱ ተርበው ይመለሳሉ" ጠብታ ወተት እንኳ አይሰጡም። የኔዎቹ ግን ጋቶቻቸው ሞልተውና ጠግበው ይመለሳሉ፡፡አላህ የተለያዩ በረከቶችን እያሳየን ይህ ልጅ አደገ"


አስተዳደግ ከሌሎች ልጆች የተለየ ነው። ሁለት ዓመት ሲሞላው ምግብ መመገብ የሚችል ሆነ። ጡት መጥባቱን አቆመ። ልጁን ባየንበት በረከት የተነሳ በጣም ብንፈልገውም ለእናቱ መመለስ ስለነበረብን ይዘነው ሄድን።
.... እናቱ ስታየው ሌላ አንድ ዓመት ከኛ ጋር ይቆይ ዘንድ ፍቀጅልን! የመካ ወረርሽኝ እንዳያገኘው እንሰጋለታለን» አልናት። በአላህ እምላለሁ! ደጋግመን ጠየቅናት። በመጨረሻ ፈቃደኛ ሆነች። መልሼ ወሰድኩት። ሦስት ወራት ያህል ቆየን።



      አንድ ቀን ከቤታችን ጀርባ ከልጅ ጋር በመጫወት ላይ እያለ ልጁ በድንጋጤ ተዉጦ መጣ...ሙሐመድን ሁለት ነጭ ልብስ የለበሱ ሰዎች መጥተው ካስተኙት በኋላ ሆዱን ቀደዱት» አለ።
....እኔና ባሌ ደንግጠን ወደርሱ በረርን። ቆሞ አግኘነው። ገፅታው ተለውጧል።ባሌ አቀፈውና ምን አገኘህ?» ሲል ጠየቀው፡ ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች መጡና

አስተኝተውኝ ሆዴን በመቅደድ አንዳች ነገር አውጥተው ጣሉት። ከዚያ በኋላ እንደነበር መለሱለት» አለን። ወደቤት መለስነው።
....ባሌም ሐሊማ ሆይ! ልጁ አንዳች ነገር አግኝቶት እንዳይሆን እሰጋለሁ» አለኝ። የምንፈራው ነገር ከመከሰቱ በፊት ለቤተሰቦቹ ልንመልሰው ተስማማን። ተሸከመን ወሰድነው፡፡ ከእናቱ ዘንድ ስንደርስ፣ ምን ሆናችሁ አመጣችሁት? ከናንተ ጋር እንዲቆይ ጓጉታችሁ አልነበረምን?» አለችን።

«አዎ፣ በእርግጥ ብለን ነበር። አላህ ፍላጎታችንን ሞልቶልናል። አንዳቸ ክፉ ነገር ሳያገኘው በፊት ወደናንተ እንመልሰው ብለን ነው» አልን።
«ምን ሆናችሁ ነው? እውነቱን ንገሩኝ?» አለች። እንድንነግራት አጥብቃ ጠየቀችን። የሆነውን ነገርናት። «ሰይጣን ሰግታችሁለት ነውን? ይህን ልጅ ሰይጣን አያገኘውም። የተለየ ተሰጥኦ ያለው ልጅ ነው.

በማለት በእርግዝናዋ ወቅት ያጋጠማትን አጫወተችን «እርግዝናዬ በጣም ቀላል ነበር። አንድ ቀን በሕልሜ አንዳች ብርሃን ከኔ ዘንድ ወጣ። የሻምን ሕንፃዎች ሲያበራ አየሁ፡፡ አወላለዱም ከሌሎች ልጆች የተለየ ነው፡፡ እጆቹን ተመርኩዞና ራሱን ወደሰማይ አቅንቶ ነበር» አለችን።»

ሀቢቡና ሙሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም

ይህ ሐዲስ በበርካታ የሐዲስ መስመሮች ተላልፏል። እጅግ ሰፊ ተቀባይነት ካላቸው ሐዲሶች መካከል አንዱ ነው፡፡



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#አላህን_የት_ትወነጅለዋለህ??
አሚር ሰይድ


ከዕለታት አንድ ቀን እንድ ሰው ወደ ኢብራሃም ኢብኑ አድሀም( አላህ ይዘንላቸውና) በመምጣት ለመፈፀም የሚፈልገውን የኃጢአት ዓይነት ጠቀሰላቸው፡፡
....እሳቸውም “አላህን ለመወንጀል ከፈለግክ እሱ በፈጠራት ምድር ላይ እንዳትኖር፤ እሱ በፈጠራት ሰማይ ሥርም አትቁም' አሉት፡፡

ሰውየውም በመገረም “አላህ ከፈጠራት ምድር ሌላ ምድር አለን? እንዲሁም ከፈጠራት ሰማይ ሌላ ሰማይ አለን?" ሲል ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም “ታዲያ ይህን ካወቅክ በእሱ መሬት ላይ እየኖርክ በርሱ ሰማይም ስር እየተጠለልክ ልትወነጅለው ይቻልሃልን?!' አሉ፡፡ ሰውየውም ፈፅሞ አይቻለኝም በማለት በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጡትን ምክሮ አዲለግሱት ጠየቀ፡፡


እሳቸውም “አላሁን ለመወንጀል ከፈለግክ ከሲሳዩ አንዳች ነገር አትመገብ አሉት፡፡ ሰውየው እንደገና በመልሳቸው በጣም በመገረም “ለአላህ ጥራት ይገባው! ከአላህ ሲሳይ ውጭ ሌላ ሲሳይ ይገኛልን?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
.....እሳቸውም በምድሩ ላይ እየኖርክ፤ በሰማዩም እየተጠለልክ፤ ከሲሳዩም እየተመገብክ ልትወነጅለው ይቻልሃልን?!' አሉት::


ሌላ ምክር ይጨምሩልኝ አላቸው፡፡
....እሳቸውም ምክራቸውን ቀጥለው "አላህን (ሱ.ወ) ለመወንጀል ከፈለግክ መለከል መዉት ወደ አንተ ሲመጣ ንስሀ እስከማደርግ ድረስ ትንሽ ጊዜያት ጠብቀኝ" በለው ወይም ከርሱ አምልጥ" አሉት።

ሰውየውም  በጣም  የሚገርም ነው! የሰው ልጅ የሕይወት ፍፃሜ ሊዘገይ ይችላል?! ፍፁም የማይመስል ነገር ነው:። ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል አይደለምን?

فَإِذَا جَاۤءَ أَجَلُهُمۡ لَا یَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةࣰ وَلَا یَسۡتَقۡدِمُونَ

"ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት ጊዜ አንዲትን ሰዓት ‎ አይቆዩም አይቀድሙም(አን ነህል 61)

“አራተኛውን ምክርዎትን ይጨምሩልኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም "በአላህ (ሱ.ወ) ምድር ላይ እየኖርክ በሰማዩም እየተጠለልክ ሲሳዩንም እየተመገብክ እሱን ልትወነጅል ይቻልሃልን!? ካሉት በኋላ "አላህን (ሱ.ወ) ለመወንጀል ከፈለግክ የጀሀነም ዘበኞች ወደ ጀሀነም እሳት ይዘውህ ሊሄዱ ሲሉ ከነርሱ አምልጥ ወይም ወደ ጀነት ሽሽ አሉት፡፡ ሰውየውም “ለአላህ ጥራት ይገባው! እነሱ እኮ


عَلَیۡهَا مَلَـٰۤىِٕكَةٌ غِلَاظࣱ شِدَادࣱ لَّا یَعۡصُونَ ٱللَّهَ مَاۤ أَمَرَهُمۡ وَیَفۡعَلُونَ مَا یُؤۡمَرُونَ
በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ሀይለኞች የሆኑ መላእክት አሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምፁም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ(አት ተህሪም6)

የተባሉት መላእክት ናቸው" አላቸው፡፡ እሳቸውም “በርሱ ምድር ላይ እየኖርክ፣ በሰማዩ እየተጠለልክ፤ የመሞቻ ቀን እየተቃረበ መሆኑን እያወቅክ፤ ከጀሀነም ዘበኞች ማምለጥ እንደማትችል እየተረዳህ አላህን (ሱ.ወ) ልትወነጅል ይቻልሃልን?" አሉት፡፡ ሰውየውም “ፍፁም አይቻለኝም ካላቸዉ ቡሀላ በዚህ የኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ምክር ወደ አላህ(ሱ.ወ)ተዉባህ አድርጎ አላህ(ሱወ)በመታዘዝ ላይ በርትቶ ብዙ አመታት ከቆየ ቡሀላ ሞተ፡፡


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

#አላህን_ምህረት_ጠይቅ

አንድ ሰው ወደ ሐሰነ-ል-በስሪይ (ረ.ዐ) መጥቶ የዝናብ መቋረጥን በምሬት ነገራቸው እሳቸውም “አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡
....ሌላ ሰው መጣና የውሀ ማነስን በምሬት ነገራቸው፡፡ ለእሱም “አላህን ምሕረት ጠይቅ” አሉት፡፡
......ሶስተኛ ሰው መጣና የልጆቹ ቁጥር ማነስ በምሬት ነገራቸው፡፡ ለእሱም እንደሌሎቹ "አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡
.....አራተኛ ሰው መጣና “ምድሪቱ ምርት ከመስጠት ደርቃለች" በማለት በምሬት ነገራቸው፡፡ እሱንም ለአንደኛው ለሁለተኛውና ለሶስተኛው ሰው እንዳሉት “አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡



ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ አብረዋቸው የነበሩት “ሐሰነል-በስሪይ ሆይ! የሚጠይቅዎት ስው በመጣ ቁጥር “አላህን ምሕረት ጠይቅ" ይላሉን?" በማለት በግርምት ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም ይህ የአላህ ቃል አልገባችሁምን? ብለው የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ ለሰዎቹ አነበቡላቸው፡፡


{ فَقُلۡتُ ٱسۡتَغۡفِرُوا۟ رَبَّكُمۡ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارࣰا }{ یُرۡسِلِ ٱلسَّمَاۤءَ عَلَیۡكُم مِّدۡرَارࣰا
{ وَیُمۡدِدۡكُم بِأَمۡوَ ٰ⁠لࣲ وَبَنِینَ وَیَجۡعَل لَّكُمۡ جَنَّـٰتࣲ وَیَجۡعَل لَّكُمۡ أَنۡهَـٰرࣰا }


አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»(ኑህ10-12)


ወንድሜ እህቴ ሆይ አላህን ምህረት መጠየቅ እናብዛ


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ዲናሩል_ከዕቢይ
አሚር ሰይድ

ዲናሩል-ከዕቢይ (አላህ ይዘንላቸውና) በኃጢአትና በወንጀል ላይ የተዘፈቁ ሰው ነበሩ፡፡ ከልጅነታቸው አንስቶ የምትመክራቸው እናት የነበራቸው ቢሆንም የእናታቸውን ምክር ፈፅሞ አይቀበሉም ነበር፡፡

    ከዕለታት አንድ ቀን ብዙ የአስክሬን አጥንቶች ባሉበት የቀብር ስፍራ  በኩል ሲያልፉ አንዱን አጥንት አንስተው ካደቀቋት በኋላ " #አንቺ_ነፍሴ_ሆይ! ወየውልሽ!" አሉ፡፡ ለትንሽ ጊዜያትም ፍፃሜያቸውንና መመለሻቸውን በምናባቸው አስታወሱ፡፡


ለራሳቸውም “ #ነፍሴ_ሆይ! እስከ አሁንም ድረስ በስሜት ላይ ነሽን?'' ካሉ በኋላ "ጌታዬ ሆይ! በራሴ ላይ የፀፀትኩ ሆኜ አግኝቻለሁ፡፡ የሕይወቴን ቁልፎች ላንተ አስረክቤያለሁና ተቀበለኝ፤ ሸሽገኝም፤ አንተ ከአዛኞች በላይ እጅግ አዛኝ የሆንክ ጌታ ሆይ!" ብለው መፀፀታቸውን ለአላህ (ሰ.ወ) ተናገሩ፡፡ ተውባህ አድርገው ጠባያቸውን አርመው ለሊትን በሰላት የሚያሳልፉ ሆነው፣ ሰውነታቸው እስኪደክም ድረስ አላህን (ሱ.ወ) በመገዛት ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡

ዘወትር " #ዲናር_ሆይ! የጀሀነም እሳትን የምትሸከምበት ኃይል አላህን?! እንደለለህ ካወቅክ እንዴት ራስህን ለአላህ ቁጣ አጋለጥክ?" በማለት ራሱን እየጠየቀ ተንሰቅስቆ ያለቅስ ነበር፡፡

     በዚህ ሁኔታ ለብዙ ጊዜ ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እናታቸው “ለራስህ ትንሽ እዘን አሏቸው፡፡ እሳቸው ግን
" #እናቴ_ሆይ! ትንሽ እንድደክም ተይኝ ምናልባት ለረዥም ጊዜያት ላርፍ እችላለሁና፡፡

እናቴ ሆይ! አላህ (ሱ.ወ) ፊት እቆማለሁ፣ የሚያስጠልል ጥላ አገኝ ወይም አላግኝ አላውቅም፡፡ እረፍት የሌለበት ችግር እንዳያጋጥመኝ እፈራለሁ" አሏቸው፡፡

....እናታቸውም “ #ልጄ_ሆይ! እጅጉን በጣም ራስህን አድክመሀል” በድጋሚ አሏቸው፡፡ እሳቸውም “እናቴ ሆይ! እረፍት እፈልግ ነበር.
.. እናቴ ሆይ! ምናለ እኔን ከመውለድ መኻን በሆንሽ ኖሮ! ለልጅሽ ረዥም ጊዜያት የሚፈጅ እስር ቀብር ውስጥ ተዘጋጅቶለታል፡፡ ከዚያም አላህ ፊት ለረዥም ጊዜ የመቆም ኃላፊነት አለበት” አሏቸው፡፡ ዲናር አብዛኛውን ጊዜ ሶላት ውስጥ

{ فَوَرَبِّكَ لَنَسۡـَٔلَنَّهُمۡ أَجۡمَعِین
{عَمَّا كَانُوا۟ یَعۡمَلُونَ
በጌታህ እንምላለን!ሁላቸዉንም እንጠይቃቸዋለን፡ይሰሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ(አል-ሐጀር 92-93)

የሚለዉን የቁርአን አንቀፅ እያነበቡ ራሳቸዉን ስተዉ ይወድቁ ነበር፡፡


#Share
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሏሁ አክበር 10 ጊዜ
አልሀምዱሊላህ 10ጊዜ
ሱብሀን አሏህ 10ጊዜ ካልክ ቡሀላ ዱአህን ጀምር
አላህ ዱአህን ይቀበልሀል!!


https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
#አሳፋሪ_ጥያቄና_አጥጋቢ_መልስ
      አሚር ሰይድ


    ከዕለታት አንድ ቀን ሮማዊው _ ቄሳር _ ለሙዓዊያህ (ረ.ዐ) የሚከተለውን የደብዳቤ መልዕክት ላከለት፡፡ “አቅጣጫ፣ አባት የሌለዉ፣ ወላጅ ስሌለው፥ ቀብሩ ውስጥ ደስተኛ ስለሆነው በማህፀን ውስጥ ስላልተፈጠሩ ሶስት ነገሮች ሙሉ፣ ግማሽና ባዶ ስለሆነ ነገሮች ንገረኝ። የማናቸውንም ነገሮች መፈጠሪያ ዘር የሆነችውንም በብልቃጥ አድርገህ ላክልኝ።''

ሙዓዊያህ (ረ.ዐ) የደብዳቤውን መልዕክት ካነበበ በኋላ መልስ ይሰጡበት ዘንድ መልዕክቱን ለዑብደላህ ኢብነ ዐብባስ (ረ.ዐ) ላከው፡፡



    ዐብደላህ ኢብነ- ዕብባስ (ረ.ዐ) የደብዳቤውን መልዕክት አንብበው የሚከተለውን ምላሽ ለሮማዊው ቄሳር ፃፉለት፡፡
☞“አቅጣጫ የሌለው ነገር የተከበረው ከዕባህ ነው፡፡
☞ አባት የሌለው ዒሳ(ዐሰ) (ኢየሱስ)ናቸው፡፡
☞ወላጅ የሌለው አደም (ዐ.ሰ) ናቸው፡፡
☞በቀብሩ ውስጥ ደስተኛ የሆነው ዩኑስ (ዐ.ሰ) ናቸው።
☞ በማህፀን ውስጥ ያልተፈጠሩት ሦስት ነገሮች
➊ የነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በግ
➋የነብዩላህ ሷሊሕ ሴት ግመልና
➌የነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) ዘንዶ ናቸው።
☞ሙሉ የሆነው ነገር አእምሮ ኖሮት በዚህ አእምሮው የሚጠቀም ሰው ሲሆን፥ ግማሹ ነገር አእምሮ የሌለው ግን አእምሮ ባላቸው ሰዎች የሚሠራ ሰው ነው፡፡
☞ ባዶ ነገር ደግሞ አእምሮ የሌለውና አእምሮ በሌላቸው ሰዎች አእምሮ የሚሠራ ነው፡፡

ከዚያ በአንዲት ብልቃጥ ውስጥ ውሀ ከሞሉ በኋላ “ይህች የማናቸውም ነገሮች መፈጠሪያ ዘር ነች በማለት ከፃፉለት በኋላ መልዕክቱን ወደ ቄሳር ላኩት።

ቄሳሩ ዐብደላህ ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) በሰጡት ምላሽ በጣም ተደነቀ።


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#የሱን_እሬሳ_ምድር_አትቀበለዉም
          

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺከኢስላም ያፈነገጠውን ሰው ሬሳ ምድር እንደማትቀበል መናገራቸው
የነብዩﷺ ተአምር ጭምር ነዉ፡፡

      ኢማም አህመድ እንደዘገቡት አነስ ኢብኑ ማሊክ የሚከተለውን አስተላልፈዋል

    የበኒ ነጃር ጎሣ አባል የሆነ አንድ ሰው   ከመካከላችን ነበር። አል. በቀራህንና አል ዒምራንን ምዕራፎችን አጠና (ቀራ)፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ፀሐፊ ነበር። ከሙስሊሞች ሸሽቶ ሄደና ከክርስቲያኖች ጋር ተቀላቀለ"

ክርስቲያኖቹም የሙሐመድ ራዕይ ፀሐፊ ነበር» በማለት የክብር ቦታ ሰጡት፡ብዙም ሳይቆይ ሞተ። ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት። ምድር ግን አልተቀበለችውም ተፋችው። እንደገና ቀበሩት አሁንም ተፋችው። ከዚያ በኋላ ግን ሳይበብሩ ተውት።


     ይህ የሆነበትን ምክንያት ዐብባስ ሲናገሩ፡ ይህ ሰው በቀራንና አል ዒምራንን ያጠና (የቀራ) በመሆኑ እኛም ለርሱ ልዩ ክብር ነበረን። የአላሀ መልዕክተኛ ﷺ «መሐሪና አዛኝ» የሚል ቃል እንዲፅፍ ሲያዙት «መሐሪና ጥበበኛ» እያለ ይፅፋል። ወዋቂና ጥበበኛ» ብሎ እንዲጽፍ ሲያዙት፡ «ሰሚና ተመልካች» ብዬ ልፃፍ ይላቸዋል...

«ይህ ሰው ከኢስላም አፈነገጠና ከጣዖታውያን ወገነ። «ስለ ሙሐመድ ልንገራችሁ። ራዕይ ፀሐፊው ነበርኩ። የፈለግኩትን ነበር የምጽፈው» በማለት የነቢዩን ስም ማጥፋት! የሐሰት ጥላሸት መቀባት ጀመረ።

ይህ ሰዉ ሲሞት ነብዩ ﷺ ምድር አትቀበለዉም በማለት ተናገሩ።

አነስ እንዳሉት አቡ ጦልሐ ሰውየው ወደሞተበት ሀገር መሄዱን ነግሮኛል። ሜዳ ላይ ተጥሎም አገኘው። «የዚህ ሰዉ ነገር ምንድን ነው?» ሲል ጠየቀ። «ደጋግመን ብንቀብረውም ምድር ልትቀበለው አልፈቀደችም። መልሳ እየተፋች አስቸገረችን» አሉት



ቡኻሪ አነስን በመጥቀስ እንደዘገቡት፡ ሰውየው ክርስቲያን ነበር ሰለመ። በቀራንና አል ዒምራንም አጠና። የነቢዩ ፀሐፊም ሆነ። ተመልሶም ወደ ክርስትና ገባ። ሙሐመድ እኔ የፃፍኩለትን ብቻ እንጅ ሌላ ነገር አያውቅም» ይል ነበር። አላህ ይህን ሰው ገደለው፡፡ ቀበሩት። ምድርም ተፍታው አደረች።

«ይህ የሙሐመድና የባልንጀሮቹ ድርጊት ነው። ከነርሱ ስለሽሽ ከመቃብሩ አውጥተውት ነው» አሉ፡፡ ይበልጥ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረውም ቀበሩት። ምድር በድጋሜ ተፍታው አደረች። «ይሀ የሙሐመድ እና የባልንጀሮቹ ድርጊት ነው። ከነርሱ ስለሽሽ ሬሳውን አውጥተው ጣሉት» አሉ። ይበልጥ ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ ቆፈሩና ቀበሩት። ምድር ለሶስተኛ ጊዜ ተፋችው" በዚህ ጊዜ የሰው ድርጊት እንዳልሆነ አወቁና ሬሳውን ወረወሩት፡፡


ሱበሀነሏህ!!!


https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መላኢካዉ አላህን ጀነትን አሳየኝ ያለበት ታሪክ

Join👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
#ቤት_እንግዳ_የመዉሰድ_ጥቅም


   ሚስት ባሏ እንግዳ ይዞ እየመጣ ስልችት ብሏት ስሞታ ለማቅረብ ወደ ረሱል ﷺ መጣች ችግሯን ዘርዘር አድርጋ  ነገረቻቸው፡፡ ነብዩ ﷺ ዝም ብለው ሰምተዋት ምንም አልመለሱላትም

ሴትዮዋ ከሄደች በኋላ ለባሏ አስጠርተው ዛሬ አንተ ቤት እንግዳ ነኝ አሉት ....ባል በጣም ተደስቶ ለሚስት ነገራት ሚስትም በጣም ተደሰተች ራሕመተል ዓለም እቤቷ ሊገቡ ነዋ ቤት  ያፈራው ነገር በደስታ አዘጋጀች

ነብዩ ﷺ ገብተው ከተስተናገዱ በኋላ ለባልየው ስወጣ ሚስትህ እኔ በምወጣበት በር ወደዛ እንድትመለከት ንገራት አሉት
    ረሱል ﷺ ሲወጡ ሚስት ትመለከታለች ከኋላቸው ጊንጥ እንሽላሊት ሌላም ጎጂ ነፍሳቶች ተከትሏቸው ሲወጡ አየች ሚስት ደንግጣ ዞረባት
....ከዚያም ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ:- "አንድ እንግዳ ከተጠራበት ቤት ሲወጣ ልክ እንደዚህ ከዛ ቤት ችግር በላ እና ጎጂ ነፍሳቶች ተከትለዉት ይወጣሉ"
  እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው አሉ

በሌላ ዘጋባ ረሱል ﷺ እንዲህ ይላሉ
አላህ ኸይር የፈለገለት ሰው ስጦታ ይልክለታል ሲሉ
... ያስጦታ ምንድን ነው???ተብለው ሲጠየቁ እንግዳ ብለዉ መለሱ

በሌላ ሀዲስ
☞ "እንግዳ የማይገባበት ቤት መላኢካ አይገባበትም"
☞"እንግዳ ወደ ጀነት አመላካች ነው"
☞"በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር" ብለዋል ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

 ⚡️⚡️⚡️ እንግዳ መጋበዝ አለብኝ ብለን የግድ ከአቅማችን በላይ መጣጣር የለብንም ቤት ባፈራው ሊላህ ብለን ብቻ እንግዳውን ቀልቡ ለማስደሰት በኢኽላስ ከሆነ እንግዳው የሚያስደስተው የምግቡ አይነት ሳይሆን እሱን አክብረን መጥራታችን ነው!



አላህ እንግዳን የምናከብርበት ተውፊቅ አላህ ይስጠን


Join👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዱአ ስታደርግ በአሏህ በተቀደሰ ስሙ ጠርተህ ዱአ አድርግ
Join👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
#ቁርአን_በዚና_ጉዳይ_ለምን_ሴቶችን_ተጠንቀቁ_ብሎ_አስቀደመ??
            አሚር ሰይድ
         

#ምንጭ☞በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ

     
     የሰው ልጆች ወደ ዚና አብዝተው የሚሳቡባቸው ሁለት አበይት ምክንያቶች አሉ፡፡

#አንድኛዉ የሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ ነው፡፡
#ሁለተኛዉ ሰይጣን የሰው ልጆችን ከምንም በላይ ጸያፍ ድርጊቶችን እንዲሠሩ ይገፋፋቸዋል፡፡ ከፀያፍ ድርጊቶች መካከል ግንባር ቀደሞቹ ደግሞ ዝሙትና ግብረ ሰዶማዊነት ናቸው፡፡

ዋናዉ የዝሙት መንደርደሪያ ሁለት ናቸዉ

1⃣ የሴቶች አለባበስ
በተፈጥሮ ለወንዶች ሲበዛ ከተሸላለሙለት ነገሮች መካከል ቀዳሚዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡ ወንዶችን በማሳሳትና በማማለል እነርሱን ይበልጥ የሚፈታተናቸው ነገር ደግሞ የሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ ነው፡፡ እናም ዛሬ ዛሬ አብዛኞቹ ሴቶች አለበበሳቸው  መረኑን የለቀቀና አሳሳች በመሆኑ ወንዶች ሲበዛ በሴቶች እየተፈተኑና ወደዝሙትም እየተሳቡ ይገኛሉ፡፡

ማረስረሻው ሒጃብ ስለተነሳ ሒጃብም ሲለበስ አላህ ያዘዘዉን ሒጃብ ባለመሆኑ የዝሙት ዛሩ በየቦታው ተስፋፍቷል፡፡ ዝሙትም በየሜዳው እየተሰበከ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ የሴቶች አለባበስ እጅግ አሳሳችና ወሲብ ቀስቃሽ ከመሆኑ የተነሳ በርካቶች በቀላሉ ዝሙት ላይ እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ የሴቶች አለባበስ ወሲብ ቀስቃሽ ሆነ ማለት እነርሱ በቀላሉ ይከፋፈታሉ፤ ጥብቆችና ንፅሕቶች አይደሉም፤ ጨዋዎችና ታማኞች አይደሉም፤ ገላቸው ለአላፊ አግዳሚው አምሮት መውጪያ ቅምሻ የቀረበ ነው፤ ወዘተ የሚል መልዕክትን ያስተላልፋል፡፡

የሴት ልጅ አለባበስ ወሲብ ቀስቃሽ ከሆነ ወንዱ በገላቸው ፍቅር ይሰከራል፤ ምክንያቱም የወንድ ልጅ ወሲባዊ ፍላጎት የሚነሳሳው በዕይታው ነውና፡፡  በዚህን ጊዜ
☞ ለሴት ልጅ ተገቢውን አክብሮት ከመስጠት ይልቅ እነርሱን እንደ ወሲባዊ ዕቃ አድርጎ መመልከት ይጀምራል፡፡
☞ለሴቶቹ ሰብአዊ ማንነት ግን ምንም ክብር አይሰጥም:: ሴቶችን ያራከስና ገላቸውን ለመደሰቻነት ይጠቀማል፡፡
☞እነርሱን እራቁቶ በገላቸው መዝናናትን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሴቶች ተሳስተው ላለማሳሳት፣ ጠፍተው ላለመጥፋትና ነድደው ላለማቃጠል ከወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ መራቅ አለባቸው፡፡


2⃣/ ሰይጣን የሰውን ልጆች ከምንም በላይ እንዲሠሩት የሚገፋፋቸው ወንጀል ቢኖር ዝሙትን ነው፡፡ ይህንኑ አስመልክቶም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች እትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው (ሀጢአትን ተሸከመ)፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና (አን-ኑር24:21)



🔰🔰#ሴቶች_በዚና_ሳቢያ_እንዴት_ከወንዱ_የበለጠ_እንደሚጎዱ_የሚከተሉትን_ነጥብ_እንመልከት



✏️✏️ ዚና ላላገባች ሴት ለድንግልናዋ መገርሰስ ዋናው መንስኤ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሴቷ በዚና ድንግልናዋን ስታጣ ከወንዱ የበለጠ ተጎጂ ትሆናለች፡፡ ይኸው ጠባሳም ዕድሜ ልኳን አይሽርላትም፡፡

በተለምዶም ሴቶችና ዝሆኖች ጠባሳቸውን ፈፅሞ አይረሱም” ይባላል፡፡ ለጋብቻ ላትመረጥ ትችላለች። ስታገባም ለባሏ የምታበረከተው ትልቁ ወሲባዊ ስጦታዋ (ከብረ ንፅህናዋ) አብሯት አይኖርም፡፡ እናም በዚህ ሳቢያ መላው የጋብቻ ሕይወቷ ይጎዳል፡፡

⚡️⚡️ ዝሙተኛይቱ ያገባች ሴት ከሆነች ደግሞ ለባሏ ትልቅና ቀጣይነት ላለው ውርደት መንስኤ ትሆነዋለች፡፡ በተለምዶም “አንድ እውነተኛ ባል የሚስቱን ምንዝርነት ከሚሰማ ተገድላ መርዶውን ቢሰማ ይሻለዋል» ይባላል፡፡

✏️✏️ ያገባች ሴት ከዚና አርግዛ ልጅን ብትወልድ የባል ቤተሰብ የዘር ሐረግ ንፅህናቸው ይበላሻል፡፡ ያላገባች ከሆነች ደግሞ በቤተሰቧ ላይ ታላቅ ሀፍረትንና ውርደትን ታስከትላለች፡፡ ይህም ቤተሰቦቿን ለበቀልና ለአፀፋዊ እርምጃዎች ያነሳሳቸዋል፡፡ አንዱ ቤተሰቡ ከሌላው ጋር ለመፋጀትም ይበቃል፡፡

⚡️⚡️ በሴት ልጅ ወሲባዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ስህተት ተፈፀመ የሚባለው እርሷ ዜናን ለመሥራት ውሳኔዋን ባሳለፈች ቀን ነው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የሴት ልጅ ወሲባዊ ሕይወቷ የመበላሸት ዕድሉ ሰፊ ነው:: ዝሙተኛ ሴት ለወደፊቱ የሕይወት አጋሯ እራሷን ጠብቃ ማቆየት አትችልም፡፡ ትዳር ወደተባለው ተቋም ስትገባ ዋናው የመግቢያ መስፈርት (ድንግልናው) አብሯት የለም፡፡

✏️✏️ በተለምዶ ሴቶች አራት ዓይነት ናቸው ይባላል፡- ➊ድንግል፤
➋ ዝሙተኛ፡
➌ፈት እና
➍ ፈትም የልጆች እናትም የሆነች፡፡ ድንግሏን ካገበሀት ያንተ ብቻ ናት፡፡ ፍቺም አይኖርም፤ ደባል ባልም አያሰጋህም፡፡ ዝሙተኛዋ ያንተ ልትሆንም ላትሆን ትችላለች፡፡ ሌላው ቢቀር ደባል ባል ይዛብህ ልትመጣ ትላለች:: ዝሙተኛ ሴቶች በቁርኣን አገላለጽ «አል-ኸቢሣት›› (መጥፎዎቹ ሴቶች፣ቆሻሾቹ) ተበለዋል።

ፈት ሴት ያንተ መሆን ብትችልም፣ ግና የቀድሞ ባሏን አትረሳውም፡፡ ፈትም የልጆች እናትም የሆነች ደግሞ ያንተ ብትሆንም ልጆቿንም የቀድሞ ባሏንም አትረሳቸውም፡፡

አሁንም ሴቶችን በአለባበስ ረገድ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሚከተሉና ሒጃባቸውን በወጉ የሚለብሱ ብለን ለሁለት መከፈል እንችላለን። ታዲያ የዚህ ኡማ ወንዶች ትልቁ ፈተናም እነዚህ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሚከተሉ ሴቶች (ቀበጥ ሒጃቢስቶች) መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡

⚡️⚡️ ዝሙተኛይቱ ከዚና አርግዛ ለውርጃ ልትዳረግ ትችላለች፡፡ ይህም በወንጀል ላይ ወንጀልን ያሸከማታል፡፡ ከዚና ከወለደችም ልጁን ለማሳደግ በርካታ ፈተናዎች ታያለች፡፡ በልጁ አስተዳደግና እነፃ ላይ ትልቅ ከፍተት ይፈጠራል፡፡ ይህም በተራው አሳዳጊ የበደለው ልጅ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀል ያደርጋል።

✏️✏️ ሴት በዚና ሳቢያ ከወንዱ የበለጠ ለአባላዘር በሽታዎችና ለኤድስ የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ ወንዱ ኮንዶምን እንዲጠቀምና ጥንቃቄ የተሞላበት ወሲብን እንዲያደርግ የማስገደድ አቅሟም አነስተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ዚናው የሚካሄደዉ ከሞላጎደል በርሱ ፍላጎት መሠረት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማሕፀኗ ሊጎዳና የማሕፀን ግድግዳዋ ሊደማ ይችላል፡፡ ለፊስቱላ በሺታም ልትጋለጥ ተላለች፡፡

⚡️⚡️ ሴት በዚና ሳቢያ ከማንኛውም የወሲብ መንገደኛ ጋር አስሬ በአፍጢሟ ስትድፉ ከብሯ ሁሉ ይቀንሳል፡፡ ዝሙተኛውም ፈፅሞ እንደሰው እይቆጥራትም።

✏️✏️ ሴት በዚና ሳቢያ ለተለያዩ ወሲባዊ አብደቶች ልትጋዝጥ ትችላለች በዝሙተኛውና በዝሙተኛይቱ መካከል ፍቅርና ውዴታ ስለሚይኖር እርነሱ ፈፅሞ አይራራላትም፡፡ ከዚህም የተነሳ የፊንጢጣ ወሲብን ሊሠራባት ይችላል፡፡ የአፍ ወሲብንም ሊሠራባት ይችላል፡፡ የነዚህ ወሲባዊ እብደቶች ጉዳት ደግሞ እጅግ የከፋ ነው፡፡ መላውን ወሲባዊ ሕይወቷን ሊያበላሽ ይችላል፡፡

⚡️⚡️ በተለይ የዘመናችን ዝሙተኞች የተለያዩ የወሲብ ማነቃቂያ ነገሮችን በመውሰድ ሴቶችን እንደሚያሰቃዩ እሙን ነው፡፡ ለምሳሌ ሱስ አስያዥ ዕፅን የወሰደ ወንድ ሴቷን በአንድ የወሲብ ዙር ብቻ እስከ 40 ደቂቃዎች ሊያሰቃያት ይችላል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሴቷ በቀላሉ ትዳከማለች፡፡ አካሏም ሆነ መንፈሷ ሲበዛ ይጎዳሉ፡፡ ይህም በርሷ ምርታማነት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለው፡፡👇👇👇
✏️✏️ ሴት ልጅ በተለይ አሁን ቴከኖሎጂው በብዛት ለመጥፎ ነገር ማስፋፈያነት በሚውልበት አግባብ ውስጥ በለየለት እኩይ ወንድ እጅ ከገባች እርሱም ዚናውን እየፈጸመባት በተጓደኝነትም ያንን ትዕይንት ቀርፆት ያስቀምጠዋል፡፡ ወንዱ ይህንን ካደረገ ደግሞ ከዚህ በኋላ የርሷ ነገር በርሱ እጅ ውስጥ ገባ ማለት ነው፡፡ እንደፈለገ ይጫወትባታል፡፡ ያስፈራራታል፤ ያስለቅሳታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሴቷ ለብላክሜይሊንግ (ማስፈራሪያ) ትጋለጣለች፡፡ ይህም ነገር በተውበት ወደ አላህ (ሱ.ወ) እንዳትለመስ ሁሉ ደንቃራ ይሆንባታል፡፡ በዚያ ቪዲዮ ሳቢያም ሴቷ ወደ ጌታዋ ሁሉ መሸሽ የማትችልበት ሁኔታ ያጋጥማታል፡፡

⚡️⚡️ ዝሙተኛ ሴት ለአስከፊው የሴተኛ አዳሪነትና ለወሲብ ንግድ የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ በተለይ ጉንተላ የሚበዛባት ከሆነ በቀላሉ ወደዚህ ሥራ ልትገባ ትችላለች፡፡ የሴተኛ አዳሪነት ሥራ ጭንቅላት፣ ተያዥ፣ የሕከምና ማስረጃ፣ የሥራ ፈቃድና የመነሻ ካፒታል ስለማይጠይቅም የዝሙት ሱስ ያለባቸውን ሴቶች የመሳብ ችሎታው ከፍ ያለ ነው፡፡

በአጠቃላይ ሴት ልጅ በዝሙተኛ ወንድ እጅ ገባች ማለት የትዳር አጋሯ ባልሆነ፣ በማይወዳት፣ በማያፈቅራት፣ በማይጠነቀቅላትና በማያዝንላት ሰው እጅ ገባች ማለት ነው፡፡ ይህ የወሲብ መንገደኛም ለራሱ ስሜት እንጂ ለርሷ ደህንነት አንዳችም ነገር አይጨነቅላትም፡፡ ለሚመጣው መዘዝም ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ ጉዳት ሲደርስባትም አብሮነቱን አያሳያትም፡፡ ከዚህም የተነሳ በወሲብ መንገደኛ እጅ የገባች ሴት ለአውሬያዊ አያያዝ ትዳረጋለች፡፡ ይህም ሴቶችን በሁሉም መልኩ ይጎዳቸዋል፡: ዚና ሴቶችን የወሲብ ሕይወታቸውን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ማንነታቸውን ጭምር ያራክሳል፡፡ ከብራቸውን ዝቅ ያደርጋል፡፡በገላቸዉ እንጂ በጭንቅላታቸው እንዳያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡ እራሳቸውን እንዲያሻቅጡና አስከፊውን የሴተኛ አዳሪነት ሕይወትን እንዲቀላቀሉ ምከንያት ይሆናቸዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ሴቶች በዚና ሳቢያ ከወንዶች በላይ ተጠቂዎችና ተጎጂዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ሲባል ነው ቁርኣን በዚና ጉዳይ ሴቶችን ያስቀደማቸው፡፡


⚠️⚠️በዚና መስመር ላይ ያለን፡በመንደር ደር ላይ ያለን ከአላህ ጋር እየተጣላን እርዚቃችንን ደስታችንን ከማሸሽ ከዚህ ከዚና አስከፊ በሽታ ሞት ሳይቀድመን ቶብተን እንጠብቀዉ

መታወቅ ያለበት የሴቶች አለባበስ ለራሱ የዚና መንደርደሪያ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡


👌የዚና ጉዳይ ሲነሳ ተፈራርቶ አይሆንም ለሌሎች ሼር ያርጉ አይታወቅም አንድ ሰዉ ወደ ቀልቡ ተመልሶ ከዚና ቢቶብት ሼር ባደረግንበት ከአጅሩ ተጠቃሚ ሆን ማለት ነዉ

ስለዚና ያተኮሩ ርዕሶች ኢንሻ አላህ ይዘጋጃሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/28 01:23:35
Back to Top
HTML Embed Code: