Telegram Web Link
1979 በሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 2

ሙሐመድ አልቃሕጣኒ እና ጁሀይማን አልዑተይቢ የሀረምን ማይኮሮፎን እያበሩ ውስጥ ላሉት የሐረም እንግዶች እና መስጂዱን ከበው ለተቀመጡት የፖሊስ አዛዦች የማስፈራሪያ እና መህዲን ተቀበሉ መልእክት ያስተላልፋሉ። በከባቢው ላይ የተሰማሩት ፖሊሶች ሀረምን መግባት እንችል እንደው ብለው ወደ በሩ ጠጋ ባሉ ቁጥር ሚናራዎች ላይ የተጠመዱት ስናይፐሮች ስራቸውን ይሰራሉ።

በቦታው ያሉት የፖሊስ ሀይላት ጉዳዩ በቀላል እንደማትፈታ ስለገባቸው የሀገሬው ሰራዊት ስራውን እንዲከውን ወደ መከላከያ ሚኒስትሩ ስልካቸውን አንቃጨሉና የሱዑዲያ ወታደሮች በተራቸው ሀረምን ከበው እገታውን ለመስበር ያላቸውን ሀይል ሁሉ አፈሰሱ። ሁኔታው ግን ምንም አልተለወጠም።

በመሆኑም አጋቾቹን ለማዳከም የሀረም ውሀ አገልግሎት እና የመብራት ስርጭት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ተደረገ። ግን የተጠበቀው ውጤት ተቀልብሶ ከአጋቾቹ ይልቅ የሐረም እንግዶች በጥማት እና ረሐብ በየቦታው መወዳደቅ ጀመሩ። ንጉስ ዃሊድ ቢጨንቀው ሽማግሌ አስልኮ ከበዛ ንትርክ በኋላ በመጅጂዱ ክልል ያሉ ህፃናት እና ሴቶች ያለምንም መታኮስ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው። እርግጥ እነ ዑተይቢ ስንቅ እያለቃቸው ስለነበር ከዚህ የተለየ የመደራደሪያ መንገድ አልነበራቸውም።

ሀረም እንዲህ በእገታ በተሟሟቀችበት ወቅት አሜሪካ እና ኢራን የጉዳዩ ጠንሳሽ አንቺ ነሽ! አንቺ ነሽ! እየተባባሉ አጋጣሚውን ለፖለቲካ ጥቅማቸው መጓተቻ ለማድረግ በየሚዲያው ይንተፋተፋሉ።

እንዳይታኮሱበት ሀረም ፤ ዝም እንዳይሉም መንግስት ግልበጣ ሆኖባቸው የተወዛገቡት ባለስልጣናት ጉዳዩን ወደ ፈታዋ ምክር ቤት መርተው የሀረምን ክብር ለማስጠበቅ ሲባል ወታደራዊ እንቅስቃሴ በውስጡ ማድረግን የሚፈቅድ አዲስ ፈታዋ ተቀብለው በየጋዜጣው እና ሚዲያ ማሰራጨት ጀመሩ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 3

«ሀይአት ኪባረል ዑለማ» የሰዑዲ ፈታዋ ምክር ቤት በሀረም ከባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የሚፈቅድ ፈታዋ ሲሰጥ እንዲህ ቀላል አልነበረም። ምክኒያቱም ከአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) የተገኙ ትክክለኛ እና ግልፅ ሀዲሶች በሀረም ዙርያ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይከለክላሉ።  ስለዚህ ፈታዋቸው ከትችት የነፃም ሆነ የዓለም ዑለማዎችን በ2 ጎራ ከፍሎ ከማነታረክ ሊተርፍ አይችልም።

ዞሮዞሮ ፈታዋው ከተሰጠም በኋላ በትንሽ ሰብአዊ ኪሳራ ሀረምን ከእገታ የማዳኑን ሀላፍትና ማን ይውሰድ የሚለው ለንጉስ ኻሊድ ሌላ ራስ ምታት ሆኖበታል። የሀገሬው ፖሊስ የሞከራቸውም ፤ የሀገሬው ሰራዊት አሳክቼዋለው የሚለው አንድም ፍሬ ነገር ማቅረብ አልቻለም።

ስለዚህ ከውጪ ሀገር ኮማንዶዎች ይህንን   ተግባር አቀላጥፎ የሚጨርስ መረጣ በጠረጴዛ ዙርያ ሲጣል ሲነሳ ከቆየ በኋላ የፈረንሳይ ኮማንዶ ተመረጠ። ኮማንዶው አለኝ የሚለውን ዘመናዊ መሳሪያ አንግቦ የሱዑዲያ ምድር ከተመ። ግን ስራውን ገና ሳይጀምር ከበድ ያለ ፈተና ገጠመው። የሀረም ክልል ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑ ሰራዊቶች እንዴት ሊገቡ ይፈቀድላቸዋል? የሚል። ጥያቄው በምን መልኩ እንደተፈታ ብዙ መላምቶች ቢሰነዘሩም የፈረንሳይ ኮማንዲ ቡድን ሀረምን ከእገታ በማስለቀቁ ላይ የአምበሳውን ድርሻ እንደወሰደ የትኛውም ተራኪ የማይክደው እውነታ ነው።

ኮማንዶው ሀረም የገባው ሸሀዳ ይዞ ነው ፤ ኮማንዶው አመራር እና ሎጅስቲክ ላይ ብቻ ነው የተሳተፈው እና ሌሎችም ተብሏል።

ኮማንዶው በሀረም የመሬት ስር መንገድ በመግባት መርዛማ ጪሶችን ወደ ሀረም ክልል አስወነጨፈ። የሀረም እንግዶች በከባድ ሳል እየተጨነቁ የድረሱልን ሰቆቃ ድምፅ ያሰማሉ። በጪሱ ነቦልቧል የተጨነቀው ሀረም በላዩ ላይ የጥይት እሩምታ ታከለበት። ሰላማዊው ክልል የጦር አውድማ ሆነ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?

የመጨረሻ ክፍል

የመስጂደል ሀረም ግቢ እገታ እንደቀልድ 14 ቀናት ጨርሶ 15ኛ ቀኑን ይዟል። በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊም በዝ ሀገራት ህዝቦችም የሀረምን መታገት በመቃወም በየቦታው የቁጣ ድምፅ ያዘሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አጧጡፈውታል።ንጉስ ኻሊድ የመጨረሻ እምነቱን የጣለባቸው የፈረንሳይ ኮማንዶዎች ሙስሊም ናቸው ወይ? የሚለው ንትርክ ሳይቋጭ ወደ መስጂደል ሀረም ዘልቀው ስራቸውን «ሀ» ብለው የጀመሩትም እገታው ከተፈፀመ 15 ቀናት በኋላ ነበር።

ኮማንዶዎቹ በመስጂደል ሀረም የመሬት ለመሬት መንገድ እየተሽሎከሎኩ ገብተው መርዛማውን ጭስ ወደ ሀረም ካስወነጨፉት በኋላ ድንገተኛ እና ያልጠበቁት ጥቃት የደረሰባቸው የዑለይቢ ቡድኖች ባገኙት አቅጣጫ ሁሉ ይተኩሳሉ። ኮማንዶዎቹም ጭንብላቸውን እንዳጠለቁ አጋች ነው ብለው ያሰቡትን በጥይቅት ይቆሉታል። በመካከል ግን የሀረም እንግዶች ከቀኝ እና ግራ በሚተኮሱ ጥይቶች እና ሀረምን ባጠነው መርዛማ ጭስ ህይወታቸው ወደ ቀጣዩ አለም ትከንፋለች።

ከብርቱ ፍልሚያ በኋላ ከዑተይቢ ቡድኖች መካከል አንድ ጉምቱ ሰው በጥይት ተጠብሶ መሬት ላይ ተዘረረ። ብዙም ሳይቀለይ ስትንፋሱ ተቋርጣ ሽቅብ ጥላው ከነፈች። ዑተይቢና ተከታዮቹ ያዩትን ማመን አልቻሉም። እሱን እስከያዝን አለምን እንገዛበታለን ያሉት መህዲያቸው ገና በመጀመሪያው ፍልሚያ ህይወቱን ተነጠቀ። አዎን! የሞተው መህዲ ነው ብለው ያሰቡት ሙሐመድ ብን ዓብደላህ አልቀሕጧኒ ነበር።

ከዚህ ወዲያ ፍልሚያም ሆነ መስዋእትነት ለነዑተይቢ ትርጉም የለውምና ቀስበቀስ መሳሪያቸውን እየጣሉ እጃቸውን ለኮማንዶው እጃቸውን ሰጡ። ፍልሚያውም ከ15 ቀን አስጨናቂ ትግል በኋላ ተጠናቀቀ። አማፂያኑም ከጥቂት የፍርድ ሂደት በኋላ በአደባባይ የሞት ፍርዳቸውን ተቀብለው ወደ ቀጣዩ የአላህ ፍርድ ተሸኙ።
ዝምታም የሙእሚን ባህሪ ነው፡፡

ለተናገረው ሁሉ መልስ ቢሰጥ፣ የሰደበውን ሁሉ ቢሳደብማ ውረደት እንጂ አያተርፍም፡፡ ውሻኮ የተናቀው አላፊ አግዳሚው ላይ ሁሉ ስለሚጮህ ነው፡፡ እሱም ቢሆን ከአንድ ድንጋይ አላለፈም፡፡
ሙእሚን ዝምታን ይመርጣል፡፡ ከተናገረም ከመናገሩ በፊት ምን ማውራ እንዳለበት ያስባል፡፡ ክብሩንም ይጠብቃል፡፡ ከአፉ መልካም እንጂ ክፉ አይወጣም፡፡ ሙእሚን በዝምታው ውሰጥ ክብሩ አለ፡፡ አንበሳ ለምን ተፈራ? ለምንስ ተከበር? በዝምታው፡፡
ጨለማን ለምን አንደፍረውም? ለምንድነው የምንፈራው? ፀጥ ያለ ስለሆነ፡፡ ሬሳን ለምንድነው የምንፈራው?ስለማያወራ።
በቁርዓን ላይ የምናገኛቸው ምልክቶች እና የሚያስተላለፍት መልዕክት

ቁርዓን በምንቀራበት ወቅት እነዚህን ምልክቶች ሁል ጊዜ እናያቸዋለው፡፡ ግን አብዛኞው ሰው የምልክቶችን መልዕክት በአግባቡ አይረዳቸውም፡፡ ከዚህ በታች ያለው ምስል እያንዳንዱ ምልክት የሚያስታልፈውን መልዕክት ያስገንዝበናል

ይህን ጠቃሚ ማስታወሻ ያዘጋጀውን ወንድም አላህ ኸይር ስራውን ይቀበለው

ይህን ጠቃሚ ማስታወሻ ለሌሎችም እናዳርስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አመት ሊሞላዉ የተወሰኑ ቀናት ሲቀረዉ ከ330 ቀን ቡሀላ ዛሬ ደሴ ከተማ  Data ተለቀቀ እንዴት ናችሁ

በመሀል ከአዲስ አበባና ከባቲ በሚመጡ Data አልፎ አልፎ አጫጭር ፁሁፍ አቅረቤ ነበር ..በአላህ ፍቃድ መልሶ data ካልተዘጋብን አልፎ አልፎ አንዳንድ ትምህርቶች የሚለቀቅ ይሆናል

አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መይት_ዛዴ(የሙት ልጅ)
አሚር ሰይድ

መይት ዛዴ ስለሚባል ቱርካዊ ሰምታችሁ ታቃላችሁ??ይህ ሰዉ በሱልጣን ሙሀመድ ቀዳማዊ ዘመን የኖረና በመልካም ምግባሮቹ  የሚታወቅ የሀይማኖት ምሁር ነበር። መይት ዛዴ (የሙት ልጅ) የተባለበት ምክንያት በሚከተለው ክስተት አማካይነት የደረሰ ነው፡፡



   የመይት ዛዴ አባት የኦቶማን ቱርክ መንግሥት ወታደር ነበር። ልክ እንደ ሌሎቹ የሀገሩ ጀግኖች ሁሉ በ1596 በተደረገውና ሱልጣን ሙሐመድ ሳልሳዊው በመራው የኢግሪ ዘመቻ እንዲሳተፍ ጥሪ ተደረገለት፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ ጊዜ ሚስቱ ልትወልድ ተቃርባ የነበረ ሲሆን ጤንነቷም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኝ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ያ ጀግና ወታደር በአላህ መንገድ ላይ መዋጋትን ከሁሉም ነገር በላይ ያፈቅር ስለነበር ሚስቱ ይቅርታ እንድታደርግለት ከጠየቃት በኋላ ለዘመቻው ዝግጅት ማድረጉን ተያያዘው፡፡ ከዚያም እጆቹን የአርሹ ባለቤት አላህ ወዳለበት ሰማያዊ ችሎት ዘርግቶ የሚከተለውን ፀሎት አደረሰ

ጌታዬ ሆይ! እኔ ባንተ መንገድ ልዋጋ መጓዜ ነው፡፡ ካንተ በቀር ሌላ ረዳት የለኝም። ጌታዬ ሆይ! ይህን ልጄን ለዚህች ታማኝና ብዙ ድካም የሚታይባት ባለቤቴ ስጥቸዋለሁ፡፡ እባክህን አንተ ጠብቅልኝ።"

ጀግናው ሰው ይህን ካለ በኋላ ከፈረሱ ላይ ወጥቶ በመጋለብ ከዓይን ተሰወረ። በአላህ እርዳታና ፀጋ የኦቶማን ጦር በውጊያው ድል አደረገ፡፡



    ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ጀግናው ወታደር፣ አዛዦቹ ወደ ቤቱ እንዲሄድ ይፈቅዱለት ዘንድ ጥያቄ አቀረበ፡፡ በቀጥታ ወደ ቤት ጋልቦ እዚያ ሲደርስ ግን በቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም😔፡፡ ባለቤቱ የድሉን ወሬ ስምታ ከሆነ ቤቱን ሞቅ አድርጋ በደስታ ልትቀበለው በተገባት ነበር፡፡ ሆኖም እንኳን አቀባበል ልታደርግለት ይቅርና በቤት ውስጥ አልተገኘችም። በታላቅ ጭንቀትና ጥንቃቄ ወደ ጎረቤቶች ሄዶ ምን እንደተፈጠረ ጠየቃቸው፡፡

እነርሱም ሰውዬውን ሲያዩት በሀዘን እንደተዋጡ እንዲህ አሉት- “አንተ ጀግና ሆይ! አላህ ድልህን ይባርክልህ፤ እንዲሁም ሕይወትህን ፀጋ የተሞላበት ያድርግልህ፡፡" ከዚህ አባባል ጀርባ ያለውን ትርጓሜ እያሰላሰለ ልቡ መቃጠል ስለጀመረ ሳይፈልገው እምባ😢😢የታከለበት ሲቃ ፈንቅሎት እንዲህ አለ፡-

"ሊሆን አይችልም:: የታለች ሚስቴ? ተወዳጁ ልጄስ የታለ? የልጄን ነገር ለዓለማት ጌታ በአደራ ሰጥቼዋለሁ፡፡ እርሱ ከሁሉም ጠባቂዎችና ተንከባካቢዎች በላጭ ነው::” ይህን ካለ በኋላ በሀዘን ተኮማትሮ እምባዉን እያነበ  ለረዥም ጊዜ ፀጥ በማለት ቆየ። ከዚያም ዙሪያውን የከበቡትን ሰዎች እንዲህ አላቸዉ፡-

“እርግጥ ነው አላህ ከሁሉም በላይ አዛኝ የሆነ ጌታ ሲሆን አደራ በመጠበቅ በኩል ደግሞ እጅግ ታማኙ ነው፡፡ የባለቤቴን መቃብር አሳዩኝ አላቸዉ::"


....ከሰዎች ጋር ወደ መቃብር ሥፍራ አብሮ ከሄደ በኋላ የባለቤቱን መቃብር ሲያይ በመቃብሩ አፈር ላይ ጆሮውን ጣል አድርጎ ያዳምጥ ጀመር። ከዚያም፡- “አዎን! የልጄን የለቅሶ ድምፅ ሰማሁ!" በማለት እንደ እብድ ጮኸ፡፡

ይህን ካለ በኋላ ዶማና አካፋ እንዲመጣለት ጠይቆ መቃብሩን ይቆፍር ጀመር፡፡ ከእርሱ ጋር የመጡት ሰዎችም እያገዙት አፈሩ ሲወገድ የሕፃኑ ለቅሶ በግልፅ ይሰማ ጀመር፡፡ መቃብሩ ጨርሶ ከተከፈተ በኋላ በለህዱ (በጓዳው) ውስጥ አስደናቂ ተዓምር ተከሰተ፡፡

በሞተችው እናቱ ደረት ላይ ልጥፍ ያለ ወንድ ልጅ ታየ፤ የጦር ጀግና የሆነው ያ ወታደር ልጁን ወዲያውኑ ከእናቱ ደረት ላይ አንስቶ ወደ ደረቱ በማስጠጋት አቀፈው፡፡ ከዚያም የሚያምሩና ሮዝ መልክ ያላቸው ጉንጮቹን ደጋግሞ ይስመው ጀመር፡፡ ህፃኑን በጨርቅ ጠቅልሎ ለስዎች ከሰጣቸው በኋላ በውድ ባለቤቱ ላይ ሶላተል ጀናዛ ሰግዶ መቃብሩን እንደነበር በጥንቃቄ ዘጋው፡፡

ይህን ሁሉ ትዕይንት ዙሪያውን ከበው ሲመለከቱት የነበሩ ሰዎች በድንጋጤ ደርቀው ቀርተዋል። እየደጋገሙ የአላህን ተዓምራት በማስታወስ ስሙን ያወሳሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ምህረት ይጠይቃሉ፡፡

አባትዬው ግን ዓይኖቹ በእንባ እንደተሞሉ ልቡ በሚስቱ ሀዘንና በልጁ በሕይወት መትረፍ በተፈጠረበት የሀዘንና የደስታ ድብልቅ ስሜት ተውጦ ግራ እንደተጋባ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

    ይህ ልጅ ከዚያ ጊዜ በኋላ በታላቅ የእምነትና አላህን የመፍራት ድባብ ውስጥ እንዲያድግ ተደረገ፡፡ በመላው የኦቶማን ቱርክ ግዛትም የታወቀ አላህን ፈሪ ሰው ለመሆን በቃ:: 'መይት ዛዴ' በሚለው መጠሪያ ስሙ በሁሉም ሰው ዘንድ የታወቀ ነበር፡፡ ይህ ሰው በእርግጥም የእውነተኛ በአላህ የመመካት ውጤትና የኃያሉ አላህ ማለቂያ የሌለው ተዓምራት መገለጫ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ኖሯል፡፡
እኛ አላህ ጋር ያለን መመካት ምን ያህል ይሆን??



ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥🔥የጀሀነም ፍራቻ🔥🔥

ልቡ በጀሃነም ፍራቻ የተሞላ አንድ የአንሷር ወጣት ነበር። ስለ ጀሃነም በተነሳ ቁጥር ማልቀስ ይጀምራል። በመጨረሻም ክፍሉ ከውስጥ ዘግቶ በመቀመጥ ወደ ውጭ ላለመውጣት ወሰነ። የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ልጁ ሁኔታ ሲነገራቸው ሊጠይቁት ሄዱ። ወጣቱ የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በጉጉት ሲመለከታቸው ከቆየ በኋላ ወዲያው ተነስቶ በእጆቹ አቀፋቸው፡፡ በዚያው ሁኔታ ላይ እያለም ነፍሱ በመውጣቷ ወለሉ ላይ ተዘረረ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉ፡-

“ወንድማችሁን እጠቡትና ከፍኑት፡፡ የጀሃነም ፍራቻ ጉብቱን በታትኖታል፡፡ ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ፤ አላህ ከጀሃነም ቅጣት ጠብቆታል፡፡ አንድን ነገር የፈራ ከዚያ ነገር ለማምለጥ መንገድ ያገኛል።" (ሃኪም፣ አሊ አል-ሙተቂ)


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
በአንድ የቁርአን አያ ደንግጦ የሞተዉ ወጣት
አሚር ሰይድ

አቡበከር ወራቅ ቁርአን የሚያጠና አንድ ትንሽ ልጅ ነበራቸዉ፡፡ አንድ እለት ከመማሪያ ቦታዉ ፊቱ ገርጥቶ ጠዉልጎና እንየተንቀጠቀጠ በጊዜ ተመለሰ፡፡ አቡበከር የልጁን ሁኔታ ሲያስተውል በመደነቅ፡- “ምን አጋጠመህ የእኔ ልጅ? ምንድን ነው ሰውነትህን እንዲህ የቀያየረው? በጊዜስ የተመለስከው ለምንድን ነው?'' በማለት ጠየቀው፡፡

በልጁ ትንሽዬ ልብ ውስጥ የአላህ ፍራቻ እያቆጠቆጠ ስለነበር እንደ በጋ ቅጠል ሁለመናውን አጠውልጎት እንዲህ አለ፡- “አባቴ ሆይ! ዛሬ መምህራችን አንድ የቁርዓን አንቀጽ አስተማሩን፡፡ እኔም ትርጉሙን ሳሰላስል እንዲህ ለመሆን በቃሁ። ''

“የትኛው አንቀጽ ነው የእኔ ልጅ?” አለ አባት፡፡ ልጁ የሚከተለውን አንቀጽ አነበበ፡-

{ فَكَیۡفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرۡتُمۡ یَوۡمࣰا یَجۡعَلُ ٱلۡوِلۡدَ ٰ⁠نَ شِیبًا }

ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡(አል ሙዘሚል 17)


ቆየት ብሎ ይህ ልጅ በዚህ የቁርአን አያ ትርጉም ምክንያት ታመመ:: የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ከቆየ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሞተ😔፡፡ አባትዬው በዚህ ክስተት ክፉኛ ነበር የተናጠው። በተደጋጋሚ ወደ ልጁ መቃበር እየሄደ በማልቀስ ለራሱ እንዲህ ይል ነበር-

"አቡበከር ሆይ! ልጅህ ቁርዓንን አንብቦ መልዕክቱን በመገንዘብ አላህን በመፍራት ነፍሱን አስረከበ፡፡ ይሁን እንጂ አንተ ግን ይህን ሁሉ ዘመን ስታነበበው ብትቆይም የልጅህን ያክል እንኳን አላህን ልትፈራ አልቻልክም እያለ ሁሌ ራሱን ይወቅስ ነበር

ምን ያህሎቻችን ነን የቁርአን አያ ትርጉም አዉቀን እራሳችንን የምንፈትሸዉ⁉️



ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላህ እኔ አፍቃሪያቸዉ ነኝ ይላል
#ለሒጃብ_መገፈፍ ነብዩ ﷺ #የተዋጉበት_ጦርነት
አሚር ሰይድ


በነብዩ ﷺ ዘመን አንዲት ሂጃቧን አስተካክላ በምትለብስ ሴት ላይ በደረሰ በደል ምክንያት
ነብዩ ﷺ ጦር መዝመታቸዉን ምን ያህላችን እናቃለን??
እስከ ወደ ታሪኩ እንለፍ

    የበኒ ቀይኑ ቃዕ አይሁድ ማህበረሰብ በመዲና አካባቢ ይኖሩ የነበሩና ወርቅ በማንጠር የሚተዳደሩ ስስታም ማህበረሰብ ነበሩ:: የጐሳው አባላት ያነጠሯቸውን የወርቅ ጌጣቸዉንም ሆነ ሌላ የወርቅ እጅ ሥራ ውጤታቸውን የሚሽጡበት ልዩ ስፍራ ነበራቸው፡፡በአንድ ወቅት ከነቢዩ ﷺ
ልደረባዎች አንዷ የነበረች ሴት ወደዚያ የወርቅ ገበያ ትሄዳለች።  አንድ እርጉም የሆነ የአይሁድ ሰው የሴትዬዋን ጅልባብ ጫፍ ጭንቅላቷ ጋር በሆነ ነገር ያያይዘዋል፡፡ ይህን ተንኮል ያልተገነዘበችው ሴት ከተቀመጠችበት ስትነሳ ሰውነቷ ለባዕድ ወንዶች በመጋለጡ ሁሉም ሳቁባት፡፡

ይህን ርኩስ ድርጊት የተገነዘበና በአቅራቢያ የነበረ አንድ የነቢዩ ﷺባልደረባ ተንኮል የሰራውን የአይሁድ ሰው ወዲያውኑ እርምጃ በመውስድ የገደለው ሲሆን በአፀፋውም የአይሁዱ ሰው ወገኖች ሙስሊሙን ስው ተረባርበው ገድሉት፡፡


    ይህ የፊትናን እሳት የቆስቆሰው ውዝግብም ጦርነትን ይወልድና ነቢዩ ﷺሰራዊታቸውን አስከትለው የበነ ቀይነ-ቃዕን መንደር ይከቡታል። ከዚያ በኋላም የጐሳው አባላት በሙሉ መዲናን ለቅቀው እንዲወጡ የተገደዱ ሲሆን ከዚያ አካባቢ ድምጥማጣቸው እንዲጠፋ ተደርጓል።

ከዚያ ሁሉ ታላቅ ተጋድሏቸው በኋላ ነቢዩ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው የዛሬውን የእኛን ሁኔታ ቢመለከቱ ምን ይሉ ነበር😔? በፍርዱ ቀን ጌታችን አላህ ፊት ስንቀርብ ምን ይሆን የምንመልሰው? ሁሉን አዋቂ ለሆነው አላህ ምን የምንደብቀው ነገር ይኖራል?

⚡️⚡️ሙስሊም ሴቶች ሆይ! ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ በጥንቃቄ ልታሰላስሉት የምትችሉትን ታሪክ አቀርብላችኋለሁ:: አንድ ዕለት ኢማም አህመድ ኢብን ሐንበል በመንገድ ላይ ሲጓዙ አንዲት በሚገባ ሒጃቧን የለበሰች ሴት ይመለከታሉ:: በዚያው ቅፅበት ንፋስ እየተግለበለበ መጥቶ ቀሚሷን ተረከዟ እስኪገለጥ ድረስ ወደ ላይ ያነሳዋል:: በዚህ ጊዜ ኢብን ሐንበል በመጐናጸፊያቸው ጠርዝ ፊታቸውን በመሸፍን የሚከተለውን ተናገሩ፡፡
ይህ የፈተና ጊዜ ነዉ!!!
ተመልከቱ! ይህ ሁኔታ እርሳቸው  አስበውት ሳይሆን በአጋጣሚ የተከሰተ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ምን ያህል ስሜታቸው እንደተጉዳ ከታሪኩ መገንዘብ አይከብድም፡፡ እኚህ ሰው በአሁነ እኛ ባለንበት ዘመን ቢኖሩ ኖሮ ምን ይሉ ነበር???


⚡️⚡️98% ሴቶች ሂጃብን በራሳቸዉ አመለካከትና የኑሮ ዘይቦ አለባበስ ለእነሱ አለባበስ እንዲመቻቸዉ አድርገዉ ሲተረጉሙት እና እንደሚመቻቸዉ ሲለብሱት የምናየዉ ሀቅ ነዉ ግን አላህ እና ነብዩ ﷺ ሂጃብን እንዴት ነዉ በቁርአንና በሀዲስ የገለፁት??

☞አላህ በቁርአኑ ስለ ሂጃብ ሲገልፅ
ይህ እንዲታወቅና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነዉ(አል አህዛብ 59)

☞ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡(አን-ኑር31)

ሒጃብን መልበስ ለሴቶች በላጭና ምትክ የማይገኝለት የመከላከያ ጋሻ ነው፡፡ ሴት ልጅ ሒጃቧን አስተካክላ ከለበሰች በሰይጣን ግፊት እየታገዙ ከሚፈታተኗት ወንዶች ጉትጕታ ሙሉ በመሉ ማለት ይቻላል ትገላገላለች። ሁሉም ሰው የሚያከብራት ሲሆን የመረጠችው የክብር መንገድ የመጭውን ዓለም ስኬትና ሽልማት የምታገኝበት ነዉ፡፡

   ሙስሊም ሴት ከፀጉሯ ጀምራ አንገቷንና ትከሻዋን፣ ደረቷን የመሸፈን ግዴታ አለባት፡፡ እንግዲህ እነዚህንና ሌሎች መሸፋፈን ያለባቸውን የሰውነት ክፍሎቿን ከባሏ ውጪ ለሆነና ከእነርሱ ጋር ጋብቻ ሊያስመሰርታት የሚችል ባዕድነት ላላቸው ወንዶች ማሳየት አይፈቀድላትም፡፡

⚠️ በነብዩ ﷺ ጊዜ የነበሩ ሴቶች ስለ ሂጃብ የቁርአን አያ ሲወርድ ሱሀቦች መልሳቸዉ ምን ነበር??

    የአላህ መልዕክተኛ ﷺባልደረባዎች ክስተቱን ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ፡- "የሴቶችን መሸፋፈን ግዳጅ የሚያደርገው የቁርአን አንቀፅ በወረደበት ጊዜ በአላህ ይሁንብን እያንዳንዷ ሴት ይህን ጉዳይ እንደሰማች ቀሚሷን ለሁለት እየቀደደች በአንደኛው ፀጉሯን፤ በሌላኛው ደግሞ አንገቷንና ደረቷን ያልሽፈነች አንድም አልነበረችም፡፡ ይህንን ያደረጉትም ከፀጉራቸው ጀምሮ ወጥ ሆኖ እስከታችኛው የሰውነታቸው ክፍል ድረስ የሚሽፍን ልብስ ለማግኘት ችግር ስለነበረባቸው ነበር።
ዛሬ ግን ልብስ ሞልቶ ለባሽ በፈለገዉ ፋሺን ሲለበስ ሂጃብን በራሳቸዉ ስሜት በሚያዛቸዉ  ልክ አላህ ካዘዘዉ መመሪያ ዉጭ ለባሽ 98% በላይ ነዉ


ነቢዩ ﷺበተጨማሪም እንዲህ ብለዋል- ከሴቶቻችሁ ሁሉ በላጮቹ
☞ወላድ የሆኑት፣
☞መልካም ፀባይ ያላቸው፤
☞ስታማክሯቸው ምክራቸውን የሚለግሱና
☞ አላህን ፈሪዎቹ ናቸው::''

ከሴቶቻችሁ መጥፎቻቹ ደግሞ
መተበሪጃት (ተገላልጠው የሚሄዱ) የሆኑት
ሙተኸይላት (በኩራት ተወጥረው የሚራመዱና በንግግር የሚደነፉት) ሲሆነ እነርሱ መናፍቃን ናቸው::"

እና አህቴ ሆይ አሁን ባለሽበት አለባበስ ነብዩ ﷺ
እንዳሉት መናፍቃን ሁኜ ይሆን እንዴ ብለሽ አስበሽ ታቂያለሽ??

የአላህ መልዕክተኛ ﷺእንዲህ በማለት ተናግረዋል፦

አሁን የማያቸው ሁለት ዓይነት ሰዎች በጀሃነም ውስጥ ክፉኛ ይቀጣሉ::
#የመጀመሪያዎቹ ቡድኖች ሁልጊዜም ቢሆን ከእጃቸው የበሬ ጅራት (መግረፊያ) የማይለያቸውና በዚያ ያገኙትን ሁሉ የሚገርፉና

#ሁለተኛዎቹ ልብስ የለበሱ ሴቶች ሆኖም ግን የተራቆቱ ከቀናው መንገድ የተዘናበሉ ሌሎችንም እንዲዘናበሉ የሚያደርጉ እንዲሁም ፀጉራቸውን እንደ ግመል ሻኛ የሚቆልሉ ናቸው፡፡ እነዚህ በእርግጥም ጀነት ሊገቡ ቀርቶ ሽታዋን እንኳን አያገኙም። ሽታዋ ከዚህ እስከዚህ ያህል ርቀት የሚገኝ ቢሆንም።
እህቴ ሆይ የአንቺ አለባበስ ከጀነት ሽታ ከሚያገኙት ወይስ ከማያገኙት ነሽ??


✏️ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን የመሰለ ሁኔታ የሚያንፀባርቁ ሰዎች እርሳቸው በነበሩበት ዘመን እንዳላዩ በዚህ ሐዲስ መግቢያ አካባቢ ተጠቅሷል፡፡በአሁን ዘመን ደግሞ ሞልቶ ተትረፍርፏል

ከዚህ አስደንጋጭ ሐዲስ በቀላሉ መገንዘብ እንደምንችለው እነዚያ የጀሃነም እድምተኞች የሆኑት ሴቶች ዋነኛ መለያ የለበሱ ሆኖም ግን ልብሳቸው መላ አካላቸውን ሊሸፍንላቸው ባለመቻሉ የተራቆቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች ለራሳቸው ጠማማ የሆነውን ይህን የሰይጣን መንገድ ለመከተል መምረጣቸው ሳያንሳቸው ሌሎች ሰዎችም የእንርሱን ፈለግ እንዲከተሉ ብርቱ ጥረትና ግፊት የሚያደርጉ እንደሆኑም ተገልጿል፡፡ አሁን በዘመናችን የፋሽንና የሞዴሊንግ ዓለም ውስጥ በሒጃብ ስም ..ሒጃብ አስመስሎ የሴት ልጅ ቅርስን የሚያሳይ ጉልህ ስፍራን እየተቆጣጠሩ የመጡ እንስታት በትክክል ይህን መንገድ እየተከተሉ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ አይገድም፡፡ እነዚህ እንስታት ፀጉራቸውን ፈፅሞ የማይሸፍኑ ሲሆን ከዚያም በባሰ እንደ ግመል ሻኛ እየከመሩና የተለያዩ የፀጉር አሰራር ዘዴዎችን፣ እየተከተሉ ሰውን ሁሉ የሚያማልሉ ፍፁም የሰይጣን ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡ እነዚህ ፈፅሞ ጀነት የማይገቡ ናቸዉ



⚠️⚠️ሴቶች ሆይ አለባበሳችንን እንፈትሽ...ወንድ ሆይ የእህትህን የልጅህን የሚስትህን የእናትህን ሂጃብ አለባበስ ፈትሽ የዉመል ቂያማ ላይ እሷም በአለባበሷ አንተም ባለመከልከልህ ተጠያቂ እንዳትሆን¡¡¡

ለሌሎች ያካፍሉ
Join👇👇


www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጋዛ😔 በዱአ እንበርታ
#ኑዓይም_ኢብኑ_መስዑድ
         አሚር ሰይድ

ስለ ኑዓይም ኢብኑ መስዑድ ምን ያህሎቻችን እናቃለን??

    ኑዓይም ኢብኑ መስዑድ አዕምሮውንና በሳልነቱን በኸንደቅ ዘመቻ ጊዜ ሙስሊሞችን ለማጥፋት የተሰበሰቡትን አህዛቦች (ሙሽሪኮች ገጥፋኖችን፤ በኒ ቁረይዟዎችን) ለመበታተንና አንድነታቸውን ለማፈራረስ ተጠቅሞበታል፡፡ ታሪኩን ኢብኑ ኢስሀቅ እንዲህ ይተርክልናል

በአህዛብ ዘመቻ ጊዜ ረሱል ﷺ ባልደረቦቻቸዉ እጅግ በአስቸጋሪና አስጨናቂ ሁኔታ ላይ ሆነዉ ቆዩ፡፡የሁኔታዉን አስቸጋሪነት አላህ ሱ.ወ በቁርአን እንዲህ በማለት ገልፆታል፡-

{ إِذۡ جَاۤءُوكُم مِّن فَوۡقِكُمۡ وَمِنۡ أَسۡفَلَ مِنكُمۡ وَإِذۡ زَاغَتِ ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَبَلَغَتِ ٱلۡقُلُوبُ ٱلۡحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِٱللَّهِ ٱلظُّنُونَا۠ }

ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ ጊዜ፣ ዓይኖችም በቃበዙ፣ ልቦችም ላንቃዎች በደረሱና በአላህም ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ ያደረገላችሁን አስታውሱ፡፡(ሱራህ አህዛብ 10)

    በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ኑዓይም ኢብኑ መስዑድ ከረሱል ﷺ ዘንድ መጥቶ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔ ሰልሜያለሁ ህዝቦቼ መስለሜን አያወቁም የፈለጉትን ይዘዙኝ አላቸው፡፡ ረሱልም ﷺ “አንተ በእኛ ውሰጥ አንድ ሰው ነህ ከእኛ ጋር ሆነሃል ከቻልክ ከእኛ እነሱን አጣላልን በታትንልን።ጦርነት ማለት ማታለል ነው›› አሉት፡፡
....ከዚያም ኑዓይም በኒቁረይዟዎች ዘንድ መጣ እሱ በጃሂሊያ ጊዜ መጠጥ አጣጫቸውና ወዳጃቸው ነበር። ከዚያም “በኒቁረይዟዎች ሆይ! ለእናንተ ያለኝን ፍቅር ታውቃላችሁ በተለይ በእኔና በናንተ መካከል ያለውን ፍቅር ታውቃላችሁ አላቸው፡፡ እውነት ብለህል አንተ ከእኛ ጋር የምትጠረጠር አይደለህም አሉት:: ከዚያም እንዲህ አላቸው፡-ቁረይሾችና ገጥፋኖች እንደናንተ አይደሉም። ጦርነት የጀመራችሁበት ሀገር ሀገራችሁ ነው:: ገንዘቦቻችሁ ልጆቻችሁ ሴቶቻችሁ ያሉት እዚሁ ነው:: ከዚህ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር መቀየር (መሸሽ) አትችሉም:: ቁረይሾችና ገጥፋኖች ሙሀመድን ለመዋጋት መጥተዋል፡፡ እናንተም አግዛችኋቸዋል:: ነገር ግን የእነሱ ገንዘባቸው ልጆቻቸውና ሴቶቻቸው ያሉበት ቦታ ራቅ ያለ ነው:: በጦርነቱ መልካም ድል ካገኙ ይጠቀሙብታል። ከዚህ ውጭ ከሆነ ወደ ሀገራቸው ይሸሻሉ፡ እናንተን ለሙሀመድ አጋፍጠው ይተዋችኋል፡፡ ስለሆነም እነሱ እንዳይከዳችሁ አብራችሁ ለመጋደል መተማመኛ የሚሆኗችሁ ከተከበሩ ሰዎቻቸው ማስያዣ የሚሆኑ ሰዎች እስክትይዙ ድረስ አነዚህ ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እንዳትጋደሉ አላቸው:: እነሱም በጣም የሚገርም ሀሳብ አመላከትከን አሉት፡፡፡

ከዚያም ኑዓይም ቁረይሾች ጋር መጣ:: ለአቡሱፍያንና ከእሱ ጋር ለነበሩት የቁረይሽ ሰዎች እንዲህ አላቸው፡- “ለእናንተ ያለኝን ፍቅርና ሙሀመድ ጋርም የተቆራረጥኩ መሆኔን ታውቃላችሁ እኔ የሆነ መረጃ ደርሶኛል፡፡ ይህም ለእናንተ እንዲሆናችሁ ለእናንተ ማሳወቅ በእኔ ላይ ግዴታ ሆኖ አግኝቻቸዋለሁ:: በሚስጥር ያዙልኝ, አላቸው:: እነሱም እሺ እንደብቅልሃለን አሉት።ከዚያም እንዲህ አላቸው- አይሁዶች በሙሀመድ ላይ በሰሩት ነገር እንደ ተፀፀቱ ታውቃላችሁ። - እንዲህ ብለው ልከውለታል፡- «እኛ በሰራነው ስራ ተፀፅተናል፡፡ ከፈለግክ ከሁለቱ ጎሳዎች ከቁረይሾችና ከገጥፋኖች የተከበሩ ከሆኑ ወንዶቻቸው ይዘን እንሰጥህና አንገታቸውን ትቀላቸዋለህ፡፡ ቀሪዎቹን ደግሞ እስኪበታተኑ ድረስ ከአንተ ጋር ሆነን እንታገላቸዋለን›› ብለውታል፡፡ እሱም እሽ ብሎ ልኮላቸዋል፡፡ ስለሆነም አይሁዶች ከእናንተ ከወንዶቻችሁ ማስያዣፈልገው ከላኩ አንድም ሰው እንዳትሰጧቸው አላቸው፡፡

ከዚያም ገጥፋኖች ጋር መጣና እናንተ የገጥፋን ስብስቦች ሆይ! እናንተ ዘሮቼ ዘመዶቼ ከሰዎች ሁሉ የምወዳችሁ ናችሁ። እኔን ትጠረጠጥሩኛላችሁ ብዬ አላስብም አላቸው:: እውነት ብለሃል አንተ የምትጠረጠር አይደለህም አሉት። እሱም ሚስጥሬን ደብቁልኝ ብሎ ለቁረይሾች የነገራቸውን አይነት ለእነሱም ነገራቸው፡፡ ያስጠነቀቃቸውን ለእነሱም አስጠነቀቃቸዉ

    ከዚያም በ5ኛው ዓመተ ሃጅራ በዛው ወር ቅዳሜ ሌሊት ቁረይሾችና ገጥፋኖች ወደ በኒቁረይዟዎች እንዲህ ብለው ላኩባቸው፡- እኛ ያለነው በሰው ሀገር ነው፤ ግመሎቻችንና ፈረሶቻችን እየጠፉብን ነው ሙሀመድን ተፋልመነው እንድንገላገል ነገ በጧት ተነሱ፡፡››

   በኒ ቁረይዟዎችም እንዲህ ብለው ላኩባቸው ቀኑ ቅዳሜ ነው:: በእዚህ ቀን ምንም የማንሰራበት ቀን ነው:: ከአሁን በፊት ከእኛ የሆኑ ሰዎች ቅዳሜ ቀን ስርተው ምን መከራ እንደመጣባቸው ከእናንተ የተደበቀ አይደለም:: ከዚህ በተጨማሪ መተማመኛ ይሆኑን ዘንድ ከእናንተ ማስያዣ እስክትሰጡን ድረስ ወደ ጦርነቱ አንገባም ምክንያቱም ፍልሚያው ሲበረታባችሁ ወደ ሀገራችሁ ሸሽታችሁ እኛ ብቻችንን ልንፋለመው ለማንችለው ለሆነው ሙሀመድ አጋፍጣችሁን እንዳትሄዱ እንፈራለን ብለው ላኩባቸው:: መልዕክተኞቹም በኑቁረይዟዎች ያሉትን ይዘው ሲመለሱ ቁረይሾችና ገጥፋኖችም በፈጣሪ እንምላለን ኑዓይም የነገራችሁ ነገር ትክክል ነው >> አሉና ወደ በኒ ቁረይዟዎች፡- እኛ አንድም ወንድ አንልክላችሁም ከፈለጋችሁ ውጡና ተጋደሉ›› ብለው ላኩባቸው::
.... በኒ ቁረይዟዎችም መልዕክቱ ሲደርሳቸው «ኑዓይም የነገረን እውነት ነው.. አሉ:: ወደ ቁረይሾችና ገጥፋኖች  ማስያዣ እስክትሰጡን ድረስ እኛ ከእናንተ ጋር ሆነን ሙሀመድን አንዋጋም ብለው ላኩባቸው፡፡ በእነሱ ላይም አመፁባቸው:: አላህ በመሀከላቸው አጣላቸው፤ አንድነታቸውን በታተነው:: ከዚያ አስፈሪ ከሆነው ጭንቀት ተገላገሉ:: ቁረይሾይችና ገጥፋኖች እርስበርሳቸው ተጣልተው ድል ሳይቀናቸው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ:: በዚህ ኑዓይም በተጠቀመው ብልሃት ሰበብ ረሱል ﷺባለድል ሆኑ።

ለዚህ ድል እንዲበቁ ያደረጋቸዉ ኑዓይም(ረ.ዐ)ነበር


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ቅን_ትዉልድ
              አሚር ሰይድ

🔰🔰በአቡበክር (ረ.ዐ) የኸሊፋነት ዘመን ዑመር ኢብነ አል-ኸጣብን (ረ.ዐ) አቡበክር (ረ.ዐ) መዲና ውስጥ በዳኝነት ሾመዋቸው ነበር፡፡

ዑመር ከተሾሙበት እለት አንስቶ አንድ ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ አንድም የሚካሰስ ሰው ጠፋ፡፡ ከዚያም ዑመር (ረ.ዐ) ከተሰጣቸው ኃላፊነት እንዲያወርዷቸው አቡበክርን ሲጠይቁ
.....“ዑመር ሆይ! ሥልጣን መልቀቁን የጠየቅከው ፍትሕ ከመስጠቱ አንፃር ነውን?'' አሏቸው፡፡ ዑመርም (ረ.ዐ) “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ምትክ ሆይ! ፍጹም አይደለም፡፡ ነገር ግን በአማኝ ሕዝቦች መካከል ምንም ጉዳይ ስለሌለኝ ነው፡፡ ሁሉም ለእሱ የሚገባውን በሚገባ አውቋል፡፡ ከሚገባው በላይም ለመጠየቅ አይፈልግም፡፡ ሁሉም በየራሱ ላይ የተጣለበትን ግዴታ አውቋል፡፡ ስለዚህም ግዴታውን ከመወጣት ወደ ኋላ አይልም፡፡ ሁሉም ለራሱ የሚወደውን ሁሉ ለወንድሙ ወድዷል፡፡ በዚህም የተነሳ ወንድማቸው ለአንዲት ቀን ከተሰወረባቸው ይፈልጉታል፡፡ ከታመመም ይጠይቁታል፡፡ ከተቸገረም ይረዱታል፡፡ ከእነሱ አንዳች ነገር ከፈለገ ይሰጡታል፡፡ አንዳች መከራ ወይም ሀዘን ከደረሰበት አብረው ይካፈሉታል፡፡ ሃይማኖታቸው መመካከር ነዉ፡፡ስነ ምግባራቸዉ በጥሩ ነገር ማዘዝ ከመጥፎ ነገርም መከልከልን ነዉና በምን ላይ ተጣልተዉ ይካሰሱ??አሏቸዉ
==========\=========\=========\===

🔰🔰 ዑመር ኢብነ አል ኸጧብ (ረ.ዐ) ስለ አበብክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል-

አቡበክር ሁልጊዜ ፈጅር ከሰገዱ በኋላ መዲና ውስጥ አንድ ቤት ያመሩ ነበር። ወደዚያ ቤትም ሄድኩ፡፡ እዚያ ቤት ወስጥ ዓይኑ ስውር የሆነችና በእድሜ የገፋች ሴት ትኖራለች፡፡ ሄድኩና "አንቺ ማን ነሽ? አልኳት፡፡ "እኔ የሽመገልኩ ሴት ነኝ ስትል መለሰችልኝ
.... "ይህ ሰው ማን ነው? ስል ጠየቅኳት "ይህ ሰው ወደቤታችን እየመጣ ፍየላችንን ያልብልናል። ልብሳችንንም ያጥብልናል። ምግባችንንም ካዘጋጀ ቡኋላ ይሄዳል" አለችኝ፡፡ ይህን ጊዜ ዑመር (ረ.ዐ) ስቅስቅ ብለው አለቀሱና አጉንብለው ከእርስዎ ቡኋላ ያሉትን ኸሊፋዎች በእርግጥ በጣም እድክመዋል አሉ፡፡
====\======\========\======\=====

 🔰🔰 በአንድ ወቅት ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ኢብነ አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ታመው ሳለ ወይን መብላት አስኛቸውና እንዲመጣላቸው አዘዙ፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ወይን የሚፈራበት ወቅት ባለመሆነ ሰ.ፈለግ ታጣ፡፡ ከብዙ ጊዜያት በኋላ አንድ ሰው ዘንድ ተገኝቶ ሰባት የወይን ፍሬዎችን በአንድ ዲርሃም ገዝተው አመጡላቸው፡፡ እሳቸው አምሮታቸውን ለማርካት ሊመገቡ ወደ አፋቸው ገና እንዳስጠጉት አንድ ምስኪን መጥቶ ለመናቸው እሳቸውም መብላታቸውን በመተው የወይኑን ጣዕም ሳይቀምስ ሁሉንም ለምስኪኑ እንዲሰጥ አደረጉ፡፡
=====\======\======\======\=====

🔰🔰 ከዕለታት አንድ ቀን ዘይነል-ዓቢዲን (ረ.ዐ) “አንተ በእርግጥ ከሰዎች የበለጠ እናትህን በማገልገል ቅን ነህ፡፡ ነገር ግን ለምንድን ነው ከእሷ ጋር በአንድ ማእድ ላይ የማትበላው?" ተብለው ሲጠየቁ ከኔ በፊት ዓይኖቿ ቀድመው ያረፉበትን ቦታ እጆቼ እጆቿን ቀድመዋቸው ዋልጌ እንዳልሆንባት አላህን ፈርቼ ነው" በማለት መለሱ፡፡


ሱብሀነሏህ!!!

✏️እስልምና ይህን ትዉልድ አፍሮቶ ነበር ዛሬስ ለሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ለጎረቤት ለቤተሰቦቻችን እንዴት ነን?


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/28 03:16:10
Back to Top
HTML Embed Code: