Telegram Web Link
ከመፅሀፍ ገፅ ➋

#ነፍስያውን_ያሸነፈው_ወጣት
አሚር ሰይድ

ኢብን ሐዝም በጣም ይዋደዱ ስለነበሩ ሁለት ጓደኛሞች ታሪክ አስተላልፈውልናል፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ከመዋደዳቸው የተነሣ በመካከላቸው ምንም ገደብ አልነበራቸውም። ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛሞቹ በአንደኛው ቤት ተቀምጠው ሳለ መሸ። ከጓደኛው ጋር ሲጫወት የነበረውና የቤቱ ባለቤት የሆነው በድንገት ለአስቸኳይ ሥራ ወጥቶ ለመመለስ ባለመቻሉ በቤቱ የቀረው ጓደኛው እዚያው የማደሩ ነገር እርግጥ ሆነ። በቤቱ ውስጥ እሱና የጓደኛው ሚስት ብቻ ቀሩ፡፡የሁለቱን ጥብቅ ጓደኝነት የማታውቀው ሚስት እኩለ ለሊት ሲደርስ ከባሏ ጓደኛ ጋር የመተኛት ፍላጐት ስላየለባት እሱ ወደተኛበት ክፍል ዘልቃ በመግባት እንዲገናኛት ወተወተችው፡ በመጀመሪያ ላይ የጠየቀችውን ለማድረግ ልቡ ቢነሣሣም የጓደኛው አመኔታ ሲታወሰው ስሜቱን ለመግታት ያልተለመደ እርምጃ ለመውሰድ ተነሣ፡፡ የጓደኛው ሚስት ስታስቸግረውና የእሱም ስሜት ሲነሣሣ አንደኛውን የእጁን ጣት አጠገቡ በነበረው ኩራዝ ላይ እያስቀመጠ “ከጀሃነም እሳት ይህ ይሻልሃል' ይል ጀመር፡፡ ሴትየዋ ይህንንም እያየች ወጣቱን ለወሲብ መፈለጓን አልተወችም፡፡ እሱም እሷ ባስቸገረችውና ስሜቱ በተቀሰቀሰበት ቅፅበት የእጆቹን ጣቶች በኩራዝ መለብለቡን ቀጠለ። ሲነጋ ከእጆቹ ጣቶች አንደኛው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ነበር፡፡

ጓደኝነት ይህ ነው


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➌
#የዱዓ_ዕምቅ_ኃይል
  አሚር ሰይድ

ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አንዲት ሴት የኢማም ማሊክ ደረሳ የነበሩ ኢስማዒል የሚባሉ ዓሊም ታገባለች የዚህ የተቀደሰ ጋብቻ ትሩፋት ሙሐመድ የሚባል ልጅ ማግኘታቸው ነበር ኢስማዒል ብዙም ሳይቆዩ አረፉ። ከበስተኋላቸው ግን ለሚስታቸውና ለሕፃን ልጃቸው ማሳደጊያ የሚሆን ብዙ ሃብት ትተው ነበር፨ እናት ልጇን ሙሐመድን በጥሩ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር ኮትኩታ አሳደገች በቂ የዲን ዕውቀትም እንዲቀስም አደረገችው ልጃ, አድጐና በዕውቀት ፋፍቶ ታላቅ ዓሊም እንዲሆንላት ምኞት ቢኖራትም ይህ ልጅ አንድ ችግር ነበረበት ዓይነስውርነት። በዘመኑ ደግሞ ለዓይነስውር ታዳጊ በዕዉቀት ለመግፋት ምቹ ሁኔታ አልነበረም፨ የዲን ዕውቀት የሚፈልጉ ሰዎች ከአገር አገር፣ ከዓሊም ዓሊም መሄድ የግድ ስለነበር ይህ ልጅ ይህን ለማድረግ ዕድል አልነበረውም፡፡እናቱ ግን ተስፋ አልቆረጠችም በየዕለቱ ዱዓ ማድረግ ጀመረች በዚህ ሁኔታ እያለች ከዕለታት አንድ ቀን በእንቅልፋ ለየት ያለ ህልም አየች። በህልሙ ውስጥ ነቢዩላህ ኢብራሂም  ወደ እሷ መጥተው “ከዱዓዎችሽ ብዛት የተነሣ አላህ ሰምቶሽ ለልጅሽ የአይኑን ብርሀን መልሶለታል አሏት

እናት እስኪነጋ ለመጠበቅ አልቻለችም፨ ተነስታ ልጁ, ወደተኛበት ክፍል ገብታ ከእንቅልፉ ስትቀሰቅሰው የሙሐመድ ዓይኖቹ በርግጥም በርተዋል አላህ የሚሳነው ነገር የለም፡፡

በታላቅ ጭንቀት ላይ ያሉና ለእርዳታ ወደርሱ የተመለሱትን ባሮች ከመርዳት ወደኋላ አይልምና አላህ የልጇን ዓይነስውርነት በመፈወሱ እጅግ የተደሰተችው እናት ልጇ ለትምህርት ያለውን ጉጉት ያብልጥ እንዲገፋበት በርትታ አዝዘችው በዚህ የዒልም ዘርፍ ከፍተኛ የተባለ ዕውቀቶችንም እንዲቀስም ረዳችው፡፡ በሕይወት ዘመኑ አጋማሽ ላይ ይህ ልጅ ከቁርኣን ቀጥሉ ታላቅ ተቀባይነት ያለውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት የበቃው የሶሒሕ ቡኻሪ አጠናቃሪ –በሙሉ ስማቸው ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማኢል አል- ቡኻሪ ናቸው፡፡

ቡኻሪ አላህ በዲናዊ ዕውቀት ያበለፀጋቸው እጅግ ብሩህ አስተዋይና አስታዋሽ አዕምሮ የሰጣቸው ታላቅ ዓሊም ነበሩ።

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➍
#አላህ_እንዲህም_ያድናል!
አሚር ሰይድ

ከምዕተ ዓመታት በፊት የኖረው መሪ ሱልጣን ሱቀይላ እንቅልፍ ቶሎ የሚጥለው ሰው ነበር። ከምሽቶቹ በአንዱ ግን እንቅልፍ ሸሸው፡፡ ቢገላበጥ ሊወስደው አልቻለም። እንቅልፍ እንደሸሸው የተረዳው ሱቀይላህ 'መንቃቴ ካልቀረ ሥራ ልሥራ በማለት የባሕር ኃይሉን ጀነራል በመቀስቀስ “ከመርከቦቻችን አንዱን ወደ አፍሪካ ላክ፡፡ ምን እየተከናወነ እንደሆነም መልዕክት እንዲልኩ አድርግ የሚል ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ ጄነራሱም እንደታዘዘው አደረገ፡ እንቅልፍ በማጣቱ በለሊት የሚንሸራሸረው ሱልጣን ቆየት ብሎ ወደ ባሕር ዳርቻው ወርዶ መርከቦቹን ሲቃኝ ወደብ የለቀቀ አንድም መርከብ አለመኖሩን ስላየ ጀነራሉን ተቆጣዉ:: ጀነራሉ የታዘዘዉን መፈፀሙን እሱ በማያቀዉ ምክንያት ተመልሶ መልህቅ መጣሉን ነገረዉ፡፡

መርከቡ ከጉዞው ለምን እንደተመለሰ የመርከቡን ካፒቴን ለመጠየቅ ተያይዘው ወደ ካፒቴኑ ሄዱ፡፡ ካፒቴኑም ለምን ከጉዞው እንደተገታ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡፡ 'የባሕር ጉዞውን ስንጀምር ድቅድቅ ጨለማ ስለነበር ምንም ነገር ለመመልከት አልቻልንም፡፡ ትንሽ እንደተጓዝን ግን ከጭለማው ውስጥ ከባሕር ላይ “አላህ ሆይ አንተ ለእርዳታ ሲጠሩት ለጠሪው የምትደርስለት አምላክ እርዳኝ" የሚል የሰው ድምፅ ስለሰማን ድምፁን ወደሰማንበት አቅጣጫ አመራን፡፡ ስንደርስ የሆነ ሰው ከመስመጥ ለመዳን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነበር፡፡ ከባሕሩ ውስጥ ጐትተን ካወጣነው በኋላ የገጠመውን ስንጠይቀው ይቀዝፍበት የነበረው ጀልባ እንደሰጠመችበትና እኛ እስከደረስንለት ጊዜ ድረስ እርዳታ ፍለጋ ሲጮህ ውሉ እንዳመሸ ነገረን

ከዚህ ታሪክ አላህ የአንድ ግለሰብ ሕይወት ለማዳን ሲል የአገሩን መሪ እንቅልፍ መንሳቱን እንገነዘባለን፡፡ አላህ ሱወ ጥበቡ የላቀ አሠራሩ የረቀቀ እርዳታው ከማይጠበቅበት አቅጣጫ የሚደርስ አምላክ ነው፡፡


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➎
#ሙእሚን_ከአንድ_ጉድጓድ_ሁለቴ_አይነደፍም
አሚር ሰይድ


የበድር ጦርነት ወቅት አቡ ዐዝዛህ አል-ጁመሂ የተባለ ባለቅኔ በምርኮነት ሙስሊሞች እጅ ወደቀ፡፡ አቡ ዐዝዛህ የግጥም ተሰጥኦውን ተጠቅሞ በሙስሊሞች ላይ ቁረይሾችን ሲያነሣሣ የነበረ ሰው ነበር። ከተማረክ በኋላ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ ሰዐወ ዘንድ ቀርቦ “እኔ ብዙ የቤተሰብ አባላትን የማስተዳድር ደሃ ስለሆንኩ ምሕረት አድርገውልኝ ይልቀቁኝ, ይዘኑልኝ• በማለት ተማፀናቸው፡፡

ነቢዩም ሰዐወ አዝነውለት እንዲለቀቅ አዘዙ፡፡ ሌላ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ግን ከቁረይሽ መሪዎች አንዱ የሆኑት ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ ለአቡ ዐዝዛህ 'ያ አቡ ዐዝዛህ አንተ ትልቅ የግጥም ችሎታ አለህ  ይህን ችሎታህን ተጠቅመህ ተከታዮቻችን ሙስሊሞችን በመውጋት ላይ ጽናት እንዲኖራቸው ቀስቅስልን∶ በማለት ተማፀነው፡፡ አቡ ዐዝዛህ ነቢዩ ሰዐወ እሱን በመልቀቅ የዋሉለት ውለታ ስላለ ውለታቸውን ውድቅ በማድረግ የሚጐዳቸው ነገር ላይ ለመሳተፍ እንደማይፈልግ ቢነግረውም ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ አቡ ዐዝዛህ በቅስቀሣው ዘመቻ የሚረዳቸው ከሆነ- “ከጦርነቱ በሰላም ከተመለስክ ከሃብቴ አካፍዬህ ሃብታም አደርገሃለሁ፡፡ በጦርነቱ ላይ ከተገደልክ ሴቶች ልጆችህን ከእኔ ሴቶች ልጆች ጋር የተቀማጠለ ኑሮ እንደማኖራቸው ቃል እገባልሃለሁ ብሎት አሳመነው፡ በተገባለት ቃል የጓጓው አቡ ዐዝዛህ ወደተባለው ጦርነት ሄደ። ለሁለተኛ ጊዜም የሙስሊሞች ምርኮ ሆነ፡፡ እንደ በፊቱም ነቢዩ ሰዐወ ፊት ቀርቦ ምሕረት እንዲያደርጉለት ጠየቃቸው፡፡ ነቢዩ  ግን “በአላህ ይሁንብኝ ከእንግዲህ ጉንጮችህ ዳግም መካን አይነኩም። በርግጥ ሙሐመድን ሁለቴ አታለሃል፡፡ አንድ ሙእሚን ደግሞ ከአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይነደፍም፡ ካሉት በኋላ ወደ ዙበይር ዞር ብለው ዝብይር ሆይ! ይህን ሰው ሰይፈው አሉት፡፡ ሁለቴ ለማታለል የሞከረው አቡ ዐዝዛህ በገዛ ቅጥፈቱ ምክንያት ሕይወቱን አጣ፡፡


http://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➏
#ስግብግብነት_ሲበዛ
አሚር ሰይድ

ሙሐመድ አደ-ዳሪ የሚከተለውን አስተላልፈዋል- “ከእኛ መሃከል አንድ ስግብግብ ሰው ነበር። ይህ ሰው ያለውን ዐሥር አህዮች እየነዳ የዳር ከተማን ለቅቆ ወጣ፡ በመጓዝ ላይ እያለም አንደኛይቷን አህያ ተቀመጠባት፡፡ አህያዋ ላይ ተቀምጦ እያለ የተቀሩትን አህዮች ሲቆጥር ዘጠኝ አህዮች ብቻ ሆኑበት፨ አህዮቹን ደጋግሞ ቢቆጥርም ቁጥራቸው ያው ዘጠኝ ሆነ። ከዚያ ከተቀመጠው አህያ በመውረድ ·ተቀምጨያት ከማገኘው ጥቅም ከአንዲት አህያ ቁጥር የማገኘው ትርፍ እመርጣለሁ🙄 በማለት በእግር መጓዙን መረጠ። መኖሪያ ቀየው ሲደርስ ረጅም ርቀት በእግሩ ተጉዞ ስለነበር ተዝለፍልፎ ሊወድቅ ደርሶ ነበር፡፡

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➐
#ሙእሚኑ_ሲፈተን!
አሚር ሰይድ

አንድ ካፊር ለሙእሚን እንዲህ አለው፡፡ “አላህ ከከተበብኝ (ከጻፈብኝ) በስተቀር ሌላ ጉዳት አይነካኝም ብለህ አልነበረም? ሙእሚኑም “አዎ ብያለሁ አለው፡፡ ካፊሩ መልሶ “እንደሱ ከሆነ በል አሁን ከዚህ ተራራ ጫፍ ላይ ዝለል። አላህ ሊያድንህ ወስኖ ከሆነ ያድንሃል” አለው፡፡ ሙእሚኑም “ይህን ያልከኝን እፈጽም ነበር። ግን ደግሞ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ባሮቹን የሚፈትነው አላህ ነው እንጅ ባሮች አላህን አይፈትኑትም በማለት የካፊሩን ተንኮል ውድቅ አደረገበት፡፡

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➑
#የኢብን_ቀይም_ወርቃማ_አባባሎች
አሚር ሰይድ

ኢብን ቀይም እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል- “አንድ የአላህ ባሪያ ከእንቅልፉ ሲነቃ ብቸኛው ምኞቱ አላህን ለማስደሰትና እርሱን ለመገዛት ከሆነ አላህ ወዲያው የዚህን ሰው ፍላጐቶች ሊያሟላለትና የሚያበሳጩትን ነገሮች ሊያስወግድለት ይወስናል። ይህ ብቻ አይደለም፨ አላህ የዚህ ሰው ልብ እርሱን ብቻ እንዲያፈቅር፣ ምላሱ እርሱን ብቻ እንዲዘክር፣ ሰውነቱ እርሱን ብቻ እንዲገዛ ያደርጋል፡

ባሪያው ሲነጋ ጭንቀቱ ሁሉ የዚህ ዓለም ጉዳይ ከሆነ አላህ የሰውየውን ጭንቀቶችና ሸክሞች ለራሱ (ለሰውየው) ይተወዋል። ልቡን በጭንቀት፣ ውሎውን በመከራና በብስጭት ይሞላል፡፡ ፍቅሩን ከዚህ ዓይነት ሰው ስለሚያርቀው የሰውየው ፍቅር ለምድራዊ ነገሮች ብቻ ይሆናል። ምላሱ ስለሌሎች ሰዎችና ሌሎች ነገሮች በማውራት ይገደባል። ሰውነቱ ያምጻል፡ ለተለያዩ ስሜቶችና ፍላጐቶች ተገዢ ይሆናል። ልፋቱ የአህያ ዓይነት ልፋት ይሆናል፡፡ ፊቱን ከአላህ ፍቅር፡ ዒባዳና
ታዛዥነት ያዞረ ሰው ደግሞ ሕይወቱ በምድራዊ ደስታዎችና ፈንጠዚያዎች፣ ለፍጡራን በመገዛትና በማጐብደድ የተሞላች ትሆናለች- አላህ ﷽ “አር-ረሕማንን ከማውሳት ራሱን ያገለለ ሰይጣንን የቅርብ ወዳጁ ይሆን ዘንድ እናዘጋጅለታለን" (ቁርኣን 43:36) ብሏልና፡፡

ኢብን ቀይም ይህ እንዳይከሰት የሚከተለውን እንድናደርግ ይመክሩናል- “በሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ስትሆኑ ልቦቻችሁን ፈልጉ
➊ ቁርኣንን ስታደምጡ፣
➋ ዚክር ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ስትቀመጡና
➌ ለብቻችሁ ስትሆኑ˚ በእነዚህ ሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ሆናችሁ ልባችሁን ለመግዛት (ለመሰብሰብ) ካልቻላችሁ አላህ ልብ ይስጣችሁ*

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➒
#የተበደለ_ሰው_ዱዓ_መሬት_ጠብ_አይልም
አሚር ሰይድ

ነቢዩ ሰዐወ በእርሱና በአላህ መሃከል ምንም ዓይነት ግርዶ የለምና የተበደለን ሰው ዱዓ ፍሩ” ማለታቸውን ኢብኑ ዐብባስ አውርተዋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሲበድሉን መፍትሔው መበሳጨት ወይም ለሌሎች ሰዎች መናገር ሳይሆን የአላህን እገዛ በነርሱ ላይ መሻት ነዉ፡፡

አርዋ ቢንት ዑወይስ ከእርሻ መሬቷ የተወሰነው በሰዒድ ኢብኑ ዓምር ኢብኑ ኑፈይል ተወስዶብኛል በማለት ለአሚር ሙሐመድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ሐዝም አቤቱታ አቀረበች፡በአላህ ይሁንብኝ የነጠቀኝን መሬት በአስቸኳይ የማይመልስልኝ ከሆነ በነቢዩ ሰዐወ መስጂድ ውስጥ ጀመዓው ፊት አዋርደዋለው በማለትም ዛተች፡፡ ሙሐመድ ግን- "እባክሽን የአላህ መልዕክተኛ ባልደረባ የሆኑትን (ሰዒድ ኢብኑ ዐምር) አትጉጂኣቸው፡፡ ሰዒድ የሚበድልሽ ወይም መብትሽንም የሚነካ ሰው አይደለም የሚል ምክር ሰጧት፡፡ አርዋ በዚህ ምላሽ ባለመርካቷ ወደ ዑመይራህ እና ዐብደላህ ኢብኑ ሰላማህ በመሄድ ተመሣሣይ አቤቱታና ዛቻ ሰነዘረች: ዑመይራና ዐብደላህ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሰዒድ ዘንድ ሄዱ፡፡ ሰዒድ በእርሻ ቦታው ላይ ሆነው ወደሳቸው የመጡትን ሁለት ሰዎች ሲመለከቱ- 'ምን ጉዳይ ገጥሞኣችሁ ነው ወደኔ ልትመጡ የቻላችሁት?" በማለት ሲጠይቁ
....አርዋ ስለሳቸው የምታቀርበውን ክስ ለማጣራት መሆኑን ነገሯቸው፡፡ ሰዒድ ኢብኑ ዓምር በሰሙት ነገር በማዘን “የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ የሌላ ሰው ሐቅ የሆነችን የእጅ መዳፍ የምታክል መሬት እንኳን ብትሆን በሕገ-ወጥ መንገድ የወሰደ ሰው በቂያማ ቀን ከሰባቱ መሬቶች የዚያችን ቦታ የሚያክል ሸክም ይንጠለጠልበታል ማለታቸውን ስለሰማሁ ትምጣና የኔ ሐቅ ነው የምትለውን መሬት ትውሰድ” ካሉ በኋላ " #አላህ_ሆይ! ይህች ሴት በሐሰት ወንጅላኝ ከሆነ ሳትሞት የዓይኗን ብርሃን ነስተሃት የሞቷንም መንስዔ ዓይነስውርነቷ እንድታደርግ እጠይቅሃለሁ የሚል ዱዓ አደረጉ፡፡ ለሰዎቹም ያደረጉትን ዱዓ ለሴትየዋ እንዲነግሯት ጠየቁ።
.... አርዋ ያሸነፈች መስሏት ሰዒድ በመሬቱ ላይ የነበረን ጎጆ በማፍረስ በምትኩ የራሷን ቤት ሠራች። ይሁን እንጂ ይህን እንዳደረገች ብዙም ሳትቆይ ዓይኖቿ ጠፉ፡፡ የምትንቀሣቀሰውም በአገልጋይዋ ድጋፍ ሆነ፡፡


አንድ ቀን ውኃ ለመቅዳት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ብቻዋን በመሄዷ ጉድጓዱ ውስጥ ገብታ ሕይወቷ አለፈ፡ የተበደለ ሰው ዱዓ በአላህ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት አለው፡፡

ሰዉን ከበደል አደራ አደራ እንጠንቀቅ!!!


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ 10
#የኪስራው_ሚስትና_አሳ_አጥማጅ
አሚር ሰይድ


የፋርስ ንጉስ የነበረው ኪስራ ኢብኑ ፐርቬዝ ዓሣ መመገብ የሚወድ ንጉስ እንደነበር ይነገራል።

አንድ ቀን ኪስራ ከሚስቱ ሺሪን ጋር ተቀምጦ ሳለ የሆነ ዓሣ አጥማጅ ያጠመደውን ግዙፍ ዓሣ ወደ ቤተ-መንግሥቱ በማምጣት በሽልማት መልክ ለንጉሱ አበረከተለት። ንጉሡም በዓሣው ትልቅነት በመገረሙ ለአምጪው 4 ሺ ዲርሃም ሸለመው፡፡ ዓሣ አጥማጁ ልክ እንደሄደ የንጉሱ ሚስት የባሏን አድራጐት በማውገዝ፦ “ይህን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለአንድ ዘመድህ ብትሰጥ ዘመድህ ለአንድ ተራ አጥማጅ የሸለምከውን ገንዘብ እንዴት ትሰጠኛለህ ብሎ ሊወቅስህ ይችላል' አለችው፡፡ ኪስራ፦ -ያልሽው ነገር እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ አስቀድሜ የሸለምኩትን ገንዘብ እንዴት መልሼ እቀበለዋለሁ?” ሲላት፥
,,,,,,ሺሪን- “እኔ ይህን የማደርግበት ዘዴ አውቃለሁ፡፡፨ ዓሣ አጥማጁን አስጠራው' አለችው፡፡ 'ሲመጣ ዓሣው ወንድ ነው ወይንስ ሴት? ብለህ ጠይቀው፡፡ ፆታው ወንድ ነው ካለህ አይ እኔ እንኳ የፈለግኩት ሴት ነበር ትለዋለህ። ሴት ናት ካለህ ደግሞ እኔ የፈለጉት ፆታው ወንድ የሆነ ዓሣ ነበር ትለዋለህ” በማለት መከረችው፡፡ ዓሣ አጥማጁ ርቆ ስላልሄደ ተጠርቶ ሲመጣ የሆነ ችግር እንዳለ ስለጠረጠረና በተፈጥሮውም ብልህ ሰው ስለነበር ገንዘቡን መልስ ቢሉት የማምለጫ ዘዴ እያሰላሰለ ንጉሱ ፊት ቀረበ፡፡
.....ንጉሡ “ቅድም ያመጣህልን ዓሣ ወንድ ዓሣ ነው ወይንስ ሴት?” ሲሉትም የዓሣ አጥማጁ ምላሽ -ንጉስ ሆይ ዓሣው እንኳን ሁለቱም ፆታ አለው፡፡ ወንድም ሴትም ነው˚ የሚል ሆነ፡፡ ዓሣ አጥማጁ ከጥያቄው በስተጀርባ
ያለውን ዓላማ ተረድቶ የማምለጫ ዘዴ በማበጀቱ የተደነቀው ንጉስ ለፈጣን ብልህነቱ ተጨማሪ 4 ሺ ዲርሃም ሸለመው፡፡

ዓሣ አጥማጁ አንድ ላይ 8 ሺ ዲርሃም ተሸክሞ ቤተ-መንሥቱን ለቆ ሊወጣ ሲል ከተሸከመው ገንዘብ ውስጥ አንዲት ድርሃም ስለወደቀችበት ሌላውን ገንዘብ መሬት አስቀምጦ ያቺን ዲርሃም ሊያነሣ አጐነበሰ። ይህን ሲያደርግ ንጉሱና ሚስቱ ይመልከቱት ነበር ድርጊት ያናደዳት ሺሪን ለንጉሱ 'የዚህን ስግብግብና ወራዳ ሰው አድራጐቱ ተመልከት! አንዲት ዲርሃም ስለወደቀችበት
እርሷን ለማንሣት ብቻ ሌሎቹን ዲርሃሞች ከትከሻው አውርዶ መሬት ሲያስቀምጥ ያቺን ዲርሃም ከአሽከሮችህ አንደኛው እንኳን እንዲወስዳት እዚያው ትቷት አይሄድም ነበር? ስትለው
.... ንጉሱ “እውነትሽን ነው ካላት በኋላ ዓሣ አጥማጁን አስጠርቶ “ለራስህ ምንም ክብር የለህምን? አንዲት ዲርሃም ለማንሳት ብለህ እንዴት በገንዘብ የተሞላ ቦርሣህን ከትከሻህ አውርደህ ታጐነብሳለህ? አንዲቷን ዲርሃም እዚያው ትተሃት አትሄድም ነበር?
....ሲለው ዓሣ አጥማጁ-ንጉስ ሆይ! አላህ ዕድሜዎን ያርዝምልዎ፧ እኔ ያቺን ዲርሃም ከወደቀችበት ያነሣሁት ትጠቅመኛለች ብዬ ሣይሆን በዚህች ዲርሃም ላይ ባንድ ጐኗ የእርስዎ ምስል በሌላው ጐኗ ደግሞ ስምዎ ተፅፎ ይገኛል፡፡ እዚያ ትቼያት ቢሄድ በቦታው የሚተላለፍ ሰው የርስዎ ስምና ምስል ያለባትን ያቺን ዲርሃም በድንገት ቢረግጥ የእርስዎን ክብር እንደመንካት ይቆጠራል የሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው፡፡ አያድርገውና ይህ ቢከሰት ደግሞ እኔ የዚያ ወንጀል መንስዔ ሆንኩ ማለት ነው አላቸው በዓሣ አጥማጁ አስተሳሰብ የተማረኩት ንጉስ እንደገና ሌላ 4000 ዲርሃም ሸለሙት፡፡

ዓሣ አጥማጁ የተሸለመውን 12 ሺ ዲርሃም ተሸክሞ ከቤተ-መንግስቱ ሲወጣ ንጉሱ ባለሟሎቹን በመሰብሰብ “ከእንግዲህ በሴት ምክር ላይ ተመርኩዛችሁ ምንም ዓይነት ውሳኔ አታስተላልፉ:: ይህን ካደረጋችሁ እንደኔ ዲርሀሞቻችሁን ልታጡ ትችላላችሁ" በማለት ፈገግ😃😁 አስባላቸዉ፡፡

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➊➊
#ወንድም_መተኪያ_የለውም
አሚር ሰይድ

አንዲት ሴት ናት። የራሷ ባሏ፣ ልጇና ወንድሟ የአገር መሪውን አል-ሙንተሲር ቢላህን ለመግደል አሲረዋል ብላ ታስወነጅላቸዋለች፡፡

ባለሥልጣናትም እሷው ባቀበለቻቸው መረጃ ላይ ተመርኩዘው ሦስቱን ሰዎች እስር ቤት አስገቧቸው፡፡ ጉዳያቸው ከተጣራ በኋላ አልሙንተሲር ቢላህ ሦስቱ ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ሴትየዋ ይህን ውሳኔ ስትሰማ ግን ሮጣ ወደ መሪው ቤት በመሄድ በእግራቸው ላይ ወደቀች። ለቤተሰቧ አባላት ምሕረት እንዲያደርጉ ወይም እሷንም ከነርሱ ጋር እንዲገድሏት ተማፀነቻቸው አልሙንተሲር ቢላህ የሴትየዋ ሁኔታ ስላሳዘናቸው ጥቂት ካሰቡ በኋላ “አንቺ ሴት ምልጃሽን ተቀብዬአለሁ፡፡ ምሕረት የማደርገው ግን ከሦስቱ ሰዎች ለአንዱ ብቻ ይሆናል:: የትኛውን ከቅጣቱ እንዲተርፍልሽ እንደምትፈልጊ መወሰን ያንቺ ፈንታ ነው አሏት፡፡

ሶስቱንም ስለምትወዳቸው ማንን እንደምትመርጥ ግራ የገባት ሴት ከብዙ ማሰብ በኋላ እንዲህ የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች።
>ሌላ ባል ማግባት ይቻላል፣
>ሌላ ልጅም መውለድ ይቻላል፣ ወንድሜን ግን መልሼ ላገኘው አልችልምı እሱ ከተገደለብኝ በምንም ልተካው አልችልም ስለዚህ እሱ እንዲተርፍልኝ እመርጣለሁ* በሴትየዋ ብልሀነትና አርቆ አስተዋይነት የተደነቁት አልሙንተሲር ቢላህ ሶስቱንም አሰናበቷት ዘመዶችሽን ምሬልሻለሁ ይዘሻቸው ሂጂ በማለት አሰናበታት፡፡

ወንድም መተኪያ ያለዉም!!!


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/20 23:00:30
Back to Top
HTML Embed Code: