Telegram Web Link
✏️✏️ ወደ መፀዳጃ ቤት ከመገባት በፊት ከሰይጣናት በአላህ መጠበቅ

ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ ማለት ..

   መፀዳጃ ቤቶች የሰይጣናት መኖሪያዎች ናቸዉ፡ የሙስሊምን እነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰይጣን ሊገባበት ይችላል፤ በሩቃ  ጊዜ አንዳንዴ ጂኖቹ  ከሰይጣናት ሳይጠበቅ ወደ መፀዳጃ ቤት በመግባቱ ምክንያት ነዉ ልገባበት የቻልኩት" በማለት ይናገራሉ

(ዉዳሴዎች) ናቸዉ” በማለት መለሰልኝ፡ ነብዩ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ የሚከተለዉን ዚክር (ጸሎት) ይሉ ነበር፡-

‎ (بسم الله اللهم إني أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْحُبْثِ وَالْخَالِيث ‎ ቢስሚ አላህ አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነ አል ኹቡሲ ወ አል ኸባኢስ” (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ትርጉም፡- በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ

እጠበቃለሁ፡፡

✏️✏️ የሶላት መከፈቻ ዚክር

የሚከተለዉን ጾለት በሶላት መክፈቻ ወቅት ማለት፡፡ ጁበይር ኢብን አል ሙጥዒም የሚከተለዉን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እንዲህ አሉ፡- ነብዩ ሲሰግዱ አየሁዋቸዉ እንዲህም ሲሉ ሰማሁ፡-


“አሏሁ አክበር ከቢራ፤ ወል ሃምዱ ሊላሂ ከሲራ፣ ወሱብሃነ አልሏሂ ቡክረተን ወአሲላ (ሶስት ግዜ)።
☞ አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ሚን ነፍኺኽ ወነፍሲኺ ወሀምዚሂ

ትርጉም፡- አላህ ታላቅ ነዉ፡፡ አላህ በብዙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጠዋት በማታ አላህ ፍፁም ነዉ፡፡ ከተረገመዉ ስይጣን ከትምክህቱ፤ ከግጥሙ እና ከእብደቱ በአላህ እጠበቃለሁ፡

✏️✏️ የጋብቻ ህይወትን በሶላት መጀመር

ዓብደላህ ኢብን አል መስዑድ የሚከተለዉን አስተምረዋል። “ከመጀመሪያዉ የጫጉላ ግንኙነታችሁ በፊት ሚስትህ ሁለት ረክዓ ሶላት እንድትሰግድ አድርግ፡፡ አንተም ስገድ፡፡ ከዚያም የሚከተለዉን ፀሎት አድርግ፡-


አሏሁመ ባሪክ ሊ ፊ አኽሊ ወባሪክ ለኁም ፊዬ፣አሏሁመ ኢጅመዕ በይነና ማ ጀመዕተ በኸይሪን.. ወፈሪቅ በይነና ኢዛ ፈረቀተ ኢለ አል ኸይር” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

ትርጉም፡- አላህ ሆይ በረካ ያላት ሚስት አድርግልኝ፣ በእኔ ላይም በረካ አድርግ ለበጎ እስከተስበለብን ድረስ አንድ አድርገን፡፡ ወደ መልካም በምትለያየን ጊዜ ለያየን፡፡

✏️✏️ በግንኙነት ወቅት የሚባል ዱዓዕ

ነብዩ የሚከተለዉን አስተምረዉናል “ማንኛዉም ሰዉ ከባለቤቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሊፈፅም ሲል የሚከተለዉን ዱዓዕ ካለ በዚህ ግንኙነታቸዉ ልጀ ቢፈጠር ልጁን ሰይጣን በፍጹም ሊጎዳዉ አይችልም ::

‎ بِسْمِ اللهِ اللَّهُمَّ جَنِّبْنَا الشَّيْطَانَ፣ وَجَنْبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنا ‎ ቢስሚላህ። አሏሁመ ጀኒብና አል ሸይጣን፤ ወ ጀኒብ አል ሸይጣን ማ ረዘቅተና

ትርጉም፡- አላህ ሆይ! ከኛ ሰይጣንን አርቅልን፡፡ ከሰጠኸን ሲሳይ ላይም ሰይጣንን አርቅልን፡፡

📌📌 በአንድ ወቅት በጂኒ የተለከፈን ሰዉ ሩቃ ሲቀራበት፡፡ ጂኒዉ እስልምናን ከተቀበለ እና ንስሃ ከገባ በኋላ ታካሚዉ ይህን ፀሎት ሳይል ሚስቱን ይገናኛት ስለነበረ ሚስቱን በወሲብ እጋራዉ ነበር ብሏል፡፡

ሱብሃን አላህ! ስንት እና ስንት እንቁ ስጦታዎች እያሉን ዋጋቸዉን ዘነጋናቸዉ!




✏️✏️ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት፡፡


ከዚያም እንቅልፍ እንስከሚያሸንፍህ ድረስ ዚክር  ማለት፡፡ ከመተኛቱ በፊት አያት አል ኩርሲይን የቀራ ከአላህ የተላከ ጠባቂ : አይለየዉም፡፡ እስከሚነጋ ድረስም ሰይጣን አይቀርበዉም የሚለዉን ሀዲስ አቡ ሁረይራ አስተላልፈዉልናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)


✏️✏️ በየቀኑ ከመገሪብ ሶላት በኋላ የሚከተሱትን የቁርአን አንቀጾች መቅራት።
የአል በቀራ ምዕራፍን ከቁጥር 1 - 5 ያለዉን
➋  አያት አል ኩርስይን እና ቀጥለዉ ያሉትን ሁለት አንቀጾች
➌ አል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎችን ሶስት አንቀፆች
   እነዚህን አንቀፆች በቀራህባቸዉ ቀናት ሌሊቱንና ቀኑን ከድግምትና ከጂኒ ልክፍት በአላህ ፈቃድ ትጠበቃለህ፡፡


✏️✏️ ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት፡፡


ይህንን በማስመልከት የሚከተለዉ ሃዲስ ተላልፎልናል። ይህን ፀሎት በቀን መቶ ጊዜ ያለ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ መቶ ምንዳ ይፃፍለታል። መቶ ሀጢያቶችን ይማራል። በዚያ ቀን እስከሚመሽ ድረስ ከሰይጣን መከላከያ ይሆነዋል፤ ይህ ሰዉ ከስራዉ ሥራ የሚበልጥ ማንም አያመጣም ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በስተቀር፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

✏️✏️ ወደ መስጊድ ስትገባ የሚከተለዉን ዱአ ማለት፡-

‎አኡዙቢላሂል አዚም፣ ወቢወጂብ አል ከሪም ወ ሱልጣኒሂ አል ቀዲም ሚነ አል ሸይጧን አል ረጅም (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

✏️✏️ ከቤትህ ስትወጣ የሚከተለው ዱዓዕ ማለት
‎ بسم الله توكلت عَلى اللهِ፣ وَلا حول ولا قوة إلا بِاللَّهِ ‎

ይህን ዱዓዕ በምትልበት ግዜ ሰይጣን እንዲህ ይላል “ተጠበክ ተመራህ፤ ተብቃቃህ እንግዲህማ ሰይጣን ይሸሽሃል ....ሌላ ሰይጣንም ሲያገኝ እንዲህ ይለዋል የተጠበቀን የተመራን የተብቃቃን ሰዉ ምንስ ልታደርገዉ ትችላለህ? ምንም ልታደርገዉ አትችልም” (አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


#ክፍል 1⃣2⃣
ይቀጥላል....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
30 አመት ወደ ኋላ የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1992

  በተሞሸረች በ3 ቀኗ የሠርጉ ድባብ በቅጡ ሳይቀዘቅዝ ፍቺው ፀድቆ ወደወላጆቿ ቤት ተመለሰች። ያለምንም ምክንያት ተፋተው ወደ እናቷ ቤት ተሸኘች። ያ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ውብ የፍቅራቸው ጊዜ በድንገት አከተመ። ሚስት የስቃይ ህይወትን መግፋት ጀመረች። እሱም ከሷ በኋላ ሳያገባ ድፍን ሰላሳ ዓመታት አለፈ። ሲህር ነበር ያለያያቸው የሠርግ ቬሎዋን ጠቅልለው ከሞተ ሰው አስክሬን አፍ ላይ ፎቷቸውን አስረው ቆፍረው ከመቃብር ስፍራው ቀበረው በስቃያቸው ተደሰቱ።

ሲህሩ ተገኝቶ ከተቀበረበት እንደወጣ ሚስቱ ድና ወደመልካም የጤንነት ሁኔታዋ ተመለሰች። ባል ወደ ቤተሰቦቿ አቀና። ሚስቱን በድጋሜ ተንበርክኮ ጠየቀ። አዲስ ፍቅር ቤታቸው ገባ። ጤንነት ከደጃፋቸው ደረሰ። ፍቅራቸውም አገረሸ። በ2022 ዳግም በእልልታ ተሞሸሩ።

የአክስቷ ልጅ ነበረች ሲህሩን ያሰራችባት። ቬሎዋን ቀዳ ለደጋሚው የሰጠች። ሳሂሩ ጥቁር ዶሮ አሽከርክሮ አንገቱን በጠሰና ደሙን ከፎቷቸው ጋር ለውሶ ከጀናዛ አፍ ጋር አስሮ ህይወታቸውን በስቃይ እንዲገፉ አደረጋቸው። አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ አዘነላቸው ከድፍን ሰላሳ አመታት በኋላ ከአፊያው ዳብሶ ዳግም አገናኛቸው።
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ
             
          
                 ⭐️
#ክፍል👉 አስራ ሁለት 1⃣2⃣


  🔰🔰በተከታታይ ➊➊ ፓርቶች ድግሞትና ሲህር ከሚለዉ መፅሀፍ 70% በራሴ ካነበብኳቸዉ ከማቃቸዉ 30% ጨምሬ ከሰዎች ታሪክ በመጨመር በምሳሌ አቅርቢያለሁ ..ከpart ➊➋ ጀምሬ እስኪ ከሰማሁት ከማቀዉና መረጃዎችን በማጣቀስ ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡


መጀመሪያ ብዙሀን ሰዉ አናምንም እኛን አይነካንም እንላለን ...ግን በራስ ሲደርስ ነዉ የሚታወቀዉ  የኢማን የመጠንከር የመላላት ጉዳይ አይደለም የሆነ የምንዘናጋበት ቀን አለ በዛ ቀን በሰዉ ምቀኛ በተለይ በቅርብ ጓደኛ በቅርብ ዘመዶች ሊያነጣጥሩብን ይችላሉ ....የት ይሰራል ብላችሁ ካሰባችሁ ...ብዙዎች እነሸህ እነ ወልይ የወደፊት ያቃሉ እያሉ እየሄዱ እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ ጀለብያ ጥምጣም ለብሰዉ ሳሂር ደጋሚ የሆኑ እንዳሉ አንዘንጋ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዉ ከሙስሊሙም ሌላም ሀይማኖት ተከታዮች የሚሄዱት ደብተራዎች ጋር ነዉ፡፡ 
ደብተራዎች face book እና tg ቻናል አላቸዉ ለምሳሌ ሁለት የማቀዉን ከtg ያገኘሁትን ከታች ተመልከቱ

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
መርጌታ ገብረ መድን በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ለማይችሉ ባሉበት እንሰራለን የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል   ☎️  09 ... 03 ....☎️ ስልኩን ያጠፋሁት ደግሞ እንዳደዉሉ ብየ ነዉ☺️
ለገበያ>>ለሀብት>>ለስንፈተ ወሲብ (ለቁመት:ለውፍረት: ቶሎ ለሚያበቃ) >> ለመስተፋቅር >>ጥይት ለማያስመታ >> ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ >> ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)>> ለፀር (ለጠላት)>>ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)>> ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)>>ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)>>ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)>> #መስተፋቅር>> ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
>> ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ>> ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)>> የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ>>ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)>> መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)>> መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)>> ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)>>ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)>> ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ>> ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ>> ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)>> ለሙግት>> ለሰላቢ>> ለስንፈት ወሲብ>> ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)>> ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)>> ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)>> ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)>> መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)>> ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)>> ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)>> በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው >> እንቅልፍ መብዛት>> የእንቅልፍ ማነስ >> የወር አበባ ችግር ካለ

09...  03 ....
ይደውሉልን

✏️✏️በተጨማሪ የሌላዉን በtg የሚፓስተዉን ልላክላችሁ👇👇👇👇

☎️📞09 4............5  የባህል መድህኒት  ጥበብ አስማት ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
መፍትሄ ሀብት መስተፋቅር = የገበያ  ለቀለም= ትምህርት ለአይነ ጥላ= ለመፍትሔ ስራይ= ለህማም = ጋኔን ለያዘው ሰው = ቡዳ ለበላው = የዛር ውላጅ ለተዋረሰው = ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) =  ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) =  ለቀለም(ለትምህርት) = ሰላቢ የማያስጠጋ =  ለመፍትሔ ሀብት =ለመስተፋቅር =  ለገብያ =  ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) = ለመድፍነ ፀር =  ሌባ የማያስነካ = ለበረከት
= ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) = አፍዝዝ አደንግዝ = ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) = ለግርማ ሞገስ =  ለዓይነ ጥላ
=  ለሁሉ መስተፋቅር =  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ = ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) = ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ =  ለድምፅ =  ለብልት እንደመቆም =  ለኤች አይቪ መድሀኒት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

ለጥያቄወ 📞☎️09 4........5 ይደውሉልን በአካል መቅረብ ለማትችሉ በሙሉ ወደ አሉበት ቦታ ድረስ ይደርሶዎታል

ይላል በTelegram በfacebook በጣም ብዙ አሉ ይሄን የላኩላችሁ ሲህር ድግምት ለእናንተ መጥፎ የሚስቡ መጥፎ ሰዎች እነዚህ ቦታ ቢሄዱ አስባችሁታል?? እነዚህ ቦታ ሂደዉ መስተፋቅር ወይ ገበያ እንድንከሰር ወይ ሌላ ነገር ቢያሰሩበን በእኛ ኢማን ድክመት በጣም ከባድ ነዉ ፡፡ እናም ብዙ ሰዉ የለም የሚል ካለ ራስን ማሞኘት ነዉ ደጋሚዎች ደብተራዎች በየሀገሩ በየመንደሩ አሉ፡፡


📌📌ማወቅ ያለብን የደብተራ ብቻ አይደለም ..በጣም በዙ ሙስሊም ተብለዉ በየገጠሩ የሚሰሩ አሉ ዱአ ላስደርግ ምናምን ጫት የሚቃምበት በጣም የሚበዛ ከሆነ ..ወይም በጫት እናስለቅቃለን ካሉ ዛር አለባቸዉ በጫት የሚያስለቅቀዉ ለትልቅ ጅን ይገብራል ማለት ነዉ እንወቅ እባካችሁሁሁሁ  ....

ወልዮች ሸሆች ጋር እያልን ጫት የሚቅሙ ጋር እየሄድን ባንዘናጋ ኸይር ነዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደዚህ እያለ የሚሄድን ወጣትም ሆነ ትልቅ ሰዉ ሰዉየዉን ባንቀርብ ወይ ሰዉየዉን ከቀረቡ እራቅ ብሎ በዉዲዕ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

የሚገርመዉ ነገር አንድ የገጠር ሰዉ የማምነዉ ለጅን ማረድ ከተወ ቡሀላ ሲያወራኝ ለጅን የሚያርድልን ሰዉ የመስጊድ ኢማማችን ነዉ ብሎኛል ...

አሏሁ የስቱርና


--------- ------ ------ ------ -----
   📚📚ግን አንዳንድ ፍቅሮች እንዴት ነዉ ???🙄

አሁን ላይ ግራ የገባኝ ነገር አለ ፍቅር እንዴት ነዉ???
ፍቅር አለ ወይስ የለም ማለት ለማለት እየከበደ ነዉ ..ፍቅር አንዳንዴ የሲህር በሽታም ሊሆንም ይችላል ብቻ እኔ አሁን ግራ እየገባኝ ያለ ፍቅርን እንዴት መገለፅ ይቻላል መልስ የሌለዉ ጥያቄ...

ግን እስኪ ከዚህ በታች አይነት ታሪክ የደረሰባችሁ ካለ በአስተያየት መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ...ግን በፊት እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ወይም እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ ብለዉ በፍቅር ሲያለቅሱ ሲሰቃዩ የነበሩ..እንደ አጋጣሚ ወይም በሌላ ምክንያትም ቢሆን ታመዉ ሩቃ ሲገባ እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ያሉትን ሰዎች 80% እሱ ጋር ቢኖሩም ባይኖሩም ምንም አይመስላቸዉም...ከሩቃ ቡሀላ አፍቃሪዉ ሲህር ወይ ጂን ከነበረበት ከለቀቀ አፍቅረዋለሁ የሚለዉ ሰዉ ረጋ ማለት እና መረጋጋት ይታይበታል፡፡👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

          
           ⭐️
#ክፍል👉አስራ ሶስት 1⃣3⃣



🟢 ጊዜዉ ከባድ ነዉ ልንገራችሁ እስኪ ብዙ መንገር ይቻላል
ግን ለመስማት የሚዘገንን ነዉ ግን ይሄ ከሌላዉ አንፃር ይሻላል ብየ ነዉ፡፡


  አንዲት እህታችን 7 ልጅ አላት..ባሏ የከባድ መኪና ሹፌር ነዉ እናም ብዙ ቀን እቤት አያድርም፡፡ እቤት ስለማያድር ሚስቲቱን ሌላ ወንድ ጋር እኔ ሳልኖር ብትሄድ ወይ ብትተኛብኝስ??ብሎ ይጠረጥራታል ፡፡
ጊዜ የማያመጣዉ የለም የመጨረሻዉ ልጅ ይታመምና እኛ ሰፈር ያለ ሩቃ የሚያደርግ አንድ ብር የማይቀበል ለአላህ ብሎ የሚሰራ ነበር እሱ ጋር መጣች ልጁን በተወሰነ ደቂቃ በአላህ ፍቃድ በአፉ ብዙ ነገር ወጥቶ ሻረ....እናቲቱም እስኪ እኔም ለሊት ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስትለዉ በቁርአን ገና ጀመር ሲያደርግ...ለማመን ይከብዳል እርይ ማለት ጀመረች...ጂኑ ተነቃብኝ ተጋለጥኩ ተጋለጥኩ ማለት ጀመረ...
ከዛ ልጁ ጂኑን መጠየቅ ጀመረ...ጂኑ ሲናገር...
ባሏ እሷን አያምናትም ሹፌር ስለሆነ ሌላ ጋር ብትማግጥስ ብሎ ስለሚያስብ ሶስት አይነት ሲህር(ድግምት) ጎጃም ሂዶ 10,000 ብር ከፍሎ አሰራ እሱ እያሰራ ለእሷ ግን የአስቤዛ የለኝም ይላታል፡፡ የተሰራዉ የተላክነዉ 3 ጂኖች ነን የተሰጠን ስራ
➊ ቤተሰብ ጋር እንዳትስማማ ልጆቿ እንዳይወዷት አንቺ ነገረኛ ነሽ አባታችን ነዉ ለኛ የሚያስብልን ብለዉ እሷን
እንዲጠሏት...የእሷም የእሱም ዘመዶች ነገረኛ ከፉ ነች ተብላ እንድትጠላ
➋ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን እንድናጠፋ
➌ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች በአደባባይ እንድትጋለጥ በዛ እፍረት እብድ እንድትሆን ነዉ ያስደገመባት ...

ድግምቱን ይዘን መጥተናል የመጀመሪያ ከልጆቿ ከቤተሰቦች እንዳትስማማ አሳክተናል፡፡ ግን ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን አጥፍተን እብድ ለማድረግ በሰከንድ ከእኛ እይታ ተደብቃ አታቅም በየሰከንዱ እንሰልላታለን እሷ ግን የዋህ ታማኝ ነች እንኳን ከሌላ ወንድ ጋር ልትተኛ ..ልጆቿ እሷን ባይወዷትም  በሰገደች ቁጥር ለልጆቿ ለባሏ  ዱአ ታደርግላቸዋለች...
ከዛ ትለቃላችሁ ሲባል አዎ እንለቃለን ግን እሱ መጥፎ ሰዉ ነዉ ይቺ ምንም የማታቅ ሚስኪን 7ልጅ ለማሳደግ እየተጨነቀች እሷን በዚና ጠርጥሮ እንደዚህ አድርጓታል አንለቀዉም ብለዉ ከእሷ ሰዉነት ጅኖቹ ወጡ

እናም ጊዜዉ ከብዷል ጎበዝ
ወላሂ እኔ ብዙ የማቀዉ ብነግራችሁ ጓደኞ ዘመድ ቤተሰብ ጋር ያለን ግንኙነት ትንሽ እንዳይሻክር በመፍራት ብዙዉን ከመፃፍ ተቆጥቢያለሁ
☞ እህት በእህት/እህት በወንድም/ወንድም በእህት
☞ሁለተኛ ወይ የመጀመሪያ ሚስት በባሏ
እስኪ አስተዉሉ ሸሪአዉ ፈቅዶ አቅም ኑሮት ሁለተኛ ሲያገባ በጣም ከባድ ፀብ ጭቅጭቅ በአንዷ ቤት ይኖራል ..ከአንዷ ጋር በጣም ፍቅር ከአንዷ ጋር ፀብ ምናምን በቃ ያገባዉ የተለያዩ ባህሪ ፀባይ እስከ ፍች ወይም ለሁለቱም ሚስቶቹ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ እንጃ ወንዶች መጠርጠሩ አይጎዳም
☞ የዘመድ የጎረቤት ያለ ጉድ ከባድ ነዉ...ብቻ የሚሻለዉ #ከሰዉ_ጋር_ያለንን_ግንኙነት_በዉዱዕ_መሆን_ነዉ_ያለብን

🟢 በደንብ አዉቀን ልናሳዉቅ ለሌች ትምህርት ልንሰጥ የሚገባዉ አንዳንዴ በዲን እዉቀት ጠለቅ ብለን የማናቅ ሙስሊሞች ላይ ሸክ ጥርጣሬ የሚገባን ጉዳይ አለ እሱም ...ጂንን ሲህር ድግምትን
🔶 ክርስቲያኖቹ በፀበል እያስለቀቁት አይደል እንዴ
🔶ጴንጤዎች አሜን እያሉ እያተበተቡ ያስለቅቁ የለ እንዴ
🔶 አንዳንድ ሸሆች እየቃሙ ያስለቅቁ የለ እንዴ
🔶 ጠንቋዮችም ሲያስለቅቁ እያየን አይደል እንዴ

አንዳንዶቹ ሲሞግቱ ከባድ ጂን ወይም ብዙ ሲህር አይነጥላ ከሆነ ቀናቶች ይፈጃሉ በቁርአን ይሄን ያህል ቀን ይፈጃል በፀበል ጠንቋይ ቤት ግን በአንድ ቀን ይለቃል ታዳ ከቁርአን ዉጭ ፀበልም የጴንጤዎች ቦታ የታመዉ መሻሉ እንጂ ለምን አንወስድም?? እያሉ እየወሰዱም ነዉ...ግን ክርስቲያኖችም ጴንጤዎች  እንዴት ማስለቀቅ ቻሉ??የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ

🌀 #ለምሳሌ በቫቲካኖች (ካቶሊኮች)  ህክምና እነርሱ ዘንድ ሊታከም የመጣ ሰው በኮከብ ውስጥ አስረው እና ጥላሸት ቀብተው እነሱ ትልልቅ ጂኖችን እያዘዙ ሰዉየዉን የያዘዉን ትንሽ  ጂን ከቦታው ያስወጣሉ። አዎ ይህ ህክምና ይሰራል ምክንያቱም ለደካማ ጅን ሁሌም ቢሆን ጠንካራ ጅን አለ ። ይሁንና ይህ ታካሚ ኢፍሪት የያዘው ወቅት ላለመውጣት ታካሚውን ሙሉ ለሙሉ ገድሎና ሰውነቱን ቀጭቶ ይወጣል። ከ 100% 25%ድንገተኛ ሟቾች ናቸው።

ይህ አይነቱ ህክምናም በተለያዩ እምነቶች ያለ ሲሆን ህክምናቸውም ሲህርን በሲህር በጅን እያደረጉ አስማት ነው በማለት ሰዎችን ይሸነግላሉ ።

አስማትን በአስማት ማከም መታከም ለድንገተኛ ሞት ይጋልጣል።ለምን የሚያዟቸዉ ትልቅ ጅንን ነዉ ሰዉየዉ የያዘዉ ከሚታዘዘዉ ጅን በላይ አቅም ካለዉ ከባድ ነዉ ሰዉየዉን በሂደት እስከመግደል ይደርሳል፡፡

ለምሳሌ እስኪ እሰቡት እስኪ በወንዶች በፊት ስናድግ በሰፈራችን የሰፈር አለቃ አለ እንበል....እሱ የፈለገ ቦታ ይልከናል እምቢ ብንል ይመታናል ያለን አማራጭ መታዘዝ ነዉ፡፡ ወይም መንግስት ግዴታ ይሄን አድርግ ካለን ምን አማራጭ አለን??? ምንም ግዴታ ከማረግ ዉጭ..,,እናም ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ ተፈሪ የሆኑ ጅንኖች ትናንሽ ደካማን ፈሪን ከሰዉየዉ ገላ  የማስወጣት አቅም አላቸዉ

በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡

☑️ ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።
ጂኒዎች እንደኛዉ ናቸዉ እነሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ ስለሆን ነዉ እንጂ

#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡

ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ወራትም አመታትም ሊሆን ይችላል ጠንቋዩ ጋር ጅኑ እንደስምምነታቸዉ ነዉ ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ማካሄድ አለባቸዉ መቼም አይለቅም  ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡

🌀 በፀበል ደግሞ ላላችሁት በሚዲያ ላይ ማዉጣት ይከብዳል የሆነ የሚሰማ የማቀዉ ስላለ ነዉ፡፡ወሎ ሲባል ቅልቅል ነን እኔም ብዙ ቤተሰቦቼ ክርስቲያን ናቸዉ👇👇
ከእነሱ አንዳንድ የምሰማዉም አለ....እስኪ በመጀመሪያ የራሳችንን እንወቅ ሙስሊም መስለዉ የሚሸዉዱት  ጥንቃቄ እናድርግ የሌላዉ ይደርሳል...ብቻ በፀበል
ይለቀናል ባላችሁ ሂዳችሁ የብስ ህመም ጨምራችሁ እንዳትመጡ ....
🌀 እነሸህ ተብየ ጫት ቅመዉ ወይ በዛር የሚያስለቅቁ ይሄ በቀላል ቋንቋ 90% እርግጠኛ ሁኑ ለጅን ይገብራሉ ትልቁ ጉልበተኛዉ ጂን ለትንሹ ቀላል ነዉ ...ሲያጎራ ሲጮሁ ሰምታችሁ ከሆነ በጣም ለአቅል ይከብዳል ሲለፈልፉ በእነሱ አድርጎ ይወጣል፡፡
አንዳንዴ ዛር ያለበት እያጨበጨበ እየጨፈረ ሲያስለቅቅ ያየሁት አሉ ጅኑ አጨብጭብ ጨፍር ብሎት ወላሂ በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡ ግን ይሄ ለጅን ግብር ነዉ ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም ልጅን ይይዛል፡፡
የሀሉም መፍትሄ ቁርአን ብቻ


 🟢  አይንናስ(ቡዳ) ..ሲህር..ጂን ብዙዎቻችን ላይ ያለ ይመስለኛል ለምን ብዙሀን ሙስሊሞች ከዲናችን  የተዘናጋን ስለሆነ ራሳችንን ቆም ብለን ብናይ  ጥሩ ነው.....ብዙዎቻችን
✏️ የጠዋት ማታ ዚክር ማድረግ አቁመናል
✏️ ቁርአን ስልክ ከመጣ ቡሀላ የምንቀራ በጣት የምንቆጠር ነን ሁሉም በስልኩ ቁርአን አዝካር አለ ያንን ለመቅራት ነይቶ ስልኩን ሲነካካ ወደ ማህበራዊ ሚዲያላይ ነዉ የሚወስደን፡፡ ግን አስተዉለናል?? በፊት ስልክ ሳይመጣ እኮ ለቁርአን ያለን ፍቅር ዚክር ለማድረግ ያለንን ጉጉት የተለየ ነበር ግን አሁን ማን ነዉ ቁርአንን አክብሮ ገልጦ የሚቀራዉ??የሚሻለዉ በስልክ ቁርአን መቅራት ብናቆም የተሻለ ነዉ እናም
የኛ ከቁርአን መዘናጋት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳለፍ ከዲን የመዘናጋት ስለሆነ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ
✏️ በማህበራዊ ሚዲያ በTG..Whatsap..facebok..instgram ወዘተ የምናደርገዉ profile pictur ፎቶ ለአይን ናስ(ቡዳ) መበላት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምን ጀሊሉ ሲፈጥር ማስጠሌ ብሎ የፈጠረዉ የለም ግን የሰዉ አይን የፈለገዉን ቆንጆ የፈለገዉን ማስጠሌ አድርጎ ይስላል፡፡ profile ስታደርጉ እራሱን ወይ እራሷን እንደ ማስጠሌ የምታይ ዉይ ሲያምር ወይም ዉይ ስታምር ሊሉ ይችላሉ እናም profile ከማድረግ እንጠንቀቅ

✏️ በtiktok ላይ video የምፓስቱም የሰዉ አይን ሰለባ ስለምትሆኑ መጠንቀቁ አይጎዳም...እስኪ እኔ ብዙም ግንዛቤዉ የለኝም በtiktok የሚታወቁ ሰዎች ትዳር አላቸዉ የላቸዉም? ካላገቡ መቼም የሚታዩት ቆንጆ ናቸዉ እንዴት አላገቡም?
መጀመሪያ በሚዲያን የቀረበ ራሱን ጨረታ ያወጣ በሀራጅ ተከስሮ ነዉ የሚሸጠዉ ጨረታ እቃ ያሸነፈ ነዉ በሀራጅ ይገዛል ኦዲት ሲደረግ ይወድቃል
በመቀጠል ግን የሰዉ አይንም(ቡዳ) ችግር ሊሆን ይችላል
✏️ ያለቅጥ የተካበደ ሰርግ ብራይድ ማድረግ በሰዉ አይን የመበላት አቅሙ ሰፊ ነዉ ለምን በዚህ በኑሮ ዉድነት ባለበት ዘመን የሚበላ የሚጠጣ ቤት ኪራይ መክፈል በአቃቃተበት ዘመን ያለቅጥ ደስታ በደሀ እምባ መቀለድ ነዉ የእናንተን ሰርግ ደሀ ሲያየዉ ወይ የበላችሁበት ወይ የጠጣችሁበት ምግብ ላይ ወይ የለበሳችሁት ልብስ ላይ አይኑ ያርፋል እናም የተቸገረ ሰዉ ቀልብ አይን ከባድ ነዉ ፡፡
በተጨማሪ በዚህ ወንዱ ብር ማስተዳደሪያ ሴት ደግሞ ባል ባጣችበት ዘመን በሚዲያ ሰርጋችሁ ተካብዶ ሲያዩት ወንዱም ወይኔ ትንሽ ኑሮኝ በነበር ሴቷም እድለኛ  ነች የሚያምር ባል አግብታለች ባይባል ጥሩ ነዉ የሰዉ አይን ከባድ ነው፡፡

የተወራለት በሚዲያ የታዩ ሰርጎች ብዙዎች ፍች ተፈጥሮ ደብቁኝ ደብቁኝ እያሉ ነዉ እናም ሁሉም በልክ ይሁን

✏️ ልጅ ሲወልዱ በደስታ prpfile pictur ማድረግ ይሄ ደግሞ በጣም ከባድ ነዉ ልጅ ያጣ ያላገባ ባለበት ዘመን ማሻ አላህ ሳይሆን አይኑ አፍንጫዉ መልኩ እናቱን ወይስ አባቱን በሚባልበት ዘመን profile ባይደረግ ባይ ነኝ፡፡

✏️ ከሰዎች የተለየ ልብሶችን መልበስ እና ቀን በቀን መቀያየር ይሄም ልብስ ያጡ አይኖች ላይ ትኩረት መግባት ነዉ ፡፡ ዱንያ ነዉ መብላት መጠጣት መልበስ ነዉ ማለት ቡሀላ ምነዉ ባልበላሁ ባልጠጣሁ ባለበስኩ ከማለት ሁሉን በልክ ማድረግ እና በዚክር በቁርአን መንቀሳቀስ ነዉ

⚡️⚡️⚡️   በሰዉ ህይወት ቀንታችሁ በማወቅም ባለማወቅም ያሰራችሁ ካላችሁ ጉዳቱ ለተደረገበትም ለእናንተም ጭምር መሆኑን አትዘንጉ የተዉበት ጊዜዉ ገና ነዉ ወደአላህ እንመለስ ...እኛ የምናምፀዉ በወንጀል ድንበር የምናልፍበት ጌታችን ቅርብ ሁኖ እያየን እንደሆነ አንዘንጋ....
ጌታችን አሏህ ሱወ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይለናል
“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፣ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፣ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ለምመሩ፡፡ ይከጀላልና፡፡” (አል-በቀራህ፡ 186)

ታዳ ለምን እኛ የሰዉንም የራሳችንን ህይወት ለማበላሸት ደጋሚዎች ደብተራዎች ጠንቋይ ቤቶች እንሄዳለን??
የምንመቀዉን ሰዉ የሰጠዉ አላህ ለምን ለእኛስ ስጠን ብለን ወደ ጠንቋይ ከመሄድ ወደ ጀሊሉ እጃችንን አንዘረጋም??

በሐዲሥ አልቁድሲይ እንደተዘገበው አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- የሰው ልጅና አጋንት በሚገርም ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ እፈጥራለሁ  የሚመለከው ሌላ ነው፡፡ ሲሳይ እሰጣቸዋለሁ የሚመሰገነው ሌላ ነው:: መልካም ነገር ሁሉ ከኔ ወደ ባሮቼ ይወርዳል፤ የነሱ መጥፎ ነገር ወደኔ ይወጣል፡፡ ከነርሱ የተብቃቃሁ ሆኜ ሳለ በእዝነቴ ወደነርሱ እወደዳለሁ፡፡ እነርሱ ግን ከኔ ፈላጊ ድሆች ሆነው ሳሉ ወንጀል በመሥራት በኔ ለመጠላት ይሠራሉ፡፡ ለኔ ቅርብ የሆኑት እኔን የሚያወሱት ናቸው፡፡ እኔ   የምወዳቸው እኔን የሚታዘቡት ናቸው፡፡ ወንጀል የሚሠሩትን ከእዝነቱ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም፡፡ በተዉባ ወደኔ የሚመለሱትን እኔ ወዳጃቸው ነኝ፡፡ ቢያምፁም አካሚያቸው እኔ ነኝ፡፡ በችግርና መከራ የምፈትናቸው ከነውር ላፀዳቸው ነው፡፡ ተውባ አድርጎ ወደኔ የሚመለስን ሰው ገና ሩቅ እያለ እቀበለዋለሁ፡፡ ከኔ ዞር ብሎ የሄደውን በቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ፡፡ ከኔ ውጭ ሌላ አምላክ አለህ እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው?› እለዋለሁ፡፡
በተጨማሪ

አላህ ለነብዩ ዳወድ እንዲህ አለ፡- ዳውድ ሆይ! ለኔ ጀርባቸውን የሰጡ ሰዎች (ወደኔ በመመለሳቸውና ተፀፅተው በመምጣታቸው) ለነርሱ ያለኝን ጉጉት ቢያውቁ ኖሮ ለኔ ከሚኖራቸው ጉጉት የተነሳ በቀለጡ ነበር፡፡ ዳውድ ሆይ! ይህ ለኔ ጀርባቸውን ለሰጡ ሰዎች ያለኝ ፍላጎት ነው፡፡ ፊታቸውን ወደኔ ላዞሩ ሰዎች እንዴት የሚሆን ይመስልሀል?
አላህ እንዲህ እያለ ይወቅሰናል
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳፅና ከቁርአንም ለወረደዉ ልቦቻቸዉ ሊፈሩ ጊዜዉ አልቀረበምን??
አላህ እየወደደን ወደኔ ቅረቡ እያለ ይለምናል እኮ
እናም ያለፈዉ ስህተት ከነበርን ቶብተን ወደ አላህ እንመለስ ያስደረግንም ካለን በሰዉ ህይወት አንጫወት ላንጠቀም ነገር ሲህሩ ድግምቱ እንዲፈታ እንዲቆም ማድረግ አለብን፡፡
ህሊና ላለዉ ሰዉ  ሲህር አስደርጎ የተደረገበት ሰዉ ሲሰቃይ ሲቸገር ሲታመም እንዴት አቅላችን ይሸከመዋል??
እንዴት ሰዉ እንዳያገባ ተደርገ የእሱ ወይ እሷ አግብቶ መዉለድ እንዴት እኛን ሊያናድደን ይችላል??ብቻ አሁንም የተዉበት በሩ ክፍት ነዉ ወደ አላህ እንመለስ


#ክፍል 1⃣4⃣
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
 
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
አሚር ሰይድ

                 ⭐️ #ክፍል👉አስራ አራት 1⃣4⃣




🟢 የሲህር(ድግምት) የቡዳ(አይንናስ ጂን ህክምናዎች


ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ እኔን በጠረጠራችሁኝ በኩል ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም ሲህር አለብን ብለን ባንጠራጠር ራሳችን ባናሳምን ጥሩ ነዉ ምልክቱ እስካልታየብን ድረስ
...በተጨማሪ በዉዱዕ የምንቀሳበቀስ ..የጠዋት ማታ ዚክር የምናደርግ...
>> አላህ የከከለልንን የምንከለከል ከሆነ 
>> ዚናን ሙዚቃን ዉሸትን ስርቆት የየቲም ሀቅ የሰዉ ሀቅ የሚዲያ አጠቃቀማችን ለሀላል ነገር ብቻ ከሆነ ..
>> ከትልቅም ከትንሽም ወንጀል የራቅን ከሆን በአላህ ፍቃድ ወደኛ ማንም መጥፎ ሰዉ ቢያስብ አይነካንም
ከነካንም በዲናችን ጠንካራ ከሆን ዚክር ቁርአን የምናበዛ ከሆነ እንደተያዝን ሳናቀዉ በራሱ ጊዜ ይለቀናል፡፡

🔻🔻 ግን ከላይ የጠቀስኳቸዉ በትልቅ ወይ በችንሽ ወንጀል በከፊልም በሙሉም የተዘፈቅን ከሆነ በተጨማሪ እስኪ ወደ ሆላ 3 ወይ 4አመታት አስታዉሱ የነበራችሁን ጥንካሬ
☞ አሁን ግን የኢማን መንሸራተት ካለባችሁ..
☞ ትዳር ሲመጣ ጭንቅጭ ጭንቅ የሚላችሁ
☞ከማግባት ይልቅ ለማበላሸት የሚቀናችሁ..ከዛ ካበላሻችሁ ቡሀላ የሚቆጫችሁ ከሆነ
☞ አጭቴችሁ ምነዉ አጭቼ ባልነበር ከአጨሁት ይሄኛዉ ይሻለኝ ነበር ወይም ያችኛዋ ትሻለኝ ነበር እያለ ሸይጧን ለማበላሸት የሚወሰዉሳችሁ ከሆነ
☞ ቁርአን ሂፍዝ እስከ መጥፋት..
☞ ቁርአን ስቀሩ ስታዳምጩ የሚጨንቃችሁ የሚያልባችሁ ካለ ሩቃ ቢደረግባችሁ ጥሩ ነዉ፡፡


🌐🌐 ሩቃ ሁለት ጥቅም አለዉ
#የመጀመሪያዉ በኛ ላይ ሲህር ወይ ድግምት ወይ አይነጥላ ጅን ካለ ይለቃል
#ሁለተኛ ጥቅሙ እኛ ሁሉም ከሌለብን ቀልባችን ይጀደዳል በቁርአን ጥንካሬ ያገኛል፡፡

  በራስ ሩቃ ማድረግ በጣም በላጩ ነዉ
ሩቃ ሲባል ከባድ አድርገን አንያዘዉ ..ሩቃ በቀላል ቋንቋ ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነትን ማስተካከል በዚክር በቁርአን ልብን ማርጠብ ማለት ነዉ
✏️ የጠዋት የማታ ዚክሮችን ማለት
✏️ ሲተኙ ሱረቱል ናስ ፈለቅ አሀድን ሶስት ሶስቴ መቅራት አያተል ኩርሲን መቅራት እነዚህን ስንቀራ ዉሀ በሀይላንድ ይዘን ዉሀዉ ላይ መቅራት ከዛ የሩቃ ዉሀ ሆነ ማለት ነዉ...የሩቃ ዉሀ መጠጣት ከተቻለም የወይራ ዘይት ጥቁር አዝሙድ ዘይት ዉሀዉ ላይ ጠብ ጠብ አድርጎ መጨመር ነዉ
✏️ ቁርአንን በቻልነዉ አጋጣሚ በቁርአን መቅራት..
ዚክሮችን በስራ ቦታ በትምህርት ቤት ታክሲ ላይ ሲንቀሳቀሱ ዚክሮችን ማድረግ አላህን ማስታወስ ነዉ...
🔶 #ነብዩላህ_የኑስ ዐ.ሰ ብዙ መልካም ስራ አልነበራቸዉም ጥፋት ባጠፉ ጊዜ አላህ ሱ.ወ በዓሳ ሆድ ዉስጥ ጣላቸዉ ከዚያ ያወጣቸዉ ያደረጉት ተስቢህ የአላህ ዉዳሴ ነዉ፡፡
አላህ ሱወ እንዲህ ይላል
እርሱ ለጌታዉ ከአወዳሾች ባልሆነ ኑሮ እስከሚቀሰቀስበት ቀን ድረስ በሆዱ ዉስጥ በቆየ ነበር
(አል ሷፋት 143-144)

እናም አላህን ማዉሳት መቶበት ለሁሉም መፍትሄ ነዉ
✏️ በቁርአን ዉስጥ በደረጃ ትልቅ አንቀፅ አያተል ኩርሲይ ነዉ በአንድ አንቀፅ ዉስጥ ስድስት ያህል መልካም የአላህ ስሞች እናገኛለን...አያተል ኩርሲን ባገኝንበት አጋጣሚ መቅራት


✏️ ወንጀል ላይ ካለን ዚና የምንሰራ ሙዚቃ የምናዳምጥ ትንሽም ትልቅም ወንጀል ላይ ካለን ከዛ መታቀብ
✏️ የማይጠቅሙ የማይጎዱ ጓደኞችን መቀነስ
✏️ በtv በስፒከር ቁርአን መክፈት ጆሯችን ጎን አድርገን የተለያዩ የሩቃ አንቀፆችን ቁርአኖችን መቅራት ነዉ...በአላህ ፍቃድ ጂኑ ሳይናገር ሳይለፈልፍ በራሱ ጊዜ እየተወገደ ይሄዳል፡፡
ከበፊቱ ለዉጥ ካለን እንቅልፍ እምቢ የሚለን ከሆነ እንቅልፍ መዉሰድ ከጀመረን መጥፎ ህልሞች እያየን በፊት ከነበረ ከዛ ቡሀላ መጥፎ ህልሞች ከራቁልን ..ሙዚቃ ካስጠላን ከዚና ቱብት ካደረግን ወይም ከዉሸት ከመጥፎ ጓደኛ ከራቅን በራሳችን ሩቃ ተሳክቶልናል ማለት ነዉ ...በዚሁ ኢማንን እያጠነከሩ መሄድ ነዉ

🟢 ጂን መቷቾሁ ከሆነ ወይም በምቀኛ ሰዉ ሲህር ድግምት ተደርጎባችሁ ከሆነ እኔ ራሴን በራሴ ሩቃ ማድረግ አይሆንልኝም ብላችሁ ካሰባችሁ...ሩቃ የሚያደርግላችሁ ፈልጋችሁ በቁርአን ሀይል የዛን ጊዜ መናገር ይጀምራል በአላህ ፍቃድ ይለቃል፡፡

📚📚 ከሁሉም ግራ የሚገባዉ ነገር ማን ጋር ሩቃ እንጀምር የሚለዉ የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ ለምን ቢባል አንደንድ ሩቃ እናደርጋለን የሚል በሩቃ ስም ሀራም የሚሰሩ ሴቶች ጋር የሚተሻሹ በተጨማሪም ሳይታመሙ ታመምን የሚሉ አሉ እዛ ሂደዉ መተሻሸት የሚፈልጉም ሴቶች እንዳሉ ልናወቅ ይገባል ..እናም ትክክለኞቹ ማን ናቸዉ??ግራ የሚያጋባ ነዉ

♻️♻️  ግን እኔ የምለዉ ቆይ እስኪ እቤት እናት አባት እህት ወንድም ሲታመም ምን የሚያስፈራ አለ?? የአላህ ቃል በስፒከር ከፍቶ በተከታታይ ቀናቶች መቅራት ነዉ ብዙዉ በአንድ ቀን ይለቃል እናም እኔም አንተም አንቺም እሱም እሷም ማላቀቅ እንችላለን መጀመሪያ በአላህ መተማመን አንተን ይዤ በአንተዉ ቃል ቁርአን አድነዋለሁ ብሎ ነይቶ መነሳት ነዉ እናም ሩቃ ቤት ከመዉሰድ መጀመሪያ በራስ መታገል ይበልጣል፡፡

የተለያዩ የሩቃ እወቀቶች መቅሰምና መፅሀፎችን ማንበብ ለቤተሰብህ ለጓደኛህ መሆን ይቻላል

ሴት የዲን እህትሽ ስትታም ለምን ለአጂ ነቢይ ወንድ አሳልፈሽ ትሰጫለሽ?? ሀስቢየሏሁ ወኒዕመል ወኪል ብለሽ አንቺዉ ቁርአን ቂሪባት

እህትህ ስትታመም ለምን ወንድ ሩቃ የሚያደርግ ትፈልጋለህ??
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምረዉ  ...ሀስቡነሏህ ብለህ ከጀመርክ ከጀመርሽ ሰበብ አድርስ አላህ ያግዘሀል ያግዝሻል ግን ያለስበብ ወደፊት ያለርምጃ የሚሆን አይደለም ሰበብ ግዴታ ነዉ

ሀስቡነላህ ወኒዕመል-ወኪል”
ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ እሳት በተወረወሩ ጊዜ የተናገሯት ቃል ነች፡፡
ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ፊርአውንን በመሸሽ ላይ እያሉ በሱ ያመኑ ሰዎች “እነ ፊርዐውን ደረሱብን!” ባሏቸው ጊዜ ይህችኑ ቃል ተናግረዋል፡፡
የአላህ መልእክተኛም (ሰዐወ ሰዎች "በኡሀድ ጦርነት ሰዎች እናንተን ለማጥቃት ተሰባስበዋልና ፍሯቸው ባሏቸው ጊዜ ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ይህችን ቃል ብለዋል፡፡
እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን ጀምረን ፈጣሪ አያሳፍረንም እርግጠኛ ሁኑ
  እናታችን ሀጀር ብቻዋን በዛ በርሀ  ለኢስማኢል ዉሀ ጠምቶት ሲያለቅስ ቁማ አልተመለከተችም ሰባት ጊዜ ስትዞር ነዉ  ጂብሪል ከሰማይ በመውረድ  በክንፉ እግር ስር በመጫር ዘምዘም ዉሀ እንዲፈልቅ ያደረገዉ
መርየም በዛ በምጥ ተሰቃይታ ባለችበት ጊዜ አላህ የሚበላ የሰጣት እኮ በጅብሪል አማካኝነት የተምሩን ዛፍ አወዛዉዢዉ ሲላት ስታወዛዉዘዉ ነዉ የሚበላ ያገኘችዉ...እናም አላህ የሚያግዘን ከኛ ትንሽ ሰበብ ይፈልጋል ሀስቡነሏህ ብለን መጀመር ነዉ 👇
👇
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምር እርግጠኛ ሁን አላህ አያሳፍርህም ፡፡ ችግሩ የኛ ኢማን ጥንካሬ መድከምና ተስፋ መቁረጥ ነዉ....ንብ አንድ ኪሎ ማር ለመስራት 400 km ትንቀሳቀሳለች ተስፋ አትቁርጥም ታሳካለች ታዳ አንቺ አንተ እናንተ ምን የሚያስፈራ አለ???ምን ተስፋ የሚያስቆርጥ አለ??
ለምን እህትህን ለአጂ ነብይ ወንድ አሳልፈህ ትሰጣለህ??? ለምን እኔ አልችልም ትላለህ/ትያለሽ⁉️

ሀስቡነሏህ ብለህ መጀመር አቅቶህ ነዉ ወይስ አላህ በኔ ተማመን እያለህ በአሏህ መተማመን ፈርተህ ነዉ⁉️
የጀአለሁ መኽረጃ የወሙጫ መንገድ አዘጋጃለሁ ያለህ ጀሊሉን እንዴት መተማመን አቃተህ⁉️
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል አላህን ይዘህ ሁሉም ነገር ቀላል ነዉ....አላህን ይዘን መፍራት አያስፈልግም


♻️♻️ ብዙ ሩቃ ቤቶች ሩቃን ለቢዚነስ አርገዉታል ከ3,000 እስከ 20,000 ከዛም በላይ እየጠየቁ እኔ መጀመሪያ ላይ ብር ላይ ፎከስ የሚያደርጉ ሰዎች ንያቸዉ ብር እንጂ ከአላህ አጅር እናገኛለን ብለዉ ስለማይሆን እንደነዚህ ሩቃ ቦታዎች እንጃ ብቻ ምን እንደምል አላቅም...በሀዲስ ይበቃል አይበቃም ፊርቃ ስላለዉ የሚሻለዉ ወላሁ አዕለም ግን ብዙም አይዋጡልኝ

የሚሻለዉ በራስ ኮንፊደስ ተወከልቱ አለሏህ ብሎ መጀመር ነዉ አሏህ ቁርአኑን መፍትሄዉን ነግሮናል ነብዩ ሰዐወ አስተምረዉናል እናም በራሳችን መታገሉ ኸይር ነዉ፡፡

ማወቅ ያለብን ጂን በደም ስር በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችል ዉሸታም ሰላቢ የማይጨበጥ ነዉ ፡፡ #ግን_ቁርአን_በሚቀራበት_ጊዜ_መላኢካ_ከታማሚዉ_ሰዉነት_እንዳይወጣ_ጠፍሮ_ይይዘዋል፡፡
ከዛ ቁርአን በሚቀራበት ጊዜ ለእሱ ቁርአኑ ሰይፍ ነዉ የሚሆንበት ይቆራርጠዋል ...ወላሂ ቶሎ ብለዉ ነዉ የሚወጡት ለምን ካልወጣም ሊገለዉ ይችላል ፡፡

🔰🔰ቁርአን ለሰዉ ልጅም ለጂንም ካመንበት መድሀኒት እርጋታ ከፈጣሪ ጋር ያለን ግንኙነት መጨመሪያ ነዉ....ጂኖች ያቃሉ ግን ተገደዉ ወደ ሰዉ ገላ ስለሚገቡ ለመዉጣት የላካቸዉ ሸይጧን ወይም ትልቁ ጂን ወይ የጎሳ አለቃ ጂኑ ቅጣቱ ከባድ ስለሚሆንባቸዉ ላለመዉጣት ይታገላሉ ግን የሚያሸንፈዉ ቁርአን ነዉ ተቃጥለዉ ተንገብግበዉ አይናቸዉ ጠፍቶ እግራቸዉ ተቆርጦ ድረስ ይለቃሉ ሲናገሩ ከሰማችሁ አይኔ ጠፋ እግሬ እጄ ተቆረጠ ይላሉ ቁርአን ሀይል ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ጀሊሉ ለሰጠን መድሀኒት ሀይል ብርታት ቁርአን

#ቁርአን 77430 ቃላት እና 430740 ፊደላት አለዉ አሏህ ፈጣሪያችን በቁርአን በአንድ ፊደል 10 ሀሰና አለዉ ብሎናል እናም 430740 ብናሰላዉ
🔶 በወር ሶስቴ ብናከትም 12,922,200 ሀሰና ሲኖረዉ
🔶 በወር ሁለቴ ብናከትም 8,614,800 ሀሰና እናገኛለን
🔶 በወር አንዴ ብናከትም 4,307,400 ሀሰና እናገኛለን

ቁርኣን አጠቃላይ ገፁ 604 ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በመጠኑ በግማሽ ያንሳል። ነገርግን ላለፉት 1,400 ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙፈሲሮች ማብራሪያውን ቢፅፉትም ፈፅሞ ሊጨርሱት አልቻሉም።
ለአብነት
♦️ ቁርጢቢ ➨ 21 ቅፅ 👉 5509 ገፅ
♦️ ኢብን ከሲር ➨ 10 ቅፅ 👉 6608 ገፅ
♦️ ጠበሪይ ➨ 12 ቅፅ 👉 3000 ገፅ
♦️ በገዊ ➨ 4 ቅፅ 👉 1487 ገፅ
♦️ ጀላለይን ➨ 1 ቅፅ 👉 1378 ገፅ
♦️ ሰዕዲ ➨ 10 ቅፅ 👉 6600 ገፅ
♦️ ቁጥብ ➨ 30 ቅፅ 👉 4018 ገፅ

ይህ ሁሉ ተፍሲር ለ604 ገፅ መጽሐፍ የተፃፈ ቢሆንም ሁሉም የሚችሉትን ያህል አብራሩት እንጅ አንዳቸውም አሟልተው ፅፈው አልጨረሱትም።

ከዚህ በተጨማሪ ቁርኣን በታሪክ፣ በህክምና፣ በጂኦግራፊ፣ በጠፈር ምርምርና በተለያዩ ዝርፎች የተጠና ሲሆን የተወሰነውን ቢያረጋግጡትም ገና ብዙ ያልተደረሱባቸው ምርምሮችን ይዟል።

ይህ ለሚያስተነትን ሰው በእርግጥ ተዓምር ነው።
«ይህ ቁርአን አንቀፆቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው።»
(ሑድ 1)
እናም እኛ እንደ ቀልድ የያዝነዉ የአላህ ቃል ቁርአን ማስተንተን አልቻልንም እንጂ ሀይላችን ቅዋችን ከህመም መሻሪያችን ነዉ እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን እንጀምር

⚠️⚠️⚠️ ማስጠንቀቂያ
በፊት ለጅን የሚገብሩ በግ ፍየል ዶሮ በሬ ላም ወዘተ የሚያርዱ.... የሚገበረዉ ለብዙ ጃሂል ጂን ስለሆነ መጀመሪያ ማስቶበት ወደ አላህ እንዲመለሱ ማድረግ አለብን፡፡  ማድማቱን ማረዱን ሲያቆሙ ሀይለኛ ህመም ጂኑ ይልካል  ሀኪም ቤት ሲሄዱ ጂኑ አዉቆ እንደ ካንሰር ኩላሊት ምናምን ያስብላል

የዛን ጊዜ ካንሰር ኩላሊት ደም ግፊት ምናምን ከተባለ አደራ መድሀኒት አይጀሞሩ የካንሰርም በጨረር የሚሰራ አለ ባይሰሩ ጥሩ ነዉ  ለምን ጅኑ ደም ሲቆምበት እንዲሞቱ ይፈልግና ወደ ልጅ ወይ ልጅ ልጅ ይተላለፋል...የዚህ ጊዜ ጥሩ ሩቃ የሚቀራ ተፈልጎ ማስለቀቅ ነዉ መፍትሄው፡፡ግን ይሄን ጂን ለማስለቀቅ ቢያንስ 2ወር ሊፈጅ ይችላል፡፡ ነጬ በላ/ጥቁር በላ/ራሄሎ/አንበሴ/ወንዘኛዉ/ወዘተ ለጂን በሚያርዱበት ጊዜ ያለማካበድ ከ30 በላይ የሚሆኑ ናቸዉ የሚገበርላቸዉ እናም ማረድ ሲያቆሙ ያሁሉ ነዉ ቂም ይዞ እስከ ሞት የሚደርሽ ህመም ካንሰር ደም ግፊት የሚያስብሉት  ...ግን ለመሻር እንደ ታማሜዉ ቀልብ ይወሰናል፡፡ ትክክለኛ ተዉበት ከሆነ 3ቀን ለራሱ በቂ ነዉ፡፡
ነገር ግን አደራ አደራ!!! ሳይቶብቱ ሩቃ እንዳይጀምሩ ለምን ዋናዉ ቀልብ ነዉ ቀልባቸዉ ማድማት ለጂን ማረድ ከሆነ  ሩቃዉ በጣጣም አድካሚ ነዉ የሚሆነዉ ካልቶበቱ ሰዉነታቸዉን በጣም የሚያስጠላ ሽታ ሊሸቱ ይችላሉ፡፡ እናም ማስቶበቱ ላይ ትኩረት ማድረጉ ነዉ ...
አንዲት ሴትየ ሲታመሙ ካንሰር ተብለዉ ልጆቻቸዉ ቁርአን በተከታታይ ቀን ሲያስቀሩ የዛር ጂኖቹ ይለቃሉ መልሰዉ ከሁለት ከሶስት ቀን ቡሀላ ይመለሳሉ ከዛ ለምን ትመለሳላችሁ⁉️ብሎ ሲጠየቅ
ወላሂ እኛ እንወጣለን መጀመሪያ እሷን አስቶብታት ስንወጣ መልሳ እየጠራችን ተቸገርን ለምን እሷን ሳታስቶብት በቁርአን ታቃጥለናለህብሎ ነበር የመለሰዉ ጂኑ

🟢 አንዷ እናታችን በፊት ለጂን ያርዱ ነበር ሁለት ወር ያህል ታመዉ በአላህ ፍቃድ በሩቃ ጅኖቹ ለቀቁ.,,ሴትየዋ ግን አልሀምዱሊላህ በአላህ ቃል ተሻለኝ አላሉም....እኔን ያመመኝ እኮ ባለማድማቴ ነዉ የሚደማበት ቦታ ልሂድ ብለዉ ሲሄዱ የአሏህ ስራ የሚሄዱበት መኪና ሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ከተሳፋሪዉ ሌሎቹ ሲተርፉ እሳቸዉ ግን ሞቱ😔😔 ኢናሊላህ ወኢኒ ኢለይሂ ራጂኡን አሟሟታቸዉ አላማረም....አላህ የመቶበቻ ጊዜ ሰጥቷቸዉ አልተጠቀሙበትም

   ትክክለኛ ተዉበት አድርገዉ ማድማቱን ሲያቆሙ ህመሙ ቁስለቱና ጂኑ ደማቸዉን ስለሚመጣቸዉ ደማቸዉ ይወርዳል ደም ግፊት ወይም ደም ብዛት ይባላሉ፡፡  በተጨማሪም የማህፀን ካንሰር ነዉ የመባል ቻንሱ ሰፊ ነዉ..ሰዉነታቸዉ ከበፊቱ በበለጠ መወፈር ወይም መክሳት ...ሆዳቸዉ እጃቸዉ አካባቢ ለብቻዉ ማበጥ ምልክት ያሳያል


⚠️ የምናቃቸዉ ደም የሚያደሙ ለጅን የሚገብሩ እናት አባቶች ካሉን በተጨማሪ አያቶቻችን ካሉ ብዙ የዲነል ኢስላም እዉቀት ስለሌላቸዉ በህይወት ካሉ  ይሄን ጊዜ እንዲቶቡ ማድረጉ ኸይር ጥሩ ነዉ ካልሆነ አሟሟታቸዉ እንደማያምር እወቁ ካንሰር ምናምን ሆነ ተብሎ ነዉ ህይወታቸዉ የሚያልፈዉ፡፡

ህመሙ በሽታዉ በሩቃ ለጅን ከሚገብረዉ አካል ካልተወገደ የዛር ጂን ቂመኛ ነዉ ወደ ልጅ ወይም ወደ ልጅ ልጅ ይተላለፋል ስለሆነም እንደ ቀላል ባናየዉ ጥሩ ነዉ፡፡



#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል.....
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ጁምአ ነዉ የሆነ ችግር ሲበዛ ወይ ነይተን ለሰዉ ነግረን ያልተሳካ ካለ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ ለጀሊሉ ነግረዉን ያሳፍረን ይሆን??
እስኪ ለጀሊሉ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ አድርገን እንገረዉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#የመጨረሻዉ_ክፍል



  🔰 #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ


🌙🌙
ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
  ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር  ነዉ ፡፡

📚📚 ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ

✍🏼 አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን  የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል  ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም  ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...

#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት  ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡

✍🏼 አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ

✍🏼 ከነዚህ ዉጭ  3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ

----- ጂን ሲናገር  ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡

🌟 ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ  ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ  ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡


 ⚡️⚡️⚡️ #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ #በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ      
         
#ምን_ማድረግ_አለበት⁉️⁉️

      ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡  ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡  ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡  

  በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት  ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡

♻️♻️ አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ  ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ😢፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡

#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...

መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
💚በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
💛ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
❤️ በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
💛  ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
❤️ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።👇👇👇
💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች።
❤️በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል ሰዎችን ይቅር ይሉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ 
እናም ፈተና  መብዛት ችግር መደራረብ ባይኖር ዱንያ የደስታ ሀገር ብትሆን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ባልተፈተኑ ነበር እናም አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም ፈተና ላይ ናቸሁ ፈተና ጨርሳችሁ ትንሽ ከተደሰታችሁ ቡሀላ ሌላ የከበደ ፈተና እንደሚጠብቀን እርግጠኛ ሁን የዛን ጊዜ ነዉ ኢማንህ የሚለካዉ፡፡
ኢማናችን መለካት እንጂ መነካት የለብንም ወገን


📌 እጅግ አምልኮ በማብዛት የሚታወቀው ታላቁ ታቢዒይ አልፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ ፈገግታ አያበዙም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግን ልጅ ሲሞትባቸው ፈገግ አሉ፡፡ ለምን ፈገግ እንዳሉ በተጠየቁ ጊዜ “አላህ የወደደው ነገር ነውና እኔም ወድጄ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የወደደውን እንድትወድ ነፍሴ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት” አሉ፡፡

ዑለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለቀሱበትንና አልፉደይል ግን ፈገግ ያሉበትን ሁኔታ በማንሳት ለመተንተን ሞክረዋል፡፡ በመታገስ ደረጃ አፉደይል ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጣሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ትርጉሙም፡- ሞት በሚመጣበት ቅፅበት ቀልብን በሁለት ሰሜት ውስጥ ይከታል፡፡ እዝነትና ውዴታ፡፡ ማንም ሰው ሁለቱን ስሜቶች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አይችልም፡፡ አልፉደይል ሁለቱን ማሳካት አልቻሉምና በውዴታ ስሜት አንድም ፈገግ ማለት አለባቸው አሊያም አብዝተው ማልቀስ ነበረባቸው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ሁለቱን ማሳካት ችለዋል፡፡ አላህ የወደደውን ወደዋል በሌላ በኩል ደግሞ አልቅሰው እዝነት ስሜት አሳይተዋል

📌 የነቢያችን አክስት የሆነችው : እመት ሶፊያ በኡሑድ ጦርነት ወቅት ቁስለኞችን ውሃ ታጠጣ ነበር፡፡ ታላቁ ጀግና ሐምዛ (ረ.ዐ) ተገደሉና አካላቸውም እንዲቆራረጥ ሆዳቸው እንዲቀደድ ተደረገ፡፡ ሒንድ በበቀል ስሜት ጉበታቸውን እስከማኘክ ደረሰች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጇ ዙበይር ኢብኑ አልዐዋም ዝበይር ሆይ! ሶፊያን ወደ መዲና ይዘሀት ሂድ ሐምዛን ማየት የለባትም፡፡” አሉት። ልጇም ሄደና “እናቴ ሆይ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ተመለሽ ብለውሻል፡፡” አላት፡፡

ልጄ ሆይ! ይህን የምታደርጉት ሐምዛን እንዳላይ ብላችሁ ነው አይደል? አለችው፡፡
....“አዎን” አላት፡፡
....እሷም “ልጄ ሆይ! አላህ ከዋለልን ፀጋ አንፃር በሐምዛ ላይ የደረሰው በጣም ቀላል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደድ አለመውደዳችንን ለማየት ነው፡፡ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሂድና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አላህ በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደዳችንን ለመፈተን ነው ብላለች ሶፊያ በላቸው ፡፡ ልጁም ወደ ነብዩ (ሲዐወ) በመመለስ ነገራቸው፡፡
... ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እንግዲያውስ ማየት ትችላለች፡፡” አሉ፡፡ ሄደችና አይታው አለቀሰች፡፡ ኢንና ሊላህ ወኢንና ኢለይሂ ራጂኡን የኛዑን እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን፡ በማለትም ዱዓእ አደረገችለት፡፡
እናም አላህ በሚያመጣብን ፈተና የዱንያም ሆነ የጂን የሲህርም አላህ ወዶን እየፈተነን እንደሆነ አንዘንጋ

ጅን ሲህር ሳሂር ደጋሚ ጠንቋይ ደብተራ እንደማይጎዳ አሏህ ብቻ ጎጂ እንደሆነ ማወቅን ከኢማኖች ውስጥ ጠንካራ ኢማን ሁኖ እናገኘዋለን!! በአሏህ ላይ የቂን እጅግ የምንፈልገው መሳርያ ነው!! ሌቦች ቤትን ሊዘርፉ ሲመጡ አለሁ ብሎ ድምፅን ማሰማት ሲቀጥልም የመሳርያን ድምፅ ማሰማት እነርሱን እንደሚያስበረግጋቸው ሁሉ የቂን ልክ እንደዛው ጅኖችን ያስፈራቸዋል እንዳይቀርቡን!! ይሁንና ያለ እውቀት ያለ መጠበቅያ የቁርአን አያዎች እና ዚክሮቸች ማለት ያለ መሳርያ መሳርያ ታጥቀው የመጡ ሌቦችን ማስፈራራት ብቻ ነው፡፡ ለኛ መሳርያችን ለጅኖች ሊያውም ከባለጌዎች ለመጠበቅ የምንታጠቀው መሳርያ ዚክርና ቁርአን እንዲሁም ዱአእ ነው፡፡ ሌላውን አይነት የመሀይማን መሳርያ የሆነውን ጥንቆላ መተት ፀበል እና አንጃ ግራንጃዎች ልክ ሌቦችን እንደመማፀን እንደመደራደር ነው የምንቆጥረው፡፡ ከሌባ ጋር ድርድር የለም ባንተ ንብረት ላይ መጥቷልና ፡፡ ከጅን ጋርም እያጠቃህ መደራደር የለም በቁርአን በዚክር ልኩን አሳይተሀው  መከባበር እንጂ፡፡


🖍🖍 እናም ፈጣሪ ይሁን ብሎ ተፅፎብን ከሆነ ትዕግስት ጥንካሬ ፅናት ያስፈልጋል፡፡ በሲህር በጂን የሚፈተን ሰዉ በዛዉም የፀና የጠነከረ አላህ ወዶን ይሆናል ዱአ ላይ መበርታት ግዴታ ነዉ...ከዱአ በጭራሽ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም
{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡[አል በቀራህ: 186]


🟢  አንድ ድንቅ የሆነ ሐዲስ አልቁድስይ ላካፍላችሁ፡፡ ነቢዩ ባስተላለፉት ሐዲስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! እኔም እፈልጋለሁ አንተም ትፈልጋለህ፡፡ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የሰጠህ እንደሆነ የምትፈልገውን አመጣልሃለሁ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የማትሰጥ ከሆነ በምትፈልገው ነገር ላይ  እንድትደከም አደርግሃለሁ፡፡ በመጨረሻ እኔ የምፈልገው ነገር ብቻ እንጂ የሚሆን የለም፡፡” ይለናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ “አላህ ካሻ በስተቀር አናንተ አትሹም (አል-ኢንሳን ፡3) ብሏል፡፡

🟢 ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዱዓዬ መቼ ተቀባይነት እንደሚያገኝ አውቃለሁ፡፡ አሉ፡፡ “እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? ተባሉ፡፡፡ “ቀልቤ በጥልቀት የአላህ ፍራቻ ካደረበት፣ መላ አካላቴ ከተንቀጠቀጠ፣ ዐይኔ ካነባች፣ ይህች ሰዓት ዱዓዬ ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በማለት በዱዓዬ እጠናከራለሁ፡፡ ብለዋል፡፡

ለዱአ መቸኮል አያስፈልግም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እስካልቸኮላችሁ ድረስ ምላሽ ይሰጣችኋል፡፡” አሉ፡፡ መቸኮል ሲባል እንዴት ነው? ሲሏቸው አንዳችሁ “ዱዓእ አደረግኩ፤ ዱዓእ አደረግኩ ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ይላል፡፡ (ተስፋ መቁረጥ) ዱዓእ ይተውን ይተዉና በዚያው ምላሽ ያጣል፡፡” ብለዋል፡፡
ሲህር ከተደረገብን ወደ አላህ የማይቋረጥ ቀጣይ የሆነ ዱአ ያስፈልጋል፡፡

🟢 ኢብኑ አልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ ብትባረርም እንኳን ከአላህ በር ላይ ከመቆም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ቢመልስህም እንኳን ምክንያት ከማቅረብ አትውረድ፡፡ በሩ ተቀባይነትን ላገኙት የተከፈተ እንደሆነ ቀስ ብለህ በስርአቱ ግባ፡፡ ድሀ ነኝ ምፅዋት እፈልጋለሁ፡፡ በለው፡፡ ምፅዋት የሚሰጠው ለድሆችና ለችግረኞች ነው፡፡ እኔም ምስኪን ደሃ ነኝ፡፡ በለው፡፡👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ
"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።
በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ
ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው
ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።
በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ
"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"
አላህ ይዘንልህ

ዛሬስ አረቦች
ዛሬስ የአለም ሙስለሞች??
በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➊

#የነብዩ ሰዐወ መቃብር ቁፈራ የተጋለጠበት!!
አዘጋጅ ☞አሚር ሰይድ
የታሪክ መጻሕፍት በ557 ዓ.ሂ የተከሰተን አንድ አስገራሚ ጉዳይ ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ ያ ዘመን የዐብባሳውያን ሥርወ-መንግሥት በመንኮታኮት ላይ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በአጐራባች አገራት ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያን መንግሥታት አንድ ከባድ ሴራ ጠነሰሱ። ሴራቸው የሙስሊሞችን መዳከም ተገን አድርገው የነቢዩን አስከሬን ከነበረበት በመስረቅ ወደ ራሳቸው ግዛት መውሰድ ነበር፡፡ ይህን በማድረግም በሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ሞራላዊ ጉዳት ለማድረስ
አሰቡ::

ስለዚህ ይህን ረቂቅ ተንኮል ለማስፈፀም ሁለት የተመረጡ ሰላዮችን የሞሮኮ ኢስላማዊ አለባበስ በማልበስ ወደ መዲና ከተማ ሰደዱ ሰዎቹም ለነዋሪዎቿ ለፀሎት ወደ ቅድስቲቷ ከተማ የመጡ ሐጃጆች መሆናቸውን እንዲናገሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ተልዕኮኣቸውን ለመወጣት እንዲችሉ መስጂደል ነበዊ (የነቢዩ መስጂድ) አጠገብ ባለ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ በጐረቤቶቻቸውም ዘንድ ለመታመን ሲሉ መስጂድ ማዘውተርና የዒባዳ ተግባራትን በጥልቀት ማከናወን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆነ፡፡ ዋናው ጉዳያቸው ግን የተላኩበትን ዓላማ ማስፈፀም እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን ተልዕኮ ለማከናወን የመጀመሪያ ሥራቸውንም ከነበሩበት ቤት አንስተው ወደ ነቢዩ መቃብር ለመድረስ ውስጥ ለውስጥ በመቆፈር መሿለኪያ ለማበጀት ቁፋሮ ጀመሩ፡፡ እንዳይነቃባቸውም በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ብቻ እየቆፈሩ የሚያወጡትን አፈር በትናንሽ መያዣዎች አድርገው ጀለቢያቸው ሥር በማንጠልጠል አል-በቂፅ ወደሚባለው የመዲና
   የቀብር ስፍራ እየወሰዱ ይደፉ ነበር። ሌሎቹ ነዋሪዎች ሰዎቹ በየዕለቱ ወደ ቀብር ሥፍራ የሚሄዱት የሞቱትን በመዘየር ሞትና አኼራን ለማሰብ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰዎቹ አንዳንዴ ሲደክማቸው መሿለኪያ ለማበጀት የሚቆፍሩትን አፈር ከሚኖሩበት ቤት አጠገብ ወዳለ ጉድጓድም ይደፉ ነበር። እንዲህ እያደረጉ በመጨረሻ መሿለኪያውን ከነቢዩ ሰዐወ ቀብር ጋር ሊያገናኙ ደረሱ፡፡ እዚህ ደረጃ ሲደርሱ ተልዕኮኣቸው ለመሳካቱ እርግጠኛ ስለነበሩ የትኩረት አቅጣጫቸው የነቢዩን አስከሬን ካወጡ በኋላ በምን መንገድ ወደ መጡበት ግዛት እንደሚያጓጉዙ ማቀድ ነበር፡ የተለያዩ ዘዴዎችን አውጥተው አወረዱ፡፡ በዚያው ወቅት አላህ የራሱን ሴራ እያሴረባቸው እንደሆነ ግን አላወቁም፡፡

የዘመኑ የሙስሊሞች መሪ የነበሩትና ከመዲና ብዙ ርቀው የሚኖሩት ኑረዲን ሙሐመድ ኢብኑ ዘንጂ በዚያው ሰሞን አንድ ለየት ያለ ሕልም እዩ፡፡ በሕልማቸው ውስጥ ነቢዩ ሰዐወ ነበር የታዩዋቸው፡ ነቢዩ ወደ ሁለት ቀያይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎች እያመለከቱ ከእነርሱ እንዲያድኗቸው ኑረዲንን ይማፀናሉ ይህን ከባድ ሕልም ሲመለከቱ ኑረዲን በድንጋጤ እየተንቀጠቀጡ ከእንቅልፋቸው ነቁ። ራሳቸውንም ለማረጋጋት ሶላት ከሰገዱ በኋላ ተመልሰው ወደ መኝታቸው ቢሄዳም አሁንም ያው ሕልም ተመልሶ መጣባቸው:: ሕልሙ ለሦስተኛ ጊዜ ሊመጣባቸው ከእንቅልፋቸው በመነሣት ከሚንስትሮቻቸው መካከል ሷሊሕና ብልህ የነበረውን ጀማሉዲን አል ሙሲሊ የተባለውን አስጠሩ፡፡ ያዩትን ሕልም ለጀማሉዲን ሲነግሩት ሕልማቸው በመዲና ውስጥ የሆነ እንግዳ ነገር እየተከናወነ መሆኑን እንደሚጠቁም አስረዳቸው፡፡ በአስቸኳይም ወደ ነቢዩ ከተማ በመሄድ ስለ ሕልሙ ለማንም ሳይናገሩ ሁኔታዎችን እንዲከታተሉ አሳሰባቸው፡፡ ኑረዲን ከለሊቱ የቀረውን ክፍል ለጉዞው ዝግጅት ሲያደርጉ አደሩ፡፡ ጀማሉዲንን ጨምሮ ሃያ ጭነት ከሃያ ሰዎች ጋር እንዲዘጋጅ አዘዙ፡ ከሻም(ሶሪያ) ተነስተው መዲና ለመድረስ የፈጀባቸው ዐሥራ ስድስት ቀናት ብቻ ነበር። መዲና ሲደርሱ በፍጥነት የሄዱት በመስጂደል ነበዊ ውስጥ ወደሚገኘው አልረውዳ ልዩ የሶላት ስፍራ ነበር፡፡ እዚያ በመሄድም ዱዓ አደረጉ:: ይሁን እንጂ ሕልሙን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ አልቻሉም፡፡ አማካሪያቸው ጃማሉዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸው ሁለት ሰዎች ምን ዓይነት እንደሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቃቸው ኑረዲን የሰዎቹን መልክና አለባበስ እንደሚያስታውሱና ቢያገኙዋቸው መለየት እንደሚችሉ ነገሩት፡፡ ጀማሉዲን ሰዎቹን ለመያዝና ሴራቸውን ለማክሸፍ ቆርጠው በመነሳታቸው ፈጣን እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ፡፡ የመዲና ነዋሪዎች በመስጂዱ ውስጥ ሲሰበሰቡም እንዲህ የሚል ማስታወቂያ አስነገሩ፡፡ 'መሪያችን በሶደቃ ለመስጠት ነይተው ያመጡት ብዙ ሃብት አለ፡፡ ሶደቃውን ለማከፋፈል እንዲመቸን በችግር ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ እየመጣችሁ ስሞቻችሁን እንድታስመዘግቡ እንጠይቃለን የሚል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ እንዳስነገሩ ሰዎች ሶደቃውን ፍለጋ ተንጋግተው መምጣት ሲጀምሩ ኑረዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸውን ሰዎች ለመለየት ዳር ቆመው እያንዳንዱን ሰው ይቃኙ ነበር። ብዙ ሰዎች መጥተው የድርሻቸውን እያነሱ ቢሄዱም ኑረዲን ተፈላጊዎቹን ሁለት ሰዎች ሊያገኙ አልቻሉም፡፡

በመጨረሻም ከሶደቃው ድርሻውን ያልወሰደ ሰው እንዳለ ሲጠይቁ የሆነ ሰው ·ከሞሮኮ የመጡ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎቹ በጣም ሷሊሕ ሰዎች ስለሆኑ ሶደቃውን ለመቀበል አልፈለጉም አላቸው፡፡ ኑረዲን ይህን እንደሰሙ ሁለቱን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው አዘዙ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች እፊታቸው እንደቀረቡ ሰዎቹ ነቢዩ ሰዐወ በሕልማቸው ያመለከቷቸው ሰዎች መሆናቸውን በቀላሉ አወቁ። ሰዎቹንም “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣችሁት? በማለት ጠየቁ፡፡ እነርሱም የመጣነው ከመግሪብ ነው፣ አመጣጣችን ለሐጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ዓመት እዚሁ ለማሳለፍ ወስነናል' አሏቸው:: ኑረዲን ሰዎቹ የሆነ ያቀዱት ሴራ መኖሩን ቢጠረጥሩም ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመለየት ስላልቻሉ ድብቅ ሴራቸውን ይፋ እንዲያወጡ በማሰብ የተለያዩ ጥያቄዎችን አከታትለው ቢጠይቁም ምንም ፍንጭ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በዚህም የተነሣ ምንም እርምጃ ሊወስዱባቸው አልተቻላቸውም:: ኑረዲን ቀጥለው ያዘዙት ቤታቸው ይፈተሽ የሚል ነበር፡፡ ቤታቸው ሲፈተሽም በቤቱ ውስጥ ካስቀመጡት በርካታ ገንዘብ ውጭ ሊያስጠረጥራቸውና ሊያስወነጅላቸው የሚችል ምንም ነገር ሳይገኝ ቀረ፡፡ ለፍተሻ ወደ ቤታቸው የገባ ሰው አንድ በአንድ መውጣት ሲጀምር ኑረዲንም ምንም ምልክት በማጣታቸው ቤቱን ለቀው ሊወጡ ሆነ: በዚያች ቅፅበት ነበር አላህ የሙስሊሞቹ መሪ አንዳች ነገር አትኩረው እንዲመለከቱ ያደረገው ኑረዲን ወለሉን ሲቃኙ በወለሉ ላይ ከተነጠፉት ጣውላዎች ው አጥብቆ እንዳልያዘ አስተዋሉ፡፡ ይህን እንዳዩ ጐንበስ በማለት ጣውላውን ሲያነሱ የመዲናን ነዋሪዎች ጉድ ያሰኘ ክስተት ተስተዋለ። በወለሉ መሿለኪያ መቆፈሩን ነዋሪዎቹ ግን ይበልጥ የተደናገጡት መሿለኪያው ወዴት እንደሚያመራ ሲረዱ ነበር፨ መሿለኪያውን የቆፈሩት በከተማይቷ ውስጥ በሷሊሕነታቸው ይታወቁ የነበሩት ሁለቱ የሩቅ አገር እንግዶች መሆናቸው ሌላው ግርምታ የፈጠረ ጉዳይ ሆነ፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሁለቱ ሞሮኮኣውያን የሚታወቁት በጥልቅ ዒባዳቸውና በላቀ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባራቸው ነበር፡፡ እጅግ የተናደዱት መሪ ኑረዲን ሁለቱን ሰዎች መግረፍ ሲጀምሩ ሰዎቹ በርግጥ ከመግሪብ (ሞሮኮ) አንዳልመጡና በመሪያቸው ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው የተላኩ ክርስቲያኖች መሆናቸውን የመጡትም የነቢዩን አጽም ቆፍረው በማውጣት በድብቅ ወደ አገራቸው ለመውሰድ መሆኑን አመኑ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች በሞት እንዲቀጡ አዝዘው የተቆፈረው መተላለፈያም በአስተማማኝ መልኩ በአለት እንዲደፈን አደረጉ፡፡ ሴራውንም እንዳከሸፉ ወደ ሻም (ሶሪያ) ተመለሱ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/21 01:15:53
Back to Top
HTML Embed Code: