Telegram Web Link
የሚገርመዉ እነዛ ልጆች የቀመሷቸዉን ሴቶች እያነሱ ያወራሉ ስንት ድንግል እንዳገኙም ይነጋገራሉ ....ድንግልና በወንድ ልጅ የዉሸት የፍቅር ቃል የሚወሰድበት ..ሴት ልጅ ለባሏ ማስረከብ ያቃታት አሳዛኝ የትምህርት ቤት ጊዚያት ...የምንሰማዉ የምናየዉ የዘንድሮም የትዳር ፍች ድንግል አይደለሽም በሚል ሁኗል፡፡ ታዳ ሴት ልጅ በወንድ ልጅ በአፍ ብቻ እያመነች እሷዉ ደዉላ ድንግልናየን ዉሰድ ካለች ምን ዋጋ አለዉ ??? የሴት ልጅ መገለጨዋ ቁጥበነቷ አይናፋርነቷ ሀያእ ማድረጓ ነዉ ታዳ ዲነል ኢስላም ለሴት ልጅ ትልቅ ክብር ሰጥቶሽ ለምን ለፍጡር ተታለሽ አላህ ያከበረሽን በራስሽ ታከስሪያለሽ ???

ሴት ልጅ የምትከበረዉ አይናፋርነቷ ሀያእ ሲኖራት ነዉ..ሴትነት ቁጥብነት ከአይነአፋርነት ጋር የተያያዘ ነዉ...
ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል፡- ሀያእ አይናፋርነት ከእምነት ሲሆን እሱን የታደለ ሰዉ ደግሞ መኖሪያዉ ጀነት ነዉ ፡፡
ሀያእ ማጣት (ዓይን አዉጣነት)
ከደረቀ ቀልብ(ልብ)ሲሆን የደረቀ ልብ ያለዉ ሰዉ መኖሪያዉ ጀሀነም ነዉ፡፡ ብለዋል
ታዳ አይናፋርነት ከሌለ ሴት ልጅ ከወንድ በምን ተለየች???በተለይ የሴት ልጅ ማንነት እና ሂወት አይናፋርነት ጋር የተያያዘ ነዉ

አሁን አንድ ወንድ የፈለገዉን ሴት መርጦ አገላብጦ አይኑን አፍጥጦ በሚያገባበት ዘመን ....ልታገቢ ስትይ ድንግል ነሽ ወይ??? ሲልሽ ድንግልና እና ዳይነሰር ከጠፋ ቆይቷል ወይም አንዳንድ ደፋሮች ደም ከፈለክ ቄራ ሂደህ ደም ማየት ትችላለሁ ወይም አንዳንድ በንፍጥ ጭንቅላት የሚያስቡ ሴቶች ..ድንግልና ከፈለክ አንድ ንፍጣም በግ ገዝተህ አርደህ እንደነብር መጠጣት ትችላለህ እያሉ ከሆድ ያልወጣ ከአፍ ያመለጠ ሙድ መያዝ መፍትሄ ነዉ ወይ ?? ጥያቄዉ ጋር የማይመሳሰል መልስ ከመመለስ ለወደፊት ጥያቄዉን ለመመለስ ከዛሬዉኑ መዘጋጀት አይሻልም ወይ ???



ከትምህርት ቤታችን ከኦል አንደኛ የምትወጣዉን ልጅ በፍቅር ለማጥመድ እነዛ ልጆቾ እልክ ተያያዙ ፡፡ ከዛም እኔ ላጥምዳት እኔ እየተባባሉ ሊስማሙ ስላልቻሉ ወረቀት ጠቅልለዉ በእጣ አደረጉት፡፡ ከዛም ስሙ የወጣለትን በፍቅር አክንፈህ እወድሀለሁ ስትልህ የፍቅር ወሬ ስታወራህ በስልክ ሪከርድ አርገህ አሰማን  አሉት
....... ልጁም ተስማማ ታያላችሁ በቅርብ ቀን የተሰጠኝን ተልዕኮ አሳካለሁ ብሎ ከትምህርት ቤታችን አንደኛ የምትወጣዉን ልጅ በፍቅር ለማጥመድ ስራዉን ጀመረ....


ይቺኑ ጎበዝ ተማሪ ተብየ አስራ አምስት ባልሞሉ ቀናት ዉስጥ በፍቅር አጥምዷት እራሷዉ ደዉላ እያለቀሰች እወድሀለሁ ያለ አንተ መኖር አልችልም ስትል ላዉድ አድርጎ አሰማን ፡፡ በጣም ገረመን እንደዚህ መሆኑ ይገርማል...ሴት ልጅ እንደዚህ ተላላ ልፍስፍስ ናት ወይ ???አልኩኝ ፡፡ እነዚህ ልጆች ብዙ ነገር አሳዩኝ
ይህ ሁሉ ሙስሊም ክርስቲያኑም ከሀይማኖት መዘናጋታችንን እና የሁሉም ሀይማኖት ተከታይ መሪዎች ፓለቲካ ላይ ስለገቡ .. ይሄን ህዝብ መታደግ ከዚህ መጥፎ ባህሪ በተለያዩ መድረኮች አዘጋጅተዉ የማስተማር አቅማቸዉ አናሳ መሆኑን ያሳያል

የሚገርመኝ እነዚህ ልጆች ሁሉም ሴት እህቶች አሏቸዉ ግን ለሴት ልጅ የሚያዝን ሩህሩህ ልብ የላቸዉም ፡፡ግን በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም አይደል የሚባለዉ የነሱም እህቶች ሌላ ወንድ ልጆች ጋር የተለያዩ ቦታዎች አያቸዋለሁ .ለሌላ ሴት ልጅ የማያዝን በእህቱ ላይ ወጥመድ እያጠመደ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም..ለምን አንተ ለሌላ ሴት ልብህ ካላዘነ ካልራራ የአንተን እህት የሚያጀዝበዉም ልብህን አይቶታል ማለት ነዉ በሌላ ሴት ቢዚ ስለመትሆን ለእህትህ ከለላ መሆን አችልም..ነገር ግን አንተ ፈጣሪህን የምፈራ ከሆነ ለሴት ልጅ ክብር ካለህ..እህትህ ለራሱ ሌላ ወንድ ጋር ምንም የፍቅር ግንኙነት አጀምርም፡፡ ሌሎች ተኩላ ወንዶች አንተን አልፈዉ እህትን መቼም እንደማያጠቁ እርግጠኛ ሁን፡፡

    እኔን ደግሞ የሚወዱኝ የሚያፈቅሩኝ የትምህርት ቤት ልጆች ነበሩ... እነሱ እኔን ማዉራት ሲፈሩኝ አጣብሱን ብለዉ ሲጠይቋቸዉ ..እሺ ብር ክፈሉ ለጉዳዩ ማስጨረሻ እያሉ ብር እያስከፈሉ ብሩን እንደሚያጠፉት ሁሌ ይነግሩኛል፡፡

እኔን ማንም ወንድ ጋር መቀራረብ እንደማልፈልግ ያቃሉ በጭራሽ አሳልፈዉ ለወንድ አይሰጡኝም...እኔን አንድ ወንድ መጥቶ አጣብሱኝ  አብሪያት እንዳድር ብሎ ከጠየቃቸዉ እስከ መጣላት እስከ መደባደብ ድረስ ብዙ ጊዜ ደርሰዋል፡፡

  አንድ ቀን የሆነ ልጅ ግድ ካላወራሽኝ እያለ ሲያስቸግረኝ ሶስቱ እሱን ደብድበዉት ለተወሰኑ ቀናት ፓሊስ ጣቢያ ታስረዋል.....ምን ጥቅም አለዉ የስንቱን ሒወት እያበላሹ እኔን ቢከላከሉልኝ ምንም ፋይዳ የለዉም....ብዙ ሴት ልጆች የነዚህ ልጆች ሰለባ ሁነዋል


አይ ትምህርት ቤት አሁን ዘመን ላይ እንዲህ ሁኗል...መፍትሄዉ መቼ ይሆን እኛ ሙስሊሞች የራሳችን የሆነ ትምህርት ቤት አቋቁመን ወንድ ለብቻ ሴት ለብቻ በተለያየ ቦታ ተከፍቶ ማስተማር እና መማር ስንችል ብቻ ነዉ፡፡
ለወደፊት ይጠቅሙናል ዲነል ኢስላምን ይረከባሉ ለጥሩ ደረጃ ይደርሳሉ ብለን ተስፋ ያደረግናቸዉ ልጆቻችን በትምህርት ቤት መዘዝ ረክሰዉ እንዳይቀሩ እላለሁ፡፡

በሁለም ከተሞች የሙስሊም ትምህርት ቤት ተብየ አለ...ግን የሚያስተምሩት ሴትና ወንድ በአንድ ላይ እንደዉም የሙስሊም ትምህርት ቤት ተብሎ ስንት ወንጀል ስንት ግፍ እየተሰራበት አይደል??
ለትዉልድ የጠቀመዉ የለም ብቻ የሙስሊም ትምህርት ቤት ተብሎ ስሙ ብቻ ተረፈን ...

በነብዩ ( ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን የነበሩ ሴቶች በመስጅድም ይሆን በገቢያ ቦታ ከወንድ ጋር በጭራሽ አይቀላቀሉም ነበር"

አላህ የነቢዩን ﷺ ባለቤቶች ያዘዘው በቤታቸው የረጉ ቁጥቦች ይሆኑ ዘንድ እንጅ ከማንኛውም ወንድ ጋር እንዲቀላቀሉ አይደለም።
አላህ በተከበረ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፦

«የነቢዩ ሴቶች ሆይ ከሴቶች እንደማናቸው አይደላችሁም፤ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ)፤ ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም፤ መልካምንም በንግግር ተናገሩ። በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፤ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምንነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፤ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፤ የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻውን ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው።»
[አል-አሕዛብ፡ 32-33]
አላህ የነቢዩን ﷺ ሚስቶችን ያዘዘበት ይህ ትዕዛዙ ሌሎች አማኝ ሴቶችን በሙሉ እንደሚመለከት ኢብኑ ከሢርና ሌሎችም የተፍሲር ሊቃውንት ተናግረዋል።

«ይህ አላህ የነቢዩን ﷺ ሴቶችና እነርሱን በዚህ ላይ የተከተሉ አማኝ ሴቶችን በሙሉ ያዘዘበት ስነ ስርዓት ነው።ብለዋል

«ሴት ልጅ ዐውራህ (ድብቅ) ናት። ብቻዋን ከቤቷ ከወጣች ሸይጧን ይከተላታል።»ብለዋል ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ


ማትሪክ ፈተና ደረሰ፡፡ ፈተናዉንም ያለምንም ቅድመ ዝግጅት  ተፈተንኩኝ........ትምህርት ተዘጋ በክረምት አልፎ አልፎ የክላስ ጓደኞቼ ጋር በመደዋወል በfb በማዉራት አሳለፍኩኝ



የማይደርስ የለም የማትሪከ ዉጤት በኢንተርኔት ተለቀቀ ..እኔም ዉጤቴን ለማየት ጓደኞቼ ጋር ሄድኩ...የማትሪክ ዉጤቴም...


#ክፍል 9⃣
ይ.........ቀ.........
......ጥ.........ላ...........ል


JOIN

           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ዘጠኝ 9⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




     የማትሪክ ዉጤት በኢንተርኔት ተለቀቀ የሚገርመዉ ነገር በኢንተርኔት ሁሉም ተመለከቱ... የኔን ኮዱን ስናሰገባዉ አልሰራ አለኝ፡፡ ቢባል ቢባል የኔን ዉጤት ለማየት በጭራሽ ሊሳካ አልቻለም ...

የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ..ናርዶስም እነዛ ስድስቱ የትምህርት ቤት ዱርየ ልጆች ሳይቀር ሁሉም ወደ አስራ አንደኛ ክፍል የሚያሳልፋቸዉን ዉጤት አግኝተዋል፡፡ የእኔን ለመመልከት ግን የአላህ ነገር እምቢ አለኝ፡፡

ናርዶስ ቢጨንቃት ነዋል እስትሬት 4 ነጥብ አምጥተሽ ይሆናል የአንቺ እምቢ ያለዉ ትለኛለች ....ደግሞ ሌሎች ጓደኞቼ ዉጤትሽ ሁሉም F ሁኖ ትምህርት ሚኒስተር የአንቺን በonline መልቀቁ ደብሮት ነዉ እያሉ ሙድ መያዣ አረጉኝ፡፡

ባለመሰልቸት እኔም ሁሉም ጓደኞቼም ከአንድ ሳምንት በላይ ለማየት ብንታገል እምቢ አለን......
  
   አዲስ አበባ ያለዉ አጎቴ ደዉሎልኝ... ነይ ትንሽ ቀን እኛ ጋር አሳልፈሽ ትመለሻለሽ አለኝ.....
እኔም እሺ ብየ ወደ ሸገር ጉዞየን ቀጠልኩኝ፡፡
አዲስ አበባ ስመጣ የማሳልፈዉ የአጎቴ ልጆች ጋር ስዝናና ነዉ የምዉለዉ ፡፡

ሸገር ሁኜ ዉጤቴን ለማየት ያላረኩት ጥረት የለኝም ግን የኔ code ሲገባ ጭራሽ አይሰራም ነበር፡፡ ጓደኞቼ እንዳሉት ዉጤት ሀሉም F ስለሆነ ትምህርት ሚኒስተር አፍሮበት በኢንተርኔት የኔን ዉጤት ያለቀቀ አስመሰለዉ እኔንም አጠራጠረኝ...
  
   አጎቴ ጠዋት ላይ ቁርስ እየበላን ነዋል ዛሬ የተጨናነቅሽዉን ዉጤት በህልሜ አየሁት ያመጣሽዉ 3.0  ነዉ  ደግሞ የኔ ህልም የሚፈታዉ በተቃራኒ ስለሆነ ወድቀሻል አለኝ...
......እኔም ህልም አኮ ዉሸት ነዉ አጎቴ እያልን ተሳሳቅን፡፡

የማትሪክ ዉጤት ኢንተርኔት ላይ ተለቆ የኔን ለማየት አልሰራም ማለቱ ቅዠትም ህልምም ከተለለቀ ጀምሮ እየተፈራረቀብኝ ነዉ፡፡ በህልሜ አንዴ አልፌ ፕሪ ፓራቶሪ ጓደኞቼ ጋር ስማር ይታየኛል፡፡ ደግሞ አንዳንዴ ወድቄ ስናደድ ይታየኛል ፡፡ ህልሜ ጥሩ ሲሆን አልሀምዱሊላህ ..ህልሜ መጥፎ ሲሆን አኡዙቢላህ ማለት የዘወትር ተግባሬ ሁኗል ...


እስኪ ስለህልም አንዲት ቀለል ያለች ቀልድ ጀባ ልበላችሁ ጥርስም ላይ ባደርስ ለአይን ጥራት ትሆናለች😊...
አንድ ዲነል ኢስላምን ጠለቅ ብሎ የማያቅ(ጃሂል) የገጠር ሰዉ እና እዛዉ አካባቢ የሚኖሩ ሸህ ነበሩ፡፡ ሸህየዉ ሚስት የላቸዉም ግን የጃሂሉን ሚስት ሚስቴ በሆነች እያሉ ትንሽ ሆዳቸዉ ይቋምጥ ነበር...
ከዛም አንድ ቀን ጃሂሉ ህልም ያያል ፡-ህልሙም ሚስቱን ሶስቴ ሲፈታት ይመለከታል..ከዛም ከእንቅልፉ ይባንናል ፡፡ ጃሂሉ ግራ ገባዉ በህልሜ ሚስትን ሶስቴ ፈትቻታለሁ ምን ይሻለኛል ??እያለ ግራ ይገበዋል ..ከዛም ያየዉን ህልም የሚያማክረዉ የሚጠይቀዉ ሰዉ ሲፈልግ የሰፈሩ ሸህ ትዝ ይሉታል...ከዛም ወደ ሸህየዉ ሄደ፡፡
ከዛም ሰላምታ ከተለዋወጠ ቡሀላ ሸሀችን ዛሬ የመጣሁት ሚስቴን በህልሜ ሶስቴ ስፈታት አይቼ ነዉ በቁርአን በሀዲሱ ህልሙ እንዴት ይታያል??ብሎ ይጠይቃቸዋል..
ሸህየዉም:-በህልምህ ሶስቴ ከፈታህማ ሚስትህን ፈተሀታል ማለት ነዉ ይሉታል፡፡
ጃሂሉም ሰዉየ በአየዉ ህልም እየተናደደ እቤቱ ተመልሶ ሚስቱን በህልሜ ሶስቴ ስለፈታሁሽ ከአላህ ጋር መጣላት አልፈልግም ብሎ ከመኖሪያ ቤቱ ያሰናብታታል፡፡

ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ ሸህየዉ የጃሂሉን ሚስት አግብተዉ ወደ ራሳቸዉ ጎጆ ወስደዉ ሂወታቸዉን እየመሩ ነዉ..ጃሂሉም ሚስቱን በነሸህ መነጠቁን ሲያይ እየለደመ ዝም ማለት ብቻ ምርጫዉ ሆነ...

የጃሂሉ አንድ ምርጥ ጓደኛ ነበረዉ...ሚስቱን እነሸህ ጋር ሲያያት ወደ ጃሂሉ መጥቶ ሲጠይቀዉ...እኔማ በህልሜ ሚስቴን ሶስቴ ስፈታት አይቼ ለነሸህ ሳማክራቸዉ ግዴታ መፍታት አለብህ ሲሉኝ እኔም እዉነት መስሎኝ ፈታሁኝ ከዛም ሸህየዉ አገቧት ብሎ ለጓደኛዉ ይነግረዋል...
ጓደኛዉም ተናዶ ና አብረን እንሂድ ጥልቆ ይዘህ ተከተለኝ ብሎ ወደ ሸህየዉ ቤት ሄዱ..ከዛም በያዙት ጥልቆ የሸህየዉን ቤት ግድግዳዉን መምታት ጀመሩ..
ሸህየዉ ከቤት ወጥተዉ ...ምን እያደረጋችሁ ነዉ?? ቤቴን እናዳታፈርሱ ብለዉ ጠየቋቸዉ
..ጓደኛዉም ፡-ሸሀችን ማታ በህልሜ የአንቱን ቤት በጥልቆ ሁለታችን እየመታን ስናፈርሰዉ አይቼ ነዉ ..አላቸዉ
..ሸህየዉም:- እንዴ ህልም እኮ ዉሸት ነዉ ቤቴን እንዳታፈርሱ .ሲሉ
..ህልም ዉሸት ከሆነ .ህልም እዉነት ነዉ ብለሁ የወሰድኳትን የጓደኛየን ሚስት መልሱ 😆😆😆ብሎ እርፍ

  አጎቷም ያየዉ ህልም እኔም ያየሁት ህልም  እንደዚህ ቀልድ ግራ የሚያጋባ ህልም ሁኗል፡፡

ደግሞ አጎቴ ህልሙን ከነገረኝ ከሁለት ቀን ቡሀላ ማታ ተኝቼ እኔም የሚገርም ተአምር የሚመስል ህልም አየሁኝ....,ሁሉም የክፍል ጓደኞቼ አልፈዉ የኔ ዉጤት ግን በጥቁር ቀለም ተሰርዞ አየሁት ከዛም ጓደኛየን ምንድን ነዉ ይሄ በጥቁር ቀለም የተሰረዘዉ ??? አልኳት
.....እሷም ነዋል አንቺ እኮ ከሁላችንም ተነጥለሽ ወድቀሻል ስትለኝ ብንን ብየ ተነሳሁኝ...አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ኢሮጂም ብየ መልሼ ተኛሁኝ፡፡

ይሄን ህልም ካየሁ ከሶስት ቀን ቡሀላ የማትሪክ ዉጤት ትምህርት ቤት መጣ፡፡ ናርዶስ የኔን ዉጤቴን ካርድ አይታ ለአባቴ ደዉላ ነገረችዉ......

አባቴም ደዉሎ መጀመሪያ እኔን ከአረጋጋኝ ቡሀላ አብሽሪ ማለፍ መዉደቅ ያለ ነዉ ትኩረት አትስጭዉ ...... የማትሪክ ዉጤትሽ ለpriparatoty የሚያስገባ ዉጤት አላመጣሽም፡፡ ተረጋጊ አላህ ያለዉ ነዉ የሚሆነዉ ሰዉ እርዚቁ በትምህርት ብቻ አይደለም አለኝ፡፡

እኔም መዉደቄን ሲነግረኝ ስልኩን ዘጋሁት እንባየ ቀደመኝ በጣጣም አለቀስኩኝ ከምነግራችሁ በላይ በጣም አዘንኩኝ ሁሉም ጓደኞቼ  ሲያልፉ ከጓደኞቼ እኔን ብቻ ስወድቅ በጣጣም ተሰማኝ፡፡ በሒወት ተስፋ ቆረኩኝ ወደፊት የመኖር ህልም አልታየኝ አለ ...ፈጣሪየ ምን አረኩህ በኔ ላይ ይሄን ያህል በደል ?? እያልኩ ማልቀስ ሆነ ስራየ፡፡ በጣም ተሰማኝ ዲፕሬሽን ዉስጥ ገባሁ...ፈታኝ ሀዘን በአንዴ ዉስጤን ወረረዉ ....ጭራሽ መቋቋም አልቻልኩም፡፡ በማልቀስ በመበሳጨት ከአንድ ሳምንት በላይ ሆነኝ

አጎቴ እና ሚስቱ እኔን ማፅናናት ማባበል ሁኗል ስራቸዉ መዉደቄን ከሰማ ቡሀላ አጎቴ ለኔ መጨነቅ ይዟል፡፡እጅግ የበዛ ደስታና እጅግ በጣም የሚከብድ ሀዘን ለሰዉ ልጅ ሂወት ትልቅ ወጥመዶች ናቸዉ ፡፡በጣም ከመበሳጨቴ ከመናደዴ የተነሳ ከአሁን ቡሀላ ጅማ ከተማ አልሄድም እዚሁ አዲስ አበባ ነዉ የምኖረዉ አልኩኝ
.........የአጎቴ ሚስትም አብሽሪ እዚሁ በግል አሪፍ ኮሌጅ ገብተሽ በዲፕሎማ ትማሪያለሽ ብላ አፅናናችኝ፡፡

አጎቴ ለአባቴ ደዉሎ ነዋል እዚሁ አዲስ አበባ በግል ኮሌጅ ልናስተምራት አስበን ነበር ፍቃደኝነትህን ልንጠይቅህ ነዉ የደወልኩልህ አለዉ
.....አባቴም አረ አይሆንም በጭራሽ አታስቡት እኔ ያለ ነዋል መኖር አልችልም ..እንኳን ከእኔ አመት እርቃ ትምህርት ልትማር ይቀርና እናንተ ጋር ለተወሰነ ቀናት ስታሳልፍ እንዴት እንደምናፍቀኝ እኔ እና አላህ ነን የምናቀዉ ..በጭራሽ የማይሆን ነዉ፡፡ እዚሁ ጂማ ስትመጣ ተማክረን የምፈልገዉን አደርግላታለሁ እንጂ መቼም ቢሆን ከእኔ እርቃ ትምህርት እንድትማር አልፈቅድም አለ አባቴ፡፡👇👇👇
ለነገሩ አይፈረድበትም አባቴ እዉነቱን ነዉ ከሁላችንም ልጆች እኔን በጣም ይወደኛል በፊት ጀምሮ አንቺ ባትኖሪ ይሄ ቤት እስከ አሁን ትዳሩ ይፈርስ ነበር ብዙ ቀን ብሎኛል፡፡

አባቴም ይሄንን ሀሳብ ከአጎቴ እንደሰማ ..,በሚቀጥለዉ ቀን አዲስ አበባ መጥቶ ወደ ጂማ ወሰደኝ....እኔን በዚሁ የምለየዉ ነዉ የመሰለዉ ...ነዋል ሁሌም ቢሆን ከጎኔ እንድትርቂኝ አልፈልግም አለኝ....

ሀምሌ ነሀሴ ክረምቱ ብርዱ አልፎ መስከረም ተተክቷል ትምህርት ተከፈተ ጓደኞቼ እየተማሩ ነዉ ፡፡

እኔ ግን ከቤት መዉጣት የለ እንደበፊቱ ጓደኞቼ ጋር መገናኘት የለ እቤት ታሽጌ ተሸሽጌ መዋል ጀምሪያለሁ.....በቃ ብዙ ነገር አስጠላኝ በሒወቴ አዘንኩኝ....አላህ ጋር በመጣላት ትልቅ ጦርነት ጀመርኩኝ ቀዷ እና ቀደር ነዉ ብየ መቀበል ሲገባኝ አላህን የተለያዩ ነገሮች እያነሳሁ ማማረር መዉቀስ ጀመርኩኝ...አላህን እንዴት ለምን እያልኩ ጥያቄ በጥያቄ ሁንኩኝ ይሄ ሁላ ፈተና ለኔ ለምን?? አልኩኝ....

>>>>ጓደኞቼ ማግባት ቢፈልጉ ትዳር ልመስርት ቢሉ የሚፈልጉት ነገር አላቸዉ ይሄዉም የሚፈለገዉ ድንግልና ነዉ የሚፈልጉትን ወንድ መርጠዉ ማግባት ይችላሉ ....እኔ እኮ ድንግል አይደለሁም በልጅነቴ አጥቸዋለሁ ..መልክ ቢኖረኝም እንዴት ብየ ነዉ ወንድ ሲጠይቀኝ የማገባዉ ?? በመልክ ብመረጥም ለትዳር ብቁ አይደለሁም ....ሰንት የማቃቸዉ ሴቶች ጂማ ላይ ከትዳር የሚፋቱት ቢክራ አይደለሸም እየተባለች ስትፈታ ስትባረር እያየሁ እንዴት እኔ ተስፋ ወኔ ይኑረኝ ??? ተስፋ ቆረጥኩኝ ደግሞም ወይ ትምህርቴን አልተማርኩ ከአስር ወደኩኝ ብማር እኮ ይሄን የልጅነቴን በደል የምነግረዉ የሚረዳኝ አገኝ ነበር ብየ ብቻየን መጨናነቅ ሆነ ስራየ የአእመሮ ጭንቀት ዲፕሬሸን ዉስጥ ወደኩኝ፡፡
     ነብዩ ሙሀመድ ﷺእንዲህ ብለዋል:- በአላህ ዓይን ጠንካራዉ የሆነዉ አማኝ ከደካማዉ ይልቅ የበለጠና የተወደደ ነዉ፡፡ የሚጠቅማችሁን ነገር ለማግኘት ጥረት አድርጉ፡፡አንዳች መጥፎ ነገር ካጋጠማችሁ እርር ኩምትር በማለት "እንዲህ እንዲህ አድርጌ ቢሆን ኖሮ ይህ ነገር አያጋጥመኝም ነበር""አትበሉ፡፡ ከዚህ ይልቅ አላህ የሻዉ ነገር ሆነ ተፈፀመ በሉ፡፡ ""ቢሆን ኖሮ""የምትለዉ አባባል ሰይጣንን ታስደስታለች..ብለዉናል
.....አላህ ባመጣዉ በቀዷና በቀድር እንዳምን ልቦናዉን ማስተንተኑን ይስጥሽ በሉኝ


    ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ አባቴ እቤት ነበር.. መኝታ ክፍሌ ሁኜ ተኝቼ ብዙ ነገር እያሰብኩኝ...አባቴ ነዋል ነዋል እያለ ሲጠራኝ ሰማሁኝ ....
...... አባቴ እተቀመጠበት ሳሎን ሄድኩኝ
.......አባቴም ነይ ከጎኔ ቁጭ በይ ዛሬ የማማክርሽ ጉዳይ አለኝ ...ዛሬ የምንማከረዉ ቀልድ አይደለም ስለወደፊት ሂወትሽ ነዉ.......የምጠይቅሽን ተረጋግተሽ ትመልሽልኛለሽ አለኝ..
....እኔም እሺ አልኩት
.......አባቴም ለወደፊት ምንድን ነዉ አላማሽ ?? ምን አስበሻል ?? በግል ኮሌጅ ገብተሽ በዲፕሎማ መማር ነዉ አላማሽ?? ወይስ አጥንተሽ ፕራይቤት ለመፈተን ነዉ ?? ወይስ ብር እና
ስራ ላመቻችልሽ እና ንግድ ዉስጥ መግባት ትፈልጊያለሽ ?? ወይስ ሌላ ያሰብሽዉ ካለ ንገሪኝ....... አለኝ
..........ይሄን ጥያቄ ሲጠይቀኝ ብቻየን ጭልጥ ያለ ሀሳብ ወሰደኝ....ወላሂ በጣም እልክ ተሰማኝ እንዴት እነዛ ሰነፍ ጓደኞቼ አልፈዉ እኔ እወድቃለሁ ?? እያልኩ አእምሮየ ጋር ማመላሰስ ጀመርኩኝ....
ግን መልሼስ ፕራይቤት ተፈትኜ ብወድቅስ ብየ ለሁለት ሀሳብ ተከፈልኩ.....
....አባቴን አሁን ላይ ምንም ማሰብ አልፈልግም መወሰንም አልችልም.... አልኩት
-----------------አባቴም፡- ነዋል ተረጋግተሽ እሰቢበት አንቺ እንድትጨናነቂ አልፈልግም...መማርም ከፈለግሽ ምን መማር እንደምፈልጊ ..ወደ ስራም መግባት ከፈለግሽ ብር ሰጥቼሽ ምን መስራት እንደምፈልጊ ..በተጨማሪም እኔ ካልኩሽ ዉጭ የራስሽ ሀሳብ እቅድ ካለሽ  የአንድ ወር ጊዜ ሰጥቸሻለሁ...በአንድ ወር ዉስጥ አስበሽ ወስነሽ ትነግሪኛለሽ  አለኝ.....
እኔም እሺ አባቴ ብየ ከአጠገቡ ተነስቼ መኝታ ክፍሌ ሂጄ ተቀመጥኩኝ.....

አባቴ እንዳለኝም አንድ ሀሳብ መጣልኝ....ጓደኞቼ የሚደርሱበት ደረጃ መድረስ አለብኝ ..ስለሆነም አጥንቼ ፕራይ ቤት ተፈትኜ ጥሩ ዉጤት አምጥቼ priparatory መግባት አለብኝ ...የኔ ችግር 10ክፍል ላይ በመጥፎ ጓደኞች ተከብቤ ተተብትቤ ስላላጠናሁ ስላልተዘጋጀሁ ነዉ እንጂ ካጠናሁ ከተዘጋጀሁ እኔ ጎበዝ ነኝ እኮ አቃለሁ...እያልኩ ያሳለፍኳቸዉ ስህተቴ ዋጋ ማስከፈሉን አወኩኝ....10ን ፕራይ ቤት ካለፍኩኝ ቡሀላ  ዩኒቨርስቲ መመረቅ አለብኝ የሚል ሀሳብ በአእምሮየ ይደጋገም ይዟል፡፡

ከሁለት ቀን ቡሀላ አባቴ ወስኛለሁ ስለዉ ..ጊዜዉ ገና ነዉ በደንብ እሰቢበት አለኝ... ከአንድ ሳምንትም ቡሀላ ወስኛለሁ ስለዉ አባቴም በጭራሽ ይሄ የፍጥነት ዉሳኔ አይሆንም አንድ ወር ሰጥቸሻለሁ አንድ ወሩ ሲያልቅ እኔዉ ምን ወሰንሽ ብየ እጠይቅሻለሁ አለኝ፡፡


የተሰጠኝ አንድ ወር የማሰብ ጊዜ አለቀ....ከአንድ ወር ቡሀላ አባቴም ጠርቶ ምን ወሰንሽ ????አለኝ
....እኔም አባቴ አጥንቼ ተዘጋጅቼ ፕራይቤት ተፈትኜ ዉጤቴን አሻሽየ 11 ክፍል ለመግባት ወስኛለሁ አልኩት፡፡
....አባቴም ግን በደንብ አስበሽበታል እርግጠኛ ነሽ?? አለኝ
........እኔም አዎ አስቤበታለሁ እርግጠኛ ነኝ አልኩት
....አባቴም እሺ በሀሳብሽ ምንም አልልም ጣልቃ አልገባም ግን ይሄ ሀሳብሽ የራስሽ ሀሳብ ነዉ ..እራስሽ መጀመሪያ አስበሽ ወስኝ ብየሽ ወስነሻል የዘንድሮዉን አመት በአንቺ ሀሳብ በአንቺ ፍላጎት ተስማምቻለሁ፡፡ ነገር ግን በሚቀጥለዉ አመት ግን አንቺ ያሰብሽዉ ባይሳካ ፕራይ ቤት ዉጤት ባይመጣልሽ አንቺ ሒወት ዉስጥ መወሰን የምችለዉ እኔ ነኝ.... የዛን ጊዜ አንቺ ሳትሆኝ እኔ አባትሽን ያልኩሽን ብቻ ነዉ መታዘዝ እና መሆን የምትችይዉ ...በዚህ በኔ ሀሳብ ትስማሚያለሽ አትስማሚም ???አለኝ
.......እኔም ትንሽ ከአሰብኩኝ ቡሀላ በአባቴ ሀሳብ.......


#ክፍል 🔟
ይ......ቀ.......
.....ጥ.........ላ.........ል


: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አስር 🔟

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




እኔም ትንሽ ከአሰብኩኝ ቡሀላ አባቴ አቃለሁ ለኔ አስበህ እንደሆነ ሁሌም ቢሆን በአንተ ሀሳብ እስማማለሁ ...መጀመሪያ እድሉን ስለሰጠሀኝ አመሰግናለሁ አልኩት፡፡
     አባቴም የኔ እኮ አይኔ ማረፊያ መኩሪያ የወደፊት ተስፋየ አንቺ ነሽ ነዋል ብሎ ግንባሬን ሳመኝ.....እኔም አንገቱ ላይ ጥምጥም አልኩኝ

    ፕራይቤት ለመፈተን የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ማጥናቴን ጀመርኩኝ ፡፡ አጋዥ መፅሀፎች ገዛሁኝ ...ቀን በቀን ችከላዉን ተያይዠዋለሁ... ጠዋት ጀምሬ እስከ ማታ ድረስ ነበር የማጠናዉ ፡፡ ወላሂ ይገርመኛል ምግብ ለመብላት ለራሱ ትዝ አይለኝም ነበር፡፡

ለሒወቴ መስተካከል ከፍተኛ ሚና የወሰደዉ ከ10 ከወደኩኝ ቡሀላ ነዉ፡፡ ከትምህርት መዉደቄ በያናድደኝ ቢያበሳጨኝም ፈጣሪ አንዳንድ ፈተናዎችን የሚያሽክመዉ ለኛዉ ለዉጥ መሆኑን የተረዳሁበት እኔ ካሰብኩት አላህ የመረጠልኝ የተሻለ መሆኑን ያየሁበት ጊዜያቶች ናቸዉ፡፡ እቤት ብቻየን ስለምዉል የትምህርት ቤት መጥፎ ጓደኞችን እራኩኝ ..ሰአቱን ሳላሳልፍ ሶላት መስገድ ጀመርኩኝ ..በወጣትነቴ ሒጃብ ለብሰሽ ባልቴት መሰልሽ ብለዉ ያስወለቁኝን ሒጃቤን መልሼ አላህን ማረኝ አይለመደኝም ብየ ለበስኩኝ.....ከነመኖሩ የረሳሁትን አንስቸዉ የማላቀዉን ቁርአን መቅራት ሙራጅአ ማድረግ ጀመርኩኝ ፡፡ እስኪ ስለሂጃብና የተከበረዉ ቅዱስ ቁርአን አንዳንድ ነገር ልበላችሁ.....

✿✿✿ ሒጃብን ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ ዘውትር ለብሶ ማክበር ነው እንጂ የሒጃብ ቀን የሚባል የተለየ ቀን የለውም!!
"ሒጃብ ማለት እስልምና በሴት ልጅ ግዴታ ያደረገባት ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበት ሰፊ ልብስ እንጂ በአመት አንዴ አናቷ ላይ ብጣሽ ሻሽ ጠምጥማ ቀን ለይታ የምታከብረው ነገር አይደለም!!
"
ሒጃብ ማለት ሴት ልጅ እዚህች አለም ላይ ከተለያዩ ባለጌዎች ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበትና የተለያዩ ጨዋ ወንዶች ደግሞ እርቃኗ በመሄዷ እንዳይፈተኑ የምታደርግበት ከፈጣሪዋ አላህ ዘንድ የታዘዘችው በህይወት ዘመኗ ሁሉ የማትለየው ልብስ ነው።
"
ሒጃብ ማለት ሸይጧን እና የእስልምና ጠላቶች እንደሚፈልጉት የምትለብሰው ልብስ ሳይሆን የፈጠራት ፈጣሪዋ እንዳዘዛት ዘውትር የምትለብሰው ወደ ፈጣሪዋም የምትቃረብበት የፅድቅ ልብስ ነው።
ከሸሪዓው ከሚፈልገው የሒጃብ አይነት ውጪ ከሆንሽ ራስሽን ለባለጌዎችና ለብልግና እያመቻቸሽ ነው ማለት ነው።
"
ሒጃብሽን አላህ ባዘዘሽ መልኩ ከለበሺው ነገ በአኼራ ሰውነትሽ እሳት እንዳይነካውም ይከላከልልሻል።
"
ሒጃብ ስለብሺ ትልቅ ሰዉ አስመሰለሽ አላማረብሽም እያሉ የሚያጃጅሉሽን ትተሽ ፈጣሪሽ ከሰባት ሰማይ በላይ ያዘዘሽን ትእዛዝ አክብረሽ ዘውትር አላህ በሚፈልገው መልኩ ሒጃብሽን ጠብቂ!!...የዛን ጊዜ አንቺን ማንም ቀጥ ብሎ አይቶሽ ልጋጉን ተፍቶብሽ የሚሄድ የለምና ....

✿✿✿ እስኪ ስለ ቅዱስ ቁርአን አንዳንድ ነገር ልበላችሁ ...ሊከበሩ ከሚገባ መፅሀፎች ትልቁና ዋናው ቁርዓኑል ከሪም ነው። ምክንያቱም የፈጠረን ጌታ የአላህ ቃል ነውና። ለኛ መመሪያ ነው። መተዳደሪያችን ነው። ማንዋላችን ነው። አዛዣችን ነው። ጀነት መግበያችን ነው።ከጀሀነም ማስጠንቀቂያችን ነው። እና ምንም ብለው መግለፅ አልችልም። ምክንያቱ የቁርዓን ሚስጥሩ ማንም ቢሆን ያወቀው የለም። ሁሌም ሩቅ ነው።
እሺ ለምንድ ነው ዛሬ እኛ ለቁርዓን ክብር ያልሰጠነው???
ቁርዓን እንኳን ሊቀደድ እንኳን ሊቃጠል ሲቀራ እንኳን ዝም በሉ ነው የተባልነው
አላህ በተከበሩ ቃሉ እንዲህ ይላል
ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም (ዝም) በሉ ይታዘንላችኋልና፡፡(አል-አዕራፍ 204)

ዛሬ ይቀደዳል። ዛሬ ይወረወራል። ዛሬ ይቃጠላል። አይ የኛ ነገር በቃ ችሎታችን ይህ ብቻ ነው?? ወላሂ እኛ ለቁርዓን ክብር ብንሰጥ ኖሮ እኛ ብንኖርለት ብንኖርበት ቦታ ብንሰጠው ዛሬ ይህ አይመጣም ነበር። እንኳን ሰሀቦች ያ~ብፁዕ ትውልድ ይቅርና ሰለፎች እንኳን ለቁርዓን ለነብዩ ﷺ ሀዲስ ቦታ ይሰጡ ነበር።
አቡበክር ረ.ዐ እንዲህ ይሉ ነበር፦
አንድ ሰው ቁርዓን ከቀራና ከሰራበት ምንም ያጣው ነገር የለም። ቁርዓን መቅራት ያልቻለና ያልሰራበት ድሀ ማለት እሱ ነው አሉ። እነሱማ እንኳን ለአላህ ይቅርና ለረሱል ﷺ ሀዲስ ክብር ነበራቸው።

ኢማም ማሊክ ረ,ዐ ታላቁ ታብይ የረሱል ﷺ ሀዲስ ለማስቀራት ሲጀምሩ ውዱዕ አድርገው ሁለት ረከዐ ሰግደው ሙሉ ሱናው ጠብቀው ይጀምሩ ነበር። አንድ ሰው ከጮኸ በረሱል ﷺ ላይ እንደ ጮኸ ይቆጥሩት ነበር። መስጅድ ውስጥ ጊንጥ አስራስድስት ቦታ ሲነክሳቸው እግራቸው በደም ሲላወስ የነብዩ ﷺ ሀዲስ ክብር ብሎ ሳይንቀሳቀሱ ያስቀሩን ነበር ።
አሉ አብድላህ ኢብን ሙባረክ ረዓ
እስቲ ማን ነው ከእኛ መሀል ይህን ያህል ፅናት ለቁርዓን ክብር ብሎ የሰጠ??

ከዚህ በፊት የነበሩ ሰለፎች እንኳን ቁርዓን ይዞ ሊጨፍሩ ቁርዐን ይዞ ሊጮሁ ሊያወሩ ይቅርና ቁርዓን የወረደበት ሀገር መካ ውስጥ መጮህ አይቻልም ይሉ ነበር። ኢማሙ አሽ~ሻፊዒ ረ.ዐ እንዲህ ይሉ ነበር፦
ቁርዓን ያለበት ቤት ውስጥ መተኛት አይቻልም ይላሉ፤ምክንያቱምበመኝታ ሰዓት ራስን መቆጣጠር ስለ ማይቻል የሚጮህ ከሆነ ፣ህልም ላይ መናዘዝ፣ ዉዱዕ የሚያስፈታ ነገር ስለሚፈፅም
ይህ ሁሉ ጥንቃቄ ቁርዓንን ይዞ ሳይሆን ቁርዓን ቤት ውስጥ ካለ ሌላ ቤት ማደር ነው። ይላሉ።
ውዱዕ ካላደረጋችሁ ቁርዓንን እንዳትነኩ ይላሉ።
ማሻዓላህ ቁርዓን አክትመናል፤ ስንት ቁርዓን ቀደድን???
ለቁርዓኑስ ምን ያህል ክብር ሰተነዋል??
በየቤታችን ቁርዐን የቡፌ ማስዋቢያ አርገነዋል። ምንአልባት ረመዳን ሲመጣ አዉርደነዉ በሶፍት ወይም በጨርቅ እንጠርገዉ ይሆናል።
አባታችን የሆነ ውርስ ቢያወርሰንና የአባት ውርስ ቦታ ይሰጠዋል እኮ እና አንዱ መጣና ስብርብር፣ ቅድድ፣ ቢያረገውና ምን ታመጣለህ ብሎ ቢጐርርብን ቆመን እናየው ነበርን?
ወላሂ እስክንሞት ወይም እስክንገድለው ድረስ በፍፁም አንተወውም ነበር።
እና የአላህ ቃል የረሱል ﷺ ውርስ እንዴት ይህ ሁሉ በደል ሲደርስበት ለምንድን ነው ዝም ያልነው???
ወላሂ ዛሬ ክብር የሰጠነው ቢሆን ኖሮ የማንም ክብር የሌለዉ ፍጥረት
ቁርዓንን እንዲህ ባልጨፈረበት፤ ነበር።አጃዒብ ሚሆነው ደሞ ቁርዓን ሲረገጥ እንደ ሶፍት ሲጠቀሙበት ምንም የማይመስለን ሰው ምን ሆነን ነው???
ፈጣሪ ሆይ በቁርአን ይምንሰራ በቁርአን የምንተዳደር በቁርአን መመሪያ ኑረን የምንሞት አድርገን ያረብ
  

                   አልሀምዱሊላህ ከትምህርት ቤት መጥፎ ጓደኞቼ አንድ ባንድ እራኩኝ የተወሰኑት እየደወሉ ያወሩኛል...
ናርዶስ ጋር ግን ቀን በቀን ሁሌ እንደዋወላለን ፡፡

ለዉጥ ከሆነ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለብኝ ብየ ወሰንኩኝ...የበፊት ትምህርት ቤት ጓደኞቼ እንዳያገኙኝ ብዙ ሰዉ ወንድም ሴትም የሚያቀዉን ስልክ ቁጥሬን ለመቀየር ወሰንኩኝ👇👇👇
.....አባቴን አዲስ ሲም ካርድ አዉጣልኝ ብየዉ አወጣልኝ... ይሄን ሲም ካርድ የሚያቁት እናት እና አባቴ በተጨማሪም ለናርዶስ ደዉየ ለማንም ይሄ የኔ ቁጥር መሆኑን እንዳትነግሪ ብየ አሳወኳት.... ከማይጠቅም ከማይጎዳ በስልክ ወሬ ከመዘናጋት በዚህ ተገላገልኩ፡፡ አሁን የቀረኝ Facebbok.ላይ የሚያወሩኝ የምጀናጀንበት ወደ ሇላ እንዳይመልሰኝ መላ መዘየድ አለብኝ .... ያለኝ አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ ነዉ..ይሄዉም ፌስቡኬንም delete አድርጌ በአዲሱ ቁጥሬ ለመጀናጀን ሳይሆን በሳምንት አንዴ መረጃ ለማየት ያህል ከፈትኩኝ......

አካበዳችሁ እንዳትሉኝ እዉነቴን ነዉ...ምንም ቢሆን ምንም ከቤት በጭራሽ አልወጣም .... በፊት ቤት ስሆን ጓደኞችሽ ጋር ሂጂ ሂጂ ነበር የሚለኝ..ደግሞ አሁን የዛ ተዘዋዋሪ ከቤት መዉጣት በጣም ነበር የሚያስጠላኝ ..,ከቤት የምወጣዉ ለጁምአ ሶላት ብቻ ሲሆን ነዉ..ጁምአም የምሰግደዉ ኑር(አጂፕ)መስጊዱ ከኛ ቤት በጣም ቅርብ ነዉ፡፡  መስጊድ አምስት ሰአት አካባቢ እገባለሁ አወለ ሶፍ ከጥግ በኩል እሆናለሁ ኹጥባዉ እስከሚጀምር ቁርአኔን እቀራለሁ ፡፡ መስጊድ ማን ይምጣ ማን ይቅር የማቀዉ ነገር የለም ...
ከቤት ከወጣሁም በ15ቀን አንዴ ለገበያ እናቴ ጋር ነዉ የምወጣዉ ፡፡ አባቴ እንደዚህ መሆኔን ሲያየኝ ከቤት እንድወጣ እንድዝናና በማሰብ የተለያየ ቦታ መልዕክት ይልከኛል
.......እኔ ግን በጭራሽ መላክም ከቤትም መዉጣት ፍላጎቱ የለኝም
አባቴ ግድ ነዉ መዉጣት አለብሽ ብሎ ይቆጣኛል...ብር ይሰጠኝ እና በዛዉም ካፌ ገብተሽ ተዝናንተሽ ነይ ይለኛል
.......በብዙ ቀናት ልዩነት ቢያንስ በ20ቀን ልዩነት ስወጣ የሰፈር ሰዎች ..በፊት የማቃቸዉ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ብዙ ሰዉ እኔን እያየ እየተገረመ ...አረ ነዋል አለሽ ወይ?? የት ጠፍተሽ ነዉ ?? ወላሂ በጣም አምሮብሻል የተወለወለ ጠመንጃ መስለሻል..በተጨማሪ ትልቅ ሰዉ ሁነሻል ሳይለኝ የማያልፈኝ ሰዉ የለም.... እኔም በሰዉ እኔን አጥብቀዉ ሲጠይቁ ግራ እየገባኝ ...አንዳንዴ መጥፋት ከሰዉ አይን መራቅ እንደዚህ ያስናፍቃል ማለት ነዉ??ብየ እራሴን እጠይቀዋለሁ .. 
  
   ፀሀዩ ንፋሱ ብርዱ ቅዝቃዜዉ ሙቀቱ ስለማያገኘኝ ስላልተፈራረቀብኝ ነዉ መሰለኝ ዉበት ይጨመርኩበት ..ፊዚካሌ ከልጅነት ወደ ትልቅነት የተቀየርኩበት አመት ነዉ፡፡  ብዙ ሰዉ ነዋል አምሮብሻል ትልቅ ሰዉ ሁነሻል ..አንዳንድ ትላልቅ የሰፈራችን ሰዎች እንደ ቀልድም ለልጄ ነዉ የምድርሽ ትልቅ ሰዉ ሁነሻል ሲሉኝ... እቤት ስመለስ ወደ ክላሴ ሂጄ ..ሰዎቹ እንዳሉኝ አምሮብኛል እንዴ ?? ትልቅ ሰዉ ሁኛለሁ እንዴ??ብየ እቤታችን መኝታ ክፍሌ ያለዉ ትልቅ መስተዋቱን እኔዉ ስመለከተዉ እሱም የቀኜን በግራ የግራየን በቀኝ አርጎ እየተመለከተኝ ፊት ለፊት እንደተፋጠጥን እጠይቀዋለሁ....
እኔ አላማየ የዉበት መጨመር ሳይሆን ፕራይ ቤት ለማለፍ ስለሆነ አባቴን ለራሱ የማወራበት ጊዜ አጣሁኝ ..,ማታ አባቴ ሲመጣ እንዴት ዋልክ ብየ 30ደቂቃ አዉርቼ መልሼ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ኢሻን ሰግጄ እተኛለሁ ከዛም  ለሊቱ 8፡00 ሰአት ለማጥናት  እነሳለሁ ከዛም ሱብሒን ሰግጄ እተኛለሁ  ትንሽ ተንቼ  የቤት ሰራተኛችን ጋር አብረን ቤት አፅድተን ሰትረን ከጨረስን ቡሀላ ቤተሰቦቼን ቁርስ አብልቼ  መልሼ ወደ ጥናት እስከ ዙሁር አጠናለሁ ፡፡ ዙሁርን ሰግጄ ምሳ በልቼ እስከ አሱር ማጥናት ፈተናዉ እስኪ ድረስ ፕሮግራሜ እንደዚህ ነበር..

ደጅ ፀሀይ እንደበፊቱ ሳያጠወልገኝ ማን ሞተ??፡ ማን አገባ ??፡ማን ታመመ?? ብየ ሳልጠይቅ ከማንም ጋር ሳልገናኝ አላማየ ለፈተና መዘጋጀት ብቻ ሆነ፡፡

    ይሄ አመት በሒወቴ ትልቅ ለዉጥ ያመጣሁበት እራሴን ማንነቴን የፈተሽኩበት ጊዜ ነዉ ፡፡ የመጀመሪያ ለዉጤ እኔ ከአሁን ቡሀላ ልጅ አይደለሁም ትልቅ ሰዉ ሁኛለሁ .. እንደትልቅ ሰዉ እንዳስብ አደረገኝ.. በተጨማሪም ብቸኛ ሁኖ መኖር የለመድኩት በዚሁ አመት ነዉ፡፡ ብቸኝነት እቤት መዋል ለምጄ ሰዉ ጋር መቀራረብ እስከሚያስጠላኝ ድረስ ነበር ከሰዉ የተለያየሁት ...እቤት ለራሱ እናቴ አትዉልም ነጋዴ ናት ጠዋት ወጥታ ማታ ነዉ የምትገባዉ፡፡ ወንድም እና እህቶቼም ጠዋት ትምህርት ቤት የሄዱ የሚመጡት ወደ 11:00 አካባቢ ነዉ፡፡አባቴም ያዉ ኮንትራክተር ስለሆነ የሚመጣዉ ማታ ላይ ነዉ፡፡ ያለነዉ እኔ እና ሰራተኛችን ነን ...የቤት ሰራተኛችንም ስራዉን ሰርታ ስትጨርስ የራሷ ክፍል አላት እዛ ነዉ የምትዉለዉ...ቤቱ እና እኔ ብቻ ነዉ የምንዉለዉ ..ቤቱ ፀጥ ሲል ብቻየን ስሆን በጣጣጣም ደስ ይለኛል፡፡ ጎረቤቶቼ እንዴት ነዉ እንደዚህ የምትኖሪዉ ??ይሉኛል...እኔ ግን ሰዉ ሲኖር ነዉ የምጠላዉ ብቻኛ መሆን ነዉ የምፈልገዉ

  ደግሞ ይሄ አመት ስለእስልምና በደንብ እንዳዉቅ አደረገኝ ....የተለያዩ ኢስላማዊ መፅሀፍ በመግዛት እያነበብኩኝ እራሴን ቀየርኩኝ፡፡ አላህን እንድወድ ተማሪ ሁኜ እነዛ መጥፎ ጓደኞች ጋር ያሳለፍኩት መጥፎ ትዝታ ሳስታዉስ እያለቀስኩ ተዉበት እያደርኩ አላህ ይቅር በለኝ እያልኩ ነዉ የምዉለዉ አልሀምዱሊላህ፡፡ እናም ለወደፊት ሒወቴ መጥፎ ጓደኛ ላልይዝ የበፊቱ ጥፋት መሆኑን አመንኩኝ፡፡
    
በተጨማሪም ለወደፊት ያሰብኩት አሁን ላለሁበት እያንዳንዱ ሒወቴ አላማ እንዲኖረኝ የወደፊት እቅድ አዉጥቼ ማሰብ ጀመርኩ ፡፡ አሁን የመጀመሪያዉ ፕራይ ቤት መፈተን አይደል አላህ ብሎ ከተሳካ ማሻ አላህ ግን ደግሞ ካልተሳካም ተስፋ ላልቅርጥ ሌላ ትምህርት በግል ለመማር ወሰንኩኝ፡፡

   ይህ አመት ለዉጥ እንዳመጣሁ ሁሉ በተዘዋዋሪም ከእስከዛሬዉ ተማሪ ልጅ በነበርኩበት ጊዜ  ያሳለፍኩት መከራ ታዉቁ የለ ከዛ በላይ ፈተና መጣብኝ፡፡ ቤት መዋል አንዳንዴ ከሰዉ የሌለንን ስም እንዲሰጠን ያደርጋል...ይህም የወንድ ልጅ የትዳር መስፈርቱ ከአፉ የማትጠፋ ሁለት ቃላት የቤት ልጅና ድንግል ናት ወይ?የምትለዉ አፋቸዉ ላይ እንደ ማስቲሽ ተጣብቆ የድርጅት ማህተም የተመታበት ነዉ የምመስለዉ...እኔም ለፕራይቤት ፈተና አጥንቶ ለመፈተን እያጠናሁ እቤቴ ብዉል .. #ነዋል_የቤት_ልጅ_ናት ተብሎ የኔ ስም አንዴ በኛ ሰፈር ለትዳር እደረሱት የዘመኑ ጎረምሳ ተብየ የሰፈር ልጆች ጋር በአንዴ ተናፈሰ ፡፡

ይሄ እቤት መዋል የቤት ልጅ መባል ...ያልጠበኩት ያላሰብኩት ሌላ መዘዝ ችግር የአእምሮ ጭንቀት ዲፕሬሽን ይዞቦኝ መጣ........የኔዉ ዉበት ቁመት ሙቀት እድገት በአንዴ በማዳበሪያ አንደተዘራ በቆሎ እሸቱ ደረሰ፡፡ በጣም ትልቅ ሰዉ ሆንኩኝ ከቤት ቢያንስ በ15ቀን አንዴ ለሆነ ሀጃ እናቴ ጋር ስወጣ ..በኔ ዉበት እራሱን የማያክ ..በሁለቱም አይኑ እስከሚነቀል ቡዝዝ ብሎ የማያየኝ ..እኔን ለማግባት የማይቋምጥ መቁጠሩ ይቀላል... የሰፈር ለትዳር የደረሱ ወጣቶች አይን ዉስጥ ተሰነቀርኩኝ..


#ክፍል 1⃣1⃣

ይ........ቀ..........
......ጥ........ላ...........ል

ቤተሰብ ሼር አይዘንጉ
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አስራ አንድ 1⃣1⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




እኔን ለማግባት የማይቋምጥ መቁጠሩ ይቀላል... የሰፈር ለትዳር የደረሱ ወጣቶች አይን ዉስጥ ተሰነቀርኩኝ..
እናቴ ጋርም አንዳንዴ ስሄድ የአንቺ ልጅ ናት ??ብለዉ ይጠይቋታል...እናቴም አዎ ትላቸዋለች ..ማሻ አላህ ብለዉ የሚያስቡትን አስበዉ ይሄዳሉ ፡፡
      እኔም ይሄን አመት ትልቅ ሰዉ መሆኔን...በፊት ልጅ እንደነብርን ባልሽ ሚስትሽ ስንባል እንደማናለቅስ ግን ሲያድጉ ትዳር የማይቀር መሆኑ ለወደፊት ትዳር እንደሚጠብቀኝ ተረዳሁኝ... እናቴ ወደ ዉጭም ይዛኝ የምታወጣዉ ሳልወድ በግዴ ነይ ገበያ እንሂድ የምትለኝ ለዚህም እንደሆነ ተጠራጠርኩኝ፡፡

እኔን ያየ ለማግባት የማይቋምጥ የለም ነበር፡፡
ወላሂ እኔን የጠየቀኝ ባል ቆጥሬ አልጨርሰዉም ለኔ የነገሩኝ አባቴ እና እናቴ ያልነገሩኝም ብዙ አሉ፡፡
የትዳር ጥያቄ በጣም በዛ እንደጎርፍ ሆነ፡፡
እናቴም:- ነዋል ምንድን ነዉ አንቺን የሚፈልግሽ በዛ እኮ ለማን እንድርሽ ይሆን ?? ግራ ገባን እኮ ትለኛለች..

እናቴን የሚያቋት እናቴን ይጠይቃሉ... አባቴን የሚያቁት ደግሞ አባቴን ይጠይቁታል፡፡ አባቴ ግን እኔን ሳያማክር በተረጋጋ በሰከነ መልኩ ይመልሳቸዉ ነበር....
......የአባቴ መልስ እጥር ምጥን ያለ ነበር .. ነዋል ታገቢያለሽ ወይ ብየ ጠይቂያት ነበር ግን እሷ አሁን ማግባት አልፈልግም ፕራይቤት ተፈትኜ ትምህርቴን መማር ነዉ የምፈልገዉ ብላለች እያለ ይመልስልኛል፡፡ በተዘዋዋሪ ደግሞ እናቴ እንደ አገባ ትፈልጋለች ሲጠይቋት ኢንሻ አላህ እያለች ተስፋ ትሰጣቸዋለች ፡፡

   ግን ከባድ ጥያቄ እና መልስ የሌለዉ የሒወቴ ጥያቄ እዚህ ላይ ነዉ...እነዚህ ለትዳር የሚመጡት ሰዎች በፍቅር ሳይሆን የመጡት በዉበት እና እቤት ስለምዉል ከማንኛዉም ሰዉ ጋር ስለማልገናኝ የቤት ልጅ ናት ተብለዉ ነዉ፡፡ እነሱ ለኔ ያላቸዉ አመለካከት ከቤት ስለማልወጣ ከሁሉም ሴቶች የተለየ ነዉ.....ግን አንድ ጥያቄ አለ.... #ድንግል_ነሽ_ወይስ_አይደለሽም ??? ብለዉ ቢጠይቁኝ ምንድን ነዉ መልሴ ?? ወይስ ገና በልጅነቴ መደፈሬን ያቃሉ ወይስ አያቁም ??? እያልኩኝ ብቻየን ሀሳብ ሁኖብኛል፡፡ በልጅነቴ በጊዜዉ ብናደድም የምናደደዉ እንዴት በቶፊቅ የተደፈርሽዉ ?? ይሉኛል ነበር..ግን አሁን በመናደድ ብቻ የሚተዉ አይደለም ለሚጠይቁኝ ጥያቄ መልስ ያስፈልገኛል፡፡

    እንደዚህ ያሉ ትዳሮች በጣም ከባድ ትዳሮች ናቸዉ ፡፡ በፍቅር በመቀራረብ ቢሆን የሚወደኝ ከሆነ ግልፁን እነግረዋለሁ ከወደደኝ እና ካመነኝ አንድ ጎጆ ቀልሰን መኖር እንችላለን .. ካመነበት ያምናል ካላመነበት ይቀራል እላለሁ ፡፡ ግን ይሄ የሚመጡት ትዳር የደህና ቤተሰብ ልጅ ናት፡ ጨዋ ናት፡ እቤት ነዉ የምትዉለዉ በሚል ምክንያት ነዉ የሚመጡት ፡፡

ግን ደስ የሚለዉ አባቴ ምን ወሰንሽ ብሎ አይጠይቀኝም እራሱ ነበር፡በተለያየ ምክንያት የሚከለክላቸዉ አንዴ በትምህርተ ሌላዉን በተለያየ ዘዴ ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፡፡

ከሁሉ ደግሞ ያስቸገረችኝ እናቴ ነች...የእኔ እና እናቴ አስተሳሰብ እህል ከዉሀዉ አልገጥም አለን .እሷን የጠየቋትን ሰዎች ብዙዎቹን ነገረችኝ እና ምረጭና አንዱን አግቢ እያለች ትነዛነዘኝ ትቸካቸከኛለች .. እናቴ በመሸ በነጋ ቁጥር አግቢ እያለች ጫና ስታበዛብኝ ...የማይሆን አስተሳሰብ ማሰብ ጀመርኩኝ
......እኔ ከትምህርት ስለወደኩኝ እቤት ስለምዉል ይሄን ያህል ሸክም ሆንኩ ማለት ነዉ ?? ገና ትዳር መጥቶ አግቢ አግቢ እያለች መቆሚያ መቀመጫ የምታሳጣኝ??? እያልኩ ሌላ ሀሳቦች አእምሮየ ላይ ተንባረቀብኝ ፡፡
......,,እናቴንም በኔ ሒወት አትግቢ እያልኩኝ ቀን በቀን መጣላት የዘወትር ተግባራችን ሆነ ...በእናቴ አንዱን አግቢ ምረጭ እያለች በምታጨናንቀኝ ጊዜ የማነባቸዉን መፅሀፎች ላይ አይኔ ቢተከልም ግን ከማገላበጥ ዉጭ ወደ አእምሮየ ዉስጥ ሊገባ አልቻለም..የእኔና እናቴ እሰጣ ገባ ቀን በቀን እየባሰ እየጨመረ መጣ.....

.እናቴ ግን እንዴት ይሆን የኔን ዉስጤን መረዳት የምትችለዉ??? ቀርባ እንደ እናት ምክንያቴን እና የሆዴን የዉስጤን የሀሳብ ማዕበል   ለመረዳት ፍቃደኛ አይደለችም ግን ለምን እናትነት ትርጉሙ ምንድን ነዉ???

እናቴንም በኔ ሒወት አትግቢ እያልኩኝ ቀን በቀን እንጥላለን....ግን ይሄንን መጣላታችንን አባቴ አያቅም.........አባቴ እቤት ባለ ሰአት አትናገረኝም ዝም ነዉ የምትለኝ ..አባቴ ከቤት ሲወጣ እግሩን ጠብቃ ጠዋት ማታ አንዱን ምረጪ እና አግቢ አግቢ እያለች በልጅነት አእምሮየ ሌላ ሀሳብ ሆነችብኝ...
 
  እኔ ደግሞ ለአባቴ እናቴ አግቢ እያለች እረብሻኛለች ብየ ብነግረዉ ..አባቴ በእሷ ሒወት ምን አገባሸ ??እንደሚላት አቃለሁኝ....እናት እና አባቴ በጣም ከባድ ፀብ እስከ ትዳር መፋታት እንደሚደርሱ ይታየኛል፡፡ ምንም አማራጭ የለኝም እናቴ ቀን በቀን ብትቸከችከኝም ለአባቴ ግን መቼም አልናገርም በኔ የተነሳ እንዲጣሉ አልፈልግም ...


ቀናቶች በተቀያየሩ ቁጥር ከዛሬ ነገ ይሻላል ብየ ተስፋ ባደርግም ባዶ ተስፋ ሆነብኝ ..የእናቴ ፀባይ ቀን በቀን እየባሰ ሄደ ....በጭራሽ አመሏን መሸከም አቃተኝ ሳንጣላ የዋልንበት ቀን መቁጠር ይቀላል
  እናቴ የትዳር ጥያቄ በሷ በኩል ሲመጣ ..ነዋል ለምን ትዳር ትመልሻለሽ?? ለምን አታገቢም??? ትለኛለች
..... እኔም አሁን ማግበባት አልፈልግም መማር ነዉ የምፈልገዉ እላታለሁ
...እናቴ ለኔ የምመልስልኝ መልስ አእምሮየን ያደማዋል አስተዉላ አገናዝባ መናገር አትችልም ሰዉ ይከፈዋል ብላ ቃላቶች መምረጥ አችልም ንግግሬ ሰዉ ይጎዳል አይጎዳም ብላ መጥና መናገር አይሆንላትም እንደ አዛባ ዱላ የምትወረዉረዉ መጥፎ የቃላት ማዕበል እኔን አእምሮየ ሊመጥነዉ ሊቀበለዉ አልቻለም...  ብዙ ቀን እንደዚህ ትለኛለች....የማታገቢዉ ለመንዘላዘል ፈልገሽ ነዉ ?? """""""""ለነገሩ አንቺም እሺ ብትይም እነሱ በተለያየ ምክንያት ላይፈልጉሽ ይችላሉ """"""""" እያለች ብዙ ቀን ትደጋግመዋለች ...ወይስ ምንድን ነዉ ትምህርቴ ትምህርቴ የምትይዉ ተምረሽ ምን ልታመጪ ነዉ ??? እያለች ሁሌ አእምሮየን ታደመዋለች፡፡ እኔ በልጅነት መደፈሬ ደግሞ ቀን በቀን ሁሌም ሳልጨነቅ አድሬ አላቅም አንዴ አእምሮየ ላይ ተቀርፇል፡፡ የእናቴ መጥፎ ንግግሮች ከዚሁ ጋር የተያያዘም ነዉ

በዚህ የትዳር ጥያቄ የተነሳ በልጅነቴ ድንግልናየን ማጣቴ  ታንቄ ወይ ኤሌክትሪክ ይዤ ብሞት እመኛለሁ ፡፡
    ግን የአባቴ ታናሽ ወንድም አለ . .አጎቴን እንደ ወንድሜም የማየዉ ብዙ ነገር አማክረዉዋለሁ፡፡ ብዙ ነገሮችን ይመክረኛል ከጎኔ እሱ ነዉ ያለኝ...በሒወቴ ለኔ ተፅእኖ ፈጣሪ ነዉ ብየ ደፍሬ የማወራዉ ከአባቴ ቀጥሎ አጎቴ ነበር፡፡

   እኛ ቤት ተቆጪ ተቆጣጣሪ ሀይለኛ አዛዥ ከልካይ ፈላጭ ቆራጭ እናቴ ስትሆን ደግሞ በተዘዋዋሪ ለልጆቹ አዛኝ ልጆቹን የሚያጫዉት የሚያዝናና ሩህሩህ አባታችን ነዉ ፡፡ እኛ ቤት የእናት አመለካከት እንደ አባቴ ሲሆን ..የእናት አመለካከት ደግሞ አባቴ ላይ ይስታወላል፡፡👇👇👇
  
   ከተወሰኑ የቀናት ቆይታ ቡሀላ  በእናቴ አማካኝነት ይሄዉ መከረኛ የትዳር ጥያቄ መጣ ...እናቴም ስታማክረኝ  .እናቴ መደጋገም አያስፈልግም አንዴ ተናግሪያለሁ እኮ መጀመሪያ ትምህርቴን መማር ነዉ  የምፈልገዉ  ብየ ብዙ ቀን ደጋግሜ ነግሬሻለሁ ስለትዳር አታንሽብኝ ብየሽ የለ እንዴ?? ስላት
.........ያለ የለለ አእምሮየን የሚነካ ንግግር እና መንገር የማልፈልገዉ የልጅነት ትዉስታዎች የሚቀሰቅስ ..በልጅነቴ መደፈሬን የሚያስታዉስ  ልብን የሚያደማ ከእናቴ የማልጠብቀዉ መርዝ ቃላቶች ተናገረችኝ፡፡የልጅነቴ ትዉስታዎችን ቀሰቀችብኝ ..ጥሩ መናገር ላያስከፍል ለምን ሰዉ መጥፎ ይናገራል??? ከሰዉም ሰዉ ይመረጣል ግን ከእናቴ ሲሆን ደግሞ ልብን ያደማል.መልካም ንግግር ሰደቃ ነዉ ተብሎ በሀዲስ ተነግሮን ምነዉ ለኛ መልካም ንግግር ከአፋችን እንዳይወጣ ምን አገደን??

...... እናቴ በተናገረችኝ ከአእምሮ መሰረዝ የማይችል የመርዝ ቃላት በጣም ከፋኝ እምባየ ቁልቁል ይወርድ ይዟል........ጭራሽ ንግግሯን መቋቋም አልቻልኩም የተናገረችኝ ንግግር መልሶ መላልሶ አእምሮየ ላይ ይደጋገም ይዟል... በቃ እኔ እዚህ ቤት መኖሬ ከበደሽ አይደል አይኔን ማየት አይደል የጠላሽዉ አልኩኝ እና ከተቀመኩበት ተነስቼ ..የቤት ሰራተኛችን የአይጥ መርዙን የምታሰቀምጥበት ቦታዉን ስለማዉቀዉ ....የአይጥ መርዙን አንስቼ መኝታ ክፍሌ ይዤ ገብቼ በሩን ከዉስጥ ቆለፍኩኝ .....


የቤት ሰራተኛችን እናቴ ጋር ስንጣላ አይታናለች ..ነዋል የሆነ ነገር እንዳትሆን እያለች እኔ ሳላያት እየተከታተለችኝ ነበር.... የአይጡንም መርዝ ይዤ ስገባ አይታኝ እየሮጠች መጥታ ለእናቴ ነዋል የአይጡን መርዝ ይዛ መኝታ ክፍሏ አሁን ገባች ብላ ነገረቻት...

እኔም ይችን የተረገመች አለም ለመገላገል አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወስኛለሁ መርዙን ልጠጣዉ ተዘጋጅቻለሁ....

እናቴ እና የቤት ሰራተኛችን ቤቱን ክፈች እያሉ እናቴም እያለቀሰች  ይለምኑኝ ይዘዋል...እኔ ግን የእናቴ ለቅሶን ወደ ጎን በመተዉ መርዙን ልጠጣ በፊት የሰራሁትን ወንጀል አላህ እንዲምረኝ እራሴን በማጥፋቴ አላህ እንዳይጠይቀኝ እማፀን ተዉበት አደርግ ይዣለሁ....

እናቴ ብትለምነኝ እምቢ ስላት የአጎቴ ቤት እኛ የምንኖርበት ሰፈር ነዉ ..... እናቴ ደወለችለት

አጎቴ ጊዜ ሳያባክን ወዳዉ መጥቶ እንድከፍት በሚያሳዝኑ ቃላቶች ለመነኝ...ነዋልየ ትወጅኝ እንደሆነ ሚስጥሬን አካፍየሽ አንቺም አካፍለሽኝ እኔ ለምኘሽ እንዳጨክኚ እያለ እያለቀሰ ለመነኝ....
  .....አጎቴ ሳያለቅስ ሆዴ ባባ እኔም እራሴን ማጥፋቱን መርዝ መጠጣቱን ትቼ በሩን ከፈትኩት....
አጎቴ ከከፈትኩት ቡሀላ አልሀምዱሊላህ ብሎ በደስታ እምባዎቹን ጠራርጎ ነዋልን ብቻዋን ማዉራት እፈልጋለሁ ብሎ እናቴ እና ሰራተኛችን እንዲሄዱ ነገራቸዉ
....ሁለቱም ሲሄዱልን እኔና አጎቴ ብቻ ቀረን
...,አጎቴም በጣም ተቆጣኝ እንዴት ይሄን ዉሳኔ ትወስኛለሽ ??? እራስሽን ልታጠፊ ያሰብሽበት ምክንያት ተይዉ አትንገሪኝ መስማት አልፈልግም እሰቢ እንጂ እንስፍስፍ ብሎ የሚወድሽ አባትሽ አንቺን አጥቶ ሰዉ ይሆናል ወይ ?? እያለ ብዙ ነገሮች አወራኝ

.........እኔም አባቴ ትዝ ሲለኝ ጥፋተኛ መሆኔ ተሰምቶኝ አለቀስኩኝ ምን ላርግ አጎቴ ምን ላርግ ተቸግሬ እኮ ነዉ እንጂ እራሴን ማጥፋት ፈልጌዉ ወድጀዉ አይደለም እያልኩ እምባየን አፈስ ይዣለሁ ..



#ክፍል 1⃣2⃣
ይ...........ቀ.....
.......ጥ........ላ..........ል


JOIN
´´´  www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አስራ ሁለት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ 1⃣2⃣


.........እኔም አባቴ ትዝ ሲለኝ ጥፋተኛ መሆኔ ተሰምቶኝ አለቀስኩኝ ምን ላርግ አጎቴ ምን ላርግ ተቸግሬ እኮ ነዉ እንጂ እራሴን ማጥፋት ፈልጌዉ ወድጀዉ አይደለም እያልኩ እምባየን አፈስ ይዣለሁ ..
አጎቴም እምባየን እየጠረገ አባበለኝ፡፡

አጎቴም ዛሬ የምታዳምጭዉ ደአዋ ብሎ እራስን ስለማጥፋት ያለዉ ወንጀል ምን እንደሆነ ልኮልኝ ሄደ ፡፡ እራሱን ያጠፋ ሰዉ ጀነት አይገባም የጀሀነም ነዉ...ምንም ነገር ኸይር ቢሰራ እራሱን አጥፍቶ የሞተ ሰዉ የጀሀነም ነዉ የሚል ደአዋ አዳመኩኝ ..ደአዋዉ በጣም ረዥም ነበር አዳምጬ እንደጨረስኩኝ
ለራሴ እንደዚህ አልኩኝ...^^^^^^^^^^^ እኔ በዱንያ ደስተኛ ሳልሆን ኑሬ ደግሞ ከሞት ቡሀላ መጀመሪያ ቀብር ላይ አላህ ራሴን በአጠፋሁበት ይቀጣኛል..ደግሞም ተቀስቅሼ ሞት በሌለዉ ኑሮ ላይ በጀሀነም እሳት መሰቃየት መቀጣት አለብኝ እንዴ?? አላህ ይቅር በለኝ አልኩኝ...,ከአሁን ቡሀላ እራሴን ላላጠፋ እንኳን ላጠፋ ላላስበዉ እራሴን አሳመንኩኝ፡፡ አጎቴ የላከልኝ ደአዋ ላይ ሌላ ጥሩ ጎን ነበረዉ ተስፋ ማድረግ አላህ ጋር ተወኩል ማድረግ እንዳለብኝ ተረዳሁኝ፡፡^^^^^^^^^^^^

ለዚች ለማትጠቅም ዱንያ ፈጣሪ ስንቱን አሳየኝ?ዱንያ የፈተናዎች አለም እንጂ የደስታ አለም እንዳልሆነች ነብዪ ሰ.ዐ.ወ አስተምረዉናል
★★★ኢብን መስኡድ ረ.ዐ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፡-
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ከሳር የተሰራ በሆነ ሰሌን ላይ ተኝተዉ ሲነሱ በሰዉነታቸዉ ላይ የሰሌን ቅርፅ ይታይ ነበር፡፡"" የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የሚተኙበት ፍራሽ ላምጣልወት እንዴ?? አልኳቸዉ
....እርሳቸዉ ግን እንዲህ አሉ፡-
.ይቺ አለም ለእኔ ምኔ ናት? እኔ በዛፍ ጥላ ስር ተጠልሎ ቆይቶ ያንን ቦታ ትቶ እንደሚሄድ ጋላቢ ነኝ ፡፡ብለዋል፡፡ ነብዩ ለዚህ ዱንያ ያላቸዉ ክብር እንዲህ ብለዉ ነበር የገለፁት...ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ ለዱንያ ቅንጣት ያህል ቦታ የላቸዉም ነበር ..የመካ ቁረይሾችን እስልምናን ተቀበሉ ብለዉ ደአዋ ሲያደርጉላቸዉ ..ብር ከፈለክ ከኛ በላይ ብር እንስጥህ ወርቅ ከፈለክ ከኛ በላይ ወርቅ እንስጥህ ስልጣን ከፈለክ ከኛ በላይ ስልጣን እንስጥህ ከአንተ የምፈልገዉ እኛንም ህዝቡንም ኢስላምን ተቀበሉ አትበል ሲሏቸዉ ተወዳጁ ያአላህ ነብይ ግን ፀሀይን በቀኝ እጄ ጨረቃን በግራ እጄ ብታሲዙኝ ከዚህ አቋሜ ፍንክች አልልም ብለዉ ነዉ የመለሱት .ታዳ እኛ ዛሬ ላይ ዲነል ኢስላምን በጥብሱ በቁርሱ የሸጥነዉ ስንቶቻችን ነን??? ነብዩ ሙሀመድ ግን ከሰዉ በላይ ልሁን ቢሉ በዛን ጊዜ ከነበሩ አንባገነን መሪዎች በላይ መሆን ይችሉ ነበር...ግን አሏህ ዱንያን የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ብሎን እኛ ግን ዱንያን አፍቅረን የፈጠረንን ጌታችንን እና ቀብርን ዘንግተናል.....

በሌላ ሀዲሳቸዉ ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል ይህች አለም ለአማኞች እስር ቤት ፡ ለከሀዲያን ደግሞ ጀነት ነች..ብለዋል ..ስለሆነም አማኞች የሆናችሁ ሆይ አሁን እስር ቤት ናችሁ ..ሰዉ እስር ቤት የሚገባዉ ባህሪዉን አስተካክሎ ማህበረሰቡ ጋር ሲቀላቀል ደስታ ይኖረዋል ለምን እስር ቤት ስቃዩ ቁንጫዉ ከዘመድ ከጓደኛ ተለይቶ መኖሩ ከባድ ነዉ ከእስር ቤት ሲወጣ ደስተኛ ይሆናል፡፡ እኛም ዱንያ ላይ ስንኖር ፈጣሪ አላህ ወደ እስር ቤት ልኮን ወደ አኼራ ስንሄድ ከእስር ቤት እንደተፈታን እንቁጠረዉ..ግን ከዱንያ እስር ቤት ስንፈታ ፀባያችንን አስተካክለን ጥሩ ስራ ሰርተን ፈጣሪ እስር ቤት ገብተን የፈተንን ፈተና አልፈናል ወይ??? ፈጣሪ ከዚህ እስር ቤት ለወጣ ሁለት ሽልማት አለዉ አንዱ ግዴታ ነዉ ..እስርቤቱን ያለፈ ጀነትን ሲሸለም..እስር ቤቱ ግን ያልቀየረዉ ምን ይደረጋል መልሶ እስር ቤት ለመግባት እድል አይሰጠዉም ሽልማቱ ጀሀነም ይሆናል...አላህ ይጠብቀን ፡፡ አላህ ሆይ የዱንያን እስር ቤት ኸይር ስራ የምንከስብበት አድርገን ያረብ...
  
አጎቴም ነዋል መርዝ የመጠጣት ያደረገችዉን ሙከራ  ሚስጥሩ እዚሁ አራታችን ጋር ይቅር አላቸዉ
ሁላችንም ለአባቴ ላለመንገር ተስማማን .....አባቴ ይሄንን ወሬ ቢሰማ እኛ ቤት በጣም የከፋ ነገር ይፈጠራል...


እንደዚህ ሁኖ ግን ከእናቴ ንዝንዝ ዉጭ እቤት በማትዉልበት ጊዜ ትምህርቴን ማጥናቴን አላቆምኩኝ፡፡ ቀን እናቴ ስትዉል በዚሁ በትዳር የተነሳ ብንጣላም ማታ አዳር አጠናለሁ
.... መቼም እንደዚሁ እየተነዛነዝኩም እያጠናሁም ትዳርም እየመጣ እየመለስኩም ...አእምሮየ በልጅነቴ መደፈሬ ትዝ እያለኝ እያዘንኩኝ...የማትሪክ ፈተና ደረሰ ፕራይቤት እዛዉ ጂማ ከተማ አጂፕ (ጅሬን) ትምህርት ቤት ተፈተን .......
ክረምት ከአንድ ሀሳብ ጥናት ከሚባል አረፍኩኝ ...
የማይመጣ የለም የማትሪክ ዉጤት መጣ ዉጤቴ በጣም አሪፍ ነበር ያመጣሁት 2.9 ነዉ ...አሪፍ የሰቃይ ተማሪ ዉጤት ባይሆንም ወደ priparatory የማያሳልፈኝን ዉጤት አገኘሁኝ....ደስ አለኝ ለአባቴ ነገርኩት አባቴም በጣም ተደሰተ ..,

ይሄ ደስታየ ግን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሆኖ ቀረ እኔ ስፈጠር ተደሰች ያልተባልኩ ይመስል ሌላ አንድ ሌላ የሚያስጠላ ወሬ ደረሰኝ......

የማትሪክ ዉጤቱ በተነገረ በሳምንቱ ፈተና ስለተሰረቀ ማለፋያ ዉጤት ተጨምሯል ተብሎ የሴት የፕራይቤት ማለፊያ 3 ሆነ እኔ ያመጣሁት 2.9 ስለሆነ ለአንድ ነጥብ ተብሎ ወደኩኝ ........
የሚገርም ነዉ ምን ይደረጋል ትንሽ ቢከፋኝም ምንም አልመሰለኝም ቀደረሏህ አላህ ቀድሮታል የተሻለ አለዉ ብየ እራሴን አሳመንኩኝ....... እኔም የአቅሜን ለማለፍ ሞክሪያለሁ በመዉደቄ ምንም አልመሰለኝም አባቴም በመዉደቄ ምንም አልመሰለዉም እንደ ቀላል ነዉ ያየነዉ ፡፡

ክረምት አልቆ መስከረም ገባ...,አባቴ ጋር የዛሬ አመት ተነጋግረን ነበር መጀመሪያ በአንቺ ምርጫ ተብየ ፕራይቤት ብየ ነበር አልተሳካም፡፡ የዛን ጊዜ የአንቺ ካልተሳካ የኔን ዉሳኔ ነዉ የምወስነዉ ብሎኛል
  በቃሉ መሰረት ከአሁን ቡሀላ የእኔን ዉሳኔ ነዉ የምወስነዉ እኔ ነኝ አለኝ..
....እኔም እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አማራጭ የለኝም
.....አባቴም  በግል በዲፕሎማ እንድማር ጅማ የሚገኘዉ የግል የሆነዉ...ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ
ሊያስመዘግበኝ አብረን ሄድን ፡፡ እኔ መማር የምፈልገዉ አካዉንቲንግ ነዉ፡፡ ኮሌጁ እንደ ደረስን አባቴ የምትማሪዉ Nursing  ነዉ አለኝ ፡፡አባቴ Acounting ብማር ይሻላል ብለዉ አይሆንም ተነጋግረናል በኔ ዉሳኔ ነዉ አለኝ፡፡ Nursing ደግሞ Clinikal nursing እና ሚድ ዋይ ፋይ ነርሲግ (አዋላጅነርስ) አለ ፡፡

እኔም አባቴን እንዲህ አልኩት Acounting አትማሪም ካልከኝ ..ግን አሁን ተማሪ ካልከኝ መማር የምፈልገዉ አዋላጅ ነርሲንግ ነዉ አልኩት
.....አባቴም አይሆንም አንቺ አዋላጅ እንድትሆኝ አልፈልግም  ብሎ ሳልወድ በግዴ ሳልፈልግ Clinikal nursing አስመዘገበኝ፡፡👇👇👇
ትምህርት ጀመርን እኔም መማር ጀመርኩኝ...አባቴም ዩኑፎርም የለም እኮ ልብስ ጫማ እና ፓርሳ መቀያየሪያ መግዣ ብር እያለ በጣም ብዙ ብር ይሰጠኛል......በዚህም ብር በጣም የሚያማምሩ ጫማዎች ልብሶች ፓርሳዎች ስለገዛሁኝ እቀያይራለሁ፡፡ በኔ ዉበት የተነሳ የትምህርት ቤት ወንዶች እኔን አይቶ ምራቁን የማይዉጥ ወንድ የለም ..
የሚገርማችሁ ኮሌጅ ለራሱ ገብቼ የአእምሮ ዲፕሬሽን አለቀቀኝም ከሰዉ ጋር አልቀላቀልም ብቸኝነት ምርጫየ ነዉ ከክላስ ዉጭ ላይብረሪ ነዉ የማሳልፈዉ...በዚህ ፊልድ ጥሩ ዉጤት ለማምጣት ቸክየ እየተማርኩ ነዉ

ወንድም ሴትም እኔ ጋር ጓደኛ መሆን ይፈልጋሉ ለምን በትምህርቴም ጎበዝ ስለሆንኩ ብዙ ሰዉ ጓደኛ እንሁን ይሉኛል ..ግን እኔ 10ክፍል ላይ መጥፎ ጓደኞች ሒወቴን ስላበላሹት ..አሁን ያሉት የሴትም የወንድም ጓደኞች እኔ በራሴ መፈተኛ ስፈተናቸዉ አይመጥኑኝም፡፡ ሴቶቹ ወሬያቸዉ አመለካከታቸዉ..ለትምህርት ያላቸዉ አመለካከት እንደ ጊዜ ማሳለፊያ ስለያዙት እነዚህ የክላስ ልጆች ጋር አብሮ ጓደኛ መሆን ልቤ አልፈቀደልኝም፡፡ትምህርቴ ላይ ጎበዝ ሆንኩኝ ስለማጠና የሚያስተሞሩን መምህሩ ጋር በጣም ተግባባን ፡፡


             አንድ ቀን እኛ ክላስ አንዲት ጅልባብ የምለብስ ልጅ ስሟ መፍቱሀ ትባላለች ደግሞ አንዲት ክርስቲያን ልጅ አለችኝ ስሟም ብሩክታይት ትባላለች ሁለቱ አንድ ላይ መጥተዉ ከአንቺ መተዋወቅ እንፈልጋለን ብለዉ እጃቸዉን ዘረጉ....

ብሩክቲን አንግባባም እንጂ አቃታለሁኝ የእኔ እናት እና የእሷ እናት ጓደኛ ናቸዉ፡፡ ክላስ ዉስጥ ሁለታችን እንፎካከራለን ....መፍቱሀ ግን ሰነፍም ጎበዝም አትባልም መካከለኛ ናት ፡፡
......እኔም እሺ እልኩኝ
..... መፍቱሀም:- ሁሌም አንቺ ጋር መተዋወቅ እንፈልጋለን ዛሬ ደፍረን ለመተዋወቅ እኛዉ መጣን በጣም አድናቂሽ ነን ለትምህርትሽ ያለሽ ትኩረት በጣም አስደሳች ነዉ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አንቺም ለአላህ ብለሽ ዉደጅኝ አለችኝ መፍቱሀ
......እኔም 10Q ችግር የለም ከአሁን ቡሀላ ጓደኞች እንሆናለን አልኳቸዉ
.....መፍቱሀም ስልክ ቁጥር እንለዋወጥ አንዳንዴ እንደዋወላለን አለችኝ....
ስልክ ቁጥሬን ሰጠሆት የሷንም Save አረኩት..አብሬም ለብሩክቲ ስልኬን ሰጠሆት
     ስልኬን ልስጣቸዉ እንጂ ብዙም ትኩረት አላረኩም ለምን እስከ 10 በምማርበት ጊዜ ለኔ ሒወት መንገድ መሳት መጥፎ የሙስሊምም የክርስቲያንም ጓደኞች ነበሩኝ እነ መፍቱሀም ከዚህ ዉጭ ምንም አስቤ አላቅም

መፍቱሀ በቀን ሁለቴ ሶስቴ ትደዉልልኛለች የምናወራዉ ስለትምህርት በተጨማሪም ስለ ቂርአት እሷ የተለያዩ ኪታቦች እንደቀራች እና እኔም ቂርአት እንድቀራ ትመክረኛለች....,መፍቱሀ ሁሌም አብሽሪ ኪታብ መቅራት እኮ ቀላል ነዉ እኔ ስቀራ ብዙ አመት አልፈጀብኝም እያለች ...እየቀለደች እየሳቀች ሒወቷን ታጫዉተኛለች

አንድ ቀን መፍቱሀ ወደ አሱር አካባቢ ደወለችልኝና ነዋል ዛሬ ይዤሽ የምሄድበት ቦታ አለኝ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ አልኳት
....አሱርን ሰግደን ተገናኘን .... የት ነዉ የምንሄደዉ ብየ ሳልጠይቅ ወደ ምትሄድበት አብሬ ሄድኩኝ
....ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ሂደን የታመሙ ሰዎችን ዘይረን፡፡ ከሆስፒታል ስንመለስ በሌላ አካባቢ ወስዳኝ  አቅማቸዉ የደከሙ ትላልቅ ሰዎች በስራ አግዘን እና ትንሽ ብር ሰጥተን እነሱም መርቀዉን ተመለስን፡፡ መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ ዛሬ የምንሄድበት አለ እያለች ኸይር መስራት የቲሞችንን ጧሪ ቀባሪ የሌላቸዉን አዛዉንት የሆኑትን መዘየር ሁኗል ስራችን ...

የእኔ ቤተሰቦች ሀብታም ስለሆን ድህነትን አላቀዉም የተቸገሩ መኖራቸዉን ድህነት እንዴት ሰዉ እንደሚጎዳ ዘያራ በምንሄድበት ጊዜ አስተዋልኩኝ ...እኔም ልብስ ግዢ ጫማ ግዢ ተብሎ ከሚሰጠኝ ብር ላይ ለተቸገረ መስጠቱ ለኔ ደስታ ሆነኝ፡፡

መፍቱሀ የሴቶች ጀመአ አሚር ናት  በወር በወር በመዋጮ የተቸገሩትን መርጠዉ ቋሚ የብር ወይም የአስቤዛ እርዳታ ይሰጣሉ .....እስኪ ሂደን አይተናቸዉ እንምጣ ትለኛለች...አብረን ሂደን ዘይረን እነሱ ጋር ተጫዉተን ብርም ከያዝኩኝ ለአንዳንድ ነገር ይሁናችሁ እያልኩ ብር ሰጥቼ እመጣለሁ.....

እኔም መፍቱሀ ጋር በዚህ የተቸገሩትን ዘያራ በምናደርግ ሰአት እራሴን እንድፈትሽ ከኔ የባሱ ብዙ መኖራቸዉን አስተዋልኩኝ..አልሀምዱሊላህ አልኩኝ..ከኔ ጀምሬ የበታችንን ብናይ አመስግነን ባልጠገብን ነበር ግን ምነ ይደረጋል የሰዉ ልጅ ዘንጊ ነዉ እንጂ በየእለት ተግባራችን ሰንት የማንሰማዉ የማናየዉ የለም ግን ስናመሰግን አይስተዋልም፡፡
ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን በምንመለከታቸዉ የለያዪ ትዕይንቶች ልባችን ተነክቶ የአላህን ዉለታ አስታዉሰን የምናመሰግነዉ??? ወይም የምስጋና ሱጁድ የምናደርገዉ? ጥያቄዉ ለሁላችንም ይቆይ ራሳችን መልሰን እኛዉ እንረመዉ....


መፍቱሀ ለኔ ኸይር እንስራ  እያለች የምታበረታታኝ ነች፡፡ አንዳንዴም ብሩክቲም አብራን ትመጣለች...ብሩክቲ ክርስቲያን ትሁን እንጂ አለባበሷ አስተሳሰባ እንደሙስሊሞች ነዉ፡፡ ክሪም ለብሰን ፀጉራችን ከታየ ሸፍኑ ፀጉራችሁ እየታየ ነዉ ትለናለች... የቱርክ የዱባይ ጠባብ ልብስ ለብሰን ስንሄድ ይሄ እኮ ሰዉነት ያሳያል ሒጃብ ልበሱ የምትል ...,አንዳንዴ የሶላት ሰአት ደርሶ እሺ እንሰግዳለን እያልን ወሬ ስናወራ መጀመሪያ ስገዱ እያለች ትገስፀናለች፡፡ ይገርማል የብሩክታያት ቅርብ ጓደኛዋ መፍቱሀ ብቻ ናት .ብሩክቲን የኢስላምን አደብ አስተምራታለች ፡፡
 
መፍቱሀም እኔን እኛ ጀመአ መግባት አለብሽ የምንገናኛዉ በሳምንት አንዴ ነዉ እያለች ብዙ ጊዜ ነገረችኝ..
...,,እኔ ሰዉ ጋር መቀላቀሉ ሌላ ጓደኛ መፍራቱን አልፈለኩም ግን መፍቱሀ ግድ እኛ ጀመአ ገብተሽ የዲን እህቶሽን ተዋዉቀሽ ኪታብ መጀመር አለብሽ እያለች ሁሌ ስለምትናገረኝ.....እሺ ቅዳሜ እንሄዳለን አልኳት
.......ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....



በፊት አስረኛ ክፍል ስማር በመጥፎ ጓደኞች ተተብትቦ አላማየን እንዳልሳትኩኝ ዛሬ ኮሌጅ ላይ ደግሞ እንደ መፍቱሀ እና ብሩክቲ አይነት ምርጥ እህቶች እና ጓደኛ ሰጥቶኝ ...ትክክለኛ መስመር የያዝኩ ሁኛለሁ ኢስቲቃማዉን ይስጥሽ በሉኝ....

#ክፍል 1⃣3⃣
ይ......ቀ.......
......ጥ......ላ........ል


JOIN
´ www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አስራ ሶስት 1⃣3⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....

ዓሊይ መስጊድ ደረስን የሴቱ ጀመአ በጣም ብዙ ናቸዉ
.....መፍቱሀም አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ዉድ የኢስላም እህቶቼ ዛሬ አንድ እህታችን መጥታለች ስሟም ነዋል ትባላለች ብላ ከሁሉም ጋር በአንዴ አስተዋወቀችኝ፡፡ ደስ የሚሉ ጀመአዎች ነበሩ ሲጀመር እኔም በባህሪየ ሰዉ ጋር መቀራረብ ሰዉ ጋር መላመድ ችግር የለብኝም ..ሁሉም ጋር ብዙም ቀን ሳይፈጅብኝ ተግባባን፡፡


መፍቱሀም፡- ሁሌ ቅዳሜ መቅረት አይቻልም የጀመአዉ አባል ተብለሽ ተመዝግበሻል አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ እመጣለሁ አልኩኝ..
    መፍቱሀ ጋር ወደ ቤት እየተመለስን ግን የወደፊት አላማሽ ምንድን ነዉ ?? ለወንድ ልጅ ያለሽ አመለካከትስ እንዴት ነዉ ?? አለችኝ
.....እኔም ወንድ ልጅን በፍቅር አልቀርብም አላህ ባለቀን boyfrind ሳልይዝ እኔን ከማንነቴ ተቀብሎኝ ቀጥታ ቤተሰብ የሚጠይቅ ነዉ የምፈልገዉ ..እኔ በዘንድሮ ፍቅር አላምንም አልኳት
...መፍቱሀም ማሻ አላህ ወላሂ የኔም ሀሳብ እንደዚሁ ነዉ የኔ ሀላል ባሌ የምፈልገዉ እኔን በቻት በተለያዩ መህበራዊ ሚዲያ ሳይጀነጅነኝ በመስኮት ሳይሆን በበር የሚገባ ለቤተሰቦቼ የሚያሳዉቅ ነዉ የምፈልገዉ አለችኝ ፡፡ሁሌ ተገናኝተን ስለፍቅር ስለትዳር ካወራን አስተሳሰባችን አንድ አይነት ነዉ፡፡

መፍቱሀ ጋር ከምነግራችሁ በላይ በጣም እንዋዳደላለን ከጓደኛ በላይ እንደ እህት ነዉ የማያት ...ጓደኝነታችን በጣም ቅርርብ ስላለን ብቻየን እኔ ከሄድኩ ወይ መፍቱሀ ብቻዋን ከሄደች ምነዉ ጓደኛሽ ዛሬ የለችም ወይ?..ወይ እሷን ነዋል ዛሬ የለችም ወይ ?ብለዉ ይጠይቁናል.. ብዙ ጊዜ በጀመአም በስብሰባም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የሆነ ጥያቄ ሀሳብ ካስፈለገ የእኔና የእሷ ሀሳብ ሁሌም አንድ ነዉ፡፡ እኔ የሆነ ነገር ሳስብ እሷም አስባዉ አገኛታለሁ..የሆነ ኸይር ስራ ለመስራት ሳስብ ላማክራት ስል ወይ እሷ ትቀድመኛለች ወይ ስነግራት እሷም እንደ አሰበችዉ ትነግረኛለች ..እሷም የሆነ ሀሳብ ስታማክረኝ እኔም የአሰብኩት ሀሳብ ሁኖ አገኘዋለሁ....ከአካል አልፎ ልባችን ለራሱ ጓደኝነት ፈጥሯል..ሰዉ ብዙ ጓደኛ አለዉ  ..በጣት የሚቆጠር የልብ ጓደኛ የሚለዉ አለ ነገር ግን ጭራሽ ልብ ለልብ አይገናኙም ጭራሽ የሆድህን ለማስረዳት ጓደኛም ለመረዳት ሳይቻል ይስተዋላል..ይሄ ገና ጓደኝነቱ ብዙ ይቀረዋል ማለት ነዉ፡፡ ለምን ጓደኝነት በሀሳብ ገና ፊትህን አንብቦ የልብህን የሚያቅ ሲሆን ነዉ፡፡ የሚገርማችሁ አመናችሁም አላመናችሁም ያዉ በአላህ ፍቃዴ እኔና መፍቱሀ የወር አበባ ለራሱ የምናይበት ቀን ድረስ የተመሳሰለ ነበር...ብዙ ቀናቶች እኔ ታምሜ ሀኪም ቤት ስሄድ እሷም ትታመም ነበር...አንድ ሀኪም ሙድ ይይዝብን ነበር ዛሬ ጓደኛሽ አልታመመችም ወይ እስከ ማለት ደርሰዉ ነበር..ይሄን ያህል ድረስ ነበር የኔና የመፍቱሀ ልብ ለልብ ጓደኝነታችን


አንድ ቀን መፍቱሀ በስጦታ መሸፈኛ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...የተጠቀለለዉን ስከፍተዉ ኪታብ ነበር ...እኔም ደስ ብሎኝ አብረን ኪታብ መቅራት ጀመርኩኝ ..ለሒወቴ ትልቅ ለዉጥ እያመጣችልኝ ነዉ፡፡

ደግሞ በሌላ ቀን መፍቱሀ በስጦታ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...መፍቱሀ የተጠቀለለ ነገር ከሰጠችኝ ለኔ አስፈላጊ በጣም የሚጠቅም ነገር እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለዉም
....እኔም ምንድን ነዉ ?? አልኳት
.......እሷም የዛሬዉ ስጦታ እቤትሽ ሒደሽ አይተሽዉ ከዛ ትደዉይልኛለሽ አለችኝ
.....እኔም የሰጠችኝን ስጦታ እስከማየዉ እየቸኮልኩኝ እቤቴ ደረስኩኝ
........የስጦታ ወረቀቱን ስፈታዉ ጥቁር ጅልባብ ነዉ፡፡
እኔም ወደ መፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ወድጀዋለሁ አላህ ይስጥልኝ አልኳት
.......እሷም ነዋል ......ልበሽዉ እና በመስታወት አንቺ ጋር እንዴት እንደሚያምር ተመልከቺዉ ከዛም ዛሬ የዙሁርን ሶላት ስገጂበት...ሰግደሽበት በጣም ትወጅዋለሽ እርግጠኛ ነኝ ትሞህርት ቤት ለብሼዉ እመጣለሁ ነዉ የምትይዉ አለችኝ

እኔም መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ በመስታወት ሳየዉ በጣም ነዉ ያማረብኝ ....መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ ዙሁሩን ሰግጄ ጨርሼ ሳሰላምት አባቴ ከሆላየ ቁማል

...አባቴም ዛሬ በሰላም ነዉ እቤት የመጠሀዉ?? አልኩት
አባቴም የምፈልገዉ እቃ ነበር ጠዋት እረስቼዉ አሁን ልወስድ ነዉ .....ነዋል ጅልባቡን መቼ ገዝተሽዉ ነዉ ??? ነዋልየ የኔ ልጅ ወላሂ እንደዚህ አምሮብሽ አይቸሽ አላቅም ወደ ቤት ስገባ ጅልባብ ለብሰሽ ስሰግጂ እንዴት ደስ እንዳለኝ ከምነግርሽ በላይ ነዉ ደስታየን መቆጣጠር አቅቶኝ የደስታ እምባ አነባሁ፡፡ ነዋል አምሮብሻል አታዉልቂዉ አለኝ፡፡
....እኔም ጓደኛየ ስጦታ ሰጥታኝ ነዉ አባቢ አልኩት
.......አባቴም ጥሩ ጓደኛሽ ናት፡፡ ለወደፊትም እሷን ጓደኛ አርገሽ ያዢ ብሎ ከአንጀቱ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ ዱአ አደረገላት...ነዋል ሲመቸኝ ጓደኛሽን ታስተዋዉቂኛለሽ አለኝ አባቴ
...,,,እኔም እሺ አስተዋዉቅሀለሁ አልኩት ...አባቴም የረሳዉን እቃ ይዞ፡ከቤት ወጥቶ ሄደ
  

እኔም አምሮብኛል ማለት ነዉ ??ብየ መልሼ መልኬ እስከሚገፍ መስተዋት ላይ አፈጠጥኩኝ፡፡

ዛሬ  ከሰአት ክላስ አለን ጅልባቡን ለብሼዉ ልሂድ ወይስ አልሄድ ??ጅልባብ ስለብስ የመጀመሪያየ ነዉ ሰዉ ምን ይለኛል ??? እያልኩ ብቻየን እያሰብኩ መልበሱን ፈራሁ

★★★ በዲነል ኢስላም ሀይማኖት ዉስጥ እምነት የሚለዉ ቃል በአረበኛ ትርጉሙ ሲፈታ አንድን ነገር እዉነት ብሎ መቀበል ሲሆን ኢስላማዊ ትርጉሙና ትንታኔ ግን ሰፊ ቢሆንም የኢስላም ሊቃዉንቶች በአጭሩ ሲያስቀምጡት እንዲህ ይላሉ ..አል አሚኑ ማወቀረ ፊል ቀልብ ወሰደቀሁል አመል ..ትርጉሙም፡-እምነት ማለት በልብ ወስጥ ተደላድሎ የተቀመጠ እና ስራ ወይም ተግባር ያረጋገጠዉ ነዉ በማለት ይገልፁታል፡፡ ሌሎች የኢስላም ሙሁራን እምነትን ሲገልፁ በልባችን (በቀልባችን)እዉነት ነዉ ብለን የምንቀበለዉ..በምላሳችን ሙሉ ፍቃደኝነት የምንናገረዉ እና በሰዉነት አካላችን የምንተገብረዉ ነገር ነዉ...በማለት ይገልፁታል ፡፡እኔም ታዳ ጅልባብ መልበስ ሰዉ ምን ይለኛል ብየ ከፈራሁ እምነቴ ላይ ችግር አለ ሀይማኖቴ ከልቤ ሳይገባ ተደላድሎ አልተቀመጠም ማለት ነዉ::

ለኔ ጅልባብ መሸፈኛየ መከበሪያየ ነዉ፡፡
ምን ያህል ስለ ሒጃብ ጥቅሞች እናዉቃለን???

★★★ ሒጃብ ለአላህና ለመልዕክተኛው መታዘዝ እንጂ የሆነ ሀገር ባህል ተከታይነት አይደለም።

⇘ሒጃብ ጥብቅነትና ንፅህና ነው። ሒጃብን የማትለብስና
ከሂጃብ የተራቆተች እንስት ሁለት ነገሩዋ ቆሽሿል ፡፡ አንዱ ንፁህ ቢሆን እንኳን አንዱ ንፁህ አይሆንም አንደኛ ልቧ ቆሽሿል ፡፡ ሁለተኛ ሸይጧን አሳስቷት ሰውነቷን በተለያየ ወንጀል አቆሸዋለች በዝሙትና በተለያየ ነገር ሰውነቷን አጨማልቃው ሊሆን ይመቻል የሚፀዳው ሒጃቧን ለብሳ ክብሩዋን ጠብቃ ጥንቁቅ ሆና ወደ ጌታዋ ቁሩጥ ያለን መመለስ ስትመለስ ብቻ ነው!!!👇👇👇
ልቧ ባይቆሽሽ አትራቆትም ነበር ከሂጃብ መራቆቷ ራሱ የወንጀል መብዛት አንዱ ምልክት ነው ሸይጧን ሴትን ልጅ ወንጀል እንድታበዛና እንድትሰራ ይገፋፋታል ከዛ በኋላ ግን ከሂጃቧ እንድትገፈፍና ክብር እንዳይኖራትና በባለጌዎች እንድትደፈርና እንደ ቀላል እንድትታይ ያደርጋል፡፡ ሒጃቧን በአግባቡ የምትለብስ ሴት ግን ሁሉም ዘንድ ክብር አላት ባለጌዎች ዘንድም ክብር አላት እሷን ቀና ብለው እንኳን አያዩዋትም መልካም ሰዎች ዘንድም ልዩ ክብር አላት።

⇘ሒጃብ ኢማን ነው ኢማን ማለት:– በልብ ማመን በምላስ መናገር በአካል መተግበር ነውና።
አንዳንዶች ካሉበት ሸሪዓን የሚቃረን ተግባር እንዲመለሱ ሲነገራቸው ኢማን በልብ ነው ልቤን ከፍተህ አይተሀል? እያሉ የውሸት ቅንብራቸውን ስያቀናብሩ ይስተዋላሉ። ጥያቄ አለኝ ልባችሁ ካመነበት ተግባራችሁ ሊመሰክር ምን ከለከላችሁ? ለአላህ ግን መዋሸት አይቻልም! ለማነኛውም ኢማን ሶስት ክፍሎች አሉት ከነዛ ውስጥ ምንም ማጉደል አይቻል ታዲያ 3ኛው በአካል መተግበር ነውና ተግብሪ ሒጃብሽን ጠብቂ አንቺ ሒጃብ ብለሽ የምትጠሪው በወገብሽ ልክ አጣብቀሽ የሰዉነት ክፍልሽን የሚያሳይ አድርገሽ ከሴቶች ሱሪ ከሚለብሱት የማይሻል አድርገሽ የምታሰሪዉ ሳይሆን ኢስላም/ሸሪዓ ሒጃብ ብሎ ያስቀመጠልሽን ሒጃብ ነው የምልሽ።

⇘ሒጃብ የህፍረተ–ገላ መደበቂያ ነው። ሴት ልጅ ደግሞ መላ ሰውነቷ ህፍረተ–ገላ ነውና መላ ሰውነቷን ልትሸፍነው ይገባታል!! አንዳንድ (ፈቂህ መስለው ሙተፈቂሆች) ስለ ዲኑ ሳይገነዘቡ የተገነዘቡ የሚመስሉ ሰዎች እና ሴትን ልጅ ልቅ እንድትሆን ከአጂ ነብይ ጋር እንደፈለገች እንድትተራመስ ኢስላምን ታኮ የመጣ ኢስላም መስሎ ኢስላምን የሚያዳክም ሊያጠፋ የመጣ የአህባሽ አስተምሮን ይመስል አይ እጅና ፊት እንኳን ሱና ነው ኪላፍ አለበት ምናምን… የሚሉትን ተረታቸውን ትተሽ አንቺ ለአላህ ብለሽ ተቃራኒ ፆታዎችን ላለ መወስወስ ብለሽ መላ ሰውነትሽን ልትሸፋፈኚ ይገባል።

⇘ሒጃብ የሼመኝነት ምልክት ነው። የሴት ልጅ ተፈጥሮ ሼመኝነት ነውና ተፈጥሮን ጥለሽ ሌላን ለመሆን መሞከር አደጋው የከፋ ነው።
ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሴት ሁና በወንድ የምትመሳሰልና ወንድ ሁኖ በሴት የመመሳሰልን አላህ ረግሟቸዋል ብለዋል። ልብ በይ እህቴ የአላህ እርግማን ነው ያለበት!

⇘ሒጃብ መልካም የሆነች አማኝ ሴት በህሪ ነው። አላህ ይጠብቅሽና እህቴ የዚህ ተቃራኒ መሆንሽ ምንኛ የከፋ ነው? መልሱን ቆም ብለሽ እንድትመልሺው ለአንቺው ተውኩት


       አንድ ኡስታዝ ደአዋ እያደረገ.. የተለያዩ ሀይማኖቶች ስብከታቸዉን እያካሄዱ ሙስሊሙ ተዳክሟል ምን ይሻላል? ተብሎ ተጠይቆ እንዲህ ብሎ መልሷል ፡-እኔ ግን የሚያሳስበኝ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሌሎች ስብከት ሌላን ሀይማኖት ይከተላል የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በስሜት ተከታይነት ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ ብሏል፡፡
⇘አዎን! በትክክል ተጨባጩም የሚያስገነዝበው ይህን ነው
በአሁኑ ሰዓት ስለ ዲኑ ጠንቅቆ የሚያውቀው በጣም አናሳ ነው በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አብዘሀኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ትንሽ ያውቃል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበትም አላህ ያዘነለት ሲቀር የስሜቱ ተከታይ ነው በስሜት ተከታይነት ሀራሙ እንደ ሀላል ተቆጥሮዋል በስሜት ተከታይነት ሱና ቢድዓ ይደረጋል ቢድዓ ደግሞ በተቃራኒው እንደ ሱና ይታያል በስሜት ተከታይነት ሽርክ እንደ ተውሂድ የሚቆጠርበት ቦታም አለ… ሌላም ሌላም
ይህንኑ የሚያበረታቱና ባለ በሌለ ሀይላቸው የሚያስፋፉ የሸይጧን ወዳጆች ደግሞ በዛው ልክ በዝተዋሉ!

ልብ በይ እህቴ!!!!! አንቺ የህብረተሰቡ መሰረት ነሽ አንቺ ከተበላሸሽ ይህ ህብረተሰብ ይበላሻል አንቺ ከተስተካከልሽና ከለማሽ ህበረተሰቡም ይስተካከላል አንቺን ለማጥመምና ከተፈጥሮሽ ለማውጣት ከሂጃብሽ ለማላቀቅ ከአላህና ከመልዕክተኛውﷺ ተከታይነት አስወጥተው የሸይጧንና የስሜትሽ ተከታይ ሆነሽ የጀሀነምን ገደል ገብተሽ ህብረተሰቡንም ወደ ጀሀነም ገደል እንድታስገቢ ሸይጧንና የሸይጧን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት አውቀሽ ለእነሱ አላማ የሚመቻቸውን አካሂድ እርግፍ አድርሽ ትተሽ ወደ አላህ ተመልሰሽ ሒጃብሽን ጠብቀሽ ስለ ዲንሽ ተምረሽ አውቀሽ ተግብረሽ ምርጥ ትውልዶችን የጀነት ሙሹሮችን አፍሪ
ይህቺ አለም እያየሻት ነው አጭርናትና ለዘላለማዊ አለም ጥሩ ስንቅ ሰንቂ።



       እኔም ጅልባቡን ልልበስ አልልበስ እያልኩ ለብቻየ ሳመነታ ዉሳኔየ ሲምታታብኝ ለመፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ለብሼ ልመጣ ነበር የሰዉ አይን ማየት እና ሰዉ ምን ይሉኛል ብየ ፈራሁ ምን ይሻለኛል?? አልኳት
......መፍቱሀም ነዋልየ አንቺ የምፈሪዉ አላህን ከሆነ ጅልባቡን እንደለበሽ ሳታወልቂ ነይ ... አንቺንም እኔንም እነሱንም የፈጠረንን አላህን ብቻ ፍሪ አላህን ካልፈራሽ ማንን ትፈሪያለሽ ??...ግን ሰዉ ከሆነ የምፈሪዉ ቀይረሽዉ ትመጫለሽ ማለት ነዉ..ለሰዉ በጭራሽ እንዳትጨነቂ ....ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........

ነዋል ጅልባቡን ትለብሰዉ ይሆን???

#ክፍል 1⃣4⃣

ይ........ቀ ......
.....ጥ.........ላ........ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አስራ አራት 1⃣4⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........
የመፍቱሀ ንግግር ልቤ ዉስጥ ገባ ..ሰዉ ምን ይለኛል የሚል ፍርሀትን አስወግጄ ወኔ ፈጠረብኝ ....ማንንም አልፈራም ደግሞ ለዘንድሮ ሰዉ ብየ ጅልባቡን እንደለበስኩኝ ከቤቴ ወደ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ መሔድ ጀመርኩኝ....ግን እደሄድኩ የመጀመሪያየ ስለሆነ እየተንቀጠቀጥኩ እየፈራሁኝ ነዉ፡፡ ሰዉ ሁሉ በመንገድ ስሄድ ሲያየኝ ምን ሁና ነዉ የሚለኝ ይመስለኛል.... በጣም ነበር የማያስፈራዉ፡፡ እንደ ምንም ብየ ኮሌጅ ደረስኩኝ...

ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ሁሉም እየተጠቋቆሙ እኔን ነዉ የሚያዩት ...በጣም ነዉ የገረማቸዉ ያልጠበቁት ተአምር ነዉ የሆነባቸዉ፡፡ ከትምህርት ቤታችን ቁጥር አንድ በፋሽን ልብስ ዘናጭ የተባልኩኝ ተማሪ ዛሬ ጅልባብ ለብሼ ከች ስል ሁሉም ገርሞት መልኬ እስከሚገፍ ተመለከቱኝ ግን እኔን ደፍሮ ለመናገር የሞከረ የለም ዝም አሉኝ

  መፍቱሀ ከሩቁ አየችኝ ፊቷ በደስታ የሚያበራ ይመስላል ..ከተቀመጠችበት ቁማ ጠበቀችኝ እሷ ጋር ስደርስ ነዋልየ ወላሂ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ዛሬ ደግሞ በጣም አስደሰትሽኝ ብላ በደስታ እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ....ደስታዋን የምገልፅበት ቃላት አጠራት የደስታ እምባ እያነባች በለበሰችዉ ክሪም እምባዋን ትጠርግና አይን አይኔን ታየኛለች መልሳ እቅፏ ዉስጥ ታስገባኝ እና ትስመኛለች፡፡ ነዋልየ አኮራሽኝ ወላሂ እንዴት እንዳስደሰትሽኝ ...አላህ ሁሌም ያስደስትሽ ነዋልየ ወላሂ እንዴት እንዳማረብሽ ልነግርሽ አልችልም፡፡ ደስታየን አንድ ቀን ብቻ እንዳታደርጊዉ ነገም ለብሰሽ እንድመጪ አንድ ቀን ብቻ ለብሰሽ እንዳታወልቂዉ አለችኝ
......እኔም እሺ መፍቱሀ ኢንሻ አላህ አለብሳለሁ አልኳት፡፡ ክላስ ገብተን ተምረን ወደ ቤታችን ተለያየን፡፡

እድሜ ለሰጠዉ ሰዉ ወደ ሞት እየተጓዝን ቢሆንም ከቀናችን አንድ ቀን ለመቀነስ መንጋቱ አይቀርም..ይሄዉ ዛሬም ነጋ ..እንደትናቱ ጅልባቤን ለብሼ ወደ ኮሌጅ አመራሁኝ ...እዛም እንደ ደረስኩ የትምህርት ቤት ልጆች እንደትናትናዉ ለመናገር አልፈሩም ..የብዙ ሰዉ አስተያየት ተቀበልኩ፡፡ የሚገርማችሁ ክርስቲያን የሆኑ የኛ ክላስ ልጆችና ትምህርት ቤት የምግባባቸዉም የማልግባባቸዉም ነዋል ይሄ አለባብስ አምሮብሻል አታዉልቂዉ .....ትናንት ለብሰሽዉ ስናይሽ ለአንድ ቀን ብቻ የለበሽዉ መስሎን ነበር የሁሌም ልብስሽ ብታደርጊዉ ያምርብሻል አሉኝ፡፡
ብዝዎቹ ክርስቲያን የክላስ ልጆችም ነዋል አንቺ ቀይ ስለሆንሽ በጥቁር ጅልባብ ከሁሉም ሴቶች አንቺ ላይ አምሮብሻል አሉኝ ፡

አስተያየት ከሰጡኝ ሁሉም ክርስቲያኖች 100% እንደአማረብኝ አታዉልቂዉ አምሮብሻል ብለዉ መሰከሩልኝ ፡፡ እዉነታቸዉን ነዉ አልተሳሳቱም መልኬ በጣም ቀይ ነኝ ጥቁር ጅልባቡ ሲጨመርበት ምንም የማይሳነዉ ጀሊሉ አምጥቶ ዉበቱን ደፋብኝ....

ብሩክታይትም ደስ ብሏት ማርያምን አምሮብሻል እንዳታወልቂ አለችኝ፡፡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶቼም ማሻ አላህ አሉኝ በጣም ደስታ ተሰማኝ፡፡

ደግሞ በተዘዋዋሪ ሙስሊም ሁነዉ ፋሽን ተከታይ ሴቶች  ደግሞ ምን ሁነሽ ጅልባብ ለበሽ?? አንቺ ገና ነሽ ወጣት ነሽ እንደ በፊቱ ብዘንጪ ነዉ የሚያምርብሽ እያሉ በለበስኩት ጅልባብ አንቋሸሹብኝ ወላሂል አዚም በጣም ተአጀብኩኝ ሙስሊሞቹ ከሰጡኝ አስተያየት 35% መልበሴን የተቃወሙ ናቸዉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያመለክተዉ ዲነል ኢስላም ላይ ገና አለመሰራቱ እና ሙስሊም ናቸዉ እንጂ ኢስላም ሀይማኖት ምን እንደሆነ ገና የሚቀረን ማህበረሰቦች ነን ያለነዉ ማለት ነዉ...አሁን ላይ በእንደዚህ ያሉ የሀይማኖት ተከታዮች ተተብትቦ ዲነል ኢስላም የምናሰድበዉ ፡፡ ዲነል ኢስላም መመዘን ያለበት በሀይማኖቱ ዉብነት ለሰዉ ልጅ ፍትህ እንደሆነ እንጂ በዲነል ኢስላም አንዳንድ ተከታዮቹ ኢስላም ቢፈተሽ አንድም ሰዉ ወደ ኢስላም ባልገባ ነበር..ግን ምን ይደረጋል ዲነል ኢስላም በአንተም በአንቺም በእሱም በእሷም በእነሱም በእነዛም የሚመዘን አይደለም ሀቅ በያዙ ደጋግ አቢድ ሷሊህ በሆኑ ባርያዎቹ እንጂ፡፡

ክርሰቲያኖች በመንገድ የሚያገኙኝ አድንቀዉኝ ሙስሊሞቹ እንደዚህ ሲያንቋሽሹኝ በእኔ ሳይሆን ሙስሊም ሁነዉ እንደዚህ በማሰባቸዉ አፈርኩባቸዉ፡፡
      የቱርክ የቻይና የዱባይ ፋሽን ተብየ ልብስ መልበስ ትቼ ጅልባብ ብቻ መልበስ
ጀመርኩኝ....,ልብስም ከገዛሁ የምገዛዉ የተለያዩ ጅልባቦች በተለያዩ ከለሮች እና የጅልባብ ማላበሻ ክሪም ብቻ ሆነ፡፡

አንድ ቀን እኔና ብሩክቲ አንድ ላይ ቁመን
አንድ ወንድ ክርስቲያን የክፍላችን ልጅ እኔ እና ብሩክቲን መጥቶ ሰላም አለን.... ወንድ ልጅ ጋር መጨባበጥ ሀራም እንደሆነ አቃለሁኝ ግን እሱን እንዳይደብረዉ ብየ ነበር ሰላም ያልኩት
...... ብሩክቲም እንዴት ወንድ ሰላም ትያለሽ ?? መፍቱሀ የአጂ ነብይን እጅ የጨበጠ ጀሀነም እሳትን እንደጨበጠ ነዉ ስትል ሰምቻታለሁ እንዴት ትጨብጫለሽ ? ደግም ከአሁን ቡሀላ ጅልባብ ለብሰሻል ወንድ ልጅ መጨበጥም አቁሚ አለችኝ ክርስቲያን ጓደኛየ ብሩክቲ
....እኔም እሺ ልክ ነሽ ብሩክቲ አልኳት ፡፡ በጣም አፈርኩኝ ብሩክቲ ክርስቲያን ሁና ስለ ኢስላም አዉቃ እኔ እንዴት እያወኩኝ መተግበር አቃተኝ ?? እንዴት አጂ ነብይ መጨበጥ ሀራም መሆኑን እያወኩ እንዴት ሰላም እላለሁ ?? ከአሁን ቡሀላ ወንድን ልጅ ማንም ይሁን ማንም ሰላም ላልል ለራሴ ቃል ገባሁ

   መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ መርከዝ ገብተሽ ተማሪ አለችኝ...
... እኔም መርሀባ በማለት ጅሬን ሰፈር የሚገኘዉ አባጅፋር መርከዝ ተመዘገብኩኝ ቁርአኔን ሙራጅአ ማድረግ ጀመሬ ብዙም ሳልቆይ ጨረስኩኝ ኪታብ መቅራትም ጀመርኩኝ በኡስሉሰላሳ ጀመርኩኝ በሉገል መራም ሌላ ኪታቦች እዛዉ ቀራሁኝ ....ሰአት እያመቻቸሁ ሌላ ቦታ ሪያደሷሊህን መቅራት ጀመርኩኝ.....እኛ ሰፈር ያለዉ አጂፕ መስጊድ ሰአት እያመቻቸሁ ቁርአን ተፍሲር መቅራት ተያይዠዋለሁ፡፡
የመፍቱሀ ግፊት ለኔ በሒወቴ መስመር የያዝኩበት ኪታብ የቀራሁበት ዲነል ኢስላምን ያወኩበት ነዉ ...መፍቱሀ ለኔ ሁለ ነገሬ ናት
#የትአሉ_ለአላህ_ብለዉ_የተዋደዱ!!!!!"
መፍቱሀን አላህ የሰጠኝ ለሂድያ ስበብ የሆነችኝ የጨለመዉን ሒወቴን መብራት ያበራችልኝ ናት

★★★★ባልደረባክን ጓደኛክን ምረጥ ……
ተወዳጁ ነብያችን ﷺ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ:-
ሰውየው ሀይማኖት በጓደኛው ላይ ነው አንድኛችሁ ባልደረባ አድርጎ ወደያዘው ሰውዬ ይመልከት

>>>አሏህ ይዘንላቸውና ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ:- የኸይር ባልተቤቶች የሆኑትን ሰዎች ጓደኛ አድርገክ በመያዝ ጓጓ ትኩረት አድርግ መልካም ጓደኞች በጠመምክ ጊዜ ይመሩካል፣ በተሳሳትክ ጊዜ ያቀኑካል፣ አሏህን በረሳክ ጊዜ ያስታውሱካል፣ ጃሂል ( መሀይም) በሆንክ ጊዜ ያስተምሩካል።ብለዋል👇👇👇
        መፍቱሀ ዓሊይ መስጂድ የሚገኘዉ የሴቶች ጀመአዉ ላይ አሚር ስለሆነች እኔ በተለለያዩ ነገር እንድሳተፍ አደረገችኝ፡፡በሳምንት ቅዳሜ የኛ የሴቶች ጀመአ ዝግጅት አለን.... እናም እሳተፋለሁ.., ሁሌም መፍቱሀ አንቺ ተሰጥኦ ታለንት አለሽ ትለኛለች፡፡ መፍቱሀ ግጥም ትፅፍ እና እኔ ነኝ የማቀርበዉ....መነባነብ ለራሱ እንደ እኔ የሚሆን የለም .....እናም በመሀል ቀልድም ሲያስፈልግ እኔ ነበርኩ ፈታ የማረጋቸዉ፡፡
በሂደት እኔዉ የተለያዩ ግጥሞች ታሪኮች ፅፌ ለሷ አነብላታለሁ እሷም ይሄ ጀመአ ላይ መቅረብ አለበት እያለች የተለያዩ ኢስላማዊ ይዘት ያላቸዉ ዝግጅቶች አቅራቢ ሆንኩኝ፡፡

ድፍረቴን ተስጦኦየን አይተዉ ዝግጅት ሲኖር የጀመአዉ መድረክ መሪ አስተዋዋቂ እኔዉ ሆንኩኝ፡፡ ፕሮግራም መሪ..ፕሮግራም ያላቸዉ...እናም የሚቀርቡትን ነገሮች ይመጥናል አይመጥንም እያልኩ እኔዉ እገመግማለሁ፡፡
ዝግጅት ሲኖር ሀሳባቸዉን ሁሉም ለኔ ትተዋል፡፡ እኔም በዚህ መድረክ መምራት ማንንም አልፈራም

መፍቱሀን ዛሬም ነገም ለወደፊትም ብሆን ዉለታዉን መመለስ ባልችልም ሁሌም ሳመሰግናት እና በልቤ ዉስጥ አስቀምጫታለሁ
★★★ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል በጎ ነገር ላደረገላችሁ ሰዉ ወረታዉን መልሱ ..ካልቻላችሁ ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን በማለት ዱዐ አርጉለት ብለዋል ፡፡
በሌላ ሀዲሳቸዉ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ሰዉ ላደረገለት በጎ ተግባር ሰዉን ያላመሰገነ አላህንም አያመሰግንም ..ብለዋል፡፡ ሁሌም ቢሆንም ለእኔም ዱአ ሳደርግ ለመፍቱሀም አብሬ ዱአ አደርጋለሁ

ይሄ ጀመአ የሴት ብቻ አይደለም ወንዶችም እራሳቸዉን ችለዉ አላቸዉ የጀመአችን ስም አንድ ነዉ Telegram ..Whatsap..Youtube አድራሻዎች አሉን በጂማ ታዋቂ ነዉ፡፡ ፋዉንዴሽንም አለዉ የቲሞችን የተቸገሩን ጧሪ ቀባሪ የሌሊቸዉን ወረሀዊ መዋጮ አለ በተጨማሪም ከባለሀብቶች በማስተባበር እየሰበሰብን በወር ብዙ ችግረኞችን የቲሞችን እንደጉማለን

   ጅልባብ ለባሽ ከሆንኩ ቡሀላ ከጀመአም ልጆች መስጊድ ከሌላም ቦታ የምንገናኝ ሙስሊም እህቶቼ በጣም ይቀርቡኛል ፡፡ አንድ አባባል አለ አንተ ጥሩ ቦታ ከሆንክ የሚቀርቡህ ጥሩ ነገር ነዉ፡፡ መጥፎ ቦታ ከሆንክ የሚጠጋህ መጥፎ ባለጌ ሰዉ ነዉ...አላህ ከወደደህ ሁሉ ሰዉ ይወደሀል አይደል የተባለዉ ሀቅ ነዉ ፡፡ እኔ ለዲኔ ጠንካራ ሆንኩኝ ለሊት እየተነሳሁ መስገድ ሱና ሶላቶች እና ሱና ፆሞችን መፆም ከጀመርኩ ቆየሁ ፡፡

ግን ሁሌ በመደጋገም ዱአ ማደርገዉ አለ ...አላህ ሆይ ከማንነቴ የሚወደኝ እኔን የሚረዳኝ የትዳር አጋር ስጠኝ እያልኩ ዱአ አደርጋለሁ

በጀመአ ዝግጅት መድረክ መሪ በሆንከበት ጊዜ ብዙ ሰዉ አይን ዉስጥ መግባት እና ለኔ ጥሩ ጥሩ ሲለሚወራ ለሰሚ ጆሮ አገኘሁ፡፡ እኔ ዝግጅት መሪ ስሆን አዳራሽ ተከራይተን ዝግጅት ስናዘጋጅ ወንዶች በመጋረጃ ተከልለዉ ይታደማሉ ፡፡ እኔ መድረክ መሪ በመሆኔ ከተለያዩ ወንዶች አድናቆት እየጎረፈ ነዉ..........፡


#ክፍል 1⃣5⃣

ይ.........ቀ.............
.......ጥ...........ላ.................ል

JOIN
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/25 12:31:18
Back to Top
HTML Embed Code: