Telegram Web Link
  ከአንደኛ ክፍል ጀምሬ አንዲት ጓደኛ ያዝኩኝ ልጅቱም ፌሩዛ ትባላለች ...ፌሩዛ በትምህርቷ ጎበዝ ነች እኔም እንደ እሷ ጎበዝ መሆን የኔም የአባቴም ምኞት ነዉ  ጓደኛየ ማድረግ ወሰንኩ ፡፡ ክፍላችን ዉስጥ ተሰሚነት ነበረኝ እኔ ከክላስ ልጅ አንድ ልጅ ጋር ከተጣላሁ የተጣላሇትን እሷን እንዳታወሩ ካልኩኝ የሚያወራት የለም ፡፡ እኔ የወደድኩትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ....እኔ የምጫወትዉን ይጫወታሉ እኔ የማይመቸኝን ጨዋታ አይጫወቱም ፡፡

   ቁርአን ደግሞ መቅራት የጀመርኩት KG ተማሪ በነበርኩበት ሰአት ሲሆን ቁርአን የገባሁትም ጅማ ኑር (አጅፕ)መስጊድ ያለዉ ቁርአን ቤት ነዉ ..ገና አፌ መናገር ሲጀምር አባቴ ቁርአን እንድቀራ በቁርአን ጎበዝ እንድሆን ይመክረኝ ያበረታታኛል..ግን ምን ዋጋ አለዉ በአንድ ሰዉ ጥረት አይሆን..ቁርአን እንድቀራ እናቴ ትኩረት ስላልሰጠችኝ መድረሳ ቁርአን ለመቅራት እመላለሳለሁ እንጂ አሊፍ ባታ ሳ ጂም ብሎ ሁሉንም ፊደል ለመለየት  ሶስት አመታት ፈጅቶብኛል፡፡
   
    ቀን ማታ መሽቶ ነግቶ ሁሌ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር የሰፈር ልጆች ልጫወት እነሱ ጋር ስሔድ አንቺ ጋር አንጨዋትም እያሉ እኔን ለብቻየ የሚያገሉኝ ነገር ሚስጥሩን ምክንያቱን ላዉቀዉ አልቻልኩም  ..እንደ ልጅነቴ የሰፈር ልጆች ጋር የመጫወት እድል ላገኝ አልቻልኩም....እኔ ከእነሱ ጋር የማልጫወትበት ምክንያት ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እራሴን ብጠይቅ መልስ ሊመጣልኝ አልቻለም..

    አባቴንም ሁሌ ቀን በቀን እኔ ጋር አልጫወትም አሉኝ እያልኩ እነግረዋለሁ የአባቴ መልስ ግን ምንም ሊቀየር አልቻለም ...
....ተያቸዉ ልጆቹ ጋር አትጫወች የምትለዉ መልስ ብቻ ነዉ የሚመልስልኝ...ተለዋጭ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም
   

    አንድ ቀን የሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ሲጫወቱ የሚጫወቱት ጨዋታ በጣም ደስ አለኝና ...እኔም  በግድም ቢሆን ሂጄባቸዉ የሰፈር ልጆች ጋር ጨዋታ ጀመርን ....ልጅነት መቼም ጨዋታዉ ፈረሰ ዶቦዉ ተቆረሰ ከተባለ መጣላታችን አይቀርም አይደል...አንዲት የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላን ...ከዛም ከልጅቱ ጋር ሲያገላግሉን መሰዳደብ ጀመርን ....
........ተጣልተን ስንሰዳደብ እኔ የልጅነት አንቺ ማስጠሌ አይጥ እያልኩ ስሳደብ እሷ ግን የሰፈር ሰዉ በተሰበሰበት መሀል ከአእምሮ የማይዋጥ የሚዘገንን በልጅ አቅሜ መሸከም የማልችለዉ ስድብ ሰደበችኝ
....እኔም ይሄን ስድብ እንደሰደበችኝ ደነገጥኩ ... እሷ ጋር ስድብ መመላለስ አፍ መካፈቴን አቁሜ ስድቡን እያብሰለሰልኩ እየተገረምኩ እንዴት እንዲህ ብላ ትሰድበኛለች???እያልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ..

እቤት ስገባ የአላህ ነገር አባቴ ቁጭ ብሎ አገኘሁት...
ፊቴ መቀያየሬ መናደዴን ያየዉ አባቴ ምን ሁነሽ ነዉ ልጄ ፊትሽ ተቀያይሯል ሰዉ ጋር ተጣልተሻል እንዴ???? አለኝ
......እኔም አባቴ የጎረቤታችን ልጅ""" ........."""ብላ ሰደበችኝ እኮ አልኩት ..
.......ወዳዉ አባቴ ፊቱ ተቀያየረ ተናደደ እና ቁጭ ካለበት በመነሳት መኝታ ክፍል ገብቶ ሽጉጡን ከአስቀመጠበት አንስቶ ወዳዉ አቀባብሎ ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ የሰደበችኝን ህፃኒቱን የኔኑ እኩያ በሽጉጥ ሊገላት ይፈልጋት ጀመር፡፡ 


አባቴ በጣም ተናዷል ጅማቱ ዉጥርጥር ብሏል....ልጅቱ መኖሪያ ቤት ሂዶ ነይ ዉጪ የት ነሽ ዛሬ እገልሻለሁ እያለ እየፈለጋት ነዉ...

ሰፈሩ በአንድ እግሩ ቆመ ..የኛ ጎረቤቶች በኛ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ዘመድ አዝማዶች ተሰብስበዉ ንዴት አብርድ እያሉ እየለመኑት ነዉ ...

አባቴን ተረጋጋ እባክህ ተብሎ በጓደኞቹ በዘመድ አዝማዶች በስንት ጉድ ተለምኖ ተመልሶ እቤቱ ገባ፡፡ ግን አባቴ ልጅቱን አለቃትም ሌላም ቀን ቢሆን በዚህ ሽጉጥ አናቷን ብየ ነዉ የምገላት እያለ ይደነፋል............

  ማታ ተኝቼ ብቻየን ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩኝ አብረን የምንጫወት የሰፈራችን ልጅ እንዴት ልሰድበኝ ቻለች ???ይሄን ለጆሮ ለመስማት የሚዘገንን ስድብ እንዴት ሰደበችኝ ???አባቴስ ስነግረዉ ለምን እገላታለሁ ብሎ ደነፋ ???? እያልኩ ብቻየን ሳስብ አደርኩኝ....ግን ይሄን ስድብ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ማጣራት አለብኝ ብየ ወሰንኩ ...ግን ማንን ልጠይቅ ???
   
የምጠይቀዉ ሳጣ ሲጨንቀኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን የቤት ሰራተኛችንን አልጠይቃትም???ብየ አሰብኩኝ...እሷን ለመጠየቅ ወሰንኩ

የቤት ሰራተኛችንን ልጅቱ ለምን"""""""____"""""እንደዚህ ብላ እንደሰደበችኝ ጠየኳት ...ሰራተኛችን ለመንገር ፍቃደኛ አልሆነችም ... ግን እኔ ንገሪኝ እያልኩ አፋጥጬ ስይዛት የቤትሰራተኛችን እያለቀሰች ....,እንደዚህ አለችኝ.........


ልጅቱ የሰደበቻት ምን ብላ ነዉ ????  የተደበቀዉ ...ማንነት ምንድን ነዉ ???ለምን አባትየዉ ገና ነፍስ ያላወቀችን ልጅ አገላለሁ ብሎ ለምን ተነሳ ??? የተቆለፈዉ ሚስጥር ምንድን ነዉ ???
በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን


#ክፍል 2⃣
ይ....ቀ...ጥ.....ላ....ል

www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሁለት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



 የቤት ሰራተኛችን እያለቀሰች እንዲህ አለችኝ፡- ነዋል አሁን ለአንቺ መንገር አልችልም ገና ልጅ ነሽ ....የወር አበባ ማየት ስጀምሪ  የዛን ጊዜ እነግርሻለሁ እንድነግሪሽ አታጨናንቂኝ አለችኝ እያለቀሰች ፡፡
...እኔም መንገር ካልፈለክሽ አላስገድድሽም አትጨናነቂ አልኳት ፡፡

እሷን ማጨናነቅ አልፈለኩም.. በቤት ሰራተኛችንም አልፈረድም ለምን እኔ እና አባቴ በጣም እንቀራረባለን ይሄ ሚስጥር እሷ እንደነገረችኝ ከአወቀ አባቴ ጋር እንደሚጣሉ አቃለሁ .......
  
የሚገርማችሁ እኔ ሳድግ እቤት ጥሩ ኑሮ ብንኖርም ብር ብቻ ለሰዉ ልጅ ደስታን አይፈጥርም እናት እና አባቴ ሁሌ እንደተጣሉ እንደተጨቃጨቁ ነበር... በሰላም ሳይጣሉ ያደሩበትን ቀን መቁጠር ይቀላል፡፡ እኔ ታዳ ማታ ማታ በተጣሉ ቁጥር እኔ መጨነቅ መጠበብ ነዉ ስራየ..

    ሁሌ ታዳ እናቴ አባቴን በነገር ስትወጋዉ ከሳሎን ተነስቶ ሌላ ክላስ ገብቶ ብቻዉን ቁጭ ይላል.....እኔም ለአባቴ እራቱን ይዤ ያለበት ክላስ እሄዳለሁ ... አባቴም ፀጉሬን እያሻሸ እንዲህ ይለኛል  .....ነዋልየ የአይኔ ማረፊያ እናትሽ ጋር ብዙ ቀን ለመፋታት አስባለሁ ግን አንቺ ትዝ ትይኛለሽ እኔና እሷ ተፋተን አንቺ ስትሰቃይ አባቴን ወይ እናቴ ናፈቁኝ እያልሽ ስትሰቃይ በአይኔ እየታየኝ እንደገና እተወዋለሁ....እኛ ስንጣላ አትጨናነቂ መኝታ ክላስ ግቢ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ ነዋል ይለኛል፡፡

_እናቴ ደግሞ እንዲህ ትለኛለች.......በሂወቴ አንቺን ካረገዝኩ ጊዜ ጀምሮ አሁን ድረስ የተረገመ ሒወት ዉስጥ ነዉ የገባሁት ምነዉ ተወልደሽ ባልነበር ትለኛለች እየተናደደች ...
.......እናቴ ከምነግራችሁ በላይ በጣም ሀይለኛ ቁጡ ዉሀ ለምን ቀጠነ ብላ የምትጨቃጨቅ ...ለሰዉ በቀላሉ የማትመለስ ናት ፡፡ እኔን ለራሱ ስትናገረኝ ሁሌም ቢሆን ለኔ ክብር የላትም ቃላቶችን መጥና ከአፏ መወርወር አትችልም ... በተዘዋዋሪ ደግሞ አባቴ አስተዋይ እረጋ ያለ ነገሮችን በትግስት የሚያልፍ ለቤተሰቡ ክብር ያለዉ እና በተናደደ ሰአት ደግሞ ፊቱ ለመቅረብ የሚፈራ ቁጡ ሀይለኛ ነዉ ግን ለነገሮች ሁሉ አይቸኩልም ፡፡ አባቴ ትዳሩ እንዳይበተን ተረጋግቶ ይዞት ነዉ እንጂ እንደ እናቴ ሀይለኝነት ትዳሩ ፈራሽ ነዉ ፡፡

ትዳር ማለት የአንዱን ጎዶሎ አንዱ ይሞላል ማለት ይህ ነዉ፡፡ አባቴ የእናቴን ጎዶሎ እየሞላ ትዳራቸዉ እንዲቀጥል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
እናቴ ይሄን የነብዩ ሀዲስ የረሳችዉ ይመስለኛል
★★★ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፡-በሚስት ላይ ያለባት ከባዱ ሀቅ የባሏ ሀቅ ነዉ..በወንድ ላይ ደግሞ ያለበት ከባዱ ሀቅ የእናትና አባቱ ሀቅ ነዉ..በማለት የባል ሀቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል..

ነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሌላ ዘገባቸዉ ማንኛዉም ሴት ባሏ እርሷን እየወደዳት በርሷ ላይ ተደስቶ ከሞተች ጀነት ትገባለች...ብለዋል፡፡ እናትሽ ፀባዯን አላህ ያስተካክልልኝ ብላችሁ እስኪ ዱአ አድርጉልኝ

  
    በትርፍ ሰአቱ ቁርአን ቤት እየሄድኩ ስቀራ  ኡስማን ከሚባል ልጅ በፍቅር ወደኩኝ........በፍቅር ስል የሌላ እንዳታደርጉት በልጅነት ስናድግ በጣም የምንቀራረብ ልጆች ነን፡፡ አንድ ቁርአን ቤትና ትምህርት ቤት ነን
  የኡስማን አባት እና እናት የመንግስት ሰራተኛ ናቸዉ .......ኡስማን አንድ እህት አለችዉ ... ቁርአን የሚያቀራን ሸህ ስለሚገርፉን መድረሳ እንገናኝና የኡስማን ቤተሰቦች እቤት ካሉ ቁርአን እንቀራለን ግን እቤት ከሌሉ ዛሬ የሉም ስራ ናቸዉ ከተባለ ቁርአናችንን መቅራት ትተን አሱር አዛን እስከሚል ድረስ እነ ኡስማን ቤት ሂደን ስንጫወት ስንደባደብ እንዉላለን ....አሱር አዛን ሲል እኔ ወደ ቤቴ ተመልሼ ቁርአን የቀራሁ መስየ እሄዳለሁ፡፡

ኡስማን ጋር ያዉ የልጅነት ነገር መጫወት መደባደብ እንጂ ሌላ ነገር የለም ግን የእቃቃ ባል ይባል የለ ....ኡስማን ጋር በልጅነታችን በጣምምም እንዋደዳለን፡፡
  
አባቴ ከትምህርት መልስ ቁርአን ቤት እንድቀራ የፈለገዉ የሰፈር ልጆች ጋር እንድቀራረብ ስለማይፈልግ ነዉ....ከሰፈር ልጅ ጋር አብሬ አላደኩም የወንድም የሴትም የሰፈር ልጅ ጓደኛ የለኝም፡፡ ለምን ያቺ ልጅ ከሰደበችኝ ቡሀላ ከሰፈር ልጆች ጋር እኔም መጫወት እየከበደኝ መጣ .....

አንዳንዴ ብቸኝነት ሊዉጠኝ ሲደርስ ልጆቹ ጋር ልጫወት ስቀርባቸዉ የሚጫወቱትን ጨዋታ ትተዉ ይነሱና እኔን ብቻየን ጥለዉኝ ይሄዳሉ
.....እኔም ስማቸዉን እየጠራሁ ለምን ትሄዳላችሁ??አብረን እንጫወት እንጂ ??? ስላቸዉ
..........እነሱም ቤተሰቦቻችን አንቺ ጋር እንዳንጫወት ከልክለዉናል አንቺ ጋር አንጫወትም እያሉኝ ጥለዉኝ ይሄዳሉ..........እኔ ለመጫወት ወደ ልጆቹ ሲሄድ እነሱም ይሸሹኛል ወይ ክፉ እድል.......
 
   ከአሱር ቡሀላ ከቁርአን ቤት ስመለስ እቤት እየመጣ ትምህርት የሚያስጠናኝ አንድ ልጅ አለ........ከዛ ዉጭ ግቢ ዉስጥ ታናሽ ወንድሜ እና እህቴ ጋር እየተጫወኩ ነዉ ጊዜየን የማሳልፈዉ፡፡


ጊዜዉ በቀልዱም በምሩም ቁሞ አይጠብቅም   ቁርአን ቤት ሄድኩኝ እያልኩ ስጫወት መዋል ከጀመርኩ ሶስት አመት ሆነኝ ፡፡ ኡስማን እና እህቱ ጋር ከሁለተኛ ክፍል ጀምረን ነበር ቁርአን ቀራሁ እያልኩ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድኩ የምጫወተዉ
 
ጉድ እና ጅራት ከስተቡሀላ ነዉ አይደል የሚባለዉ መቼም ይሄ ጉድ ተደብቆ አልቀረም....አንድ ቀን አባቴ ቁርአን ቤት መጥቶ ሸህየዉን ስለእኔ ሲጠይቃቸዉ ብዙ ቀን እንደማልመጣ እና እነ ኡስማን ቤት ስጫወት እንደምዉል መረጃዉ ደረሰዉ
  
እቤት ስገባ------- አባቴ ተቆጥቶ ፊቱ የእሳት ፉም መስሎ ጠበቀኝ.........
   
.... ነዋል ነይ ቁጭ በይ አለኝ በንዴት
......እኔም እሺ ብየ ቁጭ አልኩኝ.
...... ለስንት ደረጃ ትደርሻለሽ እያልኩ አንቺ ቁርአን ቤት ነኝ እያልሽ ሶስት አመት ስቀልጂ መቆየትሽን ዛሬ ቁርአን የሚያቀራሽ ኡስታዝ ነገረኝ....እንዴት እንደዚህ ትሰሪያለሽ ??? አለኝ
....እኔም ደንግጬ አፌ ተያያዘ የምመልሰዉ ጠፋኝ

አባቴም የመኖሪያ ቤታችንን በር ቆልፎ ለመጀመሪያ ጊዜ ገረፈኝ ....ከቀበቶ አልፎም እጄን አስሮ በርበሬ አጠነኝ

...አባቴ ከተናደደ ተናደደ ነዉ ብጮህ ብጮህ የሚገላግለሉኝ ሰዎች ወደ ቤት መግባት አልቻሉም.. አባቴ ገርፎ በርበሬ ከአጠነኝ ቡሀላ በሩን ከፈተዉ እና ጥሎኝ ሄደ
    
እናቴ ጎረቤት እና የቤት ሰራተኛችን ተሰብስበዉ ቢያባብሉኝ ቢያባብሉኝ እምባየ ሊቋረጥ አልቻለም

.........ከዚህ ቀን ቡሀላ አድቤ ቁርአን ቤት እየሄድኩ መቅራቴን ቀጠልኩ ... ከነኡስማን እና እህቱ ጋር ለጊዜዉም ቢሆን ጓደኝነታችንን ሰረዝን...


አባቴ እኔን ወደ ሶሰት ቀን የሚሆን አኮረፈኝ ...እኔም መልሼ አይኑን ማየት ፈራሁ ፡ አባቴ ሲመጣ ተጠምጥሜ እንደማልስመዉ ..አሁን ግን የእሱ መምጫ ሰአት ሲደርስ አይኑን ማየት እየፈራሁ መኝታ ክፍሌ እገባለሁ፡፡
  
ከሶሰት ቀን ቡሀላ አባቴ ነዋል ነይ ዛሬ ይዠሽ የምሄድበት ቦታ አለ አለኝ
...እኔም እሺ ብየ  አባቴ ጋር መኪናዉን እየነዳ ከጅማ በ45Km በቅርብ እርቀት የምትገኘዉ ወደ አጋሮ ከተማ አባቦቃ መናፈሻ ወስዶ ሲያዝናናኝ ሲያስደስተኝ ዋለ👇👇
አባቴም ነዋልየ አትከፊብኝ እኔ እኮ ተናድጄ ነዉ የገረፍኩሽ በቁርአንሽ ጎበዝ እንድትሆኝልኝ ነዉ ሁሌም ምኜቱ ፡ብዙ ጊዜ ነግሬሻለሁ ለአንቺ ብየ ነዉ ከእናትሽ ጋር የምኖረዉ ደልቶኝ ተመችቶኝ ሳይሆን አንቺን ብየ እንደሆነ ..ነዋል መቼም ቢሆን አንቺን አልጠላሽም.... ከገረፍኩሽ ቡሀላ የዛኑ ቀን ተፀፅቻለሁ ማታ ወደ ቤት ስገባ እኔን ፍርቻ ብቻሸን መኝታ ክፍልሽ ስትገቢ ምነዉ ባልገረፍኳት እያልኩ እየፀፀተኝ ነዉ አለኝ
.......እኔም አባቴ አንተ ልክ ነህ ጠፋቱ የኔ ነዉ ይቅርታ አድርግልኝ......ከአሁን ቡሀላ ጨዋታ አያታልለኝም መጥፎ ጓደኞችንም አልይዝም የዛሬን ይቅር በለኝ አልኩት አንገቴን አቀርቅሬ
....አባቴም አረ ዛሬ እዚህ ላዝናናሽ የመጣሁት አንቺ ተሸማቀሽ አንገትሽን እንድትደፊ ሳይሆን እኔ የገረፍኩሽን ይቅርታ ልልሽ ነዉ አለኝ፡፡ ከዛም ሁለታችንም ታረቅን አንዴ ሳቅ በሳቅ ደስታ ሆነ ..ከዛም ወደ ጅማ ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ተመለስን

  አምስተኛ ክፍል ተምረን ጨረስን እኔ በምማርበት ጊዜ ክረምት ላይ የረመዷን ፆም ያዝን ....እኛ ሰፈር የሚገኘዉ ኑር(አጅፕ) መስጂድ ተራዊህን ለመስገድ አንዲት የሰፈራችን ልጅ ጋር ተራዊህ አብረን ሂደን አብረን ወደ ቤት እንመለሳለን ፡፡

ረመዷን አጋምሰናል ኑር(አጅፕ) መስጂድ ኢሻን ልንሰግድ ተቀምጠን .....ልጅቶ እንደዚህ አለችኝ
.......ነዋል የሆነ ነገር ልንገርሽ አዳምጪኝ ?? አለችኝ
....እኔም ..ምንድን ነዉ??ንገሪኝ አልኳት እናቴ እኮ """ #ነዋል " ..........."ብላኛለች.. አለችኝ ...

ይሄንን ስትነግረኝ ፍዝዝ ድንዝዝ ብየ ቀረሁ መሬት የዋጠኝ ነዉ የመሰለኝ ላቤ በግንባሬ ችፍ ችፍ ሲል ይታወቀኛል......እራሴን መቋቋም አቃተኝ ..ጭንቅላቴ ፍልፍል ቋጥኝ ዲንጋይ ይመስል በጣም ከበደኝ...
መስጊድ እስከ መሆኔ ዘንግቸዋለሁ...

   ያቺ ልጅ በልጅነቴ የሰደበችኝ አባቴ በሽጉጥ እገላለሁ ያለዉ ሚስጥር ሙሉ በሙሉ እየተገለጠልኝ መጣ.....


  የተደበቀዉ ሚስጠር ምን ይሆን???

#ክፍል 3⃣
ይ......ቀ........
.....ጥ.......ላ..........ል



·¨: ❀ share
           `·.     www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
  •════•••🍃🌺🍃•••════•
  
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሶስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


     ያቺ ልጅ በልጅነቴ የሰደበችኝ አባቴ በሽጉጥ እገላለሁ ያለዉ ሚስጥር ሙሉ በሙሉ እየተገለጠልኝ መጣ.....
.....ኢሻ ሶላት እስከሚደርስ ደአዋ እየተደረገ ሶላቱን እየተጠባበቅን በነበርንበት ሰአት እምባየ እንደ ወራጅ ወንዝ ይወርድ ጀመር.... በአንዴ የለበስኩትን ሒጃብ በእምባ አራስኩት ....ግን የነገረችኝ እዉነት ነዉ እንዴ?እያልኩ በእድሌ ማዘን ጀመርኩ....

ልጅቱንም ከአሁን ቡሀላ አንቺ ጋር ወደ መስጊድ መሄድም መምጣትም ጓደኛም መሆን አልፈልግም ብየ ከመስጊዱ ዉጭ በመዉጣት እምባየን ጠርጌ ፊቴን ታጥቤ መልሼ መስጊድ ገብቼ ኢሻንም ተራዊህን ሰግጄ እቤቴ ብቻየን ተመለስኩኝ...........
    
በመነገታዉ ወደ መስጊድ ብቻየን ስሄድ የእሷ ቅርብ ጓደኞች መስጊድ መግቢያ በር ላይ አገኘሆቸዉና ነዋል በምን ተጣልታችሁ ነዉ ?? አብራችሁ መስጊድ እየሄዳችሁ አልነበር እንዴ ?? አንቺም ብቻሽን እሷም ብቻዋን ነዉ የምትሄደዉ ምን ሁናችሁ ነዉ ??ብለዉ ሰብሰብ ብለዉ ጠየቁኝ
......እኔም አይ ለጊዜዉ ተጣልተን ነዉ ቀላል ፀብ ነዉ እንታረቃለን ብየ ማለፉን ፈለኩኝ ለምን የተጣላንበትን ምክንያት መንገር ለኔ በጣም የሚቀፍ እና አሳፋሪ ነዉ ............
   እነሱም ነዋል ለምን ትዋሺናለሽ ?? አንቺ ባነግሪንም እኛ የተጣላችሁበትን ምክንያት አዉቀንዋል ፡፡ የተጣላችሁበትን ምክንያት እሷ የአንቺን የምታቀዉ ሚስጥር እናቷ ስለነገረቻት ስለምታዉቀዉ ነዉ አይደል አንቺ "..................." ስለሆንሽ በዚህ እዉነተኛ ወሬ አፍረሽ አይደል የተጣላሽዉ አሉኝ፡፡
.....እኔም በልጅቱ ነገረኛነት ሚስጥር አለመጠበቅ በማዘን ጥሩ ጓደኛ አለመሆኗን ታዝቤ ልጆቹን ትቻቸዉ ጥሩም መጥፎም ሳልመልስ ሄድኩኝ....አንዷ እየሄድኩ ከሆላየ እየተከተለች መጥታ """"""ነዋል አንቺ"" ............. ""ስለሆንሽ አታናግሯት ብላኛለች ስለሆነም እኛም ከአሁን ቡሀላ አናወራሽም አሉኝ፡፡
  
የዚች ልጅ መጥፎ ጓደኝነት ከነከነኝ በሰራችዉ ስራ በጣጣም አዘንኩ ...ለነገሩ ሰዉ አመሉ መጥፎ ከሆነ ጥሩ ለመሆን እድል ይጠይቃል ፡፡መጥፎ ጓደኛ በህይወት ላይ የራሱ የሆነ መጥፎ ጫና አለዉ ...
  ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ በሀዲሳቸዉ ሙዕሚንን እንጂ አትጎዳኝ ...እንዲሁም አንድ ሰዉ በጓደኛዉ እምነት ላይ ነዉ ;ከእናንተ አንዳችሁ ከማን ጋር እንደሚወዳጅ ይመልከት ..እንጂ ዝም ብሎ ወዳጅነት አይመስርት ሲሉ ይመክራሉ

አብደላ ቢን ኡመር ደግሞ አስገራሚ ምክር ለግሰዉናል ፡- "ጠላትህን ራቀዉ፡ወዳጅህን ተጠንቀቀዉ ሙዕሚን ሲቀር፡አላህን ከሚፈራ በቀር ታማኝ የለምና፡ጠማማን አትጎዳኝ ከጥመቱ ያስተምርሀል፡ሚስጥርህን ለእሱ አትንገር ፡ማማከር ስትፈልግ አላህን የሚፈሩ ግለሰቦችን አማክር...ብለዋል

ጓደኝነት በኢስላም ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸዉ ግንኙነቶች አንዱ ነዉ፡ሰዉ ዉሎዉን ይመስላል ይባላል ከመጥፎ ሰዎች የዋለ እንደዛዉ መጥፎ የመሆን እድል ይገጥመዋል ፡ ከጥሩ ሰዎች የዋለ እንደ እነሱ ጥሩ ሰዉ የመሆን እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡

    በሰፈር ልጆች ወሬ ሒወት ገና በልጅነቴ አስጠላችኝ...ለወደፊት ለመኖር ተስፋ ቆረኩ በልጅነቴ ህይወት ጨለመችብኝ ..ኑሪ ኑሪ የሚል ተስፋ ከኔ ላይ ጥሎኝ ሲሄድ ታየኝ.... ብቻየን በየመንገዱ ማልቀስ ጀመርኩ ...ግን ፈጣሪ በልጅነቴ ጀምሮ ለምን ሊፈትነኝ ፈለገ እያልኩ ብቻየን አስባለሁ..... በኔ እኩያ ያሉ ልጆች ደስታ ጨዋታና ሳስታዉስ በተዘዋዋሪ ደግሞ እኔ በመደሰቻየ ስቄ ተጫዉቼ በማደጊያየ የሰቀቀን የለቅሶ ህይወት ለመኖር ተገደድኩ .....
ወሬዉ ትክክል መሆኑን ሲደጋገም አረጋገጥኩ......... ግን የበለጠ እርግጠኛ መሆን የፈለኩት ሰራተኛዋ ስነግረኝ መሆኑን እራሴን አሳመንኩኝ....

ረመዷን አልቆ ክረምቱም አልፎ ስደስተኛ ክፍል ገባሁ ....የቤት ሰራተኛችን የአላህ ነገር የአባቴ ጓደኛ እሷን አግብቶ ወደ ናዝሬት እንደሚወስዳት ከአባቴ ሰማሁኝ....

   ይህን ወሬ አባቴ እንደነገረኝ ማሻ አላህ አልኩ..ከዛም አባቴ ለስራ ከቤት ሲሄድ ...
የቤት ሰራተኛችንን ሚስጥሩን እንድነግረኝ ...እባክሽ ስሰቃይ አልኑር እዉነቱን ንገሪኝ እኔ የሰፈር ልጆች እየነገሩኝ ነዉ አንቺ እዉነት ነዉ በይኝ እና ቁርጤን ልወቀዉ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት
......እሷም እንባየን እያበሰች ነዋል እሺ እነግርሻለሁ እምባሽን ጥረጊ አለችኝ.....
...እኔም ሚስጥሩ እዉነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወዳዉ እንባየን ጠረኩኝ
......, ሰራተኛችንም ለአባትሽ ላልናገር ብለሽ በአላህ ስም ማይልኝ አለችኝ
...........እኔም ወላሂ ለአባቴ በጭራሽ ላልናገር ብየ ማልኩኝ
....ሰራተኛችን ለስለስ ባለ ድምፅ ነዋል እኔ ባልወልድሽም የማይሽ እንደ ልጄ ነዉ እዚህ ቤት ሰራተኛ ሁኜ ማገልገል የጀመርኩት ገና አንቺ ሳትወለጅ እናት እና አባትሽ ከተጋቡበት ጊዜ ጀምሬ ነዉ.....በመንከባከብ ያሳደኩሽ እኔዉ ነኝ፡፡

ነዋል ግን በልጅነትሽ አንድ የተፈጠረ ነገር አለ.. ስነግርሽ መጨናነቅ አያስፈልግም ለወደፊት ጠንካራ እና ለሰዉ ወሬ የማትበገሪ መሆን አለብሽ ..ይሄ በአንቺ ቤተሰብ እና በኔ ቁጥጥር የሆነዉ ሚስጥር አገር ያወቀዉ ፀሀይ የሞቀዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ.... ከሰፈር ልጆች የምሰሚዉ ሚስጥሩ በሁሉም የሰፈር ሰዉ ትልቁም ትንሹም ያቀዋል .....

   ነዋል አንቺ ገና የልጅነት ሒወትሽን ሳታጣጥሚ ክፉ እና ደጉን በማትለይበት በለጋ እድሜሽ በአራት አመትሽ..........

#ክፍል 4⃣
ይ.......ቀ........
......ጥ.......ላ...........ል



JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አራት 4⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




  ነዋል አንቺ ገና የልጅነት ሒወትሽን ሳታጣጥሚ ክፉ እና ደጉን በማትለይበት በለጋ እድሜሽ በአራት አመትሽ በጎረቤታችን ልጅ  አንቺም እኔም በምናቀዉ በቶፊቅ  ተደፍረሽ ነበር ..ለዛ ነዉ ልጅቱ ጋር ስትጣሉ #በቶፊቅ_የተደፈርሽዉ ያለችሽ ..መስጊድ ዉስጥ ያቺ ልጅ እናቷ ነግራት አንቺን የነገረችሽ የማይካድ ሀቅ ነዉ ነዋልየ  

አንቺ ልጅ ስለሆንሽ ስለማታስታዉሽ ነዉ  ብላኝ እንባዋን እየዘረገፈች  የቤት ሰራተኛችን ነገረችኝ፡፡

ሰራተኛችን ስነግረኝ ቁሜ ቀረሁ እንባየ በሁለት ጉንጮቼ ኩልል እያሉ ወረዱ ...እዉነት መሆኑን አረጋገጥኩ ... ወደድኩም ጠላሁም አምኖ መቀበል እንጂ መቀየር የማልችለዉ የተፈጠረ ሀቅ ነዉ፡፡
የኔ ሂወት ዉጣ ዉረድ ስቃይ ፈተና ከዚሁ ከአራት አመቴ ይጀምራል

       ሬቱን ከማር ለይቼ ሳላውቀው
       ሀራሙን ከሀላል ከቶ ሳለየው
       አፍረተ ገላዬን መሸፈን ሳለምድ
      ጣፍጭ የሚያታለኝ በግድም በውድ

     ብልጠት ያላበቀልኩ እንቡጥ ከረሜላ
     ገና ያልበሰልኩ ጥሬ እንቡቅላ
     እንኳንስ ቀበቶ ለኔ ሊፈቱ
     የስሜታቸውን ጥግ በኔ ላይ ሊያበርዱ

      ገና ሲያዩኝ ላይን የማሳሳ
     እንኳንስ ሊነኩኝ ሲያዩኝ የሚያሳሳ
    እንዴትስ ተችሎት ስቃይ አሸከመኝ??
     አካሌን ለአካሉ ለምኑ ተመኘኝ???
     

ሰራተኛችን ከነገረችኝ ቡሀላ ወደ ሆላ ማሰብ ጀመርኩ በዛ ጊዜ አባቴ ቶፊቅን በሽጉጥ እገላለሁ ሲል እና ገና በተደፈርኩኝ አካባቢ ሆስፒታል ስሄድ ፓሊስ ጣቢያ አባቴ ጋር ስሄድ ፍርድ ቤት አብረን እየሄድን አባቴ ሲከራከር ትንሽ ትዝታዎች ብልጭ ይልልኝ ጀመር ፡፡

ቶፊቅም እዛዉ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ታወሰኝ ነገር ግን አልታሰረም በብር ቅጣት ተቀጥቶ ክሱ የተቋረጠ ይመስለኛል...ግን ለመን አልታሰረም ህይወቴን ልጅነቴን አይደል የወሰደዉ????በአራት አመቴ ህፃን ልጅ ነኝ መደፈር የሚባለዉን አላቅም..ቶፊቅ ግን ትልቅ ልጅ ነዉ ቢያንስ ሀያ አመት ይሆነዋል፡፡ ገና እኔ ሰዉነቴ ሳይጠነክር ሳያዝንልኝ እንደ ደፈረኝ አስተወስኩኝ ፡፡  ሰራተኛችኝም ብዙ ነገሮችን እያረጋጋች ነገረችኝ ...

ቶፊቅ ጅማ የሚኖረዉ ከአያቱ ጋር ነዉ ፡፡ ከእኛ ቤት ጎን ነዉ ቤታቸዉ ፡፡ ሁሌ መጫወት ስፈልግ የእኛ ግቢ በጣም ሰፊ ቢሆንም ቤታችን ሙሉወን G2 የተሰራ ሲሆን  መኪና ማቆሚያ ብቻ ነዉ ያለዉ ...ስለሆነም እነ ቶፊቅ ቤት መጨዋት ለኔ ይመቸኛል ...የቶፊቅ አያቶቹ ነጋዴዎች ስለሆኑ እሱ ነዉ ቤት ሲጠብቅ የሚዉለዉ.....
    እዛ ግቢ እቃቃ ስንጫወት እንትና የኔ ልጅ ትሁን እንትና እየተባለ ቶፊቅ እኔን የኔ ልጅ ናት ብሎ ሁሌ እቃቃ ስንጫወት የቶፊቅ ልጅ ነበር የምባለዉ ፡፡ ቶፊቅ ለቤተሰቦቼ ጥሩ መስሎ የሚታይ ሁሌ እቤቴ ሲወስደኝ አቅፎ ተንከባክቦ ስለሆነ እናቴም አባቴም አይጠረጥሩትም ....እንደዉም አባቴ ልጄን የወደደ እኔን ወደደ ይባል የለ ..ቶፊቅን በጣም ይወደዋል..,

  አንድ ቀን እናቴ ድስት ከእነቶፊቅ ቤት አምጪ ብላ ላከችኝ.... እሱ ቤት ስሄድ ቶፊቅ ማንጎ እየበላ ነበር....ማንጎ ስጠኝ ???ስለዉ
ድስቱን ለእናትሽ አድርሰሽ ነይ እና እሰጥሻለሁ አለኝ
....እኔም ለእናቴ ድስቱን ሰጥቼ ወደ ቶፊቅ ቤት ተመለስኩኝ ...ከዛም ማንጎ ሰጥቶኝ የፈለገዉን የልጅነት ገላየን ሲጫወትበት ...እናቴም ልጄ ምን ሁና ቀረች ??መጣሁ ማንጎ ተቀብየ  ብላኝ ?? ከነቶፊቅ ቤት ዉጭ ሂዳ ይሆን እንዴ ??ብላ ...እነ ቶፊቅ ቤት መኖሬን አልመኖሬን ለማረጋገጥ ስትገባ ቶፊቅ እኔን ልብሴን አስወልቆ እንዳሻዉ ሲያደርገኝ በአራት አመቴ መቀበል የማልችለዉ በደል ሲያደርስብኝ እናቴ በአይኗ ተመለከተች
......እናቴም ያየችዉን ማመን አቃታት. ባለችበት ድርቅ ብላ ቀረች..
....,የምታወራዉ የምትለዉ አጣች አፏ ተያያዘ ..ምን ይደረጋል ይሄ እንኳን የወለደችኝ እናቴ ለኔ የምትሳሳስልኝ አድጌ ብዙ ደረጃ እንድደርስ የምጠበቅ ልጅ ..በልጅነቴ ተደፈርኩ ...እናቴ የኔን ክብር ማጣት በአይኗ አየችዉ፡፡
የምትለዉ ስታጣ ጩኸቷን አቀለጠችዉ.
  የእኛ ሰፈር የሚኖሩ ሰዉ አንድም ሳይቀር ልጅ ትልቁ ወጣቱ ሽማግሌዉ የኔን መደፈር በአንዴ ታወቀ...ቶፊቅም አፍሮ ለጊዜዉ ከአካባቢዉ ተሰወረ፡፡ ሰራተኛችን በሂደት ሁሉንም ነገረችኝ፡፡

   ከሁሉም ሰዉ የቤት  ሰራተኛችን ትሻለኛለች እሷ ትረዳኛለች፡፡ ቤተሰቦቼ ጋር ብር እርዚቅ ቤታችን ላይ ይኑር እንጂ ምንም ስምምነት የለም... ሁሌ መጣላት ነዉ ስራቸዉ፡፡ የመጨረሻ ልጅ እህቴ ከተወለደች ቡሀላ እናት እና አባቴ አንድ ላይ  ሲተኙ እንኳ አይቻቸዉ አላቅም፡፡
     የኔ ስነ ልቦና ጫና እያለብኝ ግን ቤተሰብ ባለመስማማታቸዉ እኔን ከጎኔ ሁኖ አብሽሪ እያለ የሚያፅናናኝ ቤተሰብ ዘመድ ጎረቤት ጓደኛ የለኝም ፡፡

   ቶፊቅ በኔ ላይ የሰራዉ በደል ትዝ ሲለኝ ብቻየን አልቅሼ እምባየን የሚጠርግልኝ የለ እኔዉ እራሴ በአስሩም የእጅ ጣቶቼ እያቀያርኩ ከፊቴ አብሰዉ ይዣለሁ፡፡ ለማን አልቅሼ ነግሬ አብሽሪ ይበለኝ ??? ማን ነዉ ከጎንሽ ነን የሚለኝ ???

አንዳንዴ ይሄ መደፈሬ ትዝ ሲለኝ ብቻየን ሁኜ ድብር ብሎኝ ስቀመጥ....አባቴ በከፋኝ በደበረኝ ቁጥር ከጎኔ ሁኖ ነዋል ምን ሆንሽብኝ?ደብሮሻል ፊትሽ ተቀያይሯል እኮ እያለ  ያፅናናኝ ነበር ....
ግን ይሄንን ወሬ ሰራተኛችን ስለነገረችኝ ለአባቴ መናገር አልችልም፡፡ ያለኝ አማራጭ አባቴ ጋር ስሆን ደስተኛ ምንም ቅር ያላለኝ በሒወቴ የተደሰትኩ እመስላለሁኝ..ብቻየን ስሆን ደግሞ ባለቅሰዉ ባለቅሰዉ ደግሜ ባለቅሰዉ ምንም ሊወጣልኝ አልቻለም ፡፡እምባየ አለማለቁ ለራሴ ይገርመኛል
   ደግሜ ከእኔ ቁስል በላይ የሚያመኝ እናት እና አባቴ ማታ ማታ በተጣሉ ቁጥር እኔ ሌላ ሀዘን ለቅሶ ጭንቀት ነዉ ፡፡ ለማን አግዛለሁ ?? ማን ጥፋተኛ እንደሆነ አላቅም ግን ሲመስለኝ እኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታወቀኛል

ግን ብዙዉን ጥፋቱ እናቴ ትመስለኛለች..ሁሌም ቢሆን ነገር አፈንፍና ነዉ የምትጣላዉ

   እናት እና አባቴ ትዳራቸዉን አይፋቱ እኛ ሶስት ልጆች ተፈጥረናል ፡፡ ተስማምተዉ አይኖሩ መስማማት አልቻሉም ፡፡ ብር ሀብት ሳያንስ ግን መስማማት ባለመቻላቸዉ አላህ የሰጠንን ሀብት ንብረት በደስታ መጠቀም አልቻልንም ፡፡

  ከእናቴ በላይ አባቴ በጣም ይቀርበኛል የቶፊቅን በደል አብሽሪ አይዞሽ አይለኝም..ለምን እኔ የማቅ አይመስለዉም ፡፡ ይሄን ሚስጥር ማወቄን ቢሰማ ቀጥታ ሰራተኛችን ጋር እንደሚጣላ እርግጠኛ ነኝ
 
አባቴ ግን ሁሌ ባገኘኝ ቁጥር በዙ ቀን እየደጋጋመ ፀጉሬን እያሻሸ አንቺ ባትፈጠሪ ኑሮ እናትሽ ጋር መለያየታችን አይቀርም ነበር ...እናትሽ ጋር ለመፋታት አስብ እና አንቺ ትዝ ስትይኝ እንደገና እተወዋለሁ ይለኛል፡፡
ሁሌም ቢሆን የአይኔ ማረፊያየ ነሽ..አላህ ይጠብቅልኝ ብሎ ግንባሬን ሳም አርጎኝ ስሄድ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርልኛል..ልቤም እንደመረጋጋት ይላል👇👇👇
   ከልጅነት ጀምሬ የምቀራረበዉ ኡስማን  ትምህርት ቤት አንድ ስለሆነ ቁርአን ቤትም እንገናኛለን እሱም ቁርአን ላይ ጠንክሯል፡፡ ቁርአናችንን እየተዉን እቤታቸዉ እየሄድን ባንጫወትም ግን እኔ እና እሱ የልጅነት ፍቅር ተብየ በሁለታችን ልብ ዉስጥ አለ
   ኡስማን ጋር ከአንደኛ ክፍል እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ ስንማር አንድ ትምህርት ቤት ስለነበርን የፍቅር ይሁን የልጅነት ነገር ይሁን አላቅም ኡስማንን ሳየዉ ፍዝዝ የማለት ልቤ እንደመደንገጥ ሰዉነቴ አልታዘዝ አልታዘዝ እንደማለት ይሆናል ፡፡ ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ??
በነብዩ ጊዜ የነበሩ ሱሀቦች ፍቅርን እንዲህ ነበር የተረጎሙት

★★★በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ በኡሁድ ዉጊያ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ተገድለዋል የሚል ዜና መዲናን እየናጣት ነበር ..የመዲና ሰማይ በዚህ አሳዛኝ ወሬ በሀዘን አጥልሏል..መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ኡሁድ አቅጣጫ እየተመመ ነዉ
ከአንሶሮች መካከል የሆነችዉ ሱመይራ(ረ.ዐ) ሁለት ልጆቿ አባቷ ባለቤቷና ወንድሟ ሰማዕት መሆናቸዉን ተረዳች ..ሱመይራ እነዚህ ሁሉ ወገኖቿ ቢሞቱባትም በዚህ ሁሉ የሀዘን ዉርጅብኝ አልተናወፀችም ..እልቁንስ እሷን ያስጨነቃት በእዉነት የታወቀዉ የጓጓችለት አንድ ዜና አለ ይህም የነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሒወት መኖር ነዉ
..በእርሳቸዉ ላይ የደረሰ አንዳች ክፉ ነገር አለ??በማለት ጠየቀች
...የነብዩ ባልደረባዎችም ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እርሳቸዉ በሒወት ይገኛሉ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ አሏት
ሱመይራ እንዲህ አለች ፡-እሳቸዉን እስከማይ ድረስ እረፍት አላገኝም የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ)አሳዩኝ አለች
እሳቸዉን እንዳሳዩዋትም በቀጥታ ወደ እርሳቸዉ በመሄድ የካባቸዉን ጫፍ ከያዘቼ ቡሀላ እንዲህ አለች
"""""እናቴና አባቴ መስዋት ይሁንለልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እርስዎ በሂወት እስካሉ ድረስ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ ..ያ በነብዩ ዙሪያ የነበሩ የተባረከ ትዉልድ ለእርሳቸዉ ይህን የመሰለ ድካ የሌለዉ ፍቅር ይለግሳቸዉ ነበር ...እኛስ?? ፍቅርን በሰዉ አይደል የምናመሳስለዉ ???

  እኔ ስድስተኛ ክፍል በምማርበት ጊዜ ኡስማን ጋር ብዙ ጊዜ ቁርአን ቤት እና ትምህርት ቤት እንገናኛለን ቁርአን እቀራለሁ እንጂ ሶላት አልሰግድም ለዚህም ምክንያት ቤተሰቦቼ ስገጅ ብለዉ ስለማያበረታቱኝ ነዉ ...   ትምህርት ቤት ስሄድ ሱሪ እለብሳለሁ ..

ሱሪ በምለብስ ጊዜ ኡስማንም ቁርአን ቤት ስትመጪ ሒጃብ ትለብሻለሽ ትምህርት ቤት ደግሞ ሱሪ ትለብሻለሽ አንዴ ቃልቻ አንዴ ዱሪየ እስታይል አትከይ ከአሁን ቡሀላ ትምህርትም ስትመጪ ሱሪ ለብሰሽ እንዳትመጪ ብሎ ይቆጣኛል፡፡
....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ አለብስም አልኩት

እኔ ከኡስማን ጋር ጊዜ ማሳለፍ እሱም እኔ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስ ይለዋል፡፡ ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ስንመለስም ስንሄድም ተቃቅፈን ነዉ....የክላስ ልጆች ነዋል እና ኡስማን እኮ ይዋደዳሉ ተቃቅፈዉ ነዉ የሚሄዱት እያሉ ሁሌ ያወራሉ ፡፡ አዎ እዉነታቸዉን ነዉ የኡስማን ሰፈር ቆሎ በር አካባቢ ነዉ፡፡ አንዳንዴ እኔን አጂፕ ድረስ ይሸኘኛል
 
አሁን ድረስ የሚገርመኝ ሁሌ እቤቴ ስሄድ ሶላት ባልስግድም __ግን በዱአ አላህን በመለመን አምን ነበር፡፡ መስገጃ ቦታ ላይ ሱጁድ ወርጄ  ስቅስቅ ብየ እያለቀስኩ ያረቢ  ኡስማንን የኔ አድርግልኝ ኡስማን የኔ የወደፊት ባሌ አድርግልኝ አንዴ የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኝ እምቢ አልልም እንዲጠይቀኝ አርግልኝ  እያልኩ አላህን እለምናለሁ ፡፡
   ግን ቢጠይቀኝ ገና ልጅ ነኝ ምን እለዋለሁ??? እንዴ ሁለታችንም ልጆች ነን ትዳር የማይታሰብ ነዉ እንዴት ይሄንን ሀሳብ ልመኝ ቻልኩኝ??? ደግሞ ለኡስማን የተለየ አመለካከት ቢኖረኝም ወንድ ልጅ እንደ ቶፊቅ ጨካኝ ቢሆንስ እያልኩ ብቻየን የሀሳብ ማዕበል ወስዶ ይመልሰኛል ..ነገር ግን ኡስማንን መራቅ የማልችልበትም ደረጃ ላይ ነኝ፡፡

ትምህርት ቤቶች ላይ ጥንቃቄ ግድ ነዉ ትዉልዱ ገና ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ ሌላ መስመር ይጀምራል...ቤተሰብ ልጄ ገና ህፃናት የሚለዉን የድሮ ተረት ትተዉ  ልጅን እንደልጅ ሳይሆን እንደ እህትነት አርገዉ ቢቀርቡ የተሻለ ነዉ..አንድ ሰዉ ሁሌ የሚናገራት ንግግር ትዝ ይለኛል የሴት እና የአር ትንሽ የለዉም ይላል እዉነቱን ነዉ ሴት ልጅ ገና ልጅ ናት ቢባል በወንድ ልጅ አፍ መሸወዳ አይቀርም..አርም ትንሽ ብትሆን መሽተቱ አፍንጫ መረብሹ ስለማይቀር ወላጅ የትምህርት ቤት አዋዋልን ልብ ሊል ይገባል ባይ ነኝ፡፡
  
ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...








#ክፍል 5⃣
ይ.......ቀ.......ጥ
......ላ........................ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
   
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አምስት 5⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...
ሴትን ልጅ ሁለት ቃላቶች ላይ ልባቸዉ ይንጠለጠላል አንደኛዉ፡-እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚባለዉን ቃል ሲሰሙ እዉነትም ይሁን ዉሸት ልባቸዉ ይሰረቃል ሁለተኛዉ ደግሞ በመንገድ ላይ እየሄዱ ቅናሽ እቃ ይሄቃ በዚህ ዋጋ ነበር አሁን ቀንሶ በዚህ ዋጋ ሲባል ከሰሙ አሁንም ልባቸዉ ይንጠለጠላል....
 
..የክላስ ልጆች ኡስማንና ነዋል ይዋደዳሉ ሲባል ደስ ይለኛል...ግን ኡስማን ይሄን ወሬ ሲሰማ በጣጣጣም ይቆጣል ይናደዳል ..ነዋልን ወላሂ የማያት እንደ እህቴ ነዉ በሌላ አይን አትዩን እያለ የክፍል ልጆች ጋር ብዙ ቀን ተጣልቷል
 
ኡስማን ጥፋት ሳጠፋ በጣም ይቆጣኛል... በአለባበሴም ቀን በቀን ምን ልብስ እንደለበስኩ ይከታተለኛል ሱሪ ለብሼ ስመጣ ስለሚቆጣኝ ሒጃብ መልበስ ክሪም መልበስ ኡስሚ እንዳይቆጣኝ እያልኩ በዛዉ ሂጃብና ክሪም መልበሱን ጀመርኩኝ .... ከትምህርት እንደተለቀቅን እቤታችን ደርሰን ሁሌም ቁርአን ቤት እንሄዳለን ፡፡ ኡስማንን እኔ ብወደዉም እሱ ግን እንደ እህት እንጂ ሌላ አስቦ በጭራሽ አያቅም ልቡን አሳምኖታል፡፡

ቁርአን ቤት እየሄድን ...ነዋል ቁርአን ማን ጋር ደረሽ??? ልታከትሚ ስንት ጁዝ ቀረሽ ?? ትናንትና ስንት ፊት ቀራሽ?? እያለ ቀን በቀን ይቆጣጠረኛል ...........ነዋል ነግሬሻለሁ ቶሎ አክትሚ እና የቁርአን ክትሚያ በግ አርደሽ አብሊን እያለ በጣም ይከታተለኛል ...ኡስሚ በጣም ጥሩ ልጅ ነዉ..እሱ በቁርአን ይበልጠኛል ነገር ግን እኔ እንደአክትም ይቆጣጠረኛል...
   ሶላት መስገድ የጀመርኩት በኡስማን ነዉ በፊት የምሰግደዉ በረመዷን ብቻ ነበር..የረመዷን ቃልቻ ነኝ ማለት ነዉ..

የአሁኑ ዘመን ፋሽን ተከታይ ነን ባዯች የአሁን ዘመን
እኛዉ ትዉልዶች ለሶላት ያለን አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ነዉ

በፊት የነበሩ ምርጥ ትዉልዶች ለሶላት ያላቸዉ አመለካከት ምን ይመስላል ???እስኪ ከዓሊ (ረ.ዐ) እንጀምር

★★★ዓሊ(ረ.ዐ)እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር ፡-የምእመናን አዛዥ ሆይ! የሶላት ሰአት ሲቃረብ የፊትዎ ቀለም የሚቀያየረዉና የሚንቀጠቀጡት ለምንድን ነዉ ??
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡ """ይህ ሰአት ሰማያትና ምድር እንዲሁም ተራሮች ሊሸከሙት እንዳልቻሉ በመግለፅ ያልተቀበሉትን አደራ ወደ ባለቤቱ የመመለሻ ሰአት በመሆኑ ነዉ ፡፡እኔ በትክክል መቻሌን አለመቻሌን አላዉቅም

★★★የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጅ የሆነዉ ሀሰን(ረ.ዐ) ምን ጊዜም ዉዱዕ ባደረገ ቁጥር ፊቱ ይገረጣ ነበር
አንድ ዕለት አንድ ሰዉ ሀሰን ሆይ!!! ዉዱዕ ባደረግክ ቁጥር ፊትህ የሚገረጣዉና ወደ ቢጫነት የሚቀየረዉ ለምንድን ነዉ ?? በማለት ጠየቀዉ
ሀሰን (ረ.ዐ) የሚከተለዉን መልስ ሰጠ፡- ብቸኛዉ የሀይል ባለቤት ታላቅና ባለግርማ ከሆነዉ አላህ ፊት የመቅረቢያ ሰአት  በመሆኑ ነዉ ""
ሀሰን(ረ.ዐ) ወደ መስጊድ ሲገባ የሚከተለዉን ዱአ ያደርግ ነበር፡-
ጠባቂየ ሆይ!!!! ባሪያህ በቤትህ ደጃፍ ላይ ደርሷል፡፡ምህረት ሁሉ በእጅህ የሆነዉ ሆይ!!! ሀጢያተኛዉ ባሪያህ ወደ አንተ መጥቷል ፡፡ ቅን ባሪያዎችህ ሌሎች ሰዎች የሰሩባቸዉን መጥፎ ነገር ይቅር እንዲሉ አዘሀል፡፡ ምክንያቱም አንተ ይቅር ባይና ቸር ነህ፡፡ አላህ ሆይ በተለመደዉ ይቅሬ ባይነትህና ምህረትህ በደሌን ይቅር በል .እዘንልኝም፡፡ ብለዉ ለሶላት ክብር ፍራቻ ነበራቸዉ እኛስ ??ብዙዎቻችን የመስጊድ ሙአዚን አዛን ሲል ሳንጠላዉ እንቀራለን ብላችሁ ነዉ?? ከኔ ጀምር ማን ነዉ አላህን ፈርቶ ሶላትን የሚሰግደዉ??? መልሱን ሁሉም በየቤቱ

       ትምህርት ቤት ሱሪ ለብሼ መምጣት ሙሉ በሙሉ አቁሚያለሁ .........ቤተሰቦቼ ሶላት ስገጅ አይሉኝም ፡፡ ኡስማን ግን ትምህርት ቤት እና ቁርአን ቤት ስንገናኝ ሶላት ሰገድሽ ወይ እያለ ይጠይቀኛል እኔም አንዳንዴ ሳልሰግድ ሰገድኩ እላለሁ ...ኡስማንም ወላሂ በይ እንዳትዋሺ ዉሸት ሀራም ነዉ ይለኛል...እኔም በቃ ሙሉ በሙሉ ሶላት መስገድ ጀመርኩኝ አልሀምዱሊላህ....... እንደዚህ ኡስማን ጋር አሳልፈን ስድስተኛ ክፍል ጨርሰን ክረምት ገባ
በክረምት ግን ኡስማን ጋር ቁርአን ቤት እንገናኛለን ፡፡ ግን ያዉ ቁጥጥሩ ቁርአን ቅሪ ሰገድሽ ወይ ነዉ......

ኡስሚም ቁርአን ሲከታተለኝ በእኔም ጥረት ቁርአኔን ስድስተኛ ክፍል እንዳለሁ አከተምኩኝ፡፡አልሀምዱሊላህ ቁርአን ሳከትም ቤታችን በግ ታርዶ ተሰድቆ ተበላ፡፡ ከዛም ምላሽ መቅራት ጀመርኩኝ፡፡

ክረምት አልቆ ለበጋ ለአዲስ አመት ጊዜዉ አስረከበ ሰባተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ....የትምህርት ቤት ተማሪዎች ኡስማን እና ነዋል በጣም ይዋደዳሉ እየተባለ መወራቱ በሰፊዉ ሁኗል .......ፍቅር የጀመርን አስመስለዉታል ሁሉም ተማሪ ኡስማን እና ነዋል ይዋደዳሉ ነዉ የሚሉት እኔ እንደዚህ ሲወራ ደስ ይለኛል ....
........መቼም ሴት ነኝ እና ከብዙ ሴቶች ጋር ማዉራቴ አይቀርም ..አንድ ቀን ለትምህርት ቤት ጓጀኞቼ የሞቀ ወሬ ይዘን እያወራን ዉሸቴን ኡስማን እኮ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ እወድሻለሁ አለኝ ብየ ለሁሉም ነገርኳቸዉ....
....... ይሄ የዉሸት ወሬ ኡስማን ጆሮ ሳይዉል ሳያድር ደረሰ.....


ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ተለቀን አብረን ስንሄድም ቁርአንቤትም ስንገናኝ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ ብለሻል እንዴ ??? ብሎ እንኳ አልጠየቀኝም ....እኔ ግን ዉሸት ስለሆነ በተናገርኩት ቃላት አፈርኩኝ ግን ኡስሚ ሰምቶ ባልሰማ አለፈዉ....
  
ኡስማን በልጅነቴ መደፈሬን ያቃል ..,የኛ ሰፈር ልጆች እኔ ጋርም የተጣሉት እሱ ጋር በጣም ይግባባሉ ፡ለምን እሱ ወንድም ሴትም ይቀርበዋል እንኳን ይሄን ብዙ ሚስጥር ይነግሩታል፡፡ የኔ በልጅነቴ መደፈር በትምህርት ቤት ሳይቀር የሚወራ ወሬ ነዉ፡፡ ለኔ ያለዉ አመለካከት ቀረቤታ ምንም ነገር አልቀነሰብኝም....ከወንድሜ በላይ አስበልጬ ነበር የምወደዉ ...የወደፊት የትዳር አጋሬ ቢሆን ዱአየ ነዉ፡፡ አላህ ያሳካልሽ በሉኝ

  
   ትምህርት እየተማርን አንድ ቀን የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ነዋል እኮ በልጅነቷ ተደፍራለች ድንግል አይደለችም እያሉ ወሬዉን እንደ አዲስ ሰበር ዜና አናፈሱት .....እኔም ይህን ወሬ በጆሮየ ስሰማ መናደድ ማልቀስ ሆነ ስራየ .............
ይሄን ሚስጥር ያልሰሙትም እየመጡ ይጠይቁኛል...ምን መልስ አለኝ ቀን በዝምታ ማታ ከማልቀስ ዉጭ... በዚህ ወሬ እየተደጋገመ ሲወራ የክፍል ጓደኞቼም የማቃቸዉ ልጆች ሳይቀር እየጠየቁኝ ስቸገር .. ክፍል ዉስጥ ተቀምጦ መማር  እያስጠላኝ ጥያቄዉን ሲጠይቁኝ በጣም ስናደድ ትምህሬን ቀጥቼ እወጣና እዛዉ ት/ቤት ግቢ ዉስጥ ብቻየን ቁጭ ብየ እንባየን በማፍሰስ መደፈሬን ለመርሳት እሞክራለሁ ግን የማይረሳ የማይፋቅ ክስተት መቀየር አይችል ምን ይደረጋል ወደ ሰማይ ቀጥ ብሎ አልቅሶ ወደ መሬት እምባ ከማፍሰስ በቀር..ትምህሬትንም በተረጋጋ መልኩ ልማር አልቻልኩም ..ትምህርት ቤት የምሄደዉ እቤት ለምን አትሄጂም እንዳልባል ብቻ ነዉ እንጂ ትምህርት ቤት ግቢዉ ክላስ እየቀጣሁ ብቻየን ማሳለፍ ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ👇👇
አንድ ቀን እረፍት ሰአት ላይ ቁጭ ብየ ብቻየን እያሰብኩ ናርዶስ የምትባል የክፍላችን ልጅ ...ወደ እኔ መጥታ ከጎኔ ቁጭ አለች.......
.....ናርዶስም ነዋል በሰላም ነዉ ብቻሽን ቁጭ ያልሽዉ ?? አለችኝ
.......እኔም አዎ በሰላም ነዉ ከይቅርታ ጋር ብቻየን መሆን ፈልጌ ነዉ ናርዶስ ብቻየን እንደሆን ፍቀጅልኝ ......የምፈልጊኝ ከሆነ ክፍል ስንገባ እንገናኛለን አልኳት
......እሺ ነዋል አንድ ነገር ብቻ እንድናገር ፍቀጅልኝ ብቸኝነት አታብዢ አትጨናነቂ የሰዉ ወሬ እንደሆነ መቼም አያልቅም የዘንድሮ ሰዉ እንዳያወራ አፉን ቢዘጉት በቂጡ ማዉራቱ አይቀርም.....ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትተክዢ ማየት አልፈልግም ...ለምን ብትይ አንቺ ለኔ ጥንካሬ ብርታት እንድትሆኚኝ እፈልጋለሁ ነዋል አለችኝ
........እኔም ግራ ገባኝ ከአሁን በፊት ናርዶስ ጋር ብዙም አንግባባም ከክፍል ጓደኝነት ዉጭ.....ሚስጥር አዉርታኝም አዉርቻትም አታቅም አላዉቅም ......ናርዶስ የክርስቲያን ሀይማኖት ተከታይ ናት """ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ?? አልገባኝም"""አልኳት
.......ናርዶስም፡- ቅዳሜ ከሰአት ብንገናኝ በሰፊዉ ላወራሽ እችላለሁ ይመችሻል ??? አለችኝ
........እኔም አዎ ይመቸኛል አልኳት......
ናርዶስም እሺ ቅዳሜ 10 ሰአት ላይ ዶሎሎ ሆቴል መናሀሪያ አካባቢ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ እንገናኛለን አልኳት፡፡ ከዛም እረፍት ሰአት አልቆ  ተደዉሎ ወደ ክላስ ገባን....

ናርዶስ ያለችኝ ነገር በጣም ግራ ገባኝ በአእምሮየ እየደጋገምኩ ማብሰልሰል ጀመርኩ""" ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትከዢ ማየት አልፈልግም ...""" እንዴት እንዲህ ልትለኝ ቻለች???? እያልኩ ብቻየን ማሰብ ይዣለሁ.........

የተቀጣጠርንበት ቀን ቅዳሜ ደረሰ በተባባልነዉ በ10 ሰአት ስሄድ ናርዶስ ጋር ጅማ የሚገኘዉ ዳሎል ሆቴል ተገናኘን ...ከዛም ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ወንበር ይዘን ተቀምጠን
የሚጠጣ አዘን አንዳንድ ወሬ ካወረን ቡሀላ ....>>>>>ምንድን ነበር የምነግሪኝ ናርዶስ??? አልኳት
.....ናርዶስም አደራ የምነግርሽ ቤተሰቦች ወንድሜም እህቴም እናት እና አባቴ የማያቁት ሚስጥር ነዉ......የምናቀዉ  ፈጣሪ  እኔ እና ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ አንቺ ነሽ...ስለሆነም ሚስጥራችን እዚሁ ይቅር አለችኝ
..........ከዛም እሺ ናርዶስ ለማንም አላወራም ብየ ቃል ገባሁ
>>>>>>>>_ናርዶስም ወደ መሬት አጎንብሳ የምታወጣቸዉን ቃላቶች ከየት ልጀምር እያለች እንደ ምጥ ከብዷታል.......ምን መሰለሽ ነዋል እኔ በልጅነቴ ....................___


#ክፍል 6⃣
ይ...........ቀ........
.........ጥ.........ላ.............ል


Join👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEOFXIlKIXVySUTDcA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ስድስት 6⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


...ምን መሰለሽ ነዋል እኔ በልጅነቴ ... ገና የስድስት አመት ልጅ እያለሁ አጎቴ ጋር ከአባቴ በላይ በጣም እንቀራረብ ነበር ....ከመቀራረባችን የተነሳ አጎቴ ቤት እየሄድኩ አድር ነበር ..አንድ ቀን እንደተኛሁኝ አጎቴ ገና በስድስት አመቴ የልጅነት ህልሜን አበላሸዉ ...ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ የተኛሁበት አልጋ ደም በደም ሁኖ አገኘሁት... በህፃንነቴ በምወደዉ አጎቴ ተደፈርኩኝ....ከዚች ቀን ቡሀላ
አፈርኩኝ ደነገጥኩ አጎቴን ተዉ የምልበት ድፍረት እና ቃላት አጠረኝ... ወደ ቤቴ ከተመለስኩ ቡሀላ ይህንን ወሬ ለእናት እና አባቴ ሳልናገር ዝም አልኩኝ..........
.....አጎቴ በሰራዉ ስራ አፍሯል ከደፈረኝ ቀን ጀምሮ እሱ ቤት መሔድ አቆምኩኝ እሱም ወደ እኛ ቤት መምጣት አቆመ ....
እናት እና አባቴ ምን ሁነህ ጠፋህ??? ሲሉት የተለያየ ዉሸት እየደረደረ እኛ ቤት መምጣቱን አቆመ .....በልጅነቴ ይህን ጉድ ተሸክሜ ብቻየን ሳለቅስ ኖርኩኝ ፡፡
     ይሄዉ በደሌ ይሄዉ ግፍ ፈጣሪ አይበቃሽም ብሎኝ ደግሞ አጎቴ በደፈረኝ ከአንድ አመት ቡሀላ የአባቴ ጓደኛ እቤት መጥቶ አባቴም እናቴም የሉም ነበር ከዛም አባትሽ እስከሚመጣ እዚሁ ልጠብቀዉ አለኝ
...እኔም እሺ ብየ እቤት አሰገባሁት
ሳላወቀዉ ቁጭ ባልኩበት መጥቶ በጉልበት አስፈራርቶ የሚፈልገዉን በለጋ ሰዉነቴ የሚሰቀጥጥ ተግባር  ፈፀመብኝ ....በአባቴ ጓደኛ በእድሜዉ በገፋ ሰዉ ሁለተኛ በልጅነት የመደፈር ሰለባ ሆንኩኝ ......እግዚአብሔርን እስከ አሁን እናት እና አባቴ ይሄንን ሚስጥር አያቁም ...የምነግረዉ የለኝ የሚረዳኝ የለም ፡፡ ለአንቺ ስነግርሽ ትንሽ ቀለለኝ ብላ ...እምባዋን ቁልቁል ዘረገፈችዉ፡፡

ናርዶስ ስነግረኝ ጀምራ እምባየን መቋቋም አልቻልኩም ነበር ህመምህን መንገር ያለብህ ታሞ ለሚያቅ ሰዉ ነዉ ይባል የለ...እኔ ስነግረኝ እኔም በልጅነቴ የደረሰብኝ ትዝ እያለኝ አለቅስ ይዣለሁ፡፡ ሁለታችንም እያለቀስን ሁለታችንም ባለብሰተኞች ነን፡፡ በሆዳችን የፉም እሳት ነበልባል ተሸክመን ነዉ የምንሄደዉ ..ይሄ ነበልባል ሆድ ዉስጥ ይቀጣጠልና ቢተነፍሱት ለሰዉ ለመድረስ የሚከብድ ቀጥታ ወደ አይን ሂዶ አይንን ለብልቦ በእምባ የሚወጣ የማያባራ ጊዜ ቦታ የማይመርጥ እንደ ወራጅ ወንዝ መቆሚያ የሌለዉ ስቃይ ነዉ፡፡

ካፌዉ ዉስጥ ያሉ ሰዎች ትኩረታቸዉ ወደ እኛ ነዉ እኔ እንደምንም እምባየን ተቋቁሜ ናርዶስን እምባዋን እየጠረኩ አባበልኩኝ
   የዘንድሮ ሴቶች የሚያለቅሱት ወንጀል ሰርቻለሁ ሀራም ሰርቻለሁ ሳይሆን ጓደኛየ እወድሻለሁ ብሎኝ ተወኝ ሌላ አገባብኝ ሁኗል፡፡ እኛ ግን በህፃንነታችን በመደፈራችን ነዉ የእድል ነገር ሁኖብን ፈጣሪ ግፉን አሸከመን...

.......ናርዶስም እንደዚህ አለችኝ ነዋል የአንቺ የአደባባይ ሚስጥር ሁኖ ነዉ እንጂ ብዙ ሴቶች እኮ በጎረቤት በዘመድ በአባት ሳይቀር የልጅነት ህልማቸዉ የተበላሸባቸዉ ቤት ይቁጠረዉ ስለሆነም ከአሁን ቡሀላ ማንም ቢናገርሽ እንዳታለቅሺ ቆራጥ ጀግና ሁኚ...የበታችነት ሳይሰማን ተምረን ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሰን እንደዚህ ያሉ እህቶቻችንን መርዳት አለብን አለችኝ፡፡
...እኔም እሺ ቃል ገብቻለሁ ለሰዉ ወሬ ትኩረት ላልሰጥ በትምህሬቴም ጠንክሬ ተምሬ በሴት ልጅ የሚደርስን በደል ግፍ ከእህቶቼ ጎን ለመቆም ወሰንኩኝ
....ከዛም ከካፌ ወጥተን ከአሁን ቡሀላ ሀይማኖታችን ላያግደን ጓደኛ ልንሆን ቃል ተገባብተን አንቺም ከጎኔ ሁኚ እኔም ከጎንሽ አለሁ ተባብለን ተለያየን፡፡

የኡስሚ ጓደኛነት እንዳለ ሁኖ ናርዶስ ጋር ምርጥ ጓደኞች ሁነናል ...ናርዶስ ጋር ስለ ድንግልና ስናወራ ለወደፊት ለሚያገባን ባላችን ስንጠየቅ ምንድን ነዉ ግን የምንለዉ ???ብየ ጠየኳት
>>>>>>>>> ነዋል እኛ እኮ ፈልገነዉ ስሜታችን አስቸግሮን ድንግልናችንን አጥተናል እንዴ ???አላጣንም እኮ...ሳንወድ በግዳችን ነፍስ ሳናቅ በልጅነታችን የድንግልና ትርጉሙን ሳናቅ  ነዉ  በማያስቡ ሰዉነት በማይሰማቸዉ በስሜታቸዉ ያደሩ ወንዶች የተነጠቅነዉ ስለሆነም እኛ ሁሌም ቢሆን ድንግል ነን ....>>>>እኔ ሁሌ እራሴን የማሳምነዉ ድንግል ነኝ ብየ ነዉ አለችኝ፡፡ እኔም ናርዶስ እንደዚህ ካለች ቡሀላ እኔ ድንግል ነኝ ብየ እራሴን አሳመንኩ ለምን ምንም የድንግል ጥቅም ሳላቅ በልጅነቴ ስላጣሁት እራሴ ድንግል ነኝ ብየ አሳመንኩኝ....
ከዛ ቡሀላ በልጅነትሽ ተደፍረሻል ቢሉኝም ወሬ ቢያወሩ ምንም አይመስለኝም ነበር ግን ጠባሳዉ ባይለቀኝም......እራሴን አሳመንኩኝ ለዘንድሮ ሰዉ ጆሮ ላልሰጥ ብየ ...... ሰዉ ቢያወራ ቢጠቋቆሙብኝ ምንም አይመስለኝም........

ለሁሉም ነገር የሰዉንም ትችት ለመቋቋም ትዕግስት ማድረግ እንዳለብኝ እራሴን አሳመንኩኝ ...
ግን የኛ ትዕግስት እስከ የት ነዉ??? ተወዳጁ ነብያችን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ
ስድስት ልጆቻዉን በተለያየ ጊዚያት በራሳቸዉ እጅ ከመቃብራቸዉ ዉስጥ ካስገቡ ቡሀላ የህሊና ሚዛናቸዉ ሳይዛባ ሁሉንም ዋጥ አርገዉ በትዕግስት የሚኖር በዚህ አለም ግን እንደ ነብዩ ሙሀመድ
ሰ ዐ.ወ ይገኛልን ??ከልጅነት እስከ እዉቀት በዚህ ሁሉ መካራ እንደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)የተፈተነ ይገኛልን??በዚህ አለም ይህ ሁሉ የመከራ መደራረብ የተፈራረቀበት ይህም ሁኖ ጌታዉን የሚያመሰግን ከነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዉጭ ሌላ ሰዉ ፈፅሞ አይገኝም ...
አላህ ሆይ ለኔም ለዚህ ለተፈፀመብኝ ነገር ትዕግስቱን ስጠኝ እያልኩ የዘወትር ዱአየ ነዉ...እናንተም በዱአ እገዙኝ

   እኛ ክፍል አንድ ሙባረክ የሚባል ልጅ አለ ...ሁሌ ቀን በቀን ለኔ የፍቅር ደብዳቤ እየፃፈ እንደሚወደኝ ለጓደኞቼ ይልክልኛል .....ወደ ሆላ ታሪኬ ሙባረክ ጋር ያለዉን ስንመለስ ሙባረክ ደብዳቤ መላክ የጀረዉ አምስተኛ ክፍል ጀምሮ ነዉ ........እኔ ግን ለሙባረክ ምንም ጥሩ አመለካከት የለኝም ከነመፈጠሩም ትዝ አይለኝ....የኡስሚ ያለኝ አመለካከት ግን እኔም ግራ ይገባኛል፡፡ አልርቀዉ አልቀርበዉ ነገር ....

ወንድ ሲባል እንደ ቶፊቅ ተጠቅሞ የሚጥለኝ ነዉ የሚመስለኝ ....ሙባረክን ከአሁን ቡሀላ ደብዳቤ ብትልክ ብትረብሸኝ ለአባቴ ነዉ የምነግረዉ ተወኝ ብያለሁ ብየ በደብዳቤ ላኩለት ከዛ ቡሀላ ........ሙባረክ ደብዳቤ መላኩን አቆመልኝ፡፡

      የሚገርማችሁ ከአንድ እስከ ስድስት በምማርበት ጊዜ ከአንድ እስከ አምስት ነበር የምወጣዉ ....ሰባተኛ ክፍል ግን ለቤተሰብ ለመንገር የሚያሳፍር ደረጃ ወጣሁኝ...ከሀምሳ ተማሪ ሰላሳ አምስተኛ ነበር የወጣሁት.......በትምህርት ደረጃየ እኔ በጣም አዘንኩኝ ሰባተኛ ክፍል መቀለዴ ዋጋ አስከፈለኝ......ለአባቴ ካርዴን ሳሳየዉ ቢከፋዉም እኔን መጥፎ ቃል መናገር አልፈፍግም ..፡፡ ነዋል አብሽሪ ለሚመጣዉ አመት ዋና ፈተናዉ ሚኒስትሪ ላይ ታሻሽይዋለሽ አለኝ፡፡
....አባቴ አብሽሪ ቢለኝም እኔ ግን ዉጤቴ በመዉረዱ በጣም ተናደድኩኝ፡፡👇👇👇
ክረምት አልፎ ስምንተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ..ስምንተኛ ክፍል እያለሁ እኛ ክፍል የሚገኙ ሴት ልጆች ኡስማንን ...ነዋልን እወድታለሁ ብልሀል ወይ ?? እሷ እኮ ሁሌ ኡስማን የፍቅር ደብዳቤ ሰጠኝ እወድሻለሁ እለኝ እያለች ትነግረናለች እዉነቷን ነዉ እንዴ ?? ብለዉ ይጠይቁታል
.....እሱ ግን መልሱ ዝምታ ብቻ ነበር
የኛ ክላስ ልጆች በዉሸት እኔ እና ኡስማንን በተለያየ በዉሸቱም በእዉነቱም ወሬ ለማጣላት የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የላቸዉ ነበር ..

እነሱም ከእሷ ምን አለህ አንተ እኮ ብዙ ላይፍ ይጠብቅሀል ካልወደድካት ተዋት እያሉ ብዙ ነገር ካሳመኑት ቡሀላ በማላቀዉ ምክንያት በተለያዩ ወሬዎች ኡስማን እኔን ዘጋኝ......ኡስሚ በእኛ ክላስ የተቀነባበረ ወሬ ጆሮዉን ሞልቶ እኔን ጀርባዉን ሰጠኝ...



ኡስሚም በፊት ቁርአን ቤት እንገናኝ ነበር ከቁርአን ቤት ወጥቶ እቤቱ ሸህ ይዞ ኪታብ መቅራት ጀመረ....ትምህርት ቤት ስንሄድ አብረን ነበር የምንመለሰዉ ..አሁን ለብቻዉ በባጃጅ ሁኗል የሚመላለሰዉ ... በሁሉም አጋጣሚዎች እኔን እራቀኝ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ኡስማን ጋር ተጣላን...

እኔም ምን አጥፍቼ ነዉ የዘገሀኝ ምን አጥፍቼ ነዉ የተዉከኝ ??? ብየ አልጠየኩትም ዝም ሲለኝ ዝም አልኩት ሲዘጋኝ ዘጋሁት ........ልቤ ፍቅር እንደማይገዛዉ .. ማንንም ወንድ ወደ ልቤ እንደማይገባ አየሁት ..ለምን አንዴ ቶፊቅ ጉድ ሰርቶኛል ..ወንድ እንዳላምን አርጎኛል..........ኡስማን ጋር አብረን በሆንበት ጊዜ ለኔ ባለዉለታየ ብቸኝነት አይሰማኝም ነበር.... እወደዉ ነበር አልክድም ከመዉደዴ የተነሳ አልቅሼም ዱአ አድርጌያለሁ ኡስሚን ለኔ አርግልኝ ብየ ......ግን የኔ ልብ የፍቅር ልብ ማንንም መዉደድ እንደማይችል ተረዳሁኝ......አሁን አንድ ጓደኛ አለችኝ እንደ እኔዉ በልጅነቷ ክብሯን ያጣችዉ ናርዶስ ብቻ ናት.......

   የሰባተኛ ክፍል ዉጤቴ መዉረዱ በጣሞ ስላናደደኝ አሁን ሀሳቤ እና አላማየ አንድ እና አንድ፡ብቻ ነዉ ይሄዉም ለሚኒስትሪ ጥሩ ዉጤት ይዞ ማለፍ እና አባቴን ማስደሰት ነዉ የምፈልገዉ.....


  ሰምንተኛ ክፍል ላይ ትምህርቴ ላይ ብቻ ፎከስ ማድረግ ብቻ ሁኗል ትኩረቴ .....ከትምህርት ቤት ጓደኞቼም እንደበፊቱ የማይጠቀም የማይጎዳ የጊዜ ማሳለፊያ ወሬ ማዉራት ..አፍ መካፈት ዘመናይ ነኝ ከሚባሉት ከሁሉም ነገሮች እራኩኝ........ አልሀምዱሊላህ ሶላቴን ተከታትዪ ሰጋጅ ሁኛለሁ
ቁርአንም ምላሽ እየቀራሁ ነዉ፡፡
   
   በተጨማሪም ትምህርት ቤታችን ያሉት ጎበዝ ሴት ተማሪዎች ጋር ላይብረሪ እየገባሁ ማጥናት ጀምሪያለሁ፡፡ እራሴን ለመቀየር ወገቤን ጠበቅ አርጌ ተነስቻለሁ... ግራ የገባኝ ነገር ቢኖር እኔ ሳጠና ናርዶስ በጭራሽ አላጠናም አለችኝ ...ናርዶስን ቀን በቀን ተስፋ ሳልቆርጥ ላይብረሪ እንግባ እናጥና ብላት ሁሌም ከአፏ የሚወጣዉ መልስ እምቢታ ብቻ ነዉ፡፡


ናርዶስ የሀብታም ልጅ ናት ቤተሰቦቿ ጅማ ከተማ ላይ ህንፃ እና ታዋቂ ሆቴል አላቸዉ ፡፡

ትጋብዘኛለች ...ናርዶስ ብር በጣም ታባክናለች አባቷ የወጭ እያለ ይሰጣታል ብዙም አያካብድም፡፡ ብር እንደፈለገች ስለሚሰጣት አዳዲስ ልብስ መልበስና የፈለገችዉን ምግብ መብላት መጠጣት የዘወትር ተግባሯ ነዉ ...
ከትምህርት ስንለቀቅ ብዙ ጊዜ ካፌ ትጋብዘኛለች

ናርድስ ስለምታባክነዉ ብር ግራ እየገባኝ ..ተይ ብር መበተኑ ማባከኑን ቀንሽ እያልኩ ሁሌ ብመክራትም፡ የእሷ መልስ ግን እኔ በዚህ ጊዜ የምፈልገዉ እራሴን ዘና አድርጌ መኖር ነዉ የምፈልገዉ በስንቱ ልጨናናነቅ?? መጨናነቅ ይበቃኛል.....በትምህርት ጥናትም መጨናነቅ አልፈልግም ከመጣ ዉጤት ይምጣ ካልመጣም የራሱ ጉዳይ.....ትለኛለች፡፡

አንድ ቀን ናርዶስን ብቻዋን ቁጭ ብላ ጭልጥ ያለ አለም የሄደች ትመስላለች ከአጠገቧ ሂጄ ናርዶስ ናርዶስ እያልኩ ብጠራት ልትሰማኝ አልቻለችም ..ከጎኗ ሁኜ ናርዶስ ብየ ፊቷን ነካ ሳረጋት ከእንቅልፍ እንደባነነ ሰዉ ብንን ብላ ነቃች
...እኔም፡- ግን ለምን እንደዚህ በሀሳብ እርቅሽ እስከምትሄጅ ታስቢያለሽ?? ብቻሽን ተቀምጠሽ በሀሳብ ከምትበታተኝ አብረን ላይብረሪ ገብተን እናጥና ለወደፊት እኔ እና አንቺ በልጅነታችን ህልማችን ቢወሰድም ...ለወደፊት ህልም ያለን ህልማችንን መመለስ የምንችል ልጆች ነን ....ባለፈዉ ስንመካከር እኮ እኛ አርአያ መሆን አለብን ብለን ሁለታችን ቃል ገብተናል ለምን እንደዚህ ተስፋ ትቆርጫለሽ ??? ብዙ ጊዜ ብር በመበተን በመዝናናት በመልበስ መደሰት ምን ይሰራልሻል ??? አልኳት

ናርዶስም :- >>>>>>>እኔ በልጅነቴ በአጎቴ እና በአባቴ ጓደኛ የደረሰብኝ በደል አሁን ድረስ ከአእምሮየ አልጠፋም .,ቀን ቀን ስንገናኝ ደስተኛ እመስልሻለሁ ሰዉ ጋር ተጨዋች እመስላለሁ ግን ማታ መኝታየ ላይ ተኝቼ የተኛ ሰዉ ብመስልም ንፁህ እንቅልፍ ከወሰደኝ ብዙ አመታት አለፈኝ... ሁሌ ለሊት ለሊት ሳለቅስ ነዉ የማድረዉ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም፡፡ እቤቴ ምንም አልጎደለብኝም ቤታችንም ዉስጥ የምንኖረዉ በደስታ ነዉ ምንም የማስብበት የምጨነቅበት ነገር የለኝም፡፡ ግን ይሄ የልጅነቴ በደል ምንም ሊረሳኝ ሊለቀኝ ከአእምሮየ ልሰርዘዉ አልቻልኩም፡፡
ማታ ስተኛ እያለቀስኩ እየኖርኩኝ በቀኑ ደስተኛ ልምሰል ብየ ነዉ ...ትምህርት ለማጥናት ሞከርኩኝ ግን አእምሮየ ምንም ሊቀበልልኝ አልቻለም ...መፅሀፉን ስገልጠዉ ካላነበብኩት እምባየ የምማርበት መፅሀፍ ላይ ቢያርፍ ምን ጥቅም አለዉ ??ብላ ጥያቄየን በጥያቄ መለሰችልኝ ...,
    በናርዶስ አነጋገር በጣም ተሰማኝ ምን ማረግ እችላለሁ ...እኔም የእሷ አይነት አደጋ በልጅነቴ ደርሶብኛል፡፡ አብሽሪ አላህ አለን ከማለት ዉጭ

    የማይደርስ የለም ሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ተፈተንኩኝ ...........ከተፈተንኩ ቡሀላ ናርዶስ ጋር በእናቴ ስልክ እንደዋወላለን በሳምንት አልፎ አልፎ አንገናኛለን ......

የሚኒስትሪ ዉጤት ሲመጣ አባቴ ዉጤቴን ለማየት ቸኩሎ መጀመሪያ እኔ ነኝ ማየት ያለብኝ ብሎኝ ወደ ትምህርት ቤት ካርዴን ሊያመጣ ሄደ

የሚኒስትሪ ዉጤቴ አባቴ ይዞት መጣ .....በሩን ሲከፍተዉ አባቴ ጋር ፊት ለፊት ተያየን ....ምን ይለኝ ይሆን??? ጥሩ ዉጤት ነዉ ወይስ አይደለም ??"እያልኩ በቆምኩበት ጨንቀት ያዘኝ.......






#ክፍል 7⃣
ይ........ቀ......
......ጥ.......ላ.......ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሰባት 7⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




    የስምንተኛ ክፍል ዉጤቴ ሲመጣ በጣም አሪፍ እኔንም አባቴንም ያስደሰተ ዉጤት ነዉ ..ከትምህርት ቤት ሰቃይ ተማሪዎች ተርታ ሁኜ 97 አመጣሁ፡፡ አባቴ በጣም ተደሰተ ልጄ አኮራሽኝ አስደሰትሽኝ እያለ ደስታዉን መቋቋምና በቃላት መግለፅ እንደተቸገረ ከአነጋገሩ ያስታዉቃል

አባቴም:- በዚህ በሚያስደስት ዉጤት የተወሰነ ቀን ላዝናናሽ ተዘጋጂ አለኝ
..እኔም በደስታ እሺ አልኩኝ

የማይነጋ የለም ጨለማ ለጀንበር ሲያስረክብ ከጅማ ተነስተን 117 km ተጉዘን ወደ ወልቂጤ ከተማ ሄድን ..ወልቂጤ ከተማ እንደ ደረስን ማራኪ
ካፌ እና ሰላም ካፌ ገብተን የሚያምሩ ጊዚያትን አሳለፍን ..ከዛም..ከወልቂጤ ከተማ አለፍ ብሎ የሚገኙ ገስት ሀዉስ መዝናኛ እና ዋቤ መዝናኛ የሚያምሩ የማይረሱ ሁለት ቀናቶችን አባቴ ጋር አሳለፍን.....
ከሁለት ቀን ቡሀላ ወደ ጅማ ተመለስን፡፡

ከዛም አባቴ ሌላ ሽልማት አለሽ አብረን ሂደን የምፈልጊዉን ልብስ ግዢ አለኝ....ጅማ የሚገኘዉ ህብር ህንፃ መርካቶ አካባቢ አባቴ ጋር ሂጄ አዳዲስ ልብሶችና ጫማዎች በራሴ ምርጫ ገዛሁኝ፡፡ እኔም ደስ አለኝ የኛ ጎበዝ መሆን መጠንከር ከእኛ አልፎ ለቤተሰብ ደስታ ፍቅር መሆኑን ተረዳሁኝ፡፡ ክረምትን በመዝናናት እና አባቴ ጋር ሁኜ ወደ ተለያዩ ሀገሮች ወደ ድሬ ወደ አዋሽ እየወሰደ እያዝናናኝ አሳለፍኩኝ

  መስከረም ሲደርስ ዘጠነኛ ክፍልን ለመማር እኔና ናርዶስ ከኮምዩኒቲ ትምህርት ቤት መሸኛችንን ተቀብለን ከግል ትምህርት ቤት ወደ ጅሬን(አጂፕ) አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት ተመዘገብን፡፡

ከኮምዩኒቲ ት/ቤት ለመልቀቅ ዋነኛዉ ምክንያቴ ተማሪዎቹ በእኔ ስለሚጠቋቆሙ እና በልጅነቷ ተደፍራለች የሚባለዉ ወሬ መስማት ሲሰለቸኝ ነዉ ናርዶስን አማክሪያት አብረን ተስማምተን ከኮምዩኒቲ ትምህርት ቤት መሸኛ ተቀብለን ወጣን ፡፡

ትምህርት ጀምረናል ..መቼም ደህና ዋሉ ተብሎ ከቤት ከወጡ ሰዉ ጋር መደባለቁ አይቀርም...ጅሬን ትቤት ከናርዶስ ዉጭ ሌሎች አዳዲስ ጓደኞች ጨምሪያለሁ..........

ዘጠነኛ ክፍል በጓደኛ ግፊት ልበላሽ የነበረበት ኢስላም ሁኜ እነሱ ጋር ስሄድ ሀይማኔቱን የሚያዘኝን ለመተግበር እፍረት የሆነብኝ ጊዜ ነበር......

ነገሩ ምን መሰላችሁ....በምንማርበት ጊዜ ከናርዶስ ዉጭ ሶስት ክርስቲያን ጓደኞች ያዝኩኝ ..ሶስቱም የወንድ ጓደኛ አላቸዉ...መኖር ብቻ ሳይሆን አንዱ ጋር ላይፍ ቀጭተዉ አብረዉ ከአደሩ ቡሀላ የመቀየር የሌላ ወንድ ሰዉነት የሚመኙ ወንድ ልጅ ለእነሱ የሒወት እስትንፋሳቸዉ አርገዉ የሚያስቡ ናቸዉ...እነዚህ አዲስ ጓደኞቼ መጠጥ መጠጣት ቤርጎ ወንድ ጋር ማደር ክለብ ሒደዉ መጨፈር ለእነሱ ሒወታቸዉ ኑሯቸዉ ነዉ...ገና በዘጠነኛ ክፍል እነሱ አላማቸዉን የሳቱ በወጣትነት የእሳት ነበልባል ይጓዛሉ፡፡
     እናም ይሄን ሁሉ ሲያደርጉ መጥተዉ ለኔ ይነግሩኛል ፡ የት እንዳደሩ ምን እንደሰሩ ምንም የሚቀራቸዉ ነገር የለም ስለአዳራቸዉ ልጁ ጋር የነበራቸዉን የሀራም አዳር ሳይቀር ይነግሩኛል...
እኔም ምነዉ እንደ እነሱ ብሆን ብየ እመኛለሁ
መጥፎ ሀሳብ ሳስብ መልሼ አኡዙቢላህ እላለሁ

....ግን እነሱ በወንድ በመጠጥ ሲደሰቱ እኔ የሚያወሩኝ ወሬ ካለሁበት እድሜ አንፃር ለኔ ፈታኝ ከባድ ጊዜ ነዉ ..እንደ ጓደኞቼ ለመሆን ወጣትነት ቢፈታተነኝም ለዱንያ ለጊዜያዉ ደስታ ብየ አኼራየን ማጥፋት አልከለኩም ..በመቀጠል ደግሞ ቃል አለኝ አባቴን በትምህርቴ ጥሩ ደረጃ ደርሼ ለማስደሰትና እንደኔ በልጅነታቸዉ ለተደፈሩ ህፃናት ጎን ለመሆን  ..... ከትምህርት ቤት ስለቀቅ ሶስቱ ጓደኞቼ ሱሪ ለብሰዉ ሲሔዱ እኔ ደግሞ ሒጃብ ለብሼ ስሔድ መንገድ ላይ ላየኝ ሰዉ በጣም አፍራለሁ፡፡ ጓደኞቼ ምሽት ቤት ሲጨፍሩ እንደሚያመሹ የተወሰኑ የትምህርት ቤት ተማሪዎች ያቃሉ...እነሱ ጋር ስሄድ እኔም አብሬ ጭፈራ ቤት የማመሽ ታድራለች ብለዉ የሚጠረጥሩም ነበሩ፡፡
     አያችሁ ሰዉ መጥፎ ጓደኛ ጋር ስትሆን አንተ ጥሩ ብትሆንም  እንደ እነሱ መጥፎ ስራ ባሰራም የሰዉ አመለካከት እንደ መጥፎ ጓደኞች አብረዉ ነዉ የሚስሉት፡፡
መጥፎ ጓደኛ በህይወት ላይ የራሱ የሆነ መጥፎ ጫና አለዉ ...

ጓደኝነት በኢስላም ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸዉ ግንኙነቶች አንዱ ነዉ፡ሰዉ ዉሎዉን ይመስላል ይባላል ከመጥፎ ሰዎች የዋለ እንደዛዉ መጥፎ የመሆን እድል ይገጥመዋል ፡ ከጥሩ ሰዎች የዋለ እንደ እነሱ ጥሩ ሰዉ የመሆን እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡

መጥፎ ጓደኞች ጫናቸዉ ስለሚበረታ ከማህበራዊ ግንኙነት ላይ ከባድ ችግር ይፈጥራሉ ፡፡ ብዙ አመት ደህና ነዉ የተባለዉ ሰዉ መጥፎ ጓደኛ ከገጠመዉ በአንድ ቀን ወደ መጥፎነት ይቀየራል ..ሁሌም በመጥፎ ጓደኛ የተጎዱ እና ችግር ዉስጥ የገቡ ሰዎች መጨረሻ ሰአት ላይ ይነቃሉ...ግን የሚነቁት ብዙ ነገር ከተበላሸ ቡሀላ ባለቀ ሰአት ላይ ይባንናሉ ..ኢስላም ግን ቀድመህ አስብበት በማለት ግልፅ መመሪያ አስቀምጧል ..፡፡ መጀመሪያ ነበር አስቦ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ እንደተባለዉ ማለት ነዉ፡፡

 የያዝኳቸዉ አዲሶቹ ጓደኞቼ እየመጡ ማንኛዉንም ይነግሩኛል ...ብዙዉ ጥፋት የጓደኞቼ ቢሆኑም......እኔም ግን በመቆጨት መቼ ድረስ ነዉ ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ሰዉነት የሚጫወተዉ ??? ግን ለምን አንዴ ተጠቅሞ ሴትነት ወዟን ተጠቅሞ እንደ አሮጌ ጫማ የሚጥላት ???እያልኩኝ እናደድ እቆጭ ነበር....የእኔ ለወሬ አይመችም ገና በልጅነቴ ነዉ ክብሬን ያጣሁት.....በትምህርቴ ጠንከራ ሁኜ ፕሪፓራቶሪ ስገባ ወንድን ልጅ በፍቅር እያጠመድኩ እንደ ቁንጫ ፍትልትል እያረኩ በፍቅር እየጎዳሁ እነሱ ሲያለቅሱ ማየት የወደፊቱ እቅዴ አድርጌ ያዝኩኝ......
  
ዘጠነኛ ክፍል ጨርስኩኝ ጥሩ ዉጤት አምጥቼ ከክላስ 2ኛ ደረጃ ወጥቼ ወደ 10 ክፍል አለፍኩኝ.....ግን እነዛ ክርስቲያን ጓደኞቼ ሁለቱ ከዘጠነኛ ክፍል ማለፍ አልቻሉም ፡፡


ዘጠነኛ ክፍል ጨርሼ ክረምት ላይ ዘመድ ጋር  ለማሳለፍ ከጅማ 360km ርቀት ተጉዤ ወደ አዲስ አበባ ሄድኩኝ፡፡
እኔንም ያሳለፍኳቸዉን የሚያስጠሉ የሒወት መስናክሎች ጠባሳዎች ትዝም ሳይሉኝ ጥሩ ጊዜ ሸገር አሳለፍኩኝ....ትምህርት ሲጀመር ወደ ጅማ ተመለስኩ
....የ10 ክፍል ትምህርት መማር ጀምረናል..ግን 10ክፍል ላይ በነበርኩበት ጊዜ የሚያስጠላ ሒወት ያሳለፍኩበት በጓደኛ ግፊት አላማየን የሳትኩበት አመት ነበር...ዘጠነኛ ክፍል የነበሩኝ ክርስቲያን ጓደኞቼ ሌላ የወንድ ጓደኞች ነበሯቸዉ ...እኔ እና እና ናርዶስን ወደ ስድስት የሚሆኑ ክርስቲያን ወንዶች ጋር እንድንግባባ አስተዋወቁን....እኔም ከ6 ወንድ የትምህርት ቤተ ተማሪዎች ጋር ሲስተርሊ ብራዘርሊ መቀራረብ ጀመርን
    እነዚህ ክርስቲያን የወንድ ጓደኞች ጋር ከተዋወኩኝ ቡሀላ ብዙ አላማየን የሳትኩበት የተበላሸሁበት ጊዜያቶች ናቸዉ ....
  አምስት አዉቃት ሶላት መስገድ ..ቁርአን መቅራት በጓደኞቼ ግፊት ምክንያት
አቆምኩኝ👇👇👇
ደግሞ በተጨማሪም በመንገድ ሒጃብ ለብሼ የሴት ጓደኞቼ ጋር ስሄድ ምንድን ነዉ በልጅነትሽ ባልቴት መስለሽ የምትሄጂዉ??? እያሉ ቀን በቀን እኔን አሸማቀቁኝ...ሒጃብ ስለብስ ፋራ እያሉ ሲያስቸግሩኝ ሒጃብ መልበስም ሙሉ በሙሉ አቆምኩኝ.....የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ጓደኛ መያዝ በዲን ላይ ተፅእኖ አመጣብኝ፡፡ በጓደኛ ግፊት ሂጃብ መልበስ ተዉኩኝ...ግን አሁን ላይ ሳስበዉ ከኔ ዉጭ ተጠያቂ የማድረገዉ ቤተሰቦቼን ነዉ፡፡ ሂጃብ ትቼ ሌላ ፋሽን ልብስ ስለብስ አባቴም እናቴም ለምን ሂጃብ መልበስ አቆምሽ ???ብሎ የተናገረኝ የጠየቀኝ የለም...በዚህ እድሜየ የወላጅ ክትትትል ግዴታ ነዉ ብየ አምናሁ..

እነዛ የተዋወኳቸዉ የወንድ ጓደኞች የትምህርት ቤት ልጆች ሁሌ ትምህርት ቤት ስልካቸዉን ይዘዉ ይመጣሉ..በስልካቸዉ ላይ ብዙ የተለያዩ የባለጌ video ፊልሞች አሏቸዉ ....ናርዶስም እስኪ ድንግልና ሲሄድ ስሜቱን አሳዩኝ ትላቸዋለች..
እነሱም ስልካቸዉን እየሰጧት ትመለከታች...እኔ መመልከት ባልፈልግም ሳልወድ በግዴ እኛ በልጅነታችን ያጣነዉ ድንግልና እንዲዚህ ነዉ የሄደዉ ተመልከች እያለች እኔም በናርዶስ አስገዳጂነት ተመለከትኩኝ ...ናርዶስ የዚህ የባለጌ ፊልም video ሱሰኛ ሆነች ቀን በቀን ማየት ያስደስታታል...ተይ ብላት በዚህ የፊልም ሱስ ሰለባ ሆነች....

ነብዩ ሰ.ዐ.ወ መጥፎና ፀያፍ ነገር በህዝቦች ዉስጥ በምንም መልኩ ግልፅ አትሆንም ፡ በዉስጣቸዉ ቀደምት አባቶቻቸዉ የማያዉቅት ወረርሽኝ እና የተለያዩ በሽታዎች ቢከሰቱ እንጂ በማለት ይገልፃሉ

ፓርኖግራፊ(ልቅ ወሲባዊ ፊልሞች እና ምስሎች)መመልከት ያልተገደበ ወሲባዊ ጡዘትን እና የአእምሮ መረብሽን ያስከትላል፡ልቦናን መረጋጋት እንዳይኖረዉ በማድረግ ላልተፈለገ የወሲብ ሩጫ እና መልከስከስ ይጋብዛል፡፡ አንድ ቀን የሚታይ የወሲብ ፊልም ወይም ምስል ሁለት ወይ ሶስት ቀን ሙሉ አእምሮ ይረብሻል በተደጋጋሚ በአይነ-ህሊና እየመጣ የዉስጣችንን ሰላም የሚያናጋ ክስተት ነዉ፡፡

ኢስላም የተራቆቱ ገላዎች መመልከት ግልፅ በሆነ ቁርአናዊ አንቀፅ የተከለከለ እና በተለያየ ነብያዊ ሀዲሶች አፅንኦተ ተሰጥቶት የተወገዘ ተግባር ነዉ ፡፡ ይህን አስመልክቶ አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንዲህ ይላል ፡-
""ለምእመናን ንገራቸዉ ዓይኖቻቸዉን(ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልከሉ ፡ብልቶቻቸዉንም ይጠብቁ፡ይህ ለነርሱ የተሻለ ነዉ ፡ አላህ እነርሱ በሚሰሩት ሁሉ ዉስጥ አዋቂ ነዉ፡፡""(ሱረቱ ኑር 30)

ይህ የፊልም ሱስ አመጣጣጡ ዲነል ኢስላምን እና ወጣቱን ለማዳከም ነዉ .በዚህ የተነሳ በርካታ ወጣቶች ለሞት ዳርጓል;በርካቶች ለተለያዩ ህመምና ስቃይ ዉስጥ እያቃሰቱ እንዲኖሩ አድርጓል፡ በርካቶች በዚሁ ተለክፈዉ የቀን ዉሏቸዉ የለሊት አዳራቸዉ እርሱ ሁኗል...በዚህ ምክንያት ዉድ የሆነ ሒወታቸዉ ጊዜያቸዉን የገንዘብ ብኩንነት ..ሰላማቸዉ ተናግቶ ደስታ የራቀዉ ሒወት እየተገደዱ ነዉ፡፡

እንደ ተርብ እስታስቲክስ መረጃ ከሆነ ለፓርኖግራፊክስ(ለልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች)ድህረ ገፆች የሚወጣዉ ገንዘብ በአመት 57.8ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በአሜሪካ ብቻ 12 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል..የፓርናግራፊ ድህረ ገፆች ብቻ 4.2ሚሊየን እና 420.ሚሊየን ገፆች ይጠጋሉ፡ በአጠቃላይ ድህረ ገፅ 12በመቶ ለዚሁ ርካሽ ተግባር ማስፋፊያነት ተመድቧል ፡፡በሳምንት 70ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች የብልግና ምስሎችን በኢንተርኔት ይመለከታሉ ከእነዚህ ሰዎች መካከል 20ሚሊየኑ የሚገኙት በአሜሪካ እና በካናዳ ሲሆን በአዉሮፓ ደግሞ ጀርመን እንግሊዝ ስፔን ቀጣዮችን ቦታዎች ይይዛሉ..ምዕራባዊያን እራሳቸዉን ሆነ የዓለምን ህዝብ ወደ አልሆነ መጥፎ አቅጣጫ እየመሩት እንደሆነ መመልከት ይቻላል፡፡

እንደ እስታስቲካዊ መረጃዎች ከሆነ ሙስሊም በሆኑ ሀገሮች ላይ ያሉ ወጣቶች ቁጥር ሙስሊም ባልሆኑ ሀገር ላይ ካሉት ወጣቶች ቁጥር በጣም በልጦ ይገኛል ..በአጠቃላይ የሙስሊም ዓለም ወጣት ብዛት 70 በመቶ ሲጠጋ በምዕራቡ ዓለም ያለዉ ወጣት ቁጥር 25 በመቶ መሆኑን ያሳያል ፡፡ስለዚህ ለወደፊቱ አለምን የሚረከበዉ ጠንካራ ትዉልድ ያለዉ በሙስሊሙ ዓለም መሆኑ ምዕራቡን አለም ክፉኛ ስላሳሰባቸዉ ሙስሊሙን ወጣት በዚህ የፊልም ሱስ ተለክፎ ከአላህ ጋር ከቁርአን ከሀዲስ ከመስጊድ ያለዉን ግንኙነት ቀንሶ ከዲነል ኢስላም ርቆ ለኢስላም የማይጠቅም የማይጎዳ ትዉልድ ለማድረግ የመጣ ነዉ፡፡ ምእራባዉያን ለወደፊት ለሚመጣዉ ሙስሊም ትዉልድ እንዲበላሽ ከበፊት ጀምሮ ዛሬም ጭምር ቀን ለሊት እየሰሩ ነዉ ፡፡ እኛስ ለሚመጣዉ ትዉልድ ዲነል ኢስላምን ለማስረከብ ምነ እየሰራን ነዉ???

በጣም የሚያሳዝነዉ ይህን ፊልም መመልከት ለተለያዩ የወሲብ ችግሮች መፍትሄ ይሆናል በሚል እምነት የሚናገሩና የሚተገብሩ መኖራቸዉ ነዉ፡፡ ወጤቱ ግን በለቃራኒዉ መሆኑን ዘንግተዉታል

አላህ ከብልግና ፀያፍ ነገር..ከማንኛዉም መጥፎ ተግባር እንዲሁም ወሰንን ከማለፍ ይከለክላል
በሱረቱል ነህል 90 ላይ ..በዚህ አንቀፅ ፋህሽ ሙንከርና አል-በግይ የሚሉ ቃላቶች ሰፍረዋል ፡፡ ፋህሽ ማለት ብልግና .እፍረተቢስና ቆሻሻ ማለት ሲሆን ወሲባዊ ፊልሞችና ምስሎችን ያካትታል፡፡ሙንከር የሚለዉ ደግሞ ማንኛዉም በአለም ዙሪያ ያሉ ኢሞራላዊ መጥፎ ስነ-ምግባሮች መገለጫ የሆኑ ባህሪያትን ያካትታል ፡፡ አልበግይ የሚለዉ ኢፍትሀዊ የሆኑ ተግባሮችን ድንበር ያለፈ ጋጠወጥነትን ያካትታል፡፡ከዚህ የተነሳ ልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች በዚህ የቁርአን አንቀፅ ዉስጥ የተገለፀ ስለሆነ ህዝቡን የሚጎዱ ለክፉ ዉድቀት የሚዳርጉ ስለሆነ ህዝበ ሙስሊሞ ሊርቃቸዉና ሊያወግዛቸዉ ሀራም መሆኑን አዉቆ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡

ልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን የመመልከት ሱስን ለማስወገድ የሚደረገዉ ህክምና በጣም ከባድ ሁኗል..ምክንያቱም ሱሱ በአንጎል ዉስጥ በቀላሉ ለመፋቅ በማይቻል መልኩ ትዉስታዉን ጥሎ ስለሚያልፍ ይላሉ የተመራመሩ ባለሙያዎች ..ይሄ ሱስ በማንኛዉም ሁኔታ ትዝ እያለ ህይወትን ሊረብሽ የሚችል የትዝታ ዕፅ ነዉ፡፡ ነገር ግን እንደ ኢስላም አላህ ሁሉን ቻይ ከመሆኑ አኳያ እና ኢማን ከዚህም በላይ ተአምር ይሰራል ..የሰዉ ልጅ ከዚህም በላይ በከፋ በጣም መጥፎ ልምዶች ዉስጥ ተነክሮ መዉጣት በመቻሉ ከዚህ ሱስ መላቀቅና መዉጣት ይቸላል..መጀመሪያ በአላህ ተስፋ ማድረግ ከዛም ጠንካራ ዉሳኔ ወስኖ ከችግሩ ለመራቅ ቆራጥ አቋም ለመያዝ ሞክሮ መላቀቅ ይቻላል ..የመጀመሪያ መፍትሄዉ ከእነዚህ ልቅ የወሲብ ቻናሎች መዉጣት እና ከተለያዩ እነዚህ ካሉባቸዉ ሚዲያዎችና ደህረ ገፆች ማግለል የመጀመሪያዉ መፍትሄ ነዉ፡፡ ከዛም ቁርአን መቅራት እና ሙሉ በሙሉ ቶብቶ ወደ አላህ መመለስ ነዉ ይሄ ካልሆነ ለወደፊት ትዳር ቤተሰብ መምራት እንደማይቻል ሊታሰብበት ይገባል
(ስለ ልቅ የወሲብ ፊልም በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በኔ አሚር ሰይድ የተፃፈ የሕይወት መሰናክል የሚለዉን ታሪክ ቢያነቡ ጉዳቱ ምን እንደሆነ መገንዘብ ይችላሉ ያንብቡት ተጋብዛችሆል)
  
እነዛ የያዝኳቸዉ ጓደኞቼ ሁሌ Fb ላይ ሲጀናጀኑ ስልክ ሲያወሩ ቀናሁኝ .....እኔም እንደነሱ እንደመሆን ..አባቴን ስልክ ማስገዛት አለብኝ ብየ ወሰንኩኝ

#ክፍል 8⃣

ይ.........ቀ...
......ጥ.......ላ.........ል


Join👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEOFXIlKIXVySUTDcA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ስምንት 8⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



እነዛ የያዝኳቸዉ ጓደኞቼ ሁሌ Fb ላይ ሲጀናጀኑ ስልክ ሲያወሩ ቀናሁኝ .....እኔም እንደነሱ እንደመሆን ..አባቴን ስልክ ማስገዛት አለብኝ ብየ ወሰንኩኝ

አባቴ ኮንትራክተር ስለሆነ ድሬድዋ የተወሰኑ ቀናት ስራ ነበረዉ ሰርቶ ሲመለስ ... ስልክ አስገዛሁኝ...

ስልክ ከአስገዛሁኝ ቡሀላ ትምህርት ማጥናት የለ ቁርአን መቅራት የለ ሶላት መስገድ የለ በትምህርት ሰአት ሳይቀር facebook ላይ ቸክየ መዋል ስራየ ሁኗል... በfb ፎቶየን እፓስታለሁ በcomment ነዋል አምሮብሻል ሲሉኝ አቤት ያለኝ ደስታ ከኔ ዉጭ ቆንጆ ያለ አይመስለኝም ነበር ፡፡ በFb ብዙ ጓደኞች አፈራሁኝ በመጀናጀን ቢዚ አደረጉኝ....አላማየን እረሳሁኝ በfb እወድሻለሁ ያለአንቺ መኖር አልችልም የሚባሉ የወንዶች ከአንጀት ያልሆነች ከአፍ ብቻ ቃላቶች ማንበብ ለኔ የሚላኩ የፍቅር ገጠመኞች በfb message ተጨናንቆብኛል

የኔ ሴት ጓደኞችም ከኔ በላይ በfb ይጀናጀናሉ እነሱ ግን እንደፈለጉ ወንድ ጋር ማደር መጠጣት ካፌ መቀጣጠር ሲገናኙ መሳሳም ሴክስ ማድረግ ምንም አይመስላቸዉ የእነሱ አስተሳሰብ በዚህ እድሜያችን ላይፍ እንቅጭ ነዉ

እነዛ የተዋወኳቸዉ የወንድ የትምህርት ቤት ጓደኞቼም ስራቸዉ በfb አዉርተዉ ሴቶች ጋር መቀጣጠር ከዛም ማደር ዚና መስራት የተለመደ ተግባራቸዉ ነዉ ፡፡
ጠዋት ትምህርት ቤት ስንገናኝ አዳራቸዉን ይነግሩኛል ....በሚያስጠሉ ፈጣሪን የማይፈሩ ጓደኞች መሀል ሁኜ አላማየን እረሳሁኝ
አንድ ቀን ተሰባስበን ቁጭ ብለን የምታምር ልጅ በጎናችን አለፈች......አንዱ ተነስቶ ይቺን ልጅ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ጀንጅኜ አብሪያት አድራለሁ ይላል
.....ጓደኞቹም አረ በጭራሽ አይሳካልህም ይቺ ሀርድ የቦጨቀች ናት እሺ አትልህም ይሉታል
.......እሱም በእጄ አርጌ አብረን ስናድር Video ቀርጬ አሳያችሇለሁ ብሎን ከጎናችን ተነስቶ ልጅቱ በሄደችበት አቅጣጫ ተከትሏት ሄደ.....
 
ከአራት ቀን ቡሀላ ይሄዉ ልጅ ምሳ ሰአት ላይ እኛ የተቀመጥንበት መጣ .....አንድ ሳምንት እንኳ ሳይፈጅበት ልጅቱ ተበላች ትናንት አብረን አደርን እኮ አለን
......እኛም አረ በጭራሽ ልናምንህ አንችልም ዉሸትህን ነዉ አልነዉ
.....እሱም ይሄዉ ማመን ከፈለጋችሁ ብሎ 30ደቂቃ ቆይታ ያለዉ video ማስረጃ አብሮ ያደረበትን ይዞ መጣ ፡፡ ሁላችንም Video አየነዉ ልጁ እዉነቱን ነበር ልጅቱ ጋር አብሮ አድሯል፡፡

እነዚህ ስድስቱም ጓደኛሞች ስራቸዉ ሴትን ልጅ በዛ በዚህ በማያምር የፍቅር ቃላት ለመናገር ከመተንፈስ የቀለለች እወድሻለሁ በሚሉት ስድስት ፊደል ቃላት ሴቶችን በቁጥጥራቸዉ አድርገዉ የፈለጉትን ከአገኙ ቡሀላ እንደተፉት ማስቲካ ዘወር ብለዉ እንኳ አያዮቸዉም ፡፡ ደግሞ ገርሞ የሚገርመኝ ማደራቸዉ ሳያንስ አብረዋቸዉ ሲያድሩ በስልካቸዉ ቀርፀዉ ለሁላችንም ያሳዩናል

እህቴ ሆይ እንደነዚህ አይነት ወንድ ልጆች አንዴ የሚፈልጉትን ከአንቺ ከአገኙ ቡሀላ ማስቲካ ሲገዛ ወረቀቱ ይጣላል ማስቲካዉ ይታኘካል፡፡ አንቺም ማስቲካዉ ወረቀቱን ልጦ ሲበላ አንቺን የፈለገዉን አገኘ ማለት ነዉ...ማስቲካዉ ጠአሙ ሲለቅ እሱ ጋር ከነበርሽ ሰለቸሽ ማለት ነዉ...መቼም ማስቲካዉን አይዉጠዉም ቢዉጠዉ ትርፍ አንጀት ይሆንብኛል ብሎ ያስባል...አንቺንም ተፍቶ ቆሻሻ ቦታ ይጥልሻል ለምን ለእሱ እንዳትሆኝ የማስቲካዉ ጠአም ስላበቃ አንቺም ከአንቺ የሚገኘዉ ጠአም ከኒካህ በፊት አልቋል ማለት ነዉ፡፡ ማስቲካ የሰዉ ልብስ ከነካ እኮ በቀላሉ አይለቅም አይደል..አንቺም አንተን አለቅም ያለአንተ መኖር አልችልም ብለሽ ሙጥኝ ብትይ ብታለቅሽ ምን ብትይ..ማስቲካዉ በእጅ ተፈግፎጎ እንደሚለቅ ወይም በነጭ ጋዝ እንደሚለቅ ..አንቺንም በእጁ ወይ ደርግሞ ወይ በተለያየ ዘዴ ያስወግድሻል ተግባባን መጀመሪያ ላይ ክብርን መጠበቅ ጥቅም ለራስ ነዉ፡፡ አንቺ ሂወትሽ የማስቲካ ሂወት እንዲሆን አትፍቀጅለት...ስንቶቻችንን ነን በዚህ የተተፋ ማስቲካ ሂወት እያሳለፍን ያለነዉ???አሁንስ ሳንተፋ እየታኘክን ያለነዉ ስንቶቻችን ነን?? ገና ማስቲካዉ ተገዝቶ ተፈቶ ለመታኘክ የተዘጋጀነዉስ ስንቶቻችን እንሆን??ከዚህ ሁሉ ግን የሚሻለዉ ገና ፓክድ እንደሆነ የተቀመጠዉ ማስቲካ አይሻልም ወይ እህቴ??


የሚገርማችሁ በትምህርት ቤታችን ጎበዝ ናት አላህን ትፈራለች ፀባይተኛ ናቸዉ ብለን የምናስባቸዉ ከእስላምም ከክርስቲያንም የነዚህ ልጆች ሰለባ በጣጣጣጣም ብዙ ናቸዉ፡፡ ሴት ልጅ ተላላ መሆኗ በዉብ ቃላትና ስራ በፈታ አፍ እንደምታምንና ላተቅረቡ ዚና ብሎ አላህ የከለከለንን ፀያፍ ወንጀል ለእነዚህ ዱርየ በሆኑ ልጆች በቀላሉ ክብራቸዉን በቀላሉ የሚያስረክቡ መሆናቸዉን ታዘብኩ፡፡

ለ30 ደቂቃ ለማይሞላ ስሜት ለምን የ30 አመት ፕላናችንን እናበላሻለን??የሴት ልጅ ፕላን አንዴ ከተበላሸ ለመመለስ ከዲፕሬሽን ለመዉጣት ብዙ አመታት እንደሚፈጅ ለምን እንዘነጋለን??
 
  ደግሞም የሚገርመኝ እነዚህ ልጆች መጀመሪያ አካባቢ እነሱ ፍቅር ይጀምሩ እና ሴቶቹ በእጃቸዉ መሆናቸዉን ሲያቁ ይተዋቸዋል....ከዛ ቡሀላ እራሳቸዉ ሴቶቹ እየደወሉ እወድሀለሁ ምን ሁነህ ጠፋህ ??ድምፅህን ሳልሰማ ማደር አልችልም እያሉ ሲያለቅሱ ስልኩን ላዉድ እያረጉ ያሰሙኛል.....

ሴትነት እንደዚህ ነዉ ወይ ??? እላለሁኝ......
እራሳቸዉ ደዉለዉ ዛሬ አንተ ጋር ማደር እፈልጋለሁ እያሉ የሚደዉሉም አሉ ....ልጆቹም ዛሬ አይመቸንም ይሏቸዋል....እባክህ እንደር ብለዉ የሚለምኑም ነበሩ ይሄን ሁላ ለኔ ይነግሩኛል በስልክም ያሰሙኛል፡፡
  
የልጆቹ ስልካቸዉ ዉስጥ የተለያዩ ሴቶች ፎቶ እና አብረዉ የሚያድሯቸዉ ሴቶች video ነዉ የሞላዉ....... ደግሞ የሚገርመኝ ፎቶሽን ላኪልኝ ልብስሽን አዉልቀሽ እያሉ ልብስ እያስወለቁ ሴቶችን ፎቶ ያስልኳቸዉና ፎቶዉን ለጓደኞቻቸዉ ለማሳየት ያስቀምጡታል

ይገርማል ሴቶች እንማራለን እያሉ ትምህርት ይሄዳሉ ግን ትምህርቱ ባለጌነት ስድነት ሁኗል..አሁን ዘመን ተማሪዉ ትምህርት ቤት የሚሄደዉ ላይፍ ለመቅጨት ነዉ እንጂ ተምሬ ያልፍልኛል ቤተሰቤን አሳልፍላቸዋለሁ...ለነገር ለሀገር ለወገን እጠቅማለሁ ብሎ የሚማር ከመቶ አንድ ቢገኝ ነዉ፡፡ ለምን ትምህርት ተምሮም ስራ የለም ...ግን የትምህርት ቤት ላይፍ እየተባለ ብዙ ሴቶች ስንት ሒወታቸዉን የወደፊት ፕላናቸዉን ያበላሻሉ???...., ስንት ሴቶች ራሳቸዉን እንደርካሽ ቆጥረዉ ከሚያረክሱ ወንዶች ጋር በዚህ ርካሽ አለም የረከሰ ተግባር በርካሽ ቦታ በርካሽ የስሜት ነበልባል የወደፊት ሰፊ ህልማቸዉን ዛሬ ላይ ያረክሳሉ፡፡
ጥፋት የወንዶችም ቢሆን ሴቶች መጀመሪያ ፊት ባይሰጡ ባይስቁ ..ወንድ ልጅ ጋር ቅርርብ ባይፈጥሩ...
የሴት ልጅ ሁሉም ገላዋ እፍረተ ገላ ስለሆነ ኢስላማዊ አለባበስ ቢለብሱ ፈጣሪ ያለዉን ትእዛዝ ቢተገብሩ ይሄ ሁሉ ባልመጣ እላለሁ👇👇👇
2024/09/25 14:28:23
Back to Top
HTML Embed Code: