Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ አምስት 1⃣5⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



#ስህተት_አትፈልግ #ከክፍል ➊➍ የቀጠለ
>>>>>ሸማግሌዎች "እሰቲ እሷ ላይ ያየኸው ጥሩ ነገር ካለ ንገረን ?" ብለው ሲጠይቁት
>"ቆንጆ ናት ።
>በእድሜም እኩዮች ነን ።
>ኃይማኖተኛ ናት ።
>ታማኝ ናት ባለሞያ ናት ።
>ልጆች ብንወልድ በጥሩ ሰነ ምግባር አንፃ የማሳደግ ብቃት አላት ።እንዚህ ሁሉ ግን ለኔ መሰረታዊ ነገሮች አይደለም ።አንዲት የቤት ሰራተኛ ልትሰራቸው የምትችላቸው ነገሮች ናቸው ።

#እኔ ወጣት ነኝ ።
☞መጫወት እፈልጋለሁ ።
☞ያለ ምንም ፍራቻና ገደብ ራሷን የምትገልፅልኝ ሚሰት ማግኘት አለብኝ ።
☞እሷም እድሜው የገፋ ሸማግሌ ብታገባ ይዋጣላታል "ብሏል ።

#ልጅቷም_ሰትጠዬቅ
♦"ባለፉት እራት ዓመታት ያህል በየቀኑ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ እሰከ ሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ድረሰ ከእንቅልፍ ጋር እየታገልኩ በስልክ አዋርቸዋለሁ ።እያዋራሁት እንቅልፍ ከጣለኝ ለሳምንት ያህል ይዘጋኛል ።በነዚህ ዓመታት ውሰጥ ጥሩ እንቅልፍ የተኛሁብትን ቀን አላስታውስም ።በእንቅልፍ እጥረት ክብደቴ እሰኪቀንሰና ጤንነቴ እስኪዛባ ድረስ ።

♦ አስተዳደጌ ከእድሜየ በላይ እንዳስብና እንድሰራ እንዲሁም ለቁምነገር ትኩረት እንድሰጥ ቢያደርገኝም ለባል የሚሰጥ ፍቅር ምን እንደሆነ የማላውቅ ገገማ ሴት አይደለሁም ።ብዙ ነገር አውቃለሁ ።በዚሁ መሰረትም እዚያ እያለ ዘወትር እንደምውደው እገልፀለት ነበር ።በቴክሰትም በቃልም ።ደብዳቤ ሳይቀር እጽፍለታለሁ ።ፍቅርን የሚገልፁ ፖስት ካርዶችንና ለጥሩ ትዳር የሚጠቅሙ መፅሐፍትን እየገዛሁ እልክለታለሁ ።ፍቅር ነክ ምስሎችን ከፌስቡክ እየወሰድኩ በቫይበር እልክለታለሁ ።ፎቶ እየተነሳሁ እልካለሁ ።ስጦታዎችንም እልክልት ነበር ።እዚህ በቆዬበት ጊዜም ማድረግ ያለብኝን እንክብካቤ ሁሉ አደርግለት ነበር ።
♦ ከሱ አልፎ ቤተሰቦቹን ለማስደሰት ሰል ከአቅሜ በላይ እሰራለሁ ።ለምሳሌ እሱ ቁጭ ብሎ ወንድሞቹ ቁጭ ብለው ውሰጥ ገብቼ ትልቅ የውሀ ታንከር ያጠብኩበት ቀን አለ ።ይህ ሁሉ ግን በሱ ዘንድ ዋጋ የሚሰጠው ነገር አይደለም ።

#የዚህ_ሰው_መሰረታዊ_ችግር_ምን_እንደሆነ_ታውቃላችሁ ? ስህተት ፈላጊ ነው ።በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ ስህተት ሊባል የማይችለው ነገር እሱ ዘንድ ስህተት ነው ።
#ለምሳሌ ፦
✔ የወላጆቹን ቤት ስራ በሙሉ ብቻየን ስሰራ "ምንም አይደክምሸም አይደል ? ፌሮ ነሽ "ይለኛል ።ፌሮ እያለም ይጠራኛል ።
✔በተቃራኒው ራሴን አሞኝ ወይም ጉንፋን ይዞኝ ትንሽ ከተኛሁ "ተነሽና ስሪ እናቴ ሰርታ ልታበላሸ ነው እንዴ ?"ይለኛል ።
✔ የመቀለድና የመጫዋት ልምድ ስላለኝ ለመቀለድ ስሞክር "ዝም በይ ቀልድ አልወድም "ይለኛል ።
✔ቁምነገር ላይ ብቻ ሳተኩር "ቁምነገር አታብዢ "ይለኛል ።
✔ ብዙ ሞራል የሚነኩና ለኔ የማይገቡ ስድቦችን ሲሰድብኝ ችዬ ዝም ስለው "ሰሜት የለሽም እንዴ ሴት አይደለሽም "ይለኛል ።ተገቢውን መልሰ ሰሰጠው "ኃይለኛና ደረቅ ነሽ ።የሴት ባህሪ የለሽም "ይለኛል ።
✔ በስልክ የፍቅር ቃላትን አታሰሚኝም ይለኛል ።ያንን ለማድረግ ስሞክር "ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘ ? ማን መከረሸ ባክሽ ? ቢሆንም ግን አልቻልሽበትም "ይለኛል ።

ትንሽ ስህተት የተገኘ ጊዜማ ዓለም ይደበላለቃል ።አንድ ቀን የኔን የጉዞ ፕሮሰስ ለመጀመር ወደ አንድ መስሪያ ቤት ሄድን ።ወንድሙ አብሮን ነበር ።ፎርም እየሞላ እያለ አሳስቶ ፃፈ ።"ኸረ ይህ እዚህ ላይ አይደለም የሚሞላው "አልኩት የሰጡን ፎርም መበላሻቱ ሰላሰደነገጠኝ ትንሽ ድምፄን ከፍ ሳላድርግ አልቀረሁም ።ፊቱ ተቀያዬረና አኮረፌ ።
.....ቤት እንዳገባን ትፈለጊያለሽ ተባልኩ ።ስሄድ እናቱና ወንድሙ ቁጭ ብለዋል ሸምግልና መሆኑ ነው ።"ልጁን ከሰው ፊት አዋርደሸዋል "አሉኝ ።
......"ምን አድርጌ አዋረድኩት ሰደብኩት ወይሰ ምን ተናገርኩት ? ስል
...... "ጮክ ብሎ መናገርም ማዋረድ ነው ።ሴት ልጅ ሁሉን አውቀዋለሁ ካለች አትቻልም ።ሁለተኛ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይለምድሸ "አሉኝ ።
...."እሺ "አልኩ ። ይሄ ሁሉ ገጥሞኟል ።እሱ እዚህ በቆዬባቸው ሶሰት ወራት ውሰጥ ብቻ መሆኑን ልብ በሉ ።እውነቴን ነው የምላችሁ ትዳር እንድህ ከሆነ ከነጭራሹ ቢቀርሰ ? ለኔ በብቸኝነቴ ውሰጥ የማገኘው ሰላም ከሁሉም ዓለማዊ ደስታ በላይ ነው "ብላለች ።

ትክክል ናት ጥፋቱ የሷ ሳይሆን የእሱ ነዉ ለምን እሱ ጥቃቅን ስህተት ለቃሚ መሆኑ ነዉ እናም ወንድ ሆይ ከሰዉ ልጅ ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋምና

♦ በቀጣዩ ክፍል እመቤቴ ሆይ አግብተሽ ሌላ ወንድ መመልከት እንደሌለብሽ አይንሽን መስበር እንዳለብሽ እንዳስሳለን


ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ
#ክፍል ➊➏
ይቀጥላል......


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :-አስራ ስድስት 1⃣6⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➓
#ሌላ_ወንድ_አትመልከች

#እመቤት ሆይ!
ከባልሸ ጋር ከመጋባትሸ በፊት ሌሎች የትዳር ጥያቄች ቀርበውልሸ ሊሆን ይችላል ።እነዚያ ጥያቄዎች የቀረቡልሸ
>ከሀብታም ፣
>ከተማረ ፣
>ከመልከ መልካምና
>ልታገቢው ከምትመኚው አይነት ወንድ ሊሆን ይችላል

ከትዳር በፊት እነዚህ ምኞቶች ሊኖሩሸ ይችላሉ ።አሁን ግን አጋርሸን መርጠሽ ቀሪ ህይወትሸን ከሱ ጋር ለማሳለፍ ቅዱሱን የጋብቻ ውል ፈርመሻል ።የቀድሞ ምኞቶችሸንና የቀረቡልሸን የጋብቻ ጥያቄዎች በሙሉ እረስተሽ ከባልሽ ውጪ ማንንም ወንድ አትሰቢ ።

አለበለዚያ ራስሸን ችግር ውሰጥ ትከቻለሸ።ትልቁን የህይወት ውሳኔ ወስነሽ ከገባሸ በኋላ ሌላ ወንድ ማስታወስና መመልከቱ ራሰሸን በማያቋርጥ ስቃይ ውሰጥ ከመክተት ያለፈ ምንም የሚጠቅምሸ ነገር የለም ።

✿ ሌሎች ወንዶችን በምትመለከቺና ከባልሽ ጋር በምታወዳደሪ ጊዜ ያንቺ ባል የሚፈፅማቸውን ስህተቶች የማይፈጽም ወንድ ልታገኚ ትችያለሽ ።
በዚህ ጊዜ ይህ ሰው ፍፁም ነው ብለሸ ልታሰቢና ትዳርሸን አንደ ውድቀት ልትቆጥሪ ትችያለሽ ።ይህን ሰው የባልሸን ያህል ቀርበሽ ሰላላየሸው እንጂ የባሰ ሊሆን ይችላል ።ምክንያቱም ሰዎች ብዙ ጊዜ ከላይ እንደሚታዩት አይደሉም ።


☞ አንዲት ወጣት ከሶስት ዓመት የትዳር ጊዜ በኋላ ቀሰ በቀስ ባሏን አንደማትወደው በመገንዘቧ ጥላው ሰትኮበልል በፖሊስ ትያዝና ፖሊስ ጣቢያ ቀረባ ቃሏን ስትሰጥ ፦"የባለቤቴን መልክ ከሌሎች ወንዶች ጋር ማወዳደር ጀመርኩ ።መልከ ጥፉ ነው ።እሱን ማግባት አንዳልነበረብኝ ተሰማኝ ።
ከዚያም ጥዬው ሄድኩ "ብላለች ።

#እመቤት_ሆይ!
ዘላቂና ያማረ ትዳር ፣የአዕምሮ ሰላምና ጥሩ ህይወት እንዲኖርሽ የምትፈልጊ ከሆነ ባዶ ተሰፋዎችን እርሺ ።ከባልሽ ውጪ ሌላ ወንድ አትመኚ ።
☞እከሌን አግብቼ ቢሆን ኖሮ፣
☞ባሌ እከሌን ቢመሰል ኖሮ ፣
☞የባሌ ስራ ይህ ቢሆን ኖሮ .....
ይህ ቢሆን ኖሮ .......ያ ቢሆን ኖሮ እያልሽ ከማሰብ ተቆጠቢ ።
ራስሸን በእነዚህ እሳቤዎች እስር ቤት ወስጥ በመክተት የትዳርሰሸን መሰረት ለምን ታናጊያለሸ ?

#ለምሳሌ
ከምኞቶችሸ አንዱ እውን ቢሆን ኖሮ አሁን ካለሸ የበለጠ ደስታ ታገኚ አንደነበር እንዴት አውቀሸ ?" እንከን የለሽ "የሚባሉ ባሎች ያሏቸው ሴቶች በባሎቻቸው ተደስተው እንደሚኖሩ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ ? ባለቤትሽ ባንቺ ላይ ያለውን እምነት እንዳያጣ የምትፈልጊ ከሆነ ከሌሎች ወንዶች ጋር መቀላለድና መቀራረብሸን አቁሚ ።

ወንዶች ቀናተኞት ናቸው ።ሌላው ቀርቶ
#ሚስታቸው_የሌላ_ወንድን_ፎቶ_ስታደንቅ_መሰማት_አይፈልጉም ።

✿ አንዲት ሴት ቀጣዩን ታሪክ አካፍላናለች ።ባለቤቴ በጣም ጥሩ ሰው ነበር ።ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አለው ።ውጪ ያለች እህቱም በየጊዜው ገንዘብ ትልክለታለች ።ሁለት ልጆችን ወለድን ቤትም ሰራን የጠየኩትን ሁሉ ይገዛልኛል ተቆጥቶኝ ወይም ከድቦኝ አያውቅም ከመጠን በላይ ይንከባከበኛል ....ነገር ግን ጎልቶ የሚታየኝ በእድሜ የገፋ ሰው መሆኑ ብቻ ነው እሱን ከማያቸው ወጣት ወንዶች ጋር አወዳድረዋለሁ ።
ለኔ በዓለም ላይ እድለኛ ሴት ማለት ወጣት ባል ያላት ሴት ናት የድህነት ኑሮ ብትኖርም፣ባሏም የሚያሰቃያት ቢሆንም ።
ከሱ ለመላቀቅ የተቻለኝን ሁሉ አደርግ ጀመር ።ውሀ ቀጠነ እያልኩ ጧት ማታ በነገር አጠዘጥዘዋለሁ ...አሁኑኑ ፍታኝ እለዋለሁ ።እሱ ግን ሊፈታኝ አይፈልግም "ተይ እባክሽ አንቺም አትለይኝ ከልጆቼም አትለይኝ "አያለ ይማፀነኛል ።
....,እኔ ግን አልሰማውም የራስህ ጉዳይ ነው የምለው በጭንቀት የደም ግፊት ታማሚ ሆነ ።ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ተፋታን ።
.....ህይወቴን አንዳመሰቃቀልሸው ፈጣሪ የተመሰቃቀለ ኑሮ ይስጥሽ ብሎ ረገመኝ ።ምንም አልመሰለኝም ቤቱ ተሽጦ ድርሻዬን ወሰድኩ ።በየወሩ ከደሞዙ እየቆረጠ ለልጆች ማሳደጊያ ብር እንዲሰጥ ተወሰነ ።ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ሞተ ።እኔም ሌላ ወጣት ባል አገባሁና ሁለት ልጆችን ወለድኩ ።በሰላም እየኖርን እያለን ባሌ በድንገት ታመመ ።ከብዙ ስቃይ በኋላም ሞተ ።ገንዘቤ አለቀ ።የቀን ስራ ሰርቼ የቤት ኪራይ ከፍዬ አራት ልጆችን መመገብና ማስተማር አልቻልኩም ።አራቱንም ለተለያዩ ሰዎች ሰጥቼ አረብ አገር ለመሄድ ፓሰፖርት አንዳወጣሁ አረብ አገር ተዘጋ ...ከዛሬ ነገ ይከፈታል ብልም ሊከፈት አልቻለም ።በህገ ወጥ መንገድ ለመሄድም ሞከርኩ ።ከኔ በኋላ የጀመሩ ልጆች ተሳክቶላቸው ሄዱ ሲባል አሰማለሁ ።እኔ ግን ዛሬም ጠብቂ እየተባልኩ አለሁ "ብላለች ።
እናም ባልሽን ከሌላ ወንድ ተመልክተሽ ማወዳደር የትዳር ህይወት ሳይዉል ሳያድር ይናጋል፡፡

💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➊
#የባልሸን_ስህተት_ይቅር _በይ

የሰው ልጅ ይሳሳታል ።በመሆኑም በጥንዶች መካከል ይቅር ባይነት መኖር አለበት ።ይቅር ባይነት ያልታከለበት ትዳር እድሜ አይኖረውም ።ሁለት የንግድ ሸሪኮች ፣ሁለት ጎረቤታሞች ፣ሁለት ጓደኞሞች ፣በተለይ ደግሞ ባልና ሚሰት እርሰ በርስ ይቅር መባባል ይኖርባቸዋል ።በትዳር መካከል አንድ ይቅር የማይልና ስህተቶችን የሚያጋንን ሰው ካለ ቤተሰብ ይበተናል ።ወይም የተበላሸ ህይወት ለመግፋት ይገደዳል ።
#እመቤት ሆይ !
ባልሽ ስህተት ሊስራ ፣
>ሊሰድብሸ ፣
>ሊቆጣሸ ፣
>ሊዋሸሸ
>ሊመታሸም ይችላል ።እነዚህ ድርጊቶች በማንኛውም ወንድ ሊፈፀሙ የሚችሉ ናቸው ።ባለቤትሽ እነዚህንና መሰል ስህተቶችን በመፈፀሙ ከተፀፀተ ይቅር በይው ።ቢፀፀትና ነገር ግን መፀፀቱን በቃላት ለመግለፅ ዝግጁ ካልሆነ ስህተቱን ለማውጣት አትሞክሪ ።ምክንያቱም ይህን ካድረግሸ እሱም ያንችን ስህተቶች ማውጣት ይጀመራል ።ይህ ደግሞ ወደ ጭቅጭቅና ንዝንዝ ያመራችኋል ።ስለዚህ በሰራው ስህተት ራሱን አሰኪወቅሰ ድረሰ ዝም ለማለት ሞክሪ ።

ይህን በማድረግሸ ባለቤትሽ ለባሏና ለቤተሰቡ ደህንነት የምትጨነቅ ብልህ ሚስት እንዳለችው ይገነዘባል ።ስህተቱን ላለመድገምም ይወሰናል ።ሴት ልጅ የባሏን ስህተቶች ይቅር ለማለት ዝግጁ ባለመሆኗ ታላቁ የጋብቻ ውል መፍረስ የለበትም ።


ክፍል ➊➐
ይቀጥላል......
ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ ሰባት 1⃣7⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➋
#ከባልሽ_ቤተሰቦች_ጋር_ተስማሚ

በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ከሚከሰቱት ችግሮች አንዱ በባል ቤተስቦችና በሚስት መካከል የሚፈጠር አለመግባባት ነው:: አንዳድ ሴቶች ከባላቸው እናት እህትና ወንድሞች ጋር ጥሩ ግንኙነት አይኖራቸውም ::ከባል ቤተሰቦች ጋር የማትስማማ ሚስት ሙሉ በሙሉ የባልዋን ትኩረት የእሷን ብቻ ለማድረግ ስለምትሞክር ባል ሌላው ቀርቶ ለእናቱ እንኳን ትኩረት የሚሠጥበት ጊዜ ያጣል::_

〰〰_ _*እናት* ደግሞ የልጃቸውና የሚስቱ አዛዥ መሆን ይፈልጋሉ:: ልጃቸውን ከዚህች ሚስቱ በማላቀቅ እሱን ሙሉ በሙሉ የሚታዘዝ ሌላ ሚስት እንዲያገባ የሚችሉትን ሁሉ ያርጋሉ:: በእስዋ ላይ ውሽት ሊፈጥሩ ይችላሉ ወይም ስህተት መፈለግ ይጀምራሉ :: ይህ አይነት ሁኔታ ለጭቅጭቅና ለጥላቻ በር ይከፍታል

ሁሉም አንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ችግሩ የበለጠ አሳሳቢ ይሆናል ችግሩ የሚፈጠረው በሁለቱ ሴቶች መሀከል ቢሆንም ተጠቂው የሚሆነው ወንዱ ነው ከመሀከል ሆኖ አጣብቅኝ ውስጥ ይገባል::_

〰 *ሚስት* ማንም ሰው ጣልቃ ሳይገባባት በነፃነት መኖር ትፈልጋለች እሱም የእሷን የህይወት አጋሩን ፍላጎት ለማማላትና የትዳር ህይወቱን ማሳመር እንዳለበት ያስባል:: በሌላ በኩል ደግሞ የወላጅ እናቱን ለፍተው ያሳደጉት ቤተሰቦቹ በደከሙ ጊዜ የሱን ድጋፍ እንደሚሹና እነሱን ችላ ማለት አግባብ እንዳልሆነ ይረዳል::ከዚህም በላይ አሁንም ቢሆን አንድ ችግር ቢገጥመው ከቤተሰቦቹ በላይ ቀድሞ ሊደርስለት የሚችል ማንም የለም *ከየትኛው* *መሆን* *እንዳለበት* *ለመምረጥ* *ይቸገራል*::

✿ ምንም እንኳን ከባድ ቢሆንም ከሁለቱም ጋር ተስማምቶ መኖር ይጠበቅበታል:: ይህን ችግር ለማቃለል *ብቸኛው*
መፍትሄዉ በሚስት እጅ ነው ያለው ሚስት ብልህ አስተዋይ መሆን ይኖርባታል
☞አማትዋን የምታከብር
☞ምክራችውን የምትቀበልና
☞ ለሳችው ታዛዥ ከሆነች አይጠሏትም እንደውም የሷ ትልቅ አጋዥ ይሆናሉ:: በመሆኑ ባሏም እፎይታ ያገኛል::

አንድ ሰው በራስ ወዳድነትና ግትርነት ሰውን ከማራቅ *ይልቅ መልካም ባህሪና ትህትህና በማሳየት ብዙ ሰዎችን በመማርክ ነገር ያተርፍል:: በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ሰው የሌሎችን እገዛ የሚፈልጉበት ወቅት ይኖራል ::በተቸገራችሁበትና ሌላው ሰው ፊት በሚነሳችሁ ወቅት የአንቺና የባልሽ ዘመዶች ናችው በፍጥነት ደርሶ አለን አይዞሀችው የሚላችሁ:: ታዳ እነዚህን ሰዎች በመልካም ስነ ምግባራ ቀርቦ ከነ ሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠርስ ምን ይጎዳል?

ከቤተስብ ተራርቆ ከባዕድ ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠርስ ምን ጥቅም አለው? በአብዛኛው ችግር በሚገጥም ጊዜ የልብ ጓደኞች የሚባሉት ሳይቀሩ ይርቃሉ ቤተሰብ ግን ሁሌም ከጎን ይቆማል :: ምክንያቱም በሁለት ዘመዳሞች መካከል ያለው ስጋዊ ቁርኝነት በቀላሉ ሊፍቅ የሚችል አይደልም::
ዘመዶችህ ስጋህን ቢበሉት እንኳን አጥትህን አይወረውሩትም የሚባል አባባል ይህን የሚያጠናክር* *ነው::


✿ አልይ* (ረ.ዐ)አንድ ሰው ያለ ዘመዶቹ መኖር አይችልም የፈለገውን ያህል ሀብትና ልጅ ቢኖረውም ብለዋል:: የዘመድ እገዛ አስፈላጊ ነው በችግር ግዜ ፈጥኖ ደራሽ ዘመድ ነው::ከቤተሰቦቹ የራቀ ሰው ብዙ ነገሮች ያጣል::

〰〰#እመቤቴ #ሆይ !
ለባልሽና ለራስሽ ምቾት ስትይ እንዲሁም ወዳጅና ዘመድ ማብዛት ከፈለግሽ ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ተስማሚ ራስወዳድና ግትር አትሁኚ:: ብልህ ሁኚ ከነሱ ጋር በመናቆር ባለቤትሽን ችግር ውስጥ አታስገቢ :: በአላህም ሆነ በሰዎች ተቀባይነት ይኖርሽ ዘንድ ታጋሽና መስዋት ከፍይ ሁኚ።

ክፍል ➊➑
ይቀጥላል.....
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ



👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ ስምንት 1⃣8⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
8⃣
#ለአሉባልታ_ወሬዎችና_ትችቶች_ቦታ_አትስጥ

አንዳንድ ሰዎች ስለ ሌሎች ሰዎች የሆነ ያልሆነውን የማውራት ልምድ አላቸው ።ይህ መጥፎ ባህሪ >>በጓደኞችና በቤተሰቦች መካከል ጥላቻን ይፈጥራል
>>የትዳር መፍረሰን ያስከትላል ።
>>ነፍስ ያጋድላል ።
>>ለቅናት ፣ጥላቻ ፣ብቀላ ወዘተ ምክንያት ይሆናል ።

እኩይ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ፣የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ ወይም ደግሞ ለሌሎች ተቆርቋሪ ለመምሰል አሉባልታ ወሬዎችን በማምጣት የሰዎችን ሰም ያጠፋሉ ።ይህ ነገር በጎ ከማሰብ የሚፈፀምበት ጊዜ በጣም አናሳ ነው ።ስለዚህ ብልጥና ጎበዝ ወንድ ለእንዲህ አይነት ወሬ ቦታ አይሰጥም ።በሰማው ነገር ከመታለሉና ተዕጽኖ ውሰጥ ከመውደቁ በፊት የወሬውን እውነታነት ይፈትሻል ።በተለይ እናቶቻቸው እህትቻቸውና ወንድሞቻቸው ብዙ ጊዜ ከሚስታቸው ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንደማይኖራቸው ወንዶች ልብ ሊሉ ይገባል ።


♠ አንዳንድ ሰዎች ስለ ሌሎች ሰዎች የሆነ ያልሆነውን የማውራት ልምድ አላቸው ።ይህ መጥፎ ባህሪ
✔በጓደኞችና በቤተሰቦች መካከል ጥላቻን ይፈጥራል
✔ የትዳር መፍረሰን ያስከትላል ።
✔ ነፍስ ያጋድላል ።
✔ለቅናት ፣ጥላቻ ፣ብቀላ ወዘተ ምክንያት ይሆናል ።


እኩይ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ፣የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ ወይም ደግሞ ለሌሎች ተቆርቋሪ ለመምሰል አሉባልታ ወሬዎችን በማምጣት የሰዎችን ሰም ያጠፋሉ ።ይህ ነገር በጎ ከማሰብ የሚፈፀምበት ጊዜ በጣም አናሳ ነው ።
#ስለዚህ ብልጥና ጎበዝ ወንድ ለእንዲህ አይነት ወሬ ቦታ አይሰጥም ።
>>> በሰማው ነገር ከመታለሉና ተፅእኖ ውሰጥ ከመውደቁ በፊት የወሬውን እውነታነት ይፈትሻል ።በተለይ እናቶቻቸው እህቶቻቸውና ወንድሞቻቸው ብዙ ጊዜ ከሚስታቸው ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንደማይኖራቸው ወንዶች ልብ ሊሉ ይገባል ።

♦♦ አንድ ወንድ ከጋብቻ በፊት ብዙ ጊዜያችን ከወላጆቹ ጋር ያሳልፋል ።እሱን ለማሳደግ ብዙ ውጣ ውረድ ያሳለፉ ወላጆቹ እድሚያቸው በገፋ ጊዜ አጋዥ እንዲሆናቸው ይፈልጋሉ ።ልጃቸውን ድረው ለብቻው እንዲኖር ነፃነት ከሰጡት በኋላ እንኳን ቢሆን ለነሱ ምኞትና ፍላጎት ተገዥ እንዲሆን ይፈልጋሉ ።ከሚስቱ ይልቅ ለነሱ ትኩረት እንዲሰጥ ይሻሉ ።

#ነገር_ግን በተጨባጭ ሲታይ ወንድ የትዳር ህይወት በሚጀምርበት ጊዜ ለአዲሱ ቤተሰቡና ሚስቱ ደህንነት ነው ከፍተኛ ጥረት የሚያደርገው ።ለቤተሰቡ ይሰጥ የነበረውን ፍቅር ለሚስቱ ይሰጣል ።ተግባሩም ከሚስቱ ፍላጎት አንፃር ይወሰናል ።በዚህ ወቅት ከቤተሰቦቹ ጋር ያለው ግኑኝነት እየላላ ይሄዳል ።

#በዚህ_ነገር በተለይ እናትና እህቶቹ በጣም ይበሳጫሉ ።
✔ አዲሷን ሙሽራ ልጃቸውን ከነሱ ለመለየት የመጣች ሰይጣን አድርገው ይቆጥሯታል ።
✔ እናቶች አንዳንዴ ጊዜ ይህን ስጋት ለመቅረፍ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ልጃቸው ለሚሰቱ ያለውን ፍቅር መቀነስ እንዳለባቸው ያስባሉ ።
በዚህ መሰረትም
☆የሷን ጉድለቶች መፈልግ ፣
☆ስለሷ ውሸት መንዛት ፣
☆ስሟን ማጥፋት ወዘተ ይጀምራሉ ።ባል በቀላሉ የሚቀበል ከሆነ ከእናቱ ወሬ ተፅዕኖ ውሰጥ ይወድቃል ።ከሚስቱ ጋር ያለው ግንኙነት ይበላሻል ።ሚሰቱን መጨቅጨቅና ሰህተቷን መፈልግ ይጀምራል ።በየአጋጣሚው ሁሉ ያንቋሸሻታል ።በመጨረሻም የጥንዶቹ የትዳር ህይወት ይቃሳወል ።በዚህ ወቅት ሚሰት ራሷን እንደ ማጥፋት ያሉ መጥፎ እርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለች ።


♦♦ አንዲት አዲስ ሙሽራ በተዳረች በሳምንቷ ቁርጥራጭ ብረቶችን ትውጣለች ።በቀዶ ጥገና ብረቶቹ ከወጡላት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የሚከተለውን ተናግራለች ።
~~~ በቅርቡ አገባሁ ,,,,ወደ ባሌ ቤት ስገባ እንደማንኛውም ሙሽራ ደስታዬ ወደር አልነበረውም ።ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ ባለቤቴና እህቱ በሆነ ባልሆነው ይጨቀጭቁኝ ጀመር ።ሁኔታቸው ህይወት አሰቸጋሪ እንድትሆንብኝ አደረገኝ ።በመጨረሻም ራሴን ለማጥፋት በመወሰን ብረቶቹን ዋጥኩ "ብላለች ።

♦♦ "አንዲት በባሏ ወንድሞች ትችት የተማረረች ሴት ራሷን በእሳት በማቃጠል ገድላለች ።

♦♦""የባሏ እናት መጥፎ ባህሪ የማረረት ሌላዋ ሴትም ራሷን አቃጥላለች ።

ስለዚህ
☞ የባል ቤተሰብ ትችት ፣
☞መጥፎ አመለካከትና
☞ስም ማጥፋት በጣም አደገኛ ነገሮች በመሆናቸው ወንድ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ።በእርግጥ ሰዎች በተለይ ደግሞ ወላጆች ሰለ አንድ ነገር በሚያወሩበት ጊዜ አታውሩ ብሎ ማስቆም አሰቸጋሪ ነው ።ነገር ግን ይህን መሰሉን ወሬ በሚጀምሩበት ጊዜ በተቻለ መጠን ሌላ ርዕሰ እየፈጠሩ ወደ ሌላ አጀንዳ ማስቀየስ ይቻላል ።


በሚስቱ ላይ ትችት የሚያቀርቡት ከተቆርቋሪነትና ጥሩ ከማሰብ ሳይሆን
>> ከቅናት
>>ጥላቻና
>>ራስ ወዳድነት መሆኑን ልብ ሊል ይገባል ።ሚስት ትኩረት ሁሉ ወደሷ ሰለምትሰብ በሷ ላይ የጥላቻ ሰሜት ያድርባቸውና ይህን ፍቅር ለመቀነስ ሲሉ የሚጠቀሟቸው ዘዴዎች ናቸው ።


ክፍል ➊➒
ይቀጥላል
ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

Join👇👇👇
@Islam_and_Science
የወጥ ጅል ይደፋል፣የሰዉ ጅል ያኮርፋል
✍አሚር ሰይድ


የወጥ ጅል ከሆነ ጣዕም ከሌለዉ ይደፋል በተዘዋዋሪ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ሀሳብን በተሻለ በሀሳብ መሻር እየቻሉ ለማኩረፍና ለመስደብ የቻሉትን ሀይል ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ ግን ሰዉ ስድብ እና ወቀሳ ቀረርቶ ፈርቶ ወደፊት መራመድ እና ሀቅ መናገር ማቆም የለብትም ብየ አስባለሁ፡፡ በተዘዋዋሪ ደግሞ የሰዉ ልጅ ነኝ እሳሳታለሁ ከተሳሳኩ ደግሞ በአሳምኝ ምክንያት አስተካክላሁ፡፡

✿ እህቶቼ ሆይ ይሄን መረጃ እስከ አሁን ታቃላችሁ ??
በአለም ላይ 7.8 ቢሊየን ህዝብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ
✔ 5.6 ቢሊየን ሴቶች ሲሆኑ
✔ 2.2 ቢሊየን ደግሞ ወንዶች ናቸዉ
ሴቱ ከወንዱ 3.4 ቢሊየን ጭማሪ አለ ማለት ነዉ፡፡

ከ2.2 ቢሊየን ወንዶች ዉስጥ
☞ 1 ቢሊየኑ ባለትዳር ሲሆኑ
☞ 130,000 የሚሆኑት እስር ቤት ናቸዉ
☞ 70,000 እብድ ናቸዉ አላህ ወደ አቅላቸዉ ይመልሳቸዉ

♦ አሁን ባለንበት ዘመን ለማግባት ዝግጁ የሆነዉ ወንድ 1 ቢሊየኑ ብቻ ነዉ፡፡

ከ1 ቢሊየኑ ዉስጥ
✔ 50% ቤተሰብ ጋር የሚኖር ነዉ
✔ 35 % ወንድ ከ66 አመት በላይ ናቸዉ፡፡
✔ 7% ደግሞ ዘመድ አዝማድ ናቸዉ፡፡
✔3% የካቶሊክ ቄሶች እና ገዳም የገቡ ናቸዉ
✔5% ደግሞ ግብረ ሰዶም ናቸዉ

እናም 35+7+3+5= 50% ሆነ ማለት 1ቢሊየኑ ዉስጡ ግማሹ አምስት መቶ ሚሊየኑ ወንድ አሁን ላይ ለማግባት ብቁ አይደለም ማለት ነዉ፡፡

♦ 50% ከቤተሰብ ጋር አብሮ የሚኖረዉ>>> በሰዉ ሀሰባ አዳሪና በሙቅ ዉሀ ታጣቢ አንድ ነዉ ትዳር ትዝ የማይለዉ አለ በተዘዋዋሪ ደግሞ ለትዳር ትንሽ ሀሳብ ያለዉ አለ ፣ስራ የሌለዉ ፣ተምሮ የተቀመጠ ማስታወቂያ በማንበብ የሚያሳልፍ አለ ፣ቦዘኔ ቃሚ አጫሽ አለ፡፡ እናም ይሄ ሁሉ አንድ ላይ ሁኖ አምስት መቶ ሚሊየን ናቸዉ እንበል ይሄ ደግሞ ሂሳብ ሲሰራ

☞ 4.6 ቢሊየን ሴት ለአምስት መቶ ሚሊየን ሲካፈል አንድ ወንድ ለስምንት ሴት ማለት ነዉ

☞ በተጨማሪ ከአምስት መቶ ሚሊየኑ አሁን ላይ ለትዳር በአቅም በኢኮኖሚ ብቁ የሆነዉ ወንድ ሶስት መቶ ሚሊየኑ ነዉ፡፡ እናም 4.6 ቢሊየን ለ300 ሚሊየን ሲካፈል
አሁን ላይ ለማግባት ብቁ የሆነ አንድ ወንድ 13 ሴቶችን ይሆናል ፐርሰንቱ

☞ Total ስንሰራዉ ደግሞ 5.6 ቢሊየን ሴት ፣2.2 ቢሊየን ወንድ ከሆነ ቢያንስ በአለም ላይ ያለ የሁሉም ሀይማኖት ተከታይ አንድ ወንድ ለሶስት ሴት ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

☞ የአገባዉ ወንድና ሴት 2ቢሊየኑ ተቀንሶ አቅም ያለዉ ለማግባት ዝግጁ የሆነዉም ያልሆነዉም ወንድ አንድ ላይ ሂሳብ ሲሰራ 4.6 ቢሊየን ሴት
ለ1 ቢሊየን ወንድ ሲሰላ ..በአለም ላይ ያለዉ ወንድ አንድ ወንድ አራት ሴት ይሆናል ፐርሰንቱ

♦ ሴቶች ሆይ !!!! እባካችሁ ብልጥ ሁኑ የምንሰማዉ የምናየዉ ነገር ወንዶች ወደ ዚና እንዲሄዱ ሰፊ መንገድ እየከፈተ ነዉ ፡፡

ይሄን እንድፅፍ ጥናቱን ለማቅረብ ያሰብኩት ..ትናንት አንድ ጓደኛየ ለትዳር የሚያወራት ልጅ መኪናና እና ቤት ከሌለህ አላገባህም ብላ በሪከርድ ልካለት ካዳመጥኩ ቡሀላ ገርሞኝ ነዉ፡፡ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መቀንጠሷ አሉ፡ልጅቱ 10 ክፍል ተማሪ ነች ልማር አላለችም..ትምህርት ቤቶች አላማ እቅድ ለሌላቸዉ ሴቶች ለወደፊት የማይፈታ ከባድ ተፅእኖ እና የማይፋቅ ጠባሳ በእህቶቻችን ላይ እየፈጠሩ ነዉ ፡፡ እኔ በአማረኛ ፊልም ላይ ሴቶች ይላሉ ሲሉ እሰማለሁ እኔ አማረኛ ፊልም ስለማልወድ አልሰማሁም ግን በtg የተላከ አዳምጬ በጣም ገርሞኛል፡፡ ቆይ ይቺ የ10ክፍል ተማሪ መኪና ያለዉ ወንድ አንቺን ነዉ የማገባዉ ግን ከትዳር በፊት አንቺ ጋር ዚና መስራት እፈልጋለሁ ብሎ ቢጠይቃት እምቢ የምትልበት ምን ሞራል አላት??

#ነገር_ግን ሁሉንም ሴት አይወክልም መስፈርት የማያበዙ እንቁ እህቶች ብዙ ናቸዉ፡፡ ቢሆንም አንዳንድ የዋህ በዉበት የሚያስቡ ሴቶች መስፈርት ብዙዎች ብር ያለዉ ባል ቢሆን ምርጫቸዉ ነዉ፡፡

ብዙ ቆንጆ ሴቶች መኪና ቤት ያለዉ እያሉ ብር አይተዉ ከትዳር በፊት በሚሰሩት ሀራም ስራ ተከዳሁ ሸወደኝ እያሉ የተለያየ ወንድ በዚህ ሽወዳ የሚጎዱ አሉ፡፡
አንድ የማቃት በጣም ቆንጅ ልጅ እኛ ሰፈር አለች እንደዚሁ መኪና ያለዉ ቤት ያለዉ ነዉ የማገባዉ እያለች ብዙ ትዳር ስትመልስ አንድ መኪና ያለዉ የሷን መስፈርት ስላወቀ በዛ በዚህ ብሎ በሀራም ካሰለፉ ቡሀላ እንደ ማስቲካ ይተፋታል ፡፡ አንድ ቀን እንደ ቀልድ HIV ስትመረመር በደሟ ተገኘባት፡፡ በመናደድ ወንድን ማመን እያለች ብዙ ወንዶችን አዉቃ እየቀረበች እሷ ጋር ዚና እንደሰሩ ሰማሁ፡፡ ግን አሁን ሌላ ከተማ ለመኖር ሂዳለች ፡፡ እዛስ ስትገባ ስንቱን በክላ ይሆን??

♦ አንድ ጓደኛየም ሊያገባ ከጨረሰ ቡሀላ ቤት ተከራይቶ ሲያሳያት ወይ ኮንዶሚኒየም ወይም ግቢ ቤት ካልሆነ ትዳሩ ይቅርብኝ ያለችም እህት ስለገጠመኝ ነዉ፡፡

#እህቶ_ሆይ
ዉበት ወጥመድ ነዉ ..በሂደት ሲረግፍ እድሜም ሲገረድፍ ከመፀፀት እና ሁላችሁም ሴቶች ትዳርን እንደ ቀልድ አርጋችሁ ...ልሰብበት፣ ልማር ፣ገና ነኝ፣እህቴ አላገባችም፣ልጅ ነኝ እያላችሁ በሀላል የመጣን እያከላከላችሁ
እንደ ወንድሜ ነዉ የማይህ እያላችሁ ነገር አታራዝሙ፡፡ ለእሱ እህቱ የእናት አባቱ ልጅ ብቻ ነች😊


እናም ዉድ እህቴ...እድል እንደ ፀሀይ ጮራ ነዉ ጠዋት በርቶ ማታ የሚጠፋ ለሁሉም ነገር እድል አለ ...እድል ካለፈ አለፈ ነዉ እናም ብዙ ሸርጥ አታብዙ ትዳር ቀላል ሆነ ሳለ በእናንተ ሸርጥ ማብዛት ወንዱ ትዳርን እየፈራ ነዉ እናም የትዳር ጥያቄ ሲመጣ ዛሬን ሳይሆን ነገን በማሰብ አብሮ መኖር መቀየር እየተቻለ የሀላልን በር አትዝጉ፡፡

አሁን ላይ አንድ ወንድ ሀላል ፈላጊ ከሆነ ሴቶቹ ለቁም ነገር ምፈልግሽ ሲባሉ ወላሂ በጣም ግራ እያጋባ ነዉ፡፡ የሌላትን አመል ነዉ የምታመጣዉ ... ለሀላል ሲደክም ማግኘት አልቻለም ፡፡ ግን ወንድም እህት እንሁን እንጠናና ነዉ እያሉ መጀመሪያ ምሽግ ቆፋሪ ሁነዋል፡፡
የሚገርመኝ የሴቶች ፀባይ አለ ሲቀርቧቸዉ ይሸሻሉ ..ወንድየዉ ቆርጦ ትቅርብኝ ብሎ ሲሸሻት ደግሞ ትቀርበዋለች የዋሁ እንደገና ይሄን ነገር በሀላል ጎጆ እንቀልስ ሲላት እኔ እኮ እንደ ወንድሜ ነዉ የማይህ ትላለች ..ግራ ገባን እኮ እየፈለገች እየወደደች ግን ሴቶች እኔን ያገኘኝ አመት ወይ ሁለት አመት ለምኖኝ ነዉ ብለዉ ለጓደኞች ማዉራት ይፈልጋሉ፡፡ አሁን በሒወት ያለን ወንዶች በጣም ግራ ተጋብተዋል ጎበዝ
☞ ሴቶች መቼም እንስሳ ሲታረድ ሽንፊላ የሚባል አለ..ሽንፊላዉ ቢታጠብ ቢታጠብ ጠራ ሲባል ሲገለጥ ደግሞ ሌላ የሚታጠብ አለዉ ..ሽንፊላን አጥቦ ለማጥራት በጣም ጊዜ ይፈጃል አይደል .አሁን ዘመን ላይ ያሉ ሴቶች ፀባይ እንደሽንፊላ እየሆነ ነዉ ወንዱ ይሄን አስተካከልኩ ሲል የትዳር ደረጃዉን ሲወጣ ወደ ታች የሚያንሸራትት ሌላ መዘዝ ጣጣ ታመጣላችሁ ፡፡ግን 80% ሴቶች ትዳራቸዉን የሚያበላሹት በጓደኛና ባላገባች እህቷ ምክንያት ነዉ፡፡በተለይ ታላቅ እህትሽ ካላገባች ስለትዳር ታላቅ እህት ማማከር ጥሩ መስሎ አይታየኝም

አንዱ የሴቶች ባህሪ ግራ የገባዉ ስትሄድ ስመጣ ስወደዉ ስትጠላዉ እንዲህ አለ

ዶሮ ዉሀ ጠምቶት ተንጋሎ ይጠጣል
ሰዉ ከተራራቀ መረሳት ይመጣል
እየራኳት ሄድኩኝ አዉሬ እንዳባረረዉ
ስወጂኝ ስትጠይኝ አረ እንዴት ልሁነዉ? ብሏል

የዛሬ መልዕክቴ ነዉ. መልካም ጁምአ 🌹

አስተያየት ካለ በፁሁፉ ላይ የሚስተካከል በዚህ አስተያየት መስጠት ይችላሉ
👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ ዘጠኝ 1⃣9⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


ከባልሽ ቤተሰብ ጋር ተስማሚ ከክፍል ➊➐ የቀጠለ



#እመበቴ_ሆይ
ብልህ ሁኚ ከነሱ ጋር በማናቆር ባለቤትሸን ችግር ዉስጥ አታሰገቢ ።በፈጣሪም ሆነ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይኖርሸ ዘንድ ታጋሽና መሰዋዕት ከፋይ ሁኚ ።

በእናትና በልጅ መካከል ያለው ትስስር ምን ድረሰ አንደሆነ ማውቅ የተሳናት ሚሰት ከሞቀ ትዳሯ አንዴት ተፈንቅላ አንደነበር አንዲህ ተርካልናለች ።
✿ "ከባለቤቴ ጋር ተጋብተን በሰላም እየኖርን ነበር ።በመሀል እናቱ በጣም ታመሙ ።ከብዙ ስቃይ በኋላ ተሻላቸው ባለቤትቴም "ከዚህ በኋላ እናቴ ብቻዋን መኖር የለበትም ።እንክብካቤና ክትትል ሰለሚያሰፈልጋት እኛጋ መምጣት አለባት "አለኝ ።እሳቸውን መንከባከቡ ሰለከበደኝና ነፃነት ያሳጡኛል ብዬ ስላሰብኩ "አይሆንም መኖር ያለባቸው እህትህ ጋር ነው "አልኩት ።
......እሱም "እኔ እያለሁ እናቴ አማች ቤት አትገባም ። የእህቴ ባል ደስ በይለውሰ ?"አለኝ ።"እንግዲያውስ አኔም ደስ አይለኝም ።የኔም ፍላጎት መከበር አለበት "አልኩት ።"ለምንም ?አለኝ ።
....."እሳቸው እዚህ ከሆኑ ነፃነት አይኖርም "አልኩት
......"ትምጣና ለጥቂት ጊዜ እንያት የምታሰቸግረን ከሆነ ትሄዳለች "አለኝ
...... አንዴ ከገቡ የሚወጡ ስላልመሰለኝ "አልፈልግም ወይ እኔን ወይ እናትህን ምረጥ አልኩት ።
.....ምንም ብወድሸ ከእናቴ አላሰበልጥሸም መሄድ ትችያለሽ "አለኝ ።
በምድር ላይ እንዳንቺ የምወደው ሰው የለም ሲለኝ እንዳልነበረ አሁን በአንዴ ምንም ብወድሸ ከእናቴ አላሰበልጥሸም ማለቱ በጣም አናደደኝ ።ልብሴን ሰብሰቤ ቤተሰቦቼ ቤት ሄድኩ ።ጉዳዩን ያጫውትኳቸው ሰዎች ሁሉ ትልቅ ስህተት አንዳሰራሁ ይነግሩኝ ጀመር ።"ምን ነካሽ እንዴት ከእኔና ከእናትህ ምረጥ ትይዋለሸ?? በጭራሽ እንዲህ አይባልም እንዴት እሱን ወደሸ እናቱን ትጠያለሸ ?"ይሉኛል ።በተለይ አንዲት የእናቴ ጓደኛ መጥፎ ባህሪ ከላቸው አማታቸው ጋር አንዴት በሰላም እንዲኖሩና ብልህ ከሆንኩ እኔም ከባሌ እናት ጋር በፍቅር መኖር እንደምችል ረጂም ሰዓት ወሰደው መከሩኝ ።በሰራሁት ጥፋት አብዝቼ መፀፀቴን የሚገልፅ ደብዳቤ ፅፌ ሰጠሁት ።ይቅርታዬን ተቀበለውና ወደ ቤት ተመለስኩ ።

እማማ ቤታችን መጡ ።በአሳችው ምክንያት ጥዬው መሄዴን ሰምተዋል ።ጥፋቴን ማካካስ ስላለብኝ በጣም እንከባከባቸው ጀመር አንዴ ከጠሩኝ ሁለተኛ ሳይደግሙ መሄድ አለብኝ ።ምግብ አየቀያየርኩ እየሰራሁ እሰጣቸዋለሁ መድኃኒታቸውን በሰዓቱ እንደወሰዱ አደርጋለሁ ገላቸውን አጥባቸዋለሁ ሌሊት ከእንቅልፌ ስነቃ ሂጄ አያቸዋለሁ እንቅልፍ ላይ ከሆኑ ፀጥ ብዬ እመለሳለሁ ከነቁ ደግሞ አይዞዎት ምን ይፈልጋሉ??እላቸዋለሁ ።ይሄን ሁሉ አያደረኩም ካሁን ካሁን ያማርሩኛል ብዬ ስለምፈራ አልረካም ።አሳችው ግን በጎ ምላሽ አያሳዩኝ መጡ ።
......አንቱ ስትይኝ ያራቅሸኝ ስለሚመስለኝ አንቺ በይኝ አሉኝ ።በሰሜ መጥራት ትተው "መልካም "የሚል ስም አወጡልኝ ።አኔም አንቱ ማለትን ተውኩ ።"ፈጣሪ በስከ ማታ የሰጠኝ ገፀ በረከት ነሽ "ትለኛለች ።ሊጠይቃት ለመጣ ሰው ሁሉ "መልካሜን አመሰግኑልኝ ።እሷ ናት ህይወቴን ያሰረዘመችው "ትላለች ።ባለቤቴም ሌሊት መነሳቱን እንድተውና ራሴን አብዝቼ ማድከም እንደሌለብኝ ይነግረኛል
.....አኔ ግን አልቀበለውም አልፎ አልፎ ልጇ መጥታ ትወሰዳታለች እዚያ የምትቆየው ግን በዛ ከተባለ ሶሰት ቀን ነው ቶሎ መልሱኝ ትላለች "እማዬ ምን አጎደልኩብሸ እባክሽን ትንሽ ቆይ "ስትላት "ምንም አላጎደልሸብኝም ግን መሄድ አለብኝ እዚህ ቤት ስመጣ እንቅልፍ አይወሰደኝም"ትላለች
.....አድርሰውት ሲሄዱ "እማ ልጅሽን እኮ አያሰከፋሻት ነው ለምን ትንሸ አልቆዬሸም ፣እውነት እዚያ ስትሄጂ እንቅልፍ አይወስድሸም አንዴ ?"ስላት "መልካምዬ አውቄ እኮ ነው እንቅልፍ አይወሰድኝም የምለው አለዚያ አይልኩኝማ በምን ላመካኝ?? ትያለሽ እነሱ አኔን ለማስደሰት ደፋ ቀና እያሉ አኔ እማስበው ወደዚህ የምመጣበትን ሰዓት ነው ።ሂጂ ሂጂ የሚለኝ ነገር አለ "ትለኛለች ።
....... "ምኑ ነው ሂጂ ሂጂ የሚልሸ "ስላት "
......ተይኝ አስቲ አያወቅሸው ምኑን ልንገርሽ ትለኛለች ።"
.......አረ እኔሰ አላውቀውም ኝገሪኝ ስላት
..... ደግነትሸ ነው ትለኛለች ።እውነት ለመናገር እኔም እሷ ከሌሎች ቤቱ ቤት አይመስለኝም ።አትሄድም ለማለት አያፈርኩ ነው አንጂ ከቤት ባትወጣ ደስ ይለኛል ።ባለቤቴ ትንሽም ቢሆን ከተናገረኝ ታኮርፈዋለች ።
...."እማዬ ይሄን ጥፋት ሰላጠፋች ነው የተናገርኳት "ሲላት "ይሄ ጥፋት አይባልም ።"ትለዋለች ።
....."ታድያ ጥፋት ማለት ምንድነው ነው ?"ሲላት "ከትዳር ላይ መባለግ ፣ባል ለፍቶ የሚያመጣውን ገንዘብ አላግባብ ማባከን ...እያለች ከባባድ ነገሮችን ትዘረዝርለታለች ።በዚህ መልኩ ለብዙ ጊዜያት አብረን ኖረናል ።
በሞት እስክትለየን ድረስ ስትሞት በጣም ነው ያዘንኩት ምክንያቱም እሷ የትዳሬ ምሰሶ ነበረች ።በእርግጥ አሁንም ናት ምክንያቱም ለሷ ያደረግኩት እንክብካቤ በባለቤቴ ልብ ውሰጥ ዘላለማዊ ክብር እንድጎናፀፍ አድርጎኛል አንዳንድ ሴቶች በባላችን እናት ወይም በአህቱ አለያም በወንድሙ የተነሳ ትዳራችን ተበጠበጠ ሲሉ ስሰማ በጣም አናደዳለሁ ።ይህ የሚስቶች ትልቁ ድክመት ነው ብዬ ነው የማስበው ።

ብልህ ሴት የባሏን ቤተሰቦች በቁጥጥሯ ስር ማድረግ ትችላለች ።የቱንም ያህል መጥፎ ባህሪ ቢኖራቸው ።እንዴት ከተባለ ገደብ የለሽ ፍቅር በመሰጠት ።ፍቅር የማያሸንፈው ነገር እንደሌለ አምናለሁ ።

☞ አንዲት ልጅ የባሏ እናት "አንደማይወዷት ነገረችኝ ።"አንዲወዱሸ ምን ጥረት አድርገሻል ?"ስላት "ገንዘብ ከሆነ ልጃቸው ባለ ሀብት ነው ከሚፈልጉት በላይ ይሰጣቸዋል"አለችኝ ።"እሱ ከልጃቸው ነው አንቺ በግልሸ ምን ታደርጊላቸዋለሸ ?"ስላት "ለምሳሌ ሁሌ በበዓል እሳቸው ጋር ነው አራት የምንበላው ።ከዛ ውጪ ከታመሙ ሄጄ እጠይቃቸዋለሁ "አለችኝ ።
......"በቃ ይሄው ነው ?"አልኳት
........"አዎ ማወቅ ያለብሽ ያገባሁት ልጃቸውን ነው እሱን በደንብ ከተንከባከብኩላቸው ምን አነሳቸው ?"አለችኝ ።
......እኔ የባሌ እናት የምትወደኝ አንዲህ አንዲህ አደርግላት ስለነበር ነው ብዬ ሰዘረዝርለት ጭንቅላቷን ይዛ "አኔ አልችልም ።አንቺ ጠንካራ ሴት ነሽ ።አኔ ከምትነግሪኝ ነገር ውስጥ ሩቡን አንኳ ማድረግ አልችልም ትል ጀመር።

ክፍል ➋ዐ ይቀጥላል....

Join👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ 2⃣0⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➌
#ከባልሽ_ስራ_ጋር_ተስማሚ

እያንዳንዱ ሰው ስራ ይኖረዋል ።ስራዎች ደግሞ ይለያያሉ ።
#ለምሳሌ
☞ሹፌር ብዙ ጊዜውን የሚያሳልፈው መንገድ ላይ ነው ማታም በጊዜ አይገባም ።
☞ፖሊስ ምሽቶችን ከቤት ውጭ ማሳለፍ ይኖርበታል
☞ የህክምና ባለሙያ ከቤተሰቦቹ ጋር የሚያሳልፈው ሰዓት በጣም ጥቂት ነው ።
☞የምርምር ሰዎች በምሽት ብዙ ሰዓት ያነባሉ
☞የመካኒክ ልብስ ቶሎ ቶሎ ይቆሽሻል ።
☞ የፋብሪካ ሰራተኛ በምሽት ይሰራል ወዘተ

ስለዚህ ከቤተሰብ ፍላጎት ጋር ተስማሚ የሆኑ ስራዎች የሚገኙት አልፎ አልፎ ነው ።መስራት ደግሞ የግድ ነው ።ምክንያቱም ሰርቶ በሚያገኙት ገንዘብ ከመተዳደር የሚሻል ነገር የለም ።

✿ ወንዶች ከስራቸው አሰቸጋሪ ባህሪያት ጋር መላመድ ሲችሉ ቤተሰብ ግን ይህን መቀበል ሲያቅተው ይታያል

✿ሴቶች ብዙ ጊዜ የባሎቻቸው ስራ በአቅራቢያቸው የሚገኝ ፣ደህና ክፍያ ያለውና በቀን ብቻ የሚሰራ አንዲሆን ይፈልጋሉ ።ከባሎቻቸው ጋር ወጥተው ለመዝናናትም ሆነ አብረው ለማውራት በቂ ሰዓት እንዲኖራቸው ይሻሉ ።
ነገር ግን የብዙ ወንዶች ስራ ከሚስቶቻቸው ፍላጎት ጋር አልጣጣም ሲል ይስተዋላል ።ይህ ደግሞ ለአንዳንዶች ትዳር የግጭት መንሰኤ ይሆናል ።

ብዙ ጊዜያትን በመንገድ የሚሳልፍ ሾፌር ባል በወቅቱ ቤት ገብቶ መተኛት ፣ምግብ በሰዓቱ መመገብ አይችልም ።ደክሞት ወደ ቤት ስለሚገባ ከቤተሰቡ ሰላምና ረፍት ማግኘት ይፈልጋል ።አንዳንድ ሚሰት ግን ገና እንደገባ ነገር ትጀምራለች ።"ይህ ምን ኑሮ ይባላል ?አነዚህን ልጆች ብቻየን ነው አያሳደኩ ያለሁት ።ልታግዘኝ አልቻልክም ።ሁሉንም ነገር ብቻየን ነው የምወጣው ።ልጆችህ ምርር አድርጎኛል ።ሾፌርነት ጥሩ ስራ አይደለም ።ስራ ቀይር ወይም ከኔ ጋር ያለህን ጉዳይ ጨርስ።በዚህ መልኩ መቀጠል አልፈልግም "በማለት ታማርረዋለች ።

የዚህ አይነት ጨቅጫቃ ሚሰት ያለው ሾፌር ባል ሰራውን በትክክል ሊሰራ አይችልም ።"ዛሬ ደግሞ ምን ትለኝ ይሆን ?"አያለ ሲጨነቅ የራሱንም ሆነ የተሳፋሪዎችን ህይወት አደጋ ውሰጥ ይከታል ።

♦ በቀን በርካታ ህመምተኞችን የሚያስተናግድ ዶክተርም እንዲህ የሚስቱን ንዝንዝ ተቋቁሞ አንዴት ብሎ ነው ህክምናውን በትክክል ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችለው ?ጨቅጫቃ ሚሰት ያለው የማታ ሽፍት ሰራተኛ ሰራውን በትክክል አይሰራም

♦ አንድ ተመራማሪ ሚሰቱ ሁሌ የምታማርረው ከሆነ በተሰማራበት የጥናት መስክ ውጤት ሊያስመዘግብ አይችልም ።ሚሰት ለባሏ ስኬት የምታደርገው አሰተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ።በነዚህ እገዛዎቿ ነው ብልህ ሚስትን ከአላዋቂዋ መለየት የሚቻለው ።

#እመቤት ሆይ !
ዓለምን በኛ ፍላጎት መሰረት ልናንቀሳቅሳት አንችልም ።ይልቁንም ራሳችንን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማላመድ መቻል አለብን ።ባበለቤትሸ ቤተሰብን ያስተዳድር ዘንድ ገንዘብ የሚያገኝበት ስራ ያስፈልገዋል ።ስራው ደግሞ አንቺ ልትለምጃቸው የሚገቡ የተለያዩ ገፅታዎች ሊኖሩት ይችላል ።

የቤተሰብሸን ህይወት ከባለቤትሽ የስራ ባህሪ አንፃር ፕሮግራም ልታደርጊ ይገባል ።
>ስራውን አታማሪ አታጣጥይ
>ወደ ቤት ሲገባ በፈገግታ ተቀበይው
>ባለቤትሽ ብዙ ጊዜያችን መንገድ ላይ የሚያሳልፍ ሹፌር ከሆነ አንቺንና ልጆችሽን ለማስተዳደር እየጣረ መሆኑን ተረጂ ።በሰራው ላይ ምንም ስህተት የለም በሚችለው መንገድ ህብረተሰቡን እያገለገለ ነው ።እጅና እግሩን አጣጥፎ ቢቀመጥ ይሻል ነበር ? መሰረት ግዴታው መሆኑን እያወቅሽ ለምን ሁልጊዜ ከአንቺ ጋር አንዲሆን ትፈልጊያለሽ ? የሰራውን ባህሪ መልመድ አልቻልሽም ወይም አልፈልግሸም ።ትልቅ ስህተት አየሰራሸ ነውና ከሰህተትሸ ታረሚ ።ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መልመድና ዘና ብሎ መኖር መቻል ብልህነት ነው ።

ወደ ስራ ሲሄድ መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልህ ብለሸ ሸኚው ።ወደ ቤት ሲገባ አንኳን ደህና መጣህ ብለሸ ተቀበይው ።ይህ
@ለቤተሰቡ ያለው ፍቅር እንዲጨምርና
@ጠንክሮ እንዲሰራ ያደርገዋል ።
@አደጋ አያጋጥመውም
@አዕምሮውም ጤነኛ ይሆናል ።
@አንቺን ከራሱ ለይቶ አያይሸም ።
@በተቻለው መጠን በጊዜ ወደ ቤቱ ለመመለስ ይሞክራል ።


✿ #ባለቤትሽ የማታ ሸፍት ሰራተኛ ከሆነ
~~የቤተሰቡን ህይወት ለመምራት ሲል እንቅልፉን መሰዋዕት እያደረገ መሆኑን በመረዳት የሰራውን ባህሪ ለመልመድ ሞክሪ ።
~~በሰራው ቅር አንደተሰኘሸ አትግለጪ ።
~~ማታ ማታ የሚደብርሸ ከሆነ መፅሐፍት በማንበብ ፣ጥልፎችንና ዳንቴሎችን በመስፋት ወዘተ አሳልፊ ።
~~ጧት ሲመጣ ጥሩ ቁርሰ አዘጋጅተሸ ጠብቂው ።
~~ ልጆቹ ፀጥ አንዲሉ አድርጊ ።
~~አባታቸው በሚተኛበት ጊዜ መረበሽ እንደሌለባቸው አሰተምሪያቸው
~~በማታ ትንሸ በመተኛት ቀን ከሱ ጋር መተኛትም ትችያለሽ ።
ነገር ግን እሱ ሌሊቱን ሙሉ ምንም አንዳልተኛና ለሱ ቀን ማለት እንዳንቺ ሌሊት መሆኑን አትዘንጊ ።ሁለት ፕሮግራም ይኑርሽ ።ለራስሽና ለባለቤትሸ ።

✿ ባለቤትሽ ሾፌር ፣ሃኪም ፣የፋብሪካ ሰራተኛ ፣ተመራማሪ ወዘተ ከሆነ ልትኮሪ ይገባል ።ምክንያቱም ባልሽ እጅና እግሩን አጣጥፎ የተቀመጠ ስራ ፈት አይደለም ።በመጥፎ የሰራ መስክም አልተሰማራም ።ስለዝህ አድናቆትሸንና አክብሮትሸን ግለጪለት ሰራውን እንዲለቅ አትፈልጊ ።ወይም አትጠይቂው ይልቁንም ከሰራው ባህሪ ጋር ተላመጂ ።

ጥናት እያደረገ ከሆነ አትረብሸው ።ጊዜሸን የቤት ስራ በመሰራት ፣መፅሐፍ በማንበብ ፣ፈቃደኛነቱን ጠይቀሸ ወደ ዘመዶችሸና ጓደኞችሸ ቤት በመሄድ አሳልፊ ።




እረፍት ላይ በሚሆንበት ጊዜ ግን
☞ ከቤትሸ ላለመውጣት ሞክሪ
☞ምግብና ሌሎች የሚያስፈልጉትን ነገሮች አዘጋጅለት
☞ፈገግታና ጥሩ አቀራረብ አይለይሸ
ትህትናሸና አክብሮትሸ ድካሙን ያሰረሳዋል ።ይህን በማድረግሸ የሱን አድገት ብቻ አይደለም ያፋጠንሸው ።ነገር ግን ባልሽ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ባለው አገልግሎት ላይ የራሰሽን ድርሻ አከልሸ ማለት ነው ።

ሁለም ሴቶች አንዲህ አይነት ጠንካራ ሰራተኛ ባሎች አያገኙም ።አንቺ እሱን በማግኘትሸ እድለኛ ነሽ ..ስለዚህ ጥሩ ስነምግባርን በመላበሰና መስዋአትነት በመክፈል ለስኬቱ አስፈላጊ ሰው መሆንሽን አረጋግጪ ።
>የባለቤትሸ ሥራ ልብስ የሚያቆሽሽ ከሆነ ቶሎ ቶሎ አጠቢለት ።
>ስለ ስራው መጥፎ ነገር አትናገሪው ።
>ስራ አንዲቀይርም አትጠይቂው ።ስራ መቀየር ቀላል ነገር አይደለም ።በስራ የተነሳም ትዳር መፍረስ የለበትም ።

✿ "አንዲት ሴት ባለቤቷ ነዳጅ ሸያጭ ላይ ስለሚሰራ ሁሌ ጋዝ ጋዝ መሸተቱ አንዳማረራት ለዳኛ ገልፃለች ።"
እናም ባልሽ በሚሰራዉ ስራ ተጠይፈሽ እንደዚች አይነት ሴት እንዳትሆኝ አደራ ተጠንቀቂ

#ክፍል ➋➊
ይቀጥላል...

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ አንድ 2⃣1⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



🌹🌹 #ጥቂት_ምክር_ለወንዶች ፦🌹🌹

#ውድ_ወንድም_ሆይ !
#በመጀመሪያ ☞ ሚስትህ የምትቀናብህ ሰለምትወድህ መሆነን እወቅ ።ባትወድህ ኖሮ አትቀናብህም ነበር ።አንተን ማጣት አትፈልግም ።የብቻዋ እንድትሆንላት ትፈልጋለች ።ትዳሯን ትወዳለች ።ታዲያ ይህ ልዩ ውዴታ ጥርጣሬ ሊፈጥርባትና ለሰነልቦና ችግር ሊዳርጋት ይችላል ።

#ስለዚህ
✔ተንከባከባት
✔ ለሷ ክስ ምላሽህ መጥፎ አይሁን
✔ አትቆጣት ።አትዝጋት ፣አትምታት ፣
✔ ስለ መለያየትና ፍቺ አታውራ ።
✔ ወደ ፍርድ ቤት አትሂድ ።
እነዚህ ተግባራት መፍትሄ አይሆኑም ።እንደውም ችግርን ይበልጥ ያወሳስባሉ ።የሚገባትን እንክብካቤ መንፈግህ ይሆናል ጥርጣሬ የፈጠረባት ።ስለዚህ በተቻለህ መጠን እንክብካቤ አይለይህ ።አንተን አላግባብ በመጠርጠሯ ልታዝንባት ትችላለህ ።ነገር ግን ሌላ አማራጭ የለም ።ጨዋነትህን በምታረጋግጥበት መልኩ ቅረባት ።

#ሁለተኛ ☞ በሁለታችሁ መካከል መግባባት እንዲኖር ጥረት አድርግ ።ምንም ነገር አትደብቅ።
♡ በሞባይል ሰልክህ የሚመጡ መልዕክቶችን አንተ
♡ ከማንበብህ በፊት እሷ እንድታነባቸው ጋብዛት ።
♡ ስልክ ሲደወልልህ አጠገቧ ሆነህ አውራ ።
♡ የግል እቃዎችህን የምታሰቀምጥባቸውን ሳጥን ቁልፍ ሰጣት ።
♡ ኪሶችህንና ቦርሳዎችህን እንድታይ አድርግ ።
♡ ጉዳዮችህን ሁሉ አማክራት ።
♡ ስለቀን ውሎህ አጫውታት ።
♡ እምነቷን ጠብቅላት ።
♡ ያልገባትና የሚያስጨንቃት ጉዳይ ካለ ጠይቃት ።
ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በማድረግህ ቅር አትሰኝ ።ይህ በጤናማ ትዳር ውሰጥ የሚኖር ጤናማ ሂደት ነው ።

✔ከስራ በኋላ ሌላ ስራ ከሌለህ በተቻለ መጠን ቶሎ ወደ ቤት ተመለሰ ።
✔የሚያዝገይ ጉዳይ ካጋጠመህ ለሚስትህ ሁኔታውን አሳውቃት ።ስንት ሰዓት ላይ ልትመልስ እንደምትችልም ።ግለፅላት ።
✔ባልከው ሰዓት ለመመለስ ሞክር ።መድረስ የማትችል ከሆነ ምክንያቱን ንገራት ።በፍፁም አትዋሽ ...ውሸት ለጥርጣሬ በር ይከፈታል ።

#ሶስተኛ ☞ሚስትህ ከጠረጠረችህ ነገር ነፃ ልትሆን ትችላለህ ።ብዙ ጊዜ ግን ሴቶች ከመሬት ተነስተው ባሎቻቸውን አይጠረጥሩም ።ምናልባት በግዴለሽነት ያደረግከው ነገር አዕምሮዋን ጎድቶትና እንድትጠረጥርህ አድርጓት ሊሆን ስለሚችል ራሰህን ፈትሸ ።

~~~ ይህን ስታደርግ የጥርጣሮዋን ምንጭ ልታገኘው ችግሩንም በቀላሉ ልትፈታው ትችላለህ ።
#ለምሳሌ
○ከሴቶች ጋር አብዝተህ የምትቀላላድ ከሆነ ለማቆም ሞክር ።
○ በስብሰቦች ላይ ከሴት ጋር ከልክ ያለፈ ቅርበት በመፍጠር የሚስትህን ጥርጣሬ አትጨምር ።
○ ግድ ካልሆነ በስተቀር ለቢሮህም ለንግድ ተቋምህም ሴት ሰራተኛ አትቅጠር ።
○ ከቤት ሰራተኛችሁ ጋር ያለህ ጉዳይ ማለፍ ያለበት በሚሰትህ በኩል ብቻ ነው ።
○ ሚስትህ አጠገብህ እያለች የሰራተኛዋን ስም በተደጋጋሚ እየጠራህ ይሀን አድርግልኝ ይህን አምጭልኝ ማለት የለብህም ።ይህ ብዙ የቤት እመቤቶችን በቤታቸው ባይታወር የሚያደርግና የሚያሳዝን ተግባር ነው ።ለከፍተኛ የቅናት ችግርም ይዳርጋቸዋል ።


♦♦ ባሏ የሞተባትን ድሀ ሴት ለመርዳት ከፈለግክ ሁኔታውን ለሚስትህ ንገራት በሷ በኩልም መርዳት ትችላለህ ።ከነዚህ ነገሮች በመታቀብህ እሰር ቤት ነው የገባሁት ብለህ አታስብ ።አልታሰርክም ።ይልቁንም በቅን ፍላጎት ለትዳር አጋርህ ጥንቃቄ የምታደርግ ብልህ ሰው ነህ ።በዚህ መልኩ ሚስትህን ከበሽታ ልጆችህንም ከእንግልት ታድናለህ ።ለራስህም ትልቅ የአዕምሮም ሰላም ታገኛለህ ።

#ክፍል ➋➋
ይቀጥላል.....

Join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ ሁለት 2⃣2⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➍
#ወደ_ሌላ_አገር_መሄድ_ካለብሸ_ሂጂ


አንድ ሰው አገሩን ለቆ ወደ ሌላ አገር ሂዶ መኖር ሊኖርበት ይችላል ።ባለቤትሽ በግሉ ወይም በመንግስት መስሪያ ቤት ውሰጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ከሆነ በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ወደ ሌላ አገር ሊላክ ይችላል ።ወንዶች አንዲህ አይነቱን ሁኔታ ለመቀበል ሲገደዱ አንዳንድ ሴቶች ግን ከዘመዶቻቸውና ከጓደኛቻቸው አንዲሁም ከትውልድ ቀያቸው መራቅ አይፈልጉም ።"እሰከ መቼ ከወላጆቼና ከቤተሰቤ ርቄ ? በዚያ ላይ አገሩ የሚያስጠላ...በጭራሽ አዚህ መቆዬት አልችልም ።የምንመለሰበትን መንገድ አመቻች !"በማለት ባሎቻቸውን ይጨቀጭቃሉ ።

ይህን የሚያደርጉት ደካማ አሰተሳሰብ ያላቸውና ከትውልድ አገራቸው በሰተቀር ሌላ ጥሩ መኖሪያ የሌላ አድርገው የሚያስቡ ሴቶች ናቸው ።ህይወት በሌላ አገር የሚሳካላቸው አይመስላቸውም ።የሰው ልጅ በራሱ ፕላኔት አልረካ ብሎ ወደ ሌሎች ፕላኔቶች እየሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከትውልድ አገርሽ ጥቂት ኪሎ ሜትር ርቆ መኖር ለምን ይከብድሻል ?

✿ ጓደኞቼንና ዘመዶቼን ትቼ አንዴት ወደ ባእድ አገር እሄዳለሁ? ብለሸ አታሰቢ ።በአዲሱ አገር አዲስ ጓደኞችና ወዳጆች የማፍራት ብቃት አለሽ ።

#እመቤት_ሆይ !
ብልህና ጠንካራ ሁኚ ...ራሰ ወዳድ አትሁኚ
~~~~ባለቤትሸን የሚያሳዝንና የሚያበሳጭ ነገር አትፍጠሪ ።ተቀጣሪ ሰራተኛ ከሆነ ታዞ ነው ወደ ሌላ አገር የሚሄደው የራሱን ስራ ለመሰራት ከሆነ ደግሞ የራሳችሁን ኑሮ ለማሻሻል ነው አገር የምትለቁት ።አንድ ቦታ ላይ ችክ ብሎ በችግር ከመኖር ወደ ሌላ አገር ተንቀሳቅሶ የተሻለ ህይወት መፍጠር አይሻልም ትያለሽ ?ባለቤትሽ ወደ ሌላ አገር ለስራ መሄድ እንዳለባችሁ ሲነግርሸ ወዲያውኑ ተስማሚ ።አቃችሁን አዘጋጅታችሁ ሂዱ ።የሄድሸበትን ቦታ አንደ አገርሽ አድርገሽ ቁጠሪው ።ህይውትሸን በአዲሱ አገር አንኳን ለመምራትና ራሰሸን አሰማምተሸ ለመኖር አቅጂ ።

~~~ ለአገሩ አዲስ ስለሆንሽና የነዋሪዎቹን ባህሪ ሰለማታውቂ ጥንቃቄ አድርጊ ።ቀሰ በቀሰ በባልሽ እገዛና ምክር ጥሩ ባህሪ ካላችውና ከታማኝ ሴቶች ጋር ጓደኝነት ፍጠሪ ።

ሁሉም ቦታ የራሱ የሆነ ጥሩ ነገር ይኖረዋል ።ገጠር ከሆነ ተፈጥሯዊ ነገሮችን በማየትና በመጎብኘት ትዝናኛለሸ ።ከጥቂት ጊዜ በኋላ አዲሱን ኑሮ ከድሮው ኑሮሽ አስበልጠሸ ልትወጂው ትችያለሽ ።አዲሶቹ ጓደኞችሸም ከድሮዎቹ የበለጡ የሚሆኑበት አጋጣሚ ይኖራል ።

~~~አዲሱ ቦታ እንደ ድሮዉ ካልሆነልሸ ያሉትን ጥሩ ነገሮች በማሰብ ራስቅን ለማፅናናት ሞክሪ በሄድሽበት አገር ለምሳሌ ያህል
☞መብራት ባይኖር ንፁህ አየር ስለሚኖረው ጤነኛ ትሆኛለሽ ።
☞ትኩስ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችንም በቅርቡና በርካሽ ዋጋ ታገኛለሸ ።
☞ጥሩ የመኪና መንገድ ባይኖረው የመኪናና የፋብሪካ ጪሰ አያገኝሸም ።
☞ከሰውና ከመኪና ጩኸትና ጫጫታም ነፃ ነሽ ።

በሳር በተሰሩ ደሳሳ ጎጆዎች በደስታ የሚኖሩትን እና ለከተማ የቅንጦት ህይወት እንዲሁም ፎቅና ቪላ ቤቶች ምንም ደንታ ስለሌላቸው የገጠር ሰዎች ጥቂት አስታውሺ ።ሰለፍላጎቶቻቸውና ስላሉባቸው ችግሮች እሰቢ ።እነሱን መርዳት ከፈለግሽ ባለቤትሽ በተሰማራበት ሞያ እነሱን እንዲያገለግል አበረታችው ።

~~~ ብልህ ከሆንሽ በአዲሱ ቦታ በምቾት መኖርና ለባለቤትሸ እድገት ትልቅ እገዛ ማድረግ ትችያለሽ ።ይህን ካደረግሸ በክቡርና ጠንካራ ሚሰቱ ባልሽ ይኮራብሻል ።ይበልጥ ያፈቅርሻል ።በሰዎች ዘንድም ተቀባይነት ይኖርሻል ።

#ክፍል ➋➌
ይቀጥላል........

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ ሶስት 2⃣3⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL

🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
9⃣
#ሰህተቷን_አሳልፍ

የሰው ፍፁም የለውም ።ሁላችንም ስህተቶችን እንሰራለን ።ይህ ወንዶችንም ሴቶችንም ያጠቃልላል ።

ሴት ልጅ
>>> ለባለቤቷ ትሁት ባለመሆን ፣
>>> የማይፈልገውን ነገር በማደረግ ፣
>>> ለሱ ክፉና ግዴለሽ በመሆን ፣
>>> ገንዘቡን በማባከን ፣ወዘተ ስህተት ልትሰራ ትችላለች ።ጥንዶች እርሰ በርስ መከባበርና መደሰት እንጂ ማበሳጨትና ማሰከፋት የሌለባቸው ቢሆንም ሁሉም ጥንዶች ይህን ተግባር ሲፈፅሙ አይታይም ።

ሴቶች ስህተት በሚፈፅሙበት ጊዜ አንዳንድ ባሎች ለወደፊት እንዳይደግሙ በሚል በስህተቶቹ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ።ነገር ግን ከልምድ እንደታየው ነገሩ ተቃራኒ ነው የሚሆነው ።ስህተት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ባል ያላት ሴት ተደጋጋሚ ስህተቶችን ነው የምትፈፅመው ።ምክንያቱም ስህተት በምትሰራ ጊዜ ይነግረኛል የሚል ፍራቻ ሰለሚያድርባት ምላሹን ለመስጠት ስትል ሌላ ስህተት ትፈፅማለች ።ቀስ በቀስ ሀሳቧ ሁሉ ከሱ ተቃራኒ እየሆነ ይመጣል ።

✔ ሚሰቱ ጥፋት በምታጠፋበት ጊዜ ይቅር የማይል ባል ሚሰቱን ግትርና ታማኝ እንዳትሆን እየገፋፋት ነው ።በዚህ አሰተሳሰብ የሚቀጥል ከሆነ ሁሌም ከሚሰቱ ጋር ይጋጫል ።ከዚያም ሁሉቱም ቀሪ ህይወታቸውን መረራ በሆነ ሁኔታ ውሰጥ ለማሳለፍ ይገደዳሉ ።

✔ አንዳንድ ወንዶች ደግሞ ሚሰት ያደረገችውን ታድርግ በሚል ዝም ማለትን ይመርጣሉ ።በዚህ ጊዜ ሚስት የአሸናፊነት መንፈስ ሰለሚሰማት ከባሏ ፍላጎትና ምኞት ጋር ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን ትፈፅማለች ።ሆን ብላ ትልልቅ ስህተቶችን ስትሰራ ዝም ካለ ጋብቻቸው ጣዕሙን ያጣና ወደ ፍቺም ሊሄዱ ይችላሉ ።ሆኖም ፍቺ ለሁለቱም መጥፎ እንደሆነና አዲስ ህይወት መጀመር ቀላል እንዳልሆነ ማስታወስ ያሻል ።


ስለዚህ ቸልተኛ መሆንም ሆነ ወግ አጥባቂ መሆን ውጤታቸው የከፋ ስለሆነ መካከለኛውን አቋም መውሰድና ምክንያታዊ መሆን የተሻለ ነው ።

>>> ባለቤትህ ሳታውቅ የምትፈፅማቸውን ጥቃቅን ስህተቶችን እለፍ ።ባለማወቅ ስህተት በሚፈፀም ሰው ላይ መጮህ ተገቢ አይደለም ።ስህተቶች እንዳይደገሙ ማድረግ የሚቻለው ምክር በመሰጠት ነው ።ሰዎች ባለማወቅ ብዙ ስህተቶችን ይሰራሉ ።ስለሆነም በትዕግስት የተሳሳተ ተግባራቸውንና አመለካከታቸውን እንዲያርሙ መምከር ይገባል ።

ሚስትህ ሰህተቷን እንድታርም የምታደርጋት በሀይል አይደለም ።በዝግታ ያጠፋችውን ጥፋትና ጥፋቱ የሚያስከትለውን ጉዳት በማስረዳት ነው ።ከዚህም ይህን ድርጊት ዳግም ላለመፈፀም በራሷ ትወስናለች ።ይህ ከሆነ በመካከላችሁ ያለው መከባበር እንደነበር ይቅጥላል ።የሰህተቶች መደጋገም አይኖርም ።ባል በተገቢው ሁኔታ ሚሰቱ ስህተት እንዳትፈፅም ማድረጉ ብልህነት ነው ።ይህም ሆኖ በተደጋጋሚ ስህተት የምትሰራ ከሆነ ይቅር ማለትና ማሳለፍ አለበት ።
መቅጣትና ወይም ሰህተቷን አውቃ ይቅርታ እንድትጠይቅ ለማድረግ መሞከር የለበትም ።
#ምክንያቱም ሴቶች ይህ አይነቱ ነገር አይመቻቸውም ።አላግባብ ማጥበቅ ከበፊቱ ባበሰ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋቸዋል ።ይህ ደግሞ እንደ ፍቺና ነፍስ ግድያ ያሉ መጥፎና አላሰፈላጊ ክስተቶችን ሊያሰከትል ይችላል ።

♦♦ ባልና ሚሰት መካከል ግጭት ከሚፈጥሩ ምክንያቶች አንዱ በቤተሰብ ጉዳይ ላይ አማት ጣልቃ መግባታቸው ነው ።

አንዲት እናት ልጃቸውን ለባል ከመስጠታቸው በፊት የልጃቸው ባል ምንም አይነት ጉድለት የሌለበትና ልጃቸውን የሚያሰደሰትላቸው እንደሚሆን ያስባሉ ።ያከብሩታል ።ይቀርቡታል። አንዳንዴ የልጃቸው ባል እንዳሰቡት ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ያሰቡት ሳይሳካ ይቀራል ።እንዳሰቡት ካልሆነ እሱን ለማስተካከል ጥረት ያደርጋል ።ይህን ለማሳካት የራሳቸውን ወይም የሌሎችን ልምድ ይጠቀማሉ ።ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያስባሉ ።ቤቱ ውሰጥ እንደመሪና አማካሪ ልሁን ይላሉ ልጃቸው በብዙ ነገሮች ከባሏ ተቃራኒ እንድትሆን ያዟታል ።ዓላማቸው ግን ልጃቸው ከባሏ ጋር እንድትሰማማና ደስተኛ ህይወት እንዲኖራት ማድረግ ነው ።

በመጨረሻም ባል ሚስቱን በተመከረች ጊዜ ኮስታራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተለማማጭ ሆኖ ያገኛታል ።ልምድ የሌላት ሴት እናቷን ለትዳሯ ተቆርቋሪ አድርጋ ስለምታስብ የሳቸውን ምክር ትሰማለች ።ባል አማቱ በሚፈልጉት መልኩ ከሄደ ጥሩ ካልሆነ ግን በጥንዶቹ መካከል ጭቅጭቅ ይፈጠራል ።

~~~ይህ ደግሞ ለፍቺና ለሌሎች መጥፎ ነገሮች ይዳርጋል ።ለዚህ ነው ብዙ ወንዶች ከሚስቶቻቸው እናቶች ጋር የማይስማሙት ።ለሚስቶቻቸው ታዛዥ አለመሆን አማቶቻቸውን ተጠያቂ ያደርጋሉ ።ሚስቶቻቸው የሚናገሩት ነገር ሁሉ ከነሱ የመጣ እንደሆነ ያምናሉ ።

ሚስተር ኤም ጃቨድ ሲጽፍ "የኔ አማት አውሬና መርዛማ ጊንጥ ናቸው ።ህይወቴን መራራ አድርገውታል ።በአሁኑ ወቅት በረሃ ላይ ብቻየን የምሮጥ እብድ እንደሆንኩ ነው ።የሚሰማኝ ።እኔ ብቻ አይደለሁም ።በዚህ ሁኔታ የተማረርኩት ።ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆኑት ወንዶች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ናቸው ።ብዬ አስባለሁ ።ቀሪዎቹ አምስት ከመቶ ወንዶችም ሰላም ያገኙት የሚሰቶቻቸው እናት በህይወት ስለሌሉ ነው ብሏል ።

#ክፍል ➋➍
ይቀጥላል........


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ አራት 2⃣4⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL




#ሰህተቷን_አሳልፍ_የቀጠለ

ሚስተር ኤፋ ኤ በበኩሉ
>>>> "የኔ አማት ሁልጊዜ በህይወቴ ውሰጥ ጣልቃ ይገባሉ ።ያበሳጩኛል ።የወላጆቼን ሰም ያጠፋሉ ።ለሚሰቴ እንድ ነገር ገዝቼ ስመጣ የሆነ ጉድለት ይፈልጉለታል ።ቀለሙ ጥሩ አይደለም ።ሞዴሉ አያምርም በማለት ያጣጥላሉ ።


>>>> ሚስተር ኬ ፓርቪሰ ደግሞ "የሚሰቴ እናት እኔን የሚያዩኝ እንደ ልጃቸው ባል ሳይሆን ልጃቸውን እንደፈታ ሰው ነው ።መጥፎ ሴት ናቸው ።ሚስቴ ለኔ ክፉ እንድትሆን ፣የቤት ስራ እንዳትሰራና ከኔ የማይሆን ነገር እንድትጠብቅ ይመክሯታል ።ወደኛ በመጡ ጊዜ ቤታችን ወደ ሲኦል ይቀየራል ።እውነቴን ነው የምላችሁ አይናቸውን ማየት አልፈልግም "ብሏል ።


♦ ብዙ ወንዶች የሚሰቶቻቸው እናቶች በሚስቶቻቸው ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ለማስቀረት ሲሉ የሁለቱን ግንኙነት ለማቋረጥ ጥረት ያደርጋሉ ።ይህ ተግባር በብዙ ወንዶች ዘንድ የተለመደ ቢሆንም ጥሩና ገንቢ አይደለም ።ምክንያቱም በእናትና በልጅ መካከል ያለ ግኑኝነት ጠንካራና በቀላሉ ሊቋረጥ የማይችል ነው ።


አንድ ባል ሚስቱን እሷን ለማሳደግ ብዙ ነገር ካሳለፉ ወላጆቿ ጋር ለማለያየት እንዴት ይሞክራል ? ይህ ሊሆን አይችልም ።ቢሆን እንኳን እንደ አንዳንድ ቅፅበታዊ ክስተቶች ጊዜያዊ እንጂ ቋሚ ሊሆን አይችልም ።

____ ከዚህም በተጨማሪ አንዲት ሚሰት ባሏ ለቤተሰቦቿ ጥሩ አመለካከት እንደሌለው ከተረዳች እሷም ለሱ ቤተሰቦች ተመሳሳይ አመለካከት ልታዳብር ትችላለች ።እነሱን አታከብርም ።አትታዘዝም ።ባል ይህን ማድረጉ የሚስቱ እናት በትዳሩ ላይ በመጥፎ ሁኔታ ጣልቃ እንዲገቡ እድል ስለሚሰጣቸው ትዳሩ ተናግቶ ፍቺ ይፈፀማል ።

~~~ ከሚስቱ ወላጆች ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ትዳሩን ማሳመር ሲችል እሱንና ቤተሰቡን የሚጎዳ ተግባር ይፈፅማል ።


♦♦ የህንድ የፖሊስ ባለስልጣናት እንዳሰታወቁት እ.ኤ.እ በ1971 በኒውደልሂ ለተከሰቱ አንድ መቶ አርባ ስድሰት ራሰን የማጥፋት እርምጃዎች መካከል የብዙዎቹ መንሰኤ በባልና በሚስት እናት መካከል የተፈጠረ ግጭት ነው ።


✔ "የሚስቱ እናት ጭቅጭቅ ያማረረው አንድ ባል ከታክሲ ወርውሯቸዋል ።
✔ ""አንድ ባል የሚስቱን እናት በመዶሻ ጭንቅላታቸውን ይፈነክታቸዋል ።የሴትዮዋ ወንድ ልጅም እሱን በጩቤ ወግቶ ተሰወረ ።"
✔ ሌላኛው በሚስቱ እናት የተናደደ ባል ጭንቅላታቸው ላይ ትኩስ ሾርባ ያፈሰባቸዋል ።ሴትዮዋ ራሳቸውን ስተው መሬት ላይ ይዘረራሉ ።ወደ ሆስፒታል ተወሰደው ካገገሙ በኋላ ሲናገሩ እኔ እናቷ ላይ ይህን በማድረጉ ልጄ ከባሏ ጋር መኖር እንደማትችል ነግራኛለች "ብለዋል ።
✔ "አንድ በሚስቱ እናት የተማረረ ባል ራሱን አጥፍቷል ።


~~~ እዚህ ላይ ሁለት ጠቃሚ ነገሮችን መጥቀስ አሰፈላጊ ነው ።

➊ / የሚሰት እናት የልጃቸው ባል ጠላት አይደለም ።እንደውም ይወዱታል ።ለዚህም በትዳር መጀመሪያ ላይ ለሱ የሚያሳዩት ፍቅር ምስክር ነው ።ኋላ ላይ ልጃቸው አንዳንድ ችግሮች ሲገጥማት ሲያዩ የሷ ደሰታ ሰለሚያሰጨንቃቸው ለሷ ጥሩ ነገር ለመፍጠር በማሰብ ጣልቃ ይገባሉ ።በዚህ ሂደት ላይ ስህተት ይፈፅማሉ ።ስለዚህ ባል እንዲህ አይነቱ ስህተት ላይ ትኩረት መሰጠት የለበትም ።

➋ / እናትና ልጅን ለማለያየት መሞከር ስህተት ነው ።የእናትና የልጅ ግንኙነት ተፈጥሯዊ ትስሰር ያለው ስለሆነ በቀላሉ ሊበጠሰ አይችልም ።ይህን ለማድረግ የሚሞክር ሰው በርግጠኝነት አይሳካለትም ።ምክንያቱም እንዲህ አይነት ጥረቶች ከተፈጥሮ ህግ ጋር የሚቃረኑ ናቸው ።

✿ አንተ ለወላጆችህ ፍቅር እንዳለህ ሁሉ እሷም ይኖራታል ።ስለዚህ ለሁለታችሁም የሚበጃችሁ ከአማቶቻችሁ ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠሩ ነው ።ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ከብርና ፍቅር በማሳየት ነው ።በብልሃት ፣በአክብሮትና በታዛዥነት ከሚስትህ ወላጆች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ትችላለህ ።

✿ ለልጃቸው ያለህን ፍቅር ስትገልፅ ደስ ይላቸዋል ።ከነሱ ፊት እሷን ማንቋሸሽ የለብህም ።ከነሱ ምክርና ምርቃት ማግኘት አለብህ ።አንድ ሃሳብ ሲያቀርቡ ወይም አንድ ነገር ሲፈፅሙ ያ ነገር ትክክል ካልሆነ በእርጋታ ነገሩ ትክክል እንዳልሆነ ማስረዳት እንጂ መጮህና እነሱን መገላመጥ ተገቢ አይደለም ።

✿ ከሚስትህ ወላጆች ጋር ጥሩ ግንኙነት የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለብህና ይህም የሰኬታማ የትዳር ህይወት ሚሰጥር መሆኑን ማወቅ አለብህ ።ይህ ከሆነ ችግሮች ይፈታሉ ።

~~~ በአጠቃላይ ሁልጊዜ የሚስት እናቶች ብቻ አይደሉም ስህተት የሚፈፅሙት ።ወንዶችም በብልሀት እነሱን መያዝ ላይ ደካማ ሲሆኑ ይስተዋላል ።

ከሚስቶቻቸው እናቶች ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ብዙ ወንዶች አሉ ።

✉ ሚስተር ማኑቸህር ሲፅፍ "የሚሰቴ እናት ባህሪያቸው እንደ መላዕክት ነው ።ማለት ይቻላል ።ከወላጅ እናቴ አብልጬ እወዳቸዋለሁ ።ሩህሩህና አስተዋይ ሴት ናቸው ።ችግር በሚገጥመን ጊዜ ይረዱናል ።የሳቸው በህይወት መኖር ለቤተሰቤ ደሰታ ዋስትና ነው "ብሏል ።

~~ አንድ ባል ግትርና አሰቸጋሪ የሆኑ አማት ቢኖሩት እንኳ በመጥፎ ሁኔታ ሊቀርባቸው አይገባም ።ይህ አይነቱ ባህሪ ከባድ ቢሆንም ተለሳልሶና በጥሩ ፀባይ በመቅረብ በትዳር ላይ የተጋረጠውን አደጋ መቀነስ ይቻላል ።


ስኬታማ የሆነ ትዳር ይኖርህ ዘንድ
✔ ደግነትን አትርሳ ።
✔ የሚስትህን ቤተሰቦች ተንከባከብ ።ባል ከሚስቱ ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዲኖረውና በመካከላቸው መተማመን እንዲኖር ያሰፈልጋል ።ሰለ እናቷ መጥፎ ተግባራት ውይይት ማድረግና ሁኔታው በትዳራቸው ላይ ሊያሰከትል የሚችለውን አደጋ በትክክል ሲያሰረዳትና እሷም ልትቀበለው ይገባል ።


ከሷ ጋር የጠበቀ ቁርኝት መፍጠር ከቻለ ከአማቱ ጋር ያለውንም ሆነ ሌሎች በርካታ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት ይችላል ።

#ክፍል ➋➎
ይቀጥላል
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ አምስት2⃣5⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➎
#ባልሽ_ቤት_ዉስጥ_የሚሰራ_ከሆነ

ባሎቻቸው ውጪ የሚሰሩ ሚስቶች ቤት ውሰጥ ነፃነት አላቸው ።

እንድ ገጣሚ ፣ደራሲ ፣ተመራማሪ ወዘተ ያሉ ሰዎች ብዙ አያገኝም ።አኗኗራቸውም ይለያል ።እነዚህ ሙያዎች መመሰጥን ፣ፀጥታንና ማስተንተንን ይጠይቃሉ ።የአንድ ስዓት የሰላም ስራ ከብዙ ሰዓታት የተረበሸ ስራ ጋር አኩል ነው ።

ባል ለስራው ፀጥታን ይፈልጋል ።ሚሰት ደግሞ ቤቷ ወስጥ በነፃነት መዘዋወር ትፈልጋለች ።በዚህ ጊዜ ችግር ይፈጠራል ።ሚስት ሰራዎቿን ሁሉ ባሏ በማይረበሸበት መልኩ ማከናወን ከቻለች በእርግጥ ትልቅ ነገር አደረገች ።ይህን ማድረግ ግን ቀላል ነገር አይደለም ።በተለይ ህፃናት ካሉ ።የሆነው ሆኖ ግን ችግሩ መቀረፍ አለበት ።ምክንያቱም ባል በስራው ስኬታማ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነው በዚህ ነውና ።

~~~ ሚስት ከባሏ ጋር የምትተባበር ከሆነ ባሏን ለሷም ሆነ ለህብረተሰቡ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያበረክትና የተከበረ ሰው ማድረግ ትችላለች ።

~~~ ባሏ ቤት ውሰጥ የሚሰራ ሚስት
☞ ልጅ አንዲንከባከበና እንዲቆጣጠር ፣
☞በር አንዲከፍትና ስልክ እንዲያነሳ ፣
☞ወጥ ቤት እንዲገባና ምግብ አንዲያበሰል መፈልግ የለበትም ።ስራ ላይ በሚሆን ጊዜ ቤት ውሰጥ እንደሌለ አድርጋ መቁጠር አለበት ።

#እመቤት ሆይ !
ባለቤትሽ ወደ ጥናት ክፍል መግባት ከፈለገ ክፍሉን ካዘጋጀሸለትና አንድ አሰኪርቢቶ ፣ወረቀት ፣መፅሐፍትና ሌሎች አሰፈላጊ ነገሮችን ካቀረብሸለት በኋላ ትተሸው ውጪ ።ጮክ ብለሸ አትናገሪ ።ልጆቹም አባታቸው ስራ ላይ በሚሆንበት ጊዜ እየጮሁ በመጫወት አንዳይረብሹት አድርጊ ።
✔ ስለ እለታዊ ጉዳዮች አታዋሪው ።
✔የቤት ስራሸን አየሰራሸ የሚፈልገውን ሁሉ አቅርቢለት አታቋርጪው ።
✔በር ሲንኳኳ ቶሎ ክፈቺ ።
✔ስልክ ከጮኸ አንሰተሸ አናግሪ ።
✔እሱን ለመግኘት ወይም ለማናገር የሚፈልግ ሰው ከመጣ ሥራ ላይ አንደሆነ ንገሪ ።
✔እንግዶችሸን በእራፋት ሰዓቱ አሰተናግጂ ።
✔ጓደኞችሸና ዘመዶችሸ እሱ እረፍት ላይ በሚሆንበት ሰዓት እንዲመጡ ንገሪያችው ።

የልብ ጓደኞችሸ በሀሳብሸ አይበሳጩም ።አንዳንድ ሰዎች የዚህ አይነት ህይወት ከባድ ነው ብለው ሊያሰቡና አሰቸጋሪ የሆነውን የቤት ውሰጥ ሥራ እየሰሩ ባልን መንከባከብ ከዚህም አልፎ ምንም ነገር አንዳይረብሸው ማድረግ አንዴት ይቻላል ?ሊሉ ይችላሉ

በእርግጥ የዚህ አይነቱ ህይወት ያልተለመደና አሰቸጋሪ መምሰሉ ግልፅ ነው ።ነገር ግን አንዲት ሴት የባለቤቷን የመስራት አስፈላጊነት ከተገነዘበች በጥሩ እቅድ ፣መሰዋዕትነትና ብልሀት ችግሩን መቅረፍ ትችላለች ።የሴቶች ችሎታ የሚፈተሸው እዚህ ላይ ነው ።አለበለዚያ ግን ተራ የቤተሰብ ህይውትን ማንቀሳቀስ ከባድ ነገር አይደለም ።

#እመቤት_ሆይ !
>ምርምር ማድረግ ፣
>መፅሐፍትና ግጥሞችን መፃፍ ፣
>የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መቅረፅ ቀላል ተግባራት አይደሉም ።ያንቺ እገዛና ቁርጠኝነት ከታከለበት ግን እውን ይሆናሉ ።

~~~ በህይወትሸ መጠነኛ ለውጥ በማድረግና ፍላጎትሸን በመገደብ ባልሽን በስራው ላይ ለመርዳት ዝግጁ ሁኚ ።ያንቺ እገዛ ታክሎበት ባልሽ ትልቅ ደረጃ ላይ ሲደርሰ አንቺም የውጤቱ ተካፋይ ትሆኛለሽ ።

#ክፍል ➋➏
ይቀጥላል......
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/22 20:38:51
Back to Top
HTML Embed Code: