Telegram Web Link
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ስድስት 6⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
3⃣
#ሚስትህን_አክብር

ወንድ ልጅ በወንድነቱ አንደሚኮራው ሁሉ ሴት ልጅም በሴትነቷ ትኮራለች ። መከበርን ትፈልጋለች ፡፡የምትናቅና የምትዋረድ ከሆነ ስሜቷ ይጎዳል ።

> የሚያከብሯትን ሰዎች ሰትወድ ዝቅ አድርገው የሚያይዋትን ሰዎች ደግሞ ትጥላለች ።

#ውድ_ወንድም_ሆይ !
ከሌሎች በበለጠ ሁኔታ ሚስትህ የህይወት አጋሯን የቅርብ ጓደኛዋ በሆንከው ባንተ መከበር ትሻለች ።የመከበር መብትም አላት ።ለአንተና ለልጆችህ ድሎት የምታደርገውን ከፍተኛ ጥረት እንድታደንቅላትና ክብር እንድትሰጣት ትፈልጋለች ።እሷን ማክበርህ አንተን ዝቅ አያደርግህም ።ለሚስትህ ልዩ ፍቅር ያለህ ሰው መሆንህን ያረጋግጥልሃል አንጂ ።

~~~ስለዚህ ለሌሎች ከምትሰጠው ክብር በበለጠ ሁኔታ ሚስትህን አክብር ።
☆ በትህትና አናግራት ።
☆ ስትናገር አታቋርጣት ።
☆ አትጬህባት ።
☆ በቁልምጫ ስሞች ጥራት ።
☆ ወደ ቤት ስትገባ ሰላምታ አቅርብላት ።
☆ ስትወጣ ቻው በላት ።
☆ ራቅ ወዳለ ቦታ በምትሄድበት ወቅት በተለያዩ መንገዶች እሷን ከማግኘት አትቆጠብ ።ስልክ ደውልላት ።ደብዳቤ ፃፍላት ።
☆ ከሰዎች ጋር በምትሆንበት ጊዜ ክብር ስጣት ።
☆ እሷን ከመሳደብና ከማንቋሸሽ ተቆጠብ ።
☆ ለቀልድም ቢሆን አትሰደባት ።
☆ ለሷ ቅርብ በመሆንህ አትቀዬመኝም ብለህ አታስብ ።ይህን መሰሉን ድርጊት ላትወደው ነገር ግን በግልጽ ላትነግርህ ትችላለች ።

♦ አንዲት የሰላሳ አምስት ዓመት ሴት ፍቺ ለምን እንደጠየቀች ሰታብራራ ፦"ካገባሁ አሰራ ሁለት ዓመቴ ነው ።ባሌ ጥሩ ሰው ነው ።በርካታ ጥሩ ባህሪያት አሉት ነገር ግን እኔ ሚስቱና የልጆቹ እናት መሆኔንና ክብር እንደሚገባኝ መረዳት አልቻለም ።እንድ ግብዣ ፣ሰርግና የሀዘን ቤት ባሉ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ላይ መገኘት ይወዳል ።ነገር ግን እኔን በመሳደብና በማዋረድ ነው የሚያሳልፈው ።ምን ያህል እንደተሰቃየሁ ልነግራችሁ አልችልም ።አዕምሮዬ በጣም ተጎድቷል ።ወደ ስነልቦና አማካሪ መሄድ ሳይኖርብኝ አይቀርም ።ንቀት በተሞላበት ሁኔታ እንዳያየኝ ፣ሚሰቱ እንደሆንኩ ፣ትልቅ ሰው እንደሆንኩ ፣ሊያከብረኝ እንደሚገባና የሰው መሳቂያና መሳለቂያ ሊያደርገኝ እንደማይገባ ነግሬዋለሁ ።ለምኜዋለሁ ።ሊሰማኝ ግን አልቻለም ።ስለዚህ ፍቺን መርጫለሁ ።ህይወት ለብቻዬ የተሳካ እንደሚይሆንልኝ አውቃለሁ ።ነገር ግን በሰው መሀል እየተዋረዱ ከመኖር የማይሻል ነገር የለም "ብላለች ።

~~~ ሁሉም ሴቶች ባሎቻቸው እንዲያከብሯቸው ይፈልጋሉ ።በተለይ ደግሞ ከሰው ፊት ።ባሎቻቸው ከሰው ፊት ሲሰድቧቸው ዝም የሚሉ ሴቶች ቢኖሩ እንኳ ውስጣቸው ደስ ብሎት አይደለም ዝም የሚሉት ።መናገር ስላልፈለጉ እንጂ ።
☞ሚስትህን ካከበርካት እሷም በተራዋ ታከብርሃለች ።ግንኙነታችሁ ይጠነክራል ።
☞ሚስትህን አክባሪ ሰው በመሆንህ ሌሎች ሰዎችም ያከብሩሃል ።ከናቅካት እሷም ትንቅሃለች ።

#ውድ_ወንድሜ_ሆይ !
ትዳር ባርያ እንደ መግዛት አይደለም ።ሚስትህን አንተን ያገባችህ ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ከምትወደው ባሏ ጋር በሰላም ለማሰለፍ ነው ።ስለዚህ አንተ ሊደረግልህ የምትፈልገውን እንክብካቤ ለሷም አድርግላት ።

🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
4⃣
#መልካም_ባህሪ_ይኑርህ

የዚህ ዓለም እንቅስቃሴ በሰው ልጅ እጅ አይደለም ያለው ።የህይወት ገጠመኞችም እኛ በፈለግነው መልኩ አይከሰትም ።

~~~ አንድ ሰው ጠዋት ከቤቱ ከወጣበት ደቂቃ ጀምሮ ወደ ቤቱ እሰከሚመለሰባት ሰዓት ድረስ ብዙ ነገሮች ያጋጥሙታል ።
◇ከሰው ጋር ሊጣላ ፣
◇መጥፎ ጓደኛ ሊገጥመው ፣
◇ታክሲ ወይም አውቶብስ አጥቶ ብዙ ሰዓት ሊጉላላ ፣
◇በሰራ ቦታ ላይ በተፈጠረ ችግር ሊከሰሰ ፣
◇ገንዘብ ሊጥል ወይም ሊዘረፍ ይችላል
።እነዚህና መሰል ችግሮች በየትኛውም ቦታ በየትኛውም ሰዓት ይደርሳል ።
ነገር ግን አንዳንድ ወንዶች ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሁሉ ሌሎችን ወይም ይህችን ዓለም ማማረር ተገቢ አለመሆኑን እያወቁ ወደ ቤት ሲመጡ ንዴታቸውን ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ላይ ለማብረድ ይሞክራሉ ።

ይህ መጥፎ ባህሪ ከላብህ ያንተ ወደ ቤት መግባት ለቤተሰቡ የሰይጣን መግባት ይሆናል ።
♦አንተ ስትመጣ ልጆችህ እንደ አይጥ አይናቸውን አፍጠው በየቦታው ይወተፋሉ ።ፀብ ለመጫር የሚያሰችል ስህተት ትፈልጋለህ ።
>ምግቡ ጨው ሊበዛበት ወይም ሊያንሰው ይችላል ።
>የለመድከው ቡና ላይፈላ ይችላል ።
>ቤቱ ላይፀዳ ይችላል ።
>ልጆቹ ሊረብሹ ይችላሉ ።...።ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ቤትህን ቀውጢ እንድታደርገው በር ይከፍቱልሃል ።ትጮሃለህ ።ልጆችህን ትሳደባለህ ።ትመታለህ .. በዚህ ወቅት ቤትህ ሰላምና ፍቅር የሰፈነበት መሆኑ ቀርቶ ሲኦል ይሆናል ።

~~~ አንተ ቤት በገባህበት ወቅት ልጆችህ ወደ ውጭ መውጣት ከቻሉ በረው ይወጣሉ ።ካልቻሉ ደግሞ አንተ የምትወጣበትን ሰዓት በጉጉት ይጠባበቃሉ ።

♦ በዚህ ዓይነት ቤተሰብ ውሰጥ
✔ግለኝነት እና አስፈሪ ሁኔታ ይነግሳል ።
✔ጭቅጭቅና ንዝንዝ ይበዛል ።
✔ቤቱ ይታመሳል ።
✔ሚስትህ ባንተ ትሳቀቃለች ።
✔ፊትህን ማየት ያስጠላታል ።
✔ደሰታ ይርቃታል ።

እናም እዉጭ በሚፈጠሩ የህይወት ዉጣ ዉረድ የእለት ተዕለት ተግባራት በመናደድ ንዴትህን ሚስትህ ጋር የምታበርድ ከሆነ ትዳርህ አደጋ ላይ እየወደቀ መሆኑን አትዘንጋ


በሚቀጥለዉ ክፍል እህቴ ሆይ የተሳሳተ አመለካከትን ማስወገድ እንዳለብሽ እንዳስሳለን
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

#ክፍል ➐ ይቀጥላል

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሰባት 7⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL




💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➏
#የተሳሳቱ_አመለካከቶችን_አሰወግጂ !

እመቤት ሆይ! አንቺ የቤትሸ ዘውድ ነሽ ።ብልህና አስተዋይ ሁኚ ።ወጪሸ ከገቢሽ ጋር የተመጣጠነ ይሁን ።ከሰዎች ጋር በፍፁም አትፎካከሪ ።በሌሎች አትቅኚ ።የሌሎች ኑሮ ላንቺ አይሆንም ፡ያንቺ ኑሮም ለሌሎች አይሆንም ፡
☞ያየሸውን ሁሉ ልብስ ፣
☞ያየሸውን ሁሉ ጌጣጌጥ ፣
☞ያየሸውን ሁሉ እቃ ባልሽ ከአቅሙ በላይ የሆነ ገንዘብ አውጥቶ ወይም ተበድሮ እንዲገዛ አታድርጊው ይህ ሞኝነት ነው ።ይልቁንም ገቢያችሁ እስኪያድግ ድረስ በትዕግስት ጠብቂ ።ብዙ ጊዜ ለጉራ ሲሉ አላሰፈላጊ ብክነት የሚያደሰቱት አላዋቂና ራስ ወዳድ ሴቶች ናቸው ።ባሎቻቸው በእዳ አንዲዘፈቁና የሚሰቶቻቸውን የማያቋርጥ ፍላጎት ለማሟላት አንዲናውዙ ያደርጓቸዋል ።

አንደዚህ አይነት ሚስቶች ያሏቸው ወንዶች ያላቸው አማራጭ ፍቺ ነው ።ትዳርን ዓላማና ትርጉም ያልተረዱ ሴቶች ትዳር ባል የሚስቱን ህፃናዊና ቁሳዊ ፍላጎቶች የሚያሟላበት ካምፕ ይመስላቸዋል ።እንደፈለጉ ሲሆኑ ባሎቻቸው ዝም እንዳሏቸውና በገንዘብ አወጣጣቸው ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ ይፈልጋሉ ።አንዳንዴ ከዚህም አልፈው ባላቸው ከአቅሙ በላይ ወጪ እንዲያወጣና ከዚያም ለኪሳራ ተዳርጎ ወደ ወንጀልና ሌሎች አልባሌ ተግባራት እንዲሰማራ ያደርጉታል ።

#ገደብ_የለሽ_ፍላጎቷ_ለፍቺ_ያጋላጣት_ሴት
✔በሰዎች ዘንድ ትናቃለች
✔ልጆቿም ይጠሏታል
✔ለብቸኝነት ኑሮም ትዳረጋለች
✔ሌላ ትዳር ውሰጥ የመግባት አድሏም የመነመነ ነው ።
✔ብታገባም ድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ይገጥማታል ።

እመቤት ሆይ ! ያየሸውን ሁሉ መመኘትን ትተሽ ምክንያታዊ ለመሆን ሞክሪ ።ሌሎችን ለመምሰል ከመሞከር ይልቅ ብዙውን ጊዜሸን ለልጆችሸና ለባልሸ ደህንነት በመጣር አሳልፊ ።ባልሽ በከንቱ ገንዘብ የሚያወጣ ከሆነ እንዲቀንስ አድርጊ ።ለአላስፈላጊ ነገሮች ወጪ ከማውጣት ይልቅ የተወሰነ ገንዘብ እየቆጠቡ ለክፉ ቀን ማስቀመጥ ትልቅ ጠቃሜታ አለው ።


እስኪ አንድ ታሪክ ላጫዉትሽ
ባል ነዋሪነቱ ውጭ ነዉ ሚስት አግብቶ ሶስት ልጆችን ወልዷል ።ሚስቱና ልጆቹ አዲስ አበባ ነው የሚኖሩት ።አልፎ አልፎ እየመጣ ያያቸዋል ።ሚሰት ገንዘብ ማባከን ከጀመረች ውሎ አድሯል ።የሱስ ተገዥ ሆናለች ፡ ባሏ የሚልክላት ገንዘብ ሊበቃት አልቻለም ።አንዴ እኔን አመመኝ ሌላ ጊዜ ልጆቹ ታመሙብኝ እያለች ጭማሪ ገንዘብ ታስልካለች ።ከሰዎች ብር ትበደራለች ።የቤት እቃ ሳይቀር ትሸጣለች ።ባሏ የገንዘብ አወጣጧን እንድታስተካክል ቢመክራትም በያሰመክራትም ልታሻሸል አልቻለችም ።አንደውም ባሰባት ።ሌት ተቀን እየሰራ የሚያገኘው ገንዘብ አላግባብ መባከኑ ሰላማረረው በሷ ስም ብር ላለመላክ ወሰነ ።በጓደኛው በኩል እየላከ እሱ የቤት ኪራይና የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ የዓመቱን አንዴ እንዲከፍልና አንዲሁም ለወር የሚበቃውን የቤት አስቤዛ በርከት አድርጎ እየገዛ አንዲያቀርብላት አደረገ ።እሷም ሆነ ልጆቿ ህክምና ካደረጉ ደረሰኝ ትጠይቃለች ።

ሚስት ሱሷ አደብ አሳጣት ።ለወር ተብሎ የሚገዛውን የቤት አስቤዛ በርካሽ እያወጣች መሸጥ ጀመረች ።ሳምንት ሳይሞላው ያልቃል ሄዳ አለቀብኝ ትላለች ።አንደገና ተግዝቶ ይሰጣታል ።አሁንም ያልቃል ።መጠየቅ ሲያሳፍራት ልጆቿን ቁርሳቸውን ዳቦ በሻይ አያበላች ምሳቸውን እንጀራ ብቻ ትቋጥርላቸዋለች እራትም ያንኑ ...ልጆቹ ሊበላቸው አልቻለም ፡፡ ትልቁ ልጇ ለምን?? ይላት ጀመር ።"አንዲህ የሚያሰቃያችሁ አባታችሁ ነው ።አምስት ሳንቲም አይልክልኝም ።ታዲያ እኔ ከየት ላምጣ ?ልውለድ ?"ትለዋለች ።ሁኔታውን ለአባቱ ማሳወቅ ፈለገ ።ወረቀት አወጣና አንዲህ ሲል ፃፈ ።


"ዳድ እንዴት ነህ ?እኛስ ደህና አይደለንም ።ቤት ውሰጥ ምግብ የለም ።የሚቋጠርልን እንጀራ ብቻ ነው ።ዳድ አሰብ እስቲ ሁሌ እንጀራ መብላት አይሰለችም ?አኔ ግን ዳድ የሚቋጠርልኝን ምግብ አልበላውም እጥለዋለሁ ከዚያ ጓደኞቼ ያበሉኛል አንድ በጣም የሚወደኝ ጓደኛ አለኝ ።ለእናቱ ችግርተኛ ጓደኛ አለኝ ብሎ ሰለነገራት ለሁለታችንም የሚሆን የተለያየ ምግብ ትቋጥርልናለች ።እከሌ በጣም ጥሩ ሰው ናት /ሰራተኛቸው ።ባልወልዳችሁም ልጆቼ ናችሁ አሳዲያችኋለሁ ትለናለች ።እናታችንማ ክፉ ሆነች ።በሆነ ባልሆነው ትጮህብናለች ።ወንድሜን ለምን ምሳ እቃህን አልጨረሰክም እያለች ሁልጊዜ ትቀጠቅጠዋለች እሱ ዝም ይላታል ።እኔ ግን "ካልጣፈጠው አንዴት ይጨርሰ ?"ስላት "አፍህን ዝጋ አንተ ጥጋበኛ "ትለኛለች ።ብታያት ሁሌ ጫት ማኘክ ሽሻ ታጨሳለች ...መጠጥም ትጠጣለች ...ለጫት መግዣ ገንዘብ ከየት እንደምታመጣ ታውቃለህ ?ጋሼ የአንተ ጓደኛ የሚያመጣልንን የዱቄት ወተት ፣ዘይት ማርማላት ምናምን እየሸጠች ነዉ ።ይህንን የነገረችኝ ሰራተኛችን ነች

አንዳንዴ ደግሞ እቤት አታድርም ።ለሰራተኛችን ስልክ ትደውልና ዛሬ አልመጣም በጊዜ ዘጋጉና ተኙ ትላታለች ።እሷም ትልቁን ፍራሸ አውርዳ ሁላችንንም አቅፍ አደርጋን ትተኛለች ።አባዬ አንተ ጋ ውሰደን ።ሰራተኛችም ከኛ ጋር ትሂድ ።ማሚን ግን ከፈለግክ ውሰዳት ከፈለግክ አትውሰዳት ።አኔ አያገባኝም ።ቻው ።ደብዳቤ አንደፃፍኩልህ ለማሚ አንዳትነግራት ።በጣም ትቆጣኛለች ልትመታኝም ትችላለች ።ወረቀቱን አጣጥፎ በፖስታ ካሸገ በኋላ ለአባቱ ጓደኛ ሰጠው ።

እሱም ለአባቱ ላከለት ።ሚሰት እንደልማዷ ለሰራተኛዋ ደውላ "ዛሬ አልመጣም ልጆቹን በጊዜ አስተኛችው "አለቻት ።እሷም "ሴቷ ልጅኮ በጣም አሟታል ።ኃይለኛ ትኩሳት እላት ብትመጪ ይሻላል አለቻት ።"ተያት ባክሽ ።ጉንፋን ነው ።እንቅልፍ ሲወስዳት ይተዋታል "አለቻት ።

ልጅቷ ግን እንቅልፍ ሊወሰዳት አልቻለም ታቃስታለች ሰራተኛዋ ተጨነቀች ምግብ ልታበላት ብትሞክርም እሺ አላለቻትም ።ሙቀቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ ለማስተኛት አዝላ ወዲያ ወዲህ ትላለች ።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ድንገት የግቢው በር ተንኳኳ ደነገጠች ...እኩለ ሌሊት ሆኗል ።ማን ሊሆን ይችላል ?እሷ አለመኖሯን ያወቀ ሌባ ሳይሆን አይቀርም አለች ።በድጋሚ በሩ በሃይል ተንኳኳ ።መጣችና የሞት ሞቷን "ማን ነው ?"አለች ።"አኔ ነኝ ክፈቺልኝ "አላት ።ባልየው ነበር ።ከፈተችለትና ገባ ።ሚስቱን "የታለች ?"ሲል ጠየቀ ።የለችም ።"

"የት ሄደች ?"
"የት እንደሄደች አላውቅም ።"
"ሌላ ጊዜም ውጪ ታድራለች ማለት ነው ?"
"አልፎ አልፎ ታድራለች ።"
"ታድያ ልጅቷን ለምን አዘልሻት ?"
"አሟታል ።"
"ምን ሆነች ?"
"ኃይለኛ ትኩሳት አለባት ።"
"እናቷ መታመሟን አላወቀችም ነበር አንዴ ?"
"ነግሪያት ነበር ።ጉንፋን ነው ይሻላታል አለች ::"ወዲያውኑ ጓደኛውን ጠራና ሀኪም ቤት ይዘዋት ሄዱ ።ጠዋት ላይ ልጆቹን ሲያያቸው በጣም አዘነ ...አመድ መስለዋል የቤቱ ዋና ዋና እቃ የለም ..ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን ጠራ አየሆነ ያለውን ነገርም አስረዳቸው ልጁ የፃፈለትን ደብዳቤም አነበበላቸው ።በጣም አዘኑ ይህ ሁሉ ሲሆን እሷ አልመጣችም ።ስልክ ተደወለላትና መጣች ። ፍቺ እንደሚፈልግ ነገራት እያለቀሰች "በፊት አንዲህ አይነት ባህሪ አልነበረኝም ኋላ ላይ ግን መጥፎ ጓደኞች አጋጠሙኝ ።በቀላሉ መውጣት የማልችለው አደገኛ ሱሰ ውስጥም አስገቡኝ ።ገንዘብ እጄ ላይ ሰለሌለ እነዚህን ነገሮች በቀላሉ ማግኘት እችል ዘንድ ውጭ ማደር ጀመርኩ እባክህን ይቅርታ አድርግልኝ ።ይህን ነገር ቀሰ በቀስ ለመተው እሞክራለሁ👇
አለች ፡፡ባል ጥላቻው ጫፍ ደርሶበታል ።"ትሰሚያለሸ አንቺን የማሰታምምበት ጊዜ የለኝም ።ምንም አይነት ዝባዝንኪም መሰማት አልፈልግም ።አሁኑኑ ፍቺው አንዲንፈፀም ነው የምፈልገው ?"ሲል አምባረቀ ።ሰዎቹም "መፍትሔዉ ፍቺ ብቻ ነው "አሉ ።ደነገጠች ከሆነም ልጆቼን ራሴ ነኝ የምይዘው አለች ።በሶስት ምክንያቶች ልጆቹን መያዝ አትችይም ።
አንደኛ የራስሽ የሆነ የገቢ ምንጭ የለሽም ።
ሁለተኛ ያለ ጥንቃቄ ቤት ውሰጥ በምታጫጭሻቸው ሱስ አምጪ ነገሮች ልጆች ተጠቂ ሆነው ሳያሰቡት ሱስ ውሰጥ ሊገቡ ይችላሉ ።
ሶስተኛ ውጪ ሰለምታድሪ ልጆቹ ብቻቸውን ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለች ።ልጆችም ሲጠየቁ በጭራሽ እሷ ጋር መሆን አንፈልግም አሉ ።
....እሺ መግቢያ ሰለሌለኝ ቤት ይገዛልኝ አለች
.....ያጠፋሸው ገንዘብ አይደለም መኖሪያ ቤት አስፓልት ይሰራ ነበር ።አሁን ግን ላንቺ ቤት የምገዛበት አቅምም ሞራልም የለኝም አለ
....ሸማግሌዎች ብዙ ከተወያዩ በኋላ ያለውን የቤት እቃ አንድትወሰድና አንዳለችውም የምትገባበት ስለሌላት ቢያንስ የኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ የምትገዛበት ገንዘብ እንዲሰጣት ወሰነው ፍቺው ተፈፀመ ።

ባል ቤት ተከራይቶ የቤት እቃዎችን ከሟላ በኋላ ክፈለ ሀገር የሚኖሩ እናቱን አምጥቶ ልጆቹንና ሰራተኛቸውን እሳቸው ጋር አስቀምጦ ወደ አገሩ ተመለሰ ።ከወራት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ከሰራተኞችዋ ጋር ትዳር መሰረት ።

#በክፍል ➑ ለዉድ ወንድሜ ለወደፊት ስታገባ ወይም ትዳር ላይ ካለህ መልካም ባህሪ መላበስ እንዳለብህ እንዳስሳለን

ክፍል ➑ ይቀጥላል...............
ምንጭ ፍቅርና ትዳር ከሚለዉ መፅሀፍ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ስምንት 8⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL





የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አለአባወራዉ
🌹
#መልካም_ባህሪ ይኑርህ
ከPart ➏ የቀጠለ


በቀላሉም ምክንያታዊ በሆነም ባልሆነም እለት በእለት በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች አትጨቃጨቅ

እሰቢዉ እስኪ እንዴት ብላ ነው ውሀ ቀጠነ እያለ ከሚጨቃጨቅና ከሚነዛነዝ ባሏ ጋር በደስታ መኖር የምትችለው ? ከሁሉም በላይ ግን አሳሳቢ የሚሆነው በእንዲህ አይነት ቤት ውሰጥ የሚያድጉ ልጆች የወደፊት እጣ ነው ፡፡ የወላጆቻቸው ጭቅጭቅ ሁሉንም ነገር በቀላሉ የሚቀበለው አዕምሯቸውና ልባቸው ውሰጥ ጠባሳ ይጥላል ።

♦ ይህ ጠባሳ በወጣትነት እድሜ ላይ በሚደርስበት ጊዜ አስፈሪ ፣
✔ቁጠኛና ድብርታም እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ።
✔ከቤት በመውጣትም በመጥፎ ጎዳና ይጓዛሉ ።
✔ከዚያም በአልባሌ ተግባር ላይ ከተሰማሩ ሰዎች እጅ ይወድቁና የተለያዩ ወንጆሎችን ለመፈፀም ይገደዳሉ ።
✔የአዕምሮ መቃወስ ሊያጋጥማቸውና በነፍስ ግድያ ወንጀል በመሰማራት የሰዎችን ህይወት አደጋ ውሰጥ ሊከቱ አለያም ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ ።
✔ምናልባት ተሳክቶላቸው ትዳር የመያዝ እድል ቢያጋጥማቸው በቤተሰባቸው ላይ ካንተ ያዩትን ተመሳሳይ ድርጊት ይፈፀማሉ ።


● ሰታትሰቲክሳዊ መረጃዎችና አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት በከፍተኛ ወንጀልና ነፍስ ግድያ ውሰጥ የሚዘፈቁት በአብዛኛው ከዚህ አይነት ቤተሰብ ውሰጥ የወጡ ልጆች ናቸው ።ራሰህን መቆጣጠር ባለመቻልህና ቤተሰብህን በማሰቃየትህ ለሚፈጠረው ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂ አንተ ነህ ።

#ስለዚህ_ወንድም !
ይህችን ዓለም ልንቆጣጠራት አንችልም ።
~መጥፎ ሁኔታዎች ፣
~መሰናክሎች ፣
~አሳዘኝ ክስተቶች የዚህ ዓለም ገፅታዎች ናቸው ።እያንዳንዱ ሰው በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች ያጋጥሙታል ።ሆኖም ግን ከሚገጥመው ችግር ጥንካሬን ነው መማር ያለበት ።

~~~አላሰፈላጊ ድርጊት ውሰጥ በመግባት ከችግር ላይ ችግር ከመደራረብ ይልቅ መሰናክሎችን በጥንካሬ መጋፈጥና መፍትሄ መፈለግ ብልህነት ነው ።

የሰው ልጅ በርካታ ቀላልና ከባድ ችግሮችን የመቋቋም ችሎታ አለው ።ነገር ግን ለችግሮች የምንሰጠው ምላሽ ከሰው ሰው ይለያል ።ለዚህ ነው አንዳንዴ ሁለት ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸው ሰዎች አንዱ ሲበሳጭ ሌላኛው ሁኔታውን በፀጋ ተቀብሎ ሲረጋጋ የሚታየው ።ስለዚህ መረጋጋትን መምረጡ የተሻለ ነው ።

#ለምሳሌ አንድ መጥፎ ነገር አጋጠመህ እንበል ይህ ችግር ከእላት ተእለት ህይወት ጋር የተቆራኘና ከቁጥጥርህ ውጭ በሆነ መንገድ የተፈጠረ ወይም ደግሞ አንተ በፈጠርከው ስህተት የመጣ ሊሆን ይችላል ።

#በመጀመሪያው ሁኔታ ንዴትና ብሰጭት በምንም መልኩ አይጠቅምም ።ተገቢም አይደለም ።ለችግሩ መፈጠር ተጠያቂ አለመሆንህን ተገንዝበህ ለመረጋጋት ጣር ።

#ችግር_በሁለተኛው መንገድ የተፈጠረ ከሆነ ደግሞ መፍትሄ አፈላልግ ።መሰናክሎች በሚገጥሙህ ጊዜ ከተረጋጋህና ራሰህን ለመቆጣጠር ከሞከርክ በቀላሉ መቅረፍ ትችላለህ ።ከችግርህ ላይ ተጨማሪ ችግር ወደሚፈጥርብህ ብሰጭት አትሄድም ።

~~~ብልህ ሰው ማለት ለችግሮች እጁን የማይሰጥ ሰው ስለሆነ ትዕግስተኛና ብልሀተኛ ሁን ።
☞ከኛ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ለተፈጠረ ችግርስ መበሳጨት ምን ይጠቅማል ?
☞ከዚህም በላይ አንተ ላጋጠመህ ችግር ልጆችህንና ሚስትህን ለምን ታሰቸግራለህ ?
☞ሚስትህ የራሷን ግዴታና ኃላፊነት እየተውጣች ነው ።ቤቷንና ልጆቿን ትንከባከባለች ።ልብስ ታጥባለች ።ምግብ ታበሰላለች ።ቤት ታፀዳለች ።ታዲያ ይህቺን ሴት አይዞሽ በማለትና በማበረታታት ፋንታ ላንተ ችግር እሷን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ነው ?

~~~ልጆችህም በበኩላቸው የየራሳቸው ድርሻ ይኖራቸዋል ።
☆ከአባታቸው ደስታን እንጂ ስቃይን አይፈልጉም ።መልካም ነገሮችን አስተምራቸው ።
☆ትምህርታቸውን እንዲያጠኑ አበረታታቸው ።
ቤተሰቦችህን በተቆጣና በተኮሳተረ ፊት መመልከትህ አግባብነት የለውም ።
☆የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እንድታሟላላቸው ፣እዝነትና እንክብካቤን እንድትቸራቸውና በጥሩና በተረጋጋ መንፈስ እንድታዋራቸው ይሻሉ ።አለበለዚያ ይጠሉሃል ።
☆ትዕግስት ማጣትህ ለልጅችህና ለሚስትህ የስቃይ ምንጭ ከመሆኑ ባሸገር የራስክን ጤንነትም እንደሚጎዳ ማወቅ አለብህ ።ሥራህን በትክክል ልትሰራ አትችልም ።በመሆኑም ስኬት ይርቅሀል ።ሁለም ቢሆን ደሰታኛ ለመሆንና ችግሮችን በተገቢው መልኩ ለመፍታት መሞከር የተሻለ ዘዴ ነው ።


~~~ ቁጣ ችግሮች እንማይቀርፍና እንደውም ተጨማሪ ችግር እንደሚያመጣብህ ማወቅ አለብህ ።ለችግርህ ተገቢውን መፍትሄ ታገኝ ዘንድ ቤትህ ውሰጥ ረፍት በማድረግ አዕምሮህን ቤተሰብህን ፈገግታ በተሞላበት ፊት አናግር ።ከነሱ ጋር በመቀላለድ ቤትህ ውሰጥ ደስታ እንዲሰፍን አድርግ ።አብረህ ብላ ጠጣ ይህን ካደረግክ አንተም ሆነ ቤተሰብህ ደስተኛ ህይወት ይኖራችኋል ።ችግሮችህንም በቀላሉ ትፈታለህ ።


በቀጣዩ ክፍል ለባልሽ ምቹ መሆን እንዳለብሽ እንዳስሳለን
#ክፍል ➒
ይቀጥላል......

#ምንጭ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አብሀ
ክፍል :- ዘጠኝ 9⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➐
#ለባልሸ_ምቹ_ሁኚ

ቤትሰብን የማስተዳደር ኃላፊነት የሱ በመሆኑ ወንዱ በትከሻው ላይ ትልቅ የህይወት ሸክም ተጥሏል ።ይህን ኃላፊነት ለመወጣትም በርካታ መሰናክሎችን ማለፍ ይኖርበታል ።
>የገበያ መቀዝቀዝ ፣
>ኪሳራ ፣
>የኑሮ ውድነት ፣
>የትራንስፖርት እንደልብ አለመገኘት ፣
>የመንገድ መዘጋጋት ፣
>የቀኑ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ አለመመቻቸት >የጓደኛና የሰራ ባልደረባ ግጭት ፣
>የስራ ጫና ወዘተ ሊያጋጥመው ይችላል ።

የቤተሰብ ኃላፊ በሆነ ወንድ ላይ የሚደርሱ ጫናዎች በርካታና ዘርፈ ብዙ ናቸው ።ለዚህ ነው የወንዶች አማካይ የእድሜ ጣሪያ ከሴቶች ያነሰው ።የሰው ልጅ የህይወትን ጫና መቋቋም ይችል ዘንድ የሚያዳምጠውና አይዞህ የሚለው ሰው ያስፈልገዋል ።ባልሸም ከዚህ የተለዬ አይደለም ።


እነዚህ ጫናዎች ብቸኝነት አንዲሰማውና ምቾትና እፎይታ እንዲፈልግ ሊያደርጉት ይችላሉ ።ይህን ምቾትና እፎይታ የሚያገኘው ደግሞ ከሚስቱና ከቤተሰቡ ነው ።ስለዚህ ፍላጎቶቹን ለይተሸ አወቂ ።


ከሰራ ወደ ቤት በሚመለሱበት ወቅት ዘና እንዲልና ፍላጎቴን ለማሟላት ደፋ ቀና የምትል ሚሰት አለችኝ ብሎ እንዲያስብ አድርገው ።ገና እንደገባ ነገር በመጀመር ስሜቱን አትጉጂው ።ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ለሱ ከማቅረብሸ በፊት አረፍተ የሚያደርግበት ሰዓት ሰጪው ።

#ወደ_ቤት_ሲገባ
✔በፈገግታና ሞቅ ባለ ሰላምታ ተቀበይው ።
✔እርቦት ደክሞት አንደሆነ ወይም ሌላ ችግር ካለበት ጠይቀው ።ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆነ ጥሩ አድማጭና ተቆርቋሪ ሁኚ ።
✔ለሱ ያለሽን ልባዊ ጭንቀት ለመግለፅ ሞክሪ ።
✔ያጋጠመው ችግር እሱ እንዳሰበው ግዙፍና ሊፈታ የማይችል አለመሆኑን እንዲያጤን አርጂው ።
✔ችግሩን መቋቋም እንዲችል የማበረታቻ ድጋፍ ሰጪው ።


ለምሳሌ የሚከተለውን ልትይው ትችያለሽ ።"ይህ ነገር ባንተ ላይ ብቻ አይደለም የደረሰው ።እነ እከሌም ተመሳሳይ ችግር ደርሶባቸው ነበር ።ደግሞም በጥንካሬና በትዕግስት የማይፈታ ነገር የለም ።የሰው ልጅ ማንነት የሚፈተሸው እኮ በችግር ነው ።ሁሌ በደስታ መኖርን መጠበቅ የለብህም ።አይዞህ የኔ ወንድም በፈጣሪ አገዛ ችግሮችንን በቀላሉ እንፈታዋለን "በይው ።

ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል ሀሳብ ካለሸ አንዲህ ብናደርግስ? በይው አለያ ደግሞ መፍትሄ ማምጣት ትችላለች የምትያት ጥሩ ጓደኛ ካለችሸ ለእሷ አማከሪያት ።

#እመቤት_ሆይ !
✉ በችግር ወቅት ባለቤትሽ ያንቺን ፍቅርና ክትትል ይፈልጋል ።አንደ ስነልቦና አማካሪና አንደ ሚስት እሱን መንከባከብና መርዳት አለብሽ ።የስነልቦና አማካሪ ሊሰጠው የሚችለውን ድጋፍ አንቺ ልትሰጭው አንደምትችይ አወቂ ።

✉እሱን ለማጠናከርና ለመደገፍ ያለሽን ችሎታ ዝቅ አድርገሽ አትመልከቺ ።ለባለቤትሸ ደህንነት ካንቺ በላይ የሚጨነቅ ሰው የለም ።

✉አንቺ ለሱ ከምታደርገው ጥረትና ልፋት ጥንካሬን ይማራል አዕምሮውን ወጥሮ የያዘውን ችግርም በቀላሉ ይፈታዋል ።

ይህ ደግሞ የጋብቻ ህይወታችሁ አንዲለመልምና እንዲጠናከር ያደርገዋል ።

#በክፍል ➓☞ ትዳር ያሰብክ ወንድሜ ሆይ ወይም ትዳር ላይ ያላችሁ ወንዶች ሆይ አለአግባብ ማማረር እንደሌለባችሁ እንዳስሳለን
ቀጣዩ ክፍል ይቀጥላል.......

#ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✋አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

☝️ በሰሞኔ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በደሴ ከተማ ከተለያዩ የወሎ አቅጣጫዎች ከቆቦ ከአላማጣ ከመርሳ ከወርጌሳ ከወልደያ ወዘተ የመጡ ከ100,000 በላይ ተፈናቃዮች በደሴ ከተማ በአራት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች መጠለያ ተሰጥቷቸዉ በደሴ ከተማ ህዝብ ትብብር አብረን ያገኘነዉን እየተካፈልን ነዉ፡፡ በተጨማሪ ሴቶች ነፍሰጡሮችን በመለየት በደሴ ከተማ ህዝብ ተከፋፍሎ በመኖሪያ ቤት አስጠልለዉ ይገኛሉ፡፡
☞ለምሳሌ በእኛ ሰፈር ነዋሪዉ ተሰባስቦ ወደ አራት መቶ የሚሆኑትን ተከፋፍለን በየመኖሪያ ቤታችን ይዘናል...ሌሎችም ሰፈሮች እንዲሁ ተፈናቃዮችን ሁሉም በአቅሙ ይዞ አብረዉ የምንበላዉን እየበሉ የምንጠጣዉን እየጠጡ በመተሳሰብ አብረን እየኖርን ነዉ፡፡ግን ከቤት ንብረት ተፈናቅሎ መምጣቱ የህሊና ጠባሳ ስለሆነ አላህ ሰላም አዉርዶ ወደ ሀገራቸዉ የሚመለሱ ያድርጋቸዉ

♦ ተፈናቃዮች ወደ ደሴ ሲመጡ የደሴ ከተማ ከሌላ አገር መጥተዉ የሚሰሩ በሆቴል በአልጋ እና በምግብ ጭማሪ ያደረጉ በህዝቡ ጥረት በአንድ ቀን ዉስጥ ጭማሪ የጨመሩትን በቁጥጥር ስር አድርገን ወደ እስር ቤት እንዲገቡ አድርገን ከተፈናቃይ ወንድም እህቶች አባት እናቶቻችን ጋር አብረን እየኖርን እየሆነ ይታወቃል፡፡

ግን በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨዉ ደሴ ተይዟል ቦንብ ፈንድቶ ይሄን ያህል ሙቷል የሚባለዉ ዉሸት መሆኑን ሁሉም ሊያቀዉ ይገባል፡፡

♦♦ #ማሳሰቢያ_ለደሴ_ከተማ_ነዋሪዎች

በተለያዩ መስጊዶች እራስን መከላከል በሚል የዉትድርና ስልጠና ተጀምሯል ፡፡ ይሄ ራስን መከላከል ዋናዉ አላማዉ ዉትድርና መሄድ ሳይሆን ደሴ ምን እንደሚፈጠር ስለማይታወቅ እኛ የምንሸሽበት የለንም የሆነ ችግር ቢመጣ ከተማችንና ማህበረሰቡን ለመጠበቅ ታስቦ የተጀመረ ነዉ ..አሁንም ቢሆን ከፀጥታ አስከባሪዎች በላይ የደሴ ህዝብ ነቅቶ ከተማዉን እየጠበቀ ነዉ፡፡
መቼም ቢሆን ለህዉሀት እጅ አንሰጥም ጥለን ሸሽተን ከተማችንን አንለቅም..ህዉሀት በኢትዮጲያ በተይ በደሴ ከተማ እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሰራዉን ግፍ ማንም የሚረሳዉ አይደለም እነሱ የቁስል ላይ እንጨት መሆናቸዉ ይታወቃል እናም ዛሬ ድረስ የማይፈታ ሙስሊሙን የቤት ስራ ሰጥተዉት ሂደዋል እናም የጥላት ጦር መቼም ጥላት ነዉ ፡፡ይሄን ምክንያተ በመማድረግ እራሳችንን ወገኖቻችንን ቤተሰቦቻችንን ለመጠበቅ ስልጠና ተጀምሯል፡፡

☝️ ስልጠናዉ ደግሞ ከሱብሂ ሶላት ቡሀላ እስከ 1:30 ባለዉ ሰአት ነዉ፡፡፡
ስልጠና ከሚሰጥባቸዉ ቦታዎች ለምሳሌ
☞በደወይ ሜዳ መስጊድ ወደ 400 የሚሆኑ ወጣቶች ይሄዉ 15 ቀን ሆናቸዉ
☞በሸዋበር መስጊድ ዛሬ 4ተኛ ቀን ሁኗል
☞በአረብ ገንዳ መስጊድም ምዝገባ እየተካሄደ ነዉ
☞በሰኞ ገበያ በባድራ ግቢ ስልጠናዉን ሊጨርሱ ነዉ

☞በየሰፈራችሁ ባለዉ መስጊድ ማንኛዉም ወጣት ተመዝገቡ
☞የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች መሰልጠን የሚፈልግ ካለ አብሮ መሰልጠን ይቻላል

በመስጊጅ የተመዘገብን እየሰለጠንን ነዉ ፡፡ይሄ እድል መቼም ቢሆን የማይገኝ እድል መሆኑን አንዘጋ

እኔም ቢያንስ 20 የሚሆኑ ጓደኞቼ ጋር አብረን የወታደራዊ ስልጠናዉን እየሰለጠንን ነዉ እናም አብረን ይሄን ችግር ተባብረን እንለፈዉ
ይሄን መልዕክት ለተዘናጋ ለተኛዉ ማህበረሰብ በተንተን አድርጉትና አዳርሱት

✍ አሚር ሰይድ
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስር 🔟


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
5⃣
#አላግባብ_አታማር !

የህይወት ውጣ ውረዶች ብዙ ናቸው ።በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር የተሟላለት አንድም ሰው የለም ።ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ችግር ሲገጥማቸው በትዕግስት የማሳለፍ ባህሪ አላቸው ።ያጋጠሟቸውን ችግሮች በውስጣቸው ይይዙና አሰፈላጊ ካልሆነ በሰተቀር ለሰው አያወሩም ።

~~~ አንዳንድ ደካማ ሰዎች ግን ምንም ያጋጥማቸው ምን ድብቀው መያዝ አይችልም ።ላገኙት ሰው ሁሉ >እንዲህ ሆኜ ፣
>እንዲህ ገጥሞኝ ፣
>እንዲህ ደርሶብኝ በማለት ብሶታቸውን መዘርገፍ ይጀመራሉ ።የሌሎችን ደሰታ ለማደፍረስ ያግኙ በየቀኑ ያጋጠሟቸውን ችግሮች ከመዘርዘር ወደ ኋላ አይሉም ።በወጪ ፣በታክሲ ፣በጓደኛ ፣በመጥፎ የሰራ ባልደረባ ፣በስራቸው ፣በህመም ፣በሐኪም ወዘተ ይማረራሉ ።

ለህይወት ያላቸው አመለካከት ጨለምተኛ ነው ።ምንም አይነት ጥሩ ነገር አይታያቸውም ።ራሳቸው ተሰቃይተው ሌሎችንም ያሰቃያል ።በተለይ ደግሞ ቤተሰቦቻቸውን ።

#ውደ_ወንድም_ሆይ !
☆ሁሌ ማማረር ምን ጥቅም አለው ?
☆ምንስ ውጤት ያስገኛል ?
☆የታክሲ ሾፌር ሰላበሳጨህ ቤተሰቦችህ ምን ማድረግ ይችላሉ ?
☆ስራህ በምትፈልገው መልኩ ባለመሄዱሰ ሚስትህ ለምን ትወቀሳለች?
☆ ይህ መጥፎ አመለካከትህ ከቤተሰብህ እንደሚያርቅህ ታውቃለህ ?

✔ልጆችህ በአንተ ይበሳጫሉ ።
✔ቤታቸውን ይጠላሉ ።
✔ከቤት በመውጣትም ለአጉል ልማዶችና ወንጀሎች ሊዳረጉ ይችላሉ ።
✔የህን ባያደርጉ እንኳ ድርጊትህ አዕምሯቸው ውሰጥ የሚጥለው ጠባሳ ቀላል አይደለም ።ወደ ቤት በምትገባባት ጊዜ ችግሮችህን ለመርሳት ሞክር ።ከቤተሰብህ ጋር ደስተኛ ሁን ።አብረህ ተመገብ ፣ሳቅ ተጫወት ።


🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
6⃣
#ጠብ_ጫሪ_አትሁን

አንዳንድ ሰዎች በሆነ ባልሆነው ነገር በመምዘዝ ጠብ መጫር ይወዳል ።
● ጠረጴዛው ለምን ቆሸሸን ?
● እራት ለምን አልቀረበም ?
● ይህ የአበባ ማስቀመጫ ለምን ወደቀ ?
● ይህን እቃ ከዚህ ቤት አውጡ አላልኩም ወይ ? ወዘተ በማለት ይጨቃጨቃሉ ።ይህ ባህሪ በቤተሰብ መካከል ጭቅጭቅና ግጭት ይፈጥራል ።ብሎም የቤተሰብ መበታተንን ያስከትላል ።ወንዶች ለሚስቶቻቸው ይህን ስሩ ይህን አትስሩ የማለት መብት የላቸውም ማለት አይደለም ።


በዚህ መፅሐፍ የመጀመሪያ ክፍል ሴቶች የባሎቻቸውን መብት ማክበር እንዳለባቸውና ባሎቻቸው በቤት ውሰጥ ጉዳዮች ላይ አሰተያየት በሚሰጡበት ጊዜ መቀበል እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።

~~~ ወንዶችም የቤት አስተዳዳሪ እንደመሆናቸው በቤቱ ውሰጥ ጥሩ ተሳታፊ ለመሆን ከፈለጉ ብልህ መሆንና በተገቢው ሁኔታ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ።ይሁን እንጂ ወንዶች ብዙ ጊዜ በቤት ውሰጥ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ በቂ ጊዜና ልምድ ስለማይኖራቸው ቤቱን ለሚስቶቻቸው ይተዋል ።በዚህ ሁኔታ ሚስት ቤቱን እንድታንቀሳቅሰ ነፃነት መሰጠት ያሰፈልጋል ።

♦ነገር ግን በሀይል ሳይሆን በምክር አንዳንድ ነገሮችን ለሚስቱ ማስታወስ ይችላል ።ብልህ ሴት ባሏ ምን እንዳሚፈልግ ለማወቅ ዝግጁ ናት ።ፍላጎቱን ካወቀችም ያን ለማሳካት ትጥራለች ።ለቤተሰባቸው ደህንነት የሚያስቡ ጥንዶች በሰከነ ሁኔታ በመነጋገር ስምምነት ተፈጥረው በቤታቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳቸውን ተሳትፎ ያደርጋሉ ።

♦ ነገር ግን አንዳንድ ወንዶች እንሳተፋለን በሚል ማድቤት ገብተው ውሀ ቀጠነ እያሉ ሚስቶቻቸውን ይጨቀጭቃሉ ።ይህ የትዳር ህይወትን የሚበጠብጥ አደገኛ ባህሪ ነው ።

>>>> በሆነ ባልሆነው የሚጨቃጨቅ ባል ያላት ሴት ባሏን የምትንከባከብበትና ፍላጎቱን ለማሟላት የምትጥርበት ወኔ አይኖራትም ።ባሌ በእኔ ስራ ሰለማይረካ ለምን እለፋለሁ የሚል ስሜት ሰለሚያድርባት እንኳን ጥቃቅን ፍላጎቶቹን ልታሟላ ቀርቶ መሰረታዊ ነገሮችንም ትነፍገዋለች ።ከዚህም አልፎ የአፅፋ እርምጃም ልትወስድ ትችላለች ።ቤቱ የጦር እውድማ ይሆናል ።

>>>> ይህ ተደጋጋሚ ጭቅጭቅ ለፍቺ መንገድ ይከፍትና የቤተሰብ መበተን ይከሰታል ።በዚህ ሁኔታ ላይ ሴቷ ልትወቀሰ አይገባም ።ምክንያቱም ብልህና አስተዋይ የሆኑ ሴቶች ሳይቀሩ በባሎቻቸው ጭቅጭቅ ትዕግሰታቸው ተሟጦ ከቤት የሚወጡበት ሁኔታ አለ ።


♦አንድ ሰው ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ "ሚስቴ ከሁለት ወር በፊት ቤታችንን ጥላ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄደች "ሲል ይከሰሳል ።
......እሷ ስትጠየቅ ደግሞ"ባለቤቴ በቤት አያያዜ ፣በማበሰለው ምግብና አጠቃላይ በቤቱ ሁኔታ ሁሌ ይጨቀጭቀኛል ።ይህ ነገር ሰላም ሰለነሳኝ ሰላም ፍለጋ ቤቱን ለቅቄለት ሄድኩ ብላለች ።

____በቤት ውሰጥ ያለውን ሥራ ማከናወን የሴቶች ተግባር መሆኑን ወንዶች ልብ ሊሉ ይገባል ።ይህን መብታቸውን መንፈግና እነሱን አሻንጉሊት ማድረግ ተገቢ አይደለም ።
____የቤት ውስጡን ስራ በፈለጉት መልኩ እንዲያካሂዱ መፍቀድ ብልህነት ነው ።ይህ ከሆነ ሚሰት ስራዋን በጥሩ ሁኔታ ትወጣለች ።
♡ይህ አንተንም ደስተኛ ያደርግሀል ።
♡ቤትህም የደሰተኛ ቤተሰብ መኖሪያ ይሆናል ።


በሚቀጥለዉ ክፍል እመቤቴ ሆይ ባልሽን አመስጋኝ መሆን እንዳለብሽ እንዳስሳለን
#ክፍል ➊➊ ይቀጥላል

#ምንጭ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ አንድ 1⃣1⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➑
#አመስጋኝ_ሁኚ

አንድ ሰው ለፍቶና ደክሞ ያፈራውን ሀብት ለሰዎች የሚሰጥ ከሆነ ከሚሰጣቸው ሰዎች የሚያገኘው ምስጋናና አድናቆት ከፍተኛ እርካታ ይሰጠዋል ።ገንዘቡን በበጎ ተግባር ላይ ማዋልና የተቸገሩ ሰዎችን መርዳትም የአለት ተእለት ተግባሩ ይሆናል ።

ነገር ግን በሚሰጠው ነገር ምስጋና የማያገኝ ከሆነ መልካም ነገሮችን የመሰራት ፍላጎት አይኖረውም ።ላልመሰገን ለፍቼ ያገኘሁትን ገንዘብ ለምን አወጣለሁ?? የሚል ሰሜት ያድርበታል ።የሰው ልጅ ምስጋና እና አድናቆት ይፈልጋል ። ምስጋና እና አድናቆት የስጦታ ተግባር ማጠናከሪያ ሚስጥሮች ናቸው ።

#እመቤት_ሆይ !ያንቺ ባልም የሰው ፍጡር ነው
እንደማንኛውም ሰው ማመስገንና መደነቅን ይፈልጋል ።ምስጋና የሚቸረው ከሆነ ቤተሰቡን በተቻለው መጠን ለማስደሰት ይጥራል ።ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታው አድርጎም ይቆጥረዋል ።ይህን ተግባር መፈጸም ሸክም አይሆንበትም ።

ለምሳሌ
>የቤት እቃ ፣
>የቤት አስቤዛ ፣
>ለእንቺና ለልጆቻችሁ ልብስና ጫማ ገዝቶ ሲመጣ ፣
>ቤተሰቡን ለሽርሽር በሚወሰድበት ወቅት ፣
>የኪስ ገንዘብ በሚሰጥሸ ጊዜ ምስጋና አቅርቢለት ።


ላንቺ ስጦታ ብሎ የገዛው ልብስ ፣ጫማ ወይም ሌላ ነገር ፋሸን ያለፈበት ወይም ጥራት የጎደለው ቢሆን አንኳ በጣም አንደወደድሸው ንገረው ።አድናቆትሸን በመግለፅ ባለቤትሽ ሰሜቱ አንዲታደሰና ለድካሜ ሁሉ ምንዳ አለኝ ብሎ እንዲያስብ ታደርጊያለሸ ።

ግዴታው ስለሆነ ወይም ማድረግ ስላለበት ያደረገው ነው ብለሸ በማሰብ ለቤተሰቡ የሚያደርገውን አሰተዋፅኦ ከማቀጨጭ ተቆጠቢ ። ይህን የምታደርጊ ከሆነ ሰሜቱ ይጎዳና ለቤተሰቡ ደህንነት አይጨነቅም ።ገንዘቡንም ለሌሎች ሰዎች ወይም ለራሱ ብቻ ማውጣትን ይመርጣል ።

አንዲት ጓደኛሸ ወይም ዘመድሸ አንድ ክሪም ወይም አበባ ቢያበረክቱልሸ ደጋግመሸ ታመሰግኛቸዋለሸ ።ታዲያ ባለቤትሽ ላንቺ ላለው የዘወትር አሳቤና ትኩረት ብታመሰግኚው ምን ይልሻል ?ምሰጋናሸን መግለፅሽ ዝቅ ያደርገኛል ብለሸ አታሰቢ ።ይሉቁንም በባልሸ ዘንድ ይበልጥ አንድትፈቀሪና አንድትወደጂ ያድርግሻል ።


✿ በፈፀመችው ስህተት ከባለቤቷ ምንም አይነት ስጦታ እንዳታገኝ የሆነችውን የቀጣይዋን ሴት ታሪክ አንብቢ ።
ባሏ አንዲህ ብሏል ።"ገና አንደተጋባን ስሞን ነው ።በወቅቱ የበዓል ኤክስፖ ስለነበር ለሚሰቴ አንድ ነገር ልግዛላት አልኩና ኤግዚቢሽን ማዕከል ገባሁ ።ብዙ ነገሮችን ካየሁ በኋላ ሻርፕ ልገዛላት ወሰንኩ ።ጥሩ ነው ያልኩትን ሻርፕ ስጠይቅ ሰማንያ ብር አሉኝ ።እሷ የምትገዛቸው ሻርፖች ርካሸ ዋጋ ያላቸው በመሆኑ ይህ ውድ ሰጦታዬ በጣም ያስደስታታል አልኩና ገዛሁላት ።

ወስጄ ሰሰጣት ደስ አላላትም ።"ስንት ገዛሀው ?አለችኝ ።
...."ሰማንያ ብር"አልኳት ።ኤሌክትሪክ ልትጨብጥ ምንም አልቀራት ።
....."ይሄ መርካቶ ሰላሳ ብር ነው ።የሚሸጠው ።በዚያ ላይ ይነጫጫል ።ቀለሙም ቢጫ ነው ።አያምርም....አለች ።
.....በጣም አዘንኩ ።በወቅቱ ሰማንያ ብር ቀላል ብር አልነበረም ።አከለችና
...... "እኔ በሞት አለብሰውም የሚመልሱልህ ከሆነ ውሰድና መልሰው "አለችኝ ።እኔም "ሂጄ መልሱ አትመልሱ አልልም ።ሰትፈልጊ ልበሸው ካልፈለግሽዉ ደግሞ የቤት መወልወያ አድርጊው"አልኳት ።ከዚያ በኋላ ለሷ ብዬ ምንም ነገር መግዛት አንደሌለብኝም ወሰንኩ ።
ሚሰት በበኩሏ አንዲህ ብላለች ፦"ይህ ክስተት ከተፈፀመ አሰራ ሁለት ዓመት ገደማ ሆኖታል ።በወቅቱ አፍላ ወጣት ነኝ ።ብስለት የለኝም ።ልምድም የለኝም ።በወቅቱ የታየኝ የሰላሳ ብሩን ሻርፕ ሰማንያ ብር መግዛቱና አምሳ ብር ማክሰሩ አንጂ በንግግሬ የሱን ሞራል መጉዳቴ አይደለም ።ነገሩ በዚሁ ቢቆም ጥሩ ነበር ።

~~~ አንዴም እንዲሁ የፕላስቲክ ክዳን ያላቸው አምስት ተደራራቢ የወጥ ሰሀኖች በአንድ መቶ ሰላሳ አምሰት ብር ይሸጡ ነበር ።እሱ ከአዟሪዎች ላይ ሶስቱን በሁለት መቶ ብር ገዝቶ መጣ ።በጣም ተናድጄ ተናገርኩት ።ያኔ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለቤታችንም ምንም አይነት እቃ ላይገዛ ወሰነ ።ወደ ኋላ ተመልሼ ያደረግኩትን ነገር ሳሰበው በጣም ተሳስቻለሁ ።እውቀትም ብልሃትም የጎደለው ተግባር ነው የፈፀምኩት ።

ባለቤቴ ግን ይቅር ብሎ በተወው መልካም ነበር ዛሬም ድረስ በውሳኔው እንደፀና ነው ።ብር ይሰጠኛል አንጂ ምንም ነገር አይገዛልኝም ።ይህ ተገቢ አይመሰለኝም ምክንያቱም አሱም ጥፋት አለበት ።ጥሩ ተከራካሪ ቢሆንና እቃዎቹን በተገቢው ዋጋ ቢገዛ ኖሮ እኔም አንደዛ የመናገር አድል አይፈጠርልኝም ነበር ።

የሆነ ሁኖ በኔ የደረሰው ነገር በሌሎች ሴቶች ላይ አንዲደርሰ አልፈልግም ።ሚስቶች ባሎቻቸው ምንም ይሰጧቸው ምን የተገዛበት ዋጋና የእቃው ጥራት የፈለገውን ያህል የተራራቀ ይሁን :ምንም አይነት አሉታዊ አሰተያየት ሳይሰጡ ስጦታቸውን አመሰግነዉና ስቀው እንዲቀበሉ እመክራለሁ ።
ብላለች

#ክፍል ➊➋
ይቀጥላል
......
👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ ሁለት 1⃣2⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
6⃣
#አባብላት_እዘንላት

አንድ ወንድ ሁሉ ሴትም በአዕምሮዋ የተለያዩ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ ።ደሰታ ፣ሐዘን ፣ቁጣ ፣ብሰጭት ወዘተ ።
በቤት ውሰጥ ስራ ትደክማለች ።
◇ ልጆች ሊያበሳጯት ይችላሉ ።
◇ ከሌሎች ሰዎች ትችት ሊደርሰባት ይችላል ።
◇ ከጓደኞቿ ጋር ፉክክር ውሰጥ ልትገባ ትችላለች ።
◇ በአጭሩ ሴት ልጅ ብዙ ችግሮች ያጋጥሟታል ።ችግሮቹ ደግሞ በእጅጉ ይጎዷትና በሆነ ባልሆነው ተጨቃጫቂ እንድትሆን ያደርጓታል ።
#ምከንያቱም ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ስሜታዊ በመሆናቸው ያጋጠማቸውን ችግር እንዲህ ማሳለፍ አይችሉም ።ችግራቸውን ነግረውት የሚቆረቆርላቸው ሰው ይፈልጋል ።ስለዚህ ወንዶች ችግራቸውን ለያዳምጧቸው ይገባል ።ምከንያቱም ለሚስቶቻቸው ከነሱ በላይ የቀረበ የለምና ።

#ውድ_ወንድም_ሆይ !
ሚስትህ በተበሳጨችና በተቆጣች ጊዜ ያለችበትን ሁኔታ ለመረዳት ሞክር ።
☞ ወደ ቤት ስትገባ ዝም ካለችህ አንተ ሰላምታ አቅርብላት ።ይህ አንተን ዝቅ አያደርግህም ።
☆ ፈገግታ በተሞላበት ሁኔታ አናግራት ።መጥፎ ፊትን አሰወግድ ።
☞ በቤት ውሰጥ ስራ አግዛት ፡በምንም መልኩ እሷን ከመበሳጨት ተቆጠብ ።
☆ አትሰደባት ፡ለማውራት ፈቃደኛ ካልሆነች ተዋት ።ምን ሁነሸ ነው እያልክ አትጨቅጭቃት ።ማውራት ከፈለገች አዳምጣት ።
☞ ሰትነግርህ ሁኔታው ከሷ ይልቅ አንተን እንዳሰጨነቀህ ግለፅላት ።አንድ አዛኝና ተቆርቋሪ አጋር ለችግሯ መፍትሄ በመፈለግ እርዳት ትዕግስተኛ እንድትሆን አበረታታት ።
☆ በብልሀትና በምክንያታዊነት የሚያጋጥሟትን መሰናክሎች ሁሉ እንደተራ ነገር እንድትቆጥር አድርግ ።
☞ ጠንካራ ሴት እንድትሆንና የብሰጭቷ መንሰኤ የሆነውን ነገር እንድታሰወግድ እርዳት ።
☆ ተንከባከባት ፣ይህን ስታደርግ ያንተ እገዛ ጠቃሚ ሆኖ ታገኘዋለች ።ህይወት በሰላማዊ ሁኔታ ይቀጥላል ።


✿ በተቃራኒው ችግር በገጠማት ጊዜ መጥፎ አቀራረብ የምታሳያት ከሆነ የባሰ ችግር ውሰጥ ትወድቃለች ።የሷ መቸገር ደግሞ ያንተም መቸገር ነው ።


>>>> አንዲት ሴት ሁለት ልጆችን ወልዳና ሶስተኛውን አርግዛ አሰራ ስድስት ዓመት ከቆየችበት ትዳሯ ተፈናቅላለች ።መንስኤው ምን እንደሆነ ስትናገር ፦በቀላል ነገር ከአንዲት ጎረቤቴ ጋር ተጣላን ።በጨለማ ወደ ቤቴ ስገባ ጠብቃ እጄን ነከሰችኝ ።እጄ ደማ ።ሴትዮዋ የኤችአይቪ
ቫይረስ በደሟ አለ እየተባለ ይወራል ።
በጣም ደነገጥኩ ።ሀኪም ቤት ስሄድ ክኒን መውሰድ አለብሽ አሉኝ ...መድኃኒቱን ጀመርኩ ....ሊያድነኝም ላያድነኝም ይችላል ....ሴትዮዋን ከሰስኳት ።ደም ስጪ ተባለች ።አልሰጥም ስትል አሰሯት ።

ኪኒኑ በጣም ከባድ ነው ።ጨጓራዬን ከጥቅም ውጭ አደረገው ።ጭንቁቱም እንቅልፍ ነሳኝ ።ከበዙ ዓመታት በኋላ የመጣብኝ እርግዝናም የራሱ ጣጣ አለው ።ባለቤቴ ግን የእኔን ጭንቀት ከመጋራትና ከጎኔ ከመቆም ይልቅ የአገሩ ልጅ ለሆነችው ጎረቤታችን መታሰር ይጨነቅ ጀመረ ።ይባስ ብሎ አንድ ቀን ማታ ላይ መጣና "መድኃኒቱን እየወሰድሸ ነው ።ከዚህ በኋላ ምንም አትሆኝም ።እሷም ትፈታ ።ለምን ታካብጃለሸ ? አለኝ ። በጣም ከመበሳጨቴ የተነሳ የማደርገውን አላውቅም ነበር ።ኃይለኛ ግጭት ውሰጥ ገባን ።በመጨረሻም ተፋታን "ብላለች ።
እናም ወንድየ ባለቤትህን መንከባከብ እንዳለብህ በዚህ ታሪክ መረዳት አለብህ

ክፍል ➊➌
ይቀጥላል........
#ምንጭ ☞ፍቅርና ትዳር ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ
👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ ሶስት 1⃣3⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➒
#ስህተት_አትፈልጊ

ሰው ፍፁም አይደለም...
☞አንዱ በጣም አጭር
☞አንዱ ደግሞ በጣም ረጂም ፣
☞አንዱ በጣም ወፍራም
☞ ሌላው ደግሞ በጣም ቀጭን ፣
☞አንዱ ተጫዋች ሌላው ዝምተኛ ፣
☞አንዱ ቶሎ የሚናደድ ሌለው ትዕግስተኛ ፣
☞አንዱ መልክ መልካም ሌላው ደግሞ መልከ ጥፉ ወዘተ ይሆናል ።
አብዛኛው ሰው የነዚህ ጉድለቶች ባለቤት ቢሆንም የሰው ልጅ በሁሉም ነገር የተሟላ የትዳር ጓደኛ እንዲኖረው ይመኛል ይህ ምኞት ግን እውን ሊሆን አይችልም ።ለዚህ ነው ባሌ ምንም አይነት እንከን የለበትም የምትል ሴት ማግኘት የማይቻለው ።

ከባሎቻቸው ላይ ስህተት የሚፈልጉ ሴቶች ያለምንም ጥርጥር ያገኛሉ ።ያገኙትን ጥቃቅን ስህተት በማጋነን ከሌላ ከባድ ችግር ጋር ያያይዙታል ።ያትንሸ ስህተት የሱን በጎ ነገሮች ሁሉ ያጠፋባቸዋል ።ባሎቻቸውን ከሌላ ወንድ ጋር ያወዳድራሉ ።ከባላቸው ባህሪ የተለዬ ባህሪ ያለው አንድ የሀሳብ ወንድ አዕምሯቸው ውሰጥ ይሰላሉ ።በመሆኑም በትዳር ህይወታቸው ሁልግዜ ይማረራሉ ።ራሳቸውን አንድ እድለቢስ ይቆጠራሉ ።ይህም ቀሰ በቀሰ አሰቸጋሪ ሴቶች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ።

ይህን መሰል የሴቶች ባህሪ በባሎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ።አንዳንዴ ወንዱ ታጋሽ ሆኖ ይህን ችግር ተቋቁሞ መኖር ይችል ይሆናል ።ብዙ ጊዜ ግን ነገሩ ሰለሚመረው በሚስቱ ላይ ጥላቻ እያሳደረ ይሄዳል ።ይህ ደግሞ ሁለቱም እርሰ በርስ ስህተት አንዲፈላለጉ ያደርጋቸዋል ።በሚያሰጠላ ሁኔታ አብረው ለመኖር አለያም ፍቺ ለመፈፀም ይገደዳሉ ።
ፍቺ ደግሞ ለሁለቱም የሚበጅ አይሆንም ።
ምክንያቱም ሌላኛው ጋብቻ ሁኔታውን የማስተካከሉን ነገር ማረጋገጥ አይቻልም ።


አንዳንድ አላዋዊና ግትር ሴቶች በጥቃቅን ጉዳዮች የትዳር ህይወታቸውን ያቃውሳሉ ።ቀጣዮቹ የእንዲህ አይነት ሴቶችን ባህሪ የሚያሳዩ ናቸው ።


✿"አንዲት ሴት ባሏ የአፉ ጠረን ሰላስቸገራት ቤቷን ትታ ወደ አባቷ ቤት ትሄዳለች ።ችግሩ ሳይፈታም ወደ ቤት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነችም ።ባል ለፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ፍርድ ቤት አሰታርቋቸው ወደ ቤቷ ገባች ።ጥንዶቹ ወደ ቤት እንደገቡ የአፉ ጠረን አሁንም ጥሩ እንዳልሆነ አወቀችና ዘላ ወደ ሌላ ክፍል ገባች ባል ንዴቱን መቆጣጠር አቃተውና ገደላት ።

✿""አንዲት የጥርስ ሐኪም የባሏ የትምህርት ደረጃ ከሷ ደረጀ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ፈታችው ።ምክንያቱም እሱ የተመረቀው እሷ ከተመረቀች ከሶስት ዓመት በኋላ ነበር ።

✿ "ሌላዋ ሴት የፍቺ ጥያቄ ታቀርባለች ።ለምን?? ተብላ ሰትጠየቅም "ባሌ አቧራ ላይ ይቀመጣል ።ሲበላ ጣቶቹን በሙሉ ምግብ ያሰነካል ።ፂሙን ቶሎ ቶሉ አይስተካከልም ።ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር መኖር አልችልም "ብላለች ።

በእርግጥ ሁሉም ሴቶች አንድ አይነት አይደሉም ።በሳልና አስተዋይ የሆኑና የባሎቻቸውን ጉድለቶች በመፈለግ በቀላሉ የትዳር ህይወታቸውን ማበላሸት እንደሌለባቸው የሚገነዘቡ ብዙ ሴቶች አሉ።

#እመቤት_ሆይ !
ባልሽ የሰው ፍጡር ነውና ፍፁም ሊሆን ስለማይችል ጉድለቶች ይኖሩታል ።ነገር ግን የዚያኑ ያህል ጥሩ ጎኖችም አሉት ።ለቤትሸና ለትዳርሸ የምታስቡ ከሆነ ድክመቱን ለመፈለግና ለማገናኘት ጥረት አታድርጊ ።

ያለበትን ትንሽ ጉድለት አንድ ትልቅ ነገር አትቁጠሪ ።
በሌሎች ወንዶች ላይ የማይታዩ ችግሮች በባልሸ ላይ ሊታዩ ይችላሉ ።ነገር ግን እነዚያ ወንዶች ደግሞ ባልሽ የሌለበት ሌሎች አሰቸጋሪ ባህሪያት ሊኖራቸው አንደሚችል መገንዘብ ይኖርብሻል ።
☞በባልሸ ጥሩ ጥሩ ባህሪያት ተብቃቂ ።ቀስ በቀስ ጥሩ ባህሪዎቹ ከጉድለቶቹ ሲያመዝኑ ታያለሸ ።ደግሞስ አንቺ ፍጹም አይደለሽም ።እሱ አንዴት ፍፁም አንዲሆን ትጠብቂያለሸ ?አኔ ፍፁም ነኝ ብለሸ በማሰብ የምትኩራሪ ከሆነ እሰኪ ሌሎች ሰዎች ሰላንቺ ያላቸውን አሰተያየት በትክክል አንዲነግሩሸ አድርጊ ።

☞የራስን ድክመት ሸፍኖ የሌሎችን ድክመት ከመፈለግ የከፋ ነገር የለም ።ስህተትን አታጋኚ ተራ ለሆነ ነገር ህይወትሽ ለምን ይናጋል ?ብልህ ሁኚ ፣ግትር አትሁኚ ።ባልሽ ያለበትን ድክመት ለሱም ሆነ ለሌሎች ሰዎች አትንገሪ ...ባለው ነገር በመደሰት ጥሩ የትዳር ህይወት ፍጠሪ ።

ባለቤትሽ አንቺ ልታሰተካክያቸው የምትችያቸው ጉድለቶች ሊኖሩት ይችላሉ ።ስለዚህ መፍትሄ ይሆናሉ የምትያቸውን ነገሮች በመጠቀም ለማስተካከል ሞክሪ ።ስኬታማ ልትሆኚ የምትችይው ግን በትዕግስትና በጥሞና ሰትንቀሳቀሸ ብቻ ነው ።
ወቀሳና ጭቅጭቅን አስወግደሸ በጓደኝነት መንፈስ ቅረቢው ።ውጤቱን ታገኚዋለሸ ።

✿ የሚወዳትን ባሏን ፈትታ መጥፎ ትዳር ውሰጥ አየማቀቀች ያለች ሴት ቀጣዩን የፀፀት ንግግር ተናግራለች ።
"ያገባሁት በቤተሰብ ምርጫ ነው ባለቤቴ በጣም ይወደኛል በጣምም ይንከባከበኛልነገር ግን እኔ ጠላሁት ።ምክንያቴ ደግሞ የቁመቱ ማጠር ነው አብረን ስንሄድ ሰዎች ወሬ አውርተው ከሳቁ በሱ ቁመት የሳቁ እየመሰለኝ በጣም እሸማቀቃለሁ ....ከነጭራሹ ከሱ ጋር መኖርን አንደ ውርደት አየቆጠርኩት መጣሁ እየጠፋሁ ወላጆቼ ቤት እሄዳለሁ ....ይመልሰኛል አሁንም እሄዳለሁ ....ይመልሰኛል ...መጨረሻ ላይ ሰለቸውና ተወኝ ሌላ ሚስትም አገባ ፡፡አኔም የምፈልገው አይነት ባል መጣልኝ ረጂምና ቆንጆ ተጋባንና አራት ልጆች ወለድኩ ...ባለቤቴ ነጭናጫና ክፉ ሰው ነው እንደ ቤት ሰራተኛ እንጂ እንደ ሚሰት ቆጥሮኝ አያውቅም ።በውሃ ቀጠነ የሰብ ናዳ ያወርድብኛል ...መልስ ከሰጠሁ ዱላ ይከተላል ምርር ይለኝና ትቼ ለመሄድ ስነሳ ፊት ፊቴን እያዩ "እማዬ እማዬ "የሚሉኝ ልጆቼ ያሳዝኑኛል ትቻቸው ልሄድ ? ለማን ? ለእንጀራ እናት ?አንጅቴ አይጨክንም ይዣቸው ልሄድ ?ወዴት ?ከነ ልጆቼ ማን ይቀበለኛል ?እተወዋለሁ ።

በትዳሬ ደስተኛ የሆንኩብትን ቀን አላስታውስም ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ሲኦል ውሰጥ የቆየሁ ያህል ነው የሚሰማኝ የበሽታ ማጠራቀሚያ ሆኛለሁ ..አሁን የምድሩ ህይወት እያለቀ ነው ተሰፋዬ የሰማዩ ነው ፈጣሪ በሁለቱም ዓለም አንደማይበድለኝ እርግጠኛ ነኝ
ወጣት ሴቶች የትዳር አጋሮቻቸውን ሲመርጡ መልክና አቋም ላይ ትኩረት ባያደርጉ ደስ ይለኛል ዋናው ባህሪ ነው እንደውም በኔ አሰተሳሰብ ቆንጆ ወንዶች ለትዳር አይሆኑም ።"
ብላ አስተያየቷን ሰጥታለች

በቀጣዩ ክፍል የወደፊት አባወራ የተለያየ ስህተት መፈለግ እንደሌለብህ እንዳስሳለን

#ክፍል ➊➍ ይቀጥላል

#ምንጭ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ


@IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አስራ አራት 1⃣4⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


🌹የትዳር_ማጣፈጫ_ቅመም_ለአባወራዉ
7⃣
#ስህተትን_አትፈልግ

በዓለም ላይ ከገደሉት የፀዳና ሙሉ የሆነ ሰው የለም ።
☞አንዱ በጣም ወፍራም ሌላው በጣም ቀጭን ፣
☞አንዱ ረጂም ሌላው አጭር ፣
☞አንዱ ጥርሱ ወጣ ያለ ሌላው ሰልካካ አፍንጫ ያለው ፣
☞አንዱ ትህትና የጎደለው ሌላው ትሁት ፣
☞አንዱ አይናፋር ሌላው ድብርታም ፣
☞አንዱ ግንፍልተኛ ሌላው ቀናተኛ
☞ አንዱ ሰነፍ ሌላው ራሰ ወዳድ ይሆናል ።

✔አንዳንድ ሴቶች ባለሞያ ሲሆኑ ሌሎች ሞያ ይጎድላቸዋል ።
✔አንዳንዶች ወሬ ሲወዱ ሌሎች ደግሞ ለስራቸው ብቻ ትኩረት ይሰጣሉ ።
✔አንዳንዶች ገንዘብ ቆጣቢ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ያባክናሉ ።

~~~ ወንዶች አብዛኛውን ጊዜ ከጋብቻ በፊት ከጎደሎ የፀዳች ሚሰት እንደምትኖራቸው ያስባሉ ።በዓለም ላይ ፍፁም የሆነ ሰው አለመኖሩን ልብ አይሉም ።ከገባ በኋላ ሚስታቸው እንዳሰቡት ፍፁም ሴት ሆና አያገኝዋትም ።ስህተት ትሰራለች ።ሰህተቷን መቁጠር ይጀምራሉ ።የተሳሳተ ጋብቻ እንደፈፀሙ ይሰማቸዋል ።ራሳቸውን እድለቢስ አድርገው ይቆጥራሉ ።ሁልጊዜ ያማርራሉ ።ጥቃቅን ስህተት ሳይቀር ማለፍ አይፈልጉም ።በማጋነን የተራራ ያህል አግዝፈው ያቀርቡታል ።ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው ባሉበት ሳይቀር ስህተቶችን በማውጣት ሚስቶቻቸው እንዲሸማቀቁ ያደርጋሉ ።

~~~ የትዳር ህይወታቸው መፍረክረክ ይጀምራል ።እሷም በሁኔታው ታዝንና በባሏና በቤተሰቧ ላይ ያላት እምነት ይቀጭጫል ።በሆነ ባልሆነው ለሚተቸኝ ሰው ተግቶ መሰራት ተገቢ አይደለም ብላ ታሰባለች ።የበቀል እርምጃም ልትውሰድ ትችላለች ።"ምን አይነት አስቀያሚ ሴት ነሽ ?" ሲላት "መርጠህ ነው ያገባኸኝ ፣አንተስ ማን ሆነህ ነው ?""ባህሪሸ አሰቸጋሪ "ሲላት "የኛ ጥሩ ሰው ..."ትለዋለች ።

ይህ መመላለስ እየቀጠለ ሲሄድ ቤቱ የጦርነት አውድማ ይሆናል ።በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ ምቾት ይርቃቸዋል ።መከባበርና መፈቃቀር የራቀው ቤት ምቾች ሊገኝበት አይችልም ።
>>> ወንዱ ራሱን እንደ እድለቢስና ትዳሩን እንደ ውድቀት በመቁጠሩ ፣
>>> ሴቷም ሁልጊዜ በባሏ በመዋረዷ ሁለታቸውም ለአዕምሮ ጭንቀትና ለሌሎች በሽታዎች ይጋለጣሉ ።ጭቅጭቃቸው እየተባባሰ ከሄደ የፍቺ አደጋ ያንዣብባል ።ፍቺ ደግሞ ለሁለቱም ጠቃሚ አይደለም ።በተለይ ልጆች ካሉ ።

ፍቺ በህብረተሰቡ ዘንድ የተወደደ ተግባር አይደለም ።
ወንዱን ሊያገግም ወደማይችልበት የኢንኮኖሚ ኪሳራ ውሰጥ ይከተዋል ።በተለይ ደግሞ እንደገና ማግባት የሚፈልግ ከሆነ ለአዲሱ ጋብቻ ገንዘብ ማውጣት ይኖርበታል ።ከዚህም በላይ ፍቺ እሱ የሚፈልገው መልኩ የምትኖርለት ሚስት ለማግኘት እንደሚያስችለው እርግጠኛ መሆን አይቻልም ።ያለፈ የህይወት ታሪኩም እንደገና ማግባት ቀላል እንዳይሆንለት ያደርገዋል ።ሌላ ሴት ቢያገኝ እንኳ ያቺም ሴት ሰው ናትና ጉድለቶች ይኖሩባታል ።

ከመጀመሪያ ሚስቱም የባሰች ልትሆን ትችላለች ።ስለዚህ የግድ ከመጀመሪያዋ ጋር ተስማምቶ ለመኖር መጣር ይኖርበታል ።
#ምክንያቱም በሁለተኛ ትዳራቸው ሙሉ በሙሉ ደስተኛ የሆኑ ወንዶች በጣም ጥቂቶች ናቸው ።ለዚህም ነው አንዳንዶቹ ወደ መጀመሪያ ሚስታቸው ሲመለሱ የሚታየው ።


#ውድ_ወንድም_ሆይ !
♦በሚሰትህ ላይ ለምን ስህተት ትፈልጋለህ ?
♦ በጥቃቅን ጉድለቶች ላይስ ለምን ትኩረት ታደርጋለህ ?
♦ትንሹን ነገር በማግዘፍ ባንተና በቤተሰብህ ላይ ለምን ችግር ትፈጥራለህ ?
♦ፍፁም የሆነች ሴት አይተህ ታውቃለህ ?
♦ አንተ ራሰህሰ ፍፁም ነህ እንዴ ?
♦ጥቃቅን ስህተቶች እንዴት የትዳርህ ጠንቅ እንዲሆኑ ትፈቅዳለህ ?


ሚስትህን ጥሩና ጤናማ በሆነ መልኩ ከቀረብካት እሷ ላይ ብዙ ጥሩ ነገሮችን ታገኛለህ ።ቀስ በቀስ ጥሩ ጎኗ ከመጥፎ ጎኗ ከመጥፎ ጎኗ በልጦ ታገኘዋለህ ።

■■■ ወጣቱ ዲያሰፖራ ነው ።ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የታመሙ አባቱን ለመጠየቅ ቢሆንም እግር መንገዱን የትዳር ጓደኛም ይፈልግ ነበር ።ባጋጣሚ ሀይስኩል አብረው የተማረችንና ሊያገባት የሚመኛትን ጓደኛውን ያገኛታል ።ስልክ ቁጥሯን ይዞ ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ የጋብቻ ጥያቄ ያቀርብላታል ።ተሰማማችና እሱ እዚያው እንዳለ የቀለበት ሰነ ስርዓቱ ተፈፀመ ።

ከሶስት ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጣና የሰርግ ሰነ ስርዐት ተካሄደ ።ሶሰት ወር ቆይቶም ተመለሰ ።ከሄደ ከወራት በኋላ ጋብቻውን መቀጠል እንደማይፈልግ ይናገራል ።ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሰሙት እንግዳ ነገር ተገርመው እባክህን ነገሩን በጥልቀት አስብበት ።ትዳር ክቡር ነው ።በተልካሻ ምክንያት በቀላሉ መፍረስ የለበትም ብለው ሲጠይቁት በቂ ምክንያቶች አሉኝ በማለት ቀጣዮቹን ዘጠኝ ነጥቦች በሞባይል መልእክት ልኳል ።


➊ አንድ ቀን ከሰው ፊት አዋርዳኛለች ።ይህም ኃይለኛነቷን ያሳያል ።

➋ በዚህ የተነሳም ለኔ መሳዬት ያለባት ባህሪ ምን አይነት መሆን እንዳለበት በቤተሰቦቼ አሰመክሪያታለሁ ።
➌ በስልክ የምታወራኝ እንደ ሚሰት ሆና አይደለም ።እኔ ከሚስቴ ብዙና አስደሳች የፍቅር ቃላት መሰማት እፈልጋለሁ ።የሷን የኔ ውይይት ግን ቃል መጠይቅ ነው የሚመሰለው ።

➍ በዚህ ዙሪያ ሁለት ሸማግሌዎችን ልኬ አሰጠይቂያታለሁ ።ልታሻሸል አልቻለችም ።

➎ ስለ ባህሪዋ ለወንድሟ ስነግረው ችግራችሁን በራሳችሁ ፍቱ ።እኔ ጣልቃ መግባት አልፈልግም ብሎኛል ።

➏ እንደመጣሁ ወዲያውኑ ማርገዝ ስትችል ሆነ ብላ አዘግይታለች ።

➐ ለአራት ዓመት ያህል በየወሩ ገንዘብ እየላኩ እንዳኖርኳት ።ይህም ሲደመር ብዙ መሆኑ።

➑ ስመጣ ልብስና ጫማ ባመጣላትም የሚገባኝን ያህል አላመሰገነችኝም ።


➒ በአጠቃላይ ባህሪዋን መደበቅ ባለመቻሏ እኔን ከመሰለ ጥሩ ባል ጋር በተሻለ አገር ላይ የመኖር እድሏን አልተጠቀመችበትም ።
ብሎ መለሰ እሷ ይሄንን ሲነግሯት የራሷ አሳማኝ ምክንያት አቅርባ ነበር ምን ይሆን ያለችዉ
በቀጣዩ ክፍል እንዳስሳለን....

ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ
#ክፍል ➊➎
ይቀጥላል......

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
✋ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ..የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? ሁሉ ሰላም እኛ አልሀምዱሊላህ የባሰ አያምጣ ደህና ነን

ዛሬ አንድ ሀሳብ ከእህታችን መህቡባ ቢንት አቡሀ የመጣ አለ..በፊት በዚህ ቻናል
☞በጀመአ መፅሀፍ የማንበብ
☞ የግጥም ዉድድርና
☞ኢስላማዊ ጥያቄ ዉድድር ሽልማት የሚያስገኝ ሳምንታዊ ዝግጅቶች ነበሩ በጊዜ ማነስ ምክንያት አቁሜዉ ነበር፡፡
ግን አሁን በቅርቡ ሽልማት የሚያስገኝ የተለያዩ ዝግጅቶች እያቀረብን ተወዳዳሪዎች በዛዉም ኢስላማዊ እዉቀት የሚቀስሙበት ..አንባቢ ..ፀሀፊ እንዲሆኑ በማሰብ ለወደፊት የተለያዩ ሁሉንም የቻናል ቤተሰብ የሚያሳትፍ ዝግጅት ይኖረናል ፡፡

#ከእኛ_ምን ይጠበቃል?? ያላችሁመሰለኝ😊
ከእናንተ የሚጠበቀዉ በደንብ አድርጋችሁ ከታች ያሉትን የወደፊት ህጎች አይናችሁን አሸት አደርጋችሁ አንብቡ
➊ ከመፅሀፍ ጥያቄ ወጥቶ ዉድድር ካለ .. አቅም ያለዉ በቻናል የሚታዘዘዉን መፅሀፍ መግዛት ..አቅም የሌለዉ ደግሞ በሂደት መፍትሄ አናጣም

➋ የግጥም መፃፍ ተሰጥኦ ያላችሁ ይሄን message ካነበባችሁበት ሰአት ጀምሮ የምትወዳደሩበትን ግጥም አዘጋጁ ፡፡ከዛ ዉድድሩ ሲጀመር ላኩ ሲባል ትልካላችሁ
⚠️ Warning☞ በሰዉ ግጥም መወዳደር አይቻልም እኛ እናጣራለን

➌ ሳምንታዊ የጥያቄ መልስ ዉድድር ስለሚኖር በጥያቄ ዉድድር ሰአት ላይ ደቂቃ ሳይሸራርፉ በሰአቱ መገኘት

➍ ሁሌ የሚተላለፉ ትዕዛዞችን መጠበቅ መተግበር ከእናንተ የሚጠበቁ ናቸዉ ፡፡ በተጨማሪ በሂደት የምናሳዉቃችሁ ይኖራል፡፡


♦♦ ይህ ሽልማት የሚያስገኝ ዉድድር በtelegram ብቻ ሳይሆን በFacebook ጭምር ነዉ የሚካሄደዉ ..የዉድድሩ ነጥብ የሚሰበሰበዉ የtelegram እና የface book ዉጤት ተደምሮ ነዉ አሸናፊዉ የሚታወቀዉ

♦♦ የጥያቄ ዉድድር ግን በtg ለብቻዉ በFb ለብቻዉ ራሱን ችሎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ሽልማቱ ለየብቻ ይሆናል፡፡

እናም ይሄ አሳታፊ የሆነ ዉድድር ብትሳተፉ እኛ ፍትሀዊ ዳኝነት አድርገን አሻናፊዉን ቀጥታ እንደበፊቱ ሽልማቱን እናደርሳለን፡፡
እናም እንድትሳተፉ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ ወንድማችሁ አሚር ሰይድ ነኝ

✍ የግጥምና የጥያቄቄ ዉድድሩን በዚህ ቀን ላኩ ብለን መልፅክት ስንልን በዚህ bot ነዉ የምትልኩት👇👇
www.tg-me.com/Meh_Ani_bot www.tg-me.com/Meh_Ani_bot

☞4any comment ☞ www.tg-me.com/Meh_Ani_bot
በfb እና በtg መገኛችን ይከተሉን
✔ የFace book አድራሻችን👇
https://www.facebook.com/100043960661414/posts/376257703849582/?app=fbl

✔ በTelegram ደግሞ 👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
 
2024/09/22 22:36:29
Back to Top
HTML Embed Code: