Telegram Web Link
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣7⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

....."አይዞህ እኛ ሁሌም ከጎንህ ነን ይሄን ወርቅ ሽጥና የአማኔን መድሀኒት ግዛ"አለችዉ አባቢ ግን አይቻልም አለ

....እማየም እኔም አባቢ ወርቁ መሸጥ አለበት የግድ የአማን መድሀኒት በዚህ ሳምንት ዉስጥ መገዛት አለበት አልን አባቢ "እና ለመሸጥ ወሰናቹህ" አለን እኛም አወ መከፈል ያለበትን ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነን አልነዉ አባቢ በፍቅር አይኑ እየተመለከተኝ "ሀናኔ አንች እንኳን በጣም የምትወጂዉን በጣም የምትሳሽለትን ወርቅ ልትሸጪ ተስማማሽ" አለኝ እኔም አብሽር አባቢ አላህ አንድን ነገር አይወስድም ከዛ የተሻለ ሊሰጠን ቢሆን እንጂ አልኩ
.....አባቢም ቡዙ ካቅማማ ቡኋላ አማራጭ ስላልነበረዉ እሽ ብሎ ሊሸጠዉ ሄደ እማየ ከመሄዱ በፊት "ተጠንቅቀህ ሌቦች በዝተዋል እንዳይሰርቁህ" ብላ በተደጋጋሚ ነገረዋለች እባቢም ችግር የለዉም ብሏት ወርቁን ሊሸጠዉ ሄደ እኛም ስንት ይሸጥ ይሆን እያል አባቢን በጉጉት ስንጠብቀዉ ቀረብን ለብዙ ሰአት ጠበቅነዉ አልመጣም ስንደዉል ስልኩ ዝግ ነዉ ሰአቱ እየሮጠ ጊዜዉ እየመሸ ሄደ አባቢ አልመጣም እማየ ምን ሁኖ ይሆን እያለች መጨነቅ ጀመረች


....... እኔም በጣም ተጨነኩ ከመሀል በሩ ተንኳኳ እየሮጥኩ ስከፍተዉ አባቢ ነዉ አልሀምዱሊላህ ደህና መጣህ ደሞ እስካሁን የቆየህ ታክሲ አጠህ ነዉ አልኩት አባቢ ዝም ብሎ እቤት ገባ።

.... እንባ እያነቀዉ አዉፍ በሉኝ ሌቦች ወርቁን ከእጀ መንትፈዉኝ ሮጡ ተከተልኩ ተከተልኩ.... መጨረሻ ላይ ስሮጥ ቆይቸ እነሱም ጠፉኝ እኔም ፖሊስ ጣቢያ ሂጀ ሁኔታዉን ነግሬቸዉ መጣሁ እያለ ማልቀስ ጀመረ
......እማየ ሀዘንናፍቅር ከፊቷ እየተነበበ "ዉዴ!አይዞህ ለኸይር ነዉ ሌባች ይያዛሉ ወርቁም ይገኛል" ስትል አበረታታችዉ አባቢም እንዳልሽዉ ያድርግልኝ አለ እኔም ኧረ አባቢ ለዚህ ደግሞ ታዝናለህ እንዴ ይሄኮ ተራ ነገር ነዉ ሰዉ እንኳን ቁስ ነገር ሂወቱን ያጣ የለ አብሽር አልኩ ዉስጤ ግን እዉነት ለመናገር ከፍቶኛል ያአላህ ካልተገኘስ መድሀኒቱ የኛ የትምህርት ቤት ክፍያ በምን ገንዘብ ሊከፈል ነዉ ስል አሰብኩ ማሰቡ ሲደክመኝ በቃ ለኸይሩ ነዉ አልኩ።

......ነግቶ አባቢ ሌቦቹ ተይዘዉ እንደሆነ እስኪ አዲስ ነገር ካለ ብሎ ወደ ፓሊስ ጣቢያ አቀና እኔም ወደ ትምህርት ቤት ሊሄድ ስዘጋጂ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ ተሰብስበዉ ሊጠይቁን መጡ ደነገጥኩ ችግሬን እንኳን ለአላህ እንጂ ለሰዉ ተናግሬ አላቅም ምክንያቱም ችግር ፈቺ አላህ እንጂ ሰዉ አይደለም።
.... ማታ ከመተኛቴ በፊት ያረብ ቢያንስ ለአማኔ መድሀኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ እናግኝ አባቢም ወርቁን አግኝቶ ከጭንቀቱ ይገላገል ስል ነበር .......... ብቻ አላህ ዱአየን ተቀብሎኝ የተወሰነ ብር አዋጠዉ ብርና ፍራፍሬ ይዘዉ መጠዉ አማኔን አይተዉት ሄዱ እንዴት መታመሙን አወቁ ስል ሪሀናን ጠየቋት ሪሀናም እኔ እስር ቤት እንደገበሁ ሲደዉሉ ወንድሟን አሞባት ብያቸዉ ነበረ።
.... ዛሬ ለመጠየቅ መጡ አለች
.... ይዘዉት የመጡት ብር ለመድሀኒት መግዣ ባይበቃም ለመጨመሪያ ይሆናል አልሀምዱሊላህ እያልን ከእማየ ጋር ስንመካከር አባቢ ምንም አዲስ ነገር የለም ብሎ በአዘነ አንደበቱ ነገረን በቃ ቤቱ መሸጥ እንዳለበት ተስማማንና ይሸጣል የሚል ፁህፍ የግቢዉ በር ላይ ለጠፍንበት ለአንድ ለሁለት ቀን ጠያቂ የለም በሶስተኛዉ ቀን አንዱ አኔ እገዘዋለሁ ብሎ መጣ እኛም ሊሸጥ ነዉ በሚል በደስታና በሀዘን ስንጠብቅ በዋጋ አልስማማ ብለዉ ቀረ የአማኔ መድሀኒት በሳምንት ዉስጥ መገዛት አለበት ሳምንት ሊሆን ሶስት ቀን ብቻ ነዉ የቀረን በፍጥነት መገዛት አለበት እያለ አባቢ የሚገዛ ቢጠባበቅ የሚገዛ ጠፋ በአራተኛዉ ቀን ያ ..ይወደዉ የነበረዉ የአባቢ ጓደኛ በርካሽ ዋጋ ልግዛህ አለዉ አባቢም አይቻልም በዚህ ዋጋ አልሸጥም አለ

ብድሩን የለኝም አልከፍልህም ሲል እንዳልነበር አሁን ቤት ሊገዛ ብቅ ማለቱ ገረመኝ እማየም አባቢም ሁላችንም እጃችንን ወደ ላይ ዘርግተን ያረብ ማለት ጀመርን የአማኔ መድሀኒት ለመግዛት ሁለት ቀን ብቻ ቀረን በዚህ ቀን ካልተገዛ ወደ ጤናዉ በፍጥነት እንደማይመለስ ዶክተሩ ተናግሯል ምን እናርግ ወደ አላህ ፊታችንን አዞርን በርግጥም የኛ ጌታ ዱአን ይሰማል ለምኑኝ እስጣለሁ አይደል ያለ በቃ ነገ የሚገዛ ይመጣል ስንል እርስ በርሳችን ተነጋገርን ነገር ግን በነጋታዉ ገዢ ብንጠብቅ ብንጠብቅ የለም አባቢ ተስፋ ሲቆርጥ ለጎደኛዉ ና ባልከዉ ዋጋ ግዘዉ ብሎ በኔ ስልክ ደወለለት የሱንማ ከወርቁ ጋር አብረዉ ወስደዉበታል


ጓደኛዉም ጊዜ ሳያባክን መጣና ተፈራርወዉ ቤቱን ገዛዉ እኛም እቃችንን ጠቀላለን የክራይ ቤት ማፈላለግ ጀመርን


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣8⃣

......ሰሚራ ሽኩር

ጓደኛዉ ጊዜ ሳያባክን መጣና ተፈራርመዉ ቤቱን ገዛዉ እኛም እቃችንን ጠቅልለን የኪራይ ቤት ማፈላለግ ጀመርን ከሸጥነዉ ቤት ራቅ ብሎ ሶስት ክፍያ ያለዉ ቤት በጥሩ ዋጋ ተከራየን የሰዉ ወሬ ግን አላስቀምጥ አለን ሁሌም"እንደዉ ይች ሞኝ ባሏ ከየትም ያመጣዉን ልጁን ለማሳከም ቤቱን ሲሸጥ ዝም ትላለች አይ"እያሉ እማየን ማስቀየም ጀመሩ እማየም ሰምታ ባልሰማ ታሳልፋቸዋለች

.....እማየንና አባቢን ለማጣላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም እማየና አባቢ ግን የሰዉ ወሬ ስለማይሰዉ በጣም ይተማመኑና ይዋደዱ ስለነበረ እነሱ ምንም ቢያወሩ አልሰማ አሏቸዉ እንደዉም እነሱ ለማጣላት በሚያደርጉት ሩጫ የአባቢና የእማየ ፍቅር ቀን ከቀን እየጨመረ ነበር የመጣ።


.......የአባቢ ጓደኛ ግማሽ ክፍያ ሰጠዉና ግማሹን አሁን የለኝም በሌላ ጊዜ ብሎ ገገመ አባቢ ሰጠኝ ብሎ ቢለምነዉም ጓደኛዉ "ምን የሚገዛህ አጠህ በገዛሁህ ላይ" እያለ ያሾፋል።
... አባየም ለሱ ባልሸጥለት ነሮ ያረብ! ምን አጠፋሁ ምን በደልኩህ....እያለ አምርሮ አነባ!





እኔም አባቢን ለማፅናናት አባቢ ለሱ ባልሸጥለት ነሮ እያልክ አትፀፀት አላህ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል ስል ሊያረጋጉት የሚችሉትን ተናገርኩ
" በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ በማንም ላይ አትደርስም ሳንፈጥራት በፊት በመፅሀፉ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ ።" የሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ ቀድመው ተፅፈዋል ። ብዕሩ ደርቋል ፤ ወረቀቶቹ ተነስተዋል ።

ﻗُﻞ ﻟَّﻦ ﻳُﺼِﻴﺒَﻨَﺎ ﺇِﻻَّ ﻣَﺎ ﻛَﺘَﺐَ اﻟﻠَّﻪُ ﻟَﻨَﺎ

«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ » በላቸው፡፡
(አት-ተውባህ 51)

የደረሰብህ ነገር ሁሉ ሊዘልህ አይችልም ነበር ፤ የዘለለህ ነገር ሁሉም ሊደርስብህ አይችልም ነበር ። ይህ አስተሳሰብ በልብህ ውስጥ ጠልቆ መግባት አለበት ። ሁሉም መከራና ችግሮች ቀላል ይሆኑልህ ዘንድ ።

ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም " አሏህ የሚወደውን ሰው /በችግር / ይፈትነዋል " ብለዋል ። አባቢ አንተንም በትንሹ የሞከረህ ስለወደደህ ይሆናል

በመሆኑም ቢያምህ ፣ ልጅህ ቢሞት ፣ ንብረትህ ቢወድም፤ጎደኛህ ቢከዳህ አምርረህ አትዘን ። አሏህ እነዚህን ነገሮች እንድከሰቱ አስቀድሞ አዟል ። ውሳኔውም የእርሱና የእርሱ ብቻ ነው ። በዚህ ካመንን ጥሩ ምንዳ እናገኛለን ። ኃጢዓታችንም ይሰረዝልናል ።

እናንተ ችግር የደረሰባችሁ ሰወች መልካም ዜና ይጠብቃችኋል ። ስለዚህ ትዕግስተኞችና በጌታችሁ ደስተኞች ሁኑ ።

ﻻَ ﻳُﺴْﺄَﻝُ ﻋَﻤَّﺎ ﻳَﻔْﻌَﻞُ ﻭَﻫُﻢْ ﻳُﺴْﺄَﻟُﻮﻥَ

ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ፡፡
(አል-አንቢያዕ 23)

አሏህ ነገሮችን ሁሉ ቀድሞ እንደወሰነ በፅኑ ካላመንክ ችግሮችን እንደቀላል ማሳለፍ አትችልም ። ባንተ ላይ የሚደርሰው ነገር ሁሉ የተፃፈበት ብዕር ደርቋል ። ስለዚህ በአንተ እጅ ባልሆነና መቀየር በማትችለው ነገር ላይ ለምን የፀፀት ስሜት ይሰማሀል ? ብርጭቆውን ከመሰበር ፣ አጥሩን ከመውደቅ ፣ ጎርፉን ከመፍሰስ ፣ ነፋሱን ከመንፈስ ማዳን እችል ነበር ብለህ ታስባለህ ?! ወደድክም ጠላህም እነዚህን ነገሮች ማስቀረት አትችልም ። ቀድሞ የተፃፈ ሁሉ ይፈፀማል ።
ﻓَﻤَﻦ ﺷَﺎءَ ﻓَﻠْﻴُﺆْﻣِﻦ ﻭَﻣَﻦ ﺷَﺎءَ ﻓَﻠْﻴَﻜْﻔُﺮْ

« የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» ፡፡
(አል-ከህፍ 29)

እጅህን ስጥ ፦ ስሜትህን በፀፀትና በቁጭት ከመጉዳቱ በፊት በቀደር እመን ። የምትችለውን ሁሉ ካደረግክ እና እንዳይደርስ የደከምክለት ነገር ከተከሰተ ያ ነገር የማይቀር እንደነበር እመን ። ይህን ባደርግ ኖሮ ይህ ይሆን ነበር አትበል ። ይልቁንም " ይህ የአሏህ ትዕዛዝ ነው ፤ እርሱ የሻውን ሰሪ ነው" በል ።

በእርግጥም ከችግር ጋር እፎይታ አለ ።
ﺇِﻥَّ ﻣَﻊَ اﻟْﻌُﺴْﺮِ ﻳُﺴْﺮًا

ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
(አል-ሸርህ 6)

ከረሀብ በኋላ ጥጋብ ፣ ከጥማት በኋላ መጠጥ ፣ ከድካም በኋላ እንቅልፍ ፣ ከህመም በኋላ ጤና ፤ ከማጣት ቡኋላ ማግኘት ....አለ ። የጠፉት መንገዳቸውን ያገኛሉ ፤ የተቸገረው ችግሩ ያልፋል ፤ ጨለማው በብርሀን ይተካል ።

ﻓَﻌَﺴَﻰ اﻟﻠَّﻪُ ﺃَﻥ ﻳَﺄْﺗِﻲَ ﺑِﺎﻟْﻔَﺘْﺢِ ﺃَﻭْ ﺃَﻣْﺮٍ ﻣِّﻦْ ﻋِﻨﺪِﻩِ ﻓَﻴُﺼْﺒِﺤُﻮا ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﺃَﺳَﺮُّﻭا ﻓِﻲ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻧَﺎﺩِﻣِﻴﻦَ

አላህም ድል መንሳትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የኾነን ነገር (ማጋለጥን) ሊያመጣ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁትም ነገር ተጸጻቾች ሲሆኑ ተረጋገጠ፡፡
(አል-ማዒዳህ 52)

በርካታ ማይል የሚያካልለውን ሀሩር በረሃ ካየህ ከእሱ ቀጥሎ ሰፊ ጥላ ያለው ማራኪ አረንጓዴ መስክ መኖሩን ልብ በል ። እንባ በሳቅ ፣ ፍርሀት በመፅናናት ፣ መረበሽ በመረጋጋት ይተካል ። ነብዩሏህ ኢብራሂም አለይሂ ሠላም ሠወች እሳት ውስጥ ሲከቷቸው በአሏህ እርዳታ ሙቀቱ አልተሰማቸውም ነበር ።

ﻗُﻠْﻨَﺎ ﻳَﺎ ﻧَﺎﺭُ ﻛُﻮﻧِﻲ ﺑَﺮْﺩًا ﻭَﺳَﻼَﻣًﺎ ﻋَﻠَﻰٰ ﺇِﺑْﺮَاﻫِﻴﻢَ

«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡
(አል-ኢብራሂም 69)

ነብዩሏህ ሙሳ አለይሂ ሠላም በልበ ሙሉነት ፣ በጥንካሬና በፅኑ እምነት ፥
ﻗَﺎﻝَ ﻛَﻼَّ ۖ ﺇِﻥَّ ﻣَﻌِﻲَ ﺭَﺑِّﻲ ﺳَﻴَﻬْﺪِﻳﻦِ

(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡
(አል-ሹዐራዕ 62)

ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም ከአቡበክር ሲድቅ ረድየሏሁ አንሁ ወአርዷህ ጋር ዋሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩበት ጊዜ ለአቡበክር አይዞህ አሏህ ከእኛ ጋር ነው አሏቸው ። ከዚያም ሰላምና ጥበቃ አገኙ ።

አንዳንድ ሰወች የሚታይባቸው ችግርና መከራ ብቻ ነው ። ይህ የሆነበት ምክንያት ከመኖሪያቸው በርና ግድግዳ ወዲህ ያለውን ነገር ብቻ ስለሚመለከቱ ነው ። ነገር ግን ከነዚያ መጋረጃዎች ባሻገር ያለውን ነገር መመልከት ያስፈልጋል ።

አትረበሽ!ነገሮች ባሉበት መቀጠል አይችሉም ። ቀናትና አመታች ይሽከረከራሉ ። መጭው አይታይም ። አንተ ልታውቅ ባትችልም በየቀኑ አሏህ ያዘዛቸው አዳድስ ነገሮች ይከሰታሉ ። በእርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ!


አባቢ ጓደኛዉ የሰጠዉን ግማሹን ገንዘብ ይዞ የአማኔን መድሀኒት ለመግዛት በዛዉም አማኔን ቸክ ሊያስደርግ ወደ አዲስ አበባ ይዞት ሄደ

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት

ክፍል 1⃣9⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

አባቢ ጓደኛዉ የሰጠዉን ግማሹን ገንዘብ ይዞ የአማኔን መድሀኒት ለመግዛት በዛዉም አማኔን ቸክ ሊያስደርግ ወደ አዲስ አበባ ይዞት ሄደ

እኛም አላህ በሰላም ይመልሳቹህ እያልን ሸኘናቸዉ ግን ህክምናዉ ቀላል አልነበረም ወደ ስድስት ወር ሀኪም ቤት ክትትል ያስፈልገዉ ነበር ስድስት ወር ቆዩ እኛም ስድስት ወር ሙሉ በዱአ ጠንክረን፤ በናፍቆት አልቀን....... ጠበቅናቸዉ ረዥም ጊዜ ያአላህ! በስድስት ወር ዉስጥ ስንቱን ስቃይ አየንበት እኔ ትምህርቴን ለማቆረጥ ተገድጀ ነበር እማየ ግን አይቻልም አታቋርጭም ብላ እሷ በየሰዉ ቤቱ እንጀራ ጋጋሪነት ተቀጥራ የኔን የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ጀመረች አባቢ አያቅም ሚስጥር ነዉ በዛ ላይ ጤፍ፤በርበሬ.....አልቆ ደረቅ ቂጣ እየበላን ኧረረረረ ያችን ስድስት ወር ማስታወስ አልፈልግም!

አማኔን አባቢ በስድስተኛ ወሩ ይዦት ሲመጣ አማኔ መሆኑን እስከምንጠራጠር ድረስ ዘንጦ ኢትዮጵያዊ መሆኑ እስከሚያጠራጥረን ድረስ ቀይ ዉብ ፤ ሲያዩት የሚያስደነግጥ ሁኖ በደንብ እያወራ ነበር የመጣ ።




.......ማመን አቃተን ሁላችንም ወደ አማኔ ተጠግተን አማኔ እኔን አስታወስከኝ ሀናን እህትህ ሀናን ነኝ መፀሀፍ ሳነብልህ የነበርኩት ሀናን አስታወስከኝ ስል ሪሀና ደግሞ አማኔ እኔ ሪሀና እህትህ የዛኔ ስተዉን ስትስቅብኝ የነበርኩት እህትህ ሪሀና አለች እማየም አማኔ እኔን መቸም አትረሳኝም እናትህ ስመክርና ስንከባከብህ የነበርኩት አለችዉ.........


አማንም እየሳቀና እያለቀሰ እንዴት እረሳቹሀለሁ ለኔ ብላቹህ መኪናቹህን ሸጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ ከሞቀዉን ቤታቹህ ወጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ የምትወዱትን ነገር አሳልፋቹህ ሰጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ ተሰደባቹህ ለኔ ብላቹህ ያልሆናቹህትን ሆናቹህ .... ሁሉንም አባቢ ነግሮኛል እኔም አስታዉሳለሁ ብሎ ሰብስቦ አቀፈን እኛም እያለቀስን በደስታ ቀወጥነዉ

.....ወድያዉ ጓረቢቶቻችን ተሰብስበሙ የምን ጩኸት ነዉ ብለዉ መጡ እማየም "ልጆች ከደስታ ብዛት እየጫሁ ነዉ ለአላህ ምን ይዋልለታል ልጀ ዳና አማኔ ተሻለዉ ኑ ግቡ አዩት" ብላ ይዛቸዉ ገባች አማኔም ሰላም ካላቸዉ ቡሀላ አንተ አማን ነህ ሲሉ ጠየቁት ያዩቱን ማመን ከብዷቸዉ አማንም በነዛ ደስ በሚሉ ጥርሶቹ ፈገግ እያለ አወ አማን ነኝ ምነዉ ተቀየርኩባቹህ እንዴ አለ እነሱም አይ ......የሚሉት ጠፋባቸዉ ያኔ እብድ ሲሉ አእምሮን የሚነካ ነገር ሲናገሩ እንዳልነበረ ዛሬ ሁሉም አለፈ አልሀምዱሊላህ ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁን! እያልኩ የአላህ ስራ እየገረመኝ አማኔን በትኩረት መመልከት ጀመርኩ በሀሳቤ እናቱ 4 አመት እሱን ፍለጋ ስትሰቃን ታየችኝ አባቱ በሱ ናፍቆት ሲንገበገብ ሳልኩት እህት ወንድሞቹ ተስፋቸዉ ተሞጦ ሙቷል ሲሉ ሳልኳቸዉ የአላህ ቤተሰባቹ እንዴት ሁነዉ ይሆን ስል አሰብኩ ለስድስት ወር አባቢና አማኔ ከቤት ቢጠፉ የሀዘን ቤት ነበር የመሰለ በዛ ላይ ናፍቆቱ ለአመታት ከቤተሰብ ርቆ እያልኩ ሳስብ አማኔ



..... ፈገግ ብሎ "ሀናኔ ምን ፊቴጋ የሚታይ ነገር አለ አፈጠጥሽብኝ" አለና ሁለት እጆቹን ፊቱጋ አድርጎ ፊቱን ሸፈነዉ
....ሀሀሀ ናፍቀኸኝ ስለነበር ነዉ አታፍጥጭ ካልከኝ እሽ አላፈጥም ብየ ፊቴን አዞሮ ጠቀመጥኩ አማኔ
"እንዴ ሀናኔ እየቀለድኩ ነዉ ይሄዉ እንደፈለግሽ እይኝ" ብሎ ወደኔ ተጠጋ እኔ ግን አኩርፌሀለሁ አልኩት
..."እሽ ምን ላርግ"
አንድ ጥያቄ ጠይቄህ ከመለስክልኝ እዞራለሁ
"እሽ የፈለግሽዉን ጠይቂ የምችል ከሆነ እመልሳለሁ"
እርግጠኛ ነህ ስል ደጋግሜ ጠየኩት እሱም አወ አለኝ ልጠይቀዉ ያሰብኩ ስለቤተሰቡ ሁኔታ የት እንዳሉ ነበር ግን ፈራሁ በቃ ጥያቄዉን ለሌላ ጊዜ እጠይቀሀለሁ ለዛሬ ይለፍህ ስል አባቢ እየሰማ ነበር "ኧረ አንች ልጂ ከምንገድኮ ነዉ የመጣን እሱንም በወሬ አታድክሚዉ ይረፍ ምግብም አልበላንም አቅርቢልን" ብሎን ምግብ ላቀርብ ተነሳሁ


......ብከፋፍት የሚበላ ነገር የለም ለካ እማየ አባየ የሰጣትን ብር ጨርሰዋለች ጤፍ መግዣ አጣ አልገዛችም ለዛ ነበር ደረቅ ቂጣ ለሳምንት ስትሰጠን የነበረ የአላህ መቸ ይሆን ይሄ ችግር የሚያበቃ ስል አማየ ሁለት እንጀራ ከሱቅ በዱቤ ይዛ መጣችና ትንሽየ ወጥ ነበረ አቀረበችላቸዉ አባየ ነይ አብረሽን ብይ አላት


እማየም በቅርብ እንደበላች ነገረቻቸዉ እኔም ቢርበኝም አሁን በላሁ አልኩኝ ሪሀና "አባቢ አዉቀዉ ነዉ ትናንት ምሳ የደረቀ ቂጣ እንደበሉ ናቸዉ ጤፉ ካለቀ ቆይቶል እማየም መግዣ አጣ አልገዛችም ለብዙ ቀን ቂጣ ነዉ እየመረረን የበላን"አለች አይ ህፃን መሆን ሁሉ ነገራቸዉ ግልፅ ነዉ

.....አባቢም "ለምን አልነገርሽኝም"አለ
እማየም ብር ይቸግርሀል ብየ ምናልባት ብናግርህና ብሩን ብትልክልኝ አንተም ሆንክ አማኔ በብር እጥረት የምትጉላሉ መሰለኝ ከዛ የቀረችዉን ዱቄት በርበሬዉ ዘይቱም ሲያልቅ እየጋገርኩ በደረቁ መመገብ ጀመርን ለመሆኑ ብር ተረፈህ እንዴ ስትል ጠየቀችዉ
አባቢም እዝን ብሎ "እንኳን ብር ሊተርፈን ለትራንስፖርት እንኳን አጠን ዳክተሮቹ ናቸዉ የሰጡን" አለ አየህ እኔም እንደማይበቃቹህ ገምቸ ነዉ ብር ላክልኝ ያላልኩህ አለች።

አባቢም "ዉዴ የኔ ባትሆኑ ይቆጨኝ ነበር ይሄ አስተሳሰብሽኮ ነዉ እንድወድሽ ሁሌም እንድናፍቅሽ የሚያደርገኝ" ......አልጨረሰም አማን "ዉይ ፍቅራቹህ ያስቀናል በሉ እኛንም የሚያካትት ወሬ አምጡ" አለ እኔ ከመሀል አማን ግን የድሮዉን ሁሉንም ነገር ታስታዉሳለህ ስል ጠየቁት
አማኔም አወ እዚህ ምን እንዳደረኩ አባቢ ነግሮኛል እኔም አስታዉሳለሁ ልንገርሽ አለኝ ለማወቅ በጓጓ አንደበት የዚህን አላልኩህም እዚህማ አብረንህ ነበርን እኔ ያልኩኝ እዚህ ሳትመጣ በፊት ቤተሰቦቹህ የትና እንዴት ናቸዉ? አንተስ ምን ሁኔታ ላይ ነበርክ? ስል ጠየኩት አማኔም......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል


Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣0⃣
....... ሰሚራ ሽኩር

.......ለማወቅ በጓጓ አንደበት የዚህን አላልህም እዚህማ አብረንህ ነበርን እኔ ያልኩኝ እዚህ ሳትመጣ በፊት ቤተሰቦችህ የትና እንዴት ናቸዉ? አንተስ ምን ሁኔታ ላይ ነበርክ?ስል ጠየቁት አማኔም አይኑን ወደ መሬት ወርዉሮ ባዘነ ፊት"ምን ያደርግልሻል የኔ ታሪክ
..... እኔኮ የሚነገር ታሪክ የለኝም በቃ ታሪክ የለኝም! ብሎ ማልቀስ ጀመረ
አባቢ "አንች ልጂ ምን መሆንሽ ነዉ ለምን የሚያስጨንቀዉን ማስታወስ የማይፈልገዉን የትናንት ሂወቱን ትጠይቂዋለሽ ትናንትኮ ታሪክ ሁኖ አልፏል በቃ ሙቷል ላይመለስ አምልጧል ትናንት ጥሩም ሆነ መጥፎ ላይደገም ለዛሬና ለነገ ሂወታችን ትምህርት ሁኖን አልፏል።
የትናንት ሂወቱን እያስታወሰ ባለፈ ነገር የሚያለቅስ ሞኝ ነዉ ትናንት የሆነዉ ሁሉ መሆን ስላለበት ነዉ የምሆነዉም መሆን ያለበት ነዉ! አላህ ከመወለዳችን በፊት ሁሉንም ፅፎታል የተፃፈዉም ተግባራዊ ይሆናል ከኛ የሚጠበቀዉ ሰበብ ማድረስ ብቻ ነዉ።
.... ግን ሀናኔ እንዲህ የሚያስጨንቀዉን ጥያቄ ስጠይቂዉ ሁለተኛ እንዳልሰማሽ ሁለተኛ!" ብሎ ተቆጣኝ እህ አባቢ ምን አጠፋሁ እያልኩ ወደ ክላሴ ገባሁ እማኔና ሪሀና ተከትለዉኝ መጡና አማኔ ይቅርታ አለኝ እኔም ይቅርታ ማለት ያለብኝ እኔ ነኝ ይቅርታ አልኩት "አይ እኔ ነኝ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ አስቆጣሁሽ አይለል በአላህ ይቅርታ አለኝ እኔም ጣጣ የለዉም ይቅርታ አድርጌልሀለሁ አንተም ይቅርታ አድርግልኝ አልኩት አደረገልኝ ግን ዉዶቸ ተበድላቹህ ይቅርታ አድርጋቹህ ታዉቃላቹህ? ወይም እናንተ ሌላዉን በድሏቹህ ይቅርታ ጠይቃቹህ ታዉቃላቹህ?
ሁሌም አዉቀንም ሆነ ሳናቅ የምንናገረዉ ፤የምንሰረዉ ስራ የማንን ልብ እንደሚሰብር ማንን እንደሚያስቀይም አናቅም ይቅርታ እናድርግ ጣአሙን አድርገን እንጂ አናቀዉም
በአንድ ሰዉ ተበድላቹህ ወይም ተከድታቹህ ይቅርታ ማድረግ እንኳን ማሰብም ሊከብድ ይችላል ነገር ግን
ቂም፤ምሬት፤ህመም...... በዉስጣችን ስንይዝ ራሳችንን እንጎዳለን። ስለዚህ ለሁሉም ነገር ይቅርታ አድርገን መርሳት ጥሩ መፍትሄ ነዉ።


ዉዶቸ ዓለም በአዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከአንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ፡፡ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል፡፡ ከዚህም የተነሣ በሌሎች ሰዎች መገፋታችን ወይም እኛ ሰዎችን መግፋታችን አይቀርም፡፡ ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው፡፡ እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል፡፡ እኛም ለሌሎች እናስፈልጋለን ፡፡ ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው፡፡ ለሌሎች ሰጪም ነው፡፡

መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ስህተት የእንቅስቃሴና የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ሰለዚህም መሳሳት በየትኛውም የሕይወት ገጽ ላይ ሊከሰት የሚችለው ፡፡ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳትና ማጥፋት አስቀያሚ ድክመት ነው፡፡ ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ ፡፡ ከተገፋንም በይቅርታ እንለፍ፡፡ ይህ የአእምሮ ብስለትና የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ነው፡፡

ይቅርታ ማድረግ ጥሩ ነው ጨርሶ መርሳት ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡



ሰዎች በቀልን ትተው ይቅርታ ማድረግን የማይመርጡበት ምክንያት ዋጋው ስለሚወደድባቸውና የነርሱ ትንሽነትም ስለማይመጥነው ነው፡፡

አማኔ ጋር ይቅርታ ተበብለን አማኔ "ይቅርታሽ ከዉስጥ አይመስለኝም" አለኝ
ሪሀና "አወ ከዉስጧ አይደለም ታሪክህን ለማወቅ ሁላችንም ጓጉተን ነበር"

.....አማኔም "እሽ የኔ ታሪኩ ቢመራቹህም ለወደፊት ሂወታቹህ ትምህርት ይሆናቹሀልና ማወቁ ደስ ካሰኛቹህ ታሪኬን እናግራቹሀለሁ " ብሎ ታሪኩን እንዲህ መናገር ጀመረ

.....አባቴን አላቀዉም እናቴ ታናሽ ወንድሜን እርጉዝ እንደሆነች ነዉ የሞተ።
እናቴ ናት ብቸዋን ጪኗ እስከሚደማ ድረስ ጥጥ እየፈተለች እስከ አስር አመቴ ድረስ ያሳደገችኝ አንድ ታናሽ ወንድም አለኝ ሌላ እህትም ሆነ ወንድም የለኝም
በትምህርቴ በጣም ጎበዝ ስለነበርኩ እናቴን ለማገዝ ትምህርቴን ላቋርጠዉ ብላት እናቴ አይቻልም እኔ የምለፋዉ አንተን ጥሩ ደረጃ ለማድረስ ነዉ ደሞ ኢንሻአላህ ነገ ዶ.ር ሁነህልኝ ባንተ ያልፋልኛል።
....የኔ ልጂ የዛሬን ችግር አትይ ነገ ያልፋል ብቻ አንተ ጠንክረህ ተማርልኝ ትለኝ ነበር እኔ ግን የሷን ልፋት እያየሁ ተቀምጨ መማር ከበደኝ አንድ ቀን ለምን ከጠዋት እየተማርኩ ከሰአት የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን እየሰራሁ እናቴን አላሳርፋትም ብየ አሰብኩ ለናቴ ብነግራት አትፈቅድልኝም ሳልናገር ወደ አንድ እየተሰራ ወዳለ ፎቅ ተሸካሚ እንኳን ቢቀጥሩኝ ብየ አመራሁ

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል2⃣1⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

ለናቴ ብነግራት አትፈቅድልኝም ሳልናገር ወደ አንድ እየተሰራ ወዳለ ፎቅ ተሸካሚ እንኳን ቢቀጥሩኝ ብየ አመራሁ

ፎቁን በኩንትራት የያዘዉ ሰዉየ ጆርጂ ይባላል በናቱ አሜሪካዊ ሲሆን በአባቱ ቻይናዊ ነዉ ጥሩ ፀባይ አለዉ አማረኛ በደንብ ይሰማል ለማዉራት ቢከብደዉም እየተንተባተበ ትንሽ ትንሽ ያቃል ለመግባባት አይቸገርም።
....እኔም በፍራት የቤተሰቤን ችግር ነገሬዉ እዚህ ጂብሰም፤ሲሚንቶ፤ኮርኔስ የመሳሰሉ ነገሮችን...... በመሸከም እንዳመላልስላቸዉና የተወሰነች ብር ብትከፍለኝ ብየ አናገርኩት ጆርጂም "አንተኮ ገና ህፃን ነህ አትችልም" ብሎ እንቢ አለኝ እኔም ተስፋ በመቁረጥ እግሬን ዘርግቸ ቁጭ ብየ ማልቀስ ጀመርኩ ጆርጂ በኔ ሁኔታ ልብ ተንክቶ "በቃ እሽ እኔ ትንሽ ገንዘብ እሰጥሀለሁ አንተ ዝም ብለህ ተማር" አለኝ እኔ ግን አልተስማማሁም የላቤን ገንዘብ ነዉ ለእማየ ማብላት ያለብኝ አልኩት እሱም በንግግሬ ተደንቆ አንተ ህፃን አይደለምህ ትልቅ ነህ የትንሽ ትልቅ አለሽ


.....ከዛ ቀን ጀምሬ ከጥዋት ትምህርቴን ስማር እቆይና ከሰአት ከጆርጂ ጋር አዉላለሁ ምግብም አሱ ጋር እመገባለሁ ጆርጂን በጣም እወደዋለሁ እንዳአባትም ይመክረኛል፤አጋዥ መፅሀፎችን ይገዛልኛል ብቻ ደስ የሚል ፀባይ ያለዉ የዋህ ሰዉ ነዉ።

እማየ ሁሌም ከሰአት ቁርአን ቤት ቁርአን ስቀራ የምዉል ይመስላታል ካፏ የማይለየዉ የሁል ጊዜም ምክሯ ሰላትና ቁርአንህን አደራ!!!ነዉ
...እኔም ሰላቴን በሰአቱ እሰግዳለሁ ቁርአኔን ደግሞ እሁድ እሁድ ስራም ትምህርትም ስለማይኖር እቀራለሁ
አንዳንዴ ስራ ስዉል ድክም ሲለኝ ሱቢህ ሲሰገድ እየሰማሁ ለመነሳት ይከብደኛል የዛኔ እማየ በጆክ ዉሀ ይዛ ትመጣና "ትናሳለህ አትነሳም" ስትለኝ አምስት ደቂቃ አልቆይም ስነሳ"
...... ልጆችን ስናሳድግ በኢማናቸዉ ጠንካራ አድርገን ቁርአን እንዲቀሩ፤ሰላት እንዲሰግዱ ካላደረግናቸዉ ተለቀዉ እንደፈለጉ ካደጉ ቡኋላ ሲያድጉ ይስተካከላሉ ማለት ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ነዉ።



ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል በእናታቸው እጅ እንዴት እንዳደጉ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ
“እናቴ ገና በ10 ዓመቴ ነው ቁርኣንን በቃሌ እንድሐፍዝ ያደረገችኝ፡፡ የሱብሒ ሰላት ሳይደርስ በፊት ትቀስቅሰኝ ነበር፡፡ በዚያ እጅግ ቀዝቃዛ በሆነው የባግዳድ ከተማ በለሊት ተነስታ ለዉዱእ የሚሆን ዉሃ አሙቃ ታቀርብልኛለች፡፡ ልብሴን ታለብሰኝና በጉፍታዋና ነሒጃቧ በሚገባ ከተሸፋፈነች በኋላ መስጂዱ ከኛ አካባቢ ራቅ ስለሚልና ጨለማም ስለሆነ እጄን ይዛ መስጂድ አድርሳኝ ትመለሣለች”
እሳቸውም አላሳፈሯትም
ዝሆን እንኳ ቢገረፍ አቋሙን ሊቀይር የሚችልበትን ግርፊያ በስተርጅና ተገርፈው በዓላማቸው ፀንተዋል።
ገራፊያቸው የአንድ ቀኑን ትዝታ እንዲህ ይተርከው ይዟል:- "ከዕለታት አንድ ቀን ቁርአን የአላህ ቃል አይደለም እንዲሉ ተገደው ራሳቸውን በተደጋጋሚ ስተው እስኪወድቁ ድረስ ብዙ እንግልትና ግርፋት ደረስባቸው ጀርባቸው ቀልቶ ሰንበር አውጥቶ ተዝለፍልፈው ሲወድቁ ስመለከት አዝኜ አንድ ኩባያ ውሀ አቀበልኳቸው ቀና ብለው በትኩረት ተመለከቱኝና ዛሬ ፆመኛ ነኝ በማለት መለሱልኝ። አያቹህ የናታቸዉ አስተዳደግ ጠንካራ ኢማን እንዲኖራቸዉ እንዴት እንዳረገ....

ወደ አማኔ ታሪክ ስንመለስ
"እናቴ ለኔ እናት ብቻ አልነበረችም ሁሉ ነገሬ ነበረች ሲያመኝ ከኔ በላይ ታማ ሲጨንቀኝ ተጨንቃ ፤ሳትበላ አብልታ....ነዉ ያሳደገችኝ ዉለታዋን በምን ይሆን የምክሳት ሁሌም አስባለሁ
የናት ዉለታዋ

ቃላት ቢደረደር በብዙ ጋጋታ
መቸ ይገልፀዋል የናትን ዉለታ
የናትን ዉለታ እንዴት ችየ ላዉራዉ
የሁሉም ተምሳሌት መሆኖን አቃለሁ
ሀዘኖን አርቀህ ደስታዋን አብዛላት ብየ እየተማፀንኩ
ከዛ ከጭንቁ ቀን ከዉልደቷ ጀመርኩ
ስትወልድ ያለዉ ስቃይ እንዴት ይገለፃል
ከሀሊቁ በቀር ማንስ ያቅላታል
ያየችዉስ ስቃይ በምንስ ይተካል
ከወለደች በላይ ጭንቀቱ ይብሳል
ከመዉለዷ በፊት ካለዉም ይለያል
እሷ ሳትበላ ልጇን ታበላለች
አልበላም ሲላትም በጣም ታስባለች
ለምን ይሆን ብላ ከባዱን ታዝናለች
ከታመመ ደግሞ እንቅልፏን ታጣለች
በሀሳብ ተጠምዳ ብትሰለሰላለች
እስከሚያድጉ ድረስ በጭንቀት ታያለች

እሰይ አደጉልኝ ነፍስም አወቁልኝ
ስራ ስለያዙ ሀሳቤን አረፍኩኝ
ብላ ሳትጨርስ ምነዉ አመሸብኝ
ምን ነክቶብኝ ይሆን ልጀ የቀረብኝ..
.
.
ከመዉለዷ በፊት የጀመረ ስቃይ
ማብቂያዉ ቢሆን እንጂ እዱንያን ስትለይ
ሌላም ማብቂያ የለዉ
አላህ ያሳምረዉ
ደርቦ ደራርቦ ጀዘዋን ይክፈለዉ!🙏🙏
.....ሰሚራ ሽኩር

....አንድ ቀን ጆርጂ የሚሰጠኝን ገንዘብ ለእማየ ሰጠኋት እማም ከየት አመጣኋዉ ስትል አፋጠጠችብኝ እኔም ሁሉንም ነገርኳት እማየ በኔ ትደሰትብኛለች ብየ አይን አይኖን ሳይ የእማየ አይኖች በእንባ ሞልተዋል ደነገጥኩ እማ ምነዉ እኔ ልጂሽኮ በሀላል እንጂ በሀራም አይደለም ገንዘቡን ያመጣሁት አልኳት እማም እንባዎች እየወረዱ "አቃለሁ የኔ ልጂ ሳሳድግህም ሀላልን እንጂ ሀራምን እንዳትነካ አድርጌ ነዉ" አለችኝ እሽ እማ ምን ያስለቅስሻል ስላት "እኔ የሚያስለቅሰኝ ሁለት ልጆቸን ማሳደግ አለመቻሌ ነዉ አንተን በዚህ በጨቅላ እድሜህ ከሀቅምህ በላይ ስራ ለመስራት ተገደድክ"

......እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም ተይይዘን አለቀስን እማ ለትንሽ ቀን ነዉ ይሄ ሁሉ ስቃይ ያልፋል ብየ ወደ ጆርጂ አመራሁ ጆርጂን ስራ ቦታ አጠሁት ወዴት ሂዶ ይሆን ብየ ስፈልገዉ አማኔ ብሎ አንገቴን ከኋላየ አቀፈኝ በጣም ተግባብተናል የእማየን ሁኔታም አስረድቸዋለሁ

አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ ብሎኝ እማየን ላሳየዉ ይዤዉ ወደ ቤታችን አቀናሁ.....

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣2⃣

........ ሰሚራ ሽኩር


አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ ብሎኝ እማየን ላሳየዉ ይዤዉ ወደ ቤታችን አቀናሁ

እማየ ጥጥ እየፈተለች ነበር የደረስን ጭኗ ጠቁሮ ብልዝ ብሎ ጆርጂ አየዉ ...እማየም አማኔ ማን ነዉ ስትል ጠየቀችኝ እማ ጆርጂ ይባላል ከሱ ጋር ነዉ የምሰራ ብየ አስተዋወኳት ።
...... አረፍ በሉ ብላን ወደ ዉስጥ የሚበላ ነገር ልታመጣልን ሄደች ምን ልታመጣ ይሆን ብየ ተጨነኩ
.... እንጀራ በበርበሬ ይዛ መጣች ቤት ያፈራዉን ብሉ ወጥ አልሰራሁም ብላ አቀረበችልን እማ ጆርጂ በርበሬ የሚበላ አይመስለኝም ከሱ ጋር ሁሌም ሩዝ ነዉ የምበላ አልኳት ጃርጂም እየተንተባተበ በርበሬ እበላለሁ አትጨነቂ ብሎ ግድ አለግድ መብላት ጀመረ አንድ ጉራሽ በአንድ ብርጭቆ ዉሀ እያወሀደ

....የምር ጆርጂ ሰዉ አክባሪ የሰዉ ምንነት የገበዉ ስላለዉ የማይንጠራራ ከሁሉም ጋር መግባባት የሚችል ጥሩ ሰዉ ደግ ሰዉ ነዉ።

እንዲህ እንዲህ እያልን በኩንትራት የያዘዉ ፎቅ አለቀ እሱ ደስ ሲለዉ እኔ ከሱ መለየቴ ከፍኝ ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነዉ እማየም በጣም ትወደዉ ነበር አዘንኩ ጆርጂም "አይዞህ አትዘን እኔ በጉዲፈቻ አሳድገዋለሁ ብየ ይዠህ እሄዳለሁ አለኝ ደነገጥኩ ደስታና ሀዘን ባንዴ ወረሩኝ ደስ ያለኝ ከጆርጂ ጋር ቻይና መሄዴ ሲሆን የከፋኝ እናቴን እንዴት ትቻት እሄዳለሁ የሚለዉ ነበር ......ግራ ገባኝ እማየን ነገርኳት እሷም በጣም አዘነች ነገር ግን አዛ ጥሩ የትምህርት እድል እንደማገኝ ጆርጂ ሲነግራለት ቅር ቢላትም መርቃ ሸኘችን

ቻይና ዉስጥ
....... ኢስልምናን ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና የደረሰው በዑመር (ረ.ዐ) ኸሊፋነት ዘመን በታላቁ ሰሃባ ‹‹ሰዓድ ኢብን አቢ-ወቃስ›› (ረዐ) እንደሆነ ይነገራል።

በቻይና የመጀመሪያውን መስጂድ ያሰራውም ሰዓድ ሲሆን ‹‹ሑዓሼንግ›› የሚባልና አሁንም በይዞታ የሚገኝ የ1300 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ መስጂድ ነው።

በአገሪቱ 80 ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ከህዝቡን 2% ገደማ ይሸፍናሉ።

ሙስሊሞቹ በብዛት የሚኖሩበት ቦታ ‹‹ዢንጂያንግ›› ሲባል ከአፍጋስታን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ጋር የሚዋሰን ሰፊ ግዛት ነው።

‹‹ዢንጂያንግ›› ቀድሞ የዑስማያ ኸሊፌት የተርኪስታን ግዛት የነበረ ሲሆን ኸሊፋው ከወደቀ በኋላ በ1949 ቻይና በሐይል ልትወስደው ችላለች። ግዛቱም ከቻይና ሰፊው ሲሆን በማዕድን የበለፀገ ነው።

ቻይና ውስጥ ሁለት አይነት ነገድ ያላቸው ሙስሊሞች ያሉ ሲሆን ‹‹ሐም›› እና ‹‹ኡግሁር›› ይባላሉ። ሐሞች ቻይናዊ ሲሆኑ ኡግሁር ደግሞ በመልካቸውም የተለዩ የመካከለኛው ኤዥያ ዝርያዎች እንደሆኑ ይታመናል።

በቻይና ሁሉም ሙስሊሞች መድሎ ቢደርስባቸው ከፍተኛ በደል የሚፈፀምባቸው ግን የኡግሁር ሙስሊሞች ናቸው።

የኡግሁር ሙስሊሞች ከሌላው በተለየ በደል የሚደርስባቸው አንደኛው በዘራቸው ቻይናዊ ስላልሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አካባቢው በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ መንግስቱ ህዝቡን የማጥፋት ዕቅድ እንዳለው ይነገራል።

ቻይና በኡግሁር ሙስሊሞች ላይ ከምትፈፅመው ግፍ መካከል ወላጅና ልጅን መነጣጠል፣ በማጎሪያ ካምፖች ማሰር፣ አካላቸውን መበለት፣ ሰላት፣ ፆምና ቁርኣን መከልከል፣ አልኮል ማስጠጣት፣ የአሳማና ውሻ ስጋ ማስበላት፣ መግደል እና ሌሎችንም ይፈፅማሉ።

የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ አሰቃቂ ግፍ እየፈፀመ ድርጊቱ ‹‹ሽብርተኝነት›› አልተባለም።

በዑመር (ረዐ) ዘመን የቻይና መንግስት ለፋርስ ንጉስ መጠጊያ እንኳን ለመስጠት ኸሊፋውን በመፍራት እንቢ ማለቱ ይነገራል። ዛሬ የሙስሊም አገራት የኡግሁር ሙስሊሞች አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው እያዩ ከቻይና ጋር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንኳን ማቆም አልቻሉም።

‹‹አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ።››
(ማዒዳህ 82) በርግጥም ጌታየ እዉነት ተናገረ

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጃርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት....

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣3⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጆርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት እሱም"ምን ማለትህ ነዉ አንተን እዚህ ለማምጣት ስንት እንደለፋሁ ታቅ የለ ደሞስ እናትህ መርቃ የሸኘችህ ተመቸኝም አልተቸኝም ብለህ እንድትሄድ ነዉ?
.... አማን ጠንከር ብለህ ተማር እናትህ የፈለገችዉ ቦታ ደርሰህ ህልሟን እዉን አድርግላት ስማ ላንተ ሳይሆን ለዛች ሳትበላ አብልታ ፤ሳትለብስ አልብሳ፤ሲያምህ ታማ ላሳደገችህ እናት ብለህ ቆይ እኔ እያለሁስ እኔ አግዛቹህ ነበር አሁን ሂደህ በዚህ እድሜህ ምን ልሰራ ነዉ..."የትያቄ ማእበል አወረደብኝ ወላሂ ልሂድ ብየ በመጠየቄ አፈርኩ አንገቴን አቀረቀርኩ ጆርጂም አይዞህ ቋንቋዉ ከባድ ይመስላል እንጂ ቀላል ነዉ እኔ አስተምርሀለሁ አለኝ ግን የሚቻል አልመስልህ አለኝ ፁህፉ ኧረ ኢላሂ ይሄን እኔ ፅፌ ላወራዉ ነዉ እል ነበር ለካስ የሰዉ ልጂ ተአምራዊ ነዉ የማይቻል ነገር የለም ከትንሽ ጊዜ ቡሀላ በደንብ መናገርና መፃም ጀመርኩ

.....ትምህርት ቤት ብዙ ጊዜ በዘር፤በሀይማኖት....የነሱ ካልሆን ለሁሌም መጨረሻ ተሰላፊ ነን እነሱ አጥፍተዉ የምንቀጣ እኛ እኩል ዉጤት አምጥተን የሚሸለዉ እነሱ ናቸዉ ብቻ ማን እንደሀገር !ሁሉ ነገሩ ይከብዳል በተለይ ከሰዉ በታች አድርገዉ ሲያዩን ልባችን ይደማል።

.....ጆርጂ ሁሌም ይከታተለኛል ጥሩ ዉጤት እንዳመጣ ያስጠነኛል የምፈልገዉን ነገር ሳልጠይቀዉ ያሟላልኛል ከትምህርት ቤትም የተሻልኩ ተማሪ ለመሆን በቃሁ እናቴን በዱአ እረስቻት አላቅም ከተለያየን አስራ ስምንት አመት ሆነን እኔም ትምህርቴን እናቴ እንደምትፈልገዉ ዶክተር ሁኘ ተመረኩ ከሶስት አመት በፊት በጎረቢት ስልክ እየወደልኩ አንዳንዴ አወራት ነበር


.....ከሶስት አመት ቡኋላ ግን ስልኳም እቢ አለ አግኝቻት አላቅም ብቻ ሰላም ትሁንልኝ እኔም ሰሞኑን መሄዴ አይቀርም የመጠሁበትን አላማ አሳክቸ ጨርሻለሁ ብየ ጆርጂን ጠየኩት ጆርጂም በደስታ እናትህን አይተህ ትመጣለህ ብሎ እያለቀሰ ላከኝ እኔም እያለቀስኩ አመስግኘዉ ወደ ሀገሬ መጣሁ ምንገድ ላይ ልቤ መረጋጋት አልቻለም ዝም ብሎ ጭንቅ ጭንቅ ይለኝ ጀመር


.... አሁን እንዲህ አድጌ ስታየኝ ምን ትል ይሆን ስል አሰኩ ያ ሁሉ ችግር ከእንግዲህ ያበቃል ....ያረብ እናቴን በሰላም ላግኛት በጣም ንፍቅ ብላኛለች እያልኩ ወደ ቤት ገባሁ ሰርፕራይዝ ነዉ መምጣቴን ማንም አያቅም ለማየ ሂጃብ መስገጃ....ያልያዝኩት ነገር የለኝም
ለወንድሜም ብዙ ነገር ይዘዣለሁ


.... ቤት እንደደረስኩ ቤቶች ብየ ገባሁ አንዲት ሴት መጣችና ምንድን ነዉ አለችኝ እኔም ደንገጥ ብየ እማስ አልኳት ማን ነች እማ ስትል ጠየቀችኝ ግራ ገባኝ እእእእ እዚህ የነበሩት ይሄኮ የኛ ቤት ነበር እናንተ እነማን ናቹህ ወንድሜስ.....

"ቆይ አንተ የማማ ፋጡማ ልጂ ነህ" ስትል ጠየቀችኝ እኔም አወ የሷ ልጂ ነኝ "ዉይ አላህ ለጀነት ይበላቸዉ እንዴት ያሉ ጥሩ ሰዉ ነበሩ ይሄን ቤት ወንድምህ ነዉ ከሶስት አመት በፊት እናታቹህ ስትሞት የሸጠልን" አለችኝ


የምሰማዉ በህልሜ ነዉ ወይስ በዉኔ እማ አልሞተችም ትሰሚያለሽ እማ አልሞተኝም ብየ የልጂቷን አንገት ጠቅጠቄ ያዝኩት ከመሀሌ ወንድምህ መጣ ብሎ ማን እንደነገረዉ አላቅም ወንድሜ ሙሀመድ መጣና ተጨምጭሞ ማልቀስ ጨመረ እንዴት እንደለየኝ አላቅም አስራ አምስት አመት ሙሉ ተለያይተን ለነገሩ እሱ ጠቆር ማለቱ እኔ ነፃ ማለቴ ነዉ እንጂ መንታ ነዉ የምንመስለዉ።

ሙሀመድ እማየ መሞቷን ሲነግረኝ
አላመንኩም እማ መጥታቸለሁ እይኝ! እማየ እይኝ ዶክተርኮ ሆንኩልሽ! እማ ህልምሽ እዉን ሆነልሽ! እማ አቤት በይኝ! አማ ያ ሁሉ ችግርኮ በኔ በልጂሽ አሁን ሊያልፍልሽ ነዉ! እናቴ ያልፋል ብለሽኝ አልነበረ ሲያልፍ ሳታይ አማ ......ብጮህ ብነሳ ብወድቅ ከየት ትምጣ ላትመለስ ወደ ዘላለማዊዉ ሂወት ሂዳለች አላህ ለጀነት ይበላት።
እኔም ለብዙ ቀን አዘንኩ ለጆርጂም ነገርኩት አይዞህ ብሎ አፅናናኝ

....ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ በጣዉስ ብየ ፈራሁ


Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇
@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣4⃣

............ ሰሚራ ሽኩር


.......ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ ባጣዉስ ብየ ፈራሁ
ከዛ ወጀ ቻይና ልሄድ የነበርኩትን ጉዞ ሰርዠ እዚሁ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ በአንድ ቀን አንድ ትልቅ ሆስቲታል ዶክሜንቴን ሁሉ አስገባሁ በደስታ ተቀበሉኝ "

አላመንኩም!አማን ዳክተር ነዉ ደነገጥኩ እኔጃ ብቻ አላመንኩትም ግን ደግሞ አባቢ ያኔ አደጋ ሲያደርስ ካለ ነገር ልጁን በሂወት እንዲቆይ ሰበብ አልሆነም ደሞ ሀኪም ቤት ከ ዳ.ር ጋር ቀዶ ጥገና ክፍል ገብቶ ነበር እዛ ደግሞ ዳክተሮቹ ብቻ ነበር የሚገቡት ብሎናል



ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡብኝ እንዴት አልጠረጠርኩም ራሴት ታዘብኩት ግን ደግሞ አሁንም አላመንኩም ሰሞኑን ከምግቡ ይሆን ከጭንቀት ጨንጓራየን በጣም አሞኛል እንደዉም ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ነዉ አማን ዳክተር ከነበረ ስለህመሜ በቂ እዉቀት ይኖረዋል ለነገሩ የሆድ ዉስጥ እስፔሻሊት ካልሆነ እንዴት ያቃል ምናልባትም ከአንገት በላይ ፤ የአጥንት.... እየተባሉ ዳክተሮች ሲለሚከፋፈሉ እሱ ላያቅ ይችላል ለማንኛዉም እስኪ ልጠይቀዉ ብየ ልጠይቀዉ ስል ሪሀና እማን ዳክተር ነዉ ደስ ሲል ሀናን ደስ ይበልሽ ጨንጓራየን አመመኝ ቆረጠኝ የለም አማን አለልሽ እሱ ያክምሻል ፐ በአንድ ቤት ሁለት ዳክተር እያለች ሳቀች


አማኔም "ሀናን ጨንጓራሽን ያምሽ ነበር እንዴ ቆይ ምግብ መመገብ ቀንሰሻል፤ሆድሽ አካባቢ ያቃጥልሻል....ሲል ጠየቀኝ እኔም አወ ያቃጥለኛል ምግብም ብዙም አይደለሁም አልኩት



አማኔም ይሄማ የጨጓራ ባክቴሪያ / H. pylori infection ይባላል

ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ሲሆን ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች ዋነኛዉ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች
ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶች የሚታይባቸዉም
የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት
ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም
ማቅለሽለሽ ፤የምግብ ፍላጎት መቀነስ፤ በተደጋጋሚ ማስገሳት፤ የሆድ መንፋት
የክብደት መቀነስ .....ናቸዉ፡፡


ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመሽ
የመዋጥ ችግር ካለብሽ
• ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፓልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣሽ
ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ አለኝ

ገረመኝ አሁን ዳክተር እንደነበረ እርግጠኛ ሆንኩኝ ሪሀና "አማኔ ጨንጓራ ባክቴርያ እንዴት ሊፈጠር ይችላል ለኢንፌክሽኑ የሚያጋልጡ ነገሮች ምንምን ናቸዉ የማቀዉ ነገር የለም" ስትል በደንብ እንዲያብራራላት ጠየቀች አማኔም


ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች
በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር
ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር
በማደግ ላይ ባሉ/ባላደጉ አገሮች/ የሚኖሩ ሰዎች፡ ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር
የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች ደግሞ

የደም ምርመራ
የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት
የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ህክምና
የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊያዝላቹህ ይችላል ።

ሀናን ምንም አላለኝ ብለሽ ዝም አትበይ ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications ብዙ ነዉ

ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች
ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡
የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡
የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡


ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳክተር ከሆንክ ቡሀላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
..... ግን ከታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 25
........ ሰሚራ ሽኩር

........ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳ.ር ከሆንክ ቡኋላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
....ግን ታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ዳክተር ሁኘ ስሰራ ብዙ አይነት ሰዎች፤ ብዙ አይነት ህመሞች ያጋጥሙኝ ነበረ
ሱሜንም(ሱመያ) ያገኘኋት እዚሁ ሀኪም ቤት ነበር ብሎ አዮኖች እንባን ያዘንቡ ጀመር ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠረዉ አጋጣሚ በትዝታ እንዲህ ሲል አጫወተን

.....እሁድ ቀን ሆስፒታል አዳሪ ተረኛ እኔ ነበርኩ ታካሚዎችን እስከ ስድት(6) ሰአት ካስተናገድኩ ቡኋላ እንቅልፌን መቋቋም አልቻልኩም ቀንም በዝራ ቪዚ ስለነበርኩ ጋዉኔን ሳላወልቅ ከተቀመጥኩበት የተሽከርካሪ ወንበር ሳልነዛ እንቅልፍ ወሰደኝ ለሊት ወደ አስራ አንድ ሰአት ይመስለኛል ሁለት ወጣቶች አንድ በጣም ዉብ የሆነችን ወጣት አንዱ በእቅፉ ይዛ አንዱ ጫማዋንና ሂጃቧን ይዘዉ ዶክተር ዳክተር! እያሉ በጩኸት ወደኔ መጡ

....እኔም ከእንቅልፌ ደንግጨ ነበርና የተነሳሁ ምን ተፈጠረ አልኳቸዉ እነሱም ይችን ህፃን ተጫዉተዉባት እባክህ ፍጠን የምታደርገዉን አድርግ ስታቃስት ስትጮህ ቆይታ ከሁን ነዉ ራሷን የሳተች ሳይ የልጂቷ ፀጉር በጣም ረዥም ነዉ በልጁ እጂ ወደ ታች ወርዶል፤ መልኳ በጣም ቀይ አፍንጨዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች ልብሷ በደም የተነከረ ዉብ ቆንጆ እንስት ናት ።

እኔም በፍጥነት ግልኮስ ተክየላት እነሱ ከየትና እንዴት እንዳገኟት ጠየኳቸዉ ያገኟት ሱቢሂን ለመስገድ ከቤታቸዉ ሲወጡ መንገድ ላይ ነበር ስትጮህ የደረሱላት ማን እንደዚህ እንደተጫወተባት የሚያዉቁት ነገር አልነበረም ብቻ በጣም ጥሩ ልጆች ናቸዉ እስከምትነቃ ለሰአታት ከጠበቋት ቡኋላ ነቃች ሁላችንም አጠገቧ ነበርን ሁላችንንም አልያቹህ አለችን ሀኪም ቤቱን በዛ በለሊት በጩኸት ቀወጠችዉ።

ፈራናትና ሁላችንም ወጣን ለነገሩ ሲስተር ሀዋ አለች የኔ አጋዥ እሷ ናት ሲስተር ሀዋ ስትገባ ምንም አላለቻትም እኛን ግን ስታይ እየጮኸች፤እያለቀሰች ፊቷን አዙራ በፍራት ትንቀጠቀጠች።

....በወንዷች ከባድ ጉዳት ስለደረሰባት ወንዶች ሁሉ አንድ አይነት ነዉ የሚመስሏት ለማንኛዉም ሲስተር ሀዋ ስላለች ትንከባከባታለች አብሹሩ ብየ ያመጧትን ልጆች ወደ ቤታቸዉ ላኳቸዉ

ሪሀና "አማኔ ሲስተር ሀዋ ማን ናት" ስትል ወሬዉን አቋረጠችዉ

አማኔም "ሲስተር ሀዋ ማለት ከተመደብኩኝ ቀን ጀምራ አይዞህ የምትለኝ፤ከጎኔ ሁሌም የማትጠፋ በጣም የማዝንላት ሚስጥሯን የምትነግረኝ የምነግራት የሀኪም ቤት ጓደኛየ ናት

የሲስተር ሀዋ እናትና አባቶቿ የHiv በሽተኛ ናቸዉ ሲስተር ሀዋንም ሲወልዱ በቂ ክትትል አላደረጉላትም ነበር ሲስተር ሀዋ የHiv በሽተኛ ሆነች።
ስለሆነች ሁሉም ዶክተሮች ይርቋታል


አንድን ታማሚ ካገለልነዉ ለኛ ጥሩ አስተሳሰብ አይኖረዉም በጥላቻ በክፋት ያየናል እንደዉም አላህን የማይፈራ ከሆነ እኛንም ለተጠቃበት በሽታ ሊዳርገን ይችላል ስለዚህ እንጠንቀቅ በተቻለን መጠን አንራቃቸዉ በመጠኑ እየተጠነቀቅን እንቅረባቸዉ።

.....እኔ ግን ሲስተር ሀዋ ታሳዝነኛለች ሁሌም አብሬት እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ አብሬት አዉላለሁ ፤እሷን ለማፅናናት የማላረገዉ ነገር የለኝም እንደዉም ሰዉ እሷን መቅረብ የጀመረ እኔ እዛ ሀኪም ቤት ገብቸ አብሬት ስበላ ስጠጣ ሲያዩ ነዉ
በዚህም ደስ ይላታል "በአንተ ሁሉን ነገር ረሳሁት እንደአዲስ የተፈጠርኩ መሰለኝ አማኔ ዉለታህን የምመልስ ያድርገኝ" ትለኝ ነበር እኔ ሞኙ አምናታለሁ እንደእህቴ እቀርባታለሁ፤ እረዳታለሁ ገንዘብ ከፈለገች ከፈለገችዉ በላይ በቸክ እፈርምላታለሁ ደሞዜንም በሆስፒታሉ ከሚሰሩት ከሁሉም የተሻለ ስለነበረ የሚቸግረኝ አንዳች ነገር የለም ይሄን እንተወዉና ስለሱመያ ልንገራቹህ" ሲል ንግግሩን ቀጠለ



"ሱመያን ጤንነቷን ቸክ ላረግ ስገባ ትጫሀለች ትንቀጠቀጣለች የምትገባበት ይጨንቃታል ወላሂ ከልቤ አዘንኩ ምን አይነት ሰዉ መሰል ሰይጣን ይሆን የተጫወተብሽ እላለሁ ሰዉ ስሜቱን የሚከተል ምን አይነት በግ ሁኗል አሁን ይችን ሚስኪን ጨክነዉ .....ስል አስባለሁ

የግድ ጤንነቷን መከታተል ነበረብኝ ስገባ ትጮሀለች ምን ላርግ ሳስብ ወንድ በመሆኖ ከሆነ የጠላችኝ መሆን እንጂ መምሰል ቀላል ነዉ።ለምን ሴት መስየ አልገባም አልኩና ፂሜን በትልቅ ማስክ ሸፍኘ፣ ከሱሪየ በላይ የሲስተር ሀዋን ሽቲ ደርቤ፣ እጀን ጓንት አልብሸ፤ ፀጉሬን በሂጃብ ሸፍኔ.... መግባት ጀመርኩ ሪሀና ወሬዉን አቋርጣ ተክ ብላ ሳቀች ለምን እንደሳቀች አማን ሲጠይቃት
"የምር ወንድሜ አማን ሳልኩህ ሴት ነዉ የምትመስለዉ" እኔ ታሪኩን ለማወቅ በጣም ጓጉቸ ስለነበር ከዛስ አልኩ አማንም "ከዛ ሱመያም አትፈራኝም ሴት ነዉ የምመስላት ደሞ ስልክ የላት ደዉየ ለቤተሰቦቿ የተፈጠረዉን አልናገር ቤተሰባቿም ሆኑ ጓደኛ የሚባል ይኑራት አይኑሯት የማቀዉ ነገር የለም ብቻ እየገባሁ ስለ ጤንነቷ አረጋግጨ ላወራት እፈልግና ድምፄ የወንድ እንደሆነ ካወቀች ትርቀኛለች አልና እወጣለሁ በዚህ ማሀል ስመላለስ ሳያት ምግቧን በስአቱ ስሰጣት እየተሻላት ማልቀሷን ትታ ፈገግ ማለት ጀመረች እንዳይደብራት ብየም ሲም የሌለዉ ስልክ አስቂኝ ቀልዶችና የተለያዩ ሀዲሶች የተጫኑበትን ሰጠኋት እሷም እየተሻላት ስትመጣ ሆስፒታሉ አልጋ ለሌላ ተረኛ እንድትለቅ አዘዘ የት ትሂድ ወዴት አዉጥተን እንጣላት ግራ ሲገባኝ ቤት ወንድሜ ብቻ ነዉ ያለ አብራን እስከሚሻላት ድረስ ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት........

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join👇👇👇

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 26
....... ሰሚራ ሽኩር


.....እስከሚሻላት አብራን ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት ብዙ አሰብኩ ምን አልባት እየተሻላት ስለሆነ ምንም አትለኝም ብየ እንደድሮዉ ሴት ሳልመስል ጋዉኔን ለብሸ ገባሁ "ዉጣ ዉጣ ዉጣ".... እያለች መንዘርዘር ጀመረች

....ሁኔታዋን ከዉጭ ሁና ስትከታተል የነበረችዋ ሲስተር ሀዋ ፈጠን ብላ መጣችና "ዶ.ር ሂድ እኔ አለሁ" አለችኝ ሱመያም አይ "ሽቲ የምትለብሰዋን ዶ.ር ጥሪልኝ እኔ ከሷ ዉጭ ማንንም አልፈልግም" አለች ሺቲ የምትለብሰዋ እኔን ማለቷ ነዉ


.....ሴት ለመምሰል ሽቲ የምለብስ እኔ መሆኔን ባወቅሽ እያልኩ አሰብኩ እሷም "ዶ.ር ዉጣ ዉጣ ሺቲ የምትለብሰዋን ስልክ የምትሰጠኝን ይዘሀት ና!" ትእዛዝ ነዉ መሰል
.....መጣለችኮ አልኳት "የት መቸ ሲስተር ሀዋን አላልኩህም ያች ሁሌም እየገባች ምግብ የምትሰጠኝን" አለች ካልመጣች ብላ ስትቀዉጠዉ ሲስተር ሀዋ እኔ እንደነበርኩ ለሷ ብየ ሴት እመስል እንደነበረ በደንብ አስረዳቻት እኔ አፍሬ አንገቴን ደፍቸ ከክላስ ወጣሁ።


ሱመያም ተከትላኝ መጣችህ "ስማ የምታድኑ እናንተ፤ የምታቆስሉ እናንተ፣ የምታስለቅሱ ፤የምታስቁ እናንተ፤የምትወስዱ የምትመልሱ፤የምትፈርዱ የምትሽሩ የምትጥሉ የምታነሱ እናንተ... በቃ ሁሉም ነገር በእጃቹህ ነዉ ስትፈልጉ የፈለጋቹሀትን ሴት ትጫወቱባታላቹህ ሲበቃቹህ እንደሸንኮራ መጣቹህ ትወረዉሯታላቹህ!!!
....ቆይ እኛ ሴቶች ምን አረግናቹህ ምን ብንበድላቹህ ነዉ የስቃይን ጥግ የምታሳዩን እእእ መልስልኛ ..."

ምን ልመልስ አንገቴን አቀረቀርኩ አሳዘነችኝ ሱመያ ተረጋጊ ብየ አረጋገኋት።
ሱሜ ስሚኝ በርግጥ ወንዶች ብዙ በደል አድርሰዉብሽ ሊሆን ይችላል አቃለሁ ነገር ግን እነሱ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ እኔ ደግሞ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ ነኝ።
ከዚህ በፊት በገጠመሽን እያስታወሽ ሀሉንም ሰዉ በአንድ አትፈርጂ!
..... ስስተር ሀዋ ነግራሻለች እንዴት አድርጌ ስለጤናሽ ስከታተል እንደነበረ አይዞሽ የደረሰብሽ አደጋ ባንች ብቻ የደረሰ አይደለም አንች ከገባሽ ቡኋላ እንኳን ካንች የሚያንሱ በአባታቸዉ፤በአጎት በወንድም፤በቅርብ ዘመድ.... ስንት ህፃን ሴቶች ተደፍረዉ ገብተዋል አንች ቢያንስ በማታቂዉ ሰዉ ነዉ የተደፈርሽ አስበሽዋል ስሜቱን በቅርብ ዘመድ ብትደፈሪ እና አልሀምዱሊላህ አትይም ብየ ካረጋግኋት ቡኋላ የተደፈሩትን በተኙበት ክፍል እየሄድኩ አሳየኋት ትንሽ ከተረጋጋች ቡኋላ ይቅርታ ጠይቃ አመሰገነችኝና ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ እህ ሳንተዋወቅ አልኳት ስሟን ቦርሳዋጋ የነበረዉ አንዱ ደብተሯ ላይ አንብቤዉ እንጂ ስለሷ አላቅም


....."ሱመያ እባላለሁ የሁለተኛ አመት የ garment enginering ተማሪ ነኝ ብላ ራሷን አስተዋወቀችኝ እኔም አማን እንደምባል ከነገርኳት በኋላ አሁንም ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ ወዴት ልትሄጂ ነዉ ስል ጠየቋት "ከሆስፒታል እንድወጣ ትዛዝ ተሰጦኛል ወዴት እንደምሄድ አላቅም እናትና አባት የለኝም ያሳደገኝ አጎቴ ነዉ መደፈሬን ካወቀ አያስገባኝም ይገለኛል የት እንደምሄድ አላቅም እግሬ ወደሚመራኝ መንገድ እጓዛለሁ ደህና ሁን" ብላ መራመድ ስትጀምር ምን እንደነካኝ አላቅም ከኔ እንድትለይ ፍቃደኛ አልነበርኩም በቃ ሳያት ወደድኳት መሰል እኔጃ ብቻ በደንብ እስከሚሻልሽ የኔ ቤት ክፍት ነዉ መኖር ትችያለች አልኳት"

የአማንን ታሪክ እየሰማሁ ከየት መጣ ሳልለዉ እንባየ እንደጎርፍ በሁለት ጉንጮቸ ይፈስ ጀመር ምን ሁኘ ይሆን አላቅም ምን አልባት ለአማን የነበረኝ ስሜት የወንድም አልነበረም ይሆናል የልቤን ጩኸት ዋጥ አድርጌ አማን እንዳያቅብኝ ቶሎ ቶሎ እንባየን እየጠረኩ ሲያሻኝም ባልወድ በጥርሴ ፈገግታ እየተደበኩ ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ



አማኔም በትዝታ ባህር ርቆ ተጉዞ ስለነበር ለኔ እንባ ትኩረት አልሰጠዉም ሚስኪን ሪሁየ እህቴ በአማን ንግግር ደንግጣ አይን አይኔን ትመለከት ጀመር እኔም የማለቅስ በሱመያ ታሪክ አዝኘ እንደሆነ ለማስመሰል በየመሀሉ አፌን መምጠጥ ጀመርኩ ኧረ ኢላሂ! ደስታየን አጣጥሜ ሳላበቃ በሀዘን ልቤ ተሰበረ ምን አለ ታሪኩን ባላቅ ብየ ተመኘሁ አይ ዱንያ አምርሬ ረገምኳት ጩሄ አይወጣልኝ ነገር የታፈነ ጩኸት ሆነብኝ ኧረ ምን ተሻለኝ ብቻ መጨረሻዉ እንዳሰብኩት እንዳይሆን ተመኘሁና ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ አማኔም ንግግሩን ቀጠለ ...."እሷም ካቅማማች ቡኋላ ብቻህን ነዉ የምትኖር ወይስ አለችኝ
አይ አብሽሪ ከወንድሜ ጋር ነዉ የምኖር ብያት እሷም ተስማምታ ወደ ቤቴ ልንሄድ ስንወጣ ሲስተር ሀዋ በክፋት አይኖ መመልከት ጀመረች አስተያየቷ አላማረኝም ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናንተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችኝ እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር እንደሆነ ስናግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት እሷም "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!"....ሱመያ አላስጨረሰቻትም

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot
......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 27

......... ሰሚራ ሽኩር


.....ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችን እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር አንደሆነ ስነግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!".....ሱመያ አላስጨረሰቻትም ከዶ.ር አማን ጋር ነዉ የምሄድ አለች አልሀምዱሊላህ ከሷ ጋር ብትል እኔጃ ሱመያ ከኔ እንድትለይ ለምን እንደማልፈልግ አላቅም የሲስተር ሀዋም ሱመያን በክፋት እይኖ አየቻት።
.... እኔ በጣም ግራ ገብቶኛል ሱመያ ከኔ ጋር ወደቤት እሄዳለሁ ካለች ጀምሮ ባህሪዋ ተቀይሮብኛል

.....ሱመያን እኔ ቤት ወስጃት ቤቴን በደንብ አሳየኋት ወንድሜ ሙሀመድንም አስተዋወቋት እሷም በደስታ ተዋዉቃ ከኛ ጋር መኖር ጀመረች ያ ፍዝዝዝ ብሎ የነበረ ቤት አሁን የወጉ ደርሶት ቡና ይፈላበት፤ ምግብ ይዘጋጂበት ...ጀመረ እኔም ሱመያን በጊዜ ሂደት እየወደድኳት ለሷ ያለኝ ስሜት/ፍቅር እየጨመረ መጣ እሷም በተመሳሳይ
.... "ከወደድከኝ ኒካህ አስረህ አግባኝ ካልሆነ ጫፌን እንዳትነካ ወጥቸ እሄዳለሁ" እያለች መቀለድ ጀመረች
እንዳለችዉም አጎቷን አስፈቅጀ ኒካህ አስረን ደስ የሚል የሚያስቀና ሂወት መኖር ጀመርን"

ምንድን ነዉ የምታወራዉ! ስል ሳላስበዉ ጫሁኩ ወይኔ ጉዴ ምን እንደነካኝ አላቅም አማኔንና ሪሀናን አስደነገጥኳቸዉ ከገቡበት የትዝታ ባህር አወጣኋቸዉ ግን ወላሂ አዉቄኮ አይደለም ምን እንደነካኝ አላቅም እንባየን ደጋግሜ ብጠርገዉም መልሶ ይፈሳል ልቤ በፍጥነት ይመታል ሰዉነቴ ይንዘረዘራል ለመናገር አፌ ይየያዛል ኢላሂ ምን ነካኝ አሁንስ የኔ ተራ ነዉ መሰል ማበዴ ነዉ ለራሴ ፈራሁ እራሴን እንደምንም አረጋግቸ ለምን እንደጮሁኩ ሲጠይቁኝ በማግባቱ ደስ ብሎኝ እንደሆነ ነገርኳቸዉ የልቤን አላህ እንጂ ማን ያቃል በቃ ለኸይሩ ነዉ ደሞስ ወንድምነቱ አይበልጥብኝም እንዴ አይ ሀናን ከራሴ ጋር ንግግር ጀመርን በመጨረሻም ራሴን አረጋገሁ በቃ አማን ሱመያን አ*ፍ*ቅ*ሮ......አግብቶታል አለቀ!!! ለኔ አማኔ ወንድሜ እንጂ ሌላ አይደለም

ከአማን ታሪክ እንመለስና ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ይሆን? ምንጩና መኖሪያዉስ የት ነዉ .....

እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ልብ ነው። ጎጆውን የቀለሰው ከውስጥ ነው። ውሎና አዳሩ እዚያው
ነው። ህያው ሆኖ የሚንቀሳቀሰው በልብ አዳራሽ ውስጥ ነው። በተቀራኒው ቅብ የሆነ ፍቅር
መገኛው ከልብ ውጭ ባሉት የሰውነት ክፍሎች ነው። ለዚህም ነው እውነተኛ ፍቅር ዝንተ
ዓለም ሲቆይ ሁለተኛው በበኩሉ የሰውነት መጥፋትን ተከትሎ አብሮ የሚከስመው። ነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) «(አላህ) የኸዲጃን ፍቅር ችሮኛል» ብለው ሲናገሩ ለርሷ የነበራቸው
ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት እንደነበረው ይጠቁማል። የፍቅር ክብደት ምን ያህል እንደሆነም
ያሳያል።
.
.
እውነተኛ ፍቅር ቃል ኪዳን ነው!!!ሀሰተኛ ፍቅር ማስመሰል ነው!በነብዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ዘመን አንዲት አሮጊት ነበረች። ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ለመጠየቅ በመጣች
ቁጥር ከተቀመጡበት ተነስተው በአክብሮትና በፍቅር የመቀበል ልምድ ነበራቸው። በነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስደናቂ ባህሪ የተገረመችው እናታችን ዓኢሻ «ለዚህች አሮጊት
ለምንድን ነው የምትቆመው?» ብላ ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀቻቸው። «በኸዲጃ
ዘመን ትጠይቀን ነበር» ብለው መለሱላት።
.
.
በማስመሰል የታጀበ ፍቅር ፋና አልባ ነው። የሚያልፍ ጊዜ እንጂ የሚታወስ አሻራ የለውም።
ከአንጀት የሚነበብ ትዝታ ስሌሌለው የታሪክ ገፆቹ በሙሉ ወና ናቸው። የማስመሰል ፍቅር
በተፋቃሪዎች ምላሥ ላይ ማርን በአደራ እንደማስቀመጥ ነው። እውነተኛ ፍቅር ግን
በአይምሮ ላይ ተነቅሶ የሚቀር ትዝታ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ወርቃማውን የኸዲጃ ዘመን ለአፍታ እንኳ ያልዘነጉት። ትዝታው በልባቸው በጥልቀት ተምሶ
ተቀብሯል። ከህሊናቸው ማህደር በክብር ሰፍሯል። የኸዲጃ ዘመን አይረሴ ሆኗል። ለርሷ
የነበራቸው ፍቅር ማራኪ ነበር !
.
.
እውነተኛ ፍቅር ህይወትን በጥበብ የምናጣጥምበት ቅመም ነው። ታላቁ ነብይ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር በነገሰበት የዓኢሻ እቅፍ ውስጥ ቁርኣን ይቀሩ ነበር። በአንድ ማዕድ
አብረው ይመገባሉ። በተከበረው እጃቸው ያጎርሷታል። ውኃ በጠጣችበት እቃ ይጠጣሉ።
ሆነ ብለው አፏ የነካበትን ቦታ ለይተው በመምረጥ በርሱ ይጎነጫሉ። ፆመኛ ሆነው
ይስሟታል። ከዚያም ወደ መስጂድ ይገባሉ። በአንድ መታጠቢያ ዕቃ ላይ ሆነው በጋራ
ሰውነታቸውን ይታጠባሉ። ምንኛ ያማረ ፍቅር ነው! ምንኛ አስደማሚ ትስስር ነው!!! ድንቅ
በሆነው የህይወታቸው ምዕራፍ ውስጥ ፍቁድ የሆነውን ተፈጥሯዊ ስሜታቸውን ማስተናገድ
በሚችሉበት ሁናቴ እያሉ ራሳቸውን ገዝተው የዓኢሻ ዕቅፍ ውስጥ ሆነው በቅዱስ
አንደበታቸው የፈጣሪያቸውን ቃል ( ቁርአን) ይቀሩ ነበር።
.
.
እውነተኛ ፍቅር መንፈስ እና አካል የተጋመዱበት ሚስጢር ነው። የስጋ አስፈልጎትና
የመንፈስ ቀለብ የሚጣመሩበት የተለየ የግንኙነት ነጥብ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
«በዱንያ ውስጥ ካሉ (ፀጋዎች) እኔ ዘንድ ሴት እና ሽቶ የተወደዱ ናቸው። ሶላት ደግሞ
የዓይን መርጊያየ (የደስታ ምንጭ) ተደርጎልኛል» ብለዋል።
.
.
ፍቅር የሌለው ህይወት ውበት አልባ ነው። በህይወት ውስጥ የመኖር ስሜት ከነጠፈ ፍቅር
በህይወት ውስጥ መኖር አይችልም። በውበት የታጀበ ምቹ የህይወት ድባብ በሌለበት
ተጨባጭ ህያው የሆነ ስሜት መፋፋት አይችልም። እንግዲህ ይህ ሁሉ «ጥበብ»
ይጠይቃል። ጥበብ በፍቅር ውስጥ ጥንዶችን የሚያገናኝ አምባሳደር ነው። ሁለት የህይወት
አጋሮችን የሚያስተሳስር ታማኝ ልዑክ ነው። ጫፍ እና ጫፍ የነበሩ አካላትን የሚያገናኝ
ድልድይ ነው


ግን የአማን ታሪክ ትንሽ ቢያስከፋኝም ቢሰሙት የማይሰለች ጣፋጭ ታሪክ ነዉ እኔጃ ብቻ የሱን ታሪክ ስስማ ሁሉ ነገሩ ያስገርመኛል
ታሪኩ ደስ ብሎኛል የታሪኩ መጨረሻ እንደሚያምር ተስፋ እያደረኩ ወደ ታሪኩ ልመልሳቹህ አማን ቀጠለ
......"ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች ታምነኛለች አምናታለሁ ሁሌም በምንም ታአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot
.
.
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣8⃣

....... ሰሚራ ሽኩር


.... ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች አምናታለሁ ታምነኛለች ሁሌም በምንም ተአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል
....ከህመሟ ልታደጋት ብጠጋት በፍቅሯ ሳበችኝ የአላህ ነገር ይገርመኛል ሂወቴን ፤ህልሜን አጠለሹት ብላ ስታማርር አላህ ሰበብ አድርጎ አገናኘን በርግጥም የኛ ጌታ የተሻለ ነገር ሊሰጠን እንጂ እኛን በምንም ነገር አይጎዳንም !
.....ከሱሚ ጋር ከተጋባን በሁለተኛ አመታችን እኔ የሴት ልጂ አባት ሱሚ የሴት ልጂ እናት ለመሆን በቃን ቤታችን ይበልጥ ሞቀ በደስታ ደመቀ ሴት ልጂ በመሆኖ በጣም ደስ አለኝ የናቴ ምትክ !

.....አሁን እየጨነቀኝ የመጣ የሲስተር ሀዋ ነገር ነዉ ምኗንም ማወቅ አልቻልኩም በቃ ስታየኝ እንደደመኛዋ ነዉ
ሱሚን ለማየት እንኳን ፍቃደኛ አይደለችም ለምን?አላቅም
ያች የማቃት የዋህ ለሰዉ አዛኟ ሲስተር ሀዋ አልመስልህ አለችኝ

በዚህ መሀል ግራ ገብቶኝ ሱሚ በወለደች በሁለት አመቷ ሲስተር ሀዋ ከድሮዉ ይበልጥ ትቀርበኝ ጀመር አይዞህ ሚስትህ ስለወለደች ብቻዋን እንዳትሆን ሂድላት ያንተን ተራ እኔ እሸፍንልሀለሁ" ትለኝ ጀመር እኔም የዋህነቷ እየገረመኝ ይበልጥ እየቀረብኳት ሄድኩ ከለታት በአንዱ ቀን የኛ ሆስፒታል ሌላ ሀገር ቁጥር ሁለት ሆስፒታል አስገንብቶ ለሁላችንም ጥሪ ተገደረልን እኔ ደግሞ የሆስፒታሉ ዋና አስተባባሪ ስለነበርኩ መቅረት አልችልም ለመሄድ ወስኘ በማግስቱ እንደምመጣ ለሱሚ ቃል ገብቸላት እሷም በስስት አይኖቿ እየተመለከተች ስማ ሸኘችኝ እኔ ከሲስተር ሀዋና ከሌሎች ጓደኞቸ ጋር ስንጓዝ ዉለን ቀን ወደ ሰባት ሰአት አካባቢ ድክም ብሎን አዲሱ ሆስፒታል ደርሰን ወደ ዉስጥ ገባን ሻዉር ወስደን አዲሱን ሆስፒታል ስንጎበኝ ቆይተን በስብሰባዉ ታድመን ፕሮግራሙ ስናከብር ካመሸን ቡሀላ የራት ግቤዣ ነበረን ብዙ መጠጦችና ብዙ ምግቦች በየአይነት ቀርበዋል ሲስተር ሀዋ ከሁል ጊዜዉ በተለየ ዘንጣ ተዉባ የራት ግቢዣዉ ላይ መጣችና አጠገቤ ተቀመጠች ከዛ መጣሁ ብየ ሱሚ ላይ ደዉየ ራት እንደበላች ካረጋገጥኩ ቡኋላ እኔም ልበላ ወደ ተዘጋጀዉ ማአድ አቀናሁ ሲስተር ሀዋ ምግቡንም መጠጡንም ከምን ጊዜዉ በሰሀኔ አድርጋ እንደጠበቀችኝ አላቅም እኔ የተቀመጥኩበት የነበረዉ ወንበር ላይ ተቀምጧል ከዛ ብላ እያለች ሰሀኑን ወደ ጠረፒዛየ አስጠጋችልኝ መጠጡንም/የተከፈተ እስፕራይት ጠጣ አያለች ሰጠችኝ እኔም ስበላ ስጠጣ ስስቅ ስጫወት አምሽቸ ነበር"

እማየ እኛ ወደተቀመጥንበት ክፍል መጣችና" በፈገግታ ሀናኔ እስካሁን ወሬቹህን ናፍቆታቹህን አልተወጣቹህም እንዴ?" አማኔን በአይኑ እንባዎች ሞልተዋል የሆነ የሚያሳዝን ነገር እየነገረን መሆኑ ገብቷት ነዉ መሰል "ዊይ በሉ ተጫወቱ ቤቱን ታፀጂዋለሽ ብየ ነበር በቃ ተይዉ እኔ አፀደዋለሁ ባይሆን ዝም ብለሽ ከምትቀመጭ የአባትሽ ልብሷች በሻንጣ እንደሆኑ ናቸዉ ደሞ አልታጠፉም ቁምሳ ሳጥኑ ላይ አጣጥፈሽ ክተችለት የአማኔም አብሮ አለ የታጠበዉንና ያልታጠበዉን ለይዉ ከአ.አ እንደመጣ ማንም አላስተካከለዉም" አለችኝ እኔም አማ ችግር የለዉም ቤቱን ላፅዳና አጣጥፌ ቦታዉ እመልሳለሁ አሁን ግን ቆይ አልኩ የአማኔን ታሪክ ለመስማት በጓጓ አንደበቴ እማ እሽ መቸ ስትል ጠየቀችኝ ትንሽ ብቻ ጠብቂኝ "ሀናኔ አሁን ጓረቢቴቸ አማንን ሊያዩ ይመጣሉ በቃ አንች ልብሱን ከሻንጣዉ አዉጥተሽ አጣጥፊዉ ቤቱን እኔ አፀደዋለሁ አለችኝ ወይ እማ እኔ አፀደዋለሁ አ.አ ይዘዉት የሄዱትን ሻንጣ ከሳሎን ቤት ይዘዉ መጣችና ሰጠችኝ አማኔ አንች አጣጥፈሽ እስከምትጨርሽ እኔ ኡዱ ላድርግ ስመለስ ታሪኩን እጨርስላቹሀለሁ እያለ ወጣ አይኑ አብጧል ፊቱ ፍም መስሎል ለማየት ያስፈራል እኔም ግራ ገብቶኝ እሽ ቶሎ ተመለስ እንጠብቅሀለን ብየ ልብሱን ከሻንጣ እያወጣሁ አጣጥፌ ወደ ቁምሳጥኑ ማስገባት ጀመርኩ


......ከመሀል አንድ የተጠቀለለ ፌስታል ላይ አይኔ አረፈ አይ አባቢ ይሄን ደግሞ ምን ሊያደርግ ይሆን ሻንጣ ዉስጥ ያስገባዉ ደግሞስ ምንድን ነዉ ብየ ፌስታሉን ስከፍተዉ የአማኔ መድሀኒት ነዉ ኧረረ የአማኔ መድሀኒት ተቀይሮል በፊት ነጭ የሽሮብ የምትመስል እቃ ዉስጥ ነበር መድሀኒቱ ያለዉ አሁን የራሱ ማሸጊያ እንደማንኛዉም አይነት መድሀኒት ነዉ እስኪ ብየ መድሀኒቱን ከጀርባዉ ከግልባቡ ሳነበዉ ግማሹ የአእምሮ ግማሹ የHiv ነዉ የሚለዉ መቸም የህክምና ተማሪ መድሀኒት ሲያይ መድሀኒቱን ለማወቅ እጁን ይበለዋል ከዛ ግራ ገባኝ አባቢ ተሰስተዉ ሰጠዉት ይሆናል ብየ መድሀኒቱን ይዤ ወደ አባቢ እሮጥኩ ሂጀ ነገርኩት አባቢ በኔ ማስተዋል ይደሰታል ብየ ስጠብቅ ያላሰብኩትን ለመዋጥ የሚከብድ ለማመን የሚያስደነግጥ መራራ እዉነት ነገረኝ እንደ
እንጨት ደርቄ ቀረሁ ማመን አቃተኝ ለካ ሰዉነቱን የሚያጥበዉ መድሀኒቱን የሚሰጠዉ አባቢ ብቸዉን ነበር እማን መድሀኒቱን ለአማን ስጭዉ የሚላት በጣም ስራ ሲበዛበት ከሀቅሙ በላይ ሲሆን ብቻ ነበር ግን ደግሞ አባቢ ሁሌም ስልነገሮችን ከአማን አጠገብ አንሱ ይለን ነበር ደጋግሞ እና አማን.....ቆይ እሽ አባቢ እስከዛሬ የደበቀን ለምን አማኔን እንዳንርቀዉ የአማኔን ሞራል ለመጠበቅ ወይስ ለምን ለነገሩ እስከዛሬ በነገረኝ እኔም በሱ ፍቅር ባልተሰቃየሁ ነበር ተወሳሰበብኝ ከመሀል አባቢ መድሀኒቱን ከጀ ወሰደና መድሀኒቱን እየፈታ በሽሮብ እቃ ማድረግ ሲጀምር ለምን ብየ ጠየቁት አሀ ለምን አደርገዋለሁ እናታቹህ እንደሆነች ታቃለች ነግሬታለሁ ለናንተም ያልነገርኳቹህ አማኔን እንዳትርቁት በእብደቱ ላይ ሞራል የሚነካ ንግግር እየተናገራቹህ አእምሮዉን እንዳትጎዱት.....ብቻ በብዙ ምክንያት ደብቄቹሀለሁ አሁን ግን በቃ አማኔም ተሽሎታል እወቁ አለኝ የምሰማዉን አላምን አልኩኝ ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ ከመሀል ሪሀና መጣችና ሀናኔ ነይ አማኔ ታሪኩን ሊቀጥልልን ነዉ ብላ ጎትታ ወሰደችኝ የምን ታሪክ አልኳት በጣም ደንግጫለሁ አካሌ እዚህ ይሁን እንጂ ነፍሴ ከአካሌ ተለይቶ ተጉዟል ሪሁም የአማኔ ነዋ ስትለኝ አሀ እሽ ብየ ባልሰማም ብሰማም እየተርበተበትኩ ተቀምጨ ማዳመጥ ጀመርኩ


..... አማኔ ታሪኩን ካቋረጠበት " ምግቡን ሲስተር ሀዋ ሰጣህ በልተህ ጠጥተህ ከዛስ" ሪሀና ጠየቀች አማኔም "የማስታዉሰዉ ነገር የለም ጥዋት ስነሳ ራቁቴን ከሲስተር ሀዋ ጋር አንድ አልጋ ራሴን አገኘሁት የማየዉን አላምን አልኩኝ በህልሜ ይሁን በእዉኔ ብቻ አላቅም መጫህ ጀመርኩ ሲስተር ሀዋም "አቦ አትጩህብኝ ልተኛበት ምን ታካብዳለህ አለችኝ" ኧረ ማበዴ ነዉ ምን ላርግ ራሴን ጠላሁት የዛኔ ምድር ተዉጣ ብትዉጠኛ እንደኔ የታደለ ባልኖረ ነበር


ትዝ ሲለኝ ሲስተር ሀዋ የ Hiv በሽተኛ ናት ከዚህ ቡኋላ ምን ልሁን አላቅም ወዴት ልሂድ አላስታዉስም ብቻ ሱሚን ሳስታዉስ ታዛዝነኛለች ላንለያይ ምለን ነበር ምን ዋጋ አለዉ ያች የሰዉ አዉሬ ተጫወተችብኝ!......"

አማኔ ማልቀስ ጀመረ እኔም እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም "በዚህ ጊዜ ሱሚ አግባታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ" ያረብ አያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ......

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join👇👇👇

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣9⃣

..... ሰሚራ ሽኩር

...አማኔ ማልቀስ ጀመረ በዚህ ጊዜ ሱሚ አግብታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል።
ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ ያረብ እያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ...

....... ለማመን የሚከብድ መራራ እዉነት ሆነብኝ ታሪኩ ከልቤ አዘንኩ አሁን ይሄ ሚስኪን ምን አደረገኝ ብላ ነዉ አጠጥታ እንዲያብድና የ Hiv በሽተኛ እንዲሆን ያደረገችዉ እንደዛ ሰዉ ሁሉ ሲርቃት አማኔ ስለቀረባት ወይስ ስላገባና ስለወለደ ቅናት...ነዉ እንዲህ እንድትጨክን ያደረጋት ብታቀዉ ነሮስ አማኔ ለሷ ከወንድም ከሁሉም በላይ ነበር ምን አይነት ጭንቅላት ቢኖራት ነዉ ይሄን ያሳሰባት ያረብ አሁንም የስራወን እንዳታጠዉ አምርሬ ረገምኳት በዚህ ስሜቴ አጠገቤ ብትሆን ብየ አሰብኩ የምገላት መሰለኝ

...እና የአማኔ ማበድ ስበቦ እሷ ነበረች ማለት ነዉ እሷን ብሎ ዶክተር ገደል በገባች ምናለ በሂወቴ አንዴ አግኝቻት በሰደብኳት...ከራሴ ጋር አወራ ጀመር

አማኔ ግን መጨረሻዉ ምን ይሆን ቤተሰብን አይፈልጋቸዉም እንደዉም በሂወት እንደሌለ ሰዉ በፍቅራቸዉ መጎዳትን ይመርጣል እነሱ እሱን ካዩ ቡሀላ የሚጎዱ ይመስለዋል ብቻ ዉስብስብ ነዉ በዛ ላይ አማኔ የHiv....በሽተኛ ነዉ አሁን አላህ ብሎትስ ቢገናኙ ብየ አሰብኩ አይ ባይገናኙ ይሻላል ከተገናኙ ሁለቱም ይጎዳሉ አልኩ።
... ግን ምኑ ይታወቃል የሚፈጠረዉ ነገር አይታወቅም!
ቢያንስ የአማኔን ልጂና ሚስቱን እኔ ባቃቸዉና ለአማኔ ልጁን ባሳየሁትና በተደሰተ ስል አሰብኩ ግን እንዴት ከአማኔ አድራሻቸዉን ልቀበል ብዙ መፍትሄዎችን አሰብኩ ነገር ግን ምንም መፍትሄ አላገኘሁም ምን ዝም ብየ ብጠይቀዉ አልናገርም ሊለኝ ነዉ እንኳን ያሉበትን ሀገር ታሪኩንስ ነገረኝ አይደል ስል አሰብኩ.....


አማኔ ግን በፊት የት ሆስፒታል ነበር የምትሰራ ልጂህና ሚስትህስ የት ነቸዉ ያሉት ስል ጠየቁት አማኔም ቆጫ ብሎ "ምን ያድርግልሻል እኔ በሂወት እንዳለሁ አንድም ሰዉ እንዲያቅ አልፈልግም በቃ ተይኝ ሳልፈልግ ታሪኬን ነግሬሻለሁ ከዚህ በላይ ግን አልችልም በቃ አልችልም"
... እያለቀሰ በእዝነትና በልቅሶ ብዛት በደከሙ አይኖቹ አስተዛዝኖ ነገረኝ
እኔም ኧረ አማኔ አብሽር እኔም እንድትገናኙና አንድ ላይ ላትሆኑ ተያይታቹህ እንድትጎዱ አልፈልግም! ደሞኮ አማኔ እስከዛሬ ሱሚም አግብታ ወልዳ ይሆናል እንደዉ ልጂህን ማግኘት ብችልና ይዠልህ ብመጣ....ብየ ነበር በቃ ተወዉ ብየ አዝኘ ተነሳሁ


.....አማኔም በልጁ ናፍቆት ስለተጎዳ ሂጀ ይዠለት የምመጣ መሰለዉ አቅማማና "እንግዲያዉስ ማግኘት ከቻልሽ በአካል ማምጣት ሞክሪ ግን ሱሚ ልጆን ስጣጠዉ እንዳትጎዳብኝ ደሞ አንድም ነገር ስለኔ ሳትተነፍሽ በሆነ ነገር አታለሽ/ምክንያት ፈጥረሽ ለአንድ ቀን ብቻ የልጀን አይን ልየዉ በአካል ካልቻልሽ ደግሞ ፎቶቸዉን ልለምንሽ ምን ያህል እንደናፈቁኝ ብታቂ"....

አንተ ብቻ ያሉበትን ቤታቹህን ንገረኝ ብየ አድራሻ ተቀበልኩት አባቢን በሶስት ቀናት ዉስጥ እንደምመለስ ነግሬዉ ፈቅዶልኝ እማየ መርቃ ሁሉም በደስታ ሸኙኝ

....ሱሚንና ልጇን ላግኛቸዉ አላግኛቸዉ የማቀዉ ነገር የለም በዛ ላይ ሱሚ አግብታ ይሆን ....ጨነቀኝ እሽ ባገኛቸዉስ ምናቹህ ነኝ እላቸዋለሁ ምን ብየስ የአማንን ልጁን ይዠለት እሄዳለሁ ተወሳሰበብኝ ያረብ!አንተዉ አቅልልልኝ ብየ ዱአየን አደረኩ።

....ያለኝ ሀገር ያለኝ ቦታና ቤት በነገረኝ መሰረት ሄድኩኝ ቤቱ ተደራራቢ ሶስት ፎቅ ነዉ አይ ቤቱን ተሳሳትኩ መሰል ብየ ተመለስኩ በድጋሚ የሰጠኝን አድራሻ ሳይ አልተሳሳትኩም ቤቱ የራሱ ነዉ ተገረምኩ አማኔ በጣም ሀብታም ነበር ማለት ነዉ ስል አሰብኩ

....ቁሜ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በሩ ላይ የተገጠመዉን ደዉል ነካሁት ወድያዉ ቆንጂየ ልጂ በሩን ከፈተችልኝ ሱሚ ያላት መሆኖን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እንዳላትም አፍንጫዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች የምታምር እንስት ናት ግን ቀይ አይደለችም ትንሽ ጠቆር ያለች ነበረች...ምናልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ "ማን ነሽ ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽዉ!" ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ....

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 3⃣0⃣

........... ሰሚራ ሽኩር

......ምን አልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ ማን ነሽ?ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽ ? ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ ግራ ገባኝ
.....እእእእእ ያማን ያማን ምንልበል በቃ ያማን ዘመድ ነኝ ብየ ብገላገልስ አልኩና እዉነት ለመናገር ልክ እንደህቴ እንደሪሁየ የለለ አስመሳይ ነኝ እንድታምነኝ የአማን ዘመድ ነኝ
ዉይ አታቂኝም እንዴ የአክስቱ ልጂ ነኝ አማኔ ካየኝ ያቀኛል አማኔን ጥሪልኝ እሱን ለአንድ ጉዳይ ፈልጌዉ ነዉ አልኳት

.... ልብ አለማለቷ ነዉ እንጂ ዉሸቴን እንደሆነ ትንሽ ይለይ ነበር ያዉ መንተባተብ ፊቴን ማላብ እየዋሸሁ መሆኑን ያስታዉቃል።
እሷም "አማኔ አማኔ...." ምን ትበለኝ አይ የታመመዉን ማገገም የተሳነዉን ቁስሏን ነከሁኝ መሰል ከአይኖቿ እንባ እየወረዱ እዝን ብላ "ለመሆኑ አንች ማን ነሽ" ስትል ጠየቀችኝ ስሜ ሀናን ይባላል አልኩና ዘመድ መሆኔን እንድታምን አማን ስለዘመዶቹ የነገረኝን ታሪክ አጣፍጨ ነገርኳት እሷም እዉነት ዘመድ ብትሆንነዉጂ ይሄን ሁሉ ታሪክ ከየት ታቃለች እያለች የምታስብ ትመስላለች ዘመድ መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ነይ ግቢ ወደቤት ብላ ካስገባችኝ ቡኋላ ምግብ አቀረበችልኝ አይ ሱሚ በልተሽ መሞቱን ብታቂ ይሻላል በበዶ ሄድሽ ሀዘኑን አትችይዉም ብላ ይሆን ስል አሰብኩ መቸም በሂወት እንዳለ አታቅም ማን ይነግራታል! አይ እዱንያ ፈተናሽ መብዛቱ ኑሮሽ መምረሩ አታላይ የዉሸት ኑሮ ደስታሽ ትንሽ ሀዘንሽ ብዙ ዉስብስብ መራራ ኢጭ!!!


....ለማንኛዉም የመጠሁበት አላማ ሊሳካ ነዉ መሰል አላቅም ወደ ሱሚ ጠጋ አልኩና አማኔ አይመጣም እንዴ እስኪ ደዉይለት እኔ ለመሄድ እቸኩላለሁ ጉዳይ አለብኝ አልኳት ሱሚም "እእእእእእ እማኔ አማኔ.." እንባዋ እንደጎርፍ መዉረድ ጀመረ ምን ብላ ትንገረኝ ሆስፒታል ሊያስመርቅ እንደወጣ አልመጣም ወይስ ሞተ ብላ ግራ በተጋባ በናፍቆት በተቆራረጠ ድምፅ "ሀናን አማኔ ሀናን አማኔ በሂወት የለም! ከዚህ የተሻለ ቦታ ሂዷል በቃ ሙቷል አማን ሞተ አማን ጥሎን ሄደ" ....እሪ ብላ ማልቀስ ጀመረች

....ወይኔ ጉዴ ምን ልበል እኔዉ እንድትነግረኝ ጠይቄ እኔዉ ደነገጥኩ ሙቷል ብላ ነዉ ያሰበች ለነገሩ እንደዚህ እየተዋወዱ በሂወት ቢኖር ጨክኖ ሳያየኝ ከኔ እርቆ መኖር አይችልም ብላ ስለምታስብ ነዉ ሙቷል የምትል
እይ መኖሩን ባወቅሽ ስል በዝነት አየኋት በፍቅር እንደተጎዳች ማንም አይቶ ይመሰክራል።

እኔም ወደድኩት እላለሁ አይ ሀናኔ ሱመያን ሳያት ፍቅር ምን አንደሆነ ገባኝ ጠቁራለች በሱ አሳብ በአማኔ ናፍቆት ይሆናል ሚስኪን እያልኩ ሳስብ በአንዴ ፊቴ ተቀያየረ በጣም ተናደድኩ ደነገጥኩ ግራ ገባኝ

.......አንድ በግምት ስድስት አመት የሚሆናት የምታምር ህፃን "ኡሚ ኡሚየ" እያለች የተቀመጥንበት ክፍል መጣች አማኔን ነዉ የምትመስል ሱሚም እንባዎቿን ጠራርጋ "መጣሽልኝ ሀያቴ" አለችና መጣሁ ብላ ወደ ዉስጥ ገባች ትንሽ ቆይታ "አይዞሽ ተጫወች ሙሀመድ ላይ ደዉየለታለሁ አሁን ይመጣል" ..... ለወሬዋ ቦታ አልሰጠሁትም ያችን ህፃን እየተመለከትኩ የአማኔ ልጂ ናት ወይስ ብየ አሰብኩ አወ የአማኔ ልጂ ናት እሱን ነዉ የምትመስል አልሀምዱሊላህ

አይ አሁን የአማኔ ወንድም ከመጣ ጉዴ ፈላ በቃ ዘመዳችን አይደለችም ይል ይሆን ቢል በማስመሰል ተክኛለሁ ማሳመን አይከብደኝም ስል ራሴን አረጋጋሁ ከቆይታ ቡሀላ አንድ የአራት አመት ልጂ እየወደቀ እየተነሳ እኛ ወዳለንበት ሳሎን ቤት መጣ አሚሬ ተነሳህ የኔ ልጂ አለችና አቅፋ ምግብ መስጠት ጀመረች

....ያረቢ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ ቆይ አግብታ ነዉ ስል አሰብኩ ለነገሩ አራት አመት ሙሉ ሳታገባ እሱን መጠበቅ ከባድ ነዉ እንኳን አገባች አማን በሂወት እንዳለ ብነግራት ትዳሯን ማበላሸት ነዉ ለነገሩ አማን በሂወት እንዳለ ብታቅ የHiv በሽተኛ ስለሆና የመገናኘት እድላቸዉ 0% ነዉ........ ብዙ አሰብኩ

.... እንዲሁ ሳስብ የቤት መኪና ይዞ የአማን ወንድም ሙሀመድ መጣና ተተዋወቅን ነጋዴ ነዉ አማን እንዳለዉም ሙሀመድ ትንሽ ጠቆር ማለቱ ነዉ ከአማን የሚለየዉ እንጂ መንታ ነዉ የሚመስሉት።
.....ዘመዳቸዉ እንደሆንኩ ሱመያ ነገረችዉ
ዘመዳችን አይደለችም ይላል ብየ በፍራት አይን አይኑን ሳይ "እይ የኔ ነገር ሁሌም ስራ ስለምዉሉ ዘመድ ይኑረን አይኑረን የማቀዉ ነገር የለም በይ ተንግዲህ እንደዋወላለን አትጥፊ" ብሎ ስልኩን ሰጠኝ ።

.... አልሀምዱሊላህ በጣም ጨንቆኝ ነበር
በቃ ልሂድ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ ብየ ተነሳሁ ምን አደርጋለሁ የሱመያን ባለቤት ለማወቅ ለማየት ጓጉቸ ነበር ብጠብቅ ብጠብቅ አልመጣም ጊዜዉም እየመሸ መጣ ልሂድ ብየ ተነሳሁ አይቻልም አሉኝ ለነገሩ እኔም የአማኔን ልጂ ሳልይዝ ከዚህ ቤት አልወጣም እንደዉ ላስመስል ብየ እንጂ

ግን እሽ ብለዉ ቢሸኙኝ ወዴት አድር ነበር ቢሸኙኝ አባቢ ወንድም ቤት አድር ነበር ሁሉንም አቅጀ አስቤበት ነዉ የመጣሁ ኢንሻአላህ የመጠሁበት አላማ ይሳካል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 3⃣1⃣

........ ሰሚራ ሽኩር

.......ሁሉንም አቅጀ አስቤበት ነዉ የመጣሁት ኢንሻአላህ ይሳካል አዎ ይሳካል ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩት ባይሳካስ ብየ ስፈራ ይሳካል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ

....በሄድኩኝ በማግስቱ አክብረዉ አረዱልኝ በላሁ ጠጣሁ በጣም ጥሩዎች ናቸዉ። ሱመያም ከአማኔ ከተለየች ቡኋላ ጤናዋ ትክክል እንዳልሆነ ብዙ አጫወተችኝ በታሪኳ አዝና ስትነግረኝ እያለቀሰች ነዉ የምትናገር እኔም ለማፅናናት እየሞከርኩ ግን ሱመያ ባለቤትሽን ማታም አሁንም አላየሁትም የት ሂዶ ነዉ ስል ጠየቋት ሱሚም "የትኛዉ ባለቤቴን ነዉ ሙቷል እያልኩሽ" ስትል መለሰችልኝ ግራ ገባኝ እህ እና አሚር የማን ልጂ ነዉ የአማን እንዳልሆነ አቃለሁ አማኔ እኛ ቤት ከመጣ ሶስት አመት ከምናምን አራት አመት ይሆነዋል አማር አራት አመት ሀያት ስድስት አመት ይሆናታል ሱመያ ሁለት አመት እንደሆናት አይደል አማን የተለያት!..... ሳላቅ በሀሳብ
እድሜ ማሰብ ጀመርኩ

ሱመያም ቆጣ ኮስተር ብላ ስታዳምጠኝ ነበር "እንዴት አወቅሽ እንዴት ማን ነሽ አንች !...." አፋጠጠችብኝ ልሸዉዳት ሞከርኩ አልቻልኩም ደጋግማ በጥርጣሬ መመልከት ጀመረች የሆነ የደበቋት ነገር አንዳለ ግልፅ ነዉ እሷም አሚርን ባል የለኝም እያለችኝ ከማን ወለደችዉ ማወቅ እፈልጋለሁ ምን አልባት ከሙሀመድ ይሆን ስል አሰብኩ ኧረ የማይታሰብ ነዉ እንዴት የባሏን ወንድም አግብታ አይ አይሆንም ከራሴ ጋር መከራከር ጀመርኩ ሱመያም እንዴት ላቅ እንደቻልኩ ንገሪኝ ብላ አፈጠጠችብኝ ምን ልበላት አማኔ ነዉ የነገረኝ ከዛስ የማይሆን ነገር ነዉ


....የሷን መልስ ለመመለስ የግድ አሚርን ከማን እንደወለደችዉ ማወቅ አለብኝ አሚርን ከማን ወለድሽዉ ብየ ጠየኳት ከዛ እኔ ደግሞ እንዴት ላቅ እንደቻልኩ እረግርሻለሁ አልኳት

ሱሚም "አሚሬን የወለድኩት ከአማን ነዉ" ብላ ግግም አለች ባላቅ ጥሩ እሱ በአንደበቱ አንድ ሴት ልጂ ብቻ እንዳለዉ ነግሮኝ እሷ ትዋሸኛለች እንዴ!
ሱሚ አትዋሽኝ ከአማን አንድ ልጂ ብቻ ነዉ ያላቹህ ስል አፈጠጥኩባት
ረጋ ብላ "አላህ በተአምሩ ሁለት አረገልኝ አንድ ከወንድ አንድ ደግሞ ከሴት አሚር ያልኩትም ስሙን ስጠራ ሁሌም አማኔን እንዳስታዉስ አጠገቤ እንዳለ እንዲሰማኝ ብየ ነዉ"

.... መልኩን እስኪ አይዉ ብላ ወደኔ ጠጋ አደረገችዉ አማኔን ይመስላል ግን እንዴት አሰብኩ ምን አልባት እርጉዝ እኔደሆነች ይሆናል አማኔ እንደወጣ የቀረ ግን አማኔ ለምን አልነገረኝም ስል አሰብኩ ሱመያም ንግግሯን ቀጠል አድርጋ እንደገመትኩት "የሁለት ወር እርጉዝ እንደነበርኩ ነዉ እኔም እሱም እርጉዝ እንደሆንኩ ሳያቅ ሳላቅ እንደወጣ የቀረ ብዙ ሰዎች በመኪና አደጋ እንደሞተ እንደቀበሩት ነግረዉኛል"

አቤት ይሄ ህዝብ ግን ዉሸቱ መቸ ይሆን የሚለቀዉ ስል አሰብኩ ያላየዉን አየሁ ፤ያልሰማዉን ሰማሁ ፤ያልበላዉን በላሁ፤ የሌለዉን አለኝ፤የማያቀዉን አቃለሁ፣ ያልሆነዉን ሆንኩ፤ያልቀበረዉን ቀበርኩ....
አቤት አረ ሸም ነዉ!!!!
....ለነገሩ እኔስ የምር የአክስት ልጂ ሁኜ ነዉ እንዴ የአክስት ልጂ ነኝ ያልኩ!

.....እሽ ከዛስ ሱመያ ንግግሯን ቀጠለች "እርጉዝ መሆኔ የተነገረኝ ቀን አማኔ ሆስፒታል ሊያስመርቅ የሄደ ቀን ነበር ደስ አለኝ ሰርፕራይዝ ለማድረግ ሽር ጉድ ብየ ኬክ ሰርቸ፤ቡናየን አፍሎቸ፥ምግብ አብስየ፤ቤቴን አፅድቸ...ዉብ ሁኘ ብጠብቀዉ ብጠብቀዉ ቀረ በስልክ እንዳልነግረዉ አልፈለኩም የመጨረሻ ቀን ያናገረኝ ራት በላሽ ብሎ የደወለልኝ ምሽት ነበር የእሁድን ምሽት በሂወቴ መቸም አረሳትም የአማኔን የመጨረሻ ድምፅ ሰምቸባታለሁ ከሱ ቡሀላ ብዙ ባል ጠየቀኝ ማግባት አልፈለኩም ቤተሰቦቸ እንኳን ልጆችን እኛ እናሳድግ አንች አግቢ ብለዉ በተደጋጋሚ ይጨቀጭቁኛል እኔ ግን ቃል አለኝ ሁሌም ላንለያይ ከአማኔ ጋር ቃል ተግባብተናል!በዱንያ ሞት ቢለያየን በአሂራ በጀነት እንገናኛለን ኢንሻአላህ!" እንባዋን መቋቋም አልቻለችም

....አዛዘነችኝ ምን ልበላት ደሞ ደስ አለኝ የአማኔ አንድ ሴት አንድ ወንድ ልጂ አለዉ እንዴት ይደሰት እነዚህን የመሳሰሉ ቆንጆ ልጆች ሲያይ ብየ አሰብኩ

"እሽ አንችስ እንዴት ልታቂ ቻልሽ በአላህ ምንም እንዳትዋሽኝ ንገሪን" አለችኝ
.....የመጠዉ ይምጣ በፍቅር አራት አመት ሙሉ ተሰቃይታለች እሱም ተሰቃይቷል ከዚህ ቡሀኋ ግን ማልቀስ በናፍቆት መሰቃየት....ይበቃል ብየ ለመናገር ወሰንኩ ደሞ አሜኔ እንዳትናገሪ ብሎ ደጋግሞ አስጠንቅቆኛል በዚህ አሷ በአላህ እንዳትዋሽኝ ሁሉንም ንገሪኝ ትለኛለች ምን ይሻለኛል? ልናገር ወይስ አልናገር

.........ብዙ ሳስብ ቆይቸ መናገርን መረጥኩ እዉነታዉ ቢያስደነግጥ ቢመርም እዉነትና ዉሸት እያደረ ይገለፃል አይደል የሚባለዉ ቢመርም አማን በሂወት እንዳለ አብዶ በቅርብ ጊዜ እንደተሻለዉ እዚህም እንድመጣ ያረገ እሱ እንደሆነ በዝርዝር አንድም ሳላስቀር ነገርኳት አላመነችኝም "የኔ የኔ አአአአአማን በበሂወት አለ" አለችኝ አወ በሂወት አለ አልኳት
"የት እንዴት ማለቴ እሽ እርግጠኛ ነሽ የኔ አማን በሂወት አለ"አናዘዘችኝ
አወ አለ ደጋግሜ አማን በሂወት አለ ስል ነገርኳት የዚህን ጊዜ በጩኸት አማኔ የኔ አማን በሂወት አለ በሂወት አለ አማን አልሞተም"እያለች ቀወጠችዉ
"እሽ የት ነዉ ነይ ነይ አማኔ ላይ እንሂድ የኔን አማን አሳይን" ከተቀመጥኩበት ጎትታ አስነሳችን ቆይ ተረጋጊ እኔን በሂወት እንዳለሁ እንዳታቅ ብሎኛል ብየ ነገርኳት "ለምን እኔን አይወደኝም እኔ እስከዛሬ በፍቅሩ መቃጠሌን አያቅም ዉሸታም አይልሽም አማኔን አቀዋለሁ አይልሽም ነይ አሳይኝ ነይ"
..... እንደብድ የምታደርገዉን አታቅም ፀጉሯን ለራሱ በሂጃብ አልሸፈነችዉም ምን ልበላት እንዴትስ ብየ ላረጋጋት ግራ ገባኝ ታለቅሳለች ትስቃለች ድብልቅልቅ ያለ ስሜት እኔ እሷን ወስዶ ማገናኘት አላቃተኝም ነገር ግን አማኔ የHiv በሽተኛ ነዉ መገናየት አይችሉም ቢገናኙ የባሰ ጉዳት ነዉ ጨነቀኝ አማኔ የHiv በሽተኛ ነዉ ብየ እንዳልነግራት እንዴት ብየ ግን ደግሞ እንድትረጋጋ የግድ መናገር አለብኝ ተናግሬ አማኔን ማየት አለብኝ ካለች ትየዉ አላይም ካለችም ግልግል ነዉ ልጆቹ አባታቸዉን አሳይቸ እመልሳለሁ በቃ ልንገራት ብየ

ሱመያ አንድ መራራ አዉነት አለ ልብ ብለሽ ስሚኝ የምነግርሽን ሰምተሽ አማኔን ለማየት ዝግጁ ከሆንሽ ነገ በጠዋት ልጆችሽን ይዘሽ አማኔን አሳይሻለሁ የምነግርሽን እዉነት ሰምተሽ ለመሄድ ፍቃደኛ ካልሆንሽ ልጆችን ወስጀ ለአማኔ አሳይቸዉ እመልስልሻለሁ ተስማምተሽ ቃል ጊቢና ልንገርሽ አልኳት እሷም ደንግጣ አይኖን አፍጥጣ "ምን መራራ እዉነት ነዉ አማኔ ምን ሆነ ደህና አይደለም እንዴ አማኔ ምን ሁኖ ነዉ!?" ብላ ጠየቀችኝ አብሽሪ ከስንት የመከራና የስቃይ ጊዜን አልፎ ለጤናዉ በቅቷል አልሀምዱሊላህ አልኳት "ደህና ከሆነ ምን መራራ እዉነት ነዉ እሽ ንገሪኝ ቃል እገባልሻለሁ "


.....ንግግሬን ቀጠልኩ ያኔ አማኔ ከአንች ቤት ወደሚመረቀዉ ሆስፒታል የሄደ ምሽት ....ምን ብየ ልተንፍስ አይን አይኖን ማየት ጀመርኩ "እ የሄደ ምሽት ምን" ለማወቅ ጓጉታለች
የሄደ ምሽት አንችጋ ራት እንደበላሽ ሊጠይቅ ሲደዉልልሽ ምግብና መጠጡን ሲስተር ሀዋ ነበረች ያቀረበችለት ከዛ...

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇

@Meh_Ani_bot

💝በአላህ ፍቃድ የመጨረሻዉ ክፍል💝
❤️
❤️
❤️
❤️
❤️

💝💝💝Join💝💝💝
https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
💝💝💝መራራ እዉነት💝💝💝
💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖

💓💓💓 የመጨረሻዉ ክፍል💓💓💓
........ ሰሚራ ሽኩር



.....ንግግሬን ቀጠልኩ ያኔ አማኔ ከአንች ቤት ወደሚመረቀዉ ሆስፒታል የሄደ ምሽት ....ምን ብየ ልተንፍስ አይን አይኖን ማየት ጀመርኩ "እ የሄደ ምሽት ምን" ለማወቅ ጓጉታለች
የሄደ ምሽት አንችጋ ራት እንደበላሽ ሊጠይቅ ሲደዉልልሽ ምግብና መጠጡን ሲስተር ሀዋ ነበረች ያቀረበችለት ምን አድርጋበት እንደሆነ ምግብ ላይ አይታወቅም መጠጡን ምን እንደጨመረችበትም አይታወቅም ብቻ ሲነቃ አብረዉ ተኝታለች በዚህ ቡኋላ አማኔ አበደ
..."ምን ሲስተር ሀዋ!" በጣም ደነገጠች
"አላህ ለጀነት ይበላት ያኔ ከሀኪም ቤቱ ምርቃት ሲመለሱ መኪናዉ ተገልብጦ መስተዋቱ ሙሉ አካሎን እንዳልነበረ አድርጎት ተሰቃይታ አቃስታ አቃስታ ባለፈዉ አመት ሞተች አላህ የስረዋን ነዉ የሰጣት ደሞ አላህ ለጀነት ይበላት እላለሁ ክፉ ሰዉ ሰዉ የማይጠጋት አዉሬ
....ደሞ የHiv በሽተኛ ናት! እና በዚህ ምክንያት ነዉ ያበደ"ስትል ጠየቀችን አይ አይመስለኝም ያኔ በምሽት ከምግቡ ጋር ሊያሳብድ የሚችል መድሀኒት ሳሰጠዉ አትቀርም
"አወ ልክ ብለሻል አማኔ እኔን እዚህ ቤት ካመጣ ጀምሮ አስተያየቷ ባህሪዋ ሁሉ ተቀይሮ ነበር የአላህ ምን አይነት ጭካኔ ነዉ....."

አልሀምዱሊላህ እንዴት እንደምናገር ጨንቆኝ ነበር አሁን ቀለለኝ ይሄን ከነገርኳት ቡኋላ ሱመያ ማልቀስ ጀመረች"እኔ ነኝ ጥፍተኛዋ በኔ ስበብ ነዉ አማኔ ያበደ በኔ ስበብ የHiv በሽተኛ ሆነ ያኔ ባያመጣኝ ነሮ ይሄ ሁሉ ስቃይ አይደርስበትም ነበር እኔ ነኝ ጥፍተኛ እኔ..." ምን ልበል አላህ የቀደረዉኮ አይቀርም አንች አጠገቡ ስለነበርሽ ስላልነበርሽ የሚቀየር ነገር አይኖርም በቀዷቀድር እመኝ ተይ አታልቅሽ ብየ አረጋገኋት።


..... "ከመሀል ሙሀመድ መጣ ፈዛ በሀሳብ ርቃ ከቆየች ቡኋላ ለመናገር ሮጠች ወንድምህ መንድምህ አለ አለ ሞተ ስንል በሂወት አለ የኔ አማን በሂወት አለ" ሙሀመድ አላምን ብሎ ምንድን ነዉ የምታወሪዉ ነይ እስኪ ተቀመጭ ተረጋጊ ካለ ቡኋላ ወደኔ ዙሮ ምንድን ነዉ ሀናን ሲል ጠየቀኝ ሁሉንም አንድ በአንድ ነገርኩት "እዉነትሽን ነዉ ብሎ ደጋግሞ ጠየቀኝ እዉነቴን እንደሆነ ካረጋገጠ ቡሀላ ሱጁድ ወረደና ነይ ተነሽ ያለበትን ቦታ አሳይን ብለዉ ተነሱ እህ እየመሸ ነዉ ነገ ጥዋት እንሄዳለን አልኳቸዉ በጭራሽ ዛሬ ነዉ የምንሄድ አይቻልም ብለዉ ተነሱ አሁን መኪና አናገኝም ቆይ ተረጋጉ ልብሳቹህንም ቀያይሩ ሲያያቹህ ደስ እንዲለዉ ፏ በሉ አልኳቸዉ "አይቻልም እሱን መጀመሪያ እንየዉ ለመኪናዉ ችግር የለም በኔ መኪና እንሄዳለን ሱሚ ቶሎ ልጆችን አለባብሽና እንዉጣ" አለ

......ስንከራከር የመቅሪብ አዛን ተባለ ለምኜ ለምኜ በስንት መከራ በጥዋት ለመሄድ እሽ አሉኝ የዛን ምሽት ሱመያም ሙሀመድም እኔም ቁጭ ብለን አስሬ በየቀቂቃዉ ሰአት ስናይ ሳንተኛ ሱቢህ ተሰገደ እኔ አሁን ከአማን ጋር ሲተያዩ ምን ይሆን የሚሉ እያልኩ አስባለሁ እነሱም በራሳቸዉ አለም በሀሳብ ተጉዘዋል....
ሱቢህን ሰግደን ወጣን ለእማየ አብረዉኝ እየመጡ መሆኑን እንድትዘጋጂ ነገርኳት ለአማን ግን እንዳትነግሪዉ ብየ አስጠነቀኳት እሽ ብለኝ ምንገዳችንን ጀመርን ከረዥም ሰአት ቡኋላ ቤት ደርሰን የጊቢዉን በር አንኳኳን አማኔ ነበር የከፈተዉ እኔ ከፊት ሱመያ ልጆችን ይዛ ከኋላ ሙሀመድ ደግሞ ከሱመያ ጀርባ ነበር አማን በሩን ክፍት ሲያደረገዉ ሱመያ በቀኝ እጇ የያዘችዉን ቦርሳ መሬት ላይ ጣል አደረገችና በቀኝ እጂ የያዘቻቸዉን ልጆች ለቃ አማኔ ላይ እሩጣ እያለቀሰች ተጠመጠመችበት አማኔም "ሱመያ ሱሱሱመያ ማሬ".....ተለይዘዉ ማልቀስ ጀመሩ ወንድሙ ሙሀመድም እየተንሰቀሰቀ ማልቀስ ጀመረ እኔ እነሱን ሳይ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም እማየ የቤቱ በር ላይ በሩን ገደፍ ብላ ታለቅሳለች አባቢ ከአማን ጀርባ ሁኖ ያለቅሳል ሪሀና ከእኔ አጠገብ ሁና ታለቅሳለች የአማን ትናንሽ ልጆች እናታቸዉ ስታለቅስ እማ እማ ....እያሉ ማልቀስ ጀመሩ .......በልቅሶ ከግማሽ ሰአት በላይ ከቆየን ቡኋላ እማየና አባቢ ተዉት አላህ ብሎት ተገናኛቹህ አይደል ልጆችንም አታስለቅሷቸዉ ብለዉ ወደ ቤት አስገቧቸዉ

....ሁላችንም ፊታችንን ታጥበን ልቅሷችንን አቆምን ሱመያ ግን አልቻለችም እንደዉም እየባሰባት ሄደ አማን አማኔ እያለች አንዴ ፀጉሩን አንዴ ፊቱን መዳሰስ ጀመረች ከአጠገቧ የሚሄድ የማታገኘዉ እየመሰላት ሲነሳ ስትነሳ ሲቀመጥ ስትቀመጥ በናፍቆት ሲተያዩ ስአታት ተቆጠሩ

...የአማንን ፊቱንሳየዉ ተስፋ የቋረጠ በፍርሀት የሆነ ሊነግራት የፈለገ ነገር ግን እንዴትና ከየት መጀመር እንዳለበት ግራ የገባዉ ይመስላል ሱመያ ደግሞ በስስት አይኖቿ እየተመለከተችዉ ፊቷ እያበራ ተስፋ አትቁረጥ መቸም አልለይህም የምትል ትመስላለች.....

እኔዉ ጠያቂ ያንችዉ አማኔ
ለምን መጣሽ ፍቅር አለሜ?
አንድ ላይ መሆን ላንችል እኔ ታምሜ
በኔ የዋህነት
በኔ ደግነት
በኔ ጥፋት
በአንዲት ሴት በአንዲት ለሊት
የፍቅሬን ቃል አጠልሽቸ ሰባበርኩት
ምን ብየ ልንገረሽ እዉነቱ መራራ የፍቅር እንቅፋት
ከየት ጀምሬ ምን ልበልሽ
ምን አፍ አለኝ ምንስ ላዉራሽ

አማኔ ምንም አትበለኝ እዉነቱን አቃለሁ
የአራት አመት ስቃይህን ሰምቻለሁ
ዉዴ አንተን ፍለጋ መጥቻለሁ
ተንግዲህ ላንለያይ ቃል እገባለሁ
አማኔ በሽተኛ መሆንህን አቃለሁ
ትወደኛለህ እ*ወ*ድ*ሀ*ለ*ሁ
ማንነትህን ተቀብየ ስንሆን በህብረት
ማጣፈጥ እንችላለን መራራዉን እዉነት

አማኔ ዘመን የማይሽረዉ የፍቅር ገመድ
የታሰረ መቸም ላይናድ
ቃል ነበረን አሁንም አለ እንደፀሀይ የደመቀ
እንደጨረቃ የረቀቀ

ዉዴ ቃል አትበይኝ አልገባሽም እኔ ምልሽ
ላልጠቅምሽ አልቀርብሽም ትጎጃለሽ

አማኔ አትቀልድ
ያየጭንቅ ጊዜ ድፍን አራት አመት
ለሊቱ ረዥሞ አልነጋ ያለበት
ቀኑ ጨልሞብኝ ሁኘ ለብቻየ
ግራ ተጋብቸ
አማኔን አጥቸ
ሳለቅስ ይነጋል ሳለቅስ አምሽቸ

ከሀገር ሀገር ሲዞሩ እግሮቸ
ጠፍተሀቸዉ ሲያማትሩ አይኖቸ
አልነጋ ሲለኝ ከጨረቃ ጋር እንደብድ ሳወራ
ብየ ስላት የት አየሽዉ ምን ሲሰራ
ወሬት ሄደ ምን አወራ
መልስ የላትም መች መለሰች
በዝምታ እየሳቀች
ማታ ማታ እያበራች
የኔን እንባ አላበሰች

ፀሀይንም መሬትንም እጠይቃለሁ
አትዋሹኝ ካያቹህት ብየ እላለሁ
አይመልሱም እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ
በር በር ሳይ ስንቆራጠጥ
አላፊ አግዳሚዉ አፉን ሲመጥ
በሩ ሲንኳኳ አንተ መስለኸኝ ስነሳ ስሮጥ
በአንተ ፍቅር አራት አመት ሁኖ አርባ አመት ተሰቃየሁ

ዉዴ እኔምኮ አንችን ሳስብ የደም እንባን አነባለሁ


ቆይ አማኔ ልጠይቅህ
ደስታህ ደስታየ ሁኖ ካልተደሰትኩኝ
ሀዘንህ ሀዘኔ ሁኖ ካላዘንኩኝ
ህመምህ ህመሜ ሁኖ ካልተሰማኝ
እሽ ፍቅር ላንተ ምንድን ነዉ ትርጉሙን ንገረኝ

ዉዴ ለኔ ፍቅር

ፍቅር ማለት ተአምራዊ ትርጉም የሌለዉ
ፍቅር ማለት ራሱ ፍቅር ነዉ

ዉዴ በቃ ተረጂኝ ተለያይተን አንችም ኑሪ እኔም ልኑር

አማኔ ተረዳኝ መኖር አልችልም ተለይቸ እየተቃጠልኩ ባንተ ፍቅር
ዉዴ ይቆጨሀል እሞታለሁ
አብረን ካልሆን ትጎዳለህ እጎዳለሁ
ህመምህን እንጋራዉ ትድናለህ
አብረን ከሆን በደስታ ትኖራለህ
አማኔ ፍቅርህ ነዉ ለኔ መድሀኒቴ
አብረከኝ ስትሆን ነዉ ደስተኛ የምሆነዉ በሂወቴ..

ዉዴ ስጋህ ከስጋየ ደምህ ከደሜ
ልብህ ከልቤ ሁሉ ነገሬ
ተወህደዋል አማኔ ፍቅሬ......
👇👇👇👇👇👇👇
.
.
.
ዉዴ ጠልቸሽ አይምሰልሽ
ተለያይተን እንኑር የምልሽ
እንዳትጎጂብኝ ፈልጌ ነዉ ራቂኝ ያልኩሽ
እንጂማ ብጠይቂኝ ምን ያህል ብለሽ
ሚዛን የለኝም እወድሻለሁ ለኔ ሁ*ሌ*ም ልዩ ነሽ

አማኔ ትዝ ይልሀል ያኔ ሴት ሳትሆን ሴት መስለህ የቀረብከኝ
ልቤ ተሰብሮ ተስፋ ቆርጨ ተስፋ የሰጠኸኝ
እንተካ ነህ ሂወቴን የታደከኝ

አማኔ እሽ በለኝ
ህመምህ ህመሜ ሁኖ ይሰማኝ
..........ዉዴ ምን ቃል አለኝ
በምን ቋንቋ ፍቅሬን ልግለፀዉ
ብቻ ኑሩልኝ ለዘላለም እወድሻለሁ

......ተንግዲህ ይብቃ ማልቀስ በናፍቆት
........ተንግዲህ ይብቃ መለያየት
........ወዶ መቀበል እስከማንነት
........እንደሱመያ እንደአማን ሚስት

.... ፍቅር ይሉታል እንዲህ ነዉ!!!


.....ከብዙ ክርክር ከብዙ ጭቅጭቅ ቡሀላ አማኔና ሱሚ አብረዉ ለመሆን አብረዉ ለመኖር ተስማሙ በጣም ደስ አለን ደስታችን ወደር አልነበረዉም
ሂወታችንም በጣም ተቀየረ የቅንጦት ሂወት መኖር ጀመርን ከኪራይ ቤት ወደ ራሳችን ቤት ከታክሲ ወደ ቤት መኪና የደረቀ ቂጣ ከመብላት ወደ አማርጦ መብላት ተሸጋገርን ደስ አይልም!😊 የታገሰ መጨረሻዉ እንዴት ያምራል!
የኛ ጌታ በርግጥም እዉነት ተናገረ"የአደም ልጂ ሆይ ጥሩም ስራ ስራ መጥፎም ስራ ስራ ትመነደዋለህ"

...ሁላችንም ክብ ሰርተን ተቀምጠን ያን መጥፎ ጊዜ በትዝታ ስንቃኘዉ ከመሀል ሱመያ አባቢን "የደግነትን ጥግ በአንተ አየን ወላሂ ጀግና ነህ! ዘመድህ ሳይሆን ሳታቀዉ ሀብት ንብረትህን ሺጠህ ለዚህ አበቃሀዉ"አለችዉ
አባቢም "ሱመያ ልጀ ሰዉን ለመርዳትኮ ሰዉ መሆን በቂ ነዉ
ስንት ደጋግ ሰዎች አሉ መሰለሽ አይደለም ሀብት ንብረት የሚተካ ቁስ ነገር ምትክ የሌላት ሂወታቸዉን አሳልፈዉ የሚሰጡ እና እኔም ከነዚህ ጋር ደግ እባላለሁ አይ ሱመያ ልጀ...."ፈገግ አለ።
አባቢ እዉነት ተናገረ ሰዉ ለመርዳት የግድ እህት፤ወንድም፤ እናት ፤አባት፤ ዘመድ....መሆን የለባቸዉ በኢስላም ሁሉም ሰዉ እህትና ወንድም ነዉ ደግሞስ መወለድ ቋንቋ አይደል።

የዱንያ ካዝናችንን ስንሞላ ስለዱንያ ስናስብ ስንጨነቅ ያሂራ ካዝናችን ባዶ ሁኘ ያችን የጭንቅ ቀን እንዳንገናኛትና ለዘላለም ከከሳሪዎች እንዳንሆን ካለን ላይ እንስጥ እናካፍል ያለዉን የሰጠ ለአላህ ብሎ
አላህ ይሰጠዋል ደርቦ ደራርቦ
እኛ ከሰጠነዉ አምሮና ተዉቦ

በዚህ ታሪክ የፍቅርን፤የደግነትን፤የአንድነትን.....ጥግ አይተናል
የፍቅር ትርጉሙን ላላወቁ፤መስጠት ምን እንደሆነ ላልተረዱ...... ለነዚህ አይነት ሰዎች ከቻላቹህ አድርሱልኝ🙏🙏🙏


ምክር አበዛለሁ መሰል አቋረጥኩት😊


❤️❤️❤️ተፈፀመ❤️❤️❤️
ምስጋና፦

በመጀመሪያ ለሁሉ ፈጣሪ ለአላህ ክብር ምስጋና ይገባዉ

ወንድም አሚር ሰኢድን ከልብ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ ሁሌም ከጎኔ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንድፅፍ ያስጀመረኝም ያበረታታኝም እሱ ነዉና ከልብ አመሰግናለሁ
ሲቀጥል ያነበባቹህትን አንብባቹህ ለሌሎች ያጋራቹህትን አስተያየት ስትሰጡኝ የነበራቹህ እህት ወንድሞቸን ከልብ ከልብብብብብብ አመሰግናለሁ አላህ ካለ በሌላ ታሪክ እንገናኛለን።

አስተያየታቹህ ሌላ ታሪኮችን እንድፅፍ ምርኩዜ ነዉና ማንኛዉንም አስተያየት የተሰማቹህን ፃፉ በቀጥታ ይደርሰኛል ........👇👇👇

@Meh_Ani_bot


Join👇👇👇
https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
አሰላሙ አለይኩም ያጀመአ!
ብዙ አስተያየቶች እየደረሱኝ ነዉ የሁላቹህንም አስተያየቶች አንብቤለሁ ። ጊዜ በማጣት ያልመለስኩላቹህ አዉፍ በሉኝ ተቅለል አድርጌ መልስ እሰጣለሁ።

አልሀምዱሊላህ የሁላቹህም ማለት ይቻላል ጥሩ አስተያየት ነበር ወላሂ ከጠበቁት በላይ አላህ ኸይር ጀዛቹህን ይክፈልልኝ🙏🙏🙏

ሲቀጥል በተደጋጋሚ የመጡ አስተያየቶች

1 ታሪኩን ለምን ባጭሩ ቋጨሽዉ???
ሀቂቃ እኔም እንደዚህ እንዲያበቃ አልፈለኩም ግን ታሪኩ መፓሰት ከጀመረ ጀምሮ ለምን ታንዛዙታላቹህ የሚሉ የተለያዩ አስተያየቶችን አይቻለሁ የቻልኩትን ያህል ቀንሸ edit አድርጌ ቶሎ ለመጨረስ ሞክሪያለሁ።
ብዙምቻቹህም አነሰ በቀን ሁለት ክፍል ይለቀቅ ስትሉኝ ነበር
ብዙዎቻቹህም ምክር ታበዣለሽ ቀንሽ .....ብላቹህኛል ወደ መጨረሻ አካባቢ ለማስተካከል ሞክሬለሁ

2 "ለምን በሰፊዉ በመፃሀፍ መልክ ተደርጎ ለህዝቡ አይቀርብም በመፅሀፍ በሰፊዉ ፃፊዉ!"
ፈገግ ያደረገኝ አስተያየት የብዙዎቻቹህ ጥያቄ ነበር
ዉዶቸ እኔ ገና ጀማሪ ስለፁህፍ የማቀዉ ነገር የለም መፃሀፍን ያህል ነገር ኧረ የማይታሰብ ነዉ!
ኢንሻአላህ ማለቱ ኸይር ነዉ ኢንሻአላህ

3 "ታሪኩ የእዉነተኛ ታሪክ ነዉ ወይስ ልብ ወለድ?"

ታሪኩ 100% እዉነተኛ አይደለም ከስም ጀምሮ አንዳንድ ነገሮች ተቀይረዋል ብዙዎቻቹህ የታሪኩ ባለቤት እኔ ነኝ የመሰልኳቹህ እኔ አይደለሁም ታሪኩን የፃፍኩትኝ ሰሚራ ነኝ ሀናን ወይም ሱመያ አይደለሁም ።
ከታክሲ ጀምሮ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ወሬዎችን በተለያዩ ቦታዎች እንሰማለን እንገረማለን እኔም የተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ጊዜዎች የሰማኋቸዉን መራራ እዉነቶች አንድ ላይ ጨምቄ ምክሮችን ይጠቅማሉ ያልኳቸዉን የራሴን አመለካከት ጨምሬ ነዉ ለንባብ ያበቃሁት።...

4 "ታሪኩን ስትፅፊ ማን አገዘሽ?"
ሀቅ ለመናገር ማንም አላገዘኝም ማንም አልገመገመልኝም ጊዜ ያለዉ የለም ነበር ለዛም ነዉ ታሪኩ ማለቅ ባልነበረበት ሁኔታ ያለቀዉ ምናልባት ጥሩ ፅሀፊ ቢያነበዉና መጀመሪያ ገምግሞልኝ በነበር እንዳሁኑ በአጭሩ ሊቋጭ አይችልም ነበር።

5 "በታሪኩ ዉስጥ ሀገር አልጠቀሽም?"
ምን ብየ ልጥቀስ በአጋጣሚዎች የተለያዩ ሀገሮች ላይ የሰማኋቸዉን የተለያዩ ታሪኳችን ነዉ በአንድ የጨመኳቸዉ።

6 "ምእራፍ ሁለት ይቀጥል!?"

. ..ምን ተብሎ ከየት ተጀምሮ አንባቢንም ግራ ማጋባት ይመስለኛል
አሁንም አስተያየታቹህን እያየሁ በአንድ እመልሳለሁ
ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት👇👇👇

@Meh_Ani_bot

Join👇👇👇
https://www.tg-me.com/ne_siha_eslamik
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ፡፡ የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የቻናል ቤተሰብ እንዴት ናችሁ ጨጓራ ኩላሊት ሁሉ ሰላም

የተከበረዉ የረመዷን ፆም እየመጣ ስለሆነ አላህ ለረመዷን በሰላም አድርሶን ፁመዉ ከሚራቡት ሳይሆን ከሚጠቀሙት ያርገን ፡፡


በአስተያየት መስጫ bot የምታደርሱት አስተያየት 100% ይነበባል ግን ለመመለስ ጊዜ ስለሚያጥረኝ ነዉ ..እዉነተኛ ታሪክ አስነብባለሁ ብለህ ቃል ገብተህ ቃልህን በላህ የሚል አስተያየት ብዙ ቀን አንብቢያለሁ

☞አዎ አልክድም ብዙ ቀን የጀመርኩት ታሪክ አለኝ አስነብባለሁ ካልኩ ከሁለት ወር በላይ አለፈኝ ግን በተለያዩ ችግሮች አላህ ሳይሻ ቀርቶ ግን ሊሳካልኝ አልቻለም የሰዉ ልጅ ነኝና እንከን አያጣንም ... ከረመዷን በፊት ለማስነበብ ለይል ወነሀር አጣድፌዉ ነበር ስልክ በመበላሸት ምናምን አልተሳካም

ከዛም በሂደት የታሰበዉን ታሪክ ፅፌ ከጨረስኩ ቡሀላ ወደ እናንተ ለማስነበብ ዝግጅቴን አጠናቅቄ ጨርሼ ....ታሪኩ ሲፃፍ በባለታሪኮቹ ስምና አድራሻ ሳይቀየር ነበር ...ባለታሪኩ መቀየር አለበት ሲለኝ እንደገና ስሙን የሰፈር ገፀ ባህሪ ተቀይሮ 95% አልቆ ለንባብ ሊበቃ ሲል ይሄዉ ረመዷን ከፊት ለፊታችን ቀርቧል፡፡ በረመዷን ደግሞ በኔ አጅር በማያስገኝ ታሪክ እንድታፈጥሩ አልፈልግም😉 ተምርና ዉሀ እያለ ፡፡ በተጨማሪ ረመዷን በዚክር በቁርአን በሶላት ማሳለፍ እንጂ ....በማይጠቅሙ በነሽዳ በመንዙማ ታሪክ በማንበብ እንዳናሳልፍ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ለምን አምና ረመዷንን ዘንድሮ እንፆማለን ብለዉ የነይቱ ወንድም እህት እናት አባቶቻችን ወደ አኼራ የሄዱ ብዙ ናቸዉ....
በዱአ አንረሳሳ

👉መቼም የዘንድሮ ኸልቅ መንዙማ ነሽዳ በማዳመጥ ተጠምዷል፡፡ አስተካክሎ አሊፍና አይን የማይለይ ሁሉ ነሽዳ እያወጣ ትዉልድ እያጠመሙ ነዉ...እንደዉም በሙነሺዶች ነሽዳ ለማዉጣት ፉክክር ሲታይ መጅሊሱም በሙነሺዶች እንዳይመራ ያስፈራል😉😉 እና የሙነሺዶችን ስማቸዉን አልጠራም ከአፍ እንጂ የነቢይ የአላህ ወዳጅ በስመ ሙነሺድ ተግባራቸዉ ሌላ ነዉ😊
መቼም የኔ ቻናል ቤተሰቦች ቶሎ ይገባችሆል ማገዶ አፈጁም


☝️በደሀ ልጅ ፍቅር የምናቀዉ ከድር አህመድ ልጁ እንደወለደች አሳዉቂያለሁ፡፡ እኔም ያለበት ድረስ ሀርቡ ሂጄ ዘይሪያለሁ

☝️ባለፈዉ ያስነበብኳችሁ የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ታሪክ ባለቤት ነዋል ከአንድ ወር በፊት የወንድ ልጅ እናት ሁናለች በጣም ደስ ይላል ነገር ግን የወንድም የእህት ዱአ ጥሩ ነዉ በቅርብ ቀን ትንሽ ልቧን አሟት ኦፕሬሽን ስለምትደረግ በዱአ እንገዛት ፡፡ የእሷም መልዕክት ነዉ አድርሻለሁ


📥 ለወደፊት የሚቀርበዉ ታሪክ ርዕሱ #ሳትዋጋ_ንገስ ሲሆን በታሪኩ ሁለት ገፀ ባህሪ አለ የባለታሪኩና እራሱን የቻለ የመራም ማስታወሻ በአንድ ላይ ቀርቧል አዲስ የአፃፃፍ ሲስተም ተጠቅሚያለሁ፡፡
ስታነቡት በጣም እንደምወዱት እርግጠኛ ነኝ

ብዙ አስተያየት አላዘጋጀህም ዉሸትህን ነዉ ለምትሉ ታሪኩ 95% አልቋል ... የተዘጋጀዉን ታሪክ በቅርቡ እስከ part ➐ ድረስ አስነብባችሆለሁ ብዙ part ስለሆነ ከዛ ረመዷን ሊገባ ሲል ታሪኩ ከቻናል ላይ ይሰረዛል ፡፡ አላህ ካደረሰን ከረመዷን ቡሀላ ከክፍል አንድ ጀምረን በአዲስ መልክ እንጀምራለን ማለት ነዉ፡፡

⚠️⚠️⚠️ Warning
የሌላ ቻናል ባለቤቶች ሆይ !!! ታሪኩ ሙሉ በሙሉ ረመዷን ላይ ስለሚቋረጥ እና ከቻናል ስለሚነሳ በቻናላችሁ እንዳጀምሩ ከረመዷን ቡሀላ ሙሉዉ ሲፓሰት አብራችሁ ታስተላልፋላችሁ

አሚር ሰይድ


4 any comment👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
2024/09/23 06:25:35
Back to Top
HTML Embed Code: