Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሸኽ ሮመዳን!"
የወሎ ሰው «ዙር ገጣሚ አላህ ያርጋችሁ» ብሎ ይመርቃል። ከቁጥር ሳትጎድሉ ዓመት ዓመት ድረሱ ማለቱ ነው። መቼስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የዚህ ምርቃት ትርጉም አሁን የገባን ይመስለኛል። አዲያ እንዴ ተማላ (እንደ ዋዛ) ዓመቱ ደርሶ እኔም ከቁጥር ሳልጎድል ዙሩን ገጥሜ ስንቱን ባጣንበት ሜዳ ቀና የማለቱን፣ ታላቁን ወር የማግኘቱን እድያ አገኘሁም አዴል? አሁንም አሚን እያልኩ እዬሸከርኩ እዬሃመድኩ ይችን ወጌን ሃያ ጀባ እላለሁ ዛሬም!
እኛ ወሎዬዎች ብዙ የዓረብኛ ቃላትን በተለይም ስሞችን በራሳችን ፈቃድና ስልጣን ለ‘ኛ በሚመች መልኩ ወደራሳችን አማርኛ ስበናቸዋል። ስሞችን ብናይ ዑመርን "ይመር" አዒሻን "አንሻ" ኢማምን "ይማም" ከቁልምጫ ከዶ፣ ሙሄ፣ አንሾ እና ሌሎችም። ረመዷንም እንደዚሁ ነው። ሸሕሩ ረመዷን ሲባል የሰማውን የወሩን መጠሪያ ወሎ ተቀብሎ "ሸህ ሮመዳን" አለው። እስካድግ ድረስ ይህ ትክክለኛ መጠሪያው ይመስለኝ ነበር። ደሴ ውስጥ ከጨረቃ መታዬት በተጨማሪ የረመዷንን መጀመር የሚያሳውቁ ትዕይንቶች አሉ። በዛ ምሽት የመንገዶቹም ሆነ የዬመስጅዶቹ መብራቶች በታየቺዉ ጨረቃ ቀንተው በሚመስል ሁኔታ ይበልጥ ደምቀው ይታያሉ፤ ሁሉም አካባቢዎች ሙስሊም ክርስቲያን ሳይባል በሰፈር ልጆች ተክቢራ ይደምቃሉ፤ መንገዶች ጀለቢያ ለብሰው ትከሻቸው ላይ መስገጃ ጣል ባደረጉ ወንዶችና ባብዛኛው "ሸርሸፍ" ተከናንበው ወደ መስጅድ በሚያመሩ ሴቶች ይሞላሉ፤ ከዬመስጅዶቹ የሚሰሙት ተክቢራዎች ልክ አሁን እያዳመጥኳቸው ያለ ያክል ልብን በሀሴት ይሞላሉ፤ ከዚህም ከዛም «እንኳን አደረሳችሁ« «እንኳን አብሮ አደረሰን» የሚሉ ድምጾች ይሰማሉ። ብቻ ከደወይሜዳ እስከ መናፈሻ ከዛም እስከ ጧኢፍ ሰፈር፣ ከመላኩ ደሳለኝ እስከ ዓረብ ገንዳ፣ ከሸርፍ ተራ ጫት ተራ ሸዋ በርን አካሎ እስከ ሰኞ ገበያ ያለው ድምቀት የቱ ተነስቶ የቱ ይተዋል!?
የረመዷን ፆም የሚጀመርበት ቀን የዋዜማው ምሽት "ገባረላ"ተብሎ ይጠራል። ምንኛ እንደሆነና ትርጉሙን የሚያውቅ እስካሁን ባያጋጥመኝም። በዚህ ቀን ታድያ የገጠር ዘመዶቻችን ተሰብስበው እኛ ቤት ይመጡና ከመስጅድ መልስ ዱዓ እያደረጉ ይቀበሉታል ታላቁን ወር። አጎቴ "እንዴው እታለም ሸኽ ሮመዳን እንዲህ እንዴ ተማላ መጣም አዴል? አምና እህነዜም እንድሁ ትልም አልነበር?" ይላል ለእናቴ በጊዜው መንጎድ እየተገረመ። "አይወይም ቤቱን ያብጅለትና ተ‘ኛ አይነጠልም ነበር መገን አላህ!" ይላል የሞተ ወንድሙን እያስታወሰ። ትክዝ ይልና ደግሞ "እስቲ የተቀረነውን ዙር ገጣሚ አላህ ያርገን!" ሲል አሚሚሚን ይባላል በረጅሙ። ከዛማ እናቴ እያጫጫሰች ቡኗን እየቆላች "አቦል ጀባ ቀህዋ ጀባ!" ትልና ምርቃቱ ከፋቲሓ ጋር ይቀጥላል እያከታተለች ትቀዳለች። አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ረመዷኒም ይቀልጣል። ይህንን ስብስብ ትቼ መተኛት አልፈልግም። ግን ደግሞ ልጅ ነበርኩና ወደ አምስት ሰዓት ገደማ እንቅልፍ ያንገላጅጀኛል። ይህን ያዬ አጎቴ ታድያ " ሽታየዋ ህጅ ግቢ በረካ ሁኝ አቦ እሰይ ወርቄዋ ዱቃ (ዱዓ) ትወዲያለይ!" እያለ ራሴን ያሻሽና "ተኝ"ይለኛል። ቱፍታቸውን ተሸልሜ ገብቼ እተኛለሁ።
ደሴ በረመዷን የራሷ የሆነ የስሁር አላርምም ነበራት "አሊ ፓስቲኒ"። ይህ ሰው ወሩን በሙሉ በዛ በሌሊት በየሰፈሩ እየተዘዋወረ ከበሮውን ድው ድው ድው ያደርግና "አሊ ፓስቲኒ ተነሱ ሾርባ ቅመሱ ተሰሃሩ!" እያለ ሰውን ይቀሰቅሳል። አላህ ሥራውን ይውደድለትና እሱንና "ላሊበላ" (አባ ውዴዎችን) ሰው ይሁኑ አይሁኑ፣ ጥቁር ይሁኑ ቀይ፣ ፈረሰኛ ይሁኑ እግረኛ ለማዬት የነበረን ጉጉት አይረሳኝም። ሳስባቸው ፈገግ ከሚያስብሉኝ ነገሮች አንዱ የሱዳን ሙዚቃ ነሽዳ እየመሰለን የኮመኮምነው ነገር…!አንድ ልጅ ምን አለ "የሱዳን ዘፈን ስሰማ ይርበኛል ረመዳን እየመሰለኝ!" ሃሃሃ
በአንዳንድ መስጅዶች በአባቶች የሚባለው "ዓለይከ ረብበና ቢኹስኒል ኺታሚ"፣ በሌሎች መስጅዶች ከሚገኙ ወጣት አሰጋጆች የሚወጣው የተስረቀረቀ የቁርዓን ድምፅ፣ ከመስጅድ አቅራቢያ ከተኮለኮሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰሙ መንዙማዎች፣ ወደ መስጅድ ለመግባት እያሟሟቁ በዬሱቆቹ ደጃፍ ሰብሰብ ብለው የሚጨዋወቱ ሰዎች፣ በየቤቱ ሰብሰብ ብለው በአንድነት የሚያፈጥሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ጓደኞች፣ ያበሉ ያጠጧቸውን ሚስኪኖች ሳይጠዬፉ በመኪኖቻቸው ጭነው ወደዬመጡበት መልሰው ወደ መስጅድ የሚጣደፉ አዛኝ ሃብታሞች፣ የሳንቡሳው ሽታ፣ የስጋ ሾርባው መዓዛ፣ ልጅ ሆኜ ተራዊህ እሰግዳለሁ ብዬ ሄጄ እንቅልፍ የሚደፋኝ ነገር፣ ረመዷንን መቀበያ የየቤቱ ሁሉ ምንጣፍ ወጥቶ የሚታጠበው፣ በኅብረት የሚፈተገው የሾርባ እህል፣ ሌላ ሌላው ሸመታ ሁሉ በዓይነ ህሊናዬ፣ በእዝነ ልቦናዬ ይመላለሳሉ!
በረመዷን በርረ መዳን (የመዳን በር) ይከፈትልን፣ አገር አማን በላዑም ተብሪድ ይሁንልን፣ አዛ ናዚላ ሙሲባው ሓምና ጘሙ ሁሉ እንጃ ሜዳ ይውደቅ፣ ከከራሚዎቹ፣ አሁንም ዙር ከሚገጥሙት፣ ቀልብ ጀሰዳቸው ከጠራው የ‘ርሱ ሰዎች ያድርገን አሚን!!!

#ረመዷን_ሙባረክ!❤️
Atiqa Ahmed Ali



@IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#በአማሪኛ ☞እንኳን ለረመዳን ጾም በሰላም አደረሳችሁ
#በስልጥኛ ☞ሀበይ ለረመዳን ሶመን ቦገሬት አጄጄሙ
#በቀቤንኛ ☞ሀበይ ወገሬቲን ረመዳኒ ሶመኒ ኢሊሾይነ
#በኦሮሚኛ ☞Baganagan somnaa Ramdanaa gesanaa
#በማረቆኛ ☞ሀበይ ሶመነን ጡመን አፊሱኮ
#በጉራግኛ ☞በዘበር ሶመን ጌታ ቦሄቀር አሰናናሁም
#በአፋርኛ☞ Unkaq Ramadaanah soomuh yalli salaamah
#በሀላቢኛ☞ ሀበይ ወገሬቲን ረመዳኒ ሶመኒሃ ኢሊሂኔ
#በወለኒኛ☞ ሀበይ ለሶመኒ ወረ በፊያ አጄጄሁም
#በሃዲያ☞ ሀበይ ጾሚፃሚን አፊሶኮ
#በትግርኛ ☞እንካዕን ረመዳን ብሶላም አብፀሐኩም
#በወለይትኛ ☞ ሀሹሰሮረመዳና ገፂዳታ 
# ﺭﻣﻀﺎﻥ ﻛﺮﻳﻢ
Ramadan Kareem❤️❤️


  
4 another channal👇
             www.tg-me.com/Islam_and_Science
💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
ቀጥታ ስርጭት በTv ላይ አንድ ሙፍቲህ ከሱማሌ ስደተኛ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸዉ፡፡

ሱሁርም ኢፍጣርም ባይኖረን ፆማችን ተቀባይነት ይኖረዋል ወይ???😔😔
ሙፍቲሁም በፎቶዉ እንደምተዩት ሁኔታ ነበር ስሜቱን የገለፀዉ

☝️መዉላና ጀላሉዲን ሩሚ አላህ ይርሀማቸዉና እንዲህ ብለዋል፡፡
የዚህ ዓለም ህይወት እንደህልም ነዉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ሀብት ማግኘት በህልም ሀብት እንደማግኘት ነዉ፡፡ዓለማዊ ሀብቶች ከአንዱ ትዉልድ ወደሌላዉ በመተላለፍ በዚህ ምድር ላይ ይቆያሉ፡፡
የሞት መላዒካ ዝንጉዉን ከእንቅልፍ ይቀሰቅሰዋል ፡፡ሰዉየዉም በትክክል የራሱ ላላደረገዉ ነገር ሲል የሚያሳልፈዉን መከራ በማሰብ ያቃስታል፤አብዝቶም ይፀፀታል ቢሆንም ዘግይቷል ሁሉም ነገር አብቅቷል፡፡
ዓሊይ ረዐ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሰዎች በእንቅልፍ ላይ ናቸዉ የሚነቁት ሲሞቱ ነዉ ብለዋል፡፡
አላህ በተከበረ ቃሉም እንዲህ ይላል:- ከእናንተ አንዳችሁ ሞት መጥቶበት """ጌታየ ሆይ !!እመፀዉት ዘንድ ከደጋጎች ሰዎች እሆንም ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ እመኛለሁ"""ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ ብሏል (63:10)

☝️እኔ እና አንተ አንቺም እሱም እሷም ለሱሁር ለፍጡር አምስት ወይ ስድስት አይነት ምግብ እያዘጋጀን ፆምን የሆድ መሙሊያ ሙሸራ አድርገንዋል ፡፡ ነገር ግን ኢፍጣርና ሱሁር ለማዘጋጀት አቅም የሌላቸዉ ጎረቤቶች ዘመዶች ስላሉ እነዛን ማስታወስ እንዳንዘነጋ የእለቱ ምክሬ ነዉ፡፡

መልካም ረመዷን ፆም ተመኘሁ
አሚር ሰይድ

💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሊ ፓስትኒ👇
አሊ ባስትኒ
‹‹የረመዳን ወር የለሊት ድምቀት!››
በሙስሊም አማኞች ዘንድ ረመዳን የተቀደሰ ወርና መለኮታዊው የጾም ተግባር የሚፈጸምበት ከመሆኑ ባሻገር በልዩ ልዩ ማህበረሰቦች ዘንድ ለየት ያሉ ባህሎችና ተውፊቶች እንዲፈጠሩም ምክንያት መሆኑን ብዙዎች ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ ወር ጋራ በተለየ ሁኔታ የሚታወሱ ታሪካዊ ሰዎችም በየአካባቢው መኖራቸውንም እንዲሁ፡፡ ለምሳሌ በከተማችን ነዋሪዎች ረመዳን በመጣ ቁጥር “ዓሊ ባስትኒ” የደሴ መገለጫ ነበሩ፡፡ እኝህ ሽማግሌ ማይክራፎን ባልነበረበት ዘመን በውድቅት ሌሊት ተነስተው ከበሮ እየመቱ “ተሰሓሩ” በማለት ምእመናንን ለስሑር ይቀሰቅሱ ነበረ፡፡
የተወለዱት በደቡብ የመን ኤደን ላህግ በምትባል ክፍለ ከተማ ነው፡፡ በ1985 ዓ.ም በታተመው የቢላል መጽሄት በሰጡት ቃለ መጠይቅ መሰረት እድሜያቸው ከ90 ዓመት በላይ እንደሚሆን ገልጸው ነበር፡፡ እኝህ እድሜ ጠገብ አዛውንት ሙሉ ስማቸው ሰኢድ አሊ ሳላህ ይባላል፡፡ የደሴ ከተማ ነዋሪ ‹‹አሊ ባስትኒ›› እያለ ይጠራቸው ነበር፡፡
አሊ ባስትኒ የደሴ ከተማ በተለይም ሙስሊም ማህበረሰብ ያለ ድካምና መሰልቸት ከ50 ዓመታት በላይ በረመዳን የጾም ወቅት ለሊት ለሊት ዱቤ በመምታት ከእንቅልፉ እየቀሰቀሱ ስሁር እንዲያደርግ (የጾም ማሰሪያ ምግብ እንዲበላ) ሲያደርጉ የኖሩ አባት ነበሩ፡፡ ይህን በጎ ተግባር ከመጀመራቸው በፊት ፓስቲ ይሸጡ ስለነበር ነው ‹‹አሊ ፓስትኒ›› የተባሉት፡፡ ሸህ ሰኢድ ሂልባ የተባለ የየመን ተወላጅ ከሳቸው በፊት ይህን ተግባር ይከውን እንደነበር በሂወት እያሉ ጠቅሰው ሸሁ በአእምሮ ህመም ምክንያት ወደ ሀገሩ የመን በመመለሱ ሌሎች በጊዜው የነበሩ አረቦች መርጠዋቸው በደስታ ስራውን እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡
ታዲያ በነዛ ጊዜያት ብርድም ሆነ ዝናብ ወይም ሌላ ነገር ሳይበግራቸው ህዝበ ሙስሊሙን ቀስቅሰዋል፡፡ ለዚያውም ሳያስሩ በፊት፡፡ ለምን ቀድመው አያስሩም? ሲባሉ ‹‹ሆድ ከሞላማ ህዝብ ይረሳል›› ይሉ ነበር፡፡
የምትሽከረከር ሰአታቸው በተቀጠረችበት መሰረት ልክ ከለሊቱ 8 ሰዓት ላይ ‹‹ቅቅቅ...ቅቅቅ..ቅቅቅ..›› ስትል ከእንቅልፋቸው ይነሱና በመጀመሪያ ካሏቸው ሁለት (አረንጓዴና ጥቁር) ካቦርቶች አንዱን ይለብሳሉ፤ከዛ ጥምጣማቸውን እንደተለመደው ሳይሆን ከላይ ወደ ታች ይጠመጥማሉ፤ዱላቸውን ይይዛሉ፤ዱቤያቸውን ካዘሉ በኋላ ባትሪ ይይዙና ከቤት ይወጣሉ፡፡ ከዛም ‹‹ተሳሀሩ…ስሁር…ስሁር..›› በማለት ከለሊቱ 8 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ድረስ በቻሉት መጠን ብዙ ሰፈር በመዞር ሙስሊሙን ሲቀሰቅሱ ይቆያሉ፡፡ ውሻና ጅብ ይከተሏቸው ነበር ሲሉ ቤተሰባቸው ያስታውሳሉ፡፡ ይህን በጎ ተግባር ሲሰሩም ችግሮች አላጧቸውም ነበር፡፡ ሰዓት እላፊ ተብሎ ታስረው እንደነበር የሚናገሩት ቤተሰቦቻቸው ኋላ ላይ ልዩ የፍቃድ መታወቂያ ተዘጋጅቶ እንደተሰጣቸው ያስታውሳሉ፡፡
አሊ ባስትኒ በእድሜያቸው መግፋት ወገባቸው ጎብጦ እንኳ በቀናኢ ስብእና ህዝብ ሲያገለግሉ የኖሩ የጽናት ተምሳሌት ነበሩ!
E.H

መልካም የረመዷን ፆም ይሁንልን❤️
@Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስኪ ይሁን የወደፊቱን እናየዋለን ብየ ያለፉ ፓስቶች ጠፍተዋል፡፡ አልተግብባባንም ሁሉም በሂደት በበሩ በደጁ ሲደርስ ማርፈዱ ገብቶት ጭማሪ ደቂቃ ላይ ይጮሀል
የገጠር እና የከተሜዉ ሰዉ
(በአሚር ሰይድ)

ፊት የቀደመን ወፍ ይበለዋል
የተናገረን ሰዉ ይጠለዋል

..እህል ተዘርቶ እሸቱ ሲደርስ ከሰዉ በፊት ወፍ ይበለዋል ለዛ መሰለኝ ገበሬዉ ማሳዉ ላይ ወንጭፍ ይዞ የሚጠብቀዉ ..በዛዉ ቁጥር ሀቅ እዉነትን የተናገረ ሰዉ ማንኛዉም ሰዉ ይጠለዋል እዉነት መሆኑን የሚያቀዉ አንድ ቀን እራሱ እዉነት ሲናገር እዉነት ማዳመጥ እና አላምጦ መዋጥ ሲያቅታቸዉ ሲመለከት ሰዉ እዉነታን ይሄን ያህል መቀበል አቅቶታል ማለት ነዉ ? ብሎ ያስተነትናል
እኔ የሚያምርብኝ ቀጥታ ቁምነገር መናገር ሳይሆን ልብወለድና እዉነተኛ ታሪክ መፃፍ... በቀልድ አዋዝቶ እዉነቱን መንገር መሰለኝ..እስኪ ስለአንድ የጥንት አያቴ ታሪክ ጀባ ልበላችሁ

የማንክደዉ ሀቅ አለ ማንኛዉም የከተማ ልጅ ነን ከኛ በላይ አራዳ ነን ብለን እራሳችንን አግዝፈን የተመለከትን በአባቱ ወይ በአያቱ ወይ በቅድመ አያቱ የገጠር ልጅ መሆናችንን ዘንግተንዋል፡፡
እናም አያቴ እንደዛሬዉ ትምህርት ቤቶች ባልበዙበት በደርግ ዘመን መሰረተ ትምህርት ተብሎ ብዙ አያቶቻችን ሲማሩ ሒሳብ ትምህርት ዘንድሮ እኛን እንደከበደን አያቶቻችንንም ከብዷቸዉ ነበር፡፡ የአያቶቻችን ትምህርት ሒሳብ ሁኖ መደመር እና መቀነስ ነበር...መምህሩም 1+1=2 ነዉ ቢል ከዚህ ላይ ይሄ ቢቀነስ ይሄ ይመጣል ቢላቸዉ ሊገባቸዉ አልቻለም፡፡
ሒሳብ መምህሩ አያቴን በምሳሌ ለማስረዳት ፈልጎ እቤት ባለዉ በሚያቁት ይጠይቃቸዋል፡፡

አያቴ ተነሱ
መምህር :- እስኪ ጥያቄየን አዳምጡኝ...መኖሪያ ቤት እንጀራ ጋገርሽ ከዛ ሌላ አንድ ጋግረሽ ብጨምሪበት ስንት ይሆናል???
አያቴ ፡- ይሄማ ቀላል ጥያቄ ነዉ አንድ እንጀራ ላይ አንድ ሌላ ቢጨመር አነባበሮ ይሆናል ብለዉ እርፍ(አነባበሮ ማለት ሁለት ወፍራም እንጀራ በአንድ ላይ ሁኖ ዘይት ቅቤ ተለቅልቆ የሚበላ ማለት ነዉ)
የዚህን ጊዜ አያቴ ጋር አብሮ የሚማሩ ጓደኞቿ ልክ ናት ልክ ናት ብለዉ በጭብጨባ አቀለጡት
መምህሩም በመናደድ መደመር እንዲህ ከሆነ እስኪ ስለመቀነስ ልጠይቃቸዉ ብሎ በማሰብ
መምህር :- እሺ አንድ እንጀራ ላይ አንድ ሲጨመር አነባበሮ ብለሽኛል፡፡ እናንተ ቤት ስንት በግ አሉ?
አያቴ :- አስር በግ አሉ
መምህር ፡- ከአስሩ በግ አንዱ ቢሄድ ስንት ይቀራሉ
አያቴ :- እንዴ አንዱማ ከሄደ ሁሉም ይሄዳሉ
መምህር ፡- እንዴት? ከአስሩ በግ አንዱ ከሄደ ዘጠኝ ይቀራሉ ማለት ነዉ ሲል
አያቴ ፡- ተዉ እንጂ መምህር የበጎቼን ፀባይ እኔ ነኝ የማቀዉ ከአስሩ በጎች አንዱ ከሄደ ዘጡኙም ተከትለዉ ነዉ የሚሆዱት ብለዉ☺️ ሲመልሱ እንዳለ የሚማረዉ እዉነት እዉነት ነዉ ብለዉ በጭብጫቦ አረጋገጡ፡፡ ሆነም ቀረ ያልተማረዉ አያቴ ተምሮ ሊያስተምረዉ የመጣዉን መምህር በዚህ ሁኔታ አሸነፉ እላችሆለሁ ፡፡ የአያቴ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል ግን ከአያቴ ትምህርት መዉሰድ ያለብን አለ፡፡ ዲነል ኢስላም በመደመር እና በመቀነስ መካከል ያለዉን ክፍተት ከአያቴ ታሪክ ቀንጨብ ላድርግ
☞አንድ እንጀራ ላይ አንድ ሲጨመር አነባበሮ ይሆናል ብለዋል፡፡ እዉነት ነዉ እስልምናም አንድ ላይ ሲሆን ብርታት ነዉ ጥንካሬ ነዉ ሀይል ነዉ እናም ልዩነትን በማጠበብ አንድ መሆን ሳይነኩ ያስከብራል ..
☞ከአስር በግ አንዱ ሲሄድ ዘጠኝ አይቀሩም የበጎቼን ባህሪ እኔ ነኝ የማቀዉ ሁሌም ይሄዳሉ ..ትክክል ሙስሊም በሚያለያየዉም በማያለያየዉም በራሱ አረማመድ እሄዳለሁ ካለ አንዱ ከመስመር ከወጣ ብዙ ሰዉ ይዞ አብሮ እንደሚወጣ ማወቅ አለብን ...እናም የበግ መጨረሻዉ ያዉ ለመበላት ነዉ፡፡ በየአቅጣጫዉ በዉሸት በተወናበደ ወሬ ተወናብደን አንድ ላይ የሆነዉን በሂደት ሁሉም ነዉ የሚሄዱት እንደተባለዉ የምንሄድ አንሁን
ነገር ግን ይሄ ሀሉ ጥፋት አያቴን ያስተማረዉ መምህሩ ሊሆን ይችላል ፡፡ ለምን እስኪ ይቺን ግጥም ጀባ ልበላችሁ
በቀንም በማታም በጎች ከተበሉ
ቀበሮውን ሳይሆን እረኛውን ፍሩ"
ተብሎ ተገጥሟል ፡፡ ሙስሊም አንድነት እንዳይኖር ያደረገን ማን ነዉ??ቀበሮዉ ማን ነዉ እረኛዉ ማን ነዉ??
በፊት እረኛችን መጅሊስ ቀበሮዎች ደግሞ መጅሊስ እዉን እንዳይሆን እንዳይሳካ የሚጥሩ ናቸዉ፡፡ አሁን ግን ቀበሮዉም እረኛዉም አንድ ላይ ሁኖ ሙስሊም በቀንም በማታም መብቱን ማስከበር አቅቶት የበይ ተመልካች ሁኗል፡፡

የሙስሊሙ ጉዳይ ከአንጀት የሚያስለቅስና በጥርስ የሚያስቅ ሁኔታ የፈተናዎችን ብዛትና ብርታት የመቋቋም ማህበረሰባዊ የስነ_ልቦና አቅም ከተዳከመ የፊተኛዉ ሗላ፣የቀኙ ግራ ሆኖ መድህኑ የራቀ ይሆንና "ሙስሊም ሁኖ" እያለ የሌለ የመሆን እጣ ፈንታ ይገጥመናል፡፡
አላህ ሆይ ድረስልን ለሌላ ነግረን የምናሳካዉ አይደለምና....

For any comment👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ታላቅ_የምረቃ_ፕሮግራም

በደሴ ከተማ በመርከዘል አቅሷ የወንዶችና የሴቶች የተህፊዝ ማዕከል
የመጀመሪያ ዙር የሚካሄድ የሂፍዝ የምረቃ ፕሮግራም።

ኢቅረዑል ቁርዐነ ፈኢነሁ የዕቲ የውመልቂያማ ሸፊአን ሊአስሀቢሂ

መርከዘል አቅሷ የወንዶችና የሴቶች የቁርአን የሂፍዝ ማዕከል 29 ወንዶችንና 28 ሴቶችን በድምሩ 57 የቁርአን ሀፊዞችን በተከበረውና የአላህ ቃል የሆነው ቁርአን በወረደበት የረመዷን ወር የመጀመሪያ ዙር ተመራቂዎችን ታላላቅ መሻኢኾችና ጥሪ የተደረገላቸው እንጎዶች በተገኙበት በደሴ ከተማ በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ በአላህ ፍቃድ ለማስመረቅ ዝግጅቱን አጠናቆ ጨርሷል ።
በእለቱ ከሚቀርቡ ፕሮግራሞች በአጭሩ
ከፊቂህ
ከአቂዳ
ከሀድስ
ከተጅዊድና ከመሳሰሉት የተውጣጡ ለህፃናት አዝናኝና አስተማሪ እንድሁም ለእርሰዎ እውቀት ቀስመውና ራስዎን ፈትሸው የሚሄዱበት ታላቅ የምረቃ ፕሮግራም ይካሄዳል።

🔹 በመሆኑም ረመዳን 13 ሚያዚያ 17 ነገ እሁድ ከጧቱ 2:15 ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ቁርአንን አክብራችሁ ለተመራቂዎች የደስታ ተካፋይና የፕሮግራሙ ታዳሚ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት ጠርተንዎታል።

💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰዓዳ ጀማል ከስልጤ ዞን ወራቤ ሃይራንዚ ትምህርት ቤት በዘንድሮው የ12 ክፍል 650 በማምጣት ከኢትዮጵያ ሴት ተማሪዎች አሸናፊ ሆናለች። ውጤቱም የጠበኩት ነበር ስትልም ገልፃለች።

አኮራሽን ሰአዳ ጀማል👍 ሴቶች ትምህርት ቤት ሂደን እንማረን ካላችሁ አይቀር እንደ ሰአዳ ጀማል ካልሆነ እቤት ሁነሽ እናትሽን በስራ ብታግዥ ይሻላል😊

💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም
(አሚር ሰይድ)


እስኪ አንድ እዉነተኛ ታሪክ ልንገራችሁ

እስኪ ወደ ልጅነታችን ከአራት እስከ አስር እድሜያችን ወደሆሊት እንሂድ እስኪ የዛን ጊዜ በግዴታ ቁርአን ቅሩ በምንባልበት ጊዜ ፡፡ መቼም ከስንት አንዳችን ካልሆነ በቀር ቁርአን ለመቅራት ተነሳስተን በልጅነታችን የቀራነዉ እንጂ በእናት በአባት ሀይል ቁርአን እንደቀራን የማይካድ ሀቅ ነዉ ቤተሰቦቻችን አላህ እድሜ ይስጥልን ..የሞቱም ካሉ አላህ ጀነተል ፊርዶስን ይወፍቃቸዉና፡፡

እናም በልጅነት ቁርአን ተሰብስበን እየቀራን እያለን ሸሀችን ያቀሩንንና በሉ ከርሩ ትሰማላችሁ ብለዉ ወደ ዉጭ ሲወጡ ሁላችንም እያወራን እየተጫወትን በመሀል እኛን ለመሰለል ሸሀችን ሲመጡ..አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም ቢስሚላሂ ረህማን ረሂም ብለን እሳቸዉ ከወጡ ቡሀላ የቀራን ለመምሰል እንሞክራለን ..ታዳ እኛ አንድ ጁዝ ላይ የሙጥኝ ብለን ለዉጥ ማምጣት አልቻልንም ነበር

አንድ ቀን እንደተለመዉ ሸሀችን አቅርተዉን ወደ ዉጭ ሲወጡ እኛም ስንጫወት ሳናስበዉ ሸሀችን መጡብን እኛም በድንጋጤ ብዙዎቻችን ልጆች ቁርአን የቀራን ለማስመሰል አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም ብለን እንደተለመደዉ ለማስመሰል ልንቀራ ስንል
ሸሀችን በመናደድ ቆይ እስኪ እናንተ ልጆች ሁሌ ስገባ አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧኒረጅም የምትሉት እኔ ሸይጧን ሆንኩባችሁ እንዴ?? እኔ ለእናንተ ሸይጧን ነኝ ማለት ነዉ ??ያአሏህ ሁሌ ስገባ ተደጋገመ እኮ ተናገሩ ብያለሁ ዛሬ አንላቀቅም እኔ ሁሌ ስገባ ሸይጧን የገባሁባችሁ ይመስል አኡዙቢላህ የምትሉት ተብለን እኛም መልስ አጥተን ግማሹ እንደ መሳቅ 😄ግማሹ እንደመደንገጥ አድርጎን ሁላችንም ቁርአን ቤት ያለነዉ ልጆች ተገረፍን እላችሆለሁ፡፡
መቼም መድረሳ ቁርአን የቀራ ብትሩን ባይቀምስም የሚያቀሩት ሲወጡ ከርሩ የተባለዉን ትቶ ወሬ እያወሩ ቁርአን የሚያቀራን ሲያየን ለማስመሰል እንጥራለን ለምን ልጅነት ስለሆነ ነዉ.........

#ከዚህ_እዉነተኛ_ታሪክ_ከእንክርዳድ_መሀል_ስንዴዉ_ሲወጣ
☞እስኪ እንሰበዉ የልጅነት አልፏል አሁን በአለንበት ደረጃ አንድ ሰዉ እኛን የሚያስተምርን አለ ወይም መስጊድ ደአዋ አዳምጠን ይሆናል ወይም በተለያዩ ሚዲያ በtv መስኮቶች ደአዋ አዳምጠን ይሆናል ከዛ አዳምጠን ስንጨርስ ወደ ተግባር የምንቀይር አለ ወይ ?? ወይስ እንደ ልጆቹ ሰዉየዉ ወይ ዳኢዉ አስተማሪዉ ሲመጣ አኡዙቢላሂ ብሎ መደንገጡ ይሻላል ወይ??
☞ልጆቹስ ሸሀቸዉ ልጅ ስለሆኑ ከአሁን ቡሀላ እንዳይለመዳችሁ ብለዉ ገረፍዉ አስጠነቀቋቸዉ...አሁን በእዚህ እድሜያችን እያስተማሩን እያስጠነቀቁን እንደ ልጆቹ አኡዙቢላህ በዱላ ይስተካከላል ወይ?? ነገ ከነገ ወዳ አያማክሬ ፈጥኖ ደራሽ ሞት ሲመጣ የተማርነዉን ሳንተገብር ከሄድን ከሳሪዎች አይደለን እንዴ??
☞ከእኔ ጀምሮ ከእናንተ የባስኩ ስለሆንኩ ዲነል ኢስላምን ለማወቅ የምፈልገዉ በሚዲያ ፣በማህበራዊ ገፆች፣ሙስሊምን ያዳከሙ ኢስላማዊ ፊልሞች ድራማዎች ፣ ታላቅ ዝግጅት ተብሎ ወንድ ለብቻዉ ሴት ለብቻዉ ተብሎ በወንበር ልዩነት ተቀምጦ አጂ ነብይ እየተያየ እየተዝናናን ወዘተ ዲነል ኢስላምን ማወቅ መረዳት እንፈልጋለን ግን በትክክል አዉቂያለሁ እንዴ??? ብላችሁ እራሳችሁን ፈትሸን እናቃለን???
አሁን ላይ ያለዉ ትዉልድ ፈታ በል አቦ= ዘና በል አቦ የምን መጨናነቅ ነዉ..ወደድንም ጠላን አይቀርም ሞት የሚል ማህበረሰብ ዉስጥ ነን......አዉ ሞት እንደሆነ አይቀርም ግን አሟሟቱ እንጂ፡፡ አንዱ ሽንት ቤት ገብቶ ይሞታል ....ዘመዱ በአሟሟቱ አዝኖ ከሞቱ አሟሟቱ አር ጠጥቶ መሞቱ ብሏል...ታዳ ሞትም የክብር ሞት አለዉ መቼ ነዉ ተዉሂድን ቀርተን አዉቀን በተዉሂድ መንገድ ለመሞት ዝግጅት ያረግነዉ??
አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ ከኔ ጀምሮ ተዉሂድ ተዉሂድ ስንማር ለማዳመጥ እንኳ ፍቃደኛ ሳንሆን ተዉ_ሂድ የተባልን ይመስል ለመስማት እንኳ ፍቃደኛ አንሆንም ፡፡ ዉዶቼ እኛም ይሄን ባህሪያችንን አስተካክለን መጥፎ አመለካከት አስወግደን አኡዙቢላሂ ብለን ኢብሊስን አባረን በኢስላም የምኖር በኢስላም አላህ ፊት ለመገናኘት ቆርጠን እንነሳ
☞እስኪ እኔ ነኝ ወይ ሸይጧን የሆንኩባችሁ ? ሁሉ ስገባ አኡዚቢላህ የምትሉት ያሉት ሸሀችን ጋርም ስህተት ሊኖር ይችላል እኮ ...አሁን ላይ የምናያቸዉ ኡስታዞች ሲያስተምሩ እንዴት ነዉ ሰዉን በሚስብ መልኩ ነዉ ወይስ ሰዉን በሚያባርር መልኩ?? አሁን ላይ አንዳንድ ሰዎች ከኛ በላይ ዲነል ኢስላምን የሚያቅ የለም ብለዉ ሌላዉን እነሱ እንደተመቻቸዉ የቡድን ስም ሲሰጡ እያየን ነዉ፡፡ በፊት የነበሩት ትዉልዶች በዲን ዙሪያ ሲወያዩ በልባቸዉ ነይተዉ የሚወያዩት ...ከምወያየዉ ወንድሜ ጋር ሀቅ ኑሮ እኔ የምቀበል ያድረገኝ ብለዉ ነይተዉ ነበር፡፡ አሁን ዘመን ላይ እንኳን ከምከራከረዉ የአኼራ ወንድሜ ጋር እዉነት ይኖረዋል ብሎ ያስብ ይቅርና የኔ ብቻ እዉነት ነዉ ብሎ የሚሞግት ከቁርአን ከሀዲስ ማስረጃ ቢያቀርቡለት እንኳ ላለማመን ሌላ ምክንያት የሚፈጥር ስኳር ጨዉ ዱቄት እየተለያዩ ነገር ግን አንድ የጋራ ባህሪ አላቸዉ ነጭ መሆናቸዉ ብሎ ላለማመን በተመሳሳይ ማሳመን ጋር የተካነ ትዉልድ ብቅ ብቅ እያሉ ነዉ...
አላህ ሆይ ከሽርክ ከቢዳአ ተከታይ እና በስሜት ተጓዥ ባሪያዎችህን ልቦና ሰጠህ በተዉሂድ በሱና በአንድ በሰለፎች መንገድ ኑረን የምንሞት አድርገን...ማርታህ እዝነትህ ከቁጣህ ይቀድማልና በእኛ ጥሩ ኸይር ስራ ሳይሆን በማርታህ በእዝነትህ ጀነተል ፊርዶስን ወፍቀን.
ረመዷንን ፁመዉ ተራቡ ከዛም ከሰሩ ከተባሉት ሳይሆን ፁመዉ እኔ ያዘጋጀሁለትን የረመዷን ሽልማት ያገኛሉ ከተባሉ ባሪያዉቹ አድርገን
አሜን አሜን አሜን

መልካም ረመዳን ❤️


💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የወሎ እንቁዎቹ ደሴና ኮምቦልቻ ዛሬ በኢፍጣር ደምቀው ያመሻሉ !! ሁለቱም ከተሞች በተመሳሳይ ሰአት ይደምቃሉ !!
የ"እኔ እያለሁ ወገኔ አይራብም" የኮምቦልቻና አካባቢዋ ቲም ዛሬ በኮምቦልቻው ኢፍጣር ላይ ለተፈናቃይ ወገኖቻችን ገቢ ማሰባሰብ ይሰራል !!
#እኛ ጠግበን ወገኖቻችን እንዳይራቡ
#እኛ ጠጥተን ዘመዶቻችን እንዳይጠሙ
# እኛ ለብሰን ነሰቦቻችን እንዳይታረዙ
የሁላችሁንም እጅ መዘርጋት ይጠብቃሉና ከቤት ስትወጡ እያሰባችኋቸውና እያሰባችሁላቸው እንድትመጡ እንላለን !!
" # እኔ -እያለሁ-ወገኔ-አይራብም!!"

ባለፈዉ ከሚሴ ደምቀዉበታል ዛሬ በደሴና ኮምቦልቻ ሙስሊም አንድ መሆኑን ያሳያል፡፡
በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ ዙሪያ ያላችሁ ደሴ ወይ ኮምቦልቻ መጥታችሁ ከማዳችን እንድትክፋሉ ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡

በደሴ ያላችሁ ትናንትና በአረብ ገንዳ መስጊድ ወጣቶች ስብሰባ የስራ ስምሪት ስለተሰጠ አሱርን አረብ ገንዳ ስግደን ሁሉም ወደ ስምሪቱ

ደምቆ ለመታየት የተወሰኑ ሰአታት ቀርተዉናል😍

💐___⭐️______💐______⭐️_____💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ወሎ_ደሴ
#Wollo_Dessie
አይጠየፍ ሁኖ ይታያል ከሚሴ
ፎንቃ ያልገባው ሰው ምን ያረጋል ደሴ
የተባለላት የጦሳ ስር ሙሽራዬ ዛሬ ደስ በሚል መልኩ አፈጠረች

ሙስሊሞች ሲሰበሰቡ የሚጨንቀዉ ሰዉ አለ
እኛ ከሰላምታችን ጀምሮ ሰላምን እናስቀድማለን
ጌታችንም ሰላም ነዉ ሰላምም ከርሱ ነዉ
ከተማዬ አምሮባት በአንድነት ስናፈጥር
አልሀምዱሊላህ የጎዳና ላይ ፊጥራችን እንደምታዮት ውብ በሆነ መልኩ ተፈጥሯል
ለዚህ ፕሮግራም መሳካት በሁሉ ነገር ለተባበራችሁ አላህ በዱንያም በአኼራም ያስደስታችሁ
ያረቢ ምን ይሳንሃል አልሃምዱሊላህ!!
ዝናቡስ አትልም? ቀጥ መገን ጀሊሉ
ከሁሉ ደስ የሚለዉ ደግሞ ከተፈጠረ ቡሀላ ሁሉንም አንድ ሳይቀር ቆሻሻዉ በአፍጣሪዉ መሰብሰቡ ነዉ

በደሴ ከተማ የተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም በትንሹ ይሄን ይመስላል።
# ደሴ # Dessie # ኢፍጣር 1442 ዓ.ሂ/ 2013
ሙሉ ቪዲዮዉን በአጭር ጊዜ ይጠብቁ።

💢።።።።።።ᴛᴇʟᴇɢƦᴀᴍ።።።።።።።💢
⭕️ @ne_siha_eslamik ⭕️
💢።።።።።።ᴛᴇʟᴇɢƦᴀᴍ።።።።።።💢
2024/09/23 08:21:17
Back to Top
HTML Embed Code: