Telegram Web Link
12/04/2017

"የአሁኑ ትውልድ እኛን በጣም ይበልጠናል።" የህግ ባለሙያ እንዲሁም አንጋፋ የጥበብ ሰው አበበ ባልቻ።

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ ክበብ(rvc) በዛሬው እለት አንጋፋውን ሁለገብ የጥበብ ሰው እንዲሁም የህግ ባለሙያ አበበ ባልቻን በመጋበዝ ደማቅ የህይወት ልምድ ተሞክሮ መርሃግብር አካሂዷል።

በመርሃግብሩ የተገኙት የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ"የኛ ትውልድ ይበልጣል በማለት ፋንታ አሁን ላለው ትውልድ ቅድሚያ ሰጥተው የአሁኑ ትውልድ እኛን ይበልጠናል በማለት የአሁኑን ትውልድ ማድነቅ መቻል ለትውልዱ ትልቅ የሚያበረታ ንግግር ነው" ሲሉ ለአንጋፋው የጥበብ ሰው አበበ ባልቻ ያላቸው ክብር እና ምስጋና ገልጸዋል ።

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የውጭ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እመቤት በቀለ "አርአያ ከሚሆኑ የሃገራችን አንጋፋ የጥበብ ሰው መካከል አንዱ ማሳያ ነዎት" በማለት በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክታቸውን ገልፀዋል ።

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ዲን አቶ አስማማው ደምሴ እንዲሁም የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ ተግባቦት ትምህርት ክፍል ዲን አቶ እያዩ አለማየሁ በመርሃግብሩ ተገኝተውበታል።

ተውኔት ፣የድራማ ዳሰሳ፣ ሙዚቃ እና ግጥም በክበቡ አባላት የቀረበ ሲሆን ተጋባዥ እንግዳው "የአሁኑ ትውልድ እኛን ይበልጠናል።" በማለት በቀረበው ስራ መደሰቱን ገልጿል።

በመርሃግብሩ የተሳተፉ ተማሪዎች ለተጋባዥ እንግዳው ጥያቄ በማንሳት እና ሞራል በመስጠት ያላቸውን ፍቅር እና ደስታ አሳይተዋል።

እንደ rvc በነበረን ቆይታ በጣም ተደስተናል። በመርሃግብሩ ለተሳተፋችሁ በሙሉ ስላብሮነታችሁ ክብረት ይስጥልን 🙏
1👍1👏1
2025/07/12 13:36:38
Back to Top
HTML Embed Code: