Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
[ "እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ": "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ" ]
† 🕊 አቡነ አቢብ [ አባ ቡላ ] 🕊 †
ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን!
- እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል !
- ቅዱሱ አባታችን :- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::
- ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::
- እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::
- አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!
- ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!
- ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ!
- የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::
† ልደት †
አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::
በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"
† ጥምቀት †
ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ ፩ ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::
ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::
† ሰማዕትነት †
የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ፲ ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር ፯ ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ፲ ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::
በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ ፲፰ ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::
† ገዳማዊ ሕይወት †
ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::
ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::
† ተጋድሎ †
አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::
በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ፵፪ ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::
የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ [ሃቢብ] ይሁን" አለው::
"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::
† ዕረፍት †
አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ፲ ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::
ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ ፫ ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::
† 🕊 ታላቁ አባ ዕብሎይ 🕊 †
ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ [የካቲት ፫ ቀን] እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::
† 🕊 ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት 🕊 †
ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ [አድናቆት]: ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት [በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ] ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ እንኩዋን የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ - የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: [መዝ.፸፰፥፫]
እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና ፫ መቶ አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::
በወቅቱ የክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር::
በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::

ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር::+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::
ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ:: በተአምሩም መኮንኑና ሠራዊቱ አምነው ተከተሉት::
በፍጻሜውም በሌላ ሃገር መኮንኑ ቅዱስ ዮልዮስን ከቤተሰቡና ከ፩ ሺህ ፭ መቶ ያህል ተከታዮቹ ጋር: ፪ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል::
አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት በቃል ኪዳናቸው እንዲምረን ቸርነቱ ይርዳን:: በረከታቸውንም አትርፎ ይስጠን::
🕊
[ † ጥቅምት ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ]
፪. አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
፫. ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
፬. ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
፭. ቅዱሳን አሞኒና ሙስያ [የታላቁ ዕብሎ ወላጆች]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
፮. ታላቁ አባ ቢጻርዮን
" እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: " [ማቴ.፲፮፥፳፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

Forwarded from M.A
✝ቅዱስ አባታችን አቡነ ሕፃን ሞዐ
✝ አባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ።
✝ ለአቡነ ተክለሃይማኖት የአጎት ልጅ።
✝በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ስማዕትነትን የተቀበሉ።
✝ ከበሬ ጋር ተጠምደው ውለው ደክሟቸው በኃይል የተነፈሱበት ምድሪቱ አሁንም የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች ያም ለአስም በሽታ መድኃኒትነው።
✝ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ቀን ነው።
<<የአቡነ ሕፃን ሞዐ በረከታቸው ይደርብን በቃልኪዳናቸው ይማረን።>>
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

በ25 የሚጸለይ
☞ከመዝ በሉ፦
. . . ይቤ . . .
በስምየ ወበስመ አቢብ ገብርየ፤
አኃድግ ሎቱ ዘገብረ ጌጋየ
!https://www.tg-me.com/zikirekdusn
☞ከመዝ በሉ፦
. . . ይቤ . . .
በስምየ ወበስመ አቢብ ገብርየ፤
አኃድግ ሎቱ ዘገብረ ጌጋየ
!https://www.tg-me.com/zikirekdusn
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን
❖ ጥቅምት ፳፮ [ 26 ] ❖
[ † እንኩዋን ለሐዋርያት "ቅዱስ ያዕቆብ" እና
"ቅዱስ ጢሞና" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም
አደረሳችሁ † ]
† 🕊 ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ 🕊 †
ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በአባቶቻችን ሐዋርያት መካከል ትልቅ ሞገስ የነበረውና የጌታችን ወንድም ተብሎ የተጠራ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ አባቱ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ [የእመቤታችን ጠባቂ] ሲሆን በልጅነቱ ጥላው የሞተች እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች:: በቤት ውስጥም ስምዖን ዮሳና ይሁዳ የተባሉ ወንድሞችና ሰሎሜ የምትባል እህትም ነበረችው::
እናቱ ማርያም ከሞተች በሁዋላ ዕጉዋለ ማውታ [ደሃ አደግ] ሆኖ ነበር:: ነገር ግን በፈቃደ እግዚአብሔር አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከቤተ መቅደስ ሊጠብቃት [ሊያገለግላት] ተቀብሎ ሲመጣ ያ ቤተሰብ ተቀየረ:: የበረከት የምሕረትና የሰላም እመቤት የአምላክ እናቱ ገብታለችና ያ የሐዘን ቤት ደስታ ሞላው::
እመ ብርሃን ግን ገና ወደ ዮሴፍ ልጆች ስትደርስ አለቀሰች:: የአክስቷ ልጆች የሚንከባከባቸው አጥተው ቆሽሸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ትንሹ ቅዱስ ያዕቆብ ያሳዝን ነበር:: እመ ብርሃን ማረፍ አልፈለገችም:: ወዲያው ማድጋ አንስታ ወደ ምንጭ ወርዳ ውሃ አምጥታ የሕጻኑን ገላ አጠበችው:: [በአምላክ እናት የታጠበ ሰውነት ምስጋና በጸጋ ይገባዋል]
እመቤታችን ጌታ ከመወለዱ በፊት ለ፱ ወራት ከተወለደ በሁዋላ ደግሞ ለ፪ ዓመታት ሕጻኑን ያዕቆብን ተንከባከበችው:: ለ፫ ዓመታት ከ፮ ወራት ግን ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና ተለያዩ:: ከስደት መልስ ግን ለ፳፭ ዓመታት ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ጋር ሲያድግ ወላጅ እናቱ ትዝ ብላው አታውቅም:: አማናዊቷ እናት ከጐኑ ነበረችና::
ሊቃውንት እንደ ነገሩን እመቤታችን ለቅዱስ ያዕቆብ ያልሰጠችው ነገር ቢኖር ሐሊበ ድንግልናዋ [የድንግልና ወተትን] ብቻ ነው:: ስለዚህም :- "እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም ንግሥተ ኩሉ" ይላል መጽሐፍ:: [መልክዐ ስዕል]
ቅዱስ ያዕቆብ "የጌታ ወንድም" ተብሎ በተደጋጋሚ በሐዲስ ኪዳን ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ :-
፩= ለ፴ ዓመታት ሳይነጣጠሉ አብረው በማደጋቸው፡፡
፪= የጌታችን የሥጋ አያቱ የቅድስት ሐና የእህት ልጅ በመሆኑ፡፡
፫= በዮሴፍ በኩልም የአንድ ቅድመ አያት ልጆች በመሆናቸው፡፡
፬= ጌታችን ከትህትናው የተነሳ ደቀ መዛሙርቱን "ወንድሞች" ይላቸው ስለ ነበር ነው:: [ሥጋቸውን ተዋሕዶ ተገኝቷልና]
ራሱ ቅዱስ ያዕቆብ ግን "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ብሎ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ገልጧል:: [ያዕ.፩፥፩]
- ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ሲያስተምር ተከተለው
- ከ፸፪ቱ አርድእት ተቆጠረ
- ፫ ዓመት ከ፫ ወር ወንጌልን ተማረ
- ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንግል ማርያምና ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ሆኖ "የጌታን ትንሳኤ ሳላይ እሕል አልቀምስም" ብሎ ማክፈልን አስተማረ
- መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን አስተማረ
- የኢየሩሳሌም የመጀመሪያው ሊቀ ዻዻስ ሆኖ አገለገለ::
- በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት የሐዋርያት ሲኖዶሶችን በሊቀ መንበርነት መራ
- ሙታንን አስንስቶ: ድውያንን ፈውሶ የመካኖችን ማሕጸን ከፍቶ አጋንንትንም አስወጥቶ ብዙ ተእምራትን ሠራ:: እጅግ ብዙ አይሁዳውያንን ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሶ መልካሙን ገድል ተጋደለ::
በመጨረሻ ዘመኑ ያላመኑ የአይሁድ አለቆች ወደ ቤቱ ተሰብስበው "የናዝሬቱ ኢየሱስ ማነው? የማንስ ልጅ ነው?" ሲሉ ጠየቁት:: እነርሱ ሰይጣን በሰለጠነበት ልቡናቸው "የዮሴፍ ልጅ ነው: የእኔም ወንድሜ ነው" እንዲላቸው ጠብቀው ነበር:: [ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት!]
በልቡናቸው ያሰቡትን ተንኮል የተረዳው ሐዋርያ ወደ ቤቱ ጣራ ወጥቶ መናገር ጀመረ:: "ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ሥግው ቃል እግዚአብሔር ነው:: እኔም ፍጡሩና ባሪያው እንጂ እንደምታስቡት ወንድሙ አይደለሁም" አላቸው::
ንዴታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት አይሁድ ከላይ ወጥተው ወደ መሬት ወረወሩት:: በገድል የተቀጠቀጠ አካሉንም እየተፈራረቁ ደበደቡት:: አንዱ ግን ከእንጨት የተሠራ ትልቅ ገንዳ አምጥቶ የቅዱሱን ራስ ደጋግሞ መታው:: ጭንቅላቱም እንዳልነበር ሆነ:: ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ ወደ ወደደው ክርስቶስ በዚህች ቀን ሔደ::
ቅዱሱ ሐዋርያ ያዕቆብ ቤቱን እንደ ቤተ መቅደስ አበው ሐዋርያት ይጠቀሙባት ነበር:: በመላ ዘመኑ የሚያገድፍ ነገር [ጥሉላት] ቀምሶ ጸጉሩን ተላጭቶ ገላውን ታጥቦና ልብሱን ቀይሮ አያውቅም::
"ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ
ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ
ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ" እንዲል::
ከጾም ከጸሎትና ከመቆሙ ብዛትም እግሩ አብጦ አላራምድህ ብሎት ነበር:: ስለዚህም አበው "ጻድቁ [ገዳማዊው] ሐዋርያ" ይሉታል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ ይባል ዘንድ ካደለው ሐዋርያ በረከትን ያድለን:: በምልጃውም ምሕረትን ይላክልን::
† 🕊 ቅዱስ ጢሞና ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱሱ ሐዋርያ ቁጥሩ ከ፸፪ቱ አርድእትና ከ፯ቱ ዲያቆናት ነው:: በሐዲስ ኪዳን ስማቸው ከተጠቀሰ ሐዋርያትም አንዱ እርሱ ነው:: [ሐዋ.፮፥፮] በትውፊት ትምሕርት እንደ ተማርነው ቅዱስ ጢሞና ጌታችንን የተከተለው በመዋዕለ ስብከቱ ነው::
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል [፲፥፩] ላይ "ወፈነዎሙ በበክልኤቱ" እንዲል ሁለት ሁለት አድርጐ ሲልካቸው ቅዱስ ጢሞና አንዱ ነበር::
በሔዱበትም በስሙ አጋንንት ተገዝተውላቸው: ድውያንም ተፈውሰውላቸው ደስ ብሏቸዋል:: ጌታችን ግን "አጋንንት ስለ ተገዙላችሁ ደስ አይበላችሁ:: ይልቁንስ ስማችሁ በመንግስተ ሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ብሏቸዋል:: [ሉቃ.፲፥፲፯]
ቅዱስ ጢሞና ጌታችንን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: የጌታን ትንሳኤ ተመልክቶ: በዕርገቱ ተባርኮ: በበዓለ ሃምሳም ቅዱስ መንፈሱን ተቀብሎ ከፍጹምነት ደርሷል:: በመጀመሪያው ዘመንም ሐዋርያት አበው ለአገልግሎት ፯ቱን ዲያቆናት ሲመርጡ እርሱን መንፈስ ቅዱስ አብሮ መርጦታል:: [ሐዋ.፮፥፭]
በቅዱስ እስጢፋኖስ ሥር ሆኖም እንደሚገባ አገልግሏል:: ከቅዱስ እስጢፋኖስ መገደል በሁዋላም እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በዓለም ወንጌልን ሲሰብክ ኑሮ በዚህች ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል::
ከበረከቱ ያድለን::
🕊
[ † ጥቅምት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዮሴፍ]
፪. ቅዱስ ጢሞና ሐዋርያ ወዲያቆን
፫. ቅዱስ አግናጥዮስ
፬. ቅዱስ ፊልዾስ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ: ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች:: ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት:: ትዕግስትም ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም:: " [ያዕ.፩፥፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
†
🕊 💖 ቅዱስ ያዕቆብ 💖 🕊
🕊
❝ ከሐዋርያት ጵጵስናን የተቀበለ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሾሙ የቀደመ በሥጋ ዝምድና የጌታችን ወንድም ለኾነ ለያዕቆብ ሰላምታ ይገባል። ❞
[ አቤቱ የሐዋርያት ተከታዮቻቸው ስለኾኑ ስለ ሰባ ኹለቱ አርድእት ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ። ... ስለ እነርሱ ማረኝ ፤ እኔን አገልጋይኽንም በሀገራቸው ውስጥ ከነርሱ ጋር ዕድል ፈንታዬን ጽዋ ተርታዬን አድርግ ፤ አሜን።
[ ተአምኆ ቅዱሳን ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
[ ከመልዕክቱ ]
❝ ወንድሞቼ ሆይ ፥ እምነት አለኝ የሚል ፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል ? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ? . . . እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ ፤ መልካም ታደርጋለህ ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
አንተ ከንቱ ሰው ፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን ? ❞ [ ያዕ . ፪ ፥ ፲፬ ]
🕊
[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
🕊 💖 🕊

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"
ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።
መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?
ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።
ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።
በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።
በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።
አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።
በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን