Forwarded from የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ።
በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው።
1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC #ETHIOPIA
ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦
" የማኅበረሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው።
በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ #በሰላም_ወጥቶ_መግባትም_አጠራጣሪ_ሆኖአል ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡
በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል ? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው። ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል። "
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ኢትዮጵያ
#የግንቦት_ርክበ_ካህናት_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልአተ_ጉባኤ
@tikvahethiopia

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
Forwarded from M.A
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን ##ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_እንድራኒቆስ ለዕረፍቱ በዓል፣ #በደብረ_ምጥማቅ_ለእመቤታችን መገለጥ #ለሁለተኛ_ቀን መታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከምሥራቃዊ_ከቅዱስ_ያዕቆብ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_እንድራኒቆስ፦ ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።
❤ በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 22 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ሰላም_ለእንድራኒቆስ ዕብሎ። ውኂዝ መንፈስ ዘሰትየ ምስለ ሐዋርያት በአመ ድብሎ። ኀበ ሖረ ይስብክ አህጉራተ አድያም ኵሎ። አብያተ ክርስቲያን ሐኒፆ ወአብያተ ጣዖት አንሒሎ። ዕሴተ ተስፋሁ አድምዐ በሰማይ ዘሀሎ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_22።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በትርከ ወቀስታምከ አማንቱ ገሠፀኒ። ወሠራዕከ ማእደ በቅሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ"። መዝ 22፥4-5 የሚነበበው ወንጌል 27፥27-31።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 16፥6-10፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21-15-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ እንድራኒቆስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊
(ማቴ ፫:፫)
✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨
🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም።
⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።
🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን።
⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት።
🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ"
⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።
🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።
✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
ትምህርተ ሃይማኖት (አዕማደ ምሥጢር)

“ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን? እንኪያስ በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
Forwarded from Bketa @¥
ደብረ ምጥማቅ
እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም፤ ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል፤ አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።
ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል፤ ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው
ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል፤ ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ፤ ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።
እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች፤ ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል፤ እንዲህም 5 ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝✞✝ ወበዛቲ ዕለት ተወልደ አብ ክቡር አረጋዊ፡ ወሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፡፡ በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ታዴዎስ ተወለዱ ✝✞✝
✝ #አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽ ✝
✝ትውልድ ሀገራቸው ጽላልሽ (ዞረሬ) ነው። አባታቸው ሮማንዮስ እናታቸው ማርታ ይባላሉ። አባታቸው ሮማንዮስ ቄስ ነው። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት ናቸው።
በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ በጽላልሽ ረሀብ ፀንቶ ነበር። እሳቸው ግንቦት ፳፫ ቀን በመንፈቀ ሌሊት በልብሰ ብርሃን ተጠቅልለው ተወለዱ። ቤታቸው በበረከት ተመላ። ለሀገሬው ዝናብ ዘንቦለት ህዝቡ ከፃድቁ እናትና አባት የተመፀወቱትን ከፍለው ዘሩ።
አቡነ ታዴዎስ በተወለዱ በ፵ ቀናቸው ሐምሌ ፪ ቀን ሲጠመቁ የተዘራው እህል አንድ ሳይቀር አፍርቶ ተገኝቷል።
ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ ሰጥተዋቸው ሲማሩ አደጉ። አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት (ወላይታ) ተሻግረው መተሎሚን አስተምረው “በእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ፀሎት መተሎሚን በሃይማኖት ወልጄዋለሁ። በምግባር አሳድጌዋለሁና እህትህን ይዘህ በቶሎ ና፤” ብለው ላኩባቸው።
እህታቸው ትቤጽዮን ትባላለች። የመተሎሚን ወንድም ዝግናን አግብታ አባ ኤልሳዕን ወልዳለች። ከባሏ ተጣልታ ነበርና እሷን ከባሏ አስታርቀው እሳቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን እያገለገሉ ፱ አመት ኖረዋል።
በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ እሳቸውም ወደ ጽላልሽ ተመልሰው ስለነበር አፄ ይኩኖ አምላክ እንድትመክረኝ እንድትገስፀኝ ከቤቴ ተቀመጥ ብለው ከቤተመንግስት አስቀመጣቸው።
ሰይጣን ለፀብ ለምቀኝነት አያርፍምና ጠላ ቤቷን ክፉ የሚገድል ሽታ አሸተታትና ሞተች። አባ ታዴዎስ ወንዝ ገብተው ሲፀልዩ ሙቷ ተነሥታለች። ከዚህ በኋላ ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል ብለው ወደ ደብረ ሊባኖስ ተመለሱ።
አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ጽጋጋ (ጅጅጋ) ሂድ አሏቸው። ለምን ቢሉ? አባ አኖሬዎስ ሄደው ሲያስተምሩ ያገሬው ሰዎች ደብድበው አስረዋቸው ነበርና እሳቸውን ለማሰወፈታት ነበር።
የአካባቢው ንጉስ መዩጥ ይባላል። በነፋስ ሰረገላ ተጭነው ሄደው ከፊቱ ወርደው ሲቆሙ ደንግጦ ከሰማይ መላእክት ነህ ወይስ ከሰው ወገን? ቢላቸው። እኔ ከሰው ወገን ነኝ አሉት። ክርስትናንም አስተማሩት ጋኔን ከእሳት ላይ ጥሎት ሲሰቃይ የሚኖር ልጅ ነበረው አድነውለታል።
ይህን አይቶ አምኖ ሕዝቡም እንዲያምኑና ክርስትናን እንዲቀበሉ አዋጅ ነገረ።
እንደ ሐዋርያው ታዴዎስ ፳፭ ግመል በመርፌ ቀዳዳ በተአምራት አሳልፈው በማሳየታቸው አፍጃል የሚባል ያንድ ባለጠጋ ልጅ በምትሐት እንደሚያደርጉት አድርጎ በመናገሩ ከግመሎቹ አንዲቱ ረግጣው ሞተ፤ ይህን ሙሳ የሚባል ልጅም በተቀበረ በሦስተኛው ቀን «አልዓዛርን ከሙታን በአስነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ና ተነስ» ብለህ ይህንን መቋሚያዬን ወስደህ ከመቃብሩ ላይ አኑር ብለው በአፍጃል ሰጥተውት እንዳሉት ቢያደርግ አፈፍ ብሎ ተነስቷል።
ይህን አይተው ህዝቡ ሁሉ አምነዋል። ከዚህ በኋላ ሙሳን ሙሴ ብለው ሊቀ ካህናት አድርገው ፲፪ አብያተ ክርስቲያናት አሳንፀው አኖሬዎስን ይዘው ተመልሰዋል።
አቡነ ተክለሃይማኖትም ከንጉሱ ተማክረው ሊቀካህናት ዘጽላልሽ ብለው ሾመዋቸዋል።
ንጉስ ዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አድሮበት የአባቱን ቅምጥ ቢያገባት ሄደው ገሰፁት። በዚህ የተናደደች የንጉሱ ሚስት የኋሊት አሳስራ ከጥልቅ ገደል አሰጣለቻቸው።
በዚህ ጊዜ የመቶ ሃያ አመት አረጋዊ ነበሩ።
የታዘዘ መልአክ ገብረ እግዚአብሔርና ውቢት የተባሉ ደጋግ ሰዎችን አስነስቶ ስጋቸውን ወስደው ከበዓታቸው ቀብረው የተሰጣቸውንም ቃል ኪዳን በዳግማዊ አፄ ዳዊት ዘመን በህዝቡ ፊት መስክረዋል።
ንጉስ ዳዊትም ዜና ገድላቸውን አጽፈዋል፤ ስጋቸውንም ወደ ከተማቸው በክብር አፍልሰው በተቀደሰ ስፍራ አኑረውታል።
የጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!!
(Sisay Poul እንደጻፈው - ነፍሱን ይማር)
ምንጭ ፦ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

Forwarded from ✝️ የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ✝️ (ኆኅተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ
የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።
እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ነበረች ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣለች። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።
በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወገኖቼ ያለኝን ጨርሻለሁ አሁን ላይ ያለኝን ቀሪ ነገር ኩላሊቴን ልስጠው ነውና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሌለው በሃሳብና በጸሎት አግዙኝ ወንድሜን አድኑልኝ ስለፈጣሪ ተባበሩኝ የሰው ህይወት በማዳናችሁ በፈጣሪ ታገኙታላችሁ።
ፍሩታ አሻግሬ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000629004045
ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689