በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፳፭
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ አምስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል የእመቤታችን የአክስቷ ልጅ ብፅዕት ሰሎሜ አረፈች። በዚኽችም ዕለት ጌታችን የደረቁ በትሮችን ያለመለመበት ዕለት ነው፤ ይኸውም የአረገዊ ዮሴፍን በትሮች በአረንጓዴ ቦታ ላይ ቢተክላቸው ወዲያው ዛፎች ሆኑ፡፡ ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን የተቀበሉት አቡነ ሕፃን ሞዐ በዓለ ፅንሰታቸው ነው። ከእንዴና አገር የተገኘው የከበረ ቅዱስ ኮጦሎስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ስብስጣ ከሚባል አገር የተገኘው የከበረ አባ ኄሮዳ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
❖ እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህን አሮን ልጅ ናት፤ ለማጣት ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱ ስም ማርያም ነው የሁለተኛዪቱ ስም ሶፍያ የሦስተኛዪቱም ሐና ነው ይቺም ማርያም ሰሎሜን ወለደቻት ሶፍያም ኤልሳቤጥን ወለደቻት ሐናም አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት።
❖ እመቤታችንም ድንግል ስትሆን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወለደችው ጊዜ ይቺ ቅድስት ሰሎሜ የእመቤታችንን አወላለድ እንደ ሴቶች ሁሉ አወላለድ መስሏት ተጠራጠረች ከዚህም በኋላ የድንግል እመቤታችን ገላዋን ዳሠሠቻት ያን ጊዜ እጇ ተቃጠለ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ደግሞ ዳነች።
❖ በዚህም በኅቱም ድንግልና አምላክን እንደወለደች አወቀች፤ ከተረገመ ኄሮድስ ፊት እመቤታችን በሸሸች ጊዜ ከዮሴፍ ጋራ በመሆን አብራ በመሰደድ የእመቤታችንን ድካሟን ተካፍላ አገለገለቻት ከስደት እስከ ተመለሱ ድረስ ሕፃኑን ታዝለዋለች የምታጥብበትም ጊዜ አለ፤ መድኃኒታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ አልተለየችም በመከራውም ቀን ከእመቤታችን ጋራ ከከበሩ ሁሉ ሴቶች በትምህርቱ ወራት ከተከተሉት ጋራ እያለቀሰች ነበረች።
❖ በተነሣባት ዕለት ወደ መቃብር ገሥግሣ ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት፤ በኃምሳኛውም ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከባልንጆሮቿ የከበሩ ሴቶች ጋራ ሰማያዊ ሀብትን ተቀብላ በክብር ባለቤት መድኃኒታችን ስም ሰበከች ብዙዎችንም አሳመነች፤ ከአይሁድም ብዙ ስድብና ሽሙጥ አገኛት ከዚያም አረፈች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከሁላችን ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አቡነ ሕፃን ሞዐ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፤ የተወለዱት ጥር 25 ነው፤ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው፤ እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡
❖ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፤ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡
❖ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፤ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፤ ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፤ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡
❖ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፤ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፤ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፤ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ሰማዕቱ ቅዱስ ኮጦሎስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ የዚኽም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸውና ጌታችንን ልጅ እንዲሰጣቸው አጥብቀው ከለመኑትና እርሱም የተባረከ ልጅ ከሰጣቸው በኋላ ልጃቸውን በሃይማኖት በምግባር አሳደጉት፡፡
❖ አባቱም የእንዴናው ገዥ መኮንን ነው፤ጨቅዱስ ኮጦሎስም ለራሱ ሥርዓትን በመሥራት በቀን አንድ መቶ በሌሊትም አንድ መቶ ጸሎታትን ይጸልያል፤ ዕድሜውም በደረሰ ጊዜ ወላጆቹ ሊያጋቡት ሲሹ እርሱ ግን እምቢ አላቸው፤ ነገር ግን ወላጆቹ ታናሽ እኅቱ የሆነችውን ሴት ልጃቸውን ከአርያኖስ ጋር አጋቧት፡፡
❖ አባቱም ከሞት በኋላ ቅዱስ ኮጦሎስ የስደተኞችና መጻተኞች መቀበያ ቤት ሠርቶ እንግዳን ሁሉ የሚቀበል ሆነ፤ ከዚኽም በኋላ የጥበብ መጻሕፍትን ተምሮ ሐኪም ሆነ፤ ሕሙማንም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ያለምንም ዋጋ የሚፈውሳቸው ሆነ፤ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስም ጌታችንን በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለሹመቱ ከንጉሡ ጋር ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃይ ሆነ፡፡
❖ በዚኽም ጊዜ ቅዱስ ኮጦሎስ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ተመኝቶ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ወጥቶ አርያኖስን፣ ንጉሡን ዲዮቅልጥያኖስንና አለቆቹን ሁሉ ስለ ጣዖት አልኮአቸው ሰደባቸው፣ ጣዖታቱንም ሰደበ፡፡
❖ አርያኖስም ስለ እኅቱ ብሎ በቅዱስ ኮጦሎስን ከእሥር ፈታው፤ ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኮንን በተሾመ ጊዜ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና እና ገድል ነገሩት፤ ጭፍራ ልኮ ወደ እርሱ ካስመጣው በኋላ ለአማልክት እንዲሰግድ አስገደደው፡፡
❖ ቅዱስ ኮጦሎስም ‹‹ከዕውነተኛው አምላክ ከክርስቶስ በቀር የሚገዙለት አምላክ የለም፣ ለእርሱ ብቻ እሰግዳለሁ›› አለው፡፡
❖ በዚኽም ጊዜ መኮንኑ ተቆጥቶ ልዩ ልዩ በኾኑ ሥቃዮች አሠቃየው፤ ነገር ግን የታዘዘ መልአክ እየመጣ ቅዱስ ኮጦሎስን ከቁስሉ ሁሉ ይፈውሰውና ያጽናናው ነበር፤ ጌታችንም በዚኽ ቅዱስ እጆች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገ፤ መኮንኑም ቅዱስ ኮጦሎስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፤ እንደትእዛዙም ሰየፉትና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፤ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡
የሰማዕቱ የቅዱስ ኮጦሎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ሰማዕቱ አባ ኄሮዳ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ይኽም ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕጻንነቱ ጀምሮ በፈሪሃ እግዚአብሔር ያደገ ነው፤ በዘመኑም ከሃዲው ንጉጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ነበርና አባ ኄሮዳ አንድ ቀን ተኝቶ ሳለ ስለዚኽች ከንቱ አላፊ ዓለም አሰበ፡፡
❖ ጌታችን ‹‹ይኽን ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ያለውን አስታውሶ በስሙ ሰማዕት ይኾን ዘንድ ወደደ፤ ይኽንንም በልቡ ሲያስብ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹የከበርክና የተመሰገንክ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፣ ከመከራውም አጸናሃለሁና ሰማዕትነትህን በድል ትፈጽማለህ›› ብሎት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
✝ቅብዐ ሜሮን
በዚሕ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ የምንከብርበትን ቅብዐ ሜሮን አፍልቆልናል::
+በስደቱ ጊዜ ጌታችን በምድረ ግብፅ ደክሟቸው ካረፉበት ቦታ ላይ የዮሴፍ በትርን ቆራርጦ: በኪነ ጥበቡ ውሃ አፍልቆ: አጠጥቶ: ትልልቅ ዛፎች አደረጋቸው:: እዛውም ላይ ቅብዐ ሜሮንን አፈለቀ:: ቅብዐ በለሶንም ይሏቸዋል::
+በሁዋላም የጌታችን ወዙ በታጠበ ጊዜ ተቀላቅሎበታል:: ዛሬ እኛም: ንዋየ ቅድሳትም የምንከብረው በዚሁ ቅዱስ ቅብዐት ነው::
ምንጭ ፦ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት እና ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊
† በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: †
[ ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ]
🕊 † አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ † 🕊
እግዚአብሔር በ፲፫ [13ኛው] መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::
እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ [ዳኅና] አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን [ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው] ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
በአንዴም ከዳሞ [ትግራይ] ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ [ወሎ] አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ [ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው] ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው [በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ] በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
" ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! "
" ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: " [፩ዼጥ. ፭፥፫ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር። †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ማንነትህን ማወቅ"
ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።
ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10
(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)

✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሀ ወሰላም
+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+
=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::
+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::
+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::
+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)
+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-
1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::
+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::
+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::
+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::
+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::
+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::
+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::
+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::
=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::
=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

† በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ አሜን። †
† ግንቦት ፳፯ [ 27 ] †
🕊 † ቅዱስ አልዓዛር † 🕊
ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ ፸፪ [72] ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ ፴፮ [36] ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: [ዮሐ.፲፩፥፩] (11:1) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ ፬ [4] ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል::
ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: "አዳም ወዴት ነህ" ያለ [ዘፍ.፫] (3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: [ዮሐ.፲፩፥፩-] (11:1-ፍጻሜው)
ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ [ቁጥሩ ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት ነውና): ለ፵ [40] ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ ፸፬ [74] ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
🕊
[ † ግንቦት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
፪. ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ
፫. አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፮. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፯. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
" ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና" ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት" አላቸው:: " [ዮሐ.፲፩፥፵-፵፬] (11:40-44)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

†
🕊 💖 ሰ ላ ም ታ 💖 🕊
❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞
🕊
❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ 🕊 እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ ! 🕊 ]
❝ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል
በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል
እስመ ሔር አልቦ እንበሌከ ቃል:: ❞
[ ካንተ / ከቃል / በቀር ቸር የለምና . . . በቀራንዮ የተሰቀልህ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ! . . . ስለ ማርያም ድንግል [ ስለ እናትህ ] ብለህ . . . ምሬሐለሁ በለኝ ] ❞
[ መልክዐ መድኃኔ ዓለም ]