Telegram Web Link
Forwarded from Bketa @¥
#ጾሙን_አጋመስነው_አትበሉ

ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው “ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ” ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡ እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይኾን የኃጢአታቸው እኩሌታ መኼዱን [መወገዱን] ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡ ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፡፡ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው፤ ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል፣ ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት፣ ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል [በዓለ ትንሣኤን] እንድናከብር ነውና፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡

ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ኾነ፣ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡

የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡ በወርሐ ክረምቱ በብዛትም በዓይነትም የተለያየ ዓይነት የዝናብ ጠብታዎችን ተቀብለናል፤ ብዙ ተከታታይ ትምህርቶችን ተምረናል፤ መንፈሳዊ አዝርእት ተዘርተዉብናል፤ የቅምጥልነት እሾኽም ቈርጠን ጥለናል፡፡

ስለዚህ ጾሙ በተፈታ ጊዜ የጾሙ ፍሬ ይከብበን ዘንድ፣ ከጾሙ የሰበሰብናቸውን መልካም ነገሮችም ጾሙን ራሱን እናስታውሰው ዘንድ የሰማነውን ነገር አጽንተን በመያዝ እንትጋ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት 18፥1-2)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
Forwarded from መዝሙር ዘዳዊት (አክሲማሮስ 21)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል።

የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር፦ "በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።"/ዘፍ 42፥21/ ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል፦ "ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ"/ዘፍ 44፥16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኋላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡ ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።" /2ኛ ሳሙ.16፥10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል።

ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን "ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።" /ሚል 3፥7/ እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው።

ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ለበረከት ለፈላጊዎች:-

       የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሙያ እና ተራድኦ ክፍል ከሚያከናውናቸው የበረከት ሥራዎች አንዱ የተቸገሩ ወገኖቻችንን በተለያየ ነገሮች መልኩ መርዳት ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የሚተገበር ነዳያንን ለመመገብ የእናተን እርዳታ የሚፈልግ ሲሆን

አገልግሎቱን ለማከናወን የሚከተሉትን ነገሮች እንድታሟሉልን በቅዱስ ዮሴፍ ስም እንጠይቃለን።


ሽንኩርት
በርበሬ
ምስር
አተር
ጨው
ዘይት
እንጨት
የንፅህና መጠበቂያ
ሳሙና
ሞዴስ
የአዋቂና የህጻናት ዳይፐር
መለበስ የሚችሉ ንፁህ እና ያልተቀዳዱ ልብስና ጫማዎች
እንዲሁም ደግሞ በገንዘብ የተቻላችሁን ያህል ቸርነትን ታደርጉልን ዘንድ እንማጸናለን።

በአካል መጥታችሁ ለምትሰጡን ዘወትር ከሰኞ እስከ እሑድ ምሽት ከ12:00-2:00 በሰንበት ትምህርትቤቱ አዳራሽ እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ
0910544321 ፍሬሕይወት

0935204687 መሠረት

ለምታደርጉልን ትብብር ሁሉ እናመሰግናለን!!!

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን  ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የሙያና ተራድኦ ክፍል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

                         አሜን



ሠላም ውድ የተዋህዶ ቻናልና ግሩፕ ተከታታዩች እንዴት ናችሁ እንኳን ለወርሃ ሚያዚያ በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን 


  📌 መንፈሳዊ በዓል


✍️”በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ”

📖ኢሳ 56፥5



✍️“የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው”

📖ምሳ 10፥7



❖ እግዚአብሔር ለቅዱሳን በቸርነቱ ከሰጣቸው በረከት ለመሳተፍ መታሰቢያቸውን ማድረግ የግድ ነው።



✍️“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፤ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል፤ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙሬ ስም የሚያጠጣ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም”

📖ማቴ 10፥40-46



❖ ይህም የተባለው በነብያት፣ በጻድቃንና በሌሎችም ቅዱሳን ስም መታሰቢያ ማድረግ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው።



❖ መታሰቢያ አንድ ሰው ለሀገሩ በስራው መልካም ስራ ላበረከተው አስተዋፅኦ በጀግንነቱ ታይቶ በዚህች ኃላፊ ጠፊ ዓለም በስሙ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ፣መንገድ ተሰርቶለት ሲዘከር ይኖራል፤ እሱ ሕይወት ባይኖርም ስሙ ህያው ሆኖ ሲወሳ ይቆያል፤ ሰው ሁሉ እንዲያሲታውሰውም ይደረጋል የእነዚህ አርበኝነት ምድራዊ ሃላፊ ጠፊ ነው።



❖ የቅዱሳን መታሰቢያ ስንለል ግን፤ ጻድቁን ለማስታወስ በቅዱሱ ስም የሚገነባውን ቤተክርስትያን፣ የሚከበረውን በዓል ነው፤ ከምድራዊው መታሰቢያ ለየት የሚያደርገው ምድራዊ መታሰቢያቸው ከሰው ማንበብ ከሰማያዊ አምላክ ፈቃድ በመሆኑ ሥራው ነው።



✍️“ምስጋናና ግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፤ ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል”

📖መዝ 111፥3



❖ የቅዱሳኑን ዓመታዊ በዓል መታሰብያ ቀን ለጊዜው ስንክሳር እና ገድላትን በማንበብ አቅርበናል፡፡



📌 የወሩ ስም ሚያዚያ


❖ የግእዝ ሥርወ ቃሉ #መሐዘ



👉ትርጉም


❖ ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ)



📌 የወሩ ሌሊትና ቀን ስፍረ ሰዓት


❖ የሚያዝያ ወር ሌሊቱ 11 ሰዓት መዐልቱ 13 ሰዓት ነው፡፡



📌 በሚያዚያ ወር የሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት


ሚያዚያ 5

❖ ቅዱስ ያሬድ

ሚያዝያ 9

❖ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

ሚያዝያ 23

❖ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት

ሚያዝያ 27

❖ ምስካየ ሕዙናን /ስደተኛው መድኃኒዓለም ሽሮሜዳ ያለው/

ሚያዝያ 30

❖ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ያረፈበት


በዚህ ወር ከሚከበሩ ቅዱሳን መላእክት፣ ሰማዕታተት፣ ጻድቃና ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ እንዲሁም ከተሰጣቸው ቃልኪዳ ረድኤት በረከት ያካፍለን
Forwarded from Bketa @¥
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም


ሚያዝያ 1- የእመቤታችን ምሳሌ የተገለጠለት የሙሴ ወንድም ካህኑ አሮን ዕረፍቱ ነው፡፡
❖ በሕይወተ ሥጋ ሳለ ገነትንና ሲኦልን በግልጽ ያየ የከበረ አባ ስልዋኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡

❖ ታላቁ ሰማዕት አባ ብሶይ ልደታቸው ነው፡፡

❖ ጌታችን የአባ መቃርስ ገዳም መነኮሳትን ጸሎታቸውን ሰምቶ ከዐረቦች ወረራ ጠበቃቸው፡፡

❖ ቅድስት መጥሮንያ ዕረፍቷ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳታል፡፡

❖ ከአበከረዙን ጋር በሰማዕትነት ያረፉት ቅዱስ ዮስጦስና ሚስቱ መታሰቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
Forwarded from Bketa @¥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

ሰማዕቱ አባ ብሶይ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥



❖ አማኝ ክርስቲያን የሆኑ ወላጆቻቸው ልጅ ሳይኖራቸው 17 ዓመት ኖረዋል፤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ብርሃንን የለበሰ ጻድቅ ሰው ወደ አባቱ መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልድና ስሙን ብሶይ እንደሚለው ልጁም በመጨረሻ ሰማዕት እንደሚሆን ነገረው፤ ብሶይም ሚያዝያ 1 ቀን ተወለደና በሃይማኖት ኮትኩተው አሳደጉት፡፡



❖ ለመምህርም ሰጡትና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ ተማረ፤ በ27 ዓመቱም ክርስቲያኖችን ይገድል ወደ ነበረው ከሃዲ ንጉሥ ዘንድ ሄዶ ክርስቲያን መሆኑን ተናገረ፤ ንጉሡም አሳሰረውና በማግሥቱ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዘዘው፡፡



❖ አባ ቢሶይም የንጉሡን ትእዛዝ መቀበልን እምቢ ባለ ጊዜ ንጉሡ ይዞ እጅግ አሠቃየው፤ ነገር ግን የታዘዘ መልአክ ተገልጾ አበረታው፡፡



❖ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ቁልቁልያኖስ ወደሚባል መኰንን ላኩት፤ ይህም ከሀዲ መኰንን ‹‹ለምን ለጣዖቶቻችን አትሰግድም›› ብሎ ብዙ አሠቃየው፤ በብረት ችንካሮች ዐይኖቹን አወጣቸው፣ በፈላ ውኃ ውስጥም ጨመሩት፣ እጆቹንና እግሮቹንም በየተራ ቆረጧቸው፡፡



❖ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም የተቆራረጡ አካሎቹን ሁሉንም ፈውሶ እንደቀድሞው አንድ አደረጋቸው፡፡



❖ ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ሀገርም አመጡት፤ ለዲዮቅልጥያኖስ አስረከቡት፤ እርሱም በተራው እጅግ ጽኑ መከራዎችን አደረሰበት፡፡



❖ ሰኔ 5 ቀንም አንገቱን በሰይፍ አስቆርጦት የሰማዕትነት ፍጻሜ ሆኖ የክብርን አክሊል ተቀዳጀ፡፡


የሰማዕቱ የአባ ብሶይ ረድኤት በረከቱ፤ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

አባ ስልዋኖስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ይኽም ቅዱስ ገና በልጅነቱ ይኽችን ከንቱ ዓለም ፍጹም በመናቅ በአባ መቃርስ ገዳም አስቄጥስ ገብቶ በተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡

❖ በትሕትናና በፍቅር በጽኑ ተጋድሎ ከኖረ በኋላ ታላቅ አባት ሆነ፤ የክብር ባለቤት ጌታችንም ራእይን ይገልጽለት ጀመር፤ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ምሥጢራትንም ይነግረዋል፡፡

❖ ከዕለታት በአንዲት ዕለት አባ ስልዋኖስ በተመስጦ ምድር ላይ ተደፍቶ ብዙ ጊዜ ቆየ፤ ከዚህም በኋላ ነቅቶ ራሱን ቀና አደረገ፡፡

❖ በዚህም ጊዜ ከእርሱ ዘንድ ያሉ ወንድሞች መነኮሳት ያየውን ነገር እንዲነግራቸው አባ ስልዋኖስን በለመኑት ጊዜ እርሱ ግን ዝም ብሎ መሪር ልቅሶን ያለቅሳል እንጂ ምንም አልተናገረም፤ እነርሱም ግድ ባሉት ጊዜ አባ ስልዋኖስ እንዲህ አላቸው

✍️‹‹…ተድላ ገነት ወዳለበት ገነት አውጥተውኝ በዚያ የጻድቃንን መኖሪያ አየሁ፤ ዳግመኛም የሥቃይ ቦታዎችን አጠሁ፤ ሁለተኛም ብዙዎች መነኮሳትን ወደ ገሃነም ብዙዎች ምእመናንንም ወደ መንግሥተ ሰማያት ሲወስዷቸው አየሁ፤ እንግዲህ እኔ ለነፍሴ የማላለቅስ ለምንድነው›› አላቸው፡፡

✍️ከዚያች ቀን ጀምሮ አባ ስልዋኖስ ‹‹…በኋላ ወደ ዘላለም ጨለማ ሊወስዱኝ ዛሬ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ብርሃን ማየት አልሻም›› እያለ ፊቱን በቆቡ ሸፍኖ እያለቀሰ የሚኖር ሆነ፡፡

❖ አባ ስልዋኖስ እና ደቀ መዛሙርቶቹ በመንፈሳዊ ሥራ የተጠመዱ ሆነው ለምግባቸውም የሚያስፈልጋቸውን ያህል በጉልበታቸው እየሠሩ ከሠሩትም ላይ እየቀነሱ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር፡፡

❖ አንድ ቀን አንድ ታካች ሰው ወደ አባ ስልዋኖስ መጥቶ ሳለ ደቀ መዛሙርቶቹ ለዕለት ቀለብ የሚሆነውን ሲሠሩ አይቶ

✍️‹‹..ለኃላፊ ምግብ ትሠራላችሁ ትደክማላችሁ፤ የዘላለም ሕይወት ለሚሆን ሥሩ ድከሙ እንጂ፤ በወንጌል እንደተጻፈ ማርያምም የማይቀሟትን በጎ ዕድል መርጣለች ትምህርትን እንደመረጠች ብሎ በመጥቀስ ተናረ፡፡

❖ ሽማግሌው አባ ስልዋኖስም በዚህ ጊዜ ደቀ መዝሙራቸውን ጠርተው ‹‹ይህን መነኩሴ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት ውስጥ አስገብተህ የሚያነበው መጽሐፍ ስጠው፤ በሩንም ዝጋበት፤ የሚበላውንም ምንም ነገር አትስጠው›› አለው፤ ደቀ መዝሙሩም እንደታዘዘው አደረገ፡፡

❖ ዘጠኝ ሰዓትም መሆነ ጊዜ መነኮሳቱ ተሰብስበው ከአባ ስልዋኖስ ጋር ጸሎት አድርገው ምግባቸውን ተመገቡ፤ ያን እንግዳ መነኩሴ ግን አልጠሩትም፡፡

❖ እሱም ይጠሩኝ ይሆናል ብሎ በሩን በሩን በያይ የሚጠራው የለም፤ ረሀብም በጠናበት ጊዜ ወደ ውጭ በመውጣት ወደ አባ ስልዋኖስ ዘንድ ሔዶ ‹‹አባቴ ሆይ መነኮሳቱ እራታቸውን በሉ እንዴ›› ብሎ ጠየቀው፡፡


❖ አባ ስልዋኖስም ‹‹አዎን ሁሉም በልተዋል›› አለው፤ እንግዳውም መነኩሴ ዳግመኛ ‹‹እኔ እንግዳ ሆን ለምን አልጠራችሁኝም›› ብሎ አባ ስልዋኖስን ጠየቀው፡፡

❖ አባ ስልዋኖስም ‹‹አንተማ ሥጋዊ መብልን የማትሻ መንፈሳዊ ሰው ነህ፤ በጎ ዕድልን መርጠሃል፡፡

❖ እኛ ሥጋውያን ሰዎች ለሥጋዊ መብል የምሠራ የምንደክም ነን፤ ስለዚህ ለምግባችን የሚሆነውን በእጃችን እንሠራለን›› አለው፡፡



❖ በዚህም ጊዜ ያ መነኮስ በንግግሩ እንደበደለ አውቆ አባ ስልዋኖስን ‹‹አባቴ ሆይ እኔ በድያለሁና ይቅር በለኝ›› ብሎ ለመነው፤ እሱም ከአባ ስልዋኖስ ተገሥጾነ ተምሮ በጉልበቱ የሚሠራ፣ ከሚተርፈውም የሚመጸውት ሆነ፡፡


❖ አባ ስልዋኖስም ለምእመናን የሚጠቅሙ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ጻፈ፤ ዕድሜውም በሸመገለ ጊዜ በሞት የሚያርፍባትን ሰዓት እግዚአብሔር ነገረው፡፡

❖ ከዚህም በኋላ መነኮሳት ልጆቹን ተሰናብቶ ጌታችን በነገረው እንደዛሬይቱ ባለችው ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡

ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን
Forwarded from Bketa @¥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

ካህኑ ቅዱስ አሮን
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥



አሮን ማለት



❖ ‹‹ደብረ እግዚአብሔር›› ማለት ነው፤ ከሌዊ ነገድ ሲሆን የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም ነው፤ የቤተ መቅደሱ የደብተራ ኦሪቱ አገልጋይ ነበር፤ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር በእጆቹ ታላላቅ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡



❖ የቆሬም ልጁች በጠላትነት በተነሡበ ጊዜ እግዚአብሔር ፈርዶ አጥፍቷቸዋል ምድርንም አዘዛትና አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው፡፡



❖ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከሞተ በኋላ እስራኤልን የመራቸው አሮን ነው፤ እርሱም ሲሞት ልጁ አልዓዛር የካህናት አለቃ ሆኖ እስራኤልን መርቷቸዋል፡፡



❖ ሙሴን እግዚአብሔር አዞት ወደ ደብረ ሲና ተራራ ወጥቶ ታቦተ ጽዮንን ከመቀበሉ በፊት 40 ቀንና 40 ሌሊት ሲጾም ስለዘገየባቸው እስራኤላውያን በአሮን ላይ በነገር ተነሡበት፤ ‹በፊታችን የሚሄዱልን አማልክት ሥራልን› አሉት፡፡



✍️ዳግመኛም ‹‹ከግብፅ ምድር ያወጣን ሙሴ የሚባል ሰው ምን እንደሆነ አናውቅም ወደ ግብፅ ተመልሶ ሄዶ እንደሆነ ወይም በደብረ ሲና ያያት እሳት አቃጥላው እንደሆነ አናውቅም›› አሉት፡፡



❖ አሮንም ‹‹ወርቃችሁን ሰብስባችሁ አምጡ›› አላቸው፤ አሮን እንዲህ ማለቱ ‹‹እስራኤላውያን እጅግ ክፉዎችና ቁጡዎች ስለሆኑ በድንጋይ ወግረው በእሳት አቃጥለው ይገድሉኛል፤ ይሁን ብላቸውም እግዚአብሔር ይፈርድብኛል የወርቅ ጌጣቸውን አምጡ ያልኳቸው እንደሆነ ግን እስራኤል ገንዘብ እጅግ ወዳጆችና ስስታሞች ስለሆኑ በወርቃችሁ ልሥራላችሁ ብላቸው ጨክነው ወርቃቸውን አይሰጡኝም ነገ ከነገ ወዲያ ሲሉ ወንድሜ ሙሴ ይመጣልኛል ከነገርም እድናለሁ›› ብሎ ስላሰበ ነው፡፡



❖ ዳግመኛም አሮን ወርቁ ጠፍቶና ቀልጦ ይቀራል ብሎ በማሰብ ጉድጓድ ቆፍሮ እሳት አንድዶ ወርቁን ሁሉ ከዚያ ቢጥለው ሰይጣን የጥጃ ምስል አድርጎት ከጉድጓዱ አወጣው፡፡

📚ኦሪት ዘጸአት አንድምታ ትርጓሜ



❖ የአሮን በትሩ የእመቤታችን ምሳሌ ናት፤ እነ አቤሮንና ዳታን ደጋፊዎቻቸውም ጭምር በሙሴና በአሮን ሹመት ላይ በጠላትነት በመነሣታቸው ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው፡፡



❖ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ከ12ቱ የእስራኤል ነገድ 12 በትር ወስዶ የእያንዳንዱንም ስም በበትራቸው ላይ ጽፎ በመገናኛው ድንኳን በመስክሩ ታቦት ፊት እንዲያኖራቸው አዘዘው፤ እግዚአብሔርም ለሹመቱ የመረጠው ሰው በትሩ እንደምታቆጠቁጥ ነገረው፤ ሙሴም እንደታዘዘው አድርጎ ሲጸልይባቸው አድሮ በትሮቹን ቢያወጣቸው የአሮን በትር ከሌሎቹ በትሮች ተለይታ ሳይተክሏት በቅላ፣ ውሃ ሳያጠጧት ለምልማ፣ አብባ፣ የበሰለ ለውዝ አፍርታ ተገኝታለች፡፡


❖ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ያች በትር ለሚያምፁ ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና እንድትጠበቅ አዘዞታል፡፡

📖ዘኁ 7፡1-10



✍️‹‹እግዚአብሔርም ሙሴን የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ፤ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው›› ተብሎ ነው የተጻው፡፡



❖ ይኸውም ምሳሌ ነው፤ ለጊዜው እስራኤል በሹመት ምክንያት ተጣልተዋልና በዚህ ለይቷቸዋል፤ ፍጻሜው ግን የአሮን በትር ከሌሎች ተለይታ ለምልማ አብባ ፍሬ አፍርታ እንደተገኘች ሁሉ ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች ከእስራኤል ሴቶች ተለይታ በሥጋ፣ በነፍስ፣ በልቡና አብባ አጊጣ ያለዘር ያለሩካቤ በድንግልና ወልዳ ተገኝታለችና በእውነት የአሮን በትሩ የወላዲተ አምላክ ምሳሌ ናት፡፡



❖ ይህንንም ሊቃውንት አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ ቅዱስ ያሬድና እነ አባ ጊዮርጊስ በሚገባ አመስጥረውታል፤ እንደመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ የአሮን በትር እንዳይሞቱ ለሚያምፁ ልጆች ምልክት ሆና እንደተጠበቀች ሁሉ ድንግል ማርያምም ለእኛም ለሐዲስ ክርስቲኖች በኃጢአት እንዳንሞት ምልክት ሆና ተሰጥታናለች፡፡



❖ ነቢያቱም ‹‹ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፣ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች….›› እያሉ የነገሩንም ይህንኑ ነው፡፡

📖ኢሳ 7፥14



❖ ቅዱስ አሮንም በበጎ ተጋድሎውና የኦሪትንም ሕግ በመጠበቅ እግዚአብሔርን ካገለገለ በኋላ ሚያዝያ 1 ቀን በሖር ተራራ ላይ ሲያርፍ እስራኤላውያን 30 ቀን አልቅሰውለታል፡፡



ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን



📌 የሚያዝያ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ አሮን ካህን (የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም)

2. አባ ስልዋኖስ ጻድቅ

3. ቅዱሳን መነኮሳት

4. ቅድስት መጥሮንያ



📌 ወርኀዊ በዓላት
1. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ

2. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

3. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት

4. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ

5. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
Forwarded from መዝሙር ዘዳዊት (አክሲማሮስ 21)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኑ! ያለንን በማካፈል በዓለ ትንሳኤን ከነዳያንና የአብነት ተማሪዎች ጋር በፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት አብረን እናክብር።

በዚህ የበረከት ጥሪ ነዳያንን እና የአብነት ተማሪዎችን የማስፈሰክ ስራ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ በሚከተለው አካውንት አማካኝነት ተሳትፎ ታደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ለፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት
ዳሽን ባንክ
የሂሳብ ቁጥር 5033012404001

ለበለጠ መረጃ፦
➛ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋሁን- 09 13 23 10 26
➛ ዶክተር ሰሎሞን በላይ - 09 16 03 35 43

አምላከ ቅዱሳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን።
†† እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ክርስቶፎሮስ †††

††† ክርስቶፎሮስ ትርጉሙ "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ መሆኑ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ይጠሩ ነበር:: ከነዚህ አንዱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ሃገሩ በላዕተ ሰብእ (ሰውን የሚበሉ) ውስጥ ነበር::

ይህች ሃገር አሁን የት እንዳለች በውል ባይታወቅም የቅዱስ ማትያስ ሃገረ ስብከት በመሆኗ አውሮፓና እስያ ድንበር አካባቢ እንደሆነች ይገመታል::

የአካባቢው ሰዎች ከሰው ሥጋ ውጪ እህልን አይቀምሱም ነበር:: ቅዱስ ማትያስ በነርሱ ያደረውን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ አሳምኗቸዋል::

ከሃገሩ ሰዎችም አንዳንዱ ገጻተ ከለባት (የውሻ መልክ ያላቸው) ነበሩ:: ክርስቶፎሮስም ከነርሱ አንዱ ነበር:: በክርስቶስ አምኖ ከተጠመቀ በሁዋላ በስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ : ስለ ሃይማኖትም ብዙ ጸዋትወ መከራ ተቀብሎ በዚህች ቀን በሰማዕትነት አርፏል::

††† ከሰማዕቱ በረከት አምላኩ ያድለን::

††† ሚያዝያ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ክርስቶፎሮስ (ሐዋርያና ሰማዕት)
2.አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ
3.ቅዱስ መላልኤል (የያሬድ አባት - ከአዳም 5ኛ ትውልድ)
4.እግዚአብሔር ፀሐይን : ጨረቃን : ከዋክብትን ፈጠረ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
4.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
5.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
7.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" †††
(1ቆሮ. 10:14-18)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።

(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
🎚ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፫ 🎚

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ሦስት በዚች ቀን የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የከበረ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ።

🎚 በዚችም ቀን ደግሞ የከበረ አባት በእስክንድርያ ለተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ አንደኛ የሆነ አባ ሚካኤል አረፈ፤ ይህ አባት ከታናሽነቱ ጀምሮ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ወደደ በአስቄጥስ ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን መንኲሶ እስከ ሸመገለ ድረስ በዚያ ኖረ።

🎚 በዚችም ቀን ዳግመኛ ክርስቲያናዊ ነጋዴ መርቄ አረፈ።


  📌 ሚያዝያ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
4.እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

📌 ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
2024/09/28 12:17:01
Back to Top
HTML Embed Code: