Telegram Web Link
Forwarded from Bketa @¥
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑ ቸርነትን እናድርግ "

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ገልጿል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " በየጊዜው በሚከሰከቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ወገን ለወገኑ መርዳት ስላለበት ሌሎች አገልግሎቶችን ለጊዜው በመግታት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራ ተወስኗል " ብለዋል።

በተለይም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በስፋት ድጋፍና እርዳታ እንደሚደረግ በዚህ የጾም ወቅት ደግሞ ምጽዋት ማድረግ አግባብም እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ፤ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በዚህ ወቅት ፤ በአንድ ልብ እና ሀሳብ በመሆን ለተቸገሩት መድረስ እንደሚገባ ፤ ብፁዓን አባቶች በማስተማር ፤ ማኅበራት ፣ ሰንበት ት/ቤቶች ፣ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ በገንዘብ በዓይነት ሊበላሹ የማይችሉ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማኅበሩ ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ፦
- ብፁዓን አባቶች ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ ፤
- በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ትምህርተ ወንጌል ፤
- የመዝሙር አገልግሎት፤
- ዶክመንተሪ ቪዲዮ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አባቶችን ጨምሮ የሚደረግ መርሐ ግብር ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከማህበሩ ባገኘው መረጃ ፤ የመግቢያ ትኬት መቶ ብር እየተሸጠ ሲሆን በዕለቱ እዛው በር ላይም ይሸጣል።

አሁን በተዘጋጀው የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ለማይችሉ በተለያዩ በሚዘጋጁ የድጋፍ ማድረጊያዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የመርሐ ግብሩን የመግቢያ ትኬት :-
1.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2.  በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3.  በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5.  በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6.  በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ይገኛል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ በ09 44 71 82 82 እና 09 42 40 76 60 መደወል ይችላሉ።

@tikvahethiopia
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

መጋቢት 10 የጌታችን መስቀል የተገኘበት
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥



❖ በደመ ወልደ እግዚአብሔር የከበረ፤ ጌታ ቅዱሳት እጆቹን የዘረጋበት፣ ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት፣ መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ የተሻረበት፣ ዘላለማዊ ደዌ የጠፋበት፣ የጥል ግድግዳን ያፈረሰበት፣ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ድል የተነሣበት የጌታችን መስቀል ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሙት እያነሣ፣ ደዉይ እየፈወሰ ለክርስያኖች ታላቅ ክብር በመኾኑ፤ አይሁድ በዚኽ ክፉኛ ይበሳጩ ነበር።



✍️ ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵ“ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፤ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ፤ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ አሳባቸው ምድራዊ ነው” እንዳለ ጒድጓድ ቈፍረው በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ሁሉ ቤቱን የሚጠርግ ጒድፉን አምጥቶ እንዲያፈስስበት በማዘዛቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ300 ዓመታት ያኽል ተቀብሮ ኖረ፡፡
📖ፊሊ 3፥18-19



❖ የእሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስም በመስቀሉ ኃይል የክርስቲያኖች ጠላት የሆነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ በሶል ጴጥሮስ ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነ፤ ርሷም ልጄ ክርስቲያን ከሆነ ኢየሩሳሌም ሄጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለኊ፤ የጌታዬ መስቀልን ከተቀበረበት አስወጣለሁ ብላ ስዕለት ተስላ ነበርና ያ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ፤ ለልጇ ነገረችው፤ ርሱም በደስታ ብዙዎች ሰራዊትን ስንቅ አስይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፤ በደረሰችም ጊዜ ሱባኤን አድርጋ የመስቀሉ ጠላቶችን በጽኑ እስራት አሰረቻቸው፤ በኋላም አሚኖስና ኪራኮስ የሚባሉ በዕድሜ የጠገቡ ሽማግሌዎችን ብትጠይቃቸው ሊነግሯት ፈቃደኛ አልኾኑምና በጽኑ እስራት ብታስጨንቃቸው ታሪኩን ነገሯት፤ ቦታውንም ጠቈሟት፡፡



❖ ከዚያም በጸሎቷ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾላት በዕጣን ጢስ አማካይነት እንደምታገኘው ተረድታ፤ መስከረም 16 ደመራን አስደምራ በእሳት እንዲቃጠል አድርጋ እጅግ ብዙ ዕጣንን ብታስጨምር ጢሱ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ ካለበት ቦታ ላይ ተተክሎ ሰገደ፤



✍️“ተተክለ ጢስ ኀበ አንጻረ መስቀል፤ ሰገደ ጢስ ወባረከ” እንዲል ቅዱስ ያሬድ።


❖ ርሷም ፈጣሪዋ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ አመስግና ቊፏሮውን ከመስከረም 17 ጀምሮ እስከ መጋቢት 10 ድረስ እንዲቆፈር አስደርጋለች፤ በቁፋሮው ወቅትም የፈያታዊ ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም መስቀል ቢገኙም ዕውር አላበሩም፣ ሕሙማንን አልፈወሱም፡፡



❖ ከዚያም መጋቢት 10 በ327 ዓ.ም ክብር ይግባውና ጌታችን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀሉ ተገኘ፤ በዚኽ ጊዜ ከሕሙማን ላይ ቢያደርጉት ኹሉንም ፈወሳቸው፣ ዕዉራን በሩ፣ ሙታንም ተነሡ፡፡



❖ ከዚኹም ጋር የተወጋበት ጦሩ፣ የተቸነከረባቸው ቅንዋት ሁሉ ተገኝተዋል፤ ርሷም በፈረሷ ልጓም ላይ የመስቀል ምልክትን አስቀርጻበታለች፡፡



❖ ርሷም ጌታችን ተአምራት በሠራባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናትን በማሠራት፤ በተለይም በጎልጎታ የተሠራው ቤተ ክርስቲያን መስከረም 17 ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን በተገኙበት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተከብሯልና፤ርሷም ለድኾችና ለጦም አዳሪዎች ብዙ መልካም ነገርን በማድረግ ግንቦት 9 በሰላም ዐርፋለች፡፡



❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ስለ ቅድስት እሌኒ በዐርኬው ላይ



✍️“ሰላም ለእሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወሰዳ ለዘሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ አንግዳ ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ”


👉የመንፈስ ቅዱስ ምክር በወሰዳት ጊዜ ኤልዳ ወደ ተባለች የሕይወት ምድር የኼደች ለኾነች ለዕሌኒ ሰላምታ ይገባል፤ በአደባባይዋ ፊት መስቀልን በመንካት የዳነውን በድን በበረሓ ወድቀኽ የተገኘኽ አንተ እንግዳ ከወዴት ነኽ አለችው በማለት መስቀሉ ከወጣ በኋላ ስለተደረገላት ተአምር ጽፏል፡፡



❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ



✍️“ሰላም ለእሌኒ ንግሥት ዘከሠተት መስቀለ በጎልጎታ ። ለክርስቲያን ዘይከውን ወልታ፤ እምኀበ ወጽአ ጢስ በሃይማኖታ፤ ወዓዲ ረከበት ቅንዋተ መስቀሉ ለክርስቶስ፤ ወአግበረት ልጓመ ፈረስ በከመ ይቤ ዘካርያስ”


👉ጢስ በሃይማኖቷ ከወጣ ዘንድ ለክርስቲያን ጋሻ የሚኾን መስቀልን በጎልጎታ ያወጣች ለኾነች ለንግሥት እሌኒ ሰላምታ ይገባል፤ ዳግመኛም የክርስቶስን የመስቀሉን ችንካሮች አገኘች፤ ዘካርያስ እንደተናገረው ለፈረስ ልጓምን አሠራር በማለት ይጠቅሳል፡፡



❖ የነገረ መስቀሉን ነገር ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ሲያመሰጥረው



✍️“መስቀልከ ዕፅ ዘኢይነቅዝ መስቀልከ ዕፅ ዘኢየዐብር መስቀልከ ዕፅ ዘኢይማስን…”
👉መስቀልኽ የማይነቅዝ ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ የማይዋጋ (የማይደርቅ) ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ የማይጠፋ ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ የፀሓይ ሙቀት የነፋሳትም ግርፋት የማያደርቀው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ ውሆችና የነፋሳት ንውጽውጽታዎች ሊያነዋውጡት የማይቻላቸው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ የባሕር ሞገዶች ሊገፉት የማይቻላቸው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ የዝናማት ክብደት ሊጥሉት የማይቻላቸው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ ርኩሳን መናፍስት ሊቀርቡት የማይቻላቸው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ ከገነት ዛፎች መኻከል የሚመስለው የሌለ፤ ከበረሓ ዕንጨቶች መኻከልም የሚተካከለው የሌለ ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ ከዐርዘ ሊባኖስ መኻከል የሚመስለው ከምርስኔም ዛፎች መኻከል የሚተካከለው የሌለ ዕፅ ነው፤ የኢላጤኖስ ዛፎችም እንደ አበቃቀሉ አይኾኑም፤ የቄድሮን ዛፎች በውበት አይተካከሉትም፤ የጳውቄናም ዛፎች አይመስሉትም፤ መስቀልኽ በሌሎች ዛፎች ላይ የማይመካ ለስላሳ ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ በርሱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይል ዘንድ የወደደው ዕፅ ነው፤ መስቀልኽ ከቅርንጫፎቹ የወይንን ዝናማት ያንጠባጠበ ዕፅ ነው፤ ደመናውም ከአርያም የኾነ የብርሃን ደመና ነው፤ ርሱም ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ምእመናንም ከርሱ ከሚንጠባጠበው የምሕረት ዝናብ እንዲረኩ አደረገ፤ ከርሱም ምእመናን የጥምቀት ማኅተም ወሰዱ… በጌልጌል በእሳት ሠረገላ ላይ የምትቀመጠው በሊቶስጥሮስ ግን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀልኽ፤ መስቀልኽም በደምኽ ነጠብጣብ ተቀባ፤ በአምላኩ ደም የተቀደሰ ከፈጣሪው ጐን በወጣ ውሃም የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ለገነት ዛፎች አክሊል፤ ለገዳም ዛፎችም ክብር የኾናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ለአሸናፊ የእግዚአብሔር በግ መሠዊያ የኾነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ለእስራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ የጎልጎታዊዉ የምስጢር ወይን መፍለቂያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ከርሱ ምእመናንን ለማተም የሚኾን የሕግንና የሥርዐት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዐይነት ነው፤ ቡሩካን በጎችን ለማጠቢያ የሚኾን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዐይነት ነው፤ ምድርን የቀደሳት ሰማይንም ያማተበበት፤ ዓለምንም ኹሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ አዳምን ከስሕተት ያዳነው ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ስለ ርሱ በኦሪትና በነቢያት የተነገረ በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ የተከሉትን የበተናቸው ያመኑትንም የሰበሰባቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ እንደምን ያለ ነው በማለት ስለ ክብረ መስቀል ጽፎታል፡፡



✍️“ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ፅፀ መድኀኒት ኀይልነ ወጸወንነ”


👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በመስቀልኽ ኀይል ዕጠረን



📌ምንጭ
✍️ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
📚የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው መጽሐፌ ገጽ 388
Forwarded from Bketa @¥
Forwarded from Bketa @¥
††† እንኳን ለ40 ቅዱሳን እና ለታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ †††

††† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::

በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚሕች ዕለት አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::

በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል::

በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2 ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት በዚችው ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::

††† ከቅዱሳን አባቶቻችን የስደት በረከት ፈጣሪ አይለየን::

†††  አርባ ሐራ ሰማይ †††

††† አርብዐ ሐራ ሰማይ ማለት በዘመነ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሰማዕትነትን የተቀበሉ 40 ጭፍሮች ናቸው:: "ሐራ ሰማይ" የተባሉት በምድር ሲሠሩት የቆዩትን የውትድርና ሥራ ትተው የክርስቶስ (የሰማያዊው ንጉሥ) ጭፍራ ለመሆን በመብቃቸው ነው::

አርባው ባልንጀሮች ወጣትና ጐበዝ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በእርግጥ እነርሱ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት አልነበረም:: ነገር ግን ሰማዕትነት የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ : የእድሜ : የጾታ : የዘር . . . ልዩነት አያግደውምና እነዚህ ወጣቶች ለዚህ ክብር በቅተዋል::

ነገሩ እንደዚህ ነው:-
በ330ዎቹ አካባቢ የዓለም ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አንዱን መኮንኑን ወደ ቂሣርያ አካባቢ ይልከዋል:: የተላከው አካባቢውን ለማስተዳደር ሲሆን ቦታው ስብስጥያ (ሴባስቲ) ይሰኛል::

መኮንኑ ክርስቲያኖችን እንዲንከባከብ ጥብቅ ትዕዛዝ ከንጉሡ ቢሰጠውም ፍቅረ ጣዖት በልቡ የነበረበት ሰው ነውና ክርስቲያኖችን ይጨቁን : ያሰቃይ : ይገድል : አብያተ ክርስቲያናትን ያፈርስ ገባ::

በጊዜው ይህንን የተመለከቱት 40ው ጭፍሮች በአንድነት መክረው መኮንኑን ገሠጹት:: ስመ ክርስቶስንም ሰበኩለት:: እርሱም በፈንታው 40ውን አስሮ ብዙ አሰቃያቸው::

በመጨረሻ ግን 40ውንም የበረዶ ግግር አስቆፍሮ: ከነ ሕይወታቸው እስከ አንገታቸው ቀብሮ : ለ39 ቀናት ያለ ምግብ በጽኑ ስቃይ አቆያቸው:: በ40ኛው ቀን ግን ከ40ው አንዱ "ይህን ሁሉ መከራ የምቀበል ለምኔ ነው?" ብሎ "አውጡኝ!" እያለ ጮኸ::

ክርስቶስን አስክደው ወደ ውሽባ ቤት (ሻወር ቤት) ሲያስገቡት ፈጥኖ ሞተ:: በነፍስም በሥጋም ተጐዳ:: ነገር ግን ከአረማውያን ወታደሮች አንዱ "እኔን አስገቡኝ" ስላለ እንደገና 40 ሆኑ::

በዚህች ዕለትም 40ውን ጭን ጭናቸውን በመጅ እየሰበሩ ሲገድሏቸው ቅዱሳን መላእክት በአክሊል ከልለው : በዝማሬ አጅበው ወደ ገነት ወስደዋቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም በጊዜው ነበርና ገድላቸውን ጽፎ ውዳሴ ደርሶላቸዋል:: ቤተ ክርስቲያናቸውንም አንጾ የካቲት 16 ቀን እንዲቀደስ አድርጉዋል::

ብጹዕ አባታችን አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ በቅዱሳኑ ላይ የሆነውን ነገርና ሥልጣነ እግዚአብሔርን እያደነቀ እንዲህ ሲል ተናግሯል::

"ኦ አውጻኢሁ ለዘእንተ ውስጥ:: (በውስጥ ያለውን የምታስወጣ)"
"ወአባኢሁ ለዘእንተ አፍአ:: (በውጪ ያለውንም የምታስገባ)"
"ወይእዜኒ ስማዕ አውያቶሙ ለሕዝብከ እለ ይጼውዑከ በጽድቅ:: (እንግዲህ በእውነት የሚጠሩህን የወገኖችህን ጩኸት /ልመና/ ስማ)" ((ቅዳሴ ማርያም ቁ.146))

ስለዚህ በውስጥ ያለን አንታበይ:: ያለንበት የእኛ አይደለምና:: እንዳንወድቅም እንጠንቀቅ:: ብዙዎቹ የቆሙ ሲመስላቸው ወድቀዋልና:: ያሉ ሲመስላቸውም ወጥተዋልና::

በውጪ ያለንም ተስፋ አንቁረጥ:: ወደ ሁዋላም አንበል:: ወደ ቤቱ ሊመልሰን : በክብሩ ማደሪያ ሊያኖረን የታመነ አምላክ አለንና::

††† ቸሩ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ገብቶ ከመውጣት : አግኝቶ ከማጣት ይሠውረን:: ከሰማዕታቱ በረከትም አይለየን::

††† መጋቢት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ-ስደቱ)
2.ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ
3.40 ቅዱሳን ሰማዕታት (ከሃገረ ስብስጥያ)
4.ቅዱስ ዲዮናስዮስ (ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" †††
(ማቴ. 5:10)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
          አሜን
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
         ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

🛎 ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት ፲፬


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት ዐሥራ አራት በዚች ቀን በእስክንድርያ ለተሾሙ አባቶች ሰባ አምስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የቅዱስ ቄርሎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።

   
❖ እርሱም በምግባሩ ፍጹም ዐዋቂ ሆነ ሀገሩም ፍዩም ይባላል በእርሷም ቅስና ተሹሞባት ነበር፤ ከዚያም ለቆ ወደ አባ ፊቅጦር ገዳም ደረሰ እርሱም ከምስር ከተማ ውጭ የኢትዮጵያውያን ዐዘቅት የዐባይ ግድብ በአለበት ነው።
❖ በዚያም ታላቅ ገድልን እየተጋደለ ብዙ ዘመናትን ኖረ፤ ብዙ መጻሕፍትንም ተምሮ ትርጓሜያቸውንና ምሥጢራቸውን ጠንቅቆ ዐወቀ፤ አሸናፊ ወደሚባለውም ንጉሥ አደባባይ ቀርቦ የእስላሞች ታላላቅ ሊቃውንቶቻቸውና ከምሁራኖቻቸው ውስጥ መምህሮቻቸው ተከራከሩት፤ ጠቃሚ የሆነ ዕውቀት የተመላበትን መልስ አገኙ የሚጠይቁትንም ሁሉ በመልካም አመላለስ ነገራቸው።
❖ ከዚህ በኋላ የዕውቀቱና የቅድስናው ዜና በተሰማ ጊዜ ያለ ፈቃዱ ይዘው በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት መንጋውንም ጠበቀ በጸሎትና በቅዳሴ ያገለግሉ ዘንድ ለካህናት ሥርዓትንና መመሪያን ሠራ፤ ይህም አባት በሊቀ ጵጵስናው ሰባት ዓመታት ከዘጠኝ ወር ከዐሥር ቀኖች ኖረ፤ ከቀኑም በሦስት ሰዓት አረፈ በምስክርነት አደባባይም ተቀበረ።
በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
  

🛎 በዚችም ዕለት ከአረጋውያን ፍጹማን መነኰሳት ውስጥ አንዱ አባ ባጥል አረፈ።

ይህም ቅዱስ ሰው አባ ዮሐኒ የተባለ አበምኔት በመነኰሳት ላይ ነገረ ሠሪን እንደ ሚቀበል በሰማ ጊዜ በዓቱን ትቶ ወደ እስክንድርያ መጥቶ የሴት አዳሪዎችንና የአመንዝራዎችን ሁሉ ስማቸውን ጻፈ።
❖ ከኪራይ ሠራተኞችም ጋራ ሲሠራ ይውላል፤ ደመወዙን በተቀበለ ጊዜ የሽንብራ ቂጣ ግዝቶ ይበላል የቀረውንም ገንዘብ ይዞ ወደ አንዲቱ ሒዶ ይሰጣታል በዚች ቀን ከአንቺ ጋራ አድራለሁና ራስሽን ለእኔ አዘጋጂ ይላታል፤ ከኃጢአትም ሊጠብቃት ከእርስዋ ዘንድ ያድራል ሌሊቱን ሁሉ ተነሥቶ ሲጸልይና ሲሰግድ እግዚአብሔርንም ሲለምን ያድራል ሲነጋም ሥራውን ለማንም እንዳትገልጥ አምሏት ወደ ተግባሩ ይሔዳል።
❖ በየዕለቱም ወደ አመንዝራዎቹ እየሔደ እንዲህ ያደርግ ነበር አንዲቱም ሴት ምሥጢሩን ገለጠች ጋኔንም ይዞ አሳበዳት፤ ሰዎችም ስለዚህ ክፉ ሽማግሌ ክፉ ሥራ የለበትም ብላ ዋሽታለችና እግዚአብሔር መልካም አደረገባት ተባባሉ፤ እርሷም እንዳናመነዝር ገንዘብ በመስጠት ከኃጢአት ይጠብቀናል እንጂ ነውር የለበትም ብላ ነበርና።
❖ የቀሩት አመንዝራዎች በእርሷ ላይ የሆነውን በአዩ ጊዜ ደነገጡ እንደርሷም እንዳያብዱ እውነቷን ነው ማለትን ፈሩ፤ እርሱም ይችስ በእገሌ ዕለት ትጠብቀኛለች ይል ጀመረ ሰዎችም ሁሉ ያሙት ጀመር እርሱም እንደ ሰው ሁሉ ሥጋ የለኝምን ወይስ እግዚአብሔር መነኰሳትን ተቆጥቶ በፍትወት ተቃጥለው እንዲሞቱ ትቷቸዋልን አላቸው።
❖ እነርሱም ልብስህን ለውጠህ ሚስት አግባ ይህ ይሻልሃልና አሉት እርሱም አዎን ብወድ በሚስቴ እጠነቀቃለሁ በዚህም በክፉ አኗኗር እኖራለሁ እናንተ ግን ከእኔ ዘንድ ሒዱ ምን ትሻላችሁ በእኔ ላይ እግዚአብሔር ፈራጆች አድርጓችኃልን ይልቁንስ እናንተ እንዳይፈረድባችሁ ለራሳችሁ አስቡ ፈራጅ አንድ ነውና ዕለቲቱም አንዲት ናትና አላቸው ይህም ቅዱስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አገኘ በሰው ዘንድ ግን የተናቀ ሁኖ ኖረ።
❖ ከእርሱ ጥቅም የአገኙ አመንዝራዎችም ዝሙታቸውን ተው፤ ከእርሳቸውም ሕራዊ ጋብቻ ተጋብቶ የኖረ አለ ወደ ገዳምም ገብቶ መንኵሶ በጾም በጸሎት ተወስኖ የኖረ አለ፤ በአንዲት ዕለትም ከአንዲት አመንዝራ ቤት ሲወጣ ያቺን ሴት አስቀድሞ የለመዳት አንድ ሰው አገኘውና ይህ ሽማግሌ እስከ መቼ ድረስ በዚህ በክፉ ሥራ ይኖራል ብሎ ፊቱን በጥፊ መታው።
❖ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን በበዓቱ ውስጥ ሰግዶ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጥቶ በቤቱም መድረክ የዚች አገር ሰዎች ጊዜው ሳይደርስ በማንም ላይ አትፍረዱ እንዳይፈረድባችሁ የሚልም ጽሑፍ ተጽፎ ተገኘ።
በጸሎቱ የሚገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

                  

✍️ በዚችም ቀን ደግሞ ቅዱስ አባት አባ ሲኖዳ በሰማዕትነት አረፈ።

እርሱም በግብጽ አገር ከብሕንሳ ከተማ ነው ወደ መክስምያኖስም ክርስቲያናዊ ሲኖዳ አማልክትን የማያመልክ ነው ብለው ነገር ሠሩበት፤ እርሱም አስቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ ጠየቀው በንጉሡም ፊት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ እርሱም ዕውነተኛ አምላክ እንደ ሆነም መሰከረ።
❖ መክስምያኖስም ይህን የከበረ አባ ሲኖዳን በምድር ላይ ዘርግተው በበትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ፤ ዐጥንቶቹ እስቲሠነጠቁ ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ እስቲፈስ እንዲሁ አደረጉበት።
❖ ከዚህምም በኋላ እግሩን ይዘው ጐትተው ወስደው ሽታው በሚከረፋ በጨለማ ወህኒ ቤት ጣሉት የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለት፤ ቊስሎቹንም አድኖ ጤነኛ አደረገው አበረታውም በርታ አትፍራ ስለ መከራህም የክብር አክሊል ተዘጋጅቶልሃልና ደግሞም በጽኑዕ ሥቃይ ትሠቃይ ዘንድ አለህ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እኔም ከአንተ ጋራ እኖራለሁ አለው።
❖ ከዚያም ከእርሱ ተሠወረ፤ በነጋ ጊዜም የነገሥታትን ትእዛዝ የሚተላለፍ ያንን ዐመፀኛ ሒዳችሁ እዩት ሙቶም ከሆነ ለውሾች ጣሉት ብሎ መክስምያኖስ ወታደሮቹን አዘዘ፤ ወደርሱም በደረሱ ጊዜ ቁሞ ሲጸልይ አግኝተውት ያለምንም ጥፋት ጤነኛ እንደሆነና በሥጋውም ውስጥ የሕማም ምልክት እንደሌለ እርሱም ከቶ ምንም ሥቃይ እንዳላገኘው እንደ ጤነኛና ደስ እንዳለው ሰው ተግቶ እንደሚጸልይ ስለርሱ ለንጉሡ ነገሩት።
❖ ንጉሡም ወደርሱ አስመጣው ከሕይወቱም የተነሣ አደነቀ ልብሶቹንም አስወልቆ ያለጉዳት ጤነኛ እንደሆነ ሥጋውን አየ ደንግጦም ይህ ያየሁት ሥራይ ታላቅ ነው አለ።
❖ ከዚያም ዘቅዝቀው ሰቅለው ከበታቹ እሳትን እንዲአነዱ አዘዘ ይህንንም አደረጉበት ደግሞ በመንኰራኩር አሠቃዩት በአለንጋዎችም አብዝተው ገረፉት ደበደቡትም፤ ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ለውሾች እንዲጥሉት አዘዘ ውሾች ግን ፈጽሞ አልቀረቡትም ሌሊትም ሲሆን ምእመናን መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአዳዲሶች ልብሶችና በጣፋጭ ሽቶዎች ገነዙት በሣጥንም አድርገው ቀበሩት።
ከሥጋውም ብዙዎች አስደናቂዎች ተአምራቶች ተደረጉ፤ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

✍️ በዚችም ቀን ደግሞ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ ሰባት ዓመት ያህል የጋኔን ግንኙነት በአስቸገራት በአንዲት ሴት ላይ ተአምራትን አደረገ።

ሐዋርያ ቶማስንም በአየችው ጊዜ የክርስቶስ ሐዋርያው ሆይ እጅግ ከሚያሠቃየኝ ጠላት አድነኝ ብላ ወደርሱ ጮኸች።

❖ እርሱም በምን ምክንያት አገኘሽ አላት እርሷም ከመታጠቢያ ከውሽባ ቤት ስወጣ እንደ ሰው ድው ድው እያደረገ በመታወክ መጣ ድምጡም ሰላላና ቀጪን ነው በሴትና በወንድ ሥራ ሁሉ ነይ እርስበርሳችን አንድ እንሁን አለኝ በተኛሁም ጊዜ በሌሊት መጥቶ ከእኔ ጋራ አንድ ሆነ ብሸሽም አይተወኝም መጥቶ ያሠቃየኛል እንጂ እኔም ከጸሎትህ የተነሣ አጋንንት እንደሚንቀጠቀጡ አውቃለሁና ጸልይልኝ አድነኝም አለችው።
2024/09/28 20:20:36
Back to Top
HTML Embed Code: