Telegram Web Link
"ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፤ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ። የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል። ከዓይናችን ፊት ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋ አይደለምን? ዘሩ በምድር ውስጥ በሰበሰ፤ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል።"
ኢዮኤ 1፥14-17
#ከሰሙነ_ሕማማት_በፊት_መድረስ_ያለበት

ለአንድ የበረከት ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር ታናግሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።

ትሳተፉበት ዘንድ ያሰብኩት ለሕማማት አገልግሎት የሚውል ጥቁር ልብሰ ተክህኖ (የ5 ካህናት አልባሳት) ለሁለት ቤተክርስቲያን የሚሆን ነው። ይህን ንዋየ ቅድሳት ለማሰራት (ለመግዛት) ፈቃደኛ የሆናችሁ የበረከት ተሳታፊዎች በውስጥ መስመር ታናግሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።

ልታግዙኝ የምትችሉ ብቻ አናግሩኝ..

@natansolo @natansolo
@natansolo @natansolo
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።

(Deacon Abel Kassahun Mekuria)

https://www.tg-me.com/beteafework
https://www.tg-me.com/beteafework
 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቱ ቀን መታሰቢያ ሆነ።

❖ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደባት ቀን ድንቅ የሆነ ሥራን ሠራ ተነሥቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለሥላሴ ሰግዷልና ምስጋናም አቅርቧልና።

❖ ሕፃኑም ሦስት ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ እቅፍ አንሥቶ ብዙ ባሕታውያን ወዳሉበት ገዳም ወስዶ በደጅ አኖረው ወደ አበ ምኔቱ ወደ አባ ዘመደ ብርሃንም ገብቶ ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ነገረው።

❖ በዚያን ጊዜም ነገሩ እውነት እንደሆነ ይረዳ ዘንድ አባ ዘመደ ብርሃን ተነሥቶ ወደ ደጅ ወጣ፤ መልአኩም እንደ ነገረው ሕፃኑ ከበር ተቀምጦ ፈገግታን ተሞልቶ አገኘው፤ እጅግም ደስ ብሎት ለእግዚአብሔር ሰገደ ሕፃኑንም አንሥቶ ሳመው ታቅፎም ወደ በአቱ አስገባው፤ በፍቅር በሥነ ሥርዓት አሳደገው፤ የዳዊትን መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውን መጻሕፍት ሁሉ ብሉይንና ሐዲስን አስተማረው።
❖ ከዚያም በኋላም ክህነት ይሰጠው ዘንድ ስሙ አብርሃም ወደሚባል ጳጳስ ወሰደው ጳጳሱም በአየው ጊዜ ደስ አለው፤ የዲቁና ማዕረግንም ሾመው እንደ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስም ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ፤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም በጌታችን ትእዛዝ ቅስና ተቀበለ፤ በጾም በጸሎት በስግደት በብዙ ትጋትም እየተጋደለ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ፤ በበረሀም ብዙ ዘመናትን ሲኖር ነፍሱን "ነፍሴ ሆይ ዕወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ጽኚ በርቺ ታገሺ ይላት ነበር፤ ቆዳው ከዐጥንቱ እስቲጣበቅ ያለ መብልና ያለ መጠጥ በእንዲህ ያለ ግብር በገድል ተጠምዶ ኖረ፤ ከዕፅዋት ፍሬዎች ወይም ከዕንጨት ሥሮች አልተመገበምና ለሥጋውም የሚጠቅም ምንም ምን ምክንያት አልፈለገም።
❖ ከብዙ ዘመናት በኋላም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ከእንግዲህ በዓለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኰሳት ወይም ከምእመናን ሕዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግልሃለሁ፤ እንዳንተ ካሉ በቀር አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጐበኙሃል፤ የብርሃን ሠረገላም ይሁንልህ መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር እኔንም ማየትን በፈለግህ ጊዜ ከአባቴና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በሦስትነቴ ታየኛለህ፤ አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሒድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉህ አለው።

❖ ከዚህም በኋላ ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኋላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ፤ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋራ በነፋስ ሠረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር፤ ወደ ምደረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው።

❖ አባታችንም በባሕሩ ቁሞ ምሥራቁን ምዕራቡን ሰሜኑን ደቡቡን አራቱን ማዕዘን ተመለከተ፤ የኢትዮጵያ ሰዎች የሚሠሩትን ኃጢአታቸውን በዐይኖቹ ፊት የተገለጠ ሁኖ አየ፤ በራሱም ተዘቅዝቆ ተወርውሮ ወደ ባሕሩ ውስጥ ገባ እሊህን የእጅህ ፍጥረቶች የሆኑትን ካልማርካቸው ከእዚህ ባሕር እንዳልወጣ በእግሮቼም እንዳልቆም በሕያው ስምህ እምላለሁ እያለ ማለ እንዲሁም ሁኖ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ኖረ፤ ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ የሚል ቃል በመልአክ አማካይነት ወደ አባታችን መጣ፤ አባታችንም መልአኩን መላውን የኢትዮጵያን ሰው ካልማረልኝ ከዚህ ባሕር አልወጣም አለው መልአኩም ከአጠገቡ ሔደ።

❖ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ኖረ ሥጋው ሁሉ አለቀ ደሙም በባሕሩ ውስጥ ፈሰሰ አጥንቶቹም እንደበረዶ ነጭ ሆነው ታዩ፤ አጋንንትም ከአራቱ ማእዘን በየቀኑ ሰባት መቶ ሽህ ሦስት መቶ ሽህ እየሆኑ በመምጣት በቀስታቸው ይነድፉታል እስከ መቶ ዓመትም አጥንቶቹን በሻፎ ድንጋይ ይፍቁታል ይህን ሁሉ መከራ በትዕግስት ሲቀበል ኖረ።

❖ ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ ከባሕሩ ዳር ቆመ፤ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስንም መላውን የኢትዮጵያን ሰው ምሬልሃለሁና ተነሥተህ ውጣ አለው ያንጊዜም ወጣ አጥንቶቹም እንደ ወንፊት ቀዳዳ የተበሳሱ ሁነው ተገኙ ጌታም ዳሠሠውና ጤነኛ አደረገው ወደ ምድረ ከብድም ሰደደው።

❖ ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሐይ በላይ ከሰማይ በታች እስከ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ዳግመኛም ወደ ምድረ ከብድ ተልኮ እንደ ዓምድም የተተከለ ሆኖ ሰባት ዓመት ቁሞ ኖረ፤ ወደ ሰማይም ሲመለከት ቅንድቦቹን አልከደነም ራሱንም ወደ መሬት ዝቅ አላደረገም ነበር እጆቹም ወደ ሰማይ ተዘርግተዋል፤ እነሆ ሰይጣንም በቁራ ተመስሎ መጣ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ ያንጋጠጡ ሁነው አገኛቸው በራሱ ላይም ተቀምጦ ሁለቱን ዐይኖቹን አንቊሮ አሳወረው፤ እርሱ ግን ምንም ሳያጓድል እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ እንደ ቀድሞው በመትጋት ሲጸልይ ኖረ።

❖ ከዚህም በኋላ ሚካኤልና ገብርኤል መጥተው በፊቱ ቆሙ በሁለቱ ዐይኖቹ ላይም እፍ አሉበት ብርሃንም ተሰጥቷቸው እንደ ቀድሞው አዩ፤ ከሰማይ ታላቅ ኃይል ተሰጥቶሃልና ጠላቶችህን ትበቀላቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ሒድ አሉት ከዚያም መላእክት ከአጠገቡ ሔዱ።

❖ እርሱም ተነሥቶ ወደ ዝቋላ ተጓዘ በጐዳናም ሲጓዝ ሦስት ሽማግሌዎች ከዕንጨት ጥላ በታች ተቀምጠው አየ አባታችንም በአያቸው ጊዜ ልሠውራቸው ብሎ በልቡ አሰበ፤ እነርሱም ፈጥነው በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጥነናልና ሦስታችንንም በጀርባህ እያዘልክ አንዳንድ ምዕራፍ ሸኘን እንጂ አትተውን ብለው ተጣሩ፤ በመጣም ጊዜ ሁለመናቸውን ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሎች ሁነው አገኛቸው አንደኛውንም አንሥቶ በጀርባው አዘለው ወደ አንድ ምዕራፍም አደረሰው ሽማግሌውም ከዚህ አሳርፈኝ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ስለሆንክ አለው አባታችንም ሽማግሌ ሆይ በምን ዐወቅከኝ አለ።
❖ ሽማግሌውም ሒደህ ባልንጀሮቼን አምጣልኝ አለው ተመልሶ ሁለቱ ወደአሉበትም ደርሶ ሁለተኛውን ሽማግሌ በጀርባው አዝሎ ወደ ቀደመው ሽማግሌ አድርሶ አብሮ አስቀመጠው ሦስተኛም ተመልሶ ሦስተኛውን ሽማግሌ አዝሎ ሁለቱ ወዳሉበት አድርሶ በአንድነት አኖረው፤ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም እነዚያን አረጋውያን እናንተ ከወዴት ናችሁ መዓዛችሁ ልብ ይመሥጣል እጅግም ደስ ያሰኛል አላቸው፤ እነርሱ ግን ተነሥተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሃም እንደ አየ።

❖ ያንጊዜም የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ክብር አየ የእሊያ አረጋውያንም ፊታቸው ተንቦገቦገ ከፀሐይና ከመብረቅ ብልጭታም ሰባት እጅ በራ አባታችንም በምሥጢራት ጐርፍ የተዋጠ ሆኖ ፈራ ተንቀጠቀጠ በምድር ላይም ወደቀ፤ ሕልምን የሚአልምም መሰለው ከዚያም ጌታችን አባታችንን አነቃውና መቶ ዓመት ያህል ሥጋህን ሲነድፉህ ዐጥንቶችህን ሲፍቁህ የኖሩ አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ተራራ ውጣ አለው።
❖ እኔ እንደ ወሰድኩህ ባለማወቃቸው በባሕር ውስጥ አለ በማለት በትዕቢት ላይ ናቸው ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ይረዱሃል መባርቅትም በፊት በኋላ ሁነው ይከተሉሃል አለው፤ ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ። ደመናትም ከበቡአቸው መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱአቸው አመድም ሁነው በነፋስ በተኑአቸው።
❖ የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር፤ ከዚህም በኋላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምዕራብ ሀገር ወሰደው፤ጠነገሥታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚወጡበትና በሚገቡበት ጐዳና ላይ አቆመው ጌታችንም በዚች ጐዳና ብዙ መከራ ያገኝሃል ግን በርታ ታገሥ ብሎት በዚያ ተወው።

❖ በዚያን ጊዜም የዓርብ ንጉሥ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱን ሠራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጐዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጐዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣዖታቱ ወድቀው ተሰባበሩ፤ ንጉሡም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድነህ ሰው ነህን አለው። አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉሥ መለሰለት።

❖ ንጉሡም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ። ስለ እኔ በተሰቀለው አላፍርበትም ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋራ ስለ አሉትም ነው እንጂ ንጉሥ ሆይ የዘላለም ሕይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው።

❖ ንጉሡም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሠራዊቱንም ጠርቶ በፍጥነት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሬቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉር ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው፤ የእሳቱም ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ።

❖ አባታችን ግን ንጉሡና ሠራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ፤ እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሠረዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፤ ንጉሡም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈጽሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞቹ ጋራ በቁጣ ተነሥቶ ያደነቁትንና ያመኑትን አንገታቸውን ቆረጠ ።
❖ በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሁነው ተቆጠሩ፤ ንጉሡም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ሰይፉን መዞ ተወርውሮ ሔደ፤ ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጐድጓድ ጋራ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ንጉሡንም ከሠራዊቱ ጋራ አጠፋው ከከሀዲው ንጉሥ ጋራ የሞቱት ቍጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ።

❖ ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋሁልህ አለው፤ አባታችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ጽልመት ወደ ሥቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሑታን ማርልኝ ሰው ስሑትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሐሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው፤ አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሠወረ።
❖ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሔደ ታላቅ ገደልም አገኘ እግሮቹንም በገመድ አሥሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ፤ ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ፤ ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሔደ።

❖ በዚያም በራሱ ቁሞ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ እስከ ሠላሳ ዓመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደእንጨት ቅርፊት ሆነ፤ ከሠላሳ ዓመትም በኋላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሦስት ጊዜ ጠራው፤ እርሱም እነሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዲዎች ምሬልሃለሁ ከዚህ ተነሣ አለው፤ ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሣ። ጥርሱም ተነቅሎ በደንጊያ ተተክሎ ቀረ፤ ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከሥጋቸው ጋራ ተነሥተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው።
❖ መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሣ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሔደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ሕይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሣቸው አለው፤ ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሒዶ አስነሣቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሔደ።

❖ ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠለት፤ ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጠው፤ የዕድሜውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ፤ ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት።

የጸሎቱ ኃይል ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
††† እንኳን ለቅዱስ ቴዎዶስዮስ ተአማኒ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቴዎዶስዮስ †††

††† በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል:: ከእነዚህ አንዱ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደሆነ በትውፊት ይታመናል:: የጉባዔውስ ነገር እንደምን ነበር ቢሉ:-
የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)

2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)

3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)

4.ቅዱስ ቴዎዶስዮስ (በምድረ ቆረንቶስ መከራን የተቀበለ)

5.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)

6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)

7.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕፃንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)

8.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)

9.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ: ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)

10.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከሁለቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውንት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በአራቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት::
በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል:: ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

ቅዱስ ቴዎዶስዮስ የቆረንቶስ ጳጳስ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን አሳልፎ ከሰማዕታት ተቆጥሯል:: ነገር ግን አልተሰየፈም ነበርና እስከ ጉባኤ ኒቅያ ቆይቶ የጉባኤው ተሳታፊ ሆነ::

ከጉባኤው በኋላ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ወደ ሃገሩ ቆረንቶስ ተመልሶ : ሕዝቡን ሲመክር ቆይቶ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን::

††† መጋቢት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ተአማኒ (ዘቆረንቶስ)
2.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሰማዕት (አማሌቃውያን የገደሉት)
3.አባ ዘሩፋኤል ጻድቅ
4.አባ እንጦንስ ገዳማዊ
5.አባ አርከሌድስ ገዳማዊ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ . . . ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"እኔ ከእርሱ [ከባልንጀራዬ] ጋር ምንም ግንኙነት የለኝምና የሚል ደካማ መልስም አትስጠኝ፡፡ ምንም ግንኙነት የሌለን ከዲያብሎስ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ኹሉ ጋር ግን በጣም ብዙ የምንጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት ባሕርይ (ሰው መኾንን) አለን፤ እኛ በምንኖርባት ምድር ይኖራሉ፤ እኛ የምንበላውን ምግብ ይበላሉ፤ አንድ ጌታ አለን፤ እኛ የተቀበልነውን ሕግ ተቀብለዋል፤ እኛ ወደ ተጠራነው መንግሥትም ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም አንበል፡፡ እንዲህ ብሎ መናገር ሰይጣናዊ ንግግር ነውና፡፡ ዲያብሎሳዊና ኢ-ሰብአዊነት ነውና፡፡ ስለዚህ ለወንድማችን ያለንን ጥንቃቄ እናሳይ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ቃላትን አንናገር፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት፣ 1፥32)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
          አሜን
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
         ቀናችንን በጸሎት እንጀም

  🛎      ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት ፯

       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት ሰባት በዚች ቀን የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ በሰማዕትነት አረፉ።

  
❖ ይህ ፊልሞንም የእንዴናው ገዥ በሆነ በአርያኖስ ፊት በአዝማሪነት ይጫወት ነበር ከአዝማሪው አብላንዮስም ጋራ እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሆኑ ለክብር ባለቤት ክርስቶስም ስለ ስሙ ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ።
❖ አዝማሪው ፊልሞንም ልብሱን ወስዶ ለአብላንዮስ ሰጠው እርሱም የአብላንዮስን ልብስ ለብሶ ወደ መኰንኑ ወደ አርያኖስ ገብቶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ።
❖ መኰንኑም ተመልክቶ አዝማሪው አብላንዮስ እንደሆነ አሰበ በፍላጻም እንዲነድፉት አዘዘ ያንጊዜም አዝማሪው ፊልሞን መሆኑን አውቆ እጅግ ተቆጣ፤ ደግሞ አብላንዮስን እንዲነድፉት አዘዘ ሁለቱንም ነደፉአቸው አንዲት ፍላጻም ወደ መኰንኑ ተመልሳ ዐይኑን አወጣቻት እጅግም አሠቃየችው፤ የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ ግን ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ።

በረከታቸውም ከኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

   

🛎 በዚችም ዕለት ደግሞ ቅዱስ ቴዎዶጦስ በሰማዐትነት አረፈ፤ እርሱም ከገላትያ አገር የሆነ በምክርና በተግሣጽ አምልኮተ እግዚአብሔርንም በማጽናት ያደገ ነው፤ ወደ ከሀዲ መኰንንም ሒደው የክርስቲያን ወገን እንደሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም አሥረው እንዲአመጡት አዘዘ።

❖ ቅዱሱም ይህን በሰማ ጊዜ ሳይዙት ወደ መኰንኑ ሔዶ መኰንኑንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ ዘለፋቸውም መኰንኑ እሱን በማስፈራት ሁኖ የሥቃይ መሣሪያዎችን ሁሉ አሳየው ለጣዖት እንዲሠዋ በመሸንገል አስገደደው ቅዱሱም ስለ ድንቁርናው ረገመው ዘለፈውም።

❖ ከዚህ በኋላም የውስጥ ዕቃው እስከሚታይ ሰቀለው ጐኖቹን ይሠነጣጥቁ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ፤ ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ይጨምሩት ዘንድ ደግሞ አውጥተው በዕንጨት እንዲሰቅሉት ቊስሎቹንም እንዲአድሱ ጐኖቹንም እንዲሠነጣጥቁ አዘዘ፤ እርሱ ግን መኰንኑ የሚያመጣውን ሥቃይ እንደ ኢምንት አደረገው በክብር ባለቤት በጌታችን ክርስቶስ በፍቅሩ ፍላጻነት ልቡ ተነድፏልና ዐይኖቹም ወደላይ ይመለከቱ ነበር፤ መኰንኑም ብርታቱን በአየ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።

❖ ቅዱስ ቴዎዶጦስም የራሱን መቆረጥ ሰምቶ እጅግ ደስ እያለው ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ሲጸልይና ሲማልድ እንዲህ አለ፤ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ከተከታተለኝ ክፉ ነገር ሁሉ አድነኸኛልና በጠላትነት የተነሡብኝንም ወደ ገሃነም አውረድካቸው እኔንም ከሞት በር ከፍ ከፍ አድረግኸኝ።

❖ ይህንንም ብሎ በሰገደ ጊዜ ወታደሩም የቅዱሱን ዐይን ይሸፍን ዘንድ መሸፈኛ አመጣ፤ ቅዱሱም ይህ ሞትን ለሚፈሩ ነው እኔ ግን በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሞትን አልፈራም አለ፤ ወታደሩም ሰይፉን መዝዞ የከበረች ራሱን ቆረጠ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።

በረከቱም በላያችን ትደር ለዘላለሙ አሜን

         

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
    ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል፤ በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845- 1860) ነው።
❖ በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው፤ ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ግማደ መስቀሉን ያመጡት)ና የተባረከችው ሚስታቸው ጽዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው።
❖ በኢትዮጵያ ለሦስት ዓመታት (ከ1396- 1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን፤ ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ይታትር የነበር፣ ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር፣ ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ፣
ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር።
❖ ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር፤ በነገሠ በሦስት ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሶ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል፤ ከመቃብሩም ላይ ጠበል ፈልቋል።


📌 መጋቢት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ሰማእታት ፊልሞንና አብላንዮስ
2.ቅዱስ ቴዎዶጦስ
3.ፃድቅ ንጉስ ቴዎድሮስ
              
📌ወርኀዊ በዓላት
1.አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ
2.ዲዎስቆሮስ
††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ †††

††† በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር::

ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ 12ቱን ሐዋርያት መረጠ::

††† እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)

††† እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::

ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)

ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)

የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19): እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: (ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው::

ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጊዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::

ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::

ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)

ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ ዓለምን በእጣ ለ12 ተካፈሏት::

ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::

በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::

ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::

ቅዱስ ማትያስ ስም አጠራሩ ይክበርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦቼ ብሎ ከመረጣቸው 120 ቅዱሳን አንዱ: 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታችን እግር ቁጭ ብሎ የተማረ: በይሁዳ ፈንታ ከ12ቱ ሐዋርያት ይቆጠር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የመረጠው ሐዋርያ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ በዕጣ በደረሰው ሃገረ ስብከቱና በሌሎቹም ዓለማት ለወንጌል አገልግሎት ብዙ ደክሙዋል:: በተለይ የሰውን ሥጋ ወደሚበሉ ሰዎች ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው ዓይኖቹን አውጥተው ከብዙ ስቃይ ጋር ለ30 ቀናት ሣር አብልተውታል::

እሱ ግን በትእግስትና በፈጣሪው ኃይል ድንቅ ተአምር አድርጐ አሳምኖ አጥምቋቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎና ቅድስና በሁዋላም በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ሐዋርያት ቸርነቱን ያብዛልን:: በምልጃቸው ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን::

††† መጋቢት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ አርያኖስ ሰማዕት (በዘመነ ሰማዕታት ብዙ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረና ጌታ በንስሃ የጠራው)
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን

††† ". . . እንዲህም ብለው ጸለዩ:: 'አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ ከእነዚህ ከሁለቱ የመረጥከውን አንዱን ግለጥ?' . . . ዕጣ አጣጣሉአቸው ዕጣውም በማትያስ ላይ ወጣ:: ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋርም ተቆጠረ::" †††
(ሐዋ. 1:24-26)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Audio
Forwarded from Bketa @¥
2024/09/28 22:20:15
Back to Top
HTML Embed Code: