Telegram Web Link
† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ዘካርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ዘካርያስ ነቢይ †††

††† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር : ወተናጸሩ ገጸ በገጽ::" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ:: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ::" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል:: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ጴጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" : "አራቱ ዐበይት ነቢያት" : "አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት" እና "ካልአን ነቢያት" ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

††† "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
1.ቅዱስ አዳም አባታችን
2.ሴት
3.ሔኖስ
4.ቃይናን
5.መላልኤል
6.ያሬድ
7.ኄኖክ
8.ማቱሳላ
9.ላሜሕ
10.ኖኅ
11.አብርሃም
12.ይስሐቅ
13.ያዕቆብ
14.ሙሴ እና
15.ሳሙኤል ናቸው::

††† "አራቱ ዐበይት ነቢያት"
1.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
2.ቅዱስ ኤርምያስ
3.ቅዱስ ሕዝቅኤል እና
4.ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

††† "አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት"
1.ቅዱስ ሆሴዕ
2.አሞጽ
3.ሚክያስ
4.ዮናስ
5.ናሆም
6.አብድዩ
7.ሶፎንያስ
8.ሐጌ
9.ኢዩኤል
10.ዕንባቆም
11.ዘካርያስ እና
12.ሚልክያስ ናቸው::

††† "ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስ እና
*ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

††† ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል) እና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

††† በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት):
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::

††† ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

††† ቅዱስ ዘካርያስ ቁጥሩ ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ450 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

††† ነቢዩ ቅዱስ ዘካርያስ:-
*ከክርስቶስ ልደት 450 ዓመታት በፊት የነበረ::
*በጻድቅነቱ የተመሰከረለት::
*14 ምዕራፎች ያሉት ሐረገ - ትንቢት የተናገረ::
*ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ በስፋት የተነበየ ነቢይ ሲሆን ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትም አንዱ ነው::

††† የአባታችን በረከት ይደርብን::

††† የካቲት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዘካርያስ ነቢይ (ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ)
2.ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ (ከጻድቅነቱ ባሻገር በግብጽ በርሃ የሚኖሩ የብዙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት የጻፈ አባት ነው::)
3.ቅዱሳን አርብዐ ሐራ ሰማይ (40 የሰማይ ጭፍሮች) ለ40 ቀናት ሰብስጥያ በምትባል ሃገር መከራ ተቀብለው በሰማዕትነት ያለፉ ክርስቲያን ጓደኛሞች::

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅዱስ ሚናስ ግብጻዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና

††† ". . . የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:: 'ወደ እኔ ተመለሱ . . . እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ::' " †††
(ዘካርያስ ፩፥፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Encoderbot file id4183629 16k
ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት አሥራ አምስት(፲፭)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
õ Eñ5 B-F5 ÈEõ5u ¢è # ØÈ- è
ASR by NLL APPS
ገድለ ቅዱስ ቂርቆስ ወቅድስት ኢየሉጣ ዘወርሃ የካቲት
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
🌺💐🌺 🌸🌸🌸 ኪዳነ ምሕረት 🌺💐🌺🌸🌸🌸
🔔 እንኳን አደረሳችሁ!!!
በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡  
 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠችውን እናታችንንም ‹‹ኪዳነ ምሕረት›› እያልን የምንማጸናት ለዚህ ነው፡፡ ለአዳም የተገባለት የምሕረት ቃል በእርሷ ተፈጽሟልና፡፡ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ወልዳዋለችና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሎ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው ከእርሷ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡  
 
በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ መቃብር ቦታ ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ስለ ነበር  በየካቲት ፲፮ ቀን በጸለየችው ጸሎት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ጸሎቷም እንዲህ የሚል ነበር፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››
 
ጌታችንም ምን ሊያደርግላት እንደምትሻ ሲጠይቃት በስሟ ለሚማጸኑ፣ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን፣ ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጨምራ ጠየቀችው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በየካቲት ፲፮ ዕለት የገባላትን ቃል ኪዳን እንዲህ በማለት በመሐላ አጽንቶታል፡፡  ‹‹መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ፡፡››   
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠበት ይህ ዕለት ታላቅ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቅት ታከብረዋለች፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነውና፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡
 
በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ የሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና ችግረኛ መርዳት ይገባናል፡፡  

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን! 
👉 በማኅበረ ቅዱሳን
Forwarded from Bketa @¥
Forwarded from ቤተ ቶማስ
"ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፤ " መዝ.፹፰፥፫

እንኳን ለኪዳነምሕረት ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ ቤተሰብ! 🤗❤️
#የብፁዕ_ወቅዱስ_ፓትርያርክ_የጾመ_ነነዌ_መልዕክት
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
'ተንሥእ ወሑር ኅበ ነነዌ ሀገር ዐባይ - ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ" (ት.ዮናስ ፩;፪)

#ብፁዓን_አበው_ሊቃነ_ጳጳሳት_ወኤጲስ_ቆጶሳት
#መንፈሳዊ_ተልእኮ_ተቀብላችሁ_በየተሰጣችሁ_ጸጋ_በተለያ_ስፍራ_ሆናችሁ_የምታገለግሉ_ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን
#በመንፈስ_ቅዱስ_ልደት_የከበራችሁ_ምእመናን1ወምእመናት_ልጆቻችን_በሙሉ

ዘመንን በዘመን እየተካ፣ መዓቱን በምሕረት እየመለሰ የሚያኖረን እግዚአብሔር እንኳን ለ2016 ዓ.ም ጾመ ነነዌ አደረሰን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት የሰው ልጆች በኃጢአት በወደቁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ የሁሉ አባት በመሆኑ ተወልዶ ብልጫ የለም" እንዲሉ ከእስራኤል ውጭ ወዳለችው ነነዌ ነቢዩ ዮናስንና ነቢዩ ናሆምን ልኳል። በበደል ውስጥ ሆነው ቢጾሙም ሆነ ቢጸልዩ ጸሎቱ ድል የሚነሣ መሥዋዕቱም የሚያስምር አይሆንምና፡ ንስሐም ለድሀና አቅም ለሌለው የሚሰበክ ሳይሆን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያደፈ ሁሉ የሚጠራበት የሕይወት መስታወት ነውና የሕይወት ትንሣኤ በሆነው ንስሐ ነነዌን ለማንሣት ዮናስ ወደ ንጉሡና ወደ ሠራዊቱ የንስሐ ሰባኪ ሁኖ ተልኳል።

ነነዌ ከተማዋ አድጎ፡ ልማቷ ቢሰለጥንም እግዚአብሔር ግን የተመለከታት ፈርሳና ተበላሽታ ነበር፡፡ በፈረሰ ልብ የሚገነቡ ከተሞች የቀን ጉዳይ እንጂ ፍርስራሽ መሆናቸው አይቀሬ ስለሆነ ዛሬ ነነዌ ከታሪክ መዝገብ ላይ ብትሰፍርም በዓይን ግን የምትታይ አይደለችም። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የነነዌን ጾም ያወጀችው ዓመት ሙሉ የተጣላ በነዚህ ሦስት ቀናት እንዲታረቅ፣ ሲካሰስ የሚኖር ሕዝብም ወደፈጣሪው በንስሐ እንዲመለስ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ነቢዩን ወደ ነነዌ ሲልከው፡- “ተነሥተህ ሂድ" ማለቱ በበደል የሳተን በሩቅ ሆኖ መተቸት መንፈሳዊ ተልእኮ ባለመሆኑ ተነሥተን ብንሄድ፣ መንገድ አጋምሰን ወገኖቻችንን ብንፈልግ ሁሉንም ለንስሐ ማብቃት እንደምንችል ሲያስተምረን ነው፡፡ ለመነሣት ስንፍናንና ፍርሃትን ድል መንሣት ያስፈልጋል። ለይቅርታ ስንነሣ ትዕቢትን እናሸንፋለን። ፉክክርን እናርቃለን። ለጋራ ሀገራችን የጋራ መፍትሔ፡ ለጋራ ቤተ ክርስቲያናችን የጋራ መድኃኒትን እናገኛለን።

በሌላ በኩል አምላካችን እግዚአብሔር በደለኛይቱን ከተማ ታላቂቱ ከተማ በማለት ሲጠራት ሕዝቡንም ግራና ቀኙን የማያውቅ በማለት ራርቷል። እግዚአብሔር አምላክ አክባሪ፤ አዛኝ፡ በደለኛውንም በክብር እንጂ በውርደት የማይጠራ አምላክ ነው። እኛም ይህንን የነነዌን ጾም ስንጾም በአንድ በኩል እንጀራን የተራቡ፣ በሌላ በኩል ሰላም የተራቡ ወገኖች ስለአሉን ወደ እነዚህ ወገኖች የንስሐን ስብከት፣ የማጽናናትን መልእክት ይዘን መሄድ አለብን። በተጨማሪም ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን፡ በረሃብ፣ በመታረዝ፣ በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን የመከራ ማቅ በሕሊናችን ተሸክመን ስለጸሙ የተውነው የዕለት ቊርሳችንን ለእነርሱ ሞትን ማባረሪያ እንዲሆን ልንፈቅድ ያስፈልጋል።

#የተወደዳችሁ_የመንፈስ_ቅዱስ_ልጆቻችን!

ይህንን የነነዌ ጾም ልንቀበል ዋዜማ ላይ ባለንበት በዚህ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ጥንታዊ ከሆኑት ገዳማት አንዱ በሆነው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኙ፣ ዓለሙን ትተው በፈቃዳቸው ረሀብተኛ እና ጥማተኛ ሆነው ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ መነኮሳት ጫካው መኖሪያችሁ፣ ዳዋው ልብሳችሁ፤ ቅጠሉ ምግባችሁ መሆን አይችልም ተብለው የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎንጭተዋል፡፡ እነርሱ በሥጋ እየሞቱ እኛም በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል፡፡

ይህ ለእነርሱ ክብር ቢሆንም ለቤተክርስቲያን ግን ታላቅ ደወል ያሰማ ክስተት ነውና ውሉደ ክህነት ቤተክርስቲያናችሁን የምትጠብቁበት፣ የመከራውን ማዕበል ለማለፍ በመንፈሳዊ ፍቅር አንድነትን ማጽናት የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም ታላቅ ሀገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጸማችን፣ ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ለሀገር ደኅንነት፡ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን፡

እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልእክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ || ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ - የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

(የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን)
#ምጽዋት

"ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈጣሪ ለመቅረብ እንደ ምጽዋት ክሂል የሚሰጥ የለም። ከሥራም ወገን ወድዶ ሰጥቶ እንደመቸገር በልቡና ኅድዓት (ፀጥታ ፣ ዕረፍት ፣ ሠላም) የሚያደርግ የለም። ሰጥተኽ መጽውተኽ አጥተኽ 'አላዋቂ' ቢሉኽ ይሻልኻል። ጨብጠኽ ይዘኽ አስተዳደር ዐዋቂ ከሚሉኽ።. . . ኅብስቱን ከውሃ ጣለው ብሎ ተናግሯልና። ከውሃ የጣሉት እንዳይመለስ ፣ 'ይ 'ሰጠኛል' ብለኽ አትስጥ ሲል ነው። አንድም ኀብስቱን ከእግዚአብሔር ፊት አኑረው ሲል ነው። በፍጻሜ ዘመንኽ ዋጋኽን ታገኛለኽ።

ባለጸጋውን ለይተኽ ለድኻ አትስጥ። 'ይኽ ይገባዋል ይኽ አይገባውም' አትበል። አላ ኩሉ ሰብእ ይኩኑ ዕሩያነ በኅቤከ -በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለኽ መጽውት እንጂ! አስተካክለኽ በመስጠትኽ ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለኽ። ምንም የበቁ ባይኾኑ ነፍስ በመብል በመጠጥ ምክንያት ወደ ክቡር እግዚአብሔር ትሳባለችና! በምጽዋት ጊዜ 'ይኽ አይሁዲዊ ነው። ይኽ ከሀዲ ነው' አትበል። 'ይኽ ነፍሰ ገዳይ ነው' አትበል። ይልቁንስ ብታስታውለው ወንድምኽ ነው እንጂ። አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ።ከበጎው ነገር ወገን ለሰው ያደረግኽ እንደኾነ መክፈልን አትውደድ።. . .

መጽውተኽ ብትቸገር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ቸርነት ከትካዝ ሥጋዊ ትድናለኽ! ከኹሉ በላይ ትኾናለኽ! ሰው ኹሉ ለገንዘቡ ሲገዛ እሱ ለእግዚአብሔር ይገዛልና። . . . 'በዝናም ያበቀለው በፀሓይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው' ብለኽ ምጽዋትኽን በትሕትና መጽውት። ጻድቃን በሚከብሩበት ጊዜ ይቅርታን ታገኛለኽ"

(ከመጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ) ፣ አንቀጽ ፩፣ ምዕ.፲፪፣ ገጽ ፳፩ - ፳፫)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


    🛎  የሦስቱ ቀናት ጾም

የካቲት፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት

ሦስት ቁጥር በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ብዙ ትርጉሞች እንዳለው ቅዱሳት መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በዋነኛነት የምናነሣው ስለ ቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ነው፡፡ ‹‹አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ናቸው›› እንዲል፤ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደውም በዕለተ እሑድ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰው በሦስት ሰዓት ነው፤ እመ አምላክም የመፀነሱን ብሥራት ከቅዱስ ገብርኤል የሰማቸው በዚሁ ሰዓት ነው፡፡

(ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት/በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ፣ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም)
አምላካችን በተወለደ ጊዜም የዜናውን ብሥራት ሰምተው እጅ መንሻ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ ያመጡለት ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ቁጥራቸው ሦስት እንደ ሆነ ቅዱስ ወንጌል ይገልጻል፡፡ (ማቴ.፪፥፲፪) ተአምረ ማርያም ደግሞ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር ሆና ጌታችን ኢየሱስ ፲፪ ዓመት በሆነው ጊዜ በቤተ መቅደስ ለሦስት ቀናት ያህል ፈልጋ እንዳጣችው ይነግረናል፡፡

ጌታችን በዘመነ ሥጋዌ በምድር ላይ ስብከተ ወንጌልን ያስተማረው ለሦስት ዓመታት ነው፤ በቀራንዮ አደባባይ መከራና ሥቃይ የተቀበለው ለሦስት ሰዓታት ነው፤ በመልዕልተ መስቀል ላይ ከሞተም በኋላ የተነሣው ከሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በኋላ ነው፡፡ (ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት/በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ፣ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም)

ይህን ብቻ አነሣን እንጂ በነገረ መላእክትና በቅዱሳን ገድል ውስጥ ሦስት ቁጥር ለብዙ የእግዚአብሔር ሥራዎች ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘእሑድ፣ ገድለ ቅዱሳን)
ለምሳሌ ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴን  ‹‹አሐዱ  አብ  ቅዱስ  አሐዱ  ወልድ  ቅዱስ  አሐዱ  ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ  አብ  ቅዱስ  ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው››  በማለት ያመሰገኑት በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ሄዶ በአንደበቱ ሊገልጸው የማይችለውን ምሥጢር እንደ ተመለከተ ቅዱስ ወንጌል ይገልጻል፡፡ ብዙ ምሳሌዎች መግለጽ ቢቻልም ጊዜ ይገድበናል፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፣፪ኛ ቆሮ.፲፪፥፪)

ለዚህ ርእሰ ጉዳይ ትኩረት ያደረግነው ግን አምላካችን ስለ አዘዘው የሦስቱ ቀናት ጾም ነው፡፡ ለማንኛውንም ጥፋትም ሆነ በደል ሥርየት የምናገኘው በጾም፣ በንስሓ፣ በጸሎት፣ በምጽዋት እንዲሁም በስግደት በመሆኑ አምላካችን ሊያድነን ስለ ወደደ ይህን ሥርዓት ሠርቶልናል፡፡ በታሪክ መጻሕፍት ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው በበደላቸው ምክንያት የነነዌ ሕዝብ ሊጠፉ በመሆናቸው ከሕፃናት ጀምሮ እስከ አረጋዊ ብቻም ሳይሆን እንስሳት ጭምር የጾሙት የሦስት ቀናት ጾም ‹‹ የነነዌ ጾም›› ተብሏል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የነነዌ ከተማን በሦስት ቀናት ውስጥ ሊያጠፋት እንደ ሆነ ለነቢዩ ዮናስ ሲነግረው ትእዛዙን ከመቀበል ይልቅ ወደ ቴርሰስ ከተማ ለመኮብለል የወሰነው፣ ልብና ኩላሊትን የሚመረምረውንና ምንም ምን ከእርሱ የማይሠወረውን ፈጣሪ ማታለል ስለሚችል ሳይሆን ሐሰተኛ ነቢይ ላለመባል ፈርቶ ነበር እንጂ፡፡

ቸር፣ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነው አምላካችን የነነዌ ሕዝብ በንስሓ፣ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ካልተመለሱ ነነዌ  እንደምትጠፋ እንዲያስተምርና እንዲያስጠነቀቅ ካዘዘው በኋላ በቸርነቱ ሲምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እንደሚባል አስቦ መሸሽን መረጠ፡፡ ‹‹ተነሥና ወደ ነነዌ ሀገር ግባ፤ በድለውኛልና ነነዌ በሦስት ቀን ትጠፋለች ብለህ ስበክ›› አለው። ዮናስ ግን ‹‹የአንተ ምሕረት እጅግ የበዛ ሲሆን ትጠፋለች ብዬ ተናግሬ እሳት ከሰማይ ሳይወርድ ቢቀር ሐሰተኛ ነቢይ ልባል አይደለምን?››  አለና ከእግዚአብሔር ሊሸሽ መንገድ ጀመረ። (ዮናስ ፩፥፩-፫)
እግዚአብሔር አምላክም እንደ ስሙ ትርጓሜ የዋህ የነበረውን የዮናስን ልብ ያውቃልና በድንቅ ጥበቡ የጉዞውን አቅጣጫ ቀይሮ ወደ ነነዌ ምድር ወሰደው፡፡ ታላቅ ነፋስን ይጓዝበት በነበረበት መርከብ ላይ ላከ፤ መርከቡም ሊሰበር ደርሶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ አሸበረ፤ ሆኖም ግን ምክንያቱን ለማወቅ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፤ አንቀላፍቶ የነበረው ዮናስም ‹‹ይህ ማዕበል በእኔ ምክንያት የመጣ ነውና ወደ ባሕሩ ጣሉኝ›› አላቸው፤ እነርሱም እውነቱን ሲረዱ እርሱ እንዳላቸው ባሕር ውስጥ ጣሉት፤ ቀጥሎም አምላክ ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አንበሪ አዘጋጀ፤ ዮናስንም ከዋጠው በኋላ በሆዱ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ፤ ይህም ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ለመኖሩ ምሳሌ ነው፡፡ (ዮናስ ፩፥፬-፲፯፣ ማቴ.፲፪፥፵-፵፩)

ከዚያም ዓሣ አንበሪው ዮናስን በየብስ እንዲተፋው አደረገ፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ ከደረሰ በኋላ የሦስት ቀን መንገድ ዙሮ መስበክ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ነገር ግን የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፤ ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች›› አለ። የነነዌ ሰዎችም የእግዚአብሔርን ቃል አምነው ተቀበሉ፡፡ ማቅ ለበሱ፤ ድንጋይም ተንተራሱ፤ ንጉሡ ስልምናሶር ሳይቀር ከዙፋኑ ወርዶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። ሕፃናት ጡት ተከለከሉ፤ እንስሳትም ጭምር ለሦስት ቀናት ያህል ከሚበሉት ተከለከሉ፡፡ ‹‹ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?›› እንዲል፡፡ (ዮናስ ፫፥፰-፱)

በእርግጥም አምላካችን እግዚአብሔር ወደ እርሱ በመመለሳቸው ምክንያት ለሕዝቡ ምሕረትን አድርጎ የነነዌ ሰዎችን እንዳዳናቸው ከትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ እንረዳለን፡፡ ነቢዩ ዮናስን ግን ይህ ነገር ደስ እንዳላሰኘው ከዚህ በኋላ በተጻፈው ታሪክ እናያለን፡፡ ‹‹ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፤ እርሱም ተቈጣ። ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና። “አቤቱ፥ እለምንሃለሁ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፣ ታጋሽም፣ ምሕረትህም የበዛ፣ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር፡፡ አሁንም አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ” አለው። እግዚአብሔርም “በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን?” አለ።
ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፤ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፤ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ። እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፤ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፤ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት፡፡ ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፤ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና “ከሕይወት ሞት” ይሻለኛል አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን “በውኑ ስለዚህች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም “እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል” አለ።

እግዚአብሔርም “አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፣ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፣ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው፡፡›› (ዮናስ ፬፥፩-፲፩)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ፈጣሪያችን በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረን ለእኛ ለሰዎች እንደሚያዝን፣ ተጸጽቶ ለሚመለስ ደግሞ ምሕረትን እንደሚያደርግ በዚህ ለነቢዩ ዮናስ በምሳሌ አድርጎ በነገረው መሠረት እንረዳለን፡፡ አምላከ ምሕረት እግዚአብሔር በከፋ ደረጃ ለበደሉት ለነነዌ ሰዎች ምሕረትን ያደረገው በሦስት ቀን ጾም ብቻ ነው፡፡ እኛም በሦስቱ ቀናት ጾም እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ባሕርይውን ዝቅ አድርጎ፣ ሥጋን ለብሶ፣ በምድር እንደ ሰው ተመላልሶ፣ መከራን ተቀብሎና ተሰቅሎ፣ በሦስተኛ ቀን በትንሣኤው ትንሣኤን የሰጠን በሦስተኛው ቀን ነውና ይህን ድንቅ ጥበብና የአምላክ ሥራ በዘመከርና በማመን በእውነት መንገድ ተጉዘን በምጽአት ቀን  ሕይወትን ልናገኝ እንዲሁም መንግሥተ ሰማያትን ልንወርስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤ አሜን!!!

በማኅበረ ቅዱሳን 
2024/09/29 06:24:34
Back to Top
HTML Embed Code: