Telegram Web Link
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ተአምሪሁ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘሥዑል በነበልባል፡፡

እሳታዊ ባሕርይ ያለው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡ ልመናው አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ቸር፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው እንደነበር ተነገረ፡፡ ለድኆችና ለችግረኞች  ቸርነትን ያደርግ ነበር፡፡ ሁልጊዜም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ለሰው ሁሉ በጎ ነገርን ያደርግ ነበር፡፡ የአዳም ልጆች ሁሉ ባላጋራ በጎ ነገርን የሚጠላ ሰይጣንም ይህን ባየ ጊዜ ቀንቶ ጽኑ ደዌ አመጣበት፡፡ ሽባ ሆነ፤ ጽኑ ደዌም ታመመ፡፡ ይህም ሰው ደዌው ስለጸናበት ሁልጊዜ ይጮህ ነበር፡፡ ከደዌውም ጽናት የተነሣ ከተኛበት መነሣት ተሳነው፡፡ ስለዚህም ዘመዶቹንና ጎረቤቶቹን ወደ መላእክት አለቃ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን በስውር ተሸክመው እንዲወስዱት ለመናቸው፡፡ እነሱም ሰው ሳያውቅ በሌሊት ወሰዱት፡፡ እንደለመናቸውም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ባለበት ወስደው አስቀመጡት፡፡ ከዚህ በኋላ ያ ሰው በፍጹም ልቡና ወደ ቅዱስ ሚካኤል ይለምን፣ ይማለል፣ ይማልድ ጀመር፡፡ እንዲህ እያለ፡

“ጌታዬ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎትህ ዐስበኝ፡፡ ከአሁንም ና እርዳኝ፡፡ ከዚህ ከአገኘኝ ጽኑ ደዌም ፈውሰኝ፤ አድነኝ፡፡ እኔ አገልጋይህ ልመናህን አምኜ መታሰቢያህን ሳደርግ ኖሬያለሁና፡፡”

ከልቅሶና ከጽኑ እንባ ጋር ደረቱን እየመታ እንዲህ ሲል እኵለ ሌሊት በሆነ ጊዜ በላዩ ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከብርሃን ውስጥ ሆኖ እንዲህ ብሎ ተናገረው፡

“ከዚህ ከደዌህ እግዚአብሔር አድኖሃልነና ከዚህ ከደዌህ ዳን፤ ተነሥ እነሆ እግዚአብሔር አድኖሃል፤ ድኅነትንም ሰጥቶሃል፤ እንግዲህ ዳግመኛ አትበድል፤ ኃጢአት አትሥራ፤ ከዚህ የበለጠ እንዳያገኝህ፡፡”

ይህንን ብሎት እጁን ዘርግቶ ሁለንተናውን ዳስሶ “እግዚአብሔር ፈጽሞ አድኖሃልና ተነሥተህ ሂድ፡፡” አለው፡፡ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ቀንቶ በእግሩ ተነሥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ፈጣሪ እያመሰገነ፡፡ ከደዌውም ስለዳነ ፈጽሞ ደስ አለው፡፡ በፍጹም ደስታ ቃል እያመሰገነ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ሰገደ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህንን ታላቅ ተአምራት ባዩ ጊዜ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገናናነት ፈጽመው አደነቁ፡፡ የተአምራቱን የነገሩን ምስጋና አበዙ፡፡ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ተአምር ያዩትም ለሰው ሁሉ ነገሩ፡፡ ያ የዳነው ሰውም ከቀድሞው ይልቅ በጎ ሥራን አበዛ፡፡ እስኪሞትም ድረስ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያ ማድረጉን አላስታጎለም፡፡ የቸርነትና የይቅርታ መልእክተኛ በሚሆን በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ወደመንግሥተ ሰማያት ገባ፡፡ እኛንም የክብር ባለቤት ጌታ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከኃጢአት ሞት ያድነን፤ ከክፉ ቀን ከመከራ ዘመን ይሰውረን፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ያውርሰን፡፡ በዚህ ዓለም፣ በሚመጣውም ዓለም የሕይወትን ተስፋ ያድለን አሜን፡፡
Forwarded from Bketa @¥
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+*" ማር ፊቅጦር "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ! ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው::

=>እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል:-
+ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና
ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ
ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት
ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ
3ኛ አድርጐ ሾመው::

+የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን
የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ
ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት:
ይወዱትም ነበር::

+እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል
ነበር:: ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ እኩሉን
የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ
እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ
የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ
ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47
ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ::
በመጋዝ ተተረተሩ:: ለአራዊት ተሰጡ:: በግፍም
ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::

+በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ
ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ::
ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::

+ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ
ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ
መኩዋንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና
ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ
ሲል መናቅን መርጧልና::

+ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኩዋንንቱ እየተፈራረቁ
አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት
አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል:
ምላሱንም ቆርጠዋል:: ሚያዝያ 27 ቀን ግን በሰይፍ
አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን
በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::

❖እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:-
"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ:
ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ
ሰማያት አስገባዋለሁ::"

❖ይህች ቀን ማር ፊቅጦር የተወለደባት ናት፡፡ እናቱን ቅድስት ማርታ (ሶፍያንም) እናስባለን፡፡

❖ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::

✞✞ ቅዱስ አውሳብዮስ ካልዕ (ጥዑመ ዜና) ✞✞

=> ቅዱስ አውሳብዮስ በወጣትነቱ ከተባረከች ሚስቱ ጋ
በድንግልና የኖረ; በዘመኑ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ይጸልይ;
4,000
አቡነ ዘበሰማያት በአንድ ቀን ያደርስ የነበረ; ስለ
ሃይማኖትም በቀስት የተወጋ; በእሳት የቃጠለ; አካሉን
ቆራርጠው
የጣሉትና እግዚአብሔር ከሞት ያስነሳው ጻድቅና ሰማዕት
ነው:: ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ ከነሥጋው ወደ ሰማይ
ተነጥቆ ለ14
ዓመታት ቆይቷል:: ወደ ምድርም ተመልሶ ለ40 ዓመታት
በሐዋርያነት ከ85,000 በላይ አሕዛብን ወደ ሃይማኖት
መልሷል::
ጌታም በስምህ የተማጸነውን እስከ 7 ትውልድ
እምርልሃለሁ ብሎታል::"

❖አባቶቻችን ደግሞ 'ስም አጠራሩ የከበረ ዜና ሕይወቱ
ያማረ' ሲሉ ይጠሩታል::

❖ ከበረከቱ ያድለን::

✞ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ (ጥዑመ ዜና)
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መፁን ቀሲስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (የቅ/ፋሲለደስ ልጅ)
6.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
7.አባ ክፍላ
8.አባ ኅብስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ : እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ :
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+*" ማር ፊቅጦር "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ! ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው::

=>እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል:-
+ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና
ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ
ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት
ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ
3ኛ አድርጐ ሾመው::

+የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን
የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ
ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት:
ይወዱትም ነበር::

+እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል
ነበር:: ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ እኩሉን
የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ
እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ
የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ
ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47
ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ::
በመጋዝ ተተረተሩ:: ለአራዊት ተሰጡ:: በግፍም
ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::

+በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ
ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ::
ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::

+ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ
ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ
መኩዋንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና
ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ
ሲል መናቅን መርጧልና::

+ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኩዋንንቱ እየተፈራረቁ
አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት
አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል:
ምላሱንም ቆርጠዋል:: ሚያዝያ 27 ቀን ግን በሰይፍ
አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን
በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::

❖እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:-
"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ:
ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ
ሰማያት አስገባዋለሁ::"

❖ይህች ቀን ማር ፊቅጦር የተወለደባት ናት፡፡ እናቱን ቅድስት ማርታ (ሶፍያንም) እናስባለን፡፡

❖ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::

✞✞ ቅዱስ አውሳብዮስ ካልዕ (ጥዑመ ዜና) ✞✞

=> ቅዱስ አውሳብዮስ በወጣትነቱ ከተባረከች ሚስቱ ጋ
በድንግልና የኖረ; በዘመኑ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ይጸልይ;
4,000
አቡነ ዘበሰማያት በአንድ ቀን ያደርስ የነበረ; ስለ
ሃይማኖትም በቀስት የተወጋ; በእሳት የቃጠለ; አካሉን
ቆራርጠው
የጣሉትና እግዚአብሔር ከሞት ያስነሳው ጻድቅና ሰማዕት
ነው:: ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ ከነሥጋው ወደ ሰማይ
ተነጥቆ ለ14
ዓመታት ቆይቷል:: ወደ ምድርም ተመልሶ ለ40 ዓመታት
በሐዋርያነት ከ85,000 በላይ አሕዛብን ወደ ሃይማኖት
መልሷል::
ጌታም በስምህ የተማጸነውን እስከ 7 ትውልድ
እምርልሃለሁ ብሎታል::"

❖አባቶቻችን ደግሞ 'ስም አጠራሩ የከበረ ዜና ሕይወቱ
ያማረ' ሲሉ ይጠሩታል::

❖ ከበረከቱ ያድለን::

✞ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ (ጥዑመ ዜና)
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መፁን ቀሲስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (የቅ/ፋሲለደስ ልጅ)
6.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
7.አባ ክፍላ
8.አባ ኅብስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ : እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ :
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
Audio
ድርሳን ዘቅዱስ ሩፋኤል ዘወርሃ የካቲት
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት አሥራ ሦስት(፲፫)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ እናሳስባለን " - ቤተክርስቲያኗ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጥንታዊው እና ታሪካዊት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም መሆኑን ገልጻለች።

በተለያዩ ጊዜያትም በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑንም አስታውሳለች።

አሁን ደግሞ 4 አባቶች በታጣቂ ቡድኖች ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ መሆኑን አመልክታለች።

አንድ አባት ደግሞ ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ይፋ አድርጋለች።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ ቤተክርስቲያኗ አሳስባለች።

@tikvahethiopia
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና የተዋሕዶ ጠበቃ ቅዱስ ሳዊሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ †††

††† ቅዱስ ሳዊሮስ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው። ወቅቱ መለካውያን (ሁለት ባሕርይ ባዮች) የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው። ሊቃውንት አንበሳ ሲሉ ይጠሩታል።

ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል። የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል። ንጉሡን ዮስጢያኖስን (Justinian) ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ።

ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ።" አለችው። እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም።" ሲል መለሰላት። አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት።

እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ። መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው። ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ። እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ።

በምድረ ግብጽም የጵጵስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ፤ አጸና። በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ።

አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት። ዶርታኦስ (ዱራታኦስ) በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት ፲፬ ቀን ዐርፏል።

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የድንግል እመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን። የአበውን ሃብትና በረከትም አይንሳን።

††† የካቲት ፲፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፪.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት
፫.አባ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳሳት
፬.ቅዱስ ዳርዮስ
፭.ቅድስት ሊድና

††† ወርኀዊ በዓላት
፩.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
፪.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፬.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
፭.አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

††† "ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።" †††
(ይሁዳ ፩፥፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Audio
ገድለ አቡነ አረጋዊ ዘወርሃ የካቲት
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
õ  a e( ­-5v5 ­ Õ+M  •õ `¨
ASR by NLL APPS
ገድለ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ከምዕራፍ ፩ በከፊል
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት አሥራ አራት(፲፬)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Channel photo updated
2024/09/29 08:17:25
Back to Top
HTML Embed Code: