Telegram Web Link
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † ✞✞✞

† ኅዳር ፳፯ †
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ +"+

=>ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ዝነኛና ታዋቂ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ቁጥሩ ከዓበይት ሰማዕታት ሲሆን የፋርስ ኮከብ በመባልም ይታወቃል:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ("ሙ" ጠብቆ ይነበብ) ተወልዶ ያደገው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ፋርስ (የአሁኗ ኢራን) ውስጥ ነው::

+ያኔ ይህቺ ሃገር በአንድ ወገን ጠንካራ ክርስቲያኖች: በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖትን የሚያመልኩ ጨካኝ ነገሥታት ነበሩባት:: ቅዱስ ያዕቆብም በክርስትና ትምሕርት አድጐ ሚስት አገባ::

+በዘመኑ ከነበረው ንጉሥ ሠክራድ ጋር በጣም ይዋደዱ ነበርና በቤተ መንግስቱ ውስጥ ሹም አድርጐ አስቀመጠው:: በቤተ መንግስት ውስጥ ምቾት የበዛበት ቅዱስ ያዕቆብ የጾምና የጸሎት ሕይወቱ እየቀዘቀዘ መጣ:: በሒደትም ንጉሡ የሚለውን ሁሉ የሚፈጽም ሰው ሆነ::

+አንድ ቀን ግን ሠክራድ ቅዱስ ያዕቆብን "ለእሳትና ለጸሐይ ስገድ: እነሱንም አምልካቸው" ሲል ጠየቀው:: ከመጀመሪያ የተሸረሸረ ነገር ስለ ነበረ "እሺ! ደስ ይበለው" ብሎ ለፀሐይ ሰገደ:: እርሷንም አመለከ::

+ይህቺ ዜና በዘመኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ስትሰማ ታላቅ ሐዘንን ፈጠረች:: ይልቁኑ ሚስቱ: እናቱና እህቱ ይህንን ሲሰሙ አንጀታቸው አረረ:: በዚህ ምክንያትም 3ቱ ተሰብስበው አንድ ደብዳቤ ጽፈው: ተፈራርመው ላኩለት::

+የደብዳቤው ይዘት እንዲህ ይላል:- "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንሀ እኛ አንተን እንደ ልጅ: እንደ ወንድምና እንደ ባል ልናምንህ ይከብደናል::"

+ይህንን ደብዳቤ ልከውለት እነርሱ አካባቢውን ለቀቁ:: ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ተቀብሎ: ወደ ቤቱ ገብቶ ሲያነበው ደነገጠ:: በዚህ ምድር ያሉት ዘመዶቹ ሚስቱ: እናቱና አንዲት እህቱ ብቻ ናቸውና ውስጡ ተሸበረ:: ተደፍቶም ምርር ብሎ አለቀሰ::

+ሲመሽም በቤቱ ውስጥ ወደ ነበረው የቀድሞ የጸሎት ቦታ ሒዶ ተንበረከከ:: ከንጉሡ ጋር በነበረው ያልተገባ ቅርርብ የፈጸመው ስህተት ሁሉ ቁልጭ ብሎ ታየው::

+በጌታችን ፊት ቁሞም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ሲል አምርሮ አለቀሰ::
+ሙሉውን ሌሊት በእንባና በጸሎት አድሮ በጠዋት ንስሃ ገባ:: ከዚያች ቀን ጀምሮም ፍጹም በክርስቶስ ፍቅር ተጠመደ:: ጾምና ጸሎትን ወዳጆቹ አድርጐ ከንጉሡ እልፍኝና አደባባይ ቀረ::

+ይህንን ያወቀው ንጉሡ ሠክራድ ወደ እርሱ አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" አለው:: ቅዱስ ያዕቆብም መልሶ "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል ተናገረው::
+ንጉሡ ቅዱሱን አስቀድሞ ሊያታልለው ሞከረ:: እንቢ ሲለው ግን ደሙ በመሬት ላይ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አስገረፈው:: አስደበደበው:: ጭንቅ መከራዎችንም አሳየው:: ቅዱስ ያዕቆብ ግን በፍቅረ ክርስቶስ ጸና::

+በዚህ የተበሳጨው ንጉሡ እንዲቆራርጡት: ግን ቶሎ እንዳይገሉት አዘዘ:: ከዚያ ቀን በሁዋላ በቀን በቀን እየገቡ ከአካሉ ይቆርጡ ጀመር:: ከእጣቶቹ ተነስተው እጆቹን እስከ ክንዱ: እግሮቹን እስከ ታፋው ድረስ ቆረጡ:: መሐል አካሉ (ወገቡና ራሱ) ብቻ ቀረ::

+ይህ ሄሉ ሲሆን እርሱ ጌታን ይቀድሰው: ይጸልይም ነበር:: "የወይን ግንድ ሆይ! እኔን ቅርንጫፍህ አድርገኝ" (ዮሐ. 15:5) ይለው ነበር:: ከአካሉ እየቆረጡ የጣሉትም ሲቆጠር 42 ሆነ:: 43ኛ ደግሞ የተረፈ አካሉ ነበር::
+ያን ጊዜ ሊጸልይ ፈልጐ "ጌታ ሆይ!" ብሎ ጮኸ:: ይህንን አበው:-
"መንፈቀ አካሉ ጸለየ መዊቶ መንፈቁ" ብለው ገልጸውታል:: ግማሽ አካሉ ሙቶ በቀረው ይጸልይ ነበርና ንጉሡም ከጩኸቱ በሁዋላ አንገቱን በሰይፍ ሲያስመታው ጌታችን ወርዶ ታቅፎ ወደ ሰማይ አሳረገው::

+እናቱ: እህቱ: ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እያለቀሱና እየዘመሩ አካሉን ሰብስበው ገንዘውታል:: ሽቱም አርከፍክፈውበታል:: የዚህ ቅዱስ ገዳም (ታቦት) በኢትዮዽያ: ታች አርማጭሆ በሚባለው በርሃ ውስጥ ይገኛል:: ድንቅ የሆነ የበረከት ቦታም ነው::

+"+ አባ ተክለ ሐዋርያት +"+

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ዐበይት ጻድቃን አንዱ ናቸው:: በተለይ በጻድቁ ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በተባሕትዎም: በትሩፋትም እጅግ የተደነቁ አባት ነበሩ::
+ጻድቁ ሲጠሩ "ዘደብረ ጽሙና": አንዳንዴም "ዘገበርማ" እየተባሉ ነው:: ምናልባትም በብዙ ቦታ ላይ ስለ ተጋደሉ በእነዚህ: ቦታዎችም ላይ ስለ ነበሩ ሊሆን ይችላል እንደዚህ ተብለው የተጠሩት::

+በብዛት የሚታወቀው ደግሞ በምድረ ሸዋ: ጐጃምና በምድረ አፋር አካባቢ በመኖራቸው ነው:: እስኪ አንዳንድ ነገሮቻቸውን እናንሳ:-
*ጻድቁ ክርስቶስን በመከራው ይመስሉት ዘንድ ዘወትር ይተጉ ነበር::
*አንዴ ሥጋ ወደሙ የተቀበለ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲያስመልሰው ተመልከተው ሁሉ ተጸይፎ ሲሸሽ እሳቸው ግን ደስ እያላቸው ተመግበውታል:: ምክንያቱም የእርሳቸው ዓይን የሚመለከተው የፈጣሪን ሥጋና ደም ነው:: በዚህ ጊዜም ጌታ ከሰማይ ወርዶ በግንባራቸው ላይ ፀሐይን ስሎባቸዋል:: በዚህ ምክንየትም ፊታቸው ያበራ ነበር::

*አንዴ ደግሞ በገዳማቸው አንድ ደሮ ለእንግዳ ሊያርዱት ሲሉ "በአባ ተክለ ሐዋርያት ተማጽኛቹሃለሁ!" በማለቱ ትተውታል::
*በአፋር በርሃ አካባቢ ለ14 ዓመታት ኑረዋል::

+በአንድ በአት ውስጥም ለ41 ዓመታት ኑረዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐዋርያት እንዲህ ተመላልሰው በተወለዱ በ71 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

+"+ ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ +"+

=>ቅዱስ ፊልሞና ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ "ጥዑመ-ቃል (አንደበቱ የሚጣፍጥ)" ተብሎ ይጠራል:: በዘመነ ሐዋርያት በጣም ልጅ በመሆኑ እየተሯሯጠ ለአበው ይታዘዝ ነበር::

+ጌታን አምኖ ተከትሎ: ለ3 ዓመት ከ3 ወር ተምሮ: ከቅዱስ መንፈሱ ነስቶ: ከቅዱስ እንድርያስ ጋር ለስብከት ወጥቷል:: ሃገረ ስብከቱም ልዳ ነበረች:: እርሱ ሲያነብ (ሲያስተምር) ሰው ሁሉ በተመስጦ ይሰማው ነበር:: ሊገድሉት የመጡ ወታደሮች እንኩዋ በተደሞ መግደላቸውን ይረሱት ነበር::

+አንዳንድ ቀን ደግሞ ወፎችና ርግቦች ያደምጡት: ያዋሩትም ነበር:: ይህቺ ቀን ለቅዱስ ፊልሞና ዕለተ ዕረፍቱ ናት::

=>አምላከ ቅዱሳን ብርሃናቸውን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
2.አቡነ ተክለ ሐዋርያት ጻድቅ
3.ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ
4.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
6.አባ ገብረ ዮሐንስ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
6.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
=>+"+ ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? .

. . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: +"+ (1ቆሮ. 10:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
5•­3- ØÈ- ó- ë 0cu ---- 16k
ASR by NLL APPS
ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ሰባት(፳፯)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
�-3� �� � � e� =� � 5
ASR by NLL APPS
ድርሳነ መድኃኔዓለም ወገድለ መብዓ ጽዮን ዘሐሙስ
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው”
ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

(ከምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

(በድጋሚ የተፖሰተ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን



✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



ቀናችንን በጸሎት እንጀምር


📌 ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፳፰


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ ስምንት በዚች ቀን የሀገረ ኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማዕትነት አረፈ።


❖ ይህም ቅዱስ በኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ለሆነ ለእስጢፋኖስ ከዘመዶቹ ውስጥ ነው፤ የአባቱም ስም አብርሃም ነው እርሱ የሌዊ ልጅ የዮሴፍ ልጅ ለስምዖን ወንድም ለእስጢፋኖስ እናት ወንድሟ የሆነ ነው።

❖ በተወለደም ጊዜ በአባቱ ስም ስምዖን ብለው ጠሩት አባቱም ሲሞት ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ፤ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ እንዲሔድ አዘዘው እንዳዘዘውም ሔደ፤ እርሱም የመድኃኒታችንን የክርስቶስን ሰው የመሆኑን ምሥጢር ገለጠለት ግን ዘመዶቹ የሆኑ አይሁድን ስለፈራ በኢየሩሳሌም አገር የክርስትና ጥምቀትን ሊአጠምቀው አልደፈረም።

❖ ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ ምን እንደሚያደርግ ሲያስብ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣለት ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ እንዲልከው አዘዘችው።

❖ ሰረባሞንም እየተጓዘ ሳለ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ቀደም ብሎ በሰው አምሳል ወደ ቴዎናስ ቀርቦ ስለ ቅዱስ ሰረባሞን አስረዳው ሰረባሞንም በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግ አስተምሮ የከበረች የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው።

❖ ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ በሆነች በአባ ሳዊሮስ ገዳም ውስጥ መነኰሰ አባ ቴዎናስም በአረፈ ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ጴጥሮስ ተሾመ፤ ያን ጊዜም መልክተኞችን ልኮ ይህን አባ ሰረባሞንን ወደርሱ አስመጥቶ በሊቀ ጵጵስናው ሥራ እንዲራዳው አደረገ።

❖ ከዚህም በኋላ ኒቅዮስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስነት ሾመው፤ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትም በእርሱ ደስ አላቸው እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራትን አደረገ በአገሩ አቅራቢያ ሰዎች የሚያመልኳቸው የጣዖታት ቤቶች ነበሩ ያጠፋቸውም ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸውና በቦታው ላይ ባሕር ሁኖ ሸፈናቸው።

❖ እግዚአብሔርም ከሀገረ ስብከቱ ጣዖታትን ደመሰሰ ዳግመኛም አብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን አንድ አካል የሚያደርግ የሰባልዮስን ስድብ አስወገደ።

❖ ዲዮቅልጥያኖስም ክዶ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ ቅዱስ ሰረባሞን የአማልክትን አምልኮ እንደሚሽር ነገሩት እርሱም ሰምቶ ተቆጣ ወደረሱም እንዲአመጡት አዘዘ ሲወስዱትም ከንጉሥ መልክተኞች ጋር እስክንድርያ ከተማ ደረሰ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስም ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋር ብዙ ካህናት ነበሩ ሰላምታም ሰጡት ፊቱም እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ብሩህ ሁኖ አዩት።

❖ ወደ ንጉሡም በደረሰ ጊዜ በተለያዩ በብዙ ዓይነት ሥቃይ አሠቃየው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ጥፋት በጤንነት አስነሣው፤ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ።

❖ ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ምክንያት በጌታችን እንዳያምኑ ንጉሡ ፈርቶ የእንዴናው ገዥ አርያኖስ ወዳለበት ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያ እንዲአሠቃየውና ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጥ በዚያንም ወቅት መኰንኑ አርያኖስ የኒቅዮስ ከተማ ወደብ አቅራቢያ በመርከብ ውስጥ ነበር።

❖ መርከቢቱም ቆመች ከቦታዋም ሊአንቀሳቅሱዋት አልተቻላቸውም ቅዱስ ሰረባሞንንም አውጥተው ለሀገሩ ደቡብ ወደ ሆነ ቦታ ወስደው በዚያ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በክብር ገነዙትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆች ተአምራት ሆኑ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

📌 በዚችም ቀን በኢትዮጵያ ምድር በደብረ ቊንጽል ተጋድሎውን የፈጸመ አባ ሊቃኖስ አረፈ፤ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡

❖ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ ‹‹ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ›› በማለት ይገልጸዋል፤ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡

❖ የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡

❖ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፤ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፤ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡

❖ በጸሎታቸውም አጋንንትን አውጥተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ዕውራንን አብርተዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡

❖ ስለ ዘጠኙ ቅዱሳን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከአቡነ አረጋዊ ገድል ጋር ጥቅምት 14 በስፋት ስለተጻፈ ከዚያ ላይ ይመለከቷል፤ ከተስዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል፡፡

❖ አቡነ አረጋዊ ጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ፤ አቡ ገሪማ ሰኔ 17 ቀን፣ አቡነ አፍጼ ግንቦት 29 ቀን፣ አቡነ ሊቃኖስ ህዳር 28 ቀን ተሰወሩ፡፡

ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን


📌 ኅዳር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ሊቃኖስ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)

2.ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት



📌 ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን

2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)

3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ

4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ

5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

6.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን



✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



ቀናችንን በጸሎት እንጀምር


📌 ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፳፱


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ለተወለደበት ልደቱ መታሰቢያ ሆነ ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

📌 በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ሰባተኛ የሆነ የተመሰገነና የከበረ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ እርሱም የሰማዕታት መፈጸሚያ በመሆን ነው።



📌 በዚችም ቀን ልደታቸው ኅዳር 29 የሚከበረው ቅዱስ በሌላም በኩል ‹‹እጨ ዮሐንስ ጎንድ ተክለ ሃይማኖት›› በሚል የሚታወቁት ጻድቁ ደመናን ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ የነበረ ሲሆን ቅዱስ መስቀልም ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡

❖ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፤ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡

❖ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፤ ይህ በዘመናችንም እየታየ ያለ ተአምር ነው (የዕረፍታቸውን ዕለት ሐምሌ ሃያ ዘጠኝን ይመለከቷል)

ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን



📌 በዚችም ቀን ለሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት የሆነ የሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ ቀሌምንጦስ በሰማዕትነት አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ከመንግሥት ልጆች ወገን የሆነ ለሮም ንጉሥ የጭፍራ አለቃ ለሆነ ለቀውስጦስ ልጁ ነው ደጎች የሆኑ አባትና እናቱም ቅዱስ ጴጥሮስ የወንጌልን ትምህርት በሰበከ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ገንዘባቸውንም ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋት አድርገው ሰጡ።

❖ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ቀውስጦስ ወደ ንጉሥ ሒዶ በዚያው በዘገየ ጊዜ ወንድሙ የመኰንኑን የቀውስጦስን ሚስት ሊአገባት አሰበ እርሷም በአወቀች ጊዜ አባታቸው እስቲመለስ ወደ አቴና ሔዳ ጥበብን ታስተምራቸው ዘንድ ቀሌምንጦስንና ታናሽ ወንድሙን ይዛ በመርከብ ተሳፈረች።

❖ በዚያንም ጊዜ ብርቱ ነፋስ በመንፈሱ ማዕበል ተነሥቶ መርከቡ ተሰበረ ቀሌምንጦስም በመርከቡ ስባሪ ተንጠለጠለ የባሕሩም ሞገድ ወደ እስክንድርያ አገር አደረሰውና በዚያ ጥቂት ቀኖች ኖረ።

❖ በዚያንም ወቅት የከበረ ሐዋርያ ጴጥሮስ ቃል ጠራውና ወደ እስክንድርያ ሀገር እንዲሔድ አዘዘው በሔደም ጊዜ በውስጥዋ የወንጌልን ቃል ሰበከ ከዚህ ከቅዱስ ቀሌምንጦስ በቀር ከሀገር ሰው አንድ እንኳን ያመነ የለም እርሱ የቅዱስ ሐዋርያ ጴጥሮስን ትምህርት በሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የክርስቶስን ጥምቀትን ተጠመቀ።

❖ ሐዋርያ ጴጥሮስም የጌታችንን የመለኮቱን ምሥጢር ለሚያመልኩትም የሚሰጣቸውን ብልጽግናውንና ክብሩን በስሙም ኃይል ድንቅ ተአምራትም እንደሚደረግ ገለጠለት።

❖ ከዚችም ዕለት ጀምሮ ቀሌምንጦስ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከተለው ደቀ መዝሙሩም ሆነ እርሱም የሐዋርያትን ገድላቸውን ከዐላውያን ነገሥታትና መኳንንት የደረሰባቸውን ሥቃይ ሁሉ ጻፈ።

❖ ከዚህም በኋላ በብዙ አገሮች ውስጥ አስተማረ ሐዋርያትም በጉባኤ ተነጋግረው የሠሩአቸውን የሥርዓት መጻሕፍትን ለርሱ ሰጡት። ከዚህም በኋላ በሮሜ አገር ሊቀ ጵጵስና ተሾመ በትምህርቱም ከሰዎቿ ብዙዎችን እግዚአብሔርን ወደማወቅ መለሳቸው።

❖ ስለርሱም ከሀዲ ንጉሥ ጠራብሎስ ሰምቶ ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጥቶ ክርስቶስን ክደህ ለአማልክት ስገድ አለው ትእዛዙንም ባልሰማ ጊዜ በዚያ ያሠቃዩት ዘንድ ወደ አንዲት አገር ሰደደው እርሱ በላዩ እንዳይነሡበት ከሀገር ሰዎችና ከዘመዶቹ የተነሣ ፈርቷልና መኰንኑንም ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃየው አዘዘው።

❖ የዚያችም አገር መኰንን በመርከቦች ውስጥ የሚኖር እግሮች ያሉት ከባድ ብረት በአንገቱ ውስጥ አንጠልጥሎ ከባሕር ውስጥ አሠጠመው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ወንጌልን እንደ ሰበኩ ሐዋርያትም በመንግሥተ ሰማያት የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ።

❖ እንዲህም ሆነ አንዲት ዓመትም ስትፈጸም ባሕሩ ተገልጦ እንደተኛ ሁኖ የቅዱስ ቀሌምንጦስ ሥጋ በጥልቁ ባሕር ውስጥ ታየ፤ እርሱም ሕይወት ያለው ይመስል ነበር ሰዎችም ገብተው ከእርሱ ተባረኩ የከበረ የደንጊያ ሣጥንም አምጥተው ሥጋውን በውስጡ አድርገው አንሥተው ከባሕር ውስጥ ሊአወጡት ፈለጉ ግን ከቦታው ሊአንቀሳቅሱት አልቻሉም ከባሕር ውስጥ መውጣትን እንዳልፈለገ አወቁ በዚያም ትተውት ወደ ቤቶቻቸው ሔዱ።

❖ ከዚህም በኋላ በመታሰቢያው ቀን በየዓመቱ ያቺ ባሕር ከቅዱስ ቀሌምንጦስ ሥጋ ላይ የምትገለጥ ሆነች ምእመናንም ሁሉ ገብተው ከእርሱ ይባረካሉ መታሰቢያውንም በማድረግ በዓሉን ያከብራሉ ከዚያም በኋላ ወጥተው ወደቤታቸው ይገባሉ።

❖ ከአስደናቂዎች ተአምራቶቹም ከተጻፉት ያዩ ይህን ተናገሩ በአንዲት ዓመት ከሥጋው ሊባረኩ በገቡ ጊዜ የቅዱስ ቀሌምንጦስ ሥጋው ካለበት ሣጥን ዘንድ ሲወጡ ታናሽ ሕፃን እንደረሱ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚወዱት ቅዱሳኑ ክብራቸውን ከርሱ የተቀበሉትንም ጸጋ ይገልጥ ዘንድ ወዷልና።

❖ ወላጆቹም ከወጡ በኋላ ሕፃኑን ፈለጉት ግን አላገኙትም ባሕሩም በላዩ ተከድኖ ነበር ሙቶ በባሕር ውስጥ ያሉ አራዊት የበሉት መስሏቸው አለቀሱለት እንደ ሥርዓቱም በማዕጠንትና በቁርባን ቅዳሴ መታሰቢያውን አደረጉ።

❖ በዳግመኛውም ዓመት ያቺ ባሕር ተገልጣ እንደ ልማዳቸው ገቡ ሕፃኑንም በሕይወት ሁኖ በቅዱስ ቀሌምንጦስ የሥጋ ሣጥን ዘንድ ቁሞ አገኙት በዚህ ባሕር ውስጥ አኗኗርህ እንዴት ነበር ምን ትበላ ነበር የባሕር አራዊትስ እንዴት አልበሉህም ብለው ጠየቁት።

❖ እርሱም ቅዱስ ቀሌምንጦስ ያበላኝ ነበር እግዚአብሔርም በባሕር ካሉ አራዊት ይጠብቀኝ ነበር ብሎ መለሰ ሰምተውም እጅግ አደነቁ በቅዱሳኑና ስለ ከበረ ስሙ ደማቸውን በአፈሰሱ ሰማዕታት የሚመሰገን ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያ ቀሌምንጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


📌 ኅዳር 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ሰማዕታተ ክርስቶስ (ሁሉም)

2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት

3.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ (ዘሮም)



📌 ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት

2.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ

3.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት

4.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ

5.ቅድስት አርሴማ ድንግል
አባታችን ጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በኢየሩሳሌም አውራጃ ሳሬራ በሚባል ቦታ ኅዳር 29 ቀን ተወለዱ። አቡነ ዮሐንስ በልጅነታቸው በእመቤታችን አማካኝነት እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉትና ኑሯቸውም እንደ መላእክት እንደሚሆን ተነግሯቸው በአገልግሎት ሲጋደሉ ቆይተው በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መንኩሰው ለዘመናት በጾም በጸሎት ተጋድሎ ፈጽመው ተአምራትንም በማድረግ መላ ኢትዮጵያን ዞረው አስተምረው ሐምሌ  29  ዐርፈዋል።
የጻድቁ አባታችን አቡነ ዮሐንስ በረከት በሁላችንም ላይ ይደር አሜን።

''ጻድቃን ጮኹ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው''
              መዝ.34፥17

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://www.tg-me.com/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"

#ታላቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ
Daniel:
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ ንጉሥ "አፄ ገብረ መስቀል" እና "ቅዱስ አካክዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችህ ✞✞✞

" ኅዳር 30 "

+"+ ጻድቅ አፄ ገብረ መስቀል +"+

=>የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ነገሮቿ የታደለች ናት:: ከእነዚህም መካከል በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ነገሥቶቿ (መሪዎቿ) ቅዱሳን (ጻደቃን) ናቸው:: ለአንዲት ሃገር የመሪዎቿ ጥሩ ክርስቲያን መሆን እጅግ ወሳኝ ነው::

+ባለፉት 40 ዓመታት እንኩዋ የደረሰብንን የመንፈስ ዝለትና የሞራል ዝቅጠት ስንመለከት አንድም ችግሩ ከመሪዎቻችን እንደ ሆነ እናስተውላለን:: የሃገራችንን ታሪክ ስንመለከት ግን በእሳትና በጦርነት መካከል ሆነው ለፈጣሪ የተገዙ ብዙ ነገሥታትን እናገኛለን::

+እንደ ምሳሌም:-
1.ንግሥተ ሳባ
2.ቀዳማዊ ምኒልክ
3.አብርሐ ወአጽብሐ
4.ካሌብ
5.ገብረ መስቀል
6.ሐርቤ
7.ላሊበላ
8.ይምርሐ
9.ነአኩቶ ለአብ
10.ዳዊት
11.ቴዎድሮስ ቀዳማዊ
12.ዘርዓ ያዕቆብ
13.በእደ ማርያም
14.ናዖድ
15.ልብነ ድንግል
16.ገላውዴዎስ
17.ዮሐንስ
18.ኢያሱ ቀዳማዊና
19.ተክለ ሃይማኖት መናኔ መንግሥትን እናገኛለን::

+ከእነዚህ መሪዎቻችን መካከል እኩሉ መንግስታቸውን ትተው በርሃ የገቡ ሲሆኑ እኩሉ ደግሞ በዙፋናቸው ላይ ሳሉ በጐ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ በጥፋታቸው ተጸጽተው ንስሃ የገቡ ናቸው::

+ከነገሥት ጻድቃን መካከልም ይህች ዕለት የአፄ ገብረ መስቀል መታሰቢያ ናት:: ጻድቁ ንጉሥ የአፄ ቅዱስ ካሌብ ልጅ ሲሆን በኢትዮዽያ የነገሠው በ515 ዓ/ም ነው:: ሲነግሥም እጅግ ወጣት ነበረ:: ምክንያቱም አባቱ ካሌብ ከናግራን ጦርነት መልስ በመመነኑ በዙፋኑ የተቀመጠ ልጁ እርሱ ነበርና::

+ከዚህ ቅዱስ የመጀመሪያ የምናደንቀው ስሙን ነው::
የዛሬ 1,500 ዓመት እንኩዋ በመስቀል የሚመኩ:
ለመስቀል የሚገዙ መሪዎች መኖራቸው በዘመኑ የነበረውን
የክርስትና ደረጃ ያሳያል:: "ገብረ መስቀል" ማለት
"የመስቀል አገልጋይ (ባሪያ)" ማለት ነውና::
+አፄ ገብረ መስቀል በጐ ንጉሥ እንዲሆን የቅዱስ አባቱ
ማንነት የረዳው ይመስላል:: ያ ኃያል: ብርቱና ዓለም
የፈራው አባቱ ሲጀመር በፍቅረ ክርስቶስና በድንግል እናቱ
ፍቅር የተያዘ ደግ ሰው መሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ያለ
ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስቱን እንደ ጨርቅ ትቶ ሲሔድ
መመልከቱ እርሱንም ያው አድርጐታል::
+እርሱም ከአባቱ እንዳየው በአክሱም ላይ በነገሠባቸው
ዓመታት በጾምና በጸሎት: ፍትሕ ርትዕ ሳደያጉዋድል:
ድሃም ሳይበድል ይኖር ዘንድ ጥረት አድርጉዋል::
+"+ አፄ መስቀል +"+
=>ይህ ጻድቅ ንጉሥ ለእኛ ከተወልን ትሩፋቶቹ አንዱ በዓለ
መስቀልን በአደባባይ ማስከበሩ ቅድሚያውን ይይዛል::
በዓሉ መስከረም አካባቢ የሚደረግ ሲሆን "አፄ መስቀል"
ይባላል::
+ሕዝቡ: ካህናቱና መሳሣፍንቱ አድዬ አበባ እየዘነጠፉ
ወደ ንጉሡ አደባባይ ይተማሉ:: በዚያም በያሬድ ዝማሬ
ለቅዱስ መስቀሉ ታላቅ በዓል ይከበራል:: ይህ በዓል
ይኼው ዛሬ በUNESCO ተመዝግቧል::
+"+ ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ +"+
=>ሃገራችን ታላቁን ሰማያዊ ዜማ ያገኘችው በአፄ ገብረ
መስቀል ዘመን ነው:: ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ያገኘውን
ማኅሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በአክሱም ጽዮን:-
"ሃሌ ሉያ . . .! ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ::
ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ
ለደብተራ::" ብሎ ከ3ቱ ጸዋትወ ዜማ በአንዱ በአራራይ
ሲያዜም ንጉሡ በዜማው ተመስጦ እየሮጠ ወደ ጽዮን
ደርሷል::
+ከዜማው ጥፍጥና (ጣዕም) የተነሳ ሁሉም ተደመሙ::
ንጉሡም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከቅዱስ ያሬድ የማይለይ
ሆነ:: ስብሐተ እግዚአብሔርንም ለብዙ ጊዜ ከቅዱሱ ሊቅ
በጥዑም ዜማ ተቀምሞለት ተመገበ::
+እንዲያውም አንዴ ሊቁ ሲያዜምለት ጻድቁ አፄ ገብረ
መስቀል የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መንግስቱን
ተክሎበታል:: ሁለቱም ከተመስጧቸው ሲነቁ ግን ንጉሡ
ደንግጦ "ምን ልካስህ?" ቢለው "ወደ በርሃ አሰናብተኝ"
አለው::
+አፄ ገብረ መርስቀልም እያዘነ ፈቅዶለታል:: ቅዱስ
ያሬድም ከመሬት ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፎ: የመሰናበቻ
ምስጋናን:-
"ውዳሴ ወግናይ: ለእመ አዶናይ: ቅድስት ወብጽዕት . . ."
ብሎ አንቀጸ ብርሃንን: በሚጣፍጥ ዜማ ሰተት አድርጐ
አደረሰ:: ይህንን ሲሰማ ንጉሡ ፈጽሞ አለቀሰ::
+እስከ መንገድ ድረስ ከሕዝቡና ሠራዊቱ ጋር ከሸኘው
በሁዋላም ቅዱስ ያሬድ ጸለምት ላይ ሲደርስ በዜማ
አሰምቶ "ሰላም ለኩልክሙ" አለ:: አፄ ገብረ መስቀልና
ሕዝቡም "ምስለ መንፈስከ" ብለውት ቀና ሲሉ ከዓይናቸው
ተሰወረ:: ንጉሡም በዘመኑ ማኅሌተ ሰማይ እንዲስፋፋ
ብዙ ጥሯል::
+"+ ንጉሡና 9ኙ ቅዱሳን +"+
=>ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ወንጌልን እንዲሰብኩ:
መጻሕፍትን እንዲተረጉሙና ገዳማዊ ሕይወትን
እንዲያስፋፉ አፄ ገብረ መስቀል ትልቅ ጥረት
አድርጉዋል::
+በተለይ ከአባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል
ጋር ልዩ ቅርበት ነበረው:: ዘወትርም ከእነርሱ ይባረክ
ነበር:: አቡነ አረጋዊንም በየጊዜው ይጐበኛቸው እንደ ነበር
ይነገራል::
+"+ ንጉሡና ታቦት +"+
=>ልክ እንደ ቅዱስ መስቀሉ ሁሉ ታቦተ እግዚአብሔር
በዑደት እንዲከበር ያደረገ ይህ ንጉሥ ነው ይባላል::
መነሻው ደግሞ የደብረ ዳሕሞ መታነጽ ነው::
አንድ ቀን አቡነ አረጋዊን ምን እንደሚሹ ቢጠይቃቸው
"የድንግል እመቤታችን ማርያምን መቅደስ አንጽልኝ"
አሉት::
+በደስታ አንቆጥቁጦ አነጻት:: የምርቃቱ ዕለትም ንጉሡ:
ጻድቁና ሊቁ (ማለትም ገብረ መስቀል: አረጋዊና ያሬድ)
ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ተገኙ:: በጊዜውም ታቦቱ ሲነግሥ
ቅዱስ ያሬድ ባቀረበው ማኅሌታዊ ዜማና አበው ባደረጉት
ዝማሬ: ታቦቱ እየዞረ ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ሆነ::
+ደብረ ዳሞ ያኔ መወጣጫ ደረጃ ነበረው:: ንጉሡና
ቅዱስ ያሬድ ከበዓል ሲመለሱ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄ
መወጣጫው ተደርምሷል::
+ጻድቁ "ዳሕምሞ (ደርምሰው)" ስላሉት ቦታው ዳሕሞ
(ዳሞ) ተብሎ ቀርቷል:: ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል
ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::
+"+ ቅዱስ አካክዮስ +"+
=>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ቅዱሳን
ሊቃውንት አንዱ ነው:: ተወልዶ ያደገው በቁስጥንጥንያ
ሲሆን ትምሕርተ ሃይማኖትንም እዚያው ተምሯል:: በ451
ዓ/ም ጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን) ሲጠራ እሱም
ጥሪ ደርሶት ነበር::
+ነገር ግን ከመጀመሪያው ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን
የተበተቡትን ሴራ ያውቅ ነበርና ሳይሔድ ቀረ:: ጉባኤው
ተጠናቆ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ መገደሉንና ሃይማኖት መካዱን
(በተሰብሳቢዎቹ) ሲሰማ አዘነ::
+ንጉሡን ረግሞ "ጌታ ሆይ! ከዚህ ከረከሰ ጉባኤ
ያልደመርከኝ ተመስገን" አለ:: ከጥቂት ዓመታት
በሁዋላም ምዕመናን ሃይማኖቱ የቀና መልካም እረኛ
መሆኑን ሲረዱ የታላቂቱ ቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ
አድርገው ሾሙት::
+ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ:: ወዲያው ግን ከመሪዎች
ተዋሕዶን እንዲተው ትዕዛዝ መጣለት:: እንቢ በማለቱም
ስደት ተፈርዶበት በስደት ላይ ሳለ ዐርፏል::
=>አምላከ ነገሥት ጻድቃን ቅኑን መሪ በሁሉም ሥፍራ
ያድለን::ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::=>ኅዳር 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አፄ ገብረ መስቀል ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ አካክዮስ ሊቅ
3.ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ
4.ቅዱስ አናንዮስ ዘዓምድ
5.አባ መርቆሬዎስ ሰማዕት

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት


++"+ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ
እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::የልቡን ፈቃድ
ሰጠኸው::የከንፈሩንም
ልመና አልከለከልኸውም::በበጐ በረከት
ደርሰህለታልና::ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ
አኖርህ::ሕይወትን ለመነህ
ሰጠኸውም::ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ::በማዳንህ ክብሩ
ታላቅነው:: +"+ (መዝ. 20:1-5)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2024/10/01 04:52:49
Back to Top
HTML Embed Code: