Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ነሐሴ ፲ (10) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያዊ_ጻድቅ ለአባታችን #ለአቡነ_ለዓቢየ_እግዚእ ተከዜ ወንዝ እንደ ባሕረ ኤርትራን ከፍለው ለተሻገሩበትና ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብን ላሳመኑበት ዓመታዊ ለተአምር በዓል በሰላም አደረሰን።

                           
#አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ_ያደረጉት_ተአምር_ይህ ነው፦ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ዐሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።

ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ዐሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል። ከአባታች አቡነ ዓቢየ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳዮስ አበበ።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

            #ነሐሴ ፲፩ (11) ቀን።

እንኳን #ለአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ሞይስስ_ለዕረፍትና ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ለሆነ #ለቅዱስ_አብጥልማዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከአረፉ በአንጾኪያ ከተማ የሠራዊት አለቃ #ከነበረው_ከቅዱስ_ፋሲለደስ በሰማዕትነት ከዐረፉ ማኅበሮች #ከሦስት_መቶ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                          
#የአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ሞይስስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም ነበረ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ ተምሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባ። በአንድ ጻድቅ ሰው ዘንድም መነኰሰ በዚያም እያገለገለ በጠባብዋ መንገድም ተጠምዶ ያለመብልና መጠጥ ያለእንቅልፍም እየተጋደለ ዐሥራ ስምንት ዓመት ኖረ።

ከብዙ ፍቅርና ትሕትና ጋር ዘወትር በጾምና በጸሎት ይተጋ ነበር። ትሩፋቱም በበዛ ጊዜ ከአባ ገሞስ በኋላ በአውሲም ከተማ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። ይህም አባ ሞይስስ በተሾመ ጊዜ ትሩፋት መሥራትን አብዝቶ ጨመረ ስለ እነርሱም በጸሎት እየተጋ መንጋዎቹን ነጣቂዎች ከሆኑ ከዲያብሎስ ተኲላዎች ጠበቀ።

በሕይወቱም ዘመን ሁሉ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ የሚሰበስብ አልነበረም። አባ ሚካኤልም በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜና ደሙ ሳይፈስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ ይህ አባ ሞይስስ በእሥር ቤት ከእርሱ ጋር ነበር ብዙ ስለገረፉት እግሮቹንም ለረጅም ጊዜ በእግር ብረት አሥረው ስለ አሠቃዩት ብዙ መከራ ደረሰበት።

በዚህ አባት ሞይስስ እጅም እግዚአብሔር ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ የሚያውቁትም በተአምራቶቹ ደግነቱንና ትሩፋቱን ተረዱ። ዳግመኛም ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ከመሆኑም በፊት ብዙ ነገርን ተናገረ እንደተናገረውም ይሆን ነበር። የምስር ኤጲስቆጶስ ስለሆነው ስለ አባ ቴዎድሮስ ከሔደበት እንደማይመለስ ትንቢት ተናግሮበት እንዲሁ ተፈጸመበት።

ዳግመኛም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ነበር። ብዙዎች ሕሙማንንም ፈወሳቸው። ገድሉንም በመልካም ሽምግልና ፈጸመ። እግዘአብሔርንም አገልግሎ ጥቂት ታመመ የሚያርፍበትንም ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና ባረካቸው በቀናች ሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነሐሴ 11 ቀን ዐረፈ። አለቀሱ ለትም ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ በዝማሬና በማኀሌት በታላቅ ክብር ገንዘው ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም የሚሆን ፈውስ ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋነ ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት በአባ ሞይስስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                           
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_አብጥልማዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ነው። ቅዱሱንም ክርስቲያን እንደሆነ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። መኰንኑም በአስቀረበው ጊዜ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃይቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብጥልማዎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

                           
"#ሰላም_ዕብል_ለሞይስስ_ፍጹም። ኤጲስቆጶስ ዘብሔረ አውሲም። ለጸሎት ዘተግሀ ወተጋደለ በጾም። አመ ርሥእናሁ በንስቲት ሕማም። እምፃማ ዓለም አዕረፈ ዮም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የነሐሴ_11

                           
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20 እና የሐ ሥራ 12፥18-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

† እንኳን ለቅዱስ አባ ሞይስስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

†  🕊  ቅዱስ አባ ሞይስስ ጻድቅ  🕊

† ቅዱሱ በኋላ ዘመን ከተነሱ አበው አንዱ ሲሆን ትውልዱ: ነገዱ ከግብፅ ነው:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ ቢሆንም ክርስቲያኖች ጠንካሮች ነበሩ:: አባ ሞይስስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: ገና በልጅነት ወደ ትምህርት ቤት ገብቷል::

† የዘመኑ ትምሕርት ሁለት ወገን ሲሆን

፩ኛው የሃይማኖት ትምሕርት::
፪ኛው ደግሞ ፍልስፍና ነበር::
የጻድቁ ምርጫው የቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ነበርና ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እንደሚገባ ተምሮ ስለ ነበርም ዲቁናን ሹመውት ተግቶ አገልግሏል::

ከጥቂት ዘመናት በኋላም በተሻለው ጐዳና እግዚአብሔርን ሊያገለግል ተመኘ:: ይህቺን ዓለምም ይንቃት ዘንድ ወደደ:: መልካም ምኞትን መፈጸም ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና የልቡናውን ተምኔት ፈጸመለት:: ከከተማ ወጥቶ: ቁራጭ ጨርቅ ለብሶ ገዳም ገባ::

በዚያም በረድእነት ያገለግል ገባ:: በፍጹም ልቡ በትሕትና እግዚአብሔርን ደስ አሰኘ:: በጉብዝናው ወራት ይህንን መርጧልና:: ገዳሙንም ሲያገለግል ዕረፍትም አልነበረውምና በመነኮሳት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው::

ከጊዜም በኋላ "በቅተሃል" ብለው አበው ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና: ከምንኩስና ወደ አስኬማ አሸጋግረውታል:: እርሱም ለአሥራ ስምንት ዓመታት አገልግሎቱን ሳያስታጉል: ወጥቶ ወርዶ ገዳሙን ረድቷል:: በእነዚህ ጊዜያት በጸሎት: በጾምና በስግደት ይጋደል ነበር::

በጠባዩም ትእግስትን: ትሕትናን: ተፋቅሮን የሚያዘወትር ነበር:: ጐን ለጐንም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይፋጠን ነበር:: በዘመኑ የግብፅ ፓትርያርክ አባ ሚካኤል ይባሉ ነበር::
አውሲም በምትባል አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ዐርፎባቸው "ማንን ልሹም" እያሉ ይጨነቁ ነበርና እግዚአብሔር ስለ አባ ሞይስስ ገለጠላቸው::

አባ ሚካኤልም "ለሕዝቤ የሚጠቅም መልካም እረኛ አገኘሁ" ብሎ ደስ አለው:: ጊዜ ሳጠፋም እርሱን አስጠርቶ "ተሾም" አለው:: አበው ትሕትና ሙያቸው ነውና "አይቻለኝም: ተወኝ ይቅርብኝ" ሲል መለሰ::

አባ ሚካኤል ግን "የምሾምህ መቼ በሰው ፈቃድ ሆነና: በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ" ብሎ ዕለቱኑ ሹመውታል:: እርሱም የአውሲም ጳጳስ ሆኗል:: ቅዱሱ አባ ሞይስስም ወደ ሃገረ ስብከቱ ሔዶ አገልግሎቱን ጀመረ::

በጵጵስና ዘመኑ እንደ ከተማ ሰው መኖርን: የሥጋ ምቾትን አልፈለገምና ጠባቡን መንገድ መርጧል:: በገዳም ሲሰራው ከነበረው ተግባር መካከል ያቋረጠው አልነበረም:: ከብቃቱ የተነሳ ለወደፊት የሚደረገውን ያውቅ ነበር:: እርሱ የተነበየው ሁሉ ተፈጽሟልና::

ሕዝቡን ይመራቸው ዘንድም ተግቶ ያስምራቸው ነበር:: ዘወትርም ከክፋት: ከኃጢአት ይጠብቃቸው ዘንድ ይጸልይላቸው ነበር:: ያዘኑትን ሲያጽናና: በደለኞችን ሲገስጽ ዘመናት አለፉ:: አንድ ወቅት ላይም ስለ ሃይማኖቱ ታሥሮ በረሃብ ተቀጥቷል: ግርፋትንም ታግሷል::

ጻድቁ ጳጳስ አባ ሞይስስ እንዲህ ተመላልሶ የሚያርፍበት ቀን ቢደርስ ሕዝቡን ሰበሰባቸው:: "እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሔዳለሁና ሃይማኖታችሁንና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ" ብሏቸው በትእምርተ መስቀል አማትቦ ዐረፈ:: ምዕመናንም በብዙ እንባና ምስጋና ቀብረውታል:: ከተቀደሰ ሥጋውና ከመቃብሩም ብዙ ተአምራት ታይተዋል::

† አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ አባት በረከት ይክፈለን::

🕊

[  † ነሐሴ ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አባ ሞይስስ
፪. ቅዱስ አብጥልማዎስ
፫. ሦስት መቶ ሰማዕታት [የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበር]

[  † ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፫. ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፬. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
፭. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት

† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" † [ሐዋ. ፳፥፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

† እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

†  🕊 ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ  🕊

† ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒ እና ከአባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የመከራ ጊዜ] ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር::

ክርስቲያኖችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በተደረገው የአርባ ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

ይህች ዕለት ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የነገሠባት ናት::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- በ፫፻፲፪ [312] ዓ/ም ዓለምን አስጨንቀው ሲገዙ ከነበሩ ነገሥታት አንዱ የሮሙ ቄሣር መክስምያኖስ ነበር:: ክርስቲያኖችን ከግዛቱ ያጠፋ ዘንድ ብዙ ጊዜ ሞክሯል::

በሰይጣን ምክር አብያተ ክርስቲያናትን ዘግቷል: መጻሕፍትን አቃጥሏል: ምዕመናንንም ጨፍጭፏል:: ነገር ግን ሰማዕታት አንዱ ሲሰዋ አንድ ሺውን እየተካ [በእምነት እየወለደ] ነውና እንኳን ሊጠፉ በየቀኑ ይበዙ ነበር::

ምንም የሚሊየኖችን ደም ቢያፈስም ክርስቲያኖች ከጽናታቸው የሚነቃነቁ አልሆኑም:: በዚህም ስለ ተበሳጨ ከክርስቲያኖች አልፎ በአሕዛብም ላይ ግፍን ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ የበራንጥያው ንጉሥ ቁንስጣ ዐርፎ ልጁ ቆስጠንጢኖስ ነግሦ ነበርና የሮም ሰዎች ዝናውን ሰሙ::

በእርሱ መንግስት ፍርድ አይጓደልም: ደሃ አይበደልም: ግፍም አይፈጸምም ነበርና ይህንን ያወቁ የሮም ሰዎች መልዕክተኛ ልከው ከአውሬው መክስምያኖስ እንዲያድናቸው ተማጸኑት:: እርሱም ነገሩን ሲሰማ አዝኖ: ከመከራ ሊታደጋቸውም ወዶ: ሠራዊቱን አስከትቶ ተነሳ::

ወደ ጦርነት እየሔደ ካረፈበት ወንዝ ዳር በመንፈቀ መዓልት [ስድስት ሰዓት ላይ] ድንገት ከሰማይ ግሩም ተአምርን ተመለከተ:: የብርሃን መስቀል በከዋክብት አጊጦ: ሰማይንም ሞልቶ: ብርሃኑ ፀሐይን ሲበዘብዛት: በላዩ ላይም "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍ ተስሎበት አየ::

"ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ አንድ ደፋር ክርስቲያን ወታደር [አውስግንዮስ ይባላል:: አርጅቶ በመቶ አሥር ዓመቱ ሰማዕት ሆኗል::] ወደ ንጉሡ ቀርቦ "ይሔማ አዳኝ ሕይወት የሆነ መስቀለ ክርስቶስ ነው::" ብሎታል::

ይሕንን እያደነቀ ሳለም በሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ነገሩን ገለጠለት: ምሥጢሩንም ተረጐመለት:: "ኒኮስጣጣን ማለት 'በዝየ ትመውዕ ጸረከ-በዚህ መስቀል ጠላትህን ድል ታደርጋለህ' ማለት ነው::" አለው::

በነጋ ጊዜም ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በሁሉም የጦር እቃ [በወታደሩ: በጦሩ: በፈረሱ: በጋሻው . . .] ላይ የመስቀል ምልክትን ሠርቶ መክስምያኖስን ገጠመው:: በኃይለ መስቀሉም ድል አድርጐ ማረከው:: የተረፈው የአሕዛብ ሠራዊትም እሸሻለሁ ሲል ድልድይ ተሰብሮበት ወንዝ ውስጥ ገብቶ አለቀ::

† ቅዱሱ ንጉሥም በኃይለ መስቀሉ ሮሜን እጅ አደረጋት::
"ሃይማኖተ ክርስቶስ ነሢኦ ወዘመስቀሉ ትርጓሜ:
ቆስጠንጢኖስ ዮም ነግሠ በሮሜ:
ዘመክስምያኖስ ዕልው ድኅረ ኀልቀ ዕድሜ::" እንዲል::

ቅዱሱ ንጉሥ ድል አድርጐ በዚህች ቀን ወደ ሮም ሲገባ ከመከራና ሞት የተረፉ ክርስቲያኖች ዕፀ መስቀሉን ይዘው በዝማሬ ተቀብለውታል:: እርሱም በዚህች ቀን በ፫፻፲፪ [312] ዓ/ም በሮም ግዛት ሁሉ ላይ ነግሦ ለሰባት ቀናት በዓለ መስቀልን በድምቀት አክብሯል:: በዘመኑ ሁሉም ቅዱስ ሚካኤል አልተለየውምና ወዳጁ ሲባልም ይኖራል::

ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያት እና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ አርፏል::
"ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::

† ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: ደግ መሪ: መልካም አስተዳዳሪን ያድለን:: ከቅዱሱ ንጉሥም በረከትን ያሳትፈን::

🕊

[  † ነሐሴ ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ [ጻድቅ ንጉሥ]
፪. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

[    †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፫. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ድሜጥሮስ
፭. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፮. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ሰማዕት]
፯. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፰. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

" እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" [፩ጢሞ. ፪፥፩-፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ነሐሴ ፲፪ (12) ቀን።

እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ #ንግሥት_ቅድስት_ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ ለተላከበት ለእርሱም ጠላቶቹን አሸንፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ለሰጠበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓሉ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰበው፦ ከንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ_ወደ_ሮሜ ከተማ ከገባበትና በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ከነገሠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
                     
                           
በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ የከበረ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ እሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስካሸነፍቸው መንግሥቱን እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።

ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እንድናደርግ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

                            
በዚችም ቀን #ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮች ሁሉ ላይ ነገሠ። ዜናውንም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ጽፈናል። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 12 ስንክሳር።

                           
"#ሰላም_ለከ_መልአከ_ኪዳኑ_ወምክሩ። ለእግዚአብሔር ልዑል ዘግሩም ግብሩ። በረድኤትከ ረዋጺ ዘአሠረ ነፋስ አሠሩ። ሶበ ላዕሌየ እኩየ መከሩ። ጉባኤ ፀርየ #ሚካኤል ዝሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_12

                           
#የዕለቱ_ማኅሌቱ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።

                           
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

እንኳን #ለጾመ_ፍልሰታ_ሁለተኛ_ሳምንት ለዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                          ✝️ ✝️ ✝️
#የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ በ፪ ሃሌ ሉያ "ዛቲ ይእቲ #ማርያም_ማኅደረ_መለኮት እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን #በከመ_ይቤ_ዳዊት በመዝሙር አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር አድባረ ድኁኃን ተሰማየት #ዛቲ_ይእቲ_ቅድስት_ድንግል ተዓቢ እምኵሉ ፍጥረት ኢያውዐያ እሳት መለኮት"። ትርጉም፦ ሰንበተ ክርስቲያን የተሰኘችው #የመለኮት_ማደሪያ_ይህቺ_ማርያም_ናት#ዳዊት_በመዝሙር ዐይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ (አቀናሁ) ብሎ እንደተናገረው ያቺ ተራራ የተራሮች ራስ ይህቺ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ናት፤ እርሷም ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች የመለኮት እሳት አላቃጠላትም። #ሊቁ_ቅዱስ ያሬድ_በድጓው_ላይ።

                           ✝️ ✝️ ✝️
#የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14 ወይም 120፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-19፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8፣ የሐዋ ሥራ 27፥31-38። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39፥47። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
2024/11/16 13:31:27
Back to Top
HTML Embed Code: