Telegram Web Link
Channel photo updated
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
🌿እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

♱ቅዱስ ኤዺፋንዮስ

📝ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው።

💡ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው።

📝ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ።

📝ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር።

💡አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ።

📝ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ። በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ።

📝 እግዚአብሔርም ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች።

📝ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ.ም. ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር።

🤲አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን!

🗓 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)
2. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ
3. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ
4. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ

🗓 ወርኀዊ በዓላት

1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4. አባ ገሪማ ዘመደራ
5. አባ ዸላሞን ፈላሢ
6. አባ ለትጹን የዋህ

📖"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።'' (1ቆሮ. 9:25)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ ፦ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
Forwarded from M.A
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ግንቦት ፲፯ (17) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከኢየሩሳሌም ከዮርዳዮስ ያመጡት ውሃ እስከ ዛሬ በገዳማቸው መነኰሳት የሚጠቀሙት ለሆነ፤ ገርዓልታ እና ሐውዜን ላይ እጅግ አስገራሚ ሁለት ታላላቅ ገዳማትን ለገደሙት #ለአቡነ_ገብረ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።

                          
#አቡነ_ገብረ_ሚካኤል፡- እኚህ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በታላቅ ተጋድሎአቸው ይታወቃሉ፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ ሚካኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማርና አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደሶችን በማነጽ ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እጅግ አስናቂው ገዳማቸው ገርዓልታ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡

ከገርዓልታ በደቡባዊ አቅጣጫ የሚገኘው ይህ የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ገዳም እንደ ደብረ ዳሞ በገመድ ብቻ ከሚወጣው ከአቡነ ገብረ ናዝራዊ ገዳም ጋር የሚዋሰን ሲሆን ገዳሙ ለመድረስ የመኪናውን መንገድ ከጨረሱ በኋላ በእግር አንድ ሰዓት ይፈጃል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ጻድቁ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ብዙ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ የጌታችን የሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውና ጻድቁ ያደርጉት የነበረው የድንጋይ ቆብ፣ መቋሚያቸው፣ የእጅ መስቀላቸውና መጻሕፍቶቻቸው ይገኛሉ፡፡ ሌላው አስደናቂ ነገር ሀገሩ በረሃ ቢሆንም ጻድቁ ከኢየሩሳሌም ዮርዳኖስ ያመጡትና ዋሻው ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ያጠራቀሙትን ውኃ መነኰሳቱ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ውኃው ግን ከዓመት እስከ ዓመት መጠኑ አይቀንስም፡፡

ሊቀ ብርሃናት መርቆርዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክና ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በሚሉት ሁለት መጽሐፎቻቸው ላይ እንደጠቀሱት በገዳሙ ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት የምትበራው አንዲት ጧፍ ብቻ ናት፡፡ ጧፏ ነዳ የማታልቅ ስትሆን አለቀች ትቀየር ሳትባል አስገራሚ በሆነ ተአምር ከዓመት እስከ ዓመት ትበራለች፡፡ ሌላኛው የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ከሀውዜን ከተማ በስተደቡብ አቅጣጫ ከአስደናቂው የአቡነ ይምዓታ ጎሕ ገዳም 16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ነው፡፡ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ይሄኛውም ገዳማቸው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂውን ዋሻ ፈልፍለው ከጨረሱ በኋላ ግድግዳውና ዓምዶቹ ላይ የሳሏቸው የሐዋርያትና የቅዱሳን ሥዕላት ከጥንታዊነታቸው በተጨማሪ እጅግ ውብና አስደናቂ ናቸው፡፡ ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ጻድቁ ቅዱሳት ሥዕላቱን የሳሏቸው በሸራ ላይ ሳይሆን በአሸዋማው የዋሻው ፍልፍል ግድግዳ ላይ መሆኑ ነው፡፡ ከአባታችን አቡነ ገብረ ሚካኤል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

ምንጭ ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ግንቦት ፳ (20) ቀን።

እንኳን #ለሀገረ_ቶና ለከበረ ልታስተው የመጣችውን ሴት በማስተማር ለቅድስና ላበቃ #ለአባ_አሞንዮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር ከምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰብት፦#አባ_አሞንዮስ ለቅድስና ካበቃት #ከቅድስት_ሳድዥ ከመታሰቢያዋ፣ #ከቅዱስ_አሞኒ ረድእ #አባ_ዳርማ ከዕረፍት፣ #ከአባ_ኄሮዳና #ከአባ_ዘካርያስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉበት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                          
#አባ_አሞንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኵስና ሲጠራው ራእይን አየ። በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ።

ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቶና ተመልሶ ለራሱ በዓትን ሠራ በታላቅ ገድልም ተጠምዶ በቀንና በሌሊትም ተጋደለ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ በሴት መነኵሲት አምሳል ወደርሱ መጣ የበዓቱን ደጃፍ በአንኳኳ ጊዜ ከፈተለትና ገባ "ቅዱሱም ተነሥተን እንጸልይ" አለው ያን ጊዜ ተንኰሉን ገለጠ መልኩም እንደ እሳት ላቦት ሆነ ቅዱሱንም "እኔ ታላቅ ጦርነት አመጣብሃለሁ" አለው።

ከዚህም በኋላ መልኳ ውብ ወደ ሆነ ወደ አንዲት ወጣት ሴት ሰይጣን ሒዶ አነሣሣት። ቅዱስ አሞንዮስን እርሷ ጋራ በኃጢአት ልትጥለው ቀጭን ልብሶችን ለብሳ ወደ ርሱ በምሽት ጊዜ ደረሰች። እንዲህም እያለች ደጃፉን አንኳኳች "እኔ መጻተኛ ሴት ነኝ መንገድንም ስቼ በምሽት ጊዜ ከዚህ ደረስኩ አራዊትም እንዳይበሉኝ በውጭ አትተወኝ እግዚአብሔርም ስለ እኔ ደም እንዳይመራመርህ" አለችው። በከፈተላትም ጊዜ የሰይጣን ማጥመጃው እንደ ሆነች የላካትም እርሱ እንደሆነ አወቀ በአምላካውያት መጻሕፍት ቃልም ገሠጻት ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ የሲዖል እሳትም አስገነዘባት ሁለተኛም ለጻድቃን ስለ ተዘጋጀ ፍጹም ተድላ ደስታ ነገራት። ያን ጊዜም የሚላትን ታስተውለው ዘንድ እግዚአብሔር ልቧን ከፈተላት። መልካሙንም ልብስ ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሮቹ በታችም ሰግደች ነፍሷንም ያድን ዘንድ በማልቀስ ለመነችው። የጠጉር ልብስም አለበሳት ራስዋንም ተላጭታ በገድል ሁሉ በብዙ ትሩፋትም ተጠመደች በቀንም በሌሊትም ዐሥራ ሁለት ጊዜ የምትጸልይ ሁናለችና በየሁለትና በየሦስት ቀንም ትጾማለች።

ሰይጣንም በአፈረ ጊዜ በመነኵሴ ተመስሎ በየአንዳንዱ ገዳም ሁሉ በመግባት እያለቀሰና እያዘነ እንዲህ አላቸው "በአባ አሞንዮስ ቤት ሴት አለችና እርሱ ታላቅ ገድል በኋላ የአንዲትን ሴት ፍቅር ወዶአልና እርሷም በእርሱ ዘንድ በበዓቱ ውስጥ ትኖራለች እነህ መነኰሳትን አሳፈራቸው እስኬማውንም አጐሳቈለ"።

የመላእክት አምሳል የሆነ ጻድቅ አባ ዕብሎ ያን ጊዜ ተነሣ አባ ዮሴፍንና አባ ቦሂንም ከእሱ ጋራ ወሰዳቸው። ወደ ቅዱስ አሞንዮስ ገዳም ደብረ ቶና ደረሱ ደጃፋንም በአንኳኩ ጊዜ ያቺ ሴት ወደ እርሳቸው ወጣች እርስ በርሳቸውም "ያ መነኵሴ የነገረን እውነት ነው ተባባሉ። የከበረ አሞንዮስም ሳድዥ ብሎ ስም አውጥቶላታል ይህም የዋሂት ማለት ነው። ገብተውም ጸሎት አድርገው የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ እስከ ምሽት ተቀመጡ። አባ አሞንዮስም "አምበሻ እየጋገረችልን ነውና ተነሡ ሳድዥን እንያት" አላቸው። በገቡም ጊዜ በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ቁማ እጆቿም ወደ ሰማይ ተዘርግተው ስትጸልይ አገኙዋት። አይተውም ስለዚህ ድንቅ ሥራ እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርም አመሰገኑ።

ከዚህ በኋላም አቅርባላቸው በሉ። በዚያችም ሌሊት መልአክ ስለ አባ አሞንዮስና ስለ ሳድዥ ገድላቸውን ለአባ ዕብሎ ነገረው "ወደዚህም ዛሬ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር ነው የሳድዥን ዕረፍት እንድታዩ" አላቸው። ሦስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ የሚያስጨንቅ የሆድ ዝማ ታመመች በእግዚአብሔር ፊት አንዲት ስግደትን ሰገደችና በዚያም ነፍሷን ሰጠች መልካም አገናነዝም ገንዘው ቀበሩዋት።

አባ አሞንዮስም ትሩፋቷን ሊነግራቸው ጀመረ እርሷ በእርሱ ዘንድ ዐሥራ ስምንት ዓመት ስትኖር ከቶ ፊቷን እንዳላያት ምግባቸውም አምባሻና ጨው እንደሆነ። ከጥቂ ቀን በኋላም አባ አሞንዮስ ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ አሞንዮስና በቅድስት ሳድዥ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 20 ስንክሳር።

                           
#"ሰላም_ሰላም_ለረዳኢተ_አሞንዮስ ሳድዥ። ዝ ብሂል የዋሂተ ግዕዝ። በሑረታቲሃ አዳም ወበምግባራ ሐዋዝ። ኢውዕየት ቀዊማ ከመ ዘመጥልል ውኂዝ። ማዕከለ ውዑይ ወርሱን ማሕበዝ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_20

                          
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"። መዝ 67፥30-31 ወይም መዝ 74፥2-3፡፡ የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥1-11፣ 1ኛ ጼጥ 2፥11-20 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥24-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ቅዱስ ካሌብ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
Forwarded from M.A
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                           
"#ሰላም_ለካሌብ ወለሣህል ኄራን መዋዕያን ነገሥት፤ #እለ_ሃይማኖቶሙ_ምሉዕ ከመ ደመና ክረምት፤ #ለመንገለ_እግዚአብሔር እለ አርአዩ ቅንአተ፤ እለ ዓቀቡ በንጽሕ መንግሥተ፤ ዘተወፈዩ ጽድቀ #ወቅድሳተ_ወሃይማኖተ_በመንፈስ_ቅዱስ እለ አፍረዩ፤ #ለእግዚአብሔር ርእሶሙ እለ አቅነዩ"። ትርጉም፦ #ለእግዚአብሔር_ራሳቸውን_ያስገዙ#በመንፈስ_ቅዱስ_ፍሬን_ያፈሩ፤ እውነትን፣ ክብርንና #ሃይማኖትን_የተቀበሉ፤ መንግሥትን በንጽሕና የጠበቁ፤ #የእግዚአብሔር ወደሚኾን አምልኮት ቅንአትን ያሳዩ፤ #ሃይማኖታቸው_እንደ_ክረምት_ደመና_ምሉእ የኾኑ ቸሮችና ድል ነሾች ለኾኑ ነገሥታት ለሣህልና #ለቅዱስ_ካሌብ_ሰላምታ_ይገባል#ሊቁ አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።

ምንጭ ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
ድጓ ዘጻድቃን ነገሥት አቡን በ፮


አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ጽድቅ እባዕ ውስቴቶን ወእግነይ ለእግዚአብሔር ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር ጻድቃን በክብር የዋሃን በክብር ራትዓን በክብር በትፍሥሕት ይበውዑ ውስቴታ በኃሤት። ገጽ ፻፲ (110)

ትርጓሜ ፦   የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤  ወደ እነርሱ    ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግን ዘንድ ፤ ይህችም በር የእግዚአብሔር ደጅ ናት ፤ ጻድቃን በክብር ፣ የዋሃን በክብር ፣  ቅኖችም በክብር     በደስታ  ወደርሷ ይገባሉ።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ
2024/06/28 15:27:09
Back to Top
HTML Embed Code: