Telegram Web Link
Forwarded from Sintu.D
እንኳን ለእናታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ደብረ ምጥማቅ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ 🙏

📌ምጥማቅ ማለት መገለጥ ማለት ነው እመቤታችን በግብፅ ገምኑዲ በምትባል ቦታ ለአምስት ቀን ከፀሐይ ፯ እጅ አብራት የተገለጸችበት ቀን ናቸው
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡

ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡

አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡

የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡

እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡

በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳ እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡

ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡

የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡

ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡

ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡

የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ”

Deacon Henok Haile
#የብርሃን_እናት - ገፅ 305-308
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
ሐመረ ብርሃን : ቅድስት ደብረ ምጥማቅ

"#ማርያም ንግሥት ውስተ ደብረ ምጥማቅ ከተማ::
ብጹዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ::
ወብጹዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ::"
( ማርያም ሆይ! በደብረ ምጥማቅ ላይ በነገሥሽ ጊዜ::
አንቺን ያዩ ዓይኖች:
በፊትሽ የቆሙ እግሮች:
ብጹዓት (ንዑዳት ክቡራት) ናቸው:: )

የእመቤታችን ጣዕመ ፍቅሯ ይደርብን:: በረድኤትም ትገለጽልን::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ  ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ።
በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት  ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው።

1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC #ETHIOPIA

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" የማኅበረሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው።

በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ #በሰላም_ወጥቶ_መግባትም_አጠራጣሪ_ሆኖአል ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡

በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል ? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው። ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል። "

#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ኢትዮጵያ
#የግንቦት_ርክበ_ካህናት_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልአተ_ጉባኤ

@tikvahethiopia
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
Forwarded from M.A
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

           #ግንቦት ፳፪ (22) ቀን።

እንኳን ##ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_እንድራኒቆስ ለዕረፍቱ በዓል፣ #በደብረ_ምጥማቅ_ለእመቤታችን መገለጥ #ለሁለተኛ_ቀን መታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከምሥራቃዊ_ከቅዱስ_ያዕቆብ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                            
#ቅዱስ_እንድራኒቆስ፦ ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።

በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው።

ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ።

ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 22 ስንክሳር።

                          
"#ሰላም_ሰላም_ለእንድራኒቆስ ዕብሎ። ውኂዝ መንፈስ ዘሰትየ ምስለ ሐዋርያት በአመ ድብሎ። ኀበ ሖረ ይስብክ አህጉራተ አድያም ኵሎ። አብያተ ክርስቲያን ሐኒፆ ወአብያተ ጣዖት አንሒሎ። ዕሴተ ተስፋሁ አድምዐ በሰማይ ዘሀሎ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_22

                          
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በትርከ ወቀስታምከ አማንቱ ገሠፀኒ። ወሠራዕከ ማእደ በቅሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ"። መዝ 22፥4-5 የሚነበበው ወንጌል 27፥27-31።

                           
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 16፥6-10፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21-15-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ እንድራኒቆስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
Forwarded from M.A
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊
(ማቴ ፫:፫)

በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!
🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም።

ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።

🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ  ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን።

ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት።

🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ"

ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።

🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
ትምህርተ ሃይማኖት (አዕማደ ምሥጢር)
Forwarded from M.A
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
“ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን? እንኪያስ በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"

( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
Forwarded from M.A
2024/06/30 21:15:22
Back to Top
HTML Embed Code: