Telegram Web Link
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
      አሜን

"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"      
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

     ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
 
🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፳፫
 
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ ሦስት በዚች ቀን የመቶ አለቃ የነበረ ጻድቁ ቆርኔሌዎስ አረፈ።

❖ ይህም ቅዱስ የፍልስጥዔም ክፍል በሆነች በቂሣርያ የመቶ አለቃ ሁኖ የተሾመ ነው፤ እርሱም ከዋክብትን ሲያመልክ ነበር እንደርሱ ማንም ሊአደርግ የማይቻለውን የሚያመልካቸው አማልክቶቹም ቢሆኑ በሐዋርያት እጅ የሚደረገውን የተአምራታቸውንና የስብከታቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወዲያውኑ ለአማልክት መስገድን ተወ።
❖ ከዚህም በኋላ የሚጾም የሚጸልይ ለድኆችና ለችግረኞች የሚመጸውት ሆነ በጸሎቱም ጊዜ እንዲህ ይል ነበር አቤቱ አምላክ ሆይ እኔ አንተን ከማወቅ ጎደሎነኝና አንተ ግን የቀና መንገድህን ምራኝ።
 
❖ ቸር ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ይቅር ብሎት መልአኩን ላከለት ወደርሱም አይቶ ቆርኔሌዎስ ፈራ አቤቱ ምን ትላለህ አለ ጸሎትህ ምጽዋትህ መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል አሁንም በጫማ ሰፊው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ስምዖን ጴጥሮስን ይጠሩልህ ዘንድ ሰዎችን በባሕር አቅራቢያ ወደአለች ኢዮጴ ከተማ ላክ አለው።
 
❖ በዚያንም ጊዜ መልአኩ እንደነገረው ሰዎችን ላከ ጴጥሮስም በመጣ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተቀብሎ ከእግሩ በታች ሰገደለት ጴጥሮስም አነሣውና ተነሥ እኔም እንዳንተ ሰው ነኝ አለው፤ ከእርሱም ጋር እየተነጋገረ ገባ ወደርሱም የመጡ ብዙ ሰዎችን አገኘ።
 
❖ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው ለአይሁዳዊ ሰው ሒዶ ከባዕድ ወገን ጋር መቀላቀል እንደማይገባው ታውቃላችሁ እኔን ግን ማንንም ማን ቢሆን እንዳልጸየፍ እግዚአብሔር አሳየኝ፤ አሁንም እንደላካችሁብኝ ሳልጠራጠር ወደ እናንተ መጣሁ የጠራችሁኝ ለምን እንደሆነ እስቲ ንገሩኝ።
❖ ቆርኔሌዎስም ዛሬ አራተኛ ቀን ነው አለ በቤቴ ውስጥ በዘጠኝ ሰዓት ስጸልይ አንድ ሰው ብርሃን ለብሶ ታየኝ፤ እንዲህም አለኝ ቆርኔሌዎስ ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም በእግዚአብሔር ፊት ታሰበልህ፤ አሁንም ከባሕር አቅራቢያ ወዳለችው ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በጫማ ሰፊው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ጴጥሮስ የተባለ ስምዖንን ይጥሩልህ እርሱ አንተ የምትድንበትን ወገኖችህም ሁሉ የሚድኑበትን ይነግርሃል።
 
❖ ያን ጊዜም ስለዚህ ወዳንተ ላክሁ ወደእኛ መምጣትህም መልካም አደረግህ አሁንም እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ ሁላችን በፊትህ አለን።
 
❖ ጴጥሮስም አንደበቱን ገልጦ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት ሰው መሆኑን መከራ ተቀብሎም ተሰቅሎ ስለ መሞቱ ስለ መነሣቱና ወደ ሰማይ ስለማረጉ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ ስለ መምጣቱ አስተማራቸው።
❖ የከበረ ቆርኔሌዎስም ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ከዚያ የነበሩ ብዙዎች አሕዛብም አመኑ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም እንደተጻፈ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠመቁ።
 
❖ ከዚህም በኋላ ቆርኔሌዎስ ይህን ዓለም ለመግዛት የተሾመውን ሹመት ተወ ቅዱስ ጴጥሮስ ለክርስቶስ ጭፍራ የመሆንን ሹመት በመስጠት ለእስክንድርያ አገር ኤጲስቆጶስነት ሹሞታልና ወደ ርሷም ሒዶ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ጣዖታትንም ለሚያመልኩ ስሕተት መሆኑን ገለጠላቸው ልባቸውንም እግዚአብሔርን በማወቅ ብሩህ አደረገላቸው በፊታቸውም ተአምራትን አደረገ ብዙዎችም አምነው ተጠመቁ ከእነርሱም በኋላ መኰንኑን ድሜጥሮስን አጠመቀው፤ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። 
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
 
           
  
🛎 በዚችም ዕለት ዳግመኛ የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይ አብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፤ የስሙ ትርጓሜ ‹‹የእግዚአብሔር አገልጋይ›› ማለት ነው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ

‹‹አብደዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር›› ተብሎ የተነገረለት እውነትም ‹‹የእግዚአብሔር አገልጋይ›› የሆነ የነቢዩ ኤልያስ ደቀመዝሙር የነበረ ታላቅ ነቢይ ነው፡፡
📖1ኛ ነገ 18፥3
❖ ይህም ቅዱስ ነቢይ ከጠረፍ በረሃ አቅራቢያ ካለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው፤ ለነቢዩ ኤልያስ ደቀ መዝሙሩ ሆኖ በንጉሡ በአክዓብምና በንግሥቲቱ በኤልዛቤል ምክንያት በእርሱ ላይ የመጣውን መከራ ሁሉ ታግሷል፡፡

❖ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ከእነ ኤልዛቤል ሸሽቶ ወደ ተራራ ላይ ወጥቶ በዋሻ ተሸሽጎ ምግቡን አሞራ እያመጣለት በኖረበት ጊዜ እንኳን አብድዩ ግን ብቻውን የእግዚአብሔርን ነቢያት ይንከባከብ ነበር፡፡

❖ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥ የነበረ ቢሆንም ንግሥት ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው የነበረ ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኩ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው
‹‹ከብዙ ቀንም በኋላ በሦስተኛው ዓመት ‹‹ሂድ ለአክዓብ ተገለጥ፥ በምድር ላይም ዝናብ እሰጣለሁ›› የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፡፡

❖ ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር፤ አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር፡፡

❖ ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ እርሱ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር፡፡
❖ አክዓብም አብድዩን ‹‹በአገሩ መካከል ወደ ውኃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን›› አለው፡፡
❖ ሁለቱም የሚመለሱበትን አገር ተካፈሉ፤ አክዓብም ለብቻው በአንድ መንገድ አብድዩም ለብቻው በሌላ መንገድ ሄዱ፡፡

❖ አብድዩም በመንገድ ሲሄድ እነሆ ኤልያስ ተገናኘው፤ አብድዩም አወቀው፣ በግምባሩም ተደፍቶ ‹‹ጌታዬ ሆይ! ኤልያስ አንተ ነህን አለ፡፡

ተገኝቶአል› በል›› አለው፤ አብድዩም ‹‹እኔን ባሪያህን እንዲገድል በአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጠኝ ዘንድ ምን ኃጢአት አድርጌአለሁ፤ አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም ‹‹በዚህ የለም›› ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር፤ አሁንም እነሆ ‹ሂድ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር› ትለኛለህ፡፡
❖ እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር፡፡

❖ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ አምሳ አምሳውንም በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸው ነበር፡፡
❖ ይህ ያደርግሁት ነገር በውኑ ለጌታዬ አልታወቀህምን አሁንም "ሄደህ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር ትላለህ" እርሱም ይገድለኛል›› አለው፡፡
❖ ኤልያስም ‹‹በፊቱ የቆምሁት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዛሬ ለእርሱ እገለጣለሁ›› አለ፡፡
❖ አብድዩም አክዓብን ሊገናኘው ሄደ፣ ነገረውም፤ አክዓብም ኤልያስን ሊገናኘው መጣ፤ አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ ‹‹እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን›› አለው፡፡
ኤልያስም ‹‹እስራኤልን የምትገለባብጡ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ፣ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም›› አለው፡፡
📖1ኛ ነገ 18፥1-20

❖ ቅዱስ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥነቱን ትቶ የኤልያስ ቀደ መዝሙሩ ሆኖ በነቢይነት እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ የትንቢቱ ወራት ሲፈጸም በዚህች ዕለት ዐርፏል፡፡


📌 ኅዳር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ (ሐዋርያዊ ጻድቅ)
2.ቅዱስ አብድዩ ነቢይ
 
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
ስንክሳር ኅዳር_24

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ አራት በዚች ቀን #የሃያ_አራቱ_ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው፣ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑበት ነው፣ #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ ልደታቸው ነው፣ #ቅዱስ_አዝቂር_ሰማዕት ከአርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት ያረፈበት ፣ #ቅዱስ_አባ_ዮሴፍ_ዘሀገረ_ፃን ያረፈበት ዕለት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ

ኅዳር ሃያ አራት በዚህች ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው ።

እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋርነ እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለእነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዙአብሔር አይቀርብም።

ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ። በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ።

ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ጽንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት ። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐረገ ።

የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም ። እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ ።

እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት ። አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን ኃይልና ምስጋና ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና ።

እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት

አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡

ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ ‹‹…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‹ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን› የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ…..›› (ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 216-223)

ይህንን ታላቅ በዓል ነው ዛሬ የምናከብረው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን አንደበታቸው የለበሱትም ልብሳቸውም ጭምር እግዚአብሔርን በሰው አንደበት እንደሚያመሰግን በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፏል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ

አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊ በቅዱስ ማርቆስ ብስራት እንደተወለዱ፦ አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ስትሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻድቅ ልጅ እንደምትወልድ አበሰራት፡፡

ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል›› በማለት ብስራቱን ነግሮታል፡፡

በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን ዜና ማርቆስ በዚህች ዕለት ኅዳር 24 ቀን በተወለዱ ጊዜ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎች ሁሉ ታይቷል፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ዘወገግ አባት ቅዱስ እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም አቡነ ዜና ማርቆስን ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናታቸው ሰጧቸው፣ እናታቸው ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው ‹‹አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ›› ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡

በ40 ቀናቸውም ሲጠመቁ የሚያጠምቃቸው ካህን የአባታቸው ወንድም እንድርያስ ውኃው ሲፈላ አይቶ ሸሽቷል፡፡ መልአኩም እንዳይፈራ ነግሮት ለእርሱም ተአምር እንደሚደረግለት አስረዳው፡፡ እንድርያስም ዕድሜው 72 ነበርና ራሰ በራ ስለነበር አባታችንን ባጠመቀበት በውኃው ራሱን ቢታጠብበት ጸጉር አብቅሏል፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይቶ አደነቀ፡፡ ያችም ውኃ ሌሎች በጣም ብዙ ተአምራትን አደረገች፡፡

አቡነ ዜና ማርቆስ አንድ ዓመት በሆናቸውም ጊዜ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየዳኹ ሲሄዱ መልአክ በክንፎቹ አቅፎ ነጥቆ ወደሰማይ ወስዶ ጌታችንና እመቤታችን ጋር አቅርቦ አስባርኳቸዋል፡፡ እንዲሁም የ15ቱን ነቢያት፣ የ12ቱን ሐዋርያት የ72ቱን አርድእት፣ ሃይማኖታቸው የቀና የ318ቱን ሊቃውንት፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን የእነዚህን ሁሉ በረከት እንዲቀበሉ ካደረጋቸው በኋላ ወደዚያች ቤተክርስቲያን መለሳቸው፡፡ የአቡነ ዜና ማርቆስን የዕረፍታቸውን በዓል ከ9 ቀናት በኋላ ታኅሣሥ 3 ቀን ስለምናከበር አምላካቸው ከዕረፍታቸው ቀን ያድርሰንና ያንጊዜ
ሙሉን ዜና ገድላቸውን እናየዋለን፡፡ በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አዝቂር_ሰማዕት

በዚችም ዕለት የናግራን አገር ቄስ የከበረ አዝቂር የሐሚር ንጉሥ ሰራብሄል በነገሠበት ወራት ከእርሱ ጋር ካሉ አርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት አረፈ ።

ይህም ንጉሥ አዝቂርን ወደ ወህኒ አስገብተው እንዲዘጉበት ጠባቂዎቹንም ከሰው ወገን ማንም እንዳይገባ ብሎ አዘዘ ። ቅዱስ አዝቂርም በጸለየ ጊዜ የወህኒ ቤቱ ደጃፍ ተከፈተና ሃምሳ ሰዎች ወደርሱ ገቡ እርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ።

ንጉሥ ሰራብሄልም በሰማ ጊዜ ከወህኒ ቤት አውጥተው ወደሌላ አገር እንዲወስዱት አዘዘ በጉዞም ላይ ስሙ ኪርያቅ ከሚባል ሰው ጋር ተገናኘ ቀሲስ አዝቂርም ኪርያቅን ኪርያቅ ሆይ ላንተ የምሥራች ይገባል ለሰማዕትነት ይወስድሃልና አለው ። የንጉሥ ሎሌዎችም ሰምተው አሥረው ከእርሱ ጋር ወሰዱት ። ዳግመኛም ሁለት ሰዎች ተገናኙትና ስለ ክርስቶስ አጥምቀን አሉት ያን ጊዜም ቅዱስ አዝቂር ጸለየና ከበረሀ ቦታ ውኃ አፍልቆ ከኪርያቅ ጋር አጠመቃቸው ።

ከዚህም በኋላ ወደበረሀ ውስጥ በደረሱ ጊዜ ለእሳቸውም ለእንስሶቻቸውም የሚጠጡት ውኃ አጥተው ወደ እግዚአብሔር እንዲለምንላቸው ቅዱስ አዝቂርን ለመኑት በጸለየም ጊዜ ደመና መጣ በመሐል እጅ በሚታፈን መጠን በገበታ ላይ ዘነበ ሰባት መቶ ያህል ሰዎች ከእንስሶቻቸው ጋር ጠጥተው ረኩ ።

ወደ ንጉሡም በአቀረቡት ጊዜ ወደ አገራችን ያመጣኸው ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው አለው ቅዱስ አዝቂርም ነቢያት በኦሪት ከሰበኩት በቀር ሌላ አዲስ ትምህርት አላመጣሁም አለ ንጉሡም ይህን ሰምቶ በክርስቲያን ሃይማኖት ላይ ተዘባበተ።

ከአይሁድ መምህራንም አንዱ ተነሥቶ እንዲህ አለ ጌታዬ ሆይ ወደ አገሩ እንዲወስዱትና በዕንጨት ላይ ሰቅለው በሕይወት ሳለ በእሳት እንዲአቃጥሉት እዘዝ አለው ንጉሡም እንደ አይሁዳዊው ቃል አዘዘ።

ወደ ናግራን አገርም በአደረሱት ጊዜ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ቅዱስ አዝቂርም ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከማሠሪያው ተፈትቶ ከእሳት ውስጥ በደኅና ወጣ አይሁድም በደንጊያ እንውገረው ተባብለው በወገሩት ጊዜ ደንጊያዎች ተመልሰው ከአይሁድ የሚበዙትን ገደሉ ።

ከተረፉትም ሰይፍን አንሥተው የቅዱስ አዝቂርን ራስ ቆረጡ ምስክርነቱንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ዮሴፍ_ዘሀገረ_ፃን

በዚችም ቀን ፃን ከምትባል አገር የሆነ አባ ዮሴፍ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በሃይማኖት የበለጸጉ ናቸው ነገር ግን ያለርሱ ልጅ አልነበራቸውም የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጻሕፍት ማንበብንም እያስተማሩ መልካም አስተዳደግን አሳደጉት መልኩም እንደ ያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ያማረ ነበር በአደገም ጊዜ ሞትን የዚህንም ዓለም ኃለፊነት ማሰብ በልቡ አደረ።

ወደ አንድ ገዳምም ሒዶ መንኵሶ በጾም በጸሎት በመስገድ በተጋድሎ የተተከለ ሆኖ ጸና በአቱንም ዘግቶ በእለተ እሑድ ከቁርባን ጊዜ በቀር አይወጣም ነበር ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ከእርሱ በረከቱን ይቀበሉ ዘንድ በአገር ዙሪያ ያሉ ሰዎች የሚመጡ ሆኑ አባቱና እናቱም የልጃቸውን ወሬ በአጡ ጊዜ እርሱን ያገናኛቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ነበር።

ወሬውንም በሰሙ ጊዜ ስለ ልጃቸው መገኘት እንዲጸልይላቸው ወደርሱ ሔዱ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ አላወቁምና ሰውም ገለል ባለ ጊዜ ልጃቸው መሆኑን እራሱን ገለጠላቸውና ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው ።

እግዚአብሔርም ድንቆች ተአምራትን የማድረግ ሀብትን ሰጠው ሰይጣን እስከ ቀናበት ድረስ ወደ አገረ ገዢውም ሔዶ ይህ መነኵሴ ዮሴፍ ብዙ ገንዘብ እንዳለው አስመስሎ ነገር ስራበት ። መኰንኑም በሰንሰለት ማሰሪያዎች አሰረው። በማግሥቱም ማሰሪያዎቹ ከላዩ ወደ ምድር ወድቀው ተገኙ መኰንኑም አይቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዥ ሆነ ።

ብዙ ከተጋደለና እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ። በክብርም ቀበሩት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ብዙ ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።https://www.tg-me.com/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን👇
https://youtube.com/@finotebirhan12
††† ❇️እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ †††

††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል::

††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ)
3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ)
4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል)
5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል)
6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል)
7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል)
8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል)
10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

††† ከእነዚህም:-
*አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ:: (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::

በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::

††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:-
1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11)

2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8)

3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3)

4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6)

5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12)

ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::

ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4)

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት)
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::

ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::

††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24)

††† ቅዱስ አዝቂር ካህን †††

††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::

"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"

ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::

ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::

በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
††† ኅዳር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."24ቱ" ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)
2.ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት
3."48" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
4.አባ ዮሴፍ ዘሃገረ ጻን
5.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጥዑመ ዜና
6.ቅዱስ ኪርያቅ ሰማዕት††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

††† "በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ:: በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው: በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር:: ከዙፋኑም መብረቅና ድምጽ: ነጐድጓድም ይወጣል:: በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር:: እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው::" †††
(ራዕይ ፬፥፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Encoderbot file id2623046 16k
ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘወርሃ ህዳር
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Encoderbot file id2623037 16k
ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ አራት(፳፬)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
õ p­ í –u Ø(aÕ 16k
ASR by NLL APPS
ገድለ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ዘረቡዕ...ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ
@SinkisarZekidusan
Daniel:
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል "*+

=>ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

+ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

+አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

+እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

+እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

+"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

+ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

+አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

+ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

+ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

+በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

+እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

+በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

+በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

+ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

+በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

+እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

+ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

+በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

+"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

+ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

+ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

+እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
<<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>>

=>አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ኅዳር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ)
3.ቅዱስ ሮማኖስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን

=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . +"+ (ዕብ. 11:35)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

† ኅዳር ፳፮ †

+*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+

=>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

+እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::

+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::

+ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::

+አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት: የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::

+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::

+በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::

+በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::

+ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

+ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::

+በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::

+ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::

+ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::

+እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::

+ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: <<ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>>

+*" አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ "*+

=>እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::

+ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::

+ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::

+ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::

+የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::

+ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::

*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
*በ40 ቀናት: ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::

*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
*በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም::

+በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::

+"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

+"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
+ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::+"+ የናግራን ሰማዕታት +"+

=>በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን (የአሁኗ የመን) የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ::

+ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ 4,000 ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው::

+ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: (ሮሜ. 8:5) ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ4,100 በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ::

+ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም (የሕዝቡ መሪ ነው) ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም 2 ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::

+ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ40 ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::

=>አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

=>ኅዳር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ
3.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
4.ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ
5.ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ (ሰማዕታት)
6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ
7.ቅድስት ዮስቴና ቡርክት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን 3. አባታችን አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ (ከእመቤታችን ጋር ወደ ግብጽ የተሰደደ ታላቅ ጻድቅ)

=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
2024/10/01 11:24:00
Back to Top
HTML Embed Code: