Telegram Web Link
💞💞💞💞💞💞💞






😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
ውዴ ብለሽ ጥሪኝ ውዴ ብዬ ልጥራሽ
ልቤ ውስጥ የፍቅር ጎጆ የዘረጋሽ
ህይወቴን ከ ሀዘን አካሌን ከስቃኝ በፍቅርሽ ያቃናሽ
ከክፋት ከተንኮል በእጅጉ የራቅሽ
እንደ ከዋክብቶች ቀና ብዬ እማይሽ
ውዴ ብዬ ልጥራሽ
መተኪያ የለለሽ
ለፍቅር የተፈጠርሽ
ውዴ አንች እኮነሽ
የአምላክ በረከቴ
ለመሳቅ ምክንያቴ
የሀዘን ድምቀቴ
ለመኖር ህይወቴ
ውዴ አንች እኮነሽ የአምላክ ስጦታዬ
ለፀሀይ ጥላዬ
ለጠላት ጋሻዬ
ለመኖሬ ምክንያት የአምላክ ስጦታዬ ......



💋💋💋💋💋







💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
@CJmanCJ
@Gitemenlenante
ግጥምን ለናንተ
እባካችሁ ተጠንቀቁ 🙏🙏🙏🙏
አልኮል ወይም ሳኒታይዘር ተቀብታችሁ እሳት ወዳለበት ቦታ በቶሎ አይሂዱ
ምክንያቱም በአካላችሁ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል
ዝምተኛ ልቦች_
`````

አምነው የወደዱ፣
ወደው የተካዱ፣
ተክደው የራዱ፣
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው?
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣

ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጠሩ፣
ተገፍትረው ወድቀው፣
ደቀው እንዳይቀሩ፣
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ
@Gitemenlenante
🌹🌹እኔ አንቺ💕💕
ብዕር ና ቀለም, ናፍጣ ና መኪና
አንዱ ከሌለ አንዱ ባዶነውና
በፍቅር ይኖራሉ በአንድ ጎዳና
.
እና ፍቅሬ እኔ አንቺ ማለት
ስንታይ ብንሆንም ሁለት
ግን በፍቅራችን ብዛት
.........ኖረን በአንድነት
ላጤኔን አንድ ላየን ሁለት
በቃ እኔ እና አንቺ ማለት
አንድ ነን አይደለንም ሁለት
@Gitemenlenante
**** እውነቱን ልንገርህ?******
እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥
እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥
እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥
ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥
እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ...
እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥
ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥
ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥
ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥
በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥
ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥
የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥
ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥
እውነቱን ልንገርህ?
ዳግም ተመልሼ እኔም ያንተ እልሆንም
@Gitemenlenante
አ .ል .ወ .ድ .ሽ .ም .እ .ን.ጂ!!!!!
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ::
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ::
💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም::
💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው እያሉ::
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው::
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤
አልወድሽም እንጂ !
አልወድሽም እንጂ !
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ::
💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ::
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ::
👑👑👑👑👑👑👑👑👑
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን።
💏💏💏💏💏💏💏💏💏💏
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት::
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም::
💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔
ግን
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
አለት በሆነ ልብ በማይጎድል ተስፋ
በማይናድ ፅናት ቅፅበት በማይጠፋ
በውበትሽ ሰክረው ቅኔ እየዘረፉ
በነበልባል ፍቅርሽ ነደው እየጠፉ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን ይሆናሉ።
@Gitemenlenante
ፍቅር
ፍቅር ማለት ያፍቀርካውን ስው የራስ
ማድርግ ብቻ አይደለም
ፍቅር ማለት የወደድከውን ስው
ማግኛት ብቻ አይድለም===
ፍቅር ማለት አብሮህ ያለውን ስው ማፍቅር
ፍቅር ማለት እይደለም ያለህን ነገር
ብቻ ማፍቅር አይደለም
ፍቅር ማለት ያልህን ነገር ብቻ ማፍቅር አይደለም
ያጣህውንም የሌለህንም መውደድና
ማፍቅር ስትችል ነው
ያፍቅርከውን ስው የራስህ ስለሆነ ሳይሆን
ያንተም ባይሆን እኳን ሁሌም የሱን
ስላም ደስታ ጤና ስኬት ተመኝለት
እውነተኛ ፍቅር ያፍቅሩትን ስው ደስተ ማየት ነው እና።

እውነተኛ ፍቅር ጊዜውን ጠብቆ እራሱ ይመጣል
እውነተኛ ፍቅር ትግስተኛ ነው ።
እውነተኛ ፍቅር ይቅር ባይ ነው ።
እውነተኛ ፍቅር በደልን አይቆጠርም ።
እውነተኛ ፍቅር እሩሩህ ነው ።
እውነተኛ ፍቅር በቀልን አይውቅም ።
እውነተኛ ፍቅር እግዚአብሔር ያከብራል ።
እውነተኛ ፍቅር በግድ ተፈልጎ አይገኝም ።
እውነተኛ ፍቅር ዘርን አይቆጠርም ።
እውነተኛ ፍቅር መደበቅ አይችልም ።
እውነተኛ ፍቅር ማንንም ከማንም መጠቅ አይችልም
እውነተኛ ፍቅር የራሱን እውነት እንጂ የሌሎችን እውነት አይከተልም ።
እውነተኛ ፍቅር ስረው ፍቅር ብቻ ነው
እውነተኛ ፍቅር በስጠው ፍቅር ልክ
ምላሽ አይጠብቅም
እውነተኛ ፍቅር ዘር ቀለም ሀይማኖት አይቆጠርም
እውነተኛ ፍቅር በውስጣዊ ማንነት እንጂ ።
በፊት ገፅታ አያምንም ።
እውነተኛ ፍቅር ክብሩን አሳልፎ ለሌሎች ይስጣል ። እንጂ ስለ ክብሩ እና ስለ ዝናው አይጨነቅም ።
እውነተኛ ፍቅር በማግኘት ውስጥ አይቀየርም ።
እውነተኛ ፍቅር ከስር መሰረቱ አብሮ ያድጋል እንጂ
ለጥቅም አይጠጋም ፐርፌክት አይደለም ግን
ፍቅሩ እውነተኛ ከሆነ የትኛውንም ፍተና
ማለፍ ይችላል ።
እውነተኛ ፍቅር በምንም ነገር አይሽነፍም ።
እውነተኛ ፍቅር ምንም ነገር አይገድበውም ።
እውነተኛ ፍቅር ጥላቻን አያውቅም ።
እውነተኛ ፍቅር ጥላቻን በፍቅር ያሽንፋል እንጂ
ፍቅርን በጥላቻ አያሸንፍም ።።።

ፍቅር ሁሉምን ያሽንፋል
ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅር ያድለን
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
@Gitemenlenante
💌 #ማ_ይንገርሽ 💌


ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ

ግና ገና ሳይሽ

ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር

ጉልበቴም ይዝላል
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል
ልቤም ያው ይፈራል

ታዲያ የኔ ፍቅር

የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ

ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ
፨፨፨፨፨፨፨፨ አትመለስ ፨፨፨፨፨፨፨
ይኸውልህ ውዴ............
የስከዛሬው ፍቅር የስካሁን መውደዴ፥
እንደሻማ ቢቀልጥ ውሀ ቢሆን ባንዴ፥
ምን ሊበጀኝ እንባ ለምንስ መንደዴ?
ካልተመቸህ ልቤ ከጎረበጠብህ፥
ፍቅሬ ካልጣፈጠህ ሀሞት ከሆነብህ፥
መለየትን ወዶ ከሸፈተ ልብህ፥
አልከለክልህም ግዴታም የለብህ።
እግርህን አስሬ አቲድ አልልክም፥
መልሱልኝ ብዬም አማላጅ አልክም።
እውነቴን ነው ውዴ ሁን እንደ ፈቃድህ፥
ከሰለቸህ ፍቅሬ ተሟጦ መውደድህ፥
ሂድ እሸኝሀለሁ ጨርቅ ይሁን መንገድህ።
ግና
እንዳለፈው ጊዜ ልክ እንደትላንቱ፥
አስሰህ ስትመጣ ሲበቃህ ዙረቱ፥
ያው እንደለመድኩት እጆቼን ዘርግቼ፥
ምቀበልህ መስሎህ ከ'ቅፌ አስገብቼ፥
አትመለስ ከቶ ዳግም ላታገኘኝ፥
በመሀላ ብዛት በቃል ልትደልለኝ።
ባክህ ተለመነኝ
አትድከም አትምጣ በማምዬ ሞቷ፥
ስለማይመለስ አንዴ ከቆረጠ የሴት ልጅ አንጀቷ።
@Gitemenlenante
«ታመሻል ይላሉ»
እግር እንደጣለው ከቤትሽ የመጣ
ለኔ የሚሰጠው ነገርም አያጣ
ፊትሽን ስላየ ጥላሸት መልበሱን
አይንሽን ስላየ እምባ መቋጠሩን
ፀጉርሽን ስላየ በኖ መንጨብረሩን
አካልሽ በሞላ እንዳይሆኑት ሆኖ
ከኔ ተለይቶ ሲኖር ባዝኖ ባዝኖ
ፀፀት አንገብግቦሽ ዛሬ በልዳማ
አንቺን ያየ ሁሉ ስላንቺ የሰማ

"ታማለች" ይለኛል ካለሁበት መጥቶ
ሙቸ መነሳቴን የኔን ጉድ ረስቶ
ላላዘነ ልብሽ ልቤ አያዝንም ከቶ
ይመምሽ አብዝቶ!


@Gitemenlenante
ያመንኩሽ ቀን ነበር፣
ሞኝነት ያጠቃኝ
ቅቤ አፍሽ አፍዝዞኝ፣
ከመሸ በሁዋላ፣ ክህደትሽ አነቃኝ!

@Gitemenlenante
~~~~ልብህ እግረኛ ነው~~~
ውዴ.......
በደሌን ሳላውቀው አንተን ያሳጣኝን
ከሞቀው መውውደዴ ድንገት የለየኝን
ዛሬም አልደከምኩም ጥያቄ ለማንሳት
ካንተ ካንድ ፍቅሬ የለየኝን ክፋት
ይህነው ጥያቄዬ
ምንድነው ጥፍቴ
ካዳም ዘር ምርጫይ
ክፉ ቀን ጥላ ጋሻ መከታዬ
ገንጥሎ ያራቀኝ
በኔ ያስጨኸነህ
የቱ ነው ጥፍቴ አንተን የነጠቀኝ
..................እያልኩ አስባለሁ
ግና
ይጠርምሀል ውዴ ዛሬም ጥያቄነው
አንደች መልስ የሌለው
ስለዚህ አለሜ
አንተን ተማስደሰት ከመኳተን በቀር
አልታይሽ አለኝ ላንተ ክፉ አስቤ
የሰራሁት በደል
ታዲያ ደጋግሜ ነገሩን ሳጤነው
ምንም ሳልከፋብህ መንገድ የመረጥከው
ለካ አጥፍቼ አይደለም ሲጀመር ጀምሮ
ልብህ እግረኛ ነው፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
@Gitemenlenante
ሰማሽ መታማቴን
ምነው ዝም አልሽ እቱ፣
ስንከራተትብሽ ብሶብኝ ናፍቆቱ።
ምነው ዝም አልሽ እቱ…
ስሜ ሲጎሳቆል በሀሜቱ ብዛት፣
ሀገር ሲዳርሱት፣
ሲያነሱ ሲጥሉት፣
ከጋራው ባሻገር እርቀሽ ተቀምጠሽ፣
ታድያ ስንከራተት ብታማ ገረምኩሽ?
እና ምነው ዝም እንዳልሰማ ሰምተሽ?
መቼም ትሰሚያለሽ በፍቅርሽ ስታማ፣
ወሬ አቀባይ ሞልቷል በሀገርማ።
ምነው አልነገርሽኝ ቅስሜ ሲሰባበር፣
መጥቼ እንዳትነግሪኝ ሩቅ ነው ያንቺ ሀገር።
@Gitemenlenante
👉የኔ ወረተኛ🙋🏻‍♀️
እስመስሎ አዳሪ ድብቅ ሚስጥረኛ
በጣፍጭ ቃሎችህ አረከኝ ምርኮኛ
አቤት ማስመሰሉን እዴት ስችልበት
ይጠቅምክ እደሆን ፊልም እስኪ ስራበት
መኖር እኮ አልችልም እኔ አችን አጥቸ
ስትለኝ አመኩህ የላይክን አይቸ
ቃሎችህ ሲወጡ አምረው ተውበው
አብሬው ተራመድኩ እኔም አምኘው
አይኔን አሳውሮት የቃላት ሌቦችህ
ግርዶሽክን ሳትገልጥ ልቤም አመነችህ
ዛሬ ስብሰባ አለኝ አልመጣም በጊዜ
እንደተመቸህ ሁን አታብዛ ኑዛዜ
እኔ ከላይ ሳይህ ቆንጆ ነህ ከምር
እውስጥህ ግን ያለው ብዙ ዝንጉርጉር
ጥዋት ማታ ስትለኝ ልዩ ማራኪየ
መቸ ገብቶኝ ነበር ስበብ ለስቃየ
ይዠ አላስቀርህም አልሆንም ምቀኛ
መልካሙን ይግጠምህ የኔ ወረተኛ
@Gitemenlenante
"በልቤ ዝመቺ"
ዝመች ወደ ልቤ መንገዱን ሳትስቺ
ፍቅርሽን ለመስጠት ምንም ሳትሰስቺ
መኖር እንደማትችል ነፍሴ ያለ አንቺ
ቀንና ሌሊቱን ተጉዘሽ ዝመቺ
በልቤ ደጃፍ ላይ ቆመሽ እንዳትቀሪ
በድፍረት አንኩዋኪ ሳትሰጊ ሳትፈሪ
እከፍትልሻለሁ አትጠራጠሪ
የልቤ አዳራሽ ባዶ ስለሆነ
መርጦ ነው የሚያስገባ እያመዛዘነ
ተጎድቶ ስላየው ስንቱን እያመነ
የመጀመሪያዬ ብዪ ላቆላምጥሽ
በልቤ አዳራሽ በደስታ እንዳኖርሽ
ፍቀጂልኝ ውዴ የኔ ይሁን ልብሽ;;
@Gitemenlenante
ሀሳብ አስተያየት ካለ በ Inbox
👇👇👇👇
@CJmanCJ
ላይ ያድርሱን
ግርዶሹ ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ስንት ሰዓት ይፈጅበታል ?

በኢትዮጵያ የሚከሰተው ግርዶሽ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ዋናው "ቀለበታዊ ግርዶሽ" በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተለያየ ሰዓት የሚታይ ሲሆን ለምሳሌ ወለጋ አካባቢ ከጥዋቱ 1:55 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ) ፣ ላልይበላ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ8 ሴኮንድ) እንዲሁም አፋር ላይ ከጥዋቱ 2:03 (ለ1 ደቂቃ ከ6 ሴኮንድ) ይታያል - #ESSS
2024/10/02 16:33:30
Back to Top
HTML Embed Code: