Telegram Web Link
ይህንን ያውቃሉ

✔️ቆሞ 102 አመታትን ያስቆጠረው መርከብ ዛፍ በቅሎበት ጫካ ሆኗል። ተንሳፋፊው ጫካም ይባላል
@Gitemenlenante
ይህንን ያውቃሉ

✔️ይህ ዩክሬን የሚገኘው የፍቅር ዋሻ በአራቱ ወቅቶች
@Gitemenlenante
ሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህን
*ምኑን አፈቀርኩሽ?*
ደስ ያለሽን በይኝ ምቾት የሰጠሽን፤
ለኔ ያለሽን ስሜት የሚገልፅልሽን።
ብትፈልጊ ደደብ፤
ብትፈልጊ ጋጥ ወጥ፤
ብትፈልጊ እርኩስ፤
ካሻሽም ልክስክስ፤
ግለጭው ውርደቴን ፤
ግለጭው ክህደቴን፤
በንቀት አይን እይው እኔ አንችን ማለቴን።
♡♡♡
ግን እንዲህ ከልብሽ እውነት ካስጠላሁሽ፤
እኔ ለኔ ሳይሆን ላንች አዘንኩልሽ።
♡♡♡
የኔ ግን ሌላ ነው የማፍቀር ጥበቤ፤
አንች ብትጠይውም አይጠላሽም ልቤ፤
አንች ብትዘልፊውም ስላንች ቸርነት ስናገር አስቤ

እውነት እምላለሁ በምነት በማተቤ።
♡♡♡
ለምን ይመስልሻል???
ስትዘልፊኝ ከዘለፉኩሽ፤
ስትጠይኝ ከጠላሁሽ፤
ስትንቂኝም ከናቅሁሽ፤
ታድያ የኔ እመቤት ምኑን አፈቀርኩሽ?።
@Gitemenlenante
ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች👥 በዚህ ቻናል ላይ በሚለቀቁት ነገሮች ደስተኛ እንደሆናችሁ እርግጠኛ ነን ለዚህም እናመሰግናለን 👍
እንዲሁም በይበልጥ አብሮነታችሁ አይለየን እንዲሁም ከታች ያለውን ደቻናላችንን ሊንክ share በማድረግ ሌሎች ወዳጆቻችሁ እንዲቀላቀሉ በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዪን 🤝


ሀሳብ አስተያየት ካለ በ inbox 👇👇
@CJmanCJ ላይ ሀሳብና አስተያየቶን ያጋሩን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ግጥምን ለናንተ ከ A & Y
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ከ A & Y channel ቤተሰቦች በዚህ channel
👉ግጥሞችን
👉የተለያዩ በአለም ላይ የተከሰቱ አስደናቂ ክስተቶችን
እንዲሁም ለእናንተ ይጠቅማል ብለን ምናሰባቸውን ነገሮች ወደ እናንተ እናደርሳለን የ ዚህ ቻናል ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን
https://www.tg-me.com/Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች በነገው እለት ያለውን የ ፀሀይ ግርዶሽ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እንድታሳልፉ እላለው
ጥንቃቄ አይለየን እባካችሁ ግርዶሹ እስኪያበቃ ድረስ በፍፁም በአይናችን ቀና ብለን ወደላይ ሳናይ ግርዶሹ እስኪያልፍ ድረስ እንጠንቀቅ
አደራ አደራ አደራ እንጠንቀቅ 🙏🙏🙏🙏
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላማጣ!!

ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ!

share share
(እራስን መሆን)

ሲያወሩ አውርተህ ዝም ሲሉ ዝም ካልክ
ሲዘፍኑ አብረህ ዘፍነህ ሲያጨሀጭቡ ካጨበጨብክ
ሲበሉ ስትበላ
ሲጣሉ ስትጣላ
ሲጮሁ አብረህ ስትጮህ
ሲያለቅሱ አልቅሰህ
ሲስቁ አብረህ ስቀህ
ሁሉን አስመስለህ
እድሜህን አትፍጀው የእራስህን ሳትሆን የሌሎችን ሆነህ፡፡

@Gitemenlenante
(በውሸት አለም)

የአብሮነት ድልድይ መሰረት ካሳጣ
የመቻቻል ኑሮ መናናቅ ካመጣ
ከዝምድና ይልቅ ባንዳነት ካዋጣ
ዝምድና ይታጠብ ደሙን ውሻ ይላሰው
ምን ያደርጋል ታድያ ልብ ለልብ መክሮ ካልተገናኘ ሰው፡፡

@Gitemenlenante
(እርጅና)

ዓይን ኃይል ቀንሶ
ጉልበት ፍጹም አንሶ
እጅ ሲንቀጠቀጥ
ሲያበዙ መቀመጥ
ሮጥ ብሎ መውጣት
ሮጥ ብሎ መግባት
ሁሉም ይቀርና
ትዝታ ይሆናል ሲቃረብ እርጅና

@Gitemenlenante
(የገባሽ ለት)

በሰማይ ዝናብ ልክ እምባ ያቀረረ
ተስፋ መቁረጥ ከብዶት እንዳቀረቀረ
ከጸጥታው ደሴት እንደተቀመጠ
ትመጪ እንደው ብሎ አይኑ እንዳፈጠጠ
መውደድና ፍቅር ባንድ እያንገላቱት
ቆሞ እየጠበቀ በአግንቻት ጉጉት
አልፈሺው ስትሄጂ ዝምታን ካበዛ
ሀይልና ጉልበቱን በፍቅር ከገዛ
ሲመሽም ሲነጋ እዛው ካገኘሽው
ፍቅር የገባሽ ለት እሱ ሰው ያንቺ ነው

@Gitemenlenante
♡ ሳፈቅርሽ ኖራለው ♡
.
የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ብትጠይኝ ብትወጂኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እንነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ
.
የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!
.
የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባታፈቅሪኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው
@Gitemenlenante
(እናት)

እምዬ እናቴ
የኔ የግል ሀብቴ
ተቀምጠሽ ከጎኔ
እያየውሽ ባይኔ
ላኑርሽ ዘላለም ህይወቴ ነሽ ለኔ
ስታዘዝሽ ልኑር
ህይወቴ እንዲሰምር
ምክርሽ ህይወቴ ነው
ቁጣሽ ተስፋዬ ነው
ደስታሽ አለሜ ነው
እምዬ አበባዬ ካንቺ ጋራ ኖሬ
ምንም ሳልደብቅሽ የውስጤን ዘርዝሬ
ሀዘኔን ደስታዬን ላንቺ ተናግሬ
ልኑር ካንቺ ጋራ
ህይወቴ እንድትበራ

@Gitemenlenante
#40ቀን #ሲታደል
።።።።።።።።።።።።።።
በበለጠ አደፍርስ

ያደግሁት በዕድሌ
.........ያደገች በዕድሏ
እናት ስትፀንስ
..........ምንድን ነበር ቃሏ?
ልጅ በዕድሉ ያድጋል
............ሁሌ እየተባለ
ዕድል የሌለውስ
..........ከወዴት ተጣለ
40 ቀን ምንድነው
........ማነው ቀንን ሰጪ
ለሌላው ከሰጠ
..........ለኔም ይስጠኝ እንጅ
የ40 ቀን ዕድል
...........ለዘመን ይዘልቃል?
ሲታደል የሌለ
.........ከወዴት ይወድቃል

ብዙ ዘመናቴን
.........ሳካፍል ለዕድሌ
ብዙ 40 ቀናቶች
.........አሉኝ በበኩሌ
በይሁን ተወልዶ
..........በፈቃድ ያደገ
ረሃብና ጥሙን
..........በዕድል የሸሸገ
ዕድሌ ነው ይላል
..........የቀብሩ ለታ
ሟች ለቋሚ ሆኖት
.........የ40ቀን ውለታ

አንችን ልጠይቅሽ
.......ባለ ሰማንያዋ
አስረሽ ያልፈታሽው
............ቀን ባዕለፀጋዋ
ሰማኒያሽን ስጭኝ
..........ሰማኒያሽን ላውጣ
ዕድልሽ አይለፈኝ
..........ከ40 ቀኔ አይውጣ
ልደትሽ ሰማኒያ
ትዳርሽ ሰማኒያ
ተዝካርሽ ሰማኒያ
ፍታትሽ ሰማኒያ
.........አንዱን 40 ሁኝ
ምን ያደርግልሻል
..........ቀንን ብት'ጫኝ

ቀን ሰው ይሸከማል
.........ፊት በዕድል ሞቆ
40 ቀኔ ይላል
.........የሰው ዕድል ሰርቆ
40 ቀን ሲታደል
..........የለም ያልደረሰ
ተካፋይ መብዛቱ
..........ሔደ እየቀነሰ

በለጠ አደፍርስ

@Gitemenlenante
የኗሪ ታዛቢ!
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።
ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።
@Gitemenlenante
//🌜በምሽት ቀጥረኝ🌛//
ቀንማ ያው ቀን ነው በወጩ ወራጅ፣
በመጪና ሂያጁ በግርግር ብዛት፤
ጎዳናው ሲጨነቅ ሆዷን ባርባር ሲላት፣
ምድር ስትሳቀቅ በጠራራ ፀሀይ፣
በሚለባለበው ካንጀት ለሚፍቀር፣
ለኔና አንተ አይነት ሰው፣
በቀን መገናኘት ፍፅሞ እማይሆን ነው፣
በቀን መቃጠሩን ጭራሽ አታስበው፣
ይልቅንስ ውዴ
ጉንጉኑ ደመና በጨርቃ ሲደምቅ፣
ጀበር ስትገባባ አመሻሽታ ስጠልቅ፣
የቀኑ ግርግር በጨለማው ሲደቅ፣
ፀሀይ በተራዋ ቦታዋን ስትለቅ፣
ኮኮቦች ሲወጡ ጨርቃን አጅበው፣
በንፍስ ተከቦ ጭር ሲል ጎዳናው ፣
ሁሉም ክትት ሲል ሲገባ ወደቤት፣
ያኔ ነው ቀጠሮ ያኔ መገናኘት፣
እጄ ከትካሻህ ካለከልካይ አቅፎ፣
ወገቤ በክርንህ እስኪ በቃው ታቅፎ ፣
ያሻንን ብንሰራ ያሻንን ብናደርግ፣
ማንም ከልካይ የለም ማንም ባለማርግ፣
ስለዚህ የኔ ውድ
የፍቅሬ ባለሟል፣
ሁካት በሌለበት፣
በጨርቃ ፀዳል፣
በምሽት ቀጥርኝ ፣
ያን ግዜ ይሻላል።
@Gitemenlenante
2024/10/02 18:16:40
Back to Top
HTML Embed Code: