Telegram Web Link
#ሳይቀሰፉ_መዳን
ኤፊ ማክ

እኚሁ ድግምተኞች ፣ የነፍስ እንቅፋቶች ፣ አይነ ጥላ ጠለፍ
ደጃቸውን ሁሉ ፣ በመተት አጥረውት ፣ በየት በኩል እንለፍ?

ለዛፍ ለመሬቱ ፣ እንትፍ ባሉት ምራቅ ፣ ደም እየገበሩ
ካንድ ሰይጣን መክረው ፣ ባጎረሱት መዳፍ ፣ ስንት ሰው ቀበሩ
ላገር ነው ምንፀልይ ፣ ብለው ባጫጫሱት ፣ ባንዲት ሙዳይ እጣን
ለፍቅራችን ብለን ፣ የዘጋነውን በር ፣ ይከፍተዋል ሰይጣን።

ስንናከስ ፥ ስንላቀስ ፣ ቂም እየቋጠርን ፣ በልባችን ስርጉድ
ካስመለኩን ሰይጣን ፣ ያላወቅነው መላክ ፣ አተረፈን ከጉድ
​​​🌹💌...        

"ብታውቂ!"🌺

ከበእውቀቱ ስዩም

😁ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ፣
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ፣
ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ፣
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ፣
😁ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ፣
መነኩሴውን ከሱባዔ፣
ፈላስፋውን ከጉባዔ፣
እንደምትጠሪ፣
ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
እንኳንስ በኔ ልትስቂ፣
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ፣
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!
ስምሽ 🎤
መመክያዬ ክብሬ የስሜ መጠርያ
ስምሽ ስም ያስንቃል
ስሰማው ኢ.ቲ.ዮ.ጵ.ያ
ስምሽ ሲተረጎም
ፍቺው ደም ነው ፍቺው አጥንት
የቱ ባለቅኔ ኧረ የቱ ሊቅ ነው
በነብስ የፃፋት
ስምሽ እስትፋስ ነው
ሕይወት ያስቀጥላል
ስምሽ ብርሀን ነው
ፀሀይን ያስንቃል
ኢትዮጵያ ሲባል
እኳን ወታደሩ ካሕን ይሰለፋል
ስምሽ ከሞት በልጦ
ጥይትን ያስጠማል
ምንድር ሕብረቃሉ
ምንድር ነው ሚስጥሩ
ዙርያው ዳር ድበርሽ በስም
መታጠሩ
ስምሽ በባሕር ላይ ውሀን
እያስጠማ
ምርኮ ሚያዘጋጀው
ለንጉስ ከተማ
ስምሽ ከስሜ ይቅደም
ባንቺ ስም ልጠራ
ግርማሽ ፊቴን ይሙላው
ለጠላት ያስፈራ
ባንቺ ይሁን ሞቴ
ከምድርሽ አልውጣ
አኔም እንደ ቴውድሮስ
ለስምሽ ልቀጣ ።

@Gitemenlenante
እፉዬ ገላ

ምንም ላይፈጠር ከቶ ያለምክንያት
በጥዑም አንደበት ያኔ የዘመርናት
የልጅነት ዜማችን እሷም ሀቅ አላት!

አንቺ እፉዬ ገላ በሰማይ ምትበሪ
ንፋስ ወደመራሽ የትም የምትዞሪ
ባለፍሽበት ሁሉ ከልብ ተፈቃሪ
በብዙ አፍላዎች ከሩቅ ተባራሪ
ሁሉም ይደክማሉ ከእጅ ላትቀሪ!

ባሎችሽ ገለባ እውነት የሌላቸው
እንዲያው ሲዘውርሽ ንፋስ የዳራቸው
ልብሽን ላይቀርቡ ከሩቅ ምሸሺያቸው
አንጋጠው የሚያዩሽ ሊይዙሽ ሚሻቸው
ከላይ ሆነሽ ቁልቁል በፌዝ ምታያቸው!

እኔ ደግሞ አለው እጅጉን ማረባ
ከባሎችሽ ምመደብ ከሆኑት ገለባ
እድሜዬን የጨረስኩ አንቺን ሳግባባ
በአዙሪታም ፍቅርሽ ግራ የምጋባ
ሜዳ ነው በማለት ገደል የምገባ!

ፍቅርሽ የጨመረን ከአዙሪቱ መሀል
ከገደሉ ገብተን ካሎጣን የምንል
የፍቅርሽ አዘቀት በጅብ የሚመሰል
ከእግር ተነስቶ ልብ ላይ የሚወል
ከቶ ማንም የለም ሊወጣ የሚችል!



በእኛ አከባቢ ስንዘመረው የነበረው መዝሙር ስንኞች ለማስታወስ ያህል:-

(እፋዬ ገላ ባልሽ ገለባ
ሜዳ ነው ብዬ ገደል ስገባ
ገደል ገብቼ ልወጣ ስል
ጅቡ መጣብኝ ከእግሬ ስር)
🐠ይህንን ያውቃሉ

👉ኦይስተር የተባሉ የአሳ ዝርያዎች በየግዜው ፆታቸውን ይቀይራሉ። ይህም ማለት አንድ ግዜ ወንድ ሌላ ግዜ ደግሞ ሴት ይሆናሉ
📪ምንጭ[Television]
መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ !
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድሀን)
======

አምባ ወጥቼ እኩለ- ሌት ፤ ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፤ ልገላገል ከህመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፤ ደጋግሜ፤ ማህሌት ቆሜ

ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ፤እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፤ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በስጋዬ እሚነደውን፤ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ፤ ውዳሴዋን ደጋግሜ . ..
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፤ ደሞ ይምጣ የቁም ህልሜ ?

ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ!

በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ!
@Gitemenlenante
መለያየት ማለት
(ገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም)

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት
@Gitemenlenante
[አስቱ]
#አንቺ_ስትቀሪ


ሽፋን ታቅፊያለው ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
……………
ትመጣለች ይሆን እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
……………
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ

እያልኩኝ…

…እያልኩኝ
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ

አይኔ እሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ
ወዴት ነው ሚጓዘው ወደማን ይሸሻል!?

ታዲያ ስትቀሪ የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
……
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በምባዬ

"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።
ምክንያቱም

እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ

አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀና
ድንገት የቀረች'ለት ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና

ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"

አስቱ የነፍስ ሰው ፣ ሰው ያልተረዳው ሁለተኛው አያ ሙሌ
@Gitemenlenante
🚘ይህንን ያውቃሉ

👉የFerrari መኪና ማምረቻ ድርጅት ለድርጅቱ ተቀጣሪዎች ፌራሪ መኪና እንዲጠቀሙ አይፈቅድም
2024/10/02 20:42:55
Back to Top
HTML Embed Code: