Telegram Web Link
ያማል!*****
ሰለሞን ሳህለ

እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ ዝናብ ቀረ መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን ! እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ
ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ከ A & Y channel ቤተሰቦች 👥 ሰላም ለናንተ ይሁን 🙏
በዚህ channel ላይ በምንለቃቸው ነገሮች ደስተኛ እንደሆናችሁ እርግጠኞች ነን ለዚህም እናመሰግናለን 👏
እኛም በይበልጥ እናንተን ለማስደሰት በምንችለው አቅም ሁሉ እንጥራለን 👍
ሀሳብ አስተያየት ካለ በ inbox @CJmanCJ_BOT ላይ ሀሳቦን ያጋሩን እኛም እንቀበላለን 👋
አብራችውን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
🦆🌱ይህንን ያውቃሉ

👉በደቡባዊ አውስትራሊያ መገኛውን ያደረገው CROTALARIA CUNNINGHAMMI የተሰኘው የዛፍ ቅጠል ቅርፅ በሚገርም ሁኔታ HAMMINGBIRD ይመስላል።
@Gitemenlenante
😯ይገርማል😲

👉ይህ ህንዳዊ ግለሰብ በ16 አመቱ ነበር ዛፎች መትከል የጀመረው። ታድያ አሁን ይህ ሰው 47 አመቱ ሲሆን የሚኖረውም የግሉ ጫካ ውስጥ ከዱር አራዎቶች ጋር ነው።
@Gitemenlenante
....አልሄድሽም ሄደሻል...
መስኮት መጋረጃ የተከፈተ በር
የውሃ ብርጭቆ መሬት ላይ ሲሰበር
ባለ ሀምሳ ብር ካርድ ሳይፋቅ የነበር
በሳንቲም ተፍቆ ስልኬ ሆድ ሲቀበር
ለማን ልደውል ነው ? እንቺ እንደሁ ሄደሻል
የውሃው ብርጭቆ ናፍቆት ሞልቶልሻል
አንቺ የለሽምና
ሂደቴ ተዛባ ስርአት ገደፈ
የእራታችን ሰአት ሳላውቀው አለፈ
ቁርሳችን ቁር ሆነ ምሳም ተጣደፈ።
አንቺ የለሽምና
ከሸሚዜ በፊት ጃኬቴን ለበስኩት
ሙዚቃውን ትቼ ዜናውን ዘፈንኩት
" የእንዴት ነህ?" ሰላምታ
የጦርነት አዋጅ መስሎ አስደነገጠኝ
ሳይቀድሙኝ ለመቅደም
ካ'ብሮ አደጎቼ ጋር መጣላት አማረኝ
መሄድሽን ማወቄ ግራ እንዲህ ካጋባኝ
ማወቅ አልፈልግም እውቀት ምን ሊረባኝ
የለም የለም የለም አልሄድሽም ሄደሻል
በሻማሽ ብርሃን ቤትሽን አድምቀሻል
መሳብያው ውስጥ ሽቶሽ ደረቴ ላይ ሽታሽ
መኖሩን እያውኩ መኖሩን እያወቅሽ
አልሄድሽም ሄደሻል ግን ቶሎ ተመለሽ።
@Gitemenlenante
// እመጣለሁ በለኝ //
ፍቅሬ እንኳ ባይገባህ ለእኔም ባታዝንልኝ
እኔ እንደማስበው አንተም ባታስበኝ
እባክህን ፍቅሬ ባትመጣም ቅጠረኝ
ወደላይ ወደ ታች ሄድ መለስ እያልኩ
አላፊ አግዳሚውን ስአት እዬጠየኩ
ባትመጣም እንኳ ትመጣለህ እያልኩ
ሳላስበው መሽቶ ሌሊቱም ቢነጋ
እራቡም ቢጠና ሽ ግዜ ባዛጋ
ልቤ ከእኔ እርቆ መጥቷል ካንተውጋ
..........እናማ ናፍቆቴ
ይህን ሁሉ ስቃይ ድካሜን ተረድተህ
እንደው በፅኑ ቃል በለዛ አንደበትህ
እመጣለሁ በለኝ ቁሜ ልጠብቅህ //
@Gitemenlenante
/ ልቤ ምን አጠፋ //
እስኪ በል ንገረኝ ልቤ ምናረገህ
አፈቀረህ እንጅ አፍቅረኝ አላለህ
እሱ ወደደ እንጅ ውደደኝ መችአለህ
የመውደዴን ልኬት የፍቅሬን ስጦታ
ፈፅሞ ባታውቀው ልብህ ባይረታ
አይኖችህ ባያዩኝ ቆሜ ከከፍታ
........እኔ ግን
በጥላቻ ፈንታ ፍቅር እየሰጠሁህ
በመገፋት ፈንታ እየተከተልሁህ
በሄድህበት ሁሉ ሰለቸኝ ሳልልህ
አንተን ላለማጣት ፍላጎቴን ትቼ
ያንተን ለማሟላት የእኔን እረስቼ
ባንተ አለም ኑሪያለሁ በእራሴ አለም ሙቼ
........ታዲያ
የወደደህ ልቤን መውደድ ባትችልም
ለሰጠሁህ ፍቅር ምላሽ ባታገኝም
ማለት በቂ ነበር እኔ ላንች አልሆንም
........አንተ ግን
በለበስኩት ልብሴ መውደዴን ለክተህ
ማፍቀር እንደማልችል ግማሽ ሠው አድርገህ
እርካሽ በሚል ቃል የሰባበርክብኝ
ልቤ ምናጠፋ ፍቅርን በሰጠሁኝ //
@Gitemenlenante
ይቅር በለኝ ትዝ ይልሀል ውዴ?...
ፍቅሬን ስገልፅልህ ስነግርህ መውደዴን፤
አንዳችም ሳልደብቅ አውጥቼ የሆዴን፤
ማፍቀር መናፈቄን፣
መነሳት መውደቄን፣
ባ'ዘንህ አዝኜ በደስታህ መሳቄን። ነግሬህ ነበረ
አላረካሽ ቢለኝ ባ'ፌ ተናግሬ፤
በቅኔ ትሩፋት ቃል አሰማምሬ፤
ፅፌ ባሳይህም ፍቅሬን በብዕሬ፤
ከንቱ ይሆንብኛል ጣእም አልባ ፍሬ፤
ገና ያልተነካ ያልበሰለ ጥሬ። መልካምነትህን ከኔ አመሳስዬ፤
ልገልፀው ብጥርም በሸራ ላይ ስዬ፤
እሱስ መች ሊያጠግበኝ መች በዚ ልረታ፤
ደግሞም ሞክራለሁ በቀለም ጠብታ።
ከጠቢባን ጎራ ቃላት መራርጬ፤
ፊደልን እንደ ሽል እህህ..ብዬ አምጬ፤ ከጨረቃችን ጎን ከዋክብት ተቃቅፈው፤
በደመና ቀለም ሰማይ ላይ ብፅፈው፤
ጭራሽ ውበትህን አጥፍቶት አረፈው።
ስያሜ ፍለጋ ቢዝልብኝ ክንዴ፤
ሚዛን ደፍቶ ፍቅርህ ቢቀል መውደዴ፤
አፈቀርኩህ ስልህ የዋሸሁ መሰለኝ ይቅር በለኝ ውዴ።
@Gitemenlenante
ፍቅር እኮ ናት:
ድሮ ድሮ ድሮ… ድንጋይ ዳቦ እያለ
ሰማይ እንደ ጣራ ሳይርቅ ዝቅ እንዳለ
ዶሮም እንደ አሞራ መብረር እየቻለ
ታስታውሺ ነበር እወድሽ ነበረ…
.
ታድያ ምን ያደርጋል ሁሉም ተቀየረ
ድንጋይ ዳቦ ትቶ ድንጋይ ሆኖ ቀረ
ሰማይ አፈንግጦ እንደዚህ ከፍ አለ
ዶሮም መብረር ትቶ መራመድ ጀመረ
ልቤ ግን ልብ ነው ያኔ እንደነበረ
በዘመኑ ሙሉ ሲያፈቅርሽ የኖረ
በፍቅርሽ ታሞ ለፍቅርሽ የኖረ
ሳልነግርሽ…
.
.
አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በሰባራ መርፌ….
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
………………………………….
ሳልነግርሽ…
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት
ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡
እንደተለየሽኝ …
አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ
ፍቅርሽ እከክ ሆኖ…
በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡
…………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን
‹‹ታምሪያለሽ ›› እያልሁኝ ፣ ‹‹ተአምር ›› ማክተሙን
የተለየሽኝ ለት…
ምፅአት መምጣቱን ፣ የኔ አለም መቆሙን፡፡
…………………………………………
ሳልነግርሽ….
ካጣሁሽ በኋላ….
ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም ፣ የስቃዬን መአት
አፍቅሮ ማጣት ነው…
በሰባራ መርፌ፣
እውነትን መስፋት ነው ፣ ለካንስ ምፅአት፡፡
ከፍቅር በላይ
:
ይህ ፍቅር አይደለም
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደይ
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በይ
ከመውደድ
በላይ ነው የወደደኝ በይ
=ከንፈርሽ የግሌ=

አንቺ ስታለቅሺ
ከአይኖችሽ መሀል እንባ ስታቀሪ
እኔን ሆድ ከባሰኝ፤
የእንባሽ ዘለላ
ጉንጭሽን ሲነካው
እኔን ካስለቀሰኝ፤
።።።።።።።።።።
ከንፈርሽ ጋር ሲደርስ
እብደት ይሰማኛል፤
እሱን ከኔ ውጪ
ሲነኩት ያመኛል።
ይሰማኛል ብርዱ

ምን ባልማረርም
አውቃለሁኝ እሳት
የኔን ቤት ከነካ ፤ ጎረቤት አይምርም
.
.
ነበልባል ፍቅርሽ ግን ...
ነ...በል...ባል ፍቅርሽ ግን...
ከኔ ገላ ተርፎ
የወዳጄን አለም ፣ አቃጠለዉ አልፎ
.
.
እና እንደዚህ ሁነን...
አንሶላ ውስጥ ሰጥመን፤
አይኖችሽ ሲነዱ
እጆችሽ ሲነዱ
ጡቶችሽ ሲነዱ
...ዎችሽ ሲነዱ
... ... ሲነዱ
ነበልባል ታቅፌ ፤ ይሰማኛል ብርዱ !፡፡
@Gitemenlenante
።።።በጭስ ተደብቄ።።።
አንተን በመጠበቅ ሲጋ ለኩሼ
አንድ ፓኮ ሁለት አጭሼ አጭሼ
በጭሱ መካከል አገኝ ይመስል
በጭሱ እንፋሎት ውብ መልክህን ስስል
በነጋ በጠባ አንተን ሳብሰለስል
ውስጤኮ ቢከፈት ማድቤት ነው ሚመስል
ሰውነቱ አረስቶ አንተን ሲያብሰለስል
ግድ የለም ላጭሰው በጭሱ ልደበቅ
ካንተ የበለጠ እርሱን ነው ምናፍቅ
ሳባዬ ቢቃጠል ቢጨስም ቢነድ
በጭስ ተደብቄ በሀሳብ ስነጉድ
ሳንባዬን ጠባቂ ሰማይ ድመት የለ
አንተ አንዴ ሄደሀል መች ትመለሳለ
በጭስ ተደብቆ ህይወቴ መረረ
አንተ ብረሳ ብሎ ለሱስ ተዳረገ
ፍቅርክና ሱሱን በእኩል አሳደገ





ሺሻነ ሲካራ ልበልክ ሀስሼ
እንዲ መንገብገቤን ባላየ አረ ሼ
ናና በቃ አክመኝ አንተ ነክ ፈዋሼ
@Gitemenlenante
።።ለኔ.......ነው።።።
ሞቴን የሞትክልኝ የይሁድ አንበሳ
ስለኔ ተቀበልክ ያንን ሁሉ አበሳ
በምድር መውረድ ክብርህን መጣል
ንጉስ ሆነ ሳለ አለመከበር
ለኔ......ነው
ቀራኒዩን ያማጥክ የተሰቃየከው
ቁስለቴን ልትቆስል ስለኔ የተገረፍከው
እንደርኩስ ሀጥያተኛ በእንጨት መስቀል
ስለኔ ነው ጌታ አንተ መሰቀል
ለኔ.....ነው
ክብርህን የጣልከው የተተፋብህ
የሀጥያቴን ዋጋ በፅድቅ ከፍለህ
ሞቴን ሞተክልኝ ስርየት አገኘው
እየሱስ ለውለታ ምን እከፍልሀለው
ከአብ አስታረከኝ ሀጥያቴን ወስደህ
አማላጄ እየሱስ ስለኔ ሞተህ
መጋረጃው ተቀደደ ነገር ተፈፀመ ባንተ
የሲኦል በር ተዘጋ የገነት በር ተከፈተ
መዳን በቤታችን ዋለ ልቡ ለተከፈተ
በደም ምልክት የሞት አዋጃችን ተሻረ
መዳን ሆነል በሞት ተባረክ ተመስገን ልበል
የዘላለም ሊቀ ካህኔ መዳኛዬ አንተ ነህ
ማራናታ የኛ ጌታ ማህተባችንን የፈታህ
ለመላው የክርስትና ሀይማኖት ተከታይ በሙሉ እንኩአን አደረሰን መልካም በአል ይሁንልን

@Gitemenlenante
ንገሯት**
***
ንገሯት ለፍቅሬ~ለዛች ለምወዳት
በሬን ክፍት አድርጌ~እንደምጠብቃት
አትቅሪ በሉልኝ~ግዜው ቢሄድ ቢረፍድ
ልቤ ስለማይችል~ሌላ ሴት ለመልመድ
ዘመናት ተቆጥረው~ቢመጣም እርጅና
ያኔም ጠባቂሽ ነኝ~በልቤውስጥ ፍቅርሽ
ሁሌም ልጅ ነው እና
~~~~~~~~~~~~~~~~~
ኑሮን ለማሸነፍ~ነብስሽ አይቅር ባዶ
ልቤም እንዳይባክን~ፍቅሬ አንቺን ወዶ
አርጅቻለው ብለሽ~አታስቢ ላፍታ
ከበሬ ቁጭ ብዬ~እጠብቅሻለው የምትመጪ ለታ
~~~~~
ፀሀይዋ እንዳትጠልቅ~እንዲው እያየናት
እባክሽ ነይልኝ~ዳግም እንሙቃት

@Gitemenlenante
ልብ ስስ አካል

ያኔ ድሮ ገና ልጅ ሳለሁ ትንሽዬ
አካሌን ማስቀጥቀት ጀመርኩ ሀ ብዬ
ውዴ እኔ ልንገርሽ ያየሁትን ፍዳ
መምሩ ሲመቱኝ አስደግፈው ሠሌዳ
ከዛም ከፍ ስል የሠፈር ጎረምሶች
ጭንቅላቴን ያሉኝ ስንጫወት ሜዳ
ያን ተይው የኔ ውድ ስሚኝማ አንዴ
ወንድምሽ የመታኝ እኪናወጥ ሆዴ
ከሷ ራቅ ብያለው ብሎ ያስፈራራኝ ትዝ ይልሻል እነዴ?
እናስ ትዝ ይልሻል በፌደራል ዱላ እግሬን ተሰብሬ
በግዜ እንድገባ ሁሌ መመከሬ
ጨረቃን ባሳይሽ ብዬ ነበር ፍቅሬ
ታዲያ ዛሬ እሙ መላ አካሌ ዳብሯል
አጥንቴም ጠግኗል ጉልበቴም ጠንክሯል
ብዬ ልል አልኩና ስለማይበገር መላ አካላቴ ላወራ አልኩና
አፌን ያዝኩኝ ቶሎ ባንቺ አንዲት ቃል
የፈራረሠውን ስሱ አካሌን ልቤን አሠብኩና

@Gitemenlenante
#ጥፋተኛው_ፍቅር "
ያኔ ነው መጃጃል፤ያኔ ነው ሞኝነት፤
በፍቅርሽ ታውሬ፤አንቺን ያመንኩኝ 'ለት።
ያኔ ነው የሞትኩት፤አፈር የከበደኝ፤
ፍቅርሽ በልቤ ውስጥ፤ያለቦታው ሲገኝ
"'ወድሀለው"አልሽኝ፤ቃላትን መራርጠሽ፤
ማመን ማይታክተው፤ልቤም ተቀበለሽ፤
ከንፈሬን ስትስሚው፤ከንፈርሽን ስስመው፤
"ፍቅር ማለት እኮ የኔና የ'ሷ ነው"፤
እያልኩ አወራለው የፍቅርሽን ጥቅም፤
ጥሩነትሽን እንጂ ክፋትሽን አላቅም

ዛሬ ግን አየሁኝ........ ........
ዛሬ ግን አየሁኝ፤የፍቅርን አይነት፤
አንዱን ማግኘት ሲሹ፤ያኛውን መሰዋት።
ከኔ በፊት ኑሮሽ፤የፍቅርሽ አጋር፤
እሱን ለማስቀናት፤ጀመርሽ ከኔ ጋር፤
እኔ ግን አመንኩሽ፤መሰለኝ የእውነት፤
ከ'ሱ ያጣሽውን እኔ ለመስጠት፤
ግን....ውዴ ለምን ??
ሂይወት ሲሳካልሽ፤ሀሳብሽ ሲሞላ፤
የቀድሞ ፍቅረኛሽ፤በንዴት ሲፈላ፤
ይቅር በይኝ ሲልሽ፤ስላየሽ ከሌላ፤
እኔን ጥለሽኝ ሔድሽ፤ከለመድሽው ገላ
እንዳይድን አድርገሽ አረድሽው በቢላ
ውበትሽ ሊስበኝ ገላሽ ሊያማልለኝ
ሳቅሽ ሊማርከኝ ጫወታሽ ሊገዛኝ፣
ቃናሽ ሊናፍቀኝ ፈፅሞ አልችል አለ፡፡
ልብሽ ልቤን ጥሎ ጠፋ ኮበለለ፡፡
ዜማዬ ተለየ
ድምፄም ተቀየረ
ምንሽም ከምኔ አልገጥምልህ አለ፡
@Gitemenlenante
2024/10/02 22:24:20
Back to Top
HTML Embed Code: