Telegram Web Link
ለጤዛ ተዋድቀን

እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛ ሰማኒያ
ይሄም ኑሮ ሁኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ፅዋ ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ በአጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የት ገብተን እንረፍ
በዶፍ ዝናብ ሀገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያበቃል አንድ ቀን

@bewuketu seyoum
@Gitemenlenante
#የጠፍ_ትውልድ_ልሳን
-
"ሀገራችንን - ኢ ት ዮ ጵ ያ ን
ዳሯን እሳት
መሃሏን ገነት ____ አድርግልን!"
-
ብለን የጸለይነው
ሽቅብ የረጨነው፣...
እንባችንን ቆጥሯል።
ስዕለታችን ሰምሯል።
-
ይኸው በዳር ዳሯ - እሳት እናያለን
ምስክር ይሆን ዘንድ - በገነት እንዳለን¡¡
___________
[ በርናባስ ከበደ ]
@Gitemenlenante
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
እየውልሽ ውዴ
ሎሚ ገዛሁና
ጥምቀትን ጠብቄ ከደረትሽ ልጥል
ፈራሁና ተውኩት
ለስላሳ ጡቶችሽ ሚፈርጡ ይመስል
እውነት ለመናገር
ለሱ ብቻ አይደለም አለኝ ድብቅ ቅናት
ሎሚ ማን ሆኖ ነው
አዳምሽን ቀድሞ ሚገኝ ካንቺ ደረት
እንደውም እንደውም
ሰውነት አስጠላኝ ሎሚነት ተመኘው
ድንገት ተወርውሬ
ከደረትሽ ብገኝ ልብሽን ባገኘው
ከይሉኝታ ርቄ ደስታዬን ብኖረው
ምነው!!!
ሺ አመት አይኖር!!
ደግሞ ለስታዬ
ከሰውነት በታች ሎሚ ሆኜ ብኖር።
ከደረትሽ ውዬ
በውብ ከንፈሮችሽ ተመጥጬ ብቀር።

© ከፍፁም ጥበበ
@Gitemenlenante
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት ይሁንልን
🍋 መልካም በአል 🍋
🍋🍋🍋 @Gitemenlenante 🍋🍋🍋🍋🍋 🍋 🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 ሰላም ለናንተ ይሁን አልአዛር ነኝ ዛሬም እንደተለመደው አንድ የቻናላችን ቤተሰብ የግጥም ስራዋን ለእኛ ለ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች አድርሳልናለች እኛ የግጥም ስራዋን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል አብራችሁን ሁኑ እናም like በማድረግ በማበረታታት አብሮነታችሁን አሳዩን እንዲሁም የራሳችሁ የግጥም ስራዎች ለቻናላችን ቤተሰቦች ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በ ውስጥ መስመር (Inbox) @AS_CJman 👈 ላይ ማድረስና ማስተዋወቅ ትችላላችሁ #የናፍቆትን የግጥም ስራዎቿን ለማየትና ለማንበብ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
አሱን ስጠኝ ብዬ

የቆንጆዎች ቆንጆ የኔ ይሁን ብዬ አለሳካ አለኝ በኔ ብቻ ጥረት
እኔ ላቁምና ለሱ ልተውለት
አውቃለው ፈጣሪ ምንም አይሳነው
ግን ባንተ ሲሆን ውስጤ የፈራ ነው
አንተን በማጣት ውስጥ እራሴን ስስለው
ሙሉ ጭለማ ነው ምን ብርሀን የለው
መሆን አልፈልግም በፍፁም የሌላ
ቢቀር ይሻለኛል ህይወት ካንተ ሌላ
ስለዚ አምላኬ ወርቅ አልማዝ ዝናው ይቅርብኝ
የደስታዬን ሚስጥር እሱን ብቻ ስጠኝ
24 m
* ግራ የገባው መውደድ *
ነጭ የፈካ ጠዋት * ጥቁር ያዘነ ምሽት
ፈገግ ያለ ውሎ * ትክዝ ያለ ሌሊት
አንድ የጨዋታ ቀን * ሌላ የሰቀቀን
ያልሰከነ ሀሳብ * አንድ ያልሆነ ምኞት
የተቀያየረ * ጉራማይሌ ህይወት
ከተጋረጠባት
ስቃ ከምታለቅስ * ግራ ከገባት ነፍስ
ግራ ተዋድጄ * ግር አላት የኔ ነፍስ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ "ግር" አዲስ አይደለም
እንኳን አንቺ ቀርቶ ግር ብሏት ዓለም
ከዋከብት አጋጭታ
ፀሀይን ጨረቃን አቅጣጫ አስታ
አስክራው ታውቃለች ሁሉን ግራ አጋብታ
እንደ አንቺ ነገሩ ግር ያለባት ለታ ።
* **
አይዞሽ አንቺ ነፍሴ ተስፋ እንዳትቆርጪ
ምን ግራ ቢገባሽ ቀኝሽን ብታጪ
ግራ ከወደድሻት
ግራ ከገባት ነፍስ ደስታ ለመቋደስ
መስሎ መራመድ ነው
ስትስቅም መሳቅ ስታለቅስ ማልቀስ
የግራ መንገዷ ቀኝ እስኪሆን ድረስ።

#ጌትነት
@Gitemenlenante
...................... ያረፈደ
ብታመም ደግፎ
........... ምግብ ውሀ ስጥቶ
በጨንቀኝ አማክሮ
........ ሀሳቤን ተጋርቶ
ድሮ እንደምንሰማው ልክ እንደ ተረቱ
ሰው ነበረ ሁል ጊዜ ለሰው መድሀኒቱ
ዛሬ ጊዜው ከፍቶ ተራራቁ ሲባል
መድሀኒት ነው ቢባል ሰው ለሰው ማን ያምናል?
ግን....... በወሬ ብዛት ሚዛኑን ላልሳተ
ነገሩን አስተውሎ ለተመለከተ
ጊዜው ስለከፋ አንደ የተቀየረው
መድሀኒቱ ሳይሆን አወሳሰዱ ነው።

ሳሙኤል
@Gitemenlenante
ሼክስፒርዝም
.
(አብርሀም ሙሉ ሰው)

ደስተኛ ለመሆን ፤ አትሁን የተከፋ
የሌለህን ፈልግ ፤ ያለህ እንደ-ጠፋ
ከተራብክ ብላ ፤ ከተጠማህ ጠጣ
ከዛሬ አትራቅ ፤ ነገ ራሷ ትምጣ።
ከቸገረህ ጠይቅ ፤ ግን ከሰው አትጠብቅ
የሰው ትንሽ አትሁን ፤ ሁንም ለሰው ትልቅ
በአይኖችህ ከማልቀስ ፤ በጥርሶችህ ፈግግ
ያማረህን ሳይሆን ፤ 'ሚያምርብህን አድርግ።
ከመፃፍህ በፊት ፤ ምትፅፈውን አስብ
ከመፅሀፍት በላይ ፤ ራስህን አንብብ
መጨረሻ መልስ ፤ ጠይቅ መጀመሪያ
ወዲ አትጨነቅ ፤ አታስብም ወዲያ።
ሳትሞት መኖርህን ፤ አረጋግጥ በስራ
ትልቅነት ካሻህ ፤ በትንሹ አትኩራ።
@Gitemenlenante
(ይታየኛል )
በተማሩ እጆች ፣ መንገድ ተለክቶ
የመከራ ችግኝ ፣ ሳይቀር ተኮትኩቶ

ይታየኛል ፣ የረከሰው ሁሉ ሲቃና
ጥበብን አውጥቶ ፣ ሲሞሽራት እንደገና

በተሰጠው መክሊት፣ ፣ትዉልዱን ሲያንፅ
እውቀትን አንግቦ ፣ጠላቱን ሲገስፅ።

አዎ ይታየኛል _ _ _
የታሪክ አረሞች ፣ እንደዋዛ ሲነቀሉ
ፅናት እርቋቸው ፣ ከሀሴት ሲገለሉ

በእሾህ ተከበው ፣ በቅናት ሲዋትቱ
ክብር ቀርቶባቸው ፣ ሀሜት ሲሸምቱ።

አዎ ይታየኛል _ _ _
እሬት እየመከለ ፣ወይን ሲበቅል
ህዝቤ በየፊናው ፣ የልቡን ሲያዳቅል

ብሂሉን ቀምሮ፣ ቅኔውን ሲፈታ
እንባውን አብሶ ፣ ሲኳትን በደስታ።

#ቤዚቾ
@Gitemenlenante
ፀ ጨ
ሀ ረ
ይ ቃ
________________________________________________

ፀ-ዳል ሞልቶት ሳለ ፣ የመንበሩን ጓዳ
ሃ-ያሲው የጫረው ፣ የብራና ሜዳ
ይ-ወዳጅ ይመስል ፣ ከጨለማ ዝንጣፍ
ፀ-ልሞ የተጣፈ ፣ የፊደላት ምንጣፍ
ሃ-ቅታ የወረሰው ፣ የትልመት ምዕራፍ
ይ-ወብቃል መሃል ፣ በሚጋረፍ ጅራፍ።

ጨ-ቅላ እያለ ገና ፣ እንደጀማመረ
ረ-መጥ ሳይዞረው ፣ ፈክቶ እያመረ
ቃ-ናው የጣፈጠ ፣ ጥሞ የጎመራ
ጨ-ለማን ያራቀ ፣ ፅልመትን ያበራ
ረ-ጅም ያልሆነ ፣ የልጅነት ብራ
ቃ-ላቱ ያሞቃል ፣ የሃያሲው ስራ።

ፀ-ባዩ ሆነና ፣ ብዕርተኛ አመሉ
ሃ-ያል ሴራ በዝቶት ፣ ይፋጃል መሃሉ
ይ-ደፍቃል ከወጀብ ፣ በሚያስልበው ቃሉ።
ፀ-ጉር እያነጣ ፣ ጉንብስ እያስሄደ
ሃ-ሩር ያቀለጠው ፣ ጡዘት እየራደ
ይ-ሳሳና ዳሩ ፣ ያሳሳል ማለቁ
<ፀሃይን ሸኝቶ ፣ ጨረቃን ማርቀቁ>።


ህ-መምነውመጨለም፣ውበት ነው መጥለቁ
ይ-መራል ያጓጓል ፣ አቅምሶ መንጠቁ።
ወ-ዝ አለው መድረሻ ፣ ብራውን ሚያፈዘው
ት-ንግርት መጨረሻ፤ ጅማሬም እንደዛው፣

<ውልደት ጅምር ሆኖ ሞት ለሚሆን ማብቂያ መከራ ሚበዛው>።
________________________________________________



ህይወት ስትሆን ፀሐይ፤
በፈተና ንዳድ ፣ ትለበልባለች ለጋነቷን ለቃ።
መግባቷ ወቸጉድ ፣ መውጣቷም አጃኢብ ፣ ኑሮን የሳለባት የደራሲው እቃ።
የየጠዋት ውበት ፣ የየምሽት ድምቀት
የቀትር ግን ሲቃ።
ፅልመት ቢውጣትም፤
ምናል ብትለሰልስ እንደ ውብ ጨረቃ?
====================

tomi
@Gitemenlenante
#በዕውቀቱ ሥዩም

ያንን ገለባ ልብ ፣ ከ'ደጅ የወደቀው
አድራሻህ ወዴት ነው ፣ ብለህ አትጠይቀው
የነገው ነፋስ ነው ፣ መንገዱን የሚያውቀው ።

@Gitemenlenante
።።።።።ፍቅር በሁለት ትርጉም።።።።።
የአንድ ትልቅ ነገር ሁለት ትርጉም
ፍቅር ለሁለት ተተንትኖ ሲተረጎም
አንዱ ፍቅርን አጥቶ ፍቅርን ይሻል
ሌላው ፍቅርን ትቶ በፍቅር ይቀልዳል
#Alazar
@Gitemenlenante
🌿እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሰን!🌿
መልካም የትንሳኤ በዓል
*ያልታደለ*

ባይረዳው እንጂ ፣ሰው ጠላሁ እያለ ፣
ሚያወራ ለቀሪ ፤
ያጣ 'ለት ያውቀዋል ፣አቤት ለማለትም ፣
ያስፈልጋል ጠሪ ።
..........//........
ቀለም እና ውበት

#Helen Fantahun
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች 👥 እንደሚታወቀው ቻናላችን ለእናንተ ለቤተሰቦቻችን ግጥምን እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑ አባባሎችና ግጥሞችን እንለቅ እንደነበር ይታወሳል እንዲሁም የቻናላችን ቤተሰቦች የራሳቸውን የግጥም ስራዎቻቸውን ለቻናላችን ቤተሰቦች እንዲደርስላቸው እናደርግ ነበር ሆኖም ከጊዜያት ቦሀላ በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ከቻናላችን ጠፍተን ነበር ለዛም ይቅርታ እንጠይቃለን 🙏 ከዚህ ቦሀላ ይህ ስህተት እንደማይደገም ቃል እንገባለን እናም በትዕግስት ለጠበቃችሁን የቻናላችን ቤተሰቦች ምስጋናን እያቀረብን አሁንም አብሮነታችን አይለየን ከነገ ጀምሮም ስራችንን የምንጀምር ይሆናል እናመሰግናለን።

#ግጥምን #ለናንተ
2024/11/15 10:04:55
Back to Top
HTML Embed Code: