Free Education Ethiopia ️︎
Photo
" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዓብይ አህመድ፣ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸው ይታወሳል።
በዚሁ እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለእነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የትምህርት እድል/ Scholarship / እንደተገኘ መግለፃቸው አይዘነጋም።
ከዚህ የትምህርት እድል ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የትምህርት እድሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት የተገኘ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎቹ ከመስከረም/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲማሩ መመቻቸቱን ገልጿል።
ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት #የእንግሊዝኛ_ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንድቆዩ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ተማሪዎች የተፈጠረላቸዉ እድል በቀጣይ እየተፈጠረ ላለዉ በዉድድር ላይ የተመሰረተ ዓለም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ምሩቃንንና ሳይንትስቶችን ፣ ቴክኖሎጂስቶችን፣ መሪዎችን የመፍጠሪያ ልዩ እድል መሆኑን የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ በሄዱበት የሀገር ስምና ገጽታ ናቸዉ ብሏል።
የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል በጣም ጥሩ እድል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች #እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም ሲል አሳውቋል።
ተማሪዎቹ መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ተገልጿል።
ተማሪዎቹ በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ ?
🏫 የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ ፦
የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ አምሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።
🏫 አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦
አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በአለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።
🏫 ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ፦
ካሊፋ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።
🏫 ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ፦
ዪኒቨርሰቲ ኦፍ ሻርጃ በ 1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።
🏫 ዛይድ ዩኒቨርስቲ ፦
በ1998 የተመሰረተና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስመ ጥር የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው።
https://www.topuniversities.com
#ትምህርት_ሚኒስቴር
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!

Top Universities
QS World University Rankings, Events & Careers Advice at TopUniversities.com
Discover the best universities worldwide - study abroad guides, upcoming events, scholarships, careers advice & latest QS rankings at TopUniversities to find your perfect University.
" የውጭ የትምህርት እድል ያገኛችሁ ተማሪዎች ወደ ተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ ግቡ " - ትምህርት ሚኒስቴር
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያመጡና የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ የተሰጣቸው 273 ተማሪዎች ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ትምህርት ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
ተማሪዎቹ የውጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው።
ለውጪ ሀገር ትምህርታቸው የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀደም ሲል ከተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ግልጿል፡፡

" ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል " - UNICEF
በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ለመክፈት ዕቅድ መውጣቱ ተገልጿል።
በትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከመራቃቸው ባለፈ መምህራንም ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አልተከፈላቸውም
ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ እንደገና ለመክፈት ዕቅድ እንደተያዘም (UNICEF) የትምህርት ኃላፊ ቻንስ ብሪግስ ተናግረዋል።
"በትግራይ ሙሉ በሙሉ የትምህርት ሥርዓቱ ፈርሷል"ያሉት ቻንስ ብሪግስ " ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ2.3 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የሚያሳይ መረጃ አለን" ብለዋል
በመቐለ ከባለቤታቸው እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ነዋሪ የሆኑት አቶ መንግሥት ገብረመድኅን የእርስ በርስ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ሁለቱ ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር።
" የአየር ጥቃቶች እና የድሮን ጥቃቶች ድምጽ ይሰማሉ። ህጻናቱን ጠመንጃ ይዘው የሚሄዱ ወታደሮችንም ያያሉ። እነሱንም ለማስመሰል ይሞክራሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።
" ደመወዛችን አየተሰጠን ስላልነበር ልጆቻችን ምን እንደምንመግባቸው ያስጨንቀን ነበር ስለዚህ እነሱን በማስተማር ላይ ማተኮር ፈታኝ ነበር። ነገር ግን ትናንትና ደመወዜን ተቀበልኩ፣ አሁን ለልጆቼም ልብስ እና ምግብ መግዛት እችላለሁ " ብለዋል
በትግራይ በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ሚሊዮኖች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል መምህራን ደግሞ በጦርነት ምክንያት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቆይቷል

" የመውጫ ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር
250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።
ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።
የመውጫ ፈተናው #በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ #ኢፕድ

Free Education Ethiopia wish to all Muslims Brothers and Sisters a Happy Ramadan Month . The divinity of this Holy Month erase all the sinful thoughts off our mind and fill it with a sense of purity and gratitude towards Allah! Ramadan Mubarak to you!
#Ramadan2023 #MuslimMonth #PrayforUnity #Peace #HolyMonth
Stay Safe

የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና
" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።
የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦
- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።
- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።
- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
👉 የሒሳብ፣
👉 የአካባቢ ሳይንስ፣
👉 አማርኛ፣
👉 አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።
- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።
- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።
- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።
- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።
- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።
- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።
#ኢፕድ

#ExitExam
ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
ምን አሉ ?
ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦
" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።
ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።
ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።
አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።
ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።
ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "
የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።
ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።
እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "
Via Tikvah

#NationalExam
" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።
የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።
የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።
ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?
- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።
- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?
ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
Via MoE

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም ይጀመራል፡፡
የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል፡፡
በበይነ መረብ አማካይነት በሚደረገው ምዝገባ፤ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች 850 ሺህ የሚጠጉ እንዲሁም በግል 200 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል፡፡
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወቃል።

የነጻ ትምህርት ዕድል !
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 - 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ወይንም በአገር አቀፍ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡
የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው በተጨማሪም በድረ-ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0256663738/1139 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡
(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)

#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆመ።
ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማትና ተቋማቱን የሚከፍቱ ባለሀብቶች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎችን እያዘጋጀ እንደሚገኝ አሳውቋል።
በዚህም ከኅዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን በተቋሙ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ም/ዋ/ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
አዲስ ለሚከፈቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት በማቆም ያሉትን የማጥራት ሥራዎች ላይ ትኩረት መደረጉን ኃላፊው ይገልጸዋል።
በተያዘው ዓመት አዲስ ፈቃድ የመስጠት ሥራ ይጀምራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።

🌹🌺💐🌹🌺💐🌹🌺💐🌹🌺💐
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!
መልካም የትንሣኤ በዓል !

🌙 🌺 🕌 🌙 🌺 🕌 🌙 🌺 🕌
እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የዒድ አልፈጥር በዓል #ነገ መሆኑ ታውቋል።
የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

#ብሔራዊ_ፈተና
" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።
ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።
ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

'' መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የውትድርና ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል " - ዲማ ኖጎ ( ዶ/ር)
መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
ሰብሳቢው ይህንን ያሳወቁት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡
ዶ/ር ዲማ ናጎ ምን አሉ ?
" ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 15 ዓመት የሞላቸው እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።
ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል። "
የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ የተጣለበትን ሀገር የመጠበቅ ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የተሻለ ሠራዊት ለመገንባት ማነቆ የሆኑ ሕግ ማዕቀፎችን እና ተቋማዊ አስተሳሰቦችን በመፈተሽ ለሀገር እና ሕዝብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነው የተገለፀው።
ምክር ቤቱ በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1286/2015 አድርጎ በስድስት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
Via HoPR

የ12ኛ ፈተና ምዝገባ ነገ ያበቃል⚠️
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኞች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።
በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችን " ከነገ በኋላ አላስተናግድም " ሲል አሳውቋል።
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ከምዝገባው መጠናቀቅ በኃላ ይፋ ይደረጋል።
ተፈታኞች እስካሁን ድረስ የመፈተኛው ቀን ይፋ #አለመደሩግን በማወቅ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ በተጋጋ መንፈስ ዝግጅታቸሁን አድርጉ።