Telegram Web Link
"የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል
የተመዘገበ መሆኑን ያመላከተ ነው" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 


ጥር 22/2025ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር)  የትምህርት ሚኒስትሩ  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ2014ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተና የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ገልጸዋል።

የዚህ አመት የፈተና ውጤት አንድምታም ለዓመታት ሲንከባለል የቆየ በርካታ ችግሮች መገለጫ እና ተሸፋፍኖ የቆየውን እውነተኛ የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ  የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተሰጠው ፈተና ስርቆትን እና ኩረጃን ማስቀረት የተቻለበት እንደሆነ ገልፀው ውጤቱም የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተገኘው ውጤት መሰረትም ከ 50 በመቶ በታች ያመጣ ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንደማይገባም ተናግረዋል።

በ2014 ዓ.ም በተሰጠው ፈተና በሁለቱም የትምህርት መስክ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ 29 ሺህ 909 የሚሆኑት ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

በመሆኑም  በቀጣይ እንደሀገር በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉም አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን  አስመልክቶ መግለጫ  መስጠቱ ይታወሳል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በ 2015 Freshman የሚማሩት 30ሺ ተማሪዎች ብቻ ናቸው‼️

29,909 ተማሪዎች በ 2015 ዩኒቨርስቲ ገብተው አንደኛ አመት ይማራሉ። ስለዚህ በቅርቡ ትጠራለችሁ።

ያለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት ኮሌጅ ገብተው Freshman ለመማር እድሉ ጠባብ ነው። ምክንያቱም በዚህ አመት College'ች የማካካሻ ትምህርት ነው የሚያስተምሩት።

ሌላው የ 100ሺ ተማሪዎች ምልመላ ከ 10 ቀን በኋላ ይደረጋል። ከበዛ እስከ 15 ቀን ብቆይ ነው።

እነዚህ ተማሪዎችም ከምልመላው በኋላ ምደባ ተደርጎላቸው የማካካሻ ትምህርት ለዚህ አመት ይማራሉ ተብሏል።

በግል ተቋም/ ኮሌጅ/ ላይ ገብቶ የማካካሻ ትምህርት መማር የሚችሉ የመቁረጫ ነጥብ ይነገራል ተብሏል።

ኮሌጅ የምትገቡት ድግሪ ለመማር ሳይሆን የማካካሻ ትምህርት ተምረው ውጤታቸውን ለማሻሻል ነው።

ለሁሉም የማካካሻ ትምህርት ለምወስዱ ( በዩኒቨርስቲም በኮሌጅም ለሚማሩ) ተማሪዎች ፈተናው #ተመሳሳይ ነው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

" ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያው ቀን ነገ 11:30 እንደሚያበቃ አውቀው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለን የሚሉትን ቅሬታ እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳቸው ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠባበቁ አሳስቧል።

በተጨማሪ ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከቱ የስም ዝርዝራቸው ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ እንደሚያሳውቅ የገለፀው አገልግሎቱ ተፈታኞች ቅሬታቸውን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራቸው ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#ማስታወሻ

የዩኒቨርስቲ ምደባ በቅርቡ ይደረጋል።

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ያመጡ 29,909 ተማሪዎች በ 2015 አንደኛ አመትን ተምረው እንዲጨርሱ ሲባል በቅርቡ ምደባ ተደርጎ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረጋል።

የ 100 ሺ ምልመላ ከሰኞ ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል። ከዚሁ ጋር አያይዘውም የማካካሻ ትምህርቱ እንዴት እንደሚሰጥ ማብራሪያ ይደረጋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የእምነት የእርዳታ ድርጅት የእርዳታ ፕሮግራም በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለሚገኙ ከ2-12ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች ትምህርታዊ የሆኑ እርዳታዎች እንደ የት/ቤት ክፍያ፣የመማሪያ ቁሳቁሶች፣ በትምህርት ለሚወጣ የቤት ኪራይና ለተለያዩ ትምህርታዊ ወጪዎች የሚሆን እርዳታ የሚያቀርብ ፕሮግራም ነው።

ለማመልከት የሚያበቁ መስፈርቶች

⁃ ከ2ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ
⁃ የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ
⁃ ለትምህርት የሚውል የገንዘብና የቁሳቁስ
⁃ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የትምህርት ማስረጃ ወይም ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
⁃ ተጨማሪ ማስረጃ በተጠየቀ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ

የማመልከቻ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን:- የካቲት 8-2015

የግል ማብራሪያ ጽሁፍ መስፈርት

ሁሉም አመልካች ከ1 እስከ 2 ገጽ የሆነ ጽሁፍ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ መጻፍ ይኖርባችዋል። ሙሉ ስም፣ የትምህርት ክፍል፣ እድሜ፣ ስልክ ቁጥር(የግልና የትምህርት ቤታችሁን)፣ እና አድራሻ( የግልና የትምህርት ቤታችሁን) ማካተት ይኖርባችኋል
ጽሁፉ ስለራሳችሁና ስለቤተሰባችሁ ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጽና ስላላችሁ የማንኛውም የስራ ልምድ፣ ትርፍ ጊዜያችሁን በምን እንደምታሳልፉ፣ ለማህበረሰቡ ያበረከታችሁት የበጎ ፍቃድ አድራጎት፣ ወደፊት ምን መሆን እንደምትፈልጉ፣ እና ይህ እርዳታ ለምን እንደሚያስፈልጋችሁ የሚገልጽ መሆን ይኖርበታል

የማመልከቻ ሂደት

ማመልከቻውን ከግል ጽሁፍ፤ የትምህርት ማስረጃ (ሰርተፊኬት) ጋር ከየካቲት 8-2015 ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ያስገቡ።

ኢሜል: [email protected]
ቴሌግራም: +1-267-366-3436 (@emnetcommunityoutreach)


ለበለጠ መረጃ
ስልክ- +1-267-366-3436
ኢሜል- [email protected]
የመገናኛ ብዙሃን- ፌስቡክ፣ቴሌግራም፤ኢንስታግራም- @emnetcommunityoutreach
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

የህንድ መንግስት በ2023/24 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 መሆን ያለበት ሲሆን እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦

http://a2ascholarships.iccr.gov.in

የማመልከቻ ጊዜው የሚጀምረው የካቲት 13/2015 ዓ.ም ሲሆን ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም ያበቃል።

Via Tikvahuniversity
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
U.S. Historically Black Colleges and Universities virtual College Fair
When: Thu, Feb 16, 2023 at 4 PM
Register: https://bit.ly/HBCU23studentreg

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#MoE

የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:  https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር ያሳውቃሉ ተብሏል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#የመቁረጫ_ነጥብ

የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263

- የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 227

- የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 220

- የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 190

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ12ኛ_ክፍል_ማጠናቀቂያ_ፈተና_ወስደው_የማለፊያ_ውጤት_ያላመጡ_ተማሪዎች_1.pdf
4.9 MB
ሙሉ ማብራሪያ የያዘ ሰነድ

የ12ኛ-ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ማስፈፀሚያ ሰነድ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ለ 2015 የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 13 - 14.

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16.

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 20-21.

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16

ባህር ዳር ዩንቨርስቲ - የካቲት 20 - 22

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ Online ምዝገባ የካቲት 20-26.
(  የመግቢያ ቀንየካቲት 27-28 )

ያልጠሩ ዩኒቨርስቲዎች ዛሬ እና ነገ ይጠራሉ።

የ Remedial ተማሪዎች ምደባ በዚህ ሳምንት ይከናወናል። ወደ ዩኒቨርስቲ የምትገቡባት ቀን ሩቅ ስላልሆነ ተዘጋጁ።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ጉዳዩ ፡ የነፃ የትምህርት ዕድልን ይመለከታል

👉ጠብታ አምቡላንስ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመሪያውን የግል የኢመርጀርሲ ሜዲካል ቴክኒሽያን ባለሙያ ደረጃ 4 ማሰልጠኛ ተቋም የሆነውን ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅን በመክፈት ከፍለው ለመማር አቅም የሌላቸው ወጣቶች የነፃ ትምህርት እድል በመስጠት አሰልጥኖ በጠብታ አምቡላንስ ቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት እና በጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው::

👉ኮሌጁ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም በግል ኮሌጆች ከፍለው መማር የማይችሉና የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ ውስን ሰልጣኞች በመመልመል የነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል ።

የመግቢያ መስፈርቶች

👉1. ከ2011 - 2013 ባለው የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ውጤታቸው ለወንዶች ከ293 በላይ ለሴት ከ278 በላይ ያመጡ፡፡

👉2. የ2014 ዓ.ም ተፈታኞች በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የቴ/ሙ/ የመግቢያ ነጥብ ያለው/ያላት፡፡

👉3. ዕድሜ ከ30 ዓመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፡፡

👉4. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል የምትችል፡፡

👉5. ከፍለው ለመማር የማይችሉ መሆኑን የሚገልጽ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

👉6. ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል

👉7. ስልጠናውን ለ20 ወራት በመደበኛ ፕሮግራም

👉የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ መጋቢት 2 /2015 ዓ.ም

👉የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቦታ ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ አድራሻ 22 አካባቢ እየሩሳሌም ህንጻ ፊት ለፊት ዮናስ ሆቴል ጀርባ

👉ለምዝገባ ሲመጡ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ፣ትራንስክሪፕት ፣ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ።

የፈተናው ጊዜ ከምዝገባ በኋላ ይገለጻል፡፡

Via: የየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ALX Data Analytics
📅 Deadline: March 27, 2023
📍 ALX

Seize the opportunity to become a Data Analyst. Our beginner-friendly and accessible program is perfect for anyone regardless of educational background or math skills.

Apply now at and unlock your full potential in a growing industry! Limited Enrollment.

Enroll: https://bit.ly/3kzfSNm
.
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል

Via ahadu
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2024/11/18 17:32:54
Back to Top
HTML Embed Code: