Telegram Web Link
Free Online Courses with Free Certificates 😳

To Get the links join our Telegram channel 👇🏾

https://www.tg-me.com/+puCKK4wyq0sxODlk

#Ad 🔖
📅 መስከረም 28 II ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
🇩🇪በጀርመን ስለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርቶች እንዴት እንዘጋጅ
📅Get prepared II October 8
🇩🇪Study in the Germany II How to prepare for it.
Register on the link below 👇👇👇👇👇👇👇
Registration link: https://docs.google.com/forms/d/1Gw0_bYue4Vvrt4uOYoF08ytl56dDPGoQUxh5fBKCByE/edit

For more info:
TikTok: @estifanosalemayehu1
Telegram: @OHUB4AllET
#science #technology #scholarships #internships #mathematics #engineering #materials #engineering #Scholarships #SDG2030 #youthsummit #youthconference #conference
\
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በወጣላቸው የጉዞ መርሃ - ግብር መሰረት ለፈተና ወደየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች እየተሸኙ ይገኛሉ።

ከዚህ ባለፈም ፤ ሰኞ መስከረም 30 ለሚጀምረው ፈተና ተማሪዎች ወደፈተና ማዕከሎቻቸው እየገቡ ሲሆን በሚገቡበት ተቋም እንዲሁም ከመነሻቸው የፀጥታ አካላት ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቀ እንዲሁም የተማሪዎች ደህንነት እና የተቋማት ሰላም እንዲረጋገጥ 8,000 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሳተፋሉ።

NB. የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29 እሁድ ጠዋት ላይ መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።

ፎቶ፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ፣ የደ/ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ፣ በሺንሺዳ ከተማ ኮሚኒኬሽን

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ ይሰጣል❗️

ዘንድሮ ወደ 12ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች በመደበኛው ጊዜ ማለትም ግንቦት ወር ላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። የትምህርት ካላንደሩም ወደ ድሮው ስርአት ይመለሳል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ85 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

አቶ ባፋ ባጋጃ ይባላሉ። የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሚወስዱ ተፈታኞች መካከል አንዱ ናቸው።

የስምንት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ባፋ፤ በ1949 ዓ.ም የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።

የ85 ዓመቱ አዛውንት በ2009 ዓ.ም ከ66 ዓመት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በድጋሚ በመጀመር በባይራ ኮይሻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

"እውቀት መቅሰም በእድሜ አይገደብም" የሚሉት አቶ ባፋ፤ ዓላማቸው ተምረው ለአገር ውለታ መስራት መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሀድያ እና ከወላይታ ዞኖች የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በመቀበል ላይ ነው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
ጥንቃቄ ‼️ የ 12ኛ ክፍል

ፈተናው ተሰርቋል በማለት ይሄንን የ #Social_Maths ጥያቄዎች ተሰራጭቷል።

ይህ የ አ.አ Model ጥያቄ ነው። ተማሪዎችን በማጭበርበር #ብር እያስከፈሉ ስለሆነ ጥንቃቄ እንድያደርጉ #ሼር አድርጉላቸው።

ውድ የ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናውን ተረጋግታችሁ እንድትሰሩ ከተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንድትርቁ እናሳስባለን።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Wishing you a Happy Mawlid al-Nabi!
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን የደስታ በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
ከልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱት አዛውንት

አቶ አበራ ቦራ ይባላሉ። የስምንት ልጆች አባት ናቸው። ከጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ነው የመጡት።

በ65 ዓመታቸው ከመጨረሻ ልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተዋል።

"መምህር የመሆን የልጅነት ህልሜን ለማሳካት በቂ ዝግጅት አድርጌ ለፈተን ቀሪቤያለው" ሲሉ ይናገራሉ።

አዛውንቱ በቤተሰብ ኃላፊነት የተነሳ ለረጅም ጊዜ ያቋረጡትን ትምህርት በ2009 ዓ.ም ካቋረጡበት በመቀጠል ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የአዛውንቱ የመጨረሻ ልጅ ተማሪ ሳሙኤል አበራ በበኩሉ አባቴ “እድሜህ ገፍቷል ትምህርት ምን ይሰራልሃል“ የሚለውን ትችት ሳይቀበል ከእኛ ጋር እኩል በመማር እዚህ መድረስ መቻሉ ለበርካቶች ትምህርት ነው ሲል ለኢዜአ ተናግሯል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
" ስልክ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ገልጿል።

የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል ያለው አገልግሎቱ ከዚህ በተጨማሪ አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል ሲል አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ #ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

ድርጊቱ #ከፍተኛ_የፈተና_ደንብ_ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ሲልም አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።


@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
ነገ የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ለምትጀምሩ ተማሪዎች መልካም ፈተና ይሁንላችሁ!!

Good luck with your exams!
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

#positive_mind #positive_vibes
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና ሂደቱን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (ሀዋሳ እና መቅደላ አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና " የማህበራዊ ሳይንስ " የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀግብር ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

በነገው ዕለት የመጨረሻው ቀን የፈተናው መርሃ ግብር ተካሂዶ ቀድሞ በወጣው መርሀ ግብር ተማሪዎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዛሬው የፈተና ውሎ ጋር በተያያዘ በተለይም በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች  አንዳንድ ተማሪዎች ከፈተና ማዕከል ለቀው ስለመውጣታቸው ለመስማት ችለናል።

በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ምንድነው የሆነው ?

#DebreTaborUniversity

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት በተወሰኑ " የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም ፤ አንፈተንም ! " ባሉ ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ተስተጓግሎ ነበር ሲል ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተለይ " ካልተኮራረጅን አንፈተንም ! " በሚል እሳቤ ለመበጥበጥ የሞከሩ አካላት ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ፣ ከደብረ ታቦር አስተዳደር ፣ ከከተማው ሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ባደረገው ጥረትና ውይይት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ሲል አሳውቋል።

በከሰአቱ መርሀ ግብር የፈተና አሰጣጥ ፤ " ስርዓቱን አክብረን እንፈተናለን " ያሉ ተማሪዎች ተለይተው ፍጹም በሆነ መረጋጋት ፈተናቸውን እንደተፈተኑ ተቋሙ ገልጿል።

ዛሬ በደብረ ታቦር ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ አንድ የደብረ ታቦር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ምክንያቱ በምን እንደተነሳ ባያውቀውም በግቢው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ጩኸት እና ተኩስ ሲሰማ እንደነበር ገልጿል።

የዶቼ ቨለ ሬድዮ በበኩሉ አንድ የአይን እማኝ በግቢው በተፈጠረው ችግር ጉዳት መድረሱን እንደገለፁለት ዘግቧል።

ፈተናውን መፈትን የማይፈልጉ ግቢውን እንዲለቅቁ ፣ ፈተናው መፈተን የሚፈልጉ ደግሞ ወደ ፈተና አዳራሽ እንዲገቡ ተነግሮ ፈቃደኛ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ እየተፈተኑ እንደሆነ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ ግቢውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉን እኙሁ የአይን እማኝ ተናግረዋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ ስለጉዳት መጠን እና ዝርዝር ያለው ነገር የለም። ስለደረሰ ጉዳት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እንጥራለን።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፤ የተማሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ ያሳሰበ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።

በተቋሙ ያልተከናወኑ ጉዳዮች የተፈጸሙ በማስመሰል ኃላፊነት የጎደለው አሉባልታ በማሰራጨት ተማሪዎች ፈተናቸውን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ እንዳይፈተኑ ለማድረግ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እያሰራጩ የመገኙ አካላት  ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አጥብቆ እሳስቧል።

የቲክቫህ ቤተሰብ የሆነ አንድ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ የግቢው መግለጫ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀው " እደግፈዋለሁ " ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ስለጉዳዩ ምንም ሳያውቁ የሚፅፉ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት ይበልጥ ትውልዱን በራሱ እንዳይተማመንና እራሱን እንዳይችል የሚያደርግ እና ሀገርንም በእጅጉ ሚጎዳ ተግባር መሆኑ ጠቁመዋል።

ዛሬ ፈተናውን ሳይፈተኑ ግቢውን ለቀው ወጡ ከተባሉ ተማሪዎች በኩል ምን እንደተፈጠረ እና እንዳጋጠመ ለማወቅ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክታቸውን ማግኘት አልቻልንም።

#DebreMarkosUniversity

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ፤ ለዶይቼ ቬሌ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ፤ " ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል። " ሲሉ ተናግረዋል። 

ተማሪዎቹ ፈተና እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ሲሉ ገልፀዋል።

" ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬ እና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል " ያሉት አቶ ይትባረክ ፤ " ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው ተፈትነዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ " እንደተደበደቡ እና እንደተዋከቡ " ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልጸዋል።

የደብረ  ማርቆስ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ተፈራ መላኩ ለአሐዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠቱ ቃል ደግሞ ፤ በዩኒቨርሲቲው ስር 4 የመፈተኛ ጣቢያች መኖራቸውን ጠቅሰው የዛሬውን ፈተናን አንፈተንም ብለው  የወጡት በ " ጤና ካምፓስ " ውስጥ ሲፈተኑ የነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።

የተማሪዎቹ ፈተና አቋርጦ በፈተና ማዕከል መውጣት ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በርካታ የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ተፈራ ፤ " ተማሪዎቹ ፈተናውን ያቋረጡበት ዋነኛው ምክንያት ከዝግጅት ጉድለት የመነጨ ነው። " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ በበኩሉ ፈተና አቋርጠው የወጡት በዩኒቨርሲቲው ጤና ካምፓስ የሚፈተኑ እና "ፈተናው የከበዳቸዉ ጥቂት ተማሪዎች " ናቸው የሚል መረጃ አጋርቷል።

ፈተና ጥለዉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ በ2013 ዓ.ም የጨረሱና ዳግም ፈተና የተፈቀደላቸው መሆናቸው ፖሊስ ያጋራው መረጃ ይገልጿል።

"ፈተና መፈተን ያልፈለጉ" ተማሪዎች በሰላም ግቢውን ለቀው ወጥተው እያለ ተቋሙ ውስጥ ብጥብጥ እንዳለ ተማሪዎችም እንደቆሰሉ ፣ እና እንደተደበደቡ ተደርጎ የሚሰራጨዉ ፍፁም መረጃ ሐሰት ነው ሲል አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር በደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ጉዳዩ ላይ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2024/12/26 16:27:16
Back to Top
HTML Embed Code: