Telegram Web Link
" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር

#MoE

• 12,787 ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም ብለው ጥለው ወጥተዋል።

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ለፈተና ከተቀመጡ 595 ሺህ ተፈታኞች ውስጥ 586 ሽህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል።

" ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጥተዋል " ሲል አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Free Online Courses with Free Certificates 😳

To Get the links join our Telegram channel 👇🏾

https://www.tg-me.com/+puCKK4wyq0sxODlk

#Ad 🔖
PREMIUM COUNSELTANCY & PAYMENT SERVICE

🔔 በአሜሪካ ባሉ አለምዓቀፍ የትምህርት ተቋማት የመማር ፍላጎቱ አሎት ?

📚 PREMIUM CONSULTANCY &  PAYMENT SERVICE ፍላጎቶትን እንዲያሳኩ ላግዞት ይሎታል።

🎈በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የ Partial scholarship እድሎችን ከእኛ ጋር ያሳኩ ።

📚በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰጠውን አገልግሎታችንን ይጠቀሙ ።

👉የ DUOLINGO ፈተናን በ 2999 ብር ብቻ በ @leinadani ከፍለው ይፈተኑ።

👉ለDUOLINGO ፈተና ለመዘጋጀትhttps://www.tg-me.com/Premiumduolingo ይቀላቀሉ።
ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

ተፈታኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ መርሃ ግብር ያሳያል።

ተፈታኞቹ ለአራት ቀናት የሚቆየውን ብሔራዊ ፈተና መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት ሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ፈተናው ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ተፈታኞች ጥቅምት 12 እና 13/2015 ዓ.ም ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

ባለፈው ሳምንት በተሰጠው የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ብሔራዊ ፈተና ነገ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከመስጠትም ባሻገር የተለያዩ ተቋማት ፈተናውን በደህንነት ካሜራ ጭምር ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ለመመለከት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስርዓትን እንደመከታተሉ ይሄ ፈተና ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በተለይም በፈተና ስርቆት እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀድሞ ማሰራጨትን በመከላከል በኩል ለውጥ የታየበት ሆኖ አግኝቶታል።

ነገር ግን በዚህኛውም የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ወቅት ስልክ ይዘው ወደ ክፍል በመግባት ፈተናውን በቴሌግራም በኩል የማሰራጨት ሁኔታ ተመልከተናል።

ይህንን ድርጊት ለመቆጣጠር ይመስላል ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ቴሌግራም እንዲገደብ እየተደረገ ነው።

በፈተና ተቋማት ስለነበረው ክፍተት / ችግር እና ጠንካራ ጎኖች ሰግሞ የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከቤተሰባችን አባላቶች ፣ ተፈታኞች ፣ ወላጆች ፣ ፈታኝ መምህራን አስተያየቶችን አሰባስበን እናክላችኃለን።


@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ፈተናው ተጠናቋል

ላለፉት አራት ቀናት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት የተሰጠውን የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል (በተለይ በቅርብ ርቀት የሚገኙ።)

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው።

ምስል፦ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#share

#mark_your_day
ቅዳሜ ጥቅምት 19 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ
ከታች ባለው ፎርም ላይ ተመዝገቡ
Registered on the link below.

Registration link: https://docs.google.com/forms/d/1SKswplBu3t3Jd2C3Afp4CyatpgV-3JEMIl_Lnha8ZtA/edit

For more info:
TikTok: @estifanosalemayehu1
Telegram: @OHUB4AllET
#science #technology #scholarships #internships #mathematics #engineering #materials #engineering #Scholarships #SDG2030 #youthsummit #youthconference #conference

Free information section with international students don't miss an opportunity.
##Update

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ! " ፈተና አንፈተንም " ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ  እንደማይችሉ አረጋግጠዋል፡፡

በግል መፈተን እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ያልተፈተኑና በተለያዩ #አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ፣ የወለዱ ተማሪዎች #ከአንድ_ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የተማሪዎች ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
የፈተናው ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይገለጻል---ትምህርት ሚንስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ እንደሚገለጽ አስታውቋል፡፡

በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ ከ900 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው የተፈታኝ ቁጥር በእጅጉ እንደሚልቅ ተገልጿል። በአጠቃላይም ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ 98.8 በመቶ ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡

ፈተናውን ለማስፈፀምም ከ25 ሺህ በላይ ፈተና አስፈፃሚዎች እና ከ 6 ሺህ በላይ የፀጥታ ሀይሎች ለፈተናው ተሰማርተዉ እንደነበር ተነግሯል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያጋጠመው አደጋ እና ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተፈታኞች ያጋጠመዉ ትራፊክ አደጋ ፣ በመቅደላ አምባ፣ ደብረማርቆስ፣ ባህር ዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርስቲዎች ላይ 12 ሺ 993 ተማሪዎች አንፈተንም ብለው ፈተና ትተው መውጣታቸው በፈተና ወቅት ያጋጠሙ ክስተቶች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታዉሰዋል።

በፈተና ወቅትም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 53 ተፈታኞች ስልክ ይዘው ለመግባት የሞከሩ ሲሆን ፈተና አስፈፃሚዎችንም የማዋከብ እና ሌሎች የፈተና ስነ-ምግባር ግድፈቶች መታየታቸውን እና በፈታኞችም በኩል የፈተና ስርዓትን ያለመከተል ችግሮች እንደነበሩም ተገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Free Education Ethiopia ️︎
የፈተናው ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይገለጻል---ትምህርት ሚንስቴር የትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ እንደሚገለጽ አስታውቋል፡፡ በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ ከ900 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው የተፈታኝ ቁጥር በእጅጉ እንደሚልቅ ተገልጿል። በአጠቃላይም ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ 98.8 በመቶ…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
👉 ጫት፣
👉 አደንዛዥ ዕፅ፣
👉 ሲጋራ፣
👉 ስለታማ ነገሮች፣
👉 ጥይት፣
👉 አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

👉 ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
👉 ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃዎች ስለሚበዛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ውጤቱ የሚመጣው ያልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኋላ አንድ ላይ የሚመጣ ይሆናል።

በሰላም እና ፀጥታ ምክንያት ፈተና ያልተቀመጡ ተማሪዎች በቅርብ ጊዜ ይፈተናሉ። (ከ 56,000 በላይ ተማሪዎች )

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2024/12/27 07:09:25
Back to Top
HTML Embed Code: