Telegram Web Link
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው በፋሲል ከነማ ቤት ቆይታውን አጠናቆ ሽኝት ይደረግለታል!!
. #የኢትዮጵያ_ዋንጫ Ethiopian CUP...
#የሙሉ_ሰዓትው_ጤት...

ተጠናቀቀ | ፋሲል ከነማ 0-4 ኢትዮጵያ ቡና 90"
⚽️85’ጌታነህ ከበደ (ፍ). ⚽️32’መሐመድኑር ናስር
. 47'አማኑኤል አድማሱ
. ⚽️65'82’መስፍን ታፈሰ

🗓️ ሀሙስ የካቲት 14/2016
🕘 9:00
🏟 አበበ በቂላ ስታዲየም

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
የኢትዮጵያ ፕሪሚዩር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲዩም እንደሚካሄድ መርኃ ግብር የወጣለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ክለባችን ፋሲል ከነማ ውድድሩ ወደ ሚደረግባት ከተማ ድሬ በዛሬው እለት ገብቷል::

የውድድሩ መርኃ ግብር በድሬዳዋ : በሀዋሳ እና አዲስ አበባ ከተማዎች እንደሚደረግ የተገለፀበት ፕሮግራም በምስል ተገልጿል::

መልካም የውድድር ጊዜ ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ቀጣይ የእግር ኳስ ህይወት መልካም እድል እየተመኘ በክለባችን ትልቅ ስራ ለሰሩ ግለሰቦች የሚሸለመውን የወርቅ ሜዳሊያ በመሸለም ከደጋፊዎቻችን ጋር ደማቅ ሽኝት ያደረገለት ሲሆን የሱራፌልን መሄድ ተከትሎ ቡድናችን ክፍተት ባሉበት ቦታዎች ለመሙላት የተጫዋቾችን ግዥ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ውላቸው በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ሲፀድቅ እምናሳውቃችሁ ይሆናል::

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
. #የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_16ኛ_ሳምንት_ጨዋታ
. Ethiopian Premier League..

. ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከተማ

🗓️ አርብ የካቲት 22/2016
🕐 1:00
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም
🏆 ድል ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ሱራየ እንወድሃለን
ከልብ ስታገለግል በክብርህ ልክ ትከበራለህ ; የእርጋተው ባላባት ገንዘብ ያላማለለው ; የጎንደሮች ባለውለታ ; የአበቄለሽ ፍቅር ተቋዳሺ በ ሄድክበት ሁሉ ጥሩውን ተመኘን

አንዴ ሱራ ኢተርቪው ላይ
ኢትዮጸያ ውስጥ ከፋሲል ውጭ አልጫወትም አለች ታማኞዋ ነብሮ

ከዚ በላይ ፍቅር የትይምጣ 🙏🙏🙏🙏🇵🇪🇵🇪❤️❤️❤️❤️

ከአፍሪካ የማይዘለው የአገራችን ዝውውር ገብያ ማስተማርያ ይቻላላል ¿¿¿
#አስደሳች_ዜና!

የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሰው ሰራሽ የመጫወቻ ሜዳ የፊፋን የጥራት መስፈርት በማሟላቱ ከአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ለ3 አመታት የሚቆይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ተሰምቷል!

ይህን ፕሮጀክት ከመወጠን አንስቶ ለተግባራዊነቱ በመትጋትና የቅርብ ክትትል በማድረግ ለስኬት ያበቁትን ከማንም በላይ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃርን እና ካቢኔያቸውን እንዲሁም ኮንትራቱን ተቀብሎ በከፍተኛ የሙያዊ ብቃት፣ በፊፋ ስታንዳርድ መሰረት ግንባታውን አከናውኖ ያጠናቀቀውን ተቋም(TAN Engineering) አለማድነቅና አለማመስገን ንፉግነት ነው!
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን ከ2011 እስከ 2016 አመት ያገለለለው ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ላይ መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካን ያደረገው ዲሲ ዩናይትድ ስፖርት ክለብ ባለቤት እና አመራሮች በተገኙበት ለመጋቢ ቡድኑ ሎንደን ዩናይትድ በይፋ ፈርሟል::

ፋሲል ከነማ ለሱራፌል ዳኛቸው እንኳን ደስ አለህ በማለት የክብር ሽኝት እና ሽልማት እንዳደረገለት የሚታወስ ሲሆን ቀሪ የእግር ኳስ ህይወቱ የስኬት እንዲሆንለት ይመኛል::

🇦🇹#መልካም_እድል 🔟 #ሱራፌል_ዳኛቸው🇦🇹
. 🇦🇹 #እናመሰግናለን!!🇦🇹

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
#የሙሉ_ሰዓት_ውጤት!!

ተጠናቀቀ | ፋሲል ከነማ 2-1 ሀዋሳ ከተማ 90"
⚽️76’አማኑኤል ገ/ሚካኤል ⚽️41’ታፈሰ ሰለሞን
⚽️88’ቃልኪዳን ዘላለም

🗓️ አርብ የካቲት 22/2016
🕐 1:00
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

🇨🇬#Adwa #VictoryofAdwa #Ethiopia 🇨🇬#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት #የአሸናፊነት_ተምሳሌት #ኢትዮጵያ🇨🇬

@FASILSC
የኢትዮጵያ ፕሪሚዩር ሊግ ደረጃ ሰንጠረዥ ከ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኃላ...
ዐፄዎቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው ፋሲል ከነማ የማጥቃት እና የመከላከል ባህሪ ያላቸው ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
በዘንድሮ የውድድር ዘመን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተን በመቅጠር ሊጉን የጀመሩት ዐፄዎቹ በ16 ጨዋታዎች 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጡ ይታወቃል። ክለቡ በሁለተኛው ዙር የበለጠ ተጠናክሮ ለመቅረብ በሁለቱ የፍፁም ቅጣት ምት ክልሎች ግልጋሎት የሚሰጡትን ሁለት ተጫዋቾች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ፋሲልን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ተከላካዩ ሀቢብ መሐመድ ነው። ጋናዊው የቀድሞ አሻንቲ ጎልድ፣ አሳንቲኮቶኮ እና ድሪምስ ተከላካይ ዓምና ኢትዮጵያ መድንን በመቀላቀል የሀገራችንን ሊግ የተዋወቀ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት ደግሞ ወደ አዳማ ከተማ አምርቶ ነበር። ተጫዋቹ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከአዳማ ከተማ ጋር ሳይስማማ ቀርቶ ውሉን በማፍረስ ለፋሲል ፊርማውን አኑሯል።

ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ አጥቂው አፍቅሮት ሰለሞን ነው። የእግርኳስ ህይወቱን መነሻ በደደቢት ተስፋ ቡድን ያደረገው አፍቅሮት በዋናው ቡድን የተወሰነ ጊዜ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መድን እና ገላን ከተማ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በሀምበሪቾ ቤት ጥሩ ጊዜ አሳልፎ አሁን መዳረሻው ፋሲል ሆኗል።
Soccer Ethiopia

@FASILSC
2024/09/28 21:37:21
Back to Top
HTML Embed Code: