Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመዝጊያ ጨዋታዎች አዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረጉ መሆኑ ይፋ ሆኗል!

👇
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛው ዙር ውድድር በድሬደዋ ከተማ ድሬደዋ ስታዲየም የካቲት 21/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል። የሁለተኛ ዙር የውድድር መርሃ ግብሩም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያሉበትን ጨዋታዎች እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎችን ታሳቢ በማድረግ ተዘጋጅቷል። በስታዲየሞች ደረጃ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሳምንት በድሬደዋ ስታዲየም ፣ ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም እንዲሁም የመጨረሻዎች ሶስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

@FASILSC
እትብቱን ፋሲል ግንብ ዙሪያ ፈልጉልን

#ዕለተ ሐሙስ መራውየ ሰዱስ ዓመት ኢትፌፀም! "😥🇦🇹🇦 : የከፍታችን ቀንዲል: የዓመታት ጣፋጭ ደስታዎቻችን ለጋሽ : በሀዘን መከራችን ቀን ከደጋፊ እኩል ማቅ ለባሽ: የሜዳ አውሬ ሽንፈትን ኮናኝ: ከቴዎድሮስ የወኔ ልብ ደምን የቀዳ : እንደ አፄ ፋሲል ኪነ-ህንፃ መሀል ሜዳውን አራቆ የገነባ: የውብ ጨዋታ አዋላጅ ሀኪም: ጨዋታን ግርማ ሞገስ አከናናቢ! ሮማሪዮን ዳግሞ በጃኖ የፈጠረ: ለአጥቂዎች እንደ መና ምቹ ፖሶችን አዝናቢ : በኳሷ ተፈቃሪ እንዲሉት እሱ እግር ስትገባ የውስጥ ውበቷን ፈልቅቃ ታሳብቃለች! የፋሲላዊያንን የሽሬ ጥቁር እንባን በህሊናው መርሳት ያልተቻለው!🖤 ያን አሰቃቂ ግፍ አደባባይ ላይ ሀቁን እንደ ወንጌል የመሰከረ! ፋሲል ለሱ እሱ ለፋሲል ሳይሰስቱ ካላቸው አቅም በላይ የተረካከቡ!👐....


በኛ የአፄዎቹ ደጋፊዎች ልብ የቁም ፃድቅ ሁነህ ለዘላለም የምትታወስ ይሆናል። በታሪክ ማህደራችን ስምህ በወርቅ ተከትቦ ለትውልድ ይሻገራል። በሄድክበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምህ Surafel Ye Romi 👋🙏

ትልቁ ዋርካ ፋሲል ከነማም🇦🇹 ሌጀንዶችን እያፈራ ከተቀመጠበት አስፈሪነት የግርማ ማማ እንደተከበረ የሚቀጥል ይሆናል! እኛም ደጋፊዎች ዝንተ ዓለም ከክለባችን ጋር በደስታም ሆነ በሀዘን ብሎም በመስዋዕትነት ስጋወ'መንፈስ እርካታ የምንዘልቅ ይሆናል!🇦🇹🇦🇹🇦🇹
✍️JohnJohn T Ethiopia
የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ መርቲ ጀጁ(ኑራኤራ) ያበቀለችው ጀግና የሀገራችን የእግርኳስ ንጉስ የመሀል ሜዳው የልብ ምት
የኳሱ ሊቁና አዋቂው የዋሊያዎቹ ስስት የአፄዎቹ የአይን ብሌን Surafel (ሱራፌል ዳኛቸው ) ነብሮ በቃ እሱ ለኳስ ብቻ የተፈጠረ የፈጣሪ ፍጥረት ኳሱ ደሞ ለሱ የተሰራች ገፀበረከቱ⚽️
እራሱን ከምንም ነገር አርቆና በክብር ጠብቆ ትዳሩንና ቤተሰቡን አክብሮ ወደ ትልቅ የስኬት ማማ ላይ እየተሰቀለ ያለ ልባም ኳሰኛ!
የሰራ የእጁን የተቀመጠ የቂጡን ያገኛልና ሱራ ወጥሮ በመሥራቱ በሥነምግባር ታንፆ ወደ ትልቅ ደረጃ ላይ እራሱን እያበቃ ያለ ምርጥ የኳስ ቴክኒሽያን
ወደ አሜሪካ ያቀናና የኢትዮጵያ ልጆች በዲቪ ብቻ ሳይሆን በእግርኳስ ችሎታ ልጆቿ መምጣት እንደሚችሉ ትልቅ አምሳያችን ይሆናል ይቅናህ ወንድሜ👏🙌
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሱራፌል ወደ ዲሲ ከማቅናቱ በፊት ዛሬ የመጨረሻ ስንብት አድርጎል !

የፋሲል ከነማው አማካይ ሱራፌል ዳኛቸው ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ጨዎታ በፊት ከፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እና ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር ተሰነባብቷል::በቅርቡ ከዲሲ ዩናይትድ መጋቢ ክለብ ሎውደን ዩናይትድ ጋር የተስማማው ሱራፌል ዳኛቸውን ኮንትራት ጉዳዮች በኃላ ወደ ዲሲ ያቀናል።
henry# Facebook

@FASILSC
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው በፋሲል ከነማ ቤት ቆይታውን አጠናቆ ሽኝት ይደረግለታል!!
. #የኢትዮጵያ_ዋንጫ Ethiopian CUP...
#የሙሉ_ሰዓትው_ጤት...

ተጠናቀቀ | ፋሲል ከነማ 0-4 ኢትዮጵያ ቡና 90"
⚽️85’ጌታነህ ከበደ (ፍ). ⚽️32’መሐመድኑር ናስር
. 47'አማኑኤል አድማሱ
. ⚽️65'82’መስፍን ታፈሰ

🗓️ ሀሙስ የካቲት 14/2016
🕘 9:00
🏟 አበበ በቂላ ስታዲየም

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
የኢትዮጵያ ፕሪሚዩር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲዩም እንደሚካሄድ መርኃ ግብር የወጣለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ክለባችን ፋሲል ከነማ ውድድሩ ወደ ሚደረግባት ከተማ ድሬ በዛሬው እለት ገብቷል::

የውድድሩ መርኃ ግብር በድሬዳዋ : በሀዋሳ እና አዲስ አበባ ከተማዎች እንደሚደረግ የተገለፀበት ፕሮግራም በምስል ተገልጿል::

መልካም የውድድር ጊዜ ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ቀጣይ የእግር ኳስ ህይወት መልካም እድል እየተመኘ በክለባችን ትልቅ ስራ ለሰሩ ግለሰቦች የሚሸለመውን የወርቅ ሜዳሊያ በመሸለም ከደጋፊዎቻችን ጋር ደማቅ ሽኝት ያደረገለት ሲሆን የሱራፌልን መሄድ ተከትሎ ቡድናችን ክፍተት ባሉበት ቦታዎች ለመሙላት የተጫዋቾችን ግዥ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ውላቸው በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ሲፀድቅ እምናሳውቃችሁ ይሆናል::

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
. #የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_16ኛ_ሳምንት_ጨዋታ
. Ethiopian Premier League..

. ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከተማ

🗓️ አርብ የካቲት 22/2016
🕐 1:00
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም
🏆 ድል ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ሱራየ እንወድሃለን
ከልብ ስታገለግል በክብርህ ልክ ትከበራለህ ; የእርጋተው ባላባት ገንዘብ ያላማለለው ; የጎንደሮች ባለውለታ ; የአበቄለሽ ፍቅር ተቋዳሺ በ ሄድክበት ሁሉ ጥሩውን ተመኘን

አንዴ ሱራ ኢተርቪው ላይ
ኢትዮጸያ ውስጥ ከፋሲል ውጭ አልጫወትም አለች ታማኞዋ ነብሮ

ከዚ በላይ ፍቅር የትይምጣ 🙏🙏🙏🙏🇵🇪🇵🇪❤️❤️❤️❤️

ከአፍሪካ የማይዘለው የአገራችን ዝውውር ገብያ ማስተማርያ ይቻላላል ¿¿¿
#አስደሳች_ዜና!

የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሰው ሰራሽ የመጫወቻ ሜዳ የፊፋን የጥራት መስፈርት በማሟላቱ ከአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ለ3 አመታት የሚቆይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ተሰምቷል!

ይህን ፕሮጀክት ከመወጠን አንስቶ ለተግባራዊነቱ በመትጋትና የቅርብ ክትትል በማድረግ ለስኬት ያበቁትን ከማንም በላይ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃርን እና ካቢኔያቸውን እንዲሁም ኮንትራቱን ተቀብሎ በከፍተኛ የሙያዊ ብቃት፣ በፊፋ ስታንዳርድ መሰረት ግንባታውን አከናውኖ ያጠናቀቀውን ተቋም(TAN Engineering) አለማድነቅና አለማመስገን ንፉግነት ነው!
2024/06/28 20:21:43
Back to Top
HTML Embed Code: